TIKVAH-MAGAZINE
الذهاب إلى القناة على Telegram
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። #ኢትዮጵያ ያግኙን +251913134524
إظهار المزيد2025 عام في الأرقام

194 396
المشتركون
-5024 ساعات
-1767 أيام
-81830 أيام
أرشيف المشاركات
Photo unavailableShow in Telegram
‼️ ይፍጠኑ
‼️ በመሀል ሳር ቤት ቫቲካን ኢምባሲ አካባቢ ‼️
# ቴምር ሪልስቴት ከ8 በላይ ሳይቶችን ጥንቅቅ አድርገን አስረክበን አሁን ደግሞ ሳርቤት ቫቲካን ኢምባሲ አካባቢ ለሽያጭ ያወጣናቸው አፓርትመንቶች
➤ 100% ለሚከፍሉ 35% ቅናሽ
👉 ባለ 2 መኝታ = 81ካሬ = 6ሚሊዮን
👉 ባለ 2 መኝታ = 106ካሬ = 7.9ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 139ካሬ = 10.3ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 152ካሬ = 11.3ሚሊዮን
➤ በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ)
👉 81ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 9.3ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (1.8ሚሊዮን)
👉 106ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 12.1ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (2.4ሚሊዮን)
👉 139ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 15.9ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (3.1ሚሊዮን)
⩩ ቀሪውን 80%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት።
⩩ 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፤ ከከፈሉት ላይ ከ15 -25% ቅናሽ አዘጋጅተናል።
ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን
☎️+251980782850
❤ 26
Photo unavailableShow in Telegram
አሜሪካ ከዚህ ቀደም ለተማሪዎች ቪዛ ለመስጠት የጀመረችውን የአመልካቾችን የማህበራዊ ሚዲያ መፈተሽ ወደ H-1B ቪዛ ልታሰፋ ነው።
የትልልቀ ክህሎት እና ሙያ ባለቤቶች ወደ አሜሪካ ለስራ ሲያቀኑ የሚሰጣቸው የH-1B ቪዛ ከዚህ በኋላ ሲሰጥ የማህበራዊ ሚዲያቸው እንደሚታይ ተገልጿል።
የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት የዚህ ቪዛ አመልካቾች የማህበራዊ ሚዲያቸውን ወደ "public" እንዲቀይሩ ያዘዘ ሲሆን የአሜሪካን ብሄራዊ ጥቅም የሚጎዳ ተግባር እንዳልፈፀሙ ይታያል ብሏል።
