YeneTube
الذهاب إلى القناة على Telegram
2025 عام في الأرقام

107 335
المشتركون
-4624 ساعات
-3747 أيام
-2 08430 أيام
أرشيف المشاركات
Photo unavailableShow in Telegram
ኬንያ ለኡጋንዳ የባሕር በር እንደምትሰጥ አረጋገጠች
የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ጎረቤታቸው ኡጋንዳ በኬንያ በኩል በነዳጅ ቧንቧ፣ በመንገድ እና በባቡር ሐዲድ አማካኝነት በሕንድ ውቅያኖስ ላይ የባሕር በር እንድታገኝ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።
ኬንያ የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧዋን የሚያስተዳድረውን የመንግሥት ኩባንያ ከኡጋንዳ ጋር በጋራ ባለቤትነት ለመያዝ ፍቃደኛ መሆኗን ገልጠዋል፤ በተጨማሪም በቻይና እርዳታ የተዘረጋው የባቡር ሐዲድ በቅርቡ እስከ ካምፓላ እንደሚዘረጋ ይፋ አድርገዋል።
ይህ ማረጋገጫ የመጣው የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ ኡጋንዳ በኬንያ በኩል የባሕር በር ካላገኘች በሁለቱ አገራት መካከል ጦርነት ሊቀሠቀስ እንደሚችል ከተናገሩ ከጥቂት ቀናት በኋላ ነው።
@Yenetube @Fikerassefa
🔥 38👍 27❤ 19👀 1
Photo unavailableShow in Telegram
ሳውዲ ዐረቢያ የአልኮል መሸጫ ሱቆችን ልትከፍት ነው።
ሳውዲ ዐረቢያ የአልኮል መጠጥ ገደቦችን በቀላሉ በማላላት፣ ተጨማሪ የአልኮል መሸጫ ሱቆችን ለመክፈት እቅድ እንዳላት ሮይተሪስ ዘግቦል።
እቅዱ ሁለት አዳዲስ መሸጫ ቦታዎችን ያካተተ ሲሆን፣ ከመካከላቸው አንዱ የመንግሥት ዘይት ኩባንያ በሆነው አራምኮ ውስጥ ለሚገኙ ሙስሊም ላልሆኑ የውጭ ሠራተኞች አገልግሎት ለመስጠት ታስቦ መሆኑ ተነገሮል።
የመጀመሪያዉ ሱቅ የሚከፈተው በምስራቃዊው ግዛት ዳህራን ውስጥ እንደሆነና ሌላኛው ሱቅ ደግሞ በምዕራባዊው የባህር በር ከተማ ጅዳ ውስጥ ለሚገኙ ዲፕሎማቶች እንደሚሆን ተገልጿል።
ይህ እርምጃ በተጨባጭ የሀገሪቱ መሪ በሆኑት በልዑል አልጋ ወራሽ መሐመድ ቢን ሰልማን እየተመራ ያለው፣ ሀገሪቱን ለውጭው ዓለም የበለጠ ክፍት የማድረግ ጥረት ቀጣይ ምዕራፍ ነው ተብሎል።
ሳውዲ ዐረቢያ እስልምና የተወለደባት ሀገር በመሆኗ፣ ለአልኮል መጠጥ ጥብቅ እገዳ እንዳላትና ባለፈው ዓመት በዋና ከተማዋ ሪያድ ውስጥ ሙስሊም ላልሆኑ ዲፕሎማቶች የተወሰነ የመጀመሪያውን የአልኮል መሸጫ ሱቅ ከፍታ እንደነበርና ይህ ሱቅ ከ73 ዓመታት በኋላ የተከፈተ የመጀመሪያው ሱቅ መሆኑ ተገልፅል።
አዲሶቹ የዳህራን እና የጅዳ ሱቆች በ2026 ዓ.ም. ውስጥ ይከፈታሉ ተብሎ ይጠበቃል ሆኖም ትክክለኛ የጊዜ ሰሌዳ ገና አለመገለፁን ሮይተርስ ዘግቦል።
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 44😁 27👎 15😭 5👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ከዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ዕዝ አዛዥ ጋር መወያየታቸውን ገለፁ
ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ከዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ እዝ አዛዥ ጄነራል ዳግቪን አር ኤም አንደርሰንን ጋር መወያየታቸውን ገለፁ።
ውይይቱ ዛሬ ጠዋት መደረጉን እና "በቀጠናዊ የጸጥታ እና የበለጠ ትብብር ለማድረግ በሚቻልባቸው" ጉዳዮች ላይ ያተኩረ መሆኑን ጠ/ ሚንስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት አስታውቀዋል።
