ar
Feedback
ግጥም ብቻ 📘

ግጥም ብቻ 📘

الذهاب إلى القناة على Telegram

✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን። ✔ @getem @serenity13@wegoch @Words19@seiloch @shiyach_bicha@zefenbicha @leul_mekonnen1

إظهار المزيد
2025 عام في الأرقامsnowflakes fon
card fon
65 756
المشتركون
-2524 ساعات
-567 أيام
-31830 أيام
أرشيف المشاركات
ጭውውት ከአይኖቿ ጠ..ጠ..ር እንደ ዳዊት ጠጠር፤ ወርወር፤ ጎላ ደግሞ ደመቅ፤ ደመና መሰንጠቅ፤ ጠንቀቅ፤ ወጋ ደግሞ ነቀል፤ ስሜትን መፈንቀል፤ ቀልቀል፤ ከብለል ከዛ ረጋ፤ ትንፋሿን ፍለጋ፤ ጠጋ። By @poetkidus @getem @getem @paappii
إظهار الكل...
36🤩 19👍 3🔥 3
ሀ...ለ...ሐ...መ ነገር አከተመ ጥበብ በሁለቱ በግጥም ስዕሉ         ስታወናብደኝ ህይወት ሚሉት ቋንቋ ካንቺ ስር አዋለኝ። መልክሽን በስዕል መልክሽን በግጥም        አተራመስኩልሽ ይኸው አበድኩልሽ። ጥበብና ህይወት... ካንቺ ጋር አጋብተው ላያኖሩኝ ነገር ለምን ይሰጣሉ "ስሜት" ብለው ማፍቀር አቤት አኳኋንሽ አቤት አሳሳቅሽ አቤት አረማመድ ምንድነው መላመድ? ለጥበበኛ ሰው መላመድ ትርፍ ነው አይቶ ማፍቀር ብቻ ጥበብ እያረገው። አይ ጥበብ አንዳንዴ ደስ አለሽ ማበዴ! የማልጨብጣትን ከምናብ አለም ሰው         በፍቅር ሰቀልሽኝ        ይኸው አሳበድሽኝ። ሀ...ለ...ሐ...መ በቃ ተፈፀመ። ታሪክ ልስራ ብዬ...ታሪኬን ጨረስኩት           ኑሮዬን አበድኩት አይ ጥበብ አንዳንዴ ደስ አለሽ ማበዴ! ዮኒ      ኣታን @yonatoz @getem @getem @getem
إظهار الكل...
49🔥 9🤩 1
ብዙ ሳይጣጣር እምብዛም ሳይለፋ ከዓይን የራቀ ከምናብ የሰፋ ይህን ዓለም ሠራ ያለ ጭንቀት ጥበት ሆነለት “ሁን” ሲለው እንዲሁ በዘበት … ሕዋውን በሙሉ ግዑዙን ተፈጥሮ በቃሉ ትዕዛዝ እንዲህ አሳምሮ ለድንጋዩ ራርቶ የንብ መንጋ መርቶ አበባን አፍክቶ ወፊቱን አብልቶ … እኔ ትንሽ ነገር ከሕይወት ቢጨንቀኝ አደራህን ብለው “እሺ ቆይ” እያለ ይህን ሁሉ ዓመት የሚያጠባብቀኝ እንዴት ብከብደው ነው ወይ እንዴት ቢንቀኝ ? …. By henok bekele @getem @getem @paappii
إظهار الكل...