የH-1B ቪዛ የአሜሪካ ተቋማት በተለይ በህክምና፣ ቴክኖሎጂ እና ፋይናንስ ላይ ልዩ ችሎታ ያላቸውን የውጪ ሃገራት ዜጎች እንዲቀጥሩ የሚፈቅድላቸው ሲሆን ከማህበራዊ ሚዲያ ፍተሻው በተጨማሪ አመልካቾች በኦንላይን ደህንነት፣ በሃቅ ማጣራት፣ በመረጃ ማዛባት፣ በይዘት ቁጥጥር እና ሌሎችም ተያያዥ ስራዎች ላይ ስለመሰራታቸውም ይታያል ተብሏል።
አሜሪካ ከዚህ በፊት በተራድኦ ድርጅቷ በኩል የሚደረጉ የመረጃ መዛባትን መከላከልና የሃቅ ማጥራት ስራዎችን ትደግፍ እንደነበር ሲታወስ አሁን ላይ ግለሰቦቹ በነዚህ ዘርፎች መስራታቸው ቪዛ ለመሰጠት መታየቱ ግርምትን አጭሯል።
አሜሪካ በአንድ ወቅት ትደግፋቸው የነበሩትን እነዚህ ተግባራት ሃሳብን በነፃነት መግለፅን የሚገድቡ የሳንሱር ተግባር እንደሆኑ ማስረጃ ካለ አመልካቾች ቪዛ ይከለከላሉ ብላለች።
የትራምፕ አስተዳደር እነዚህን ተግባራት ከሃሳብን በነፃነት የመግለፅ ተፃራሪ አድርጎ የሚመለከታቸው ሲሆን ትራምፕ ወደ ቢሮ ከተመለሱ በኋላ የፌደራል ሳንሱርን ማገዳቸው ሲታወስ፣ የውጪ ጉዳይ ቢሮውም የማህበራዊ ሚዲያ ይዘቶች ላይ ቁጥጥር እንዲደረግ ጫና የሚያደርጉ የውጪ ዜጎች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ እንደሚያደርግ መግለፁ ይታወሳል።
ዘገባው የአልጄዚራ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 96👎 15👍 6🤣 5
Photo unavailableShow in Telegram
የኬንያ መንግስት በሳፋሪኮም ውስጥ ያለውን ድርሻ ሊሸጥ ነው።
ኬንያ በሳፋሪኮም ውስጥ ያላትን የ15% ድርሻ ለደቡብ አፍሪካው ቮዳኮም በ1.6 ቢሊየን ዶላር ልትሸጥ ነው።
ውሳኔው በኬንያ የፋይናንስ ሚኒስትር ይፋ ሲሆን የመንግስት ድርጅቶችን በመሸጥ ገንዘብ ማግኘትም ምክንያት ነው ተብሏል።
የኬንያ መንግስት 40 በመቶ ገቢውን እዳ ለመክፈል እያዋለው ሲሆን ይህ ሽያጭም ይህንኑ ታሳቢ ያደረገ ነው።
ቮዳኮም የሳፋሪኮምን የ39.9% ባለድርሻ ሲሆን የኬንያ የፋይናንስ ሚኒስትር ከሳፋሪኮም ሽያጭ የሚገኘው ገንዘብ ያለ ተጨማሪ ብድር በመንገድ፣ በኃይል እንደዚሁም በኤርፖርት ስራ ኢንቨስት ለማድረግ ወደተቋቋሙት የብሔራዊ መሰረተ ልማት ፈንድና የሃብት ፈንድ( Sovereign Wealth Fund) ይገባል ብሏል።
የሳፋሪኮም ሽያጭ የፓርላማ ውሳኔ ብቻ ቀርቶታል ሲባል በተጨማሪም በቀጣይ አመት በኬንያ ነዳጅ የማሰራጨት ስራ የሚሰራው መንግስታዊ ተቋም ድርሻ ለህዝብ መሸጥ ይጀምራል።
ግዢው በፓርላማ ከፀደቀ ቮዳኮም የሳፋሪኮምን 55 በመቶ ድርሻ ሲይዝ፣ የኬንያ መንግስት ድርሻ ወደ 20 በመቶ ይቀንሳል። ቀሪው 25 በመቶ ድርሻ ደግሞ በተለያዩ ኢንቨስተሮች የተያዘ ይሆናል።
ዘገባው የሮይተርስ ነው።
@TikvahethMagazine
❤ 54😢 7👍 5🤔 4👏 2🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
የካሳንቺስ አዲሱ ፕሮጀክታችን ከካሬ 80,000 ብር ጀምሮ ሽያጭ ጀምረናል!!!
እስከ ታህሳስ 29 ብቻ የሚቆይ ከፍተኛ ታላቅ ቅናሽ!
🏡 የቤቶች መጠን
• 1 መኝታ – 97.18 ካሬ
• 2 መኝታ – 120.97 ካሬ
• 3 መኝታ – 176.00 ካሬ
…እና ሌሎችም ብዙ አማራጮች ይገኛሉ!
💰 15% ቅድመ ክፍያ ብቻ በመክፈል ቀሪውን በሶስት አመት የሚከፍሉት!