ባሳለፍነው ዓመት ሰኔ ወር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከአሜሪካ ማሪን ኮርፕስ ጄኔራል እና አፍሪኮም አዛዥ ከሆኑት ጄነራል ማይክል ላንግሌይ ጋር የጋራ ፍላጎት በሆኑ የሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል።
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 15👎 10👍 3🔥 2😁 1
Photo unavailableShow in Telegram
ሰመር ሪል እስቴት
በካሬ 73,318 ብር ብቻ
10% ቅድመ ክፍያ
50% ባንክ የተመቻቸላቸው
Location እንግሊዝ ኢምባሲ አጠገብ
✅ አፓርትመንቶች ቤቶች እንግሊዝ ኢምባሲ ደስ እሚል እይታ ያላቸው ቤቶች በሺያጭ ላይ ነን ከባለ 2 መኝታ - ባለ 4 መኝታ ደረስ
☑️ እስታንድ ባይ ጀኔኔትር
☑️5ሊፍት ያለው
☑️የዋና ገንዳ
☑️ፓርኪንግ
☑️ጅም, እስፓ ,ሚኒ ማርኬት,
☑️ቴራስ
✅ ባለ 2 መኝታ
134.6 ካሬ
137.6 ካሬ
155.6 ካሬ
✅ ባለ 3 መኝታ
183.8 ካሬ
156.9 ካሬ
197.8 ካሬ
✅ ባለ 4 መኝታ
260 ካሬ
ለበለጠ መረጃዎች
📞 0912355631
❤ 10
(ዘ-ሐበሻ ዜና) "በፌዴራል መንግስቱ እጅግ አዝነናል" ሲል ስምረት ፓርቲ ገለፀ፡፡ አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራውና በቀድሞ የህወሀት አመራሮች የተመሰረተው ዲሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) ፓርቲ ባወጣው መግለጫ በፌዴራል መንግስቱ እጅግ ማዘኑን አስታወቀ፡፡
ፓርቲው በመግለጫው የፕሪቶሪያ ስምምነት ሁሉም አይነት ውዝግቦችና ልዩነቶች በህገ መንግስቱ መሰረት እንዲፈቱ እድል የሰጠ መሆኑን አውስቶ ‹‹ይሁን እንጂ በዚህ ያልተደሰቱ የውስጥና የውጭ አካላት በሚያደርጉትና እያደረጉ ባለው ጥረት ስምምነቱ የተጠበቀውን ውጤት እንዳያመጣ አድርገውታል›› ብሏል፡፡ መግለጫው ሲቀጥልም በዚህ ስምምነት መሰረትና በህገ መንግስቱ በተቀመጠው አግባብ የምእራብ ትግራይ ተፈናቃዮች ዋስትና ባለው አግባብ እንዲመለሱ በከፍተኛ የፌዴራል አካላት እየተመራ የተሻለ ደረጃ እንደደረሰ ጠቅሷል፡፡
ጨምሮም ‹‹ነገር ግን አካባቢውን ወረው ያዙና በፕሪቶሪያው ውል መሰረት ያለአንዳች ቅድመ ሁኔታ እንዲወጡ ስምምነት የተደረሰባቸው ሀይሎች የተጀመረውን የሰላም ሂደት አፈፃፀም የሚያደናቅፉ መግለጫዎችን እያወጡ ነው›› ያለው ስምረት ፓርቲ፣ ይህ ይስተካከላል በሚል ዝምታን መምረጡን አውስቷል፡፡
ገር ግን የስምምነቱ ባለቤት የሆነው የፌዴራል መንግስቱ ይህንን ለማረም ምንም ጥረት ሲያደርግ አለማየቱን የጠቀሰው ስምረት ‹‹የፌዴራል መንግስት ለማረም ያደረገው ጥረት ባለማየታችን እጅጉን አዝነናል›› ብሏል፡፡ እንደምሳሌም ህዳር 10 ቀን 2018 የተከሰተውን አንስቷል፡፡
በእለቱ የነበረውን ሁኔታ ስምረት ፓርቲ የገለፀው ‹‹ቀድሞም ቢሆን ህዝባችን እንዲፈናቀል ከፊት ሆነው ሲያነሳሱ የነበሩ አንዳንድ ምሁራንና የሀይማኖት መሪዎች በዚያ ሳይፀፀቱ ዛሬም ይህንን ስምምነት የሚያደናቅፍ፣ የተጀመረውን ሰላማዊ የትግል ሂደት የሚያውክና የትግራይን ህገ መንግስታዊ ግዛት የሚፃረር ሀላፊነት የጎደለው አሳፋሪ ተግባር ሲፈፅሙ ውለዋል›› በማለት ነው፡፡
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 50😁 12👍 3
የቀድሞ የሰላም ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደአ አዲስ ሦስት ክሶች ቀረበባቸው!