42👎 19😱 4😢 3🔥 2👍 1😁 1
( ተይ ጡር አለው ... ) ================= መቅረት እኮ ብርቅ አይደለም መጣሁ ያለ ሁሉ አይመጣም መተው እኮ ጥንትም ነበር አንዳች እክል ሰው አያጣም አይደንቀኝም ወዶ ማጣት አልከፋኝም በመጥፋትሽ ግን ንገሪኝ .... እንደማትመጭ እያወቅሽው ለምን ይሆን ማስጠበቅሽ ? አንድ ህይወት ነው የተሰጠኝ የማልኖረው ደጋግሜ ግፍ አይደል ወይ ..  ከዚችም ላይ በጥበቃ መስረቅ እድሜ ?? ቅርብ አሳቢ ምስኪን ልብሽ ባያስተውል ልብ ባይለው በወደደው ለጨከነ ላልራራለት ለከጀለው የዘሩትን የሚያሳጭድ ፍቅርም እኮ ተይ ጡር አለው ! By @kiyorna @getem @getem @getem
إظهار الكل...
45😢 13🔥 6👍 4👎 1
--- የአብስራ ሳሙኤል  *・꙳・꙳・꙳・꙳・・* እጠራሀለው  በስምህ አቤት በለኝ ከሰማኀው "ጠይቁ?" ብለህ አልነበር  እጠይቃለሁ አንተ እንዳልከው  ከፀሀይ ጀርባ  ምን አለ? ከህይወት አድማስ ባሻገር  ሞት የህይወት ፍጻሜ ነው?  ወይስ ድልድይ የሚሻገር?  አላዛር ያኔ ቢጠየቅ  የሞተ ግዜ የት ነበር?  ወዴት ነው  የመኖር ማብቂያው?  ወዴት ነው መጠናቀቂያው?  ነፍሴን የማጽናናበት  ምኞቴን የምዳኝበት  ምን አለ ከጸሀይ ጀርባ?  ወዴት ነው ነፍሴ የምትሸሸው?  ይብቃህ እረፍ ተብዬ  የስቃይ ቀኔ የሚያመሸው  አውቃለሁ እንደ ነገርከኝ  ብረዳም ከድርሳን ቅጽህ  ማ? በለኝና ማን ልመን  ብዙ ነው ስምና ገጽህ  *"ጠይቁ?" ብለህ አልነበር・・・ራባይ*  ―☾― አየሁኝ  እውር አንበሣን  አንካሳ ነብር ሲመራው  እንዲህ ነው መንግስት የሚዘልቅ  እንዲህ ነው ፍጡር የሚመራው  ካልተማመነ  መንገዱን በነብር አይን ተረድቶ  መጠራጠር ይገላል  አንዱን ከአንዱ አባልቶ  ይኀው ነው የነፍሴ ጣሯ  አታምነኝ ወይም አላምናት  ማ? በለኝና ማን ልበል  በየቱ ቃልህ ላባብላት  ማመን ነው  የተስፋ ምርኩዝ  መከተል የአይኑ ብርሀን  ወዴት ነው የመኖር ማብቂያው?  ወዴት ይሆን የመራኀን?  ―✦― እጠራሀለው  በስም አቤት በለኝ  ከሰማኀው ጠይቁ ብለህ አልነበር  እጠይቃለሁ አንተ እንዳልኀው  ከጸሀይ ጀርባ  ምን አለ? ኦና'ነት ወይ ፍጻሜ  የት ይሆን ጅምር መቋጫው?  ስንት ይሆን የመኖር እድሜ?  ወዴት ነው የመኖር ማብቂያው?  ወዴት ነው መጠናቀቂያው?  አውቃለሁ  እንደ ነገርከኝ  ብረዳም ከድርሳን ቅጽህ  ማ? በለኝና ማን ልመን  ብዙ ነው ስምና ገጽህ  *・☽・・・☾・・・* @getem @getem @paappii
إظهار الكل...