📩 ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ይደውሉ +251936002200 093 080 7780
info@pvtcenter.com
Private Center Real Estate — Your Foundation Stone for Success
❤ 20😢 2🕊 2🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
በደቡብ ሱዳን የእርዳታ አውሮፕላን ከተጠለፈ በኋላ መገኘቱ ተነገረ።
ንብረትነቱ የወንጌላዊት ክርስቲያን የእርዳታ ቡድን የሆነው አውሮፕላን በታጠቀ ግለሰብከተጠለፈ በኋላ አብራሪው ወደ ቻድ እንዲበር ተደርጎ ነበር።
አውሮፕላኑ የህክምና ቁሳቁሶችን ጭኖ እንደነበር ሲዘገብ ታጣቂው አውሮፕላኑ ውስጥ ቀድሞ ገብቶ መደበቁ ተነግሯል።
ግለሰቡ ለምን ወደ ቻድ መብረር እንደፈለገ ያልተገለፀ ሲሆን አብራሪው አውሮፕላኑ ነዳጅ እንደሚያስፈልገው ከነገረው በኋላ ዋኡ በተባለች ከተማ ማሳረፉና ጠላፊው መያዙ ተነግሯል።
ግለሰቡ በጁባ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት የሚገኝ የአየር ቻርተር ድርጅት ልብስ ለብሶ ነበር ሲባል ድርጅቱ እንደዚህ አይነት ሰራተኛ እንደሌለው አሳውቋል።
ባለፈው ሳምንት የተመሳሳይ የእርዳታ ድርጅት አውሮፕላን የምግብ እርዳታ ጭኖ ሲጓዝ ተከስክሶ በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ ሶስቱም ሰዎች መሞታቸውም ተጠቅሷል።
ዘገባው የአሶሽየትድ ፕረስ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 69🤣 21😢 11👍 5
Photo unavailableShow in Telegram
ተመድ የ2026 በጀቱን በ577 ሚሊየን ዶላር ይቀንሳል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በ2026 የ15.1% የበጀት ቅነሳ እንደሚደረግና የሰራተኞቹ ቁጥርም በ18.8% እንደሚቀንስ ተናግረዋል።
ዋና ፀሃፊው የተመድ የ2026 በጀት 3.24 ቢሊየን ዶላር እንደሚሆንና ከ2025 አንፃር በ577 ሚሊየን ዶላር ቅናሽ እንደሚኖር ተናግረዋል።
አሜሪካ፣ ቻይና፣ ሩሲያና ሜክሲኮ መክፈል የሚጠበቁባቸውን ክፍያዎች ያልፈፀሙ ሃገራት ናቸው ሲባል ይህም ለበጀት እጥረቱ ምክንያት ነው ተብሏል።
ጉተሬዝ የፍልስጤም ስደተኞችን የሚደግፈው UNRWA ምንም አይነት ቅነሳ እንዳይደረግበት አዝዣለሁም ብለዋል።
ተመድ የአባል ሃገራቱ ያልከፈሉት አጠቃላይ ክፍያ 1.59 ትሪሊየን ዶላር መድረሱን ገልፆ 2681 የስራ ቦታዎችንም እንደሚቀንስ አስታውቋል።
ተመድ የልዩ የፖለቲካ ተልዕኮዎች በጀትን በ21.6 በመቶ የቀነሰ ሲሆን አንዳንድ ተልዕኮዎቹ ሊቋረጡ እንደሚችሉም አስታውቋል።
የተለያዩ ቢሮዎቹን ከኒውዮርክ ለማዞር ያቀደው ተመድ በኒውዮርክ ያሉትን ሁለት ሊዞች በ2027 እንደሚያቋርጥና ይህም ከ2029 ጀምሮ 24 ሚሊየን ዶላር በአመት እንደሚያድን ዋና ፀሃፊው ገልፀዋል።
ዘገባው የአልጄዚራ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 45👍 8😢 7👎 3🙏 2
Photo unavailableShow in Telegram
በአመት 5.6 ሚሊየን ፓስፖርቶችን የማምረት አቅም ያለው ፋብሪካ ወደመጠናቀቅ መቃረቡ ተነገረ።
በቦሌ ለሚ ሁለት የኢንዱስትሪ ፓርክ እየተሰራ ያለውና 12,000 ስኩዌር ሜትር ቦታ ላይ ያረፈው እንደዚሁም የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በባለድርሻነት የተሳተፈበት የፓስፖርት እና የመታወቂያ ማምረቻ ወደመጠናቀቁ ተቃርቧል ተብሏል።
ፋብሪካው በፈረንጆቹ 2026 መጀመሪያ ይጠናቀቃል ሲባል ሙሉ ለሙሉ ወደ ስራ ሲገባም በአመት 5.6 ሚሊየን ፓስፖርት እና 28 ሚሊየን የመታወቂያ እና የባንክ ካርዶችን የማምረት አቅም ይኖረዋል ተብሏል።
ማምረቻው ለ200 ሰዎች የስራ እድል እንደሚፈጥር ሲጠበቅ በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ማምረቱ የሚኖርን የመታወቂያ ማጭበርበር ይቀንሳል ተብሎ ይጠበቃል።
ከዚህ በፊት የፓስፖርት ህትመት በውጪ ሃገራት መከናወኑ የኢትዮጵያ ፓስፖርት በማይገባቸው ሰዎች እጅ እንዲገኝ ምክንያት መሆኑ እንደዚሁም የውጪ ምንዛሬ እንደሚያስወጣና ተገልጋዮችን እንደሚያጉላላ በተደጋጋሚ መነገሩ ሲታወስ በሃገር ውስጥ መመረት መጀመሩ ከደህንነት በተጨማሪ አገልግሎትን በጊዜ ለመስጠት ያስችላል ተብሏል።
ዘገባው የአዲስ ፎርቹን ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 71👍 43🤣 18🤔 7🤷♂ 6👎 3
Photo unavailableShow in Telegram
የካሳንቺስ አዲሱ ፕሮጀክታችን ከካሬ 80,000 ብር ጀምሮ ሽያጭ ጀምረናል!!!