የቀድሞ የሰላም ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደአ ላይ ዐቃቤ ሕግ አዲስ ሦስት አይነት ክሶችን እንዳቀረበባቸው ጠበቃቸው አበራ ንጉስ ለአሐዱ ሬዲዮ ተናግረዋል።አቶ ታዬ በዛሬው ዕለት የቅጣት አስተያየት ለማቅረብ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት የጸረ ሽብር ችሎት ቀርበው፤ ቀድሞ በተሰጣቸው ተለዋጭ ትዕዛዝ መሰረት ጥፋተኛ በተባሉት "የፀና ፍቃድ ሳይኖር የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት" ወንጀል የቅጣት ላይ አስተያየታቸውን ያቀረቡ መሆኑን አብራርተዋል።
በዚህም ዐቃቤ ሕግ የአቶ ታዬ ደንደአ የቀጣት አስተያየት የተቀበለ ሲሆን፤ ችሎቱም የግራ ቀኙ የቅጣት አስተያየት በመመርመር ቅጣት ለመወሰን ለሕዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።በዛሬው የችሎት ውሎ ዐቃቤ ሕግ አዲስ የወንጀል ክስ የከፈተ ሲሆን፤ ይህን አዲስ የወንጀል ፋይል ለአቶ ታዬ ደንደአ በፅሑፍ የደረሳቸው መሆኑን እና በተጨማሪም ችሎቱ በንባብ አስምቷቸዋል ሲሉ ጠበቃው ለአሐዱ ተናግረዋል።
ዛሬ የቀረበው አዲስ የወንጀል ክስ በይዘት ደረጃ አቶ ታዬ Horn conversation ከተሰኘው የዩቲዩብ ቻናል ጋር ያደረጉት እና በሦስት ተከታታይ ምዕራፍ ከቀረበው ፕሮግራም ጋር የተያያዘ ሲሆን፤ በክሱ ሦስት ተደራራቢ ወንጀሎች ቀርቦውባቸዋል ሲሉ ጠበቃቸው አቶ አበራ ንጉስ አብራርተዋል።
የመጀመሪያው ክስ የወንጀል ሕግ ቁጥር 257(ሀ)፡ (ሰ) በመጥቀስ የቀረበ ሲሆን፤ የወንጀል መጠሪያውም "መንግሥትን በኃይል ለመጣል ግዙፋዊ መሰናዶ ማድረግ" ሲሆን፣ ሁለተኛው ክስ ደግሞ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 337 በመጥቀስ የቀረበ "የሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ ሃሰተኛ እና አደናጋሪ ወሬዎችን መንዛት የሚል ነው ብለዋል።
በስተመጨረሻ የቀረበባቸው ክስ የወንጀል ህግ አንቀፅ 244(1) በመጥቀስ፤ "በሕገ-መንግሥት መሰረት የተመረጠ የሀገሪቱ መንግሥት መድፈር" የሚል መሆኑን ከዛሬው የችሎት ውሎ መረዳት መቻላቸውን ጠበቃው ለአሐዱ ገልጸዋል።
አቶ ታዬ ደንደአ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ጸረ ሽብር ችሎት "ከጠላት ጋር መተባበር"፣ መገፋፋትና ግዙፋዊ መሰናዳት እንዲሁም፤ የፀና ፍቃድ ሳይኖር የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት በሚል ሦስት ተደራራቢ ወንጀሎች ተከሰው በክርክር ሂደት ላይ እንደነበሩ የሚታወስ ሲሆን፤ ፍርድ ቤቱ ሕዳር 3 ቀን 2018 ዓ.ም. ባስተላለፈው ውሳኔ 'ተከሳሹ ከተጠረጠሩበት ሦስት ወንጀሎች በሁለቱ ነጻ ናቸው' ማለቱ አይዘነጋም።
ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ አቶ ታዬ ጥፋተኛ በተባሉት አንድ ክስ ማለትም "የፀና ፍቃድ ሳይኖር የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት" ክስ የቅጣት አስተያየት ለመስማት ለዛሬ ሕዳር 15 ቀን 2018 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ የበነረ ሲሆን፤ በዛሬው የችሎት ውሎውም የቀጣት አስተያየቱን በመቀበል ቅጣት ለመወሰን ለሕዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
Via Ahadu
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 21👎 14😭 10
Photo unavailableShow in Telegram
አዋሽ ባንክ 25.6 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡንና ጠቅላላ የሃብት መጠኑ ከ442 ቢሊየን ብር በላይ መድረሱን አስታወቀ!