37🔥 7👎 1
የአብስራ ሳሙኤልዘመን ባይቀድምም እዚህ ህይወት አለ  ከመኖር ወጀብ በመውደድ ሰበዝ የተከለለ  ❀   ❀ እዚህ እናት አለች  ልጇ ሲመጣ ፈገግ ትላለች  እዚህ አባት አለ  ደቂቅ ትከሻው ዝግባ ያከለ  ❀    ❀ እዚህ . . . . .  እኔና አንቺ ባለንት  ነፍስ በዘራንበት  ጠባብ ጎጆ ድንክ ማገር  ታሪክ አለ ለዘመናት የሚሻገር ከገሀድ ጮራ ፈንጥቀን  በፈጠርናት ህብረ ቀለም  መዋደድ ነው የህይወት ቋንቋ  ቤተሰብ ነው የ'ኛ አለም  እዚህ በምታይው  በመኳረፍ እልህ ጥልቅ ፍቅር አለ  የጊዜን ግሳንግስ በሳቅ ያቀለለ  ዕልፍ ተሰብስቦ ቡራኬ የሚቋደስ  እዚህ �ህይወት አለ  አንተ ብላ በሚል ጥጋብ የሚታደስ  እንዴት እንዲህ ይወደዳል  እንዴት እንዲህ ይዋደዳል  የመኖርን �አጸድ በአንዱ ዳና መትከል  ጨርቄን ማቄን ሳይሉ ላመኑት መከተል  እዚህ ብቻ ነው ያለው  ለ'ኛ ብቻ ነው ያደለን  እዚህ ውስጥ ሁላችን አለን  እናት ሆነን አባት ሆነን  ወንድም ሆነን እህት ሆነን  አንድ የመሆን ብዙ መልኮች  የአንድ ሰፌድ ህብራዊ ሰበዝ ገጾች  የህይወት መርህ ያጠላለፈን  የመዋደድ ቅጽ ያደጋገፈን  እዚህ . . . . .  እኔና አንቺ ካለንበት  ህያው ታሪክ አለበት @getem @getem @paappii
إظهار الكل...
27🔥 5
ደርሷል ያልሽኝ ፍሬ በሳል ያልኩሽ ጥሬ ሰላ ያልሽኝ ፍቅር ፀና ያልኩሽ ውቅር ተንዶ በድንገት ለኔም ላንቺም እብለት ላንቺም ለኔም ውሸት እንጭጭ ሳለ ጥሬ ለቀጠፍነው እሸት።         By @poetkidus @getem @getem @getem
إظهار الكل...
18👍 7🔥 1
"ፀሎት ወምኞት"               (ግዮናይ ነኝ)!፧ ከሐምሌ ጨለማ  ከክረምቱ ቆፈን፣ ከበጋው በረሃ   ከግንቦት ወላፈን፣ እኔና አንችን ብቻ  አምላክ ያሳልፈን።                   ...... ካሉባልታ ወሬ  ከምቀኛ ሐሜት፣ ሰይጣን ለሚጠራ  ካልተገራ ስሜት። መንታ ምላስ ይዞ   ከሚሰነጥቀን፣ የፍቅራችን ጌታ   እሱ ይጠብቀን።                   ....... ትዳር ስንክሳሩን  የሳልነው በምናብ፣ ከላይ ይፈሰስልን  እንደ ሐምሌ ዝናብ። በህይወተ-ፍካት በኔና አንቺ ማማር፣ መስከረም ይቅናብን  ጥቅምት ከኛ ይማር። @getem @getem @paappii
إظهار الكل...
33👍 5🔥 2🎉 2🤩 2
( ተደብቆ ) ========= ጠብ ካልሻቱ በቀር እድሜ አይጠየቅም .. ሄዋንን አጥብቆ መፈላለግ እንጂ ፈገግታዋ መሐል ካለ ተደብቆ !!! By @kiyorna @getem @getem @paappii
إظهار الكل...