እስከ ታህሳስ 29 ብቻ የሚቆይ ከፍተኛ ታላቅ ቅናሽ!
🏡 የቤቶች መጠን
• 1 መኝታ – 97.18 ካሬ
• 2 መኝታ – 120.97 ካሬ
• 3 መኝታ – 176.00 ካሬ
…እና ሌሎችም ብዙ አማራጮች ይገኛሉ!
💰 15% ቅድመ ክፍያ ብቻ በመክፈል ቀሪውን በሶስት አመት የሚከፍሉት!
📩 ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ይደውሉ +251936002200 093 080 7780
info@pvtcenter.com
Private Center Real Estate — Your Foundation Stone for Success
👎 6❤ 4
Photo unavailableShow in Telegram
የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቻትቦቶች በግጥም መልክ ሲጠየቁ የደህንነት ህጎችን እንደሚዘነጉ አዲስ ጥናት አመላከተ።
በጣልያን የሚገኙ ተመራማሪዎች መጥፎ የሆኑ "prompts"በግጥም መልክ ቻትቦቶችን በመጠየቅ የደህንነት ሁኔታዎችን ማለፍ ይቻላል ብለዋል።
በጥናቱ የጎግል፣ የኦፕንኤአይ እና የኤክስኤአይን ቻትቦቶች ጨምሮ 25 ብዙ ተጠቃማ ያላቸው ቻትቦቶች ተካተው ነበር።
በጥናቱ እነዚህ የኤአይ ሞዴሎች 62 በመቶ ለሚሆኑት በግጥም ለቀረቡ ተገቢ ያልሆኑ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።
ተገቢ ባልሆኑት ጥያቄዎች ውስጥ የጥላቻ ንግግር፣ የወሲብ፣ ራስን ስለመግደል እና መሳሪያ እንዴት እንደሚሰራ የሚሉትን በግጥም መልክ መጠየቅ ሲገኙበት የኦፕንኤአዩ GPT-5 nano ለየትኛውም መጥፎ ጥያቄ ምላሽ አለመስጠቱ በአንፃሩ የጎግሉ Gemini 2.5 pro ለሁሉም መልስ መስጠቱ ተነግሯል።
ተመራማሪዎቹ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሞዴሎቹ በመደበኛ ሁኔታ ስር እና በተለመደው የቋንቋ አፃፃፍ መሰልጠናቸው በግጥም መልክ ተገቢ ያልሆኑ ጥያቄዎችን ሲጠየቁ ምላሽ እንዲሰጡ ምክንያት ሆኗል ያሉ ሲሆን ለተቋማቱ የጥናቱን ሰነድ እንዲመለከቱና እንዲያስተካክሉ መላካቸውን ገልፀዋል።
ዘገባው ከዩሮኒውስ የተገኘ ነው።
#IsitAi?