አዋሽ ባንክ በ2017 የበጀት ዓመት በግል ባንክ ታሪክ ከፍተኛ የተባለውን 25.6 ቢሊዮን ብር ያልተጣራ ትርፍ ማስመዝገቡን እና አጠቃላይ የሃብት መጠኑም 442.6 ቢሊዮን ብር መድረሱን ይፋ አድርጓል።ባንኩ ይህን ያስታወቀው ቅዳሜ ዕለት ባካሄደው የባለአክስዮኖች 30ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጉባኤ እና 18ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ነው።
በጉባኤው የአዋሽ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፀሐይ ሽፈራው እንዳሉት፣ ባንኩ በሂሳብ ዓመቱ 25 ነጥብ 67 ቢሊየን ብር ያልተጣራ ትርፍ አስመዝግቧል። ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር 137 በመቶ እድገት ማሳየቱንና ከፍተኛ ትርፍ መሆኑን መግለጻቸውን ኤፍ ኤም ሲ ዘግቧል።
በተጨማሪም የባንኩ ጠቅላላ ተቀማጭ 358 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር መሆኑን ገልጸው ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 125 ነጥብ 9 ቢሊየን እድገት ማሳየቱን ጠቁመዋል።
ዋና ስራ አስፈፃሚው ባንኩ በሂሳብ ዓመቱ ከ2 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ማግኘት መቻሉንና የተሰጠ የብድር ክምችትም 20 በመቶ እድገት ማስመዝገቡንም ተናግረዋል።
የባንኩ የተከፈለ ካፒታል 27 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ደርሷል ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው፤ ይህም ብሄራዊ ባንክ ነባር ባንኮች በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሊደርሱበት ይገባል ብሎ ካስቀመጠው የካፒታል መጠን የሚበልጥ መሆኑን አስረድተዋል።
ባንኩ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ረገድ 600 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓልም ነው ያሉት።አዋሽ ባንክ ከ15 ሚሊየን በላይ ደንበኞች ማፍራቱ እና የቅርንጫፎቹን ቁጥር 989 መድረሱ ተመላክቷል።
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 23👎 6🔥 3
Photo unavailableShow in Telegram
ወንድማማቾች በአንድ ቀን በተለያዩ የመኪና አደጋዎች ህይወታቸው አለፈ
የሁለት ወንድማማቾች ዕለታዊ ድርብ ሐዘን
1. ታላቁ ወንድም - ይስሐቅ አብርሃም
በአርባ ምንጭ ሃይላንድ ሙሉ ወንጌል አባልና አገልጋይ የነበረ። ከአዲስ አበባ ወደ አርባ ምንጭ በሚያደርገው ጉዞ ላይ እያለ በድንገተኛ የመኪና አደጋ ሕይወቱ አልፏል።
2. ታናሹ ወንድም - አቤኔዘር አብርሃም
በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዓመት የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪ የነበረ። የታላቅ ወንድሙን (ይስሐቅን) መርዶ እንደሰማ፣ ቀብር ለመድረስ ከሆሳዕና ወደ ወላይታ ሶዶ ሲጓዝ ነበር። በትላንትናው ዕለት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ በከምባታ ዞን በደረሰ ሌላ የመኪና አደጋ ሕይወቱ አልፏል።
ምንጭ:-ዳጉ ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa
😭 275❤ 31
የአፋሩ እሳተ ገሞራ ፍንዳታ አስደንጋጭ ሆኗል!
የእሳተ ጎሞራው ፍንዳታ ያስከተለው ጭስ በአቅራቢያ የሚገኙ አከባቢዎችን ነዋሪዎችን ማፈን ጀምሯል።
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 6😭 6
Photo unavailableShow in Telegram
በኤርታሌ ከወትሮው የተለየ ጭስ እና የፍንዳታ ድምጽ ተከስቷል!
በአፋር ክልል ኤርታሌ ያልተለመደ ነው የተባለለት የእሳተ ገሞራ አይነት የፍንዳታ ድምጽ መከሰቱ ተገልጿል።የተከሰተው ፍንዳታ ከፍተኛ መጠን ያለው በመሆኑ በተለያዩ አካባቢዎች መሠማቱን ከነዋሪዎች ማረጋገጥ ተችሏል።
የተከሰተውን ፍንዳታ ተከትሎ የሚያጣራ ቡድን ወደስፍራው የተላከ ሲሆን ከፍንዳታው ጋር የተገናኙ ተጨማሪ መረጃዎችን የምናደርሳችሁ ይሆናል።የፍንዳታ ድምጹን ሰምታችኋል? የሰማችሁት ከየት ሆናችሁ ነው? ሃሳባችሁን አጋሩን
Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 23
Photo unavailableShow in Telegram
የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ላለፉት ቀናት በመቀለ ሲመክር ሰንብቶ ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ በፌደራል መንግስት ላይ ከባድ ክስ እና ማስጠንቀቂያ አሰምቷል።