37😁 17🔥 3😢 1🎉 1
🕊️  የአብስራ ሳሙኤል  🕊️  ተይኝ ሞቴን ልሙት ትውልድ ምናምን አትበይኝ  በፏፏቴ በተራራው በሳር በቅጠል አደልይኝ  እማ ልጄን አትበይኝ  የታሪክ ስንክ ሳር ኋላ ታላቅነትሽን  የድል የድሎት ዘመንሽን  አባይ ሆኖ ጅረት ፈሶ ለሌላ እንጂ የሚ'ደርሰው  ለኔ ብኩን ደካማ ሰው  የዕንባ ብናኝ የደም ወዜን  ግልገል ወንዝሽ መች አርሶት  ለምለም ጤዛሽ መች አብሶት  መቼም ከተራራሽ ብብት  ድንጋይ ቢፋጭ ውሀ ቢላተም  እጇን በዘረጋች እናት አለም  ጸሎት ምልጃዋ ያውጣት እንጂ  ማን እጁን ወዳንቺ ይሰዳል  ምኞት ተስፋሽ ይማግዳል  እናም አልችለውና በሰው አቅም በሰው ገላ  ስጋ ነፍሴን ከ'ነ ህልሟ መሀጸንሽ ተቀብላ  ጸጸት ብሶቷን ታምጥ ግድ የለም  ልጄ አትበይኝ እናት አለም  ተይኝ ሞቴን ልሙት እማ ሆዴን አታባቢው  ተስፋ ምኞት አቀልቢው  መቼም ትታዘቢኝ ይሆናል ያዝናል ወላድ አንጀትሽ  ይነጥፋል ያጠባ ጡትሽ  ሽል ሆኜብሽ የዘር አምሳል አደራሽን ብሸሽም  እማ ትሙች ብሞት �ንጂ ኖሬም ምንም አልጠቅምሽም  እናም አንቺ ውለጅ መውለድ ይክሳል  የኔ አይነት እልፍ ተቀብሮ ከትቢያሽ ህይወት ይነሳል  የምኞትሽን ልጅ ይስጥሽ የተመኘውትን አትንሺኝ  አለወለድኩም ብለሽ እርሺኝ  ለ'ኔ አልሆነም ይሄ ትግል  ምልጃሽ ያውጣኝ በግልግል  ተይኝ ሞቴን ልሙት ትውልድ ምናምን አትበይኝ  በፏፏቴ በተራራው በሳር በቅጠል አደልይኝ  እማ �ጄን �ትበይኝ        _ንሸጣ ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድህን_        _ተወኝ_ @getem @getem @getem
إظهار الكل...
27👍 2🔥 2🎉 1🤩 1
( ልመርቅሽማ ... ) =============== እማ ..... የተረሳው ማንነቴን እንዳወጣሽ ከጨለማ ልትጠይቂው ያሰብሽውን ቃል ሳይወጣሽ ጌታ ይስማ እንደሸፈንሽ ገመናዬን ስሜ ባገር ሳይ'ታማ ኃፍረት አሳር ያገኘሽ ለት ትከልልሽ ጸሐይ ጸልማ ቀን ሲጥለኝ ላጽናናሽኝ እስኪረሳኝ ክፉ ግብሬ የሰማይ ዘብ መላዕክታን ያረጋጉሽ በዝማሬ ...  ወድቄ አይተሽ እንዳልናቅሽኝ ከሰው ተራ በታች ስገኝ ቀን ሰምሮልኝ ከብሬ እንኳ አገልጋይሽ ሎሌሽ ያርገኝ ... አሜን !!! By @kiyorna @getem @getem @paappii
إظهار الكل...
91🔥 14🤩 6😱 2👎 1
ሀገር ሲሰርቅ ጀግኖቹ ዘማቾች! በገደል፣ በደኑ፤ ሌባ ሲያሳድዱ፣ ቀማኛ ሲያድኑ። ጀግኖቹ ዘማቾች! ከጫካው፣ ከዱሩ፤ ነጣቂ ሲያስሱ፣ ሽፍታ ሲያባርሩ። ከዘመቻው ብዛት፣ ከዘማቹ ብዛት − አንድ ‘ዕውቀት’ ተረፈን፤ ለካስ! ሽፍቶች መሀል በቅሎ ‘ጫካው’ ነው ‘ሚዘርፈን። ------ በረከት በላይነህ @getem @getem @paappii
إظهار الكل...