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 75🤣 42😢 3🕊 1
Photo unavailableShow in Telegram
ህንድ የስማርት ስልክ አምራቾች በራሷ የበለፀገውን የሳይበር ደህንነት መተግበሪያ ቀድመው በስልኮቹ እንዲጭኑ አዛለች።
የህንድ የቴሌኮም ሚኒስትር የስማርት ስልክ አምራቾች በመንግስት የበለፀገውን የሳይበር ደህንነት መተግበሪያ ቀድመው አዳዲስ በሚያመርቷቸው ስልኮች እንዲጭኑ በሚስጥር መጠየቁ የተነገረ ሲሆን መተግበሪያውን ከስልክ ላይ ማጥፋት አለመቻሉ ደግሞ የግለሰባዊ ደህንነት ጥያቄን አጭሯል።
ህንድ እየበዛ ያለውን የማጭበርበር እና የሳይበር ወንጀሎች ለመከላከል እንደዚሁም ሰዎች በተሰረቁ ስልኮች ወንጀሎችን እንዳይፈፅሙ ለመከላከል ይህንን እርምጃ መውሰዷ ተሰምቷል።
እንደ አፕልና ሳምሰንግ ያሉ የስልክ አምራቾችም ይህንን መተግበሪያ በአዳዲስ ስልኮች መጫን እንዲጀምሩ የ90 ቀናት የጊዜ ገደብ ሲሰጣቸው እየተመረቱ ባሉ ስልኮች ላይ ደግሞ በሶፍትዌር ማሻሻያ መልክ እንዲጫኑ ለህዝብ ይፋ ባልሆነው ጥያቄ አዛለች።
ሳንቻር ሳታሂ የተባለው ይህ መተግበሪያ የሩሲያ ማክስ የተሰኘ መልዕከት መለዋወጫ በስልኮች ላይ ቀድሞ እንዲጫን ባለፈው ነሐሴ ወር ካስገደደች በኋላ የመጣ ነው።
ህንድ ይህ መተግበሪያ ባለፈው ጥር ወር ከተለቀቀ በኋላ ከ700,000 በላይ የጠፉ ስልኮች እንዲገኙ ምክንያት ሆኗል ስትል 30 ሚሊየን የሚሆን የማጭበርበር ግንኙነቶችንም አቋርጧል ብላለች።
በ2025 በህንድ ከሚገኙት 735 ሚሊየን ስማርት ስልኮች ውስጥ 4.5% ተጠቃሚዎች ያሉት አፕል ህጉ የመንግስት መተግበሪያዎችን ቀድሞ በስልኮች ላይ መጫንን የሚከለክል ሲሆን ሌሎች የስልክ አምራቾች በጉዳዩ ላይ ምላሽ አልሰጡም።
ዘገባው የሮይተርስ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 46👎 7👍 6
Photo unavailableShow in Telegram
ኤይርባስ A320 በተሰኘው አውሮፕላኑ የተወሰኑ አውሮፕላኖች ላይ የጥራት ችግር እንዳለ አስታወቀ።
ግዙፉ የአውሮፕላን አምራች ኤይርባስ A320 በተሰኘው የአውሮፕላን ሞዴሉ የተወሰኑ አውሮፕላኖች ላይ የቀረበለት የሜታል ፓነል ላይ የጥራት ችግር መኖሩን ገልፆ በዚህ የጥራት ችግር የተጠቁ አውሮፕላኖች ጥቂት መሆናቸውንና ምርመራ መጀመሩን ገልጿል።
ኤይርባስ ይህንን ካስታወቀ በኋላ የአክሲዮን ገበያው በ10% መቀነሱ ተዘግቧል።
ኤይርባስ በዚህ አመት 820 አውሮፕላኖችን ለማቅረብ ያቀደ ሲሆን ይህንን እቅዱን ለማሳካት በዚህ ወር ብቻ 160 አውሮፕላኖችን ማቅረብ ይጠበቅበታል።
በሳምንቱ መጨረሻ 6000 የሚሆኑ የA320 አውሮፕላኖች የሶፍትዌር ችግር ገጥሟቸው ነበር ሲባል የአውሮፓ ተቆጣጣሪዎች ለበረራ ቁጥጥር ወሳኝ የሆነው መረጃ በፀሃይ ጨረር የተነሳ ሊበላሽ እንደሚችል በመጠቆም ማስጠንቀቂያ ሰጥተው ነበር።
ከዛ በኋላ በርካታ አየር መንገዶች የሶፍትዌር ማሻሻያ በማድረግ በረራቸውን መቀጠላቸው ተሰምቷል።
የአሁኑ የጥራት ችግር ከዚህ ጋር ተዳምሮ ኤይርባስ እቅዱን እንዳያሳካ ሊያደርገው ይችላል ተብሏል።
ዘገባው የቢዝነስ ኢንሳይደር አፍሪካ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 34👍 6🕊 2🙏 1
Photo unavailableShow in Telegram
የካሳንቺስ አዲሱ ፕሮጀክታችን ከካሬ 80,000 ብር ጀምሮ ሽያጭ ጀምረናል!!!