ዋናው ነጥብ ምንድን ነው? በመግለጫው የፌደራል መንግስትን ተጠያቂ ያደረገ ሲሆን መንግስት ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው ለመመለስም ሆነ በ'ምዕራብ ትግራይ'ና ሌሎች አካባቢዎች ያሉ ታጥቀው ያሉ ሃይሎችን ለማስወጣት ፈቃደኛ አይደለም፤ ስምምነቱን እያጓተተና እያዳከመ ነው ብሏል።
መግለጫው ቅሬታ ብቻ አይደለም፤ ዛቻም አለበት። የፌደራል መንግስት ይህንን አካሄድ ካላረመ "ለሚፈጠረው ቀውስ እና ጥፋት ሙሉ ሃላፊነቱን ይወስዳል" ሲል ሕወሓት አስጠንቅቋል። ለአፍሪካ ህብረትም "ጉዳዩን እዩት" የሚል መልእክት ልኳል።
በሌላ በኩል ሕወሓት ወደ ራሱ ጓዳም ተመልክቷል። በክልሉ ውስጥ ሌብነት፣ ዝርፊያ እና የአስተዳደር ብልሹነት በከፍተኛ ሁኔታ መስፋፋቱን አምኖ፣ ይህን ለማስተካከል ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጋር እጅና ጓንት ሆኖ እንደሚሰራ ቃል ገብቷል። "ውስጣችንን እያጠራን ነው፣ አንድነታችንም ተመልሷል" የሚል መልእክትም አለው።
በአጭሩ፥ መግለጫው በአንድ እጅ "ቤታችንን እናጸዳለን"፣ በሌላ እጅ ደግሞ "ፌደራል መንግስት ስምምነቱን ካላከበረ ነገሮች አያምሩም" የሚል ነው።
ይህ ጉዳይ ቀጣይ ምን ያመጣ ይሆን? መንግስትስ ምን ምላሽ ይሰጣል? አብረን የምናየው ይሆናል።
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 32😁 4👀 2
Photo unavailableShow in Telegram
ከቦሌ ብራስ - በኤድናሞል ወደ አትላስ ሆቴል የሚወስደው ኮሪደር በግንባታ ምክንያት ዝግ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን አስታወቀ።
በሥፍራው የሚካሄደውን የኮሪደር ልማት በፍጥነት ለማጠናቀቅ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች በከፍተኛ ትጋት እየሰራ መሆኑን እየገለፀ፣ በቀጣዮቹ ሁለት ቀናት በአትላስ መብራትና አካባቢው በሚከናወነው የግንባታ ሥራ ምክንያት፤ ቅዳሜ ህዳር 13 እና እሁድ ህዳር 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከቦሌ ሩዋንዳ አቅጣጫ ወደ ውሃ ልማትና ተቃራኒ አቅጣጫ የሚወስደው መንገድ ለትራፊክ ዝግ የሚደረግ መሆኑን ያስታውቃል፡፡
በመሆኑም አሽከርካሪዎች በተጠቀሱት ቀናት አማራጭ መንገዶችን በመጠቀም ለግንባታው መፋጠን እና የትራፊክ መጨናነቅ እንዳያጋጥም እንዲተባበሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል።
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 29👍 10🔥 2
Photo unavailableShow in Telegram
በዛሬው ዕለት በ #ማርበርግ ቫይረስ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ ተጨማሪ ሁለት ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ሪፖርት ተደረገ
በዛሬው ዕለት ከተደረጉ 13 የላብራቶሪ ምርመራዎች ተጨማሪ 2 ሰዎች ላይ የማርበርግ ቫይረስ መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
በዛሬው ዕለት በተደረገው ምርመራ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው ታማሚ ከዚህ በፊት ከተገለፀው ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጂንካ ከተማ በለይቶ ማቆያ የነበሩ ሲሆኑ በተመሳሳይ ቦታም የህክምና ክትትላቸውን እያደረጉ እንደሚገኙ ሚኒስቴሩ ገልጿል።
በተጨማሪም በዛሬው ዕለት አንድ ሰው በቫይረሱ ህይወቱ ሲያልፍ በአጠቃላይ በቫይረሱ ህይወታቸው እንዳለፈ የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር አራት መድረሱ ተጠቁሟል።
በሽታው መከሰቱ ከተገለጸበት ቀን አንስቶ እስካሁን 46 የላብራቶሪ ምርመራዎች የተከናወኑ ሲሆን በአጠቃላይ ቫይረሱ በ8 ሰዎች ላይ መገኘቱ ተመላክቷል። እንዲሁም አራት ሰዎች ደግሞ በህክምና ላይ እንደሚገኙ ተጠቁሟል።
የጤና ሚኒስቴር በትናንትናው ዕለት በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 2 ሰዎች በማርበርግ ቫይረስ መያዛቸውን ማስታወቁ አይዘነጋም።
@Yenetube @Fikerassefa
😭 32❤ 31
የህንድ አየር ኃይል ተዋጊ ጀት ተከሰከሰ
ዛሬ አርብ (ህዳር 12፣ 2018 ዓ.ም) በዱባይ እየተካሄደ ባለው ዓለም አቀፍ የዱባይ ኤር ሾው (Dubai Air Show) ማሳያ ወቅት፣ የህንድ አየር ኃይል (Indian Air Force - IAF) ንብረት የሆነውና በሀገር ውስጥ የተሰራው HAL Tejas Mark-1 የተሰኘው ተዋጊ ጀት (Fighter Jet) መከስከሱ ተዘግቧል።
@Yenetube @Fikerassefa
😁 10❤ 5😭 2
Photo unavailableShow in Telegram
የሲንጋፖሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ከጂ-20 ስብሰባ በኋላ ኢትዮጵያን እንደሚጎበኙ ተገለፀ!
የሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር እና የገንዘብ ሚኒስትር ላውረንስ ዎንግ በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ ባለው የጂ-20 ጉባኤ ከተካፈሉ በኋላ ከኅዳር 13 እስከ 15 ድረስ በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ተገለፀ።
የሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ዛሬ ኅዳር 12 ቀን 2018 ባወጣው መግለጫ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዎንግ በደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ግብዣ ከኅዳር 12 እስከ 13 ድረስ በጆሃንስበርግ በሚካሄደው የጂ-20 ጉባኤ ላይ ይሳተፋሉ ብሏል።
መግለጫው፣ "አንድነት፣ እኩልነት፣ ዘላቂነት" በሚል ጭብጥ የሚካሄደው ጉባዔው በአየር ንብረት ለውጥ፣ በእኩልነት እና በጂኦፖለቲካዊ መረጋጋት ዙሪያ ያሉ ተያያዥ ዓለም አቀፍ ችግሮችን ለመፍታት ያለመ ነው ብሏል።
ከጉባኤው በኋላ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዎንግ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ግብዣ በአዲስ አበባ ይፋዊ ጉብኝት ያደርጋሉ ሲል ጽ/ቤቱ አስታውቋል። ሁለቱ መሪዎች የልዑካን ቡድን ስብሰባ ያደርጋሉ፤ ከዚያም የመግባቢያ ሰነዶችን ይፈራረማሉ ተብሏል። በተጨማሪም መሪዎቹ በመግባቢያ ስምምነቶች የተካተቱ የትብብር ዘርፎችን የሚያስታውቁበት የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣሉ።
Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 35👍 5👎 3😁 2🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
በማርበርግ ቫይረስ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች አስከሬን ለቤተሰብ አይሰጥም ተባለ
በሽታው በንክኪ የሚተላለፍ በመሆኑ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች አስከሬን ለቤተሰባቸው እንደማይሰጥ ነው የተነገረው።
ህይወታቸው ካለፈ በኋላ አስከሬኑ የማይታጠብ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፥ ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ የቀብር ስርዓታቸው ይፈፀማል ተብሏል።
ቀብር የተፈፀመባቸው ቦታዎችም በደንብ መጠበቅ እንዳለባቸው ተገልጿል።
ማህበረሰቡ የበሽታውን ከባድነት ተረድቶ ይህንን ውሳኔ መቀበል እና መተባበር አለበት ተብሏል።
በሌላ በኩል ቫይረሱ በወንድ የዘር ፈሳሽ ውስጥ ለአንድ አመት ጊዜ የሚቆይ በመሆኑ ፥ ከህመሙ ያገገሙ ሰዎች ልቅ የሆነ የግብረስጋ ግንኙነት ከማድረግ መቆጠብ አለባቸው ነው የተባለው።
ተገቢው ክትትል እና ህክምና ተደርጎለት የዳነ ሰው በሽታውን ማስተላለፍ አይችልም።
እንደ ኮሮና ቫይረስ በአየር ይተላለፋል የሚል የተዛባ አመለካከት መኖሩ የተገለፀ ሲሆን፥ ህመሙ በአየር የማይተላለፍ ነው ተብሏል።
ህመሙ በንክኪ የሚተላለፍ በመሆኑ ህመሙ ካለባቸው ሰዎች ጋር ያለን ግንኙነት ከንክኪ የራቀ መሆን እንዳለበትም ተገልጿል።
ማርበርግ እንደ ኮቪድ በአየር የሚተላለፍ ባይሆንም፥ከኮቪድ በበለጠ ህይወት የሚነጥቅ ነው ተብሏል።
እንደ ወረርሽኙ ክብደት የሞት ምጣኔው ከ24 እስከ 88 በመቶ ይደርሳል።
33 ሰዎች ተመርምረው 6 ሰዎች ህመሙ የተገኘባቸው ሲሆን፥ ሶስቱ ህይወታቸው ሲያልፍ ሶስት ሰዎች ደግሞ በህይወት አሉ ተብሏል።
ይህን መረጃ ያገኘነው ጤና ሚኒስቴር ከህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር በማርበርግ በሽታ ምንነት ዙሪያ ለሚዲያ ባለሙያዎች ባዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ላይ ነው።
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 26👍 7⚡ 1
Photo unavailableShow in Telegram
ዶ/ር አንዷለም ዳኘ ላይ የግድያ ወንጀል የፈጸመው ተከሳሽ በ25 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ!!