29👍 10🔥 5🎉 2😁 1
አታውቋትም።። (የሞገሴ ልጅ) እህት ማለት- ወንድምነት እንዲታወቅ - ወንድ መሆን ልኩ እንዲታይ፣ መስታወት ናት፣ በታየበት በኩል ሆና - ያልታየውን አይታ አሳይ። የወላጆች- ዘር አጋምዷት ሤትነቷ - ችግኝ ሆኖ የሚጠበቅ፣ እርስት ናት- ውብ ስጦታ ከጎን ሆና - በየ እለቱ የምትናፍቅ። እያላችሁ- እህትነት የኅዝብ ሆኖ - በወል ሚዛን ብትለኳትም፣ እናት መሆን, ለእህትነት ካልተሰጠ - የኔን እህት አታውቋትም። አታውቋትም።።. እንደእድሏ- ነጋ መሸ በልጅ አቅሟ - ልጅ ማሳደግ እጣ ደርሷት፣ ለወንድሟ፣ እናት መምሰል መሆን ጋርዶት - አቻ ላቻ ከእህትነት። የአንድ ሁለት- የሁለት አንድ ምስጢር ሆና - ያለልብ አይን ብታዩአትም፣ አለም ሲኖር፣ በሚአይበት መነጽሩ - የእኔን እህት አታዩአትም. አታዩአትም.. ስም ነው እና፣ እንበል እንጂ ለእህቴ - እህትነት አይገልጻትም. By @tafachgitm @getem @getem @getem
إظهار الكل...
50👍 5🔥 4
( የሚያጋጥም ) ============ ኤዲያ .... : ልክ አብሮ እንደሚሄድ አብሮ እንደሚመጣ አብሮ እንደሚበላ አብሮ እንደሚጠጣ አብሮ የሚያጋጥም ደህና ወዳጅ ልጣ .. !! By @kiyorna @getem @getem @paappii
إظهار الكل...
36👍 6😁 2🔥 1
ልቡ ለከነፈ ፥ ለናፈቀ ወዳጅ ምን ያደረጋል ታክሲ ? ምን ያደረጋል ባጃጅ ? ወራጅ ! የመኪናው ጎማ ፥ ሺ ጊዜ ቢፈጥን መውደዴን ላያክል ጉጉቴን ላይመጥን ! ወራጅ ! ወራጅ ! ናፍቆቷ እንዳልደክም ፥ ይሆነኛል ነዳጅ ። ጫማዬን አስሬ ፥ ወደ ቤቷ ላዝግም አጋዥ አልፈልግም ። መኪናም ይቅርብኝ ፥ ፈረስም አልጋልብ እግር ይቀርባል ላሳብ እግር ይቀርባል ለልብ ። By Hab HD @getem @getem @paappii
إظهار الكل...