እስከ ታህሳስ 29 ብቻ የሚቆይ ከፍተኛ ታላቅ ቅናሽ!
🏡 የቤቶች መጠን
• 1 መኝታ – 97.18 ካሬ
• 2 መኝታ – 120.97 ካሬ
• 3 መኝታ – 176.00 ካሬ
…እና ሌሎችም ብዙ አማራጮች ይገኛሉ!
💰 15% ቅድመ ክፍያ ብቻ በመክፈል ቀሪውን በሶስት አመት የሚከፍሉት!
📩 ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ይደውሉ +251936002200 093 080 7780
info@pvtcenter.com
Private Center Real Estate — Your Foundation Stone for Success
❤ 12👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ በሃገሯ ለ16ኛ ጊዜ የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ ማብቃቱን አውጃለች።
ከህክምና ተቋም የመጨረሻው ታካሚ ከወጣ በኋላ በነበሩት 42 ቀናት ምንም አዲስ ሰው በበሽታው አለመያዙን ተከትሎ ኮንጎ ወረርሽኙ ማብቃቱን አውጃለች።
በሽታው ለመጀመሪያ ጊዜ በ1976 ከተከሰተ በኋላ ለ16ኛ ጊዜ በተቀሰቀሰው ወረርሽኝ 64 ሰዎች በኢቦላ ተይዘው 45 ሰዎች መሞታቸውም ተዘግቧል።
በሽታውን ለመቆጣጠር ከ47500 በላይ ሰዎች ክትባት መውሰዳቸው ሲነገር የአለም ጤና ድርጅትም በቁሳቁስና በባለሙያ ድጋፍ አድርጎ ነበር።
😀 | @tikvahethmagazine
👏 56❤ 22👍 4🤔 2🙏 2🕊 1
Photo unavailableShow in Telegram
ቭላድሚር ፑቲን የቻይና ዜጎች ያለ ቪዛ ወደ ሩሲያ እንዲገቡ የሚፈቅደ አዋጅ ፈርመዋል።
የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የቻይና ዜጋ የሆኑ ቱሪስቶች፣ የቢዝነስ ሰዎች፣ የስፖርት ሰዎች፣ የአካዳሚ ሰዎችና አርቲስቶች ወደ ሩሲያ ያለ ቪዛ ገብተው ለ30 ቀናት መቆየት እንዲችሉ ወስነዋል።
ቻይናም ለሩሲያ ዜጎች ተመሳሳይ ነፃ ፈቃድ ከባለፈው መስከረም ወር ጀምራ የሰጠች ሲሆን ይህ የነፃ ቪዛ አገልግሎት እስከ መጪው መስከረም 2026 ይቆያል ተብሏል።
በአዲሱ የፑቲን ውሳኔ በሎጅስቲክስ እና ትራንስፖርት ዘርፍ የሚሰሩ ሰዎችና የረጅም ጊዜ ተማሪዎች አልተካተቱም።
ሩሲያና ቻይና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግንኙነታቸውን ማጥበቅ ሲቀጥሉ በተለይ ሩሲያ በዩክሬን ጦርነት የተነሳ በምዕራባውያኑ ተደጋጋሚ ማዕቀብ ከተጣለባት በኋላ ከቤጂንግ ጋር ያላትን ወታደራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እያጠበቀች ትገኛለች።
ዘገባው የሮይተርስ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 85👍 26🤣 9
Photo unavailableShow in Telegram
አሜሪካ ድንበር ተሻጋሪ ክፍያዎችን በተመለከተ ማስጠንቀቂያ ሰጠች።
የአሜሪካ የፋይናንስ ወንጀሎች መረብ በህገወጥ መንገድ የተገኘ ገንዘብ ድንበር ተሻግሮ ሊላክ ስለሚችል ይህንን የገንዘብ ዝውውር ለሚያሳልጡ ተቋማት ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።
እነዚህ ተቋማት ከ2,000 ዶላር በላይ የሆነ ድንበር ተሻጋሪ ክፍያ ሲፈፀም ህጋዊ ካልሆነ ቅጥር የተገኘና ከህገወጥ ተግባር ጋር የተያያዘ ነው ብለው ከጠረጠሩ ሪፖርት ማድረግ አለባቸው ተብሏል።