የባሕር ዳርና አካባቢው ከፍተኛ ፍ/ቤት የጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሐኪም በነበሩት ዶ/ር አንዷለም ዳኘ ላይ የግድያ ወንጀል በፈፀመው ተከሳሽ ላይ የ25 ዓመት ጽኑ እስራት ወስኗል።
@Yenetube @Fikerassera
😭 23❤ 11👍 2
የተመረዘ ምግብ በልተው ከታመሙ 8 የአንድ ቤተሰብ አባላት ዉስጥ የ7ቱ ሕይወት ማለፉ ተገለጸ!
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስራቅ ጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ በአብሮነት እራት ተመግበው በጠና ከታመሙ ስምንት የአንድ ቤተሰብ አባላት ውስጥ፤ አባወራዉ ከስድስት ልጆቹ ጋር ሰባት የአንድ ቤተሰብ አባላት ሕይወታቸዉ ማለፉን የክልሉ ፖሊስ ገልጿል።
የክልሉ ፖሊስ የወንጀል መረጃ ኢንተለጀንስ ዳይሬክቶሬት ተወካይ ምክትል ኮማንደር ያለው ተመስገን፤ በወረዳው መሰረተ ወገራም ቀበሌ ዳሾ ቆቶ ተብሎ በሚጠራው መንደር ሕዳር 6 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽት 1:00 ሰዓት ስምንቱ የቤተሰብ አባላት አብረዉ እራት ከተመገቡ በኋላ በድንገት መታመማቸውን ተናግረዋል።
በአብሮነት እራት እንደተመገቡ ብዙም ሳይቆዩ ከፍተኛ ለሆነ ሕመም መዳረጋቸውን መረጃ የደረሳቸው የአካባቢው ነዋሪዎች የተጎጂዎችን ሕይወት ለማትረፍ ተረባርበው ወደ ሆስፒታል ማድረሳቸው ነው የተገለጸው።
ነገር ግን ከተጎዱ የቤተሰቡ አባላት የ5 ዓመቱ መንግሥቱ ኃይሌ፣ የ7 ዓመቱ መክብነ ኃይሌ እና የ17 ዓመቱ ተክሉ ኃይሌ የተባሉት ሦስቱ ወንድማማቾች በዕለቱ ሆስፒታል እንደደረሱ ሕይወታቸው ማለፉን ፖሊስ ተናግሯል።
የተቀሩ ተጎጂዎችን ሕይወት በሕክምና ለማትረፍ ሐኪሞች ያልተቋረጠ ጥረት ቢያደርጉም፤ የ14 ዓመቷ መቅደስ ኃይሌ እና የ15 ዓመቱ ገብሬ ኃይሌ የሁለቱ እህትና ወንድም ሕይወት በማግስቱ ሕዳር 7 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽት 11:00 ሰዓት ሲያልፍ የሟቾች ቁጥር አምስት ደርሷል።
ከተቀሩት ተጎጂዎች ደግሞ የ1 ዓመት ከ7 ወሩ ሕጻን ሲሳይ ኃይሌ ሕዳር 9 ቀን 2018 ዓ.ም ጥዋት 2:00 ሰዓት ላይ ሕይወቱ ሲያልፍ፤ የስድስቱ ሟች ልጆች አባት የሆነው የ46 ዓመቱ አቶ ኃይሌ አበራ ሕዳር 10 ቀን 2018 ዓ.ም ለሊት በሰመመን ዉስጥ ሆኖ ከእንቅልፉ ሳይነቃ ሕይወቱ ማለፉ ተገልጿል፡፡
የባለቤቷንና የስድስት ልጆችዋን ህልፈት ያልተረዳችው ወይዘሮ ዳመነች ደንበል፤ በሚኒሊክ ሆስፒታል በሕክምና እየተረዳች በሕይወት መኖሯንም የክልሉ ፖሊስ አስታውቋል።
ፖሊስ ተጎጂዎች የተመገቡት ምግብ የተመረዘው በማንና እንዴት? የሚለዉን እውነታ በማጣራት ለማረጋገጥ፤ ከምስራቅ ጉራጌ ዞን እና ከመስቃን ወረዳ የተወጣጣ የምርመራ አጣሪ ግብረ ኃይል አዋቅሮ ምርመራ የማጣራቱን ሥራ መጀመሩን ገልጿል፡፡
ኮማንደር ያለዉ ተመስገን የምርመራ ግብረ ኃይሉ 'በድርጊቱ የሌሎች እጅ ሊኖር ይችላል' በሚል ጥርጣሬ አስር ሰዎችን በቁጥጥር ሥር አዉሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ተናግረዋል።
"ተጎጂዎች በዳግማዊ ምንሊክ ሆስፒታል ሕክምና ተከታትለዋል" ያለው ፖሊስ፤ የሟቾች የአስክሬን ምርመራ ውጤት እየተጠበቀ መሆኑንና ስለጉዳዩ የተሻለ ፍንጭ ሊሰጥ እንደሚችል መረጃ ሊገኝ እንደሚችል መገመቱ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፓሊስ ኮሚሽን ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
@YeneTube @FikerAssefa
😭 107❤ 31👀 3😁 1
Photo unavailableShow in Telegram
በዛሬው ዕለት በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 2 ሰው በማርበርግ ቫይረስ መያዙ ተገለፀ!