48👍 4🔥 4
የኔን ልንገርሽ        አፈቅርሻለሁ፣ እየኖርኩኝ ምቼ                 እጠብቅሻለሁ። የኔን ልንገርሽ       ሀሳቤ ሆነሻል፣ አካሌ ተወርሶ   ልቤ ልብ ሰቶሻል። የኔን ልንገርሽ   ባንቺ ሰግቻለሁ፣ ምን ሆነች እያልኩኝ    የትም አስባለሁ። የኔን ልንገርሽ ለሰው አወራለሁ፣ የኔ ናት እያልኩኝ   ቀኔን አረዝማለሁ። የኔን ልንገርሽ መወሰን ከብዶኛል፣ እያጠፋሽ መተሽ     ይቅርታ ቀሎኛል። የኔን ልንገርሽ ሳላጠፋ ይቅርታ እላለሁ፣ አንቺን ባፈቀርኩኝ     ጌታን መስያለሁ። የኔን ልንገርሽ    ጨጓራዬ በስሏል፣ በቀናሁኝ ቁጥር     ጥላሸት ይመስላል። የኔን ልንገርሽ    ቃላት አብዝቻለሁ፣ ፍቅር ፍቅር እያልኩ     መድረስ ጀምሬአለሁ። የኔን ልንገርሽ    ሰው ያለ አይመስለኝም፣ ሴትም ሰውም ውብም አንቺ ሆነሽ ሌላ አይታየኝም። የኔን ልንገርሽ     አይቀረኝ ሙሉቀን፣     አይቀረኝ ብዙአየሁ፣     አይቀረኝ ታምራት፣     አይቀረኝ ቴዲ አፍሮ፣ ማዳመጥ ነው ልምዴ             እየሰጠው ጆሮ👂፣   አያቅም እኔ ጋር ዘፈን ውሎ አድሮ ።    የአንቺን ግን ንገሪኝ ?          እንደኔ ሆነሻል፣      ወይስ እኔ እንደፃፍኩልሽ          ለአንዱ ሰው ፅፈሻል። ምንጭ፡- የሷን መልስ በመጠበቅ ላይ ሆኜ የተፃፈ ማጀቢያ ሙዚቃ ፡- ልዑል ሲሳይ ( የኔ አመል ) ገጣሚ፡- ፓፒኤል @getem @getem @getem
إظهار الكل...
46👍 4🔥 3🤩 2
እደውላለሁኝ የሚል ቃል ሳይወጣሽ ስልኬን በፍጥጫ ቀለሟን ገፈፍኩት ያለምንም ተስፋ በባዶ ሜዳ ላይ ተስፋዬን ሰነኩት ጉድ እኮ ነው.... ወይ ደውለሽ ልቤ አረጋም ወይ ትተሽኝ ቀኔ አልነጋም እንዲ ስብከነከን እንደ ሰረቀ ሰው ባጉል ተስፋ ኖሬ ሆዴን እንባ ባሰው። ጉድ እኮ ነው.... ትንሽ ቆየሁና ስልኬን አስቀመትኩት እርሳሴን አንስቼ ሃሳቤን አማጥኩት ልግጠም ልሳል ልፃፍ መርጊያ ምስ አጣሁኝ የመድረሻዬን ጫፍ ልግጠምላት.....ስለምኗ? ጠባይ መልኳን ወይንስ ላይኗ ምኗን ልሳል.....ቀይ ከንፈሯን? ሰውነቷን ወይንስ ጠጉሯን ጉድ እኮ ነው.... እንዴት ልፃፍ ምን አንስቼ እሷን ላግኝ እኔን ትቼ? እጄን ላብ ጠመቀው በጨበትኩት እርሳስ ቆይ...ብትመጣስ? ልትመጣ ነው! ምን እየሆንኩ ልጠብቃት? ምን ነበርኩኝ እሷን ሳቃት? ኧረ እኔንጃ ጉድ እኮ ነው.... ወይ አትደውል ወይ አትመጣ እንዲ አያበድኩኝ ቀልቤን ስንቴ ልጣ አሃ! አሃሃ አሃሃ አሃሃ አሃሃ! አይ የኔ ነገር ለካ አታውቀኝም...ኧረ እኔም አላውቃት ታድያ ምን ቤት ሆና ልቤ ሚጠብቃት? ጉድ እኮ ነው.... የት ነበር ያየኋት...? ጎንደር ሸገር ጅማ ሽረ የት ነው ያገኘኋት ልቤስ ነት ነበረ? ወይ አታውቀኝ ወይ አላውቃት ለምንድንው ምጠብቃት? ዮኒ     ኣታን @yonatoz @getem @getem @getem
إظهار الكل...