አሜሪካ በየአመቱ ከ72 ቢሊየን ዶላር በላይ ገንዘብ ከሃገር ውጪ ያሉ ሰዎችን ለማገዝ በሬሚታንሰ መልክ ይወጣል ብትልም ሌሎች አነስተኛ መጠን ያላቸው ገንዘቦች ግን ሽብርተኝነት እና ወንጀልን ለመደገፍ ይላካሉ ብላለች።
አሜሪካ ይህ ቁጥጥር በህጋዊ መንገድ በአሜሪካ የሚኖሩ ሰዎችን አይመለከትም ያለች ሲሆን የፋይናንስ ተቋማትና የገንዘብ አዘዋዋሪዎች ተጨማሪ ማብራሪያዎችን እንዲከታተሉ አዛለች።
ዘገባው ከዳዋን አፍሪካ የተገኘ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 32🤷♂ 2👎 2🕊 2
Photo unavailableShow in Telegram
‼️ ይፍጠኑ
‼️ በመሀል ሳር ቤት ቫቲካን ኢምባሲ አካባቢ ‼️
# ቴምር ሪልስቴት ከ8 በላይ ሳይቶችን ጥንቅቅ አድርገን አስረክበን አሁን ደግሞ ሳርቤት ቫቲካን ኢምባሲ አካባቢ ለሽያጭ ያወጣናቸው አፓርትመንቶች
➤ 100% ለሚከፍሉ 35% ቅናሽ
👉 ባለ 2 መኝታ = 81ካሬ = 6ሚሊዮን
👉 ባለ 2 መኝታ = 106ካሬ = 7.9ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 139ካሬ = 10.3ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 152ካሬ = 11.3ሚሊዮን
➤ በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ)
👉 81ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 9.3ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (1.8ሚሊዮን)
👉 106ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 12.1ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (2.4ሚሊዮን)
👉 139ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 15.9ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (3.1ሚሊዮን)
⩩ ቀሪውን 80%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት።
⩩ 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፤ ከከፈሉት ላይ ከ15 -25% ቅናሽ አዘጋጅተናል።
ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን
☎️+251980782850
❤ 15
Photo unavailableShow in Telegram
በባለፈው አመት የአለማችን ግዙፎቹ የጦር መሳሪያ አምራቾች ገቢ በ5.9% መጨመሩ ተነገረ።
በአለማችን ላይ እየበዛ የመጣውን ጦርነት ተከትሎ የምድራችን ትላልቆቹ የጦር መሳሪያ ሻጮች ገቢ ባለፈው አመት በ5.9 በመቶ ጨምሯል ተብሏል።
የስቶኮልም የሰላም ጥናት ተቋም 100 የሚሆኑ የአለማችን ትላልቆቹ የጦር መሳሪያ አምራቾች ገቢ በ2024 ወደ 679 ቢሊየን ዶላር መድረሱንና ይህም የተመዘገበ ከፍተኛው ገቢ መሆኑን ገልጿል።
ሃገራት ከፍተኛ የሚባል በጀትን በመከላከያ ላይ ማውጣታቸውም የድርጅቶቹ ገቢ እንዲጨምር ምክንያት ሆኗል።
አብዛኞቹ የጦር መሳሪያ አምራች ድርጅቶች በአሜሪካና አውሮፓ የሚገኙ ናቸው።