በዛሬው ዕለት በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 2 ሰዎች በማርበርግ ቫይረስ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።በዕለቱ 5 የላብራቶሪ ምርመራዎች መካሄዱ የተገለፀ ሲሆን፥ 2 ሰው በቫይረሱ መያዙንና 3 ሰዎች ደግሞ ነጻ መሆናቸው ተገልጿል።
በሽታው መከሰቱ ከተገለጸበት ቀን አንስቶ እስካሁን 33 የላብራቶሪ ምርመራዎች የተከናወኑ ሲሆን ቫይረሱ በ6 ሰዎች ላይ መገኘቱ ተመላክቷል።በተጨማሪም ቫይረሱ ተገኝቶባቸው ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ሶስት ሲሆን ሶስት ሰዎች ደግሞ በህክምና ላይ እንደሚገኙ ተጠቁሟል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጂንካ ከተማ በተከሰተው ማርበርግ ቫይረስ አንድ ተጨማሪ ሰው መያዙን የጤና ሚኒስቴር ህዳር 9/2018 ዓ.ም ማስታወቁ ይታወሳል።የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ የቫይረሱ ምልክት ታይቶባቸው ህይወታቸው ካለፈ ስድስት ሰዎች መካከል ሦስቱ ሰዎች የሞቱት በቫይረሱ መሆኑን ህዳር 8 ቀን በሰጡት መግለጫ ማስታወቃቸው አይዘነጋም።
ይህ በእንዲህ እያለ የማርበርግ ቫይረስ በሽታን በመከላከል እና በመቆጣጠር ረገድ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ የአሜሪካ መንግስት ዝግጁ መሆኑን አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ገልጸዋል።
አምባሳደሩ ይህን የገለጹት፣ በኢትዮጵያ በተከሰተው የማርበርግ የቫይረስ በሽታ አጠቃላይ እና ፈጣን ምላሽ መስጠት ዙሪያ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው።
ዶ/ር መቅደስ የበሽታውን የላብራቶሪ ምርመራ፣ ከታማሚዎች ጋር የነበሩ ንክኪዎች ክትትል፣ የአደጋ ዝግጁነት እና የማህበረሰብ ተሳትፎን ጨምሮ አስቀድመው የተተገበሩ ዘርፈ ብዙ እርምጃዎችን አብራርተዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 41👀 8😭 6👍 3
አንድ ቤተሰብ ለ100 ዓመታት በጀርመን የቆዩ ቅርሶችን ለኢትዮጵያ መለሰ!
ከአንድ መቶ ዓመታት በላይ በአንድ ጀርመናዊ ቤተሰብ ተይዘው የነበሩ አስራ ሁለት የኢትዮጵያ ታሪካዊ ቅርሶች በይፋ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተደረገ።አሁን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለኢትዮጵያ ጥናት ተቋም የተሰጡት እነዚህን ቅርሶችን በመጀመሪያ ሰብስበው በባለቤትነት ይዘዋቸው የነበሩት በ1920ዎቹ በኢትዮጵያ የጀርመን መንግሥ መልዕክተኛ የነበሩት ፍራንዝ ዌይስ እና በባለቤታቸው ሄድዊግ ነበሩ።
የተመለሱት የቅርስ ስብስቦች ዘውዶች፣ ጋሻዎች እና ሥዕሎች የተካተቱባቸው ሲሆኑ፤ ለኢትዮጵያ ባሕላዊ እና ታሪካዊ ጠቀሜታ ያላቸው ናቸው።"ቅርሶቹ አሁንም ድረስ በኢትዮጵያ እና በጀርመን መካከል ያለውን የወዳጅነት የሚያሳዩ ምልክቶች ሆነው አሁንም ይቀጥላሉ" ሲሉ በኢትዮጵያ የጀርመን መልዕክተኛ የሆኑት ፈርዲናንድ ቮን ዌይህ ተናግረዋል።
እነዚህን ቅርሶች ለኢትዮጵያ የመለሱት አባታቸው በኢትዮጵያ የጀርመን ዲፕሎማት በነበሩበት ጊዜ የተወለዱት ፕሮፌሰር ራሞን ዌይስ ናቸው።ቅርሶቹ የቱሪዝም ሚኒስትሯ ሰላማዊት ካሳ በታደሙበት ሥነ ሥርዓት ላይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለኢትዮጵያ ጥናት ነው የተሰጡት።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cgqlqe8yynvo
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 42👍 11😁 6🔥 1