56🔥 11🤩 4👍 2🎉 2
...ስወድህ እኔ አንተን ስወድህ መስፈርት አላወጣው መልክና ቁመና ምንህን አላየው እኔ አንተን ስወድህ ፍቅርህን ነው ያየው መልክህ ምግባርህ ነው ሁሉን የሚገልፀው እኔ ምልህ ሆዴ መውደድክን ልውደደው By @Hanipia @getem @getem @getem
إظهار الكل...
8👍 3
¹ ገና ወጣት ንፁህ ነበር ..... ያለ  ግብሩ  ወነጀሉት ፤ ይግባኝ  ቢልም አልገባቸው ግራ ቀኝ ሳይሉ ገ ደ ሉት ። ከመሬት አጋድመው አፈ ሙዝ ደግነው እየፎከሩበት እሳት ያዘለ እርሳስ አርከፈከፉበት ። ² የእሱስ ይሁን አንዴ ሄደ እንደ ንፋስ ....ነፍሶ (ደርሶ) አተረፈው ከሕይወቱ (ከስቃይ አዳነው ሞቱ !) ይብላኝ ለኗሪ እናቱ ። ³ ያኔ ፊትለፊቷ.... ልጇን  በመስቀል ላይ የቸነከሩት ለት ያሰረችበትን የወላድ አንጀቷን አላቀበለቻት ማርያም መቀነቷን ። ውስጥ ውስጡን ተከፍታ በሀዘን ዝላለች ስዕሏ ፊት ቆማ እንዲህ ትላታለች “ለደረሰበት ምኑ ሊነገር ? ታውቂው የለም ወይ የልጅን ነገር !? የልጅን ነገር ታውቂው የለም ወይ ? አይተሽ የለም ወይ? ወስደው ሲያዳፉት አስረው ሲገርፉት በምስማር ፊትሽ ሲቸነክሩት አካል ገላውን በደም ሲነክሩት አይተሽ የለም ወይ? ታመሽ የለም ወይ? . . . «ያንቺስ ተነስቷል በሦስት ቀኑ የኔ ግን ይሄው ስንት ዘመኑ በአካል በስጋ መች ይገለጣል ትዝታው ብቻ በሌት ይመጣል ። እስኪ ንገሪኝ ? እነዛ አይሁዶች አንቺን እንደኔ በድለውሻል? ልጅሽን ገድለው አታልቅሽ ብለው ከልክለውሻል?» ⁴ የታወቀ ነው..... ደስታ ቢታሰር በሳቅ ያመልጣል ሀዘን ፈንቅሎ በእንባ ይወጣል (እሷ ትላለች ....) «አልበቃ ብሎ ልጄን የነሱኝ ባዋጅ በሕጉ እየመለሱኝ እንደው በወጉ አላስለቀሱኝ » ⁵ ብዙ ቀን ሄዶ....ብዙ ቀን አልፎ ከሕይወት ዛፍ ላይ ዘመን ረግፎ ጎረቤቶቿ አብረው ሚኖሩ በየሰርጉ ዳስ በየማበሩ ድግስ ሲጠሩ ትታደማለች ፤ እንደ ተፅናና ፈገግ ትላለች ። ሀዘኗ ሳይሽር አውልቃው ማቋን ፤ ዕምባ ዕምባ ይላል ቢቀምሱት ሳቋን ። እየዋሸች ነው እያስመሰለች "እንደ ሚኖሩት ልኑር" እያለች ። (አልተፅናናችም ) ⁶ ተፅናናች እንዴ? ፀኣዳ ቢሆን ከላይ ቀሚሷ የሀዘን ማቋን ካልጣለች ነፍሷ ውስጧ እንዳዘነ.... ልቧ ተከፍቶ ዘቅዝቆ ጥለት ‘ሞቶ መኖር’ ነው .... “መፅናናት” ማለት ? ------ By @Bekalushumye ነሃሴ 23 — 2016 ዓም @getem @getem @getem
إظهار الكل...