ዘገባው የአሶሽየትድ ፕረስ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
😢 66❤ 47🤔 9
Photo unavailableShow in Telegram
#Update
የጃኮብ ዙማ ልጅ ዱዱዚሌ ዙማ ከሳምንታት በፊት 17 ወንዶችን ለሩሲያ ጦርነት መልምላለች ከተባለች በኋላ ከፓርላማ አባልነቷ በገዛ ፈቃዷ ለቃለች።
በአባቷ ጃኮብ ዙማ የሚመራው ፓርቲ ለሩሲያ በተመለመሉ ወጣቶች ዙሪያ ምንም ተሳትፎ የለኝም ያለ ሲሆን ለወጣቶቹ ቤተሰቦች ድጋፍ አደርጋለሁ ብሏል።
ዱዱዚሌ ዙማ ወጣቶቹን ለሩሲያ መመልመሏን ያስታወቀችውና ክስ የመሰረተችው እህቷ ስትሆን ፖሊስም ምርመራ መጀመሩን አስታውቋል።
ዘገባው የዘ ኢንዲፔንደንት ነው።
👋 | @tikvahethmagazine
❤ 33👍 13🤣 4
Photo unavailableShow in Telegram
የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ በሃገራቸው ያሉ ቤተክርስቲያናትን ወቅሰዋል።
የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ አንዳንድ ቤተክርስቲያናት እምነትን ከማስተማር ይልቅ ዜጎችን መበዝበዝ ተያይዘዋል በማለት እያደገ የመጣውን የቤተክርስቲያን ቁጥር ተችተዋል።
ባለፈው ነሐሴ ወር ሩዋንዳ የጤና እና ደህንነት መመሪያዎች አላሟሉም ያለቻቸውን 4000 ቤተክርስቲያናት ዘግታለች።
ሩዋንዳ የቤተክርስቲያን ቁጥር እየጨመረ ያለው አንዳንድ የቤተክርስቲያን መስራቾች የግል ጥቅማቸውን ለመጨመር በማሰባቸው ነው ብላለች።
በተጨማሪም ሐሰተኛ ትምህርቶችን በማስፋፋት የግል የፋይናንስ ጥቅማቸውን የሚያስቀድሙና ከአባሎች ንብረት የሚወስዱ መስራቾች በዝተዋል ነው የተባለው።
ፕረዚዳንት ፖል ካጋሜ፥ የሃይማኖት ተቋማት ትርፍ ከመፈለግ በትምህርት፣ ጤና እና ማኅበረሰባዊ ለውጥ ላይ ትኩረት ማድረግ አለባቸው ሲሉ ገልጸዋል።
ዘገባው የ DW ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 168👍 64👏 31🤔 4🙏 3🤷♂ 2🤝 2🤣 1
Photo unavailableShow in Telegram
ያልተመጣጠነው የደሞዝ ልዩነት
በአለም አቀፍ ደረጃ የድርጅቶች ዋና ስራ አስፈፃሚዎች ከ2019 ወዲህ ክፍያቸው በ50 በመቶ ሲጨምር የመደበኛ ሰራተኞች ክፍያ ግን የጨመረው በ0.9% ብቻ ነው።
አማካይ የድርጅቶች ዋና ስራ አስፈፃሚዎች ክፍያ በ2019 ከነበረበት 2.9 ሚሊየን ዶላር በ2024 4.3 ሚሊየን ዶላር ደርሷል።
አየርላንድ እና ጀርመን ለዋና ስራ አስፈፃሚዎች ከፍተኛ አማካይ ክፍያ የሚከፈልባቸው ሃገራት ሲሆኑ በ2024 በአማካይ በቅደም ተከተል 6.7 ሚሊየን ዶላርና 4.7 ሚሊየን ዶላር አመታዊ ክፍያ ይከፈላል።
በደቡብ አፍሪካ ይህ አማካይ የዋና ስራ አስፈፃሚዎች ክፍያ 1.6 ሚሊየን ዶላር ይደርሳል።
በየጊዜው በድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚዎች እና በመደበኛ ሰራተኞች መካከል ያለው የደመወዘ እድገትና ክፍያ እየሰፋ የመጣ ሲሆን እንደ ኦክስፋም ያሉ ድርጅቶች በነዚህ ሃብታሞች ላይ የሚጣለው ታክስ እንዲጨምር ጥሪ እያደረጉ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 69😢 19👍 18👎 10