41😢 24
✤•⊰❉⊱•✤  የአብስራ ሳሙኤል  ✤•⊰❉⊱•✤ ☆  * * * * * * * * * * * * * * * ☆    ልብ በይ አለሜ    ንጋት እንዳይመስልሽ ወገግ ያለው ሁሉ    ጀንበር 'ና ጥላ ይመሳሰላሉ ☆ * * * * * * * * * * * * * * * ☆ ☀️ 1.  ለምሳሌ  ☀️  ༺༻༺༻༺༻༺༻༺༻༺༻༺༻༺༻ አንቺ ከአለሽበት ሴት አዳሪ መንደር  ለዕሳት ዕራት ገላ ዕሳት ሲንደረደር  ጭኗን ለአደባባይ ከፍታ ያመሳቀለች  ጡቷን ለጎዳናው ሸርፋ የሰቀለች  ወንድ ስትራገም ደግሞም ስትጣራ  መንገዱ ሆኖበት በዚህ ለሚያመራ  ༺༻༺༻༺༻༺༻༺༻༺༻༺༻༺༻  ▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂  ማለዳ ጥላ ነው 'ሌት የህይወት መልኩ  የቄሳር ለቄሳር ብለው ለሚረኩ  ▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂  ༺༻༺༻༺༻༺༻༺༻༺༻༺༻༺༻  እናም በዚች መንደር  ከምስራቅ የወጣ ንጋት ያልሽው ጀንበር  ቀንና ለሊቱን እንዳፈራረቀ  ላይነጋ ይበራል ላይመሽ የጠለቀ  ༺༻༺༻༺༻༺༻༺༻༺༻༺༻༺༻ 🌊 ምሳሌ.2  🌊  ~~~~  ጉሊት ከምታይው መደብ ከመደበ  የሰማይ እጣቢ ፊቱ እየረገበ  ሸርፎ ሲወስድበት  ነጥቆ ሲያጎልበት  ~~~~  ≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈  ጎርፍ አያሳድድም በውሀ ተሳፍሮ  ≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈  ✦✦✦✦✦✦✦✦✦✦✦✦✦✦✦✦  ተመስገን ነው ህይወት  ተመስገን ነው ኑሮ  ✦✦✦✦✦✦✦✦✦✦✦✦✦✦✦✦  🌫️ ምሳሌ.3  🌫️  ◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈  ብርሌውን አንቆ ከንፈሩን ለሚስም  ተርዚና ወጥሮ ቅጠል ለሚቀስም  ታታሪ ሱሰኛ ህላዌውን ገፊ  ◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈  ጨለማ �ነው ሲልሽ  ጀንበር ወቷል እያልሽ ሀቁን አትጋፊ  ▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃  ሳትሰክሪ አታ'ቂውም  ሳትቅሚ አይገባሽም  በሱሰኞች አለም  ▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃  ✵ ✵ ✵ ✵ ✵ ✵ ✵ ✵ ✵ ✵  ሳይቃም አይነጋም  ለሰከረ አይመሽሞ  ✵ ✵ ✵ ✵ ✵ ✵ ✵ ✵ ✵ ✵  .·:·. .·:·. .·:·. .·:·.    ልብ በይ 'ሄን ሁሉ  ንጋት እንዳይመስልሽ ወገግ ያለው ሁሉ  .·:·. .·:·. .·:·. .·:·. ✧༺♥༻∞ ∞༺♥༻✧  አምኖ ላደረነው  አሀዱ ወይ አዛን ማለዶ የሚያነቃው  በቀን ለተረሱ  ✦⋆✦ ንጋት ነው ኮከቡ ✦⋆✦  ✦⋆✦ ንጋት ነው ጨረቃው ✦⋆✦  ∞•🌙•✧•☀️•✧•🌙•∞ @getem @getem @getem
إظهار الكل...
53👍 7🔥 5👎 2