en
Feedback
TIKVAH-MAGAZINE

TIKVAH-MAGAZINE

Open in Telegram

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። #ኢትዮጵያ ያግኙን +251913134524

Show more
2025 year in numberssnowflakes fon
card fon
194 402
Subscribers
-5024 hours
-1767 days
-81830 days
Posts Archive
"በ09 ቁጥራቸው የተመዘገቡ ደንበኞች መተግበሪያው መግባት እና ገንዘባቸውን ማንቀሳቀስ እንዳይችሉ እገዳ ተጥሎባቸዋል" - ኤምፔሳ ኢትዮጵያ ኤምፔሳ ኢትዮጵያ "M-PESA ለሁሉም" የተሰኘ በማንኛውም ሲም ካርድ የሚሰራ የሞባይል የክፍያ ሥርዓት ወደ ገቢያው ማስገባቱን ከቀናት በፊት አስታውቆ ነበር። ሆኖም ዛሬ ባወጣው መግለጫ፥ "መተግበሪያውን ለመጠቀም በ09 ቁጥራቸው በራሳቸው ፈቃድ የተመዘገቡ ደንበኞች አገልግሎቱን በኢትዮ ቴሌኮም ዳታ ተጠቅመው እንዳያገኙ ወደ መተግበሪያው መግባት እና ገንዘባቸውን ማንቀሳቀስ እንዳይችሉ እገዳ ተጥሎባቸዋል።" ሲል አስታውቋል። M-PESA ኢትዮጵያ አገልግሎቱን ለማስጀመር ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የከፍያ መፈጸሚያ ሰነድ አውጪ ፈቃድ (Payment Instrument Issuer License) እንደተሰጠው እና ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ተገቢውን ፈቃድ ማግኘቱን አንስቷል። M-PESA ኢትዮጵያ ጉዳዩን የሚመለከታቸው ተቆጣጣሪ አካላት እንዲያውቁት እና ችግሩን በአስቸኳይ ለመፍታት እንዲቻል እየሰራ እንደሚገኝ በመግለጫው ላይ አንስቷል። "M-PESA ለሁሉም" የተሰኘው መተግበሪያ በልዩ ሁኔታ ደንበኞች የሳፋሪኮም ሲም ካርድ ባይኖራቸው እንኳን አሁን በሚጠቀሙበት ስልክ ቁጥራቸው አገልግሎቱን መጠቀም የሚያስችላቸው እንደሆነ መግለጹ ይታወሳል። 😀   |   @tikvahethmagazine
Show all...
❤ 54🤣 25🤔 7👎 3🤷‍♂ 2
Photo unavailableShow in Telegram
"የወባ በሽታ በኢትዮጵያ ፣ ማዳጋስካርና የመን በልዩ ሁኔታ ጨምሯል" - የዓለም ጤና ድርጅት ° በ2024 ብቻ በወባ በሽታ 610 ሺህ ሰዎች መሞታቸውን የአለም ጤና ድርጅት አስታወቀ። የአለም ጤና ድርጅት የወባ በሽታ አሁንም አሳሳቢ መሆኑን ጠቅሶ በ2024 610,000 ሰዎች መሞታቸውንና አብዛኛው ሞትም ከሰሃራ በታች ባለው አፍሪካ እና በህፃናት ላይ መመዝገቡን ገልጿል። ድርጅቱ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥርም 282 ሚሊየን ደርሷል ያለ ሲሆን ለመጨመሩ የድጋፍ መቋረጥ፣ የአየር ንብረት ለውጥና በሽታው መድሃኒት መላመዱ ምክንያት ሆኗል ብሏል። የአለም ጤና ድርጅት በ2000ዎቹ እ.ኤ.አ በወባ በሽታ የተመዘገበው ስኬት ሊቀለበስ ይችላል ብሎ አስጠንቅቋል። በ2024 በሽታው በኢትዮጵያ ፣ ማዳጋስካርና የመን በልዩ ሁኔታ መጨመሩን የዓለም ጤና ድርጅት ገልጿል። ዘገባው የአፍሪካ ኒውስ ነው። 😀   |   @tikvahethmagazine
Show all...
😢 37❤ 21👍 6🕊 3🤣 2
#አፋልጉኝ ስም: ተፈራ ተሾመ መታፈሪያ እድሜ: 53 ረቡዕ በቀን 24/03/2018 ዓ.ም ከሸገር ከተማ አለምገና(ኬንቴሪ) ካለው ቤቱ ለሾል ብሎ ወጥቶ አልተመለሰም። የለበሰው ልብሴ፡ ውሃ ሰማያዊ ሱሪ፣ ጥቁር ጃኬት እና ነጭ ጫማ ሁለት እናታቸው የሌለች ሕፃናት ልጆች አሉት ሾል የሚሰራበት አካባቢ ኮልፌ ፣ አጠና ተራ፣ ሽሎ ሜዳ ፣ ሰንዳፋ አካባቢዎች ስልክ 0909668955 አብረሃም 0911505185 0989019046  በሱፍቃድ @tikvahethmagazine
Show all...
😢 72❤ 38🙏 5🔥 1
"ወደ ሁለቱ ሃገራት ታላላቆቹን ድርጅቶቻችንን እንልካለን፤ የከበሩ ማዕድናትን አውጥተን እንከፍላለን ሁሉም ብዙ ገንዘብ ያገኛል" - ትራምፕ የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜና የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ ፕረዚዳንት ፌሊክስ ሼሲኬዲ የሰላም ስምምነት በዋሽንግተን ተፈራርመዋል። ኮንጎ፥ በሃገሯ ምስራቃዊ ክፍል ያለውን የኤም 23 ታጣቂ ኃይል ሩዋንዳ ትደግፋለች ብላ በተደጋጋሚ ትከስ የነበረ ሲሆን የሁለቱ ሃገራት መሪዎች ይህንን ለማቆም ተስማምተዋል። ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካን የሰላም ተቋም ስያሜ ወደ ዶናልድ ትራምፕ የሰላም ተቋም ከቀየሩ በኋላ ስምምነቱ በተቋሙ ውስጥ ተፈፅሟል። ትራምፕ ስምምነቱን ለአፍሪካና ለአለም ትልቅ ቀን ሲሉ የገለፁ ሲሆን የሁለቱን ሃገራት መሪዎችም ብልህ ሲሉ ገልፀዋል። በስምምነቱ መፈረም ወቅት በትራምፕ ግብዣ የኬንያውን ፕሬዚዳንት ጨምሮ የአንጎላ፣ የቡሩንዲ እና የቶጎ መሪዎች ሲገኙ የኡጋንዳ ምክትል ፕሬዚዳንት እንደዚሁም የኳታር እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች ተገኝተዋል። ፖል ካጋሜ ትራምፕ ወገንተኛ ስላልሆኑ ስምምነቱ ተፈፅሟል ያሉ ሲሆን ፌሊክስ ሼሴኬዲ ሩዋንዳ ስምምነቱን ታከብራለች ብለን እንጠብቃለን ብለዋል። በስምምነቱ የአማፂው ኤም 23 áˆłá‹­áŠŤáˆáˆ ሲቀር፥ ትራምፕ አሜሪካ ማዕድናትን ከሁለቱም ሃገራት ለመግዛትም የሁለትዮሽ ስምምነት ታደርጋለች ብለዋል። ትራምፕ " ወደ ሁለቱ ሃገራት ታላላቆቹን ድርጅቶቻችንን እንልካለን፤ የከበሩ ማዕድናትን አውጥተን እንከፍላለን ሁሉም ብዙ ገንዘብ ያገኛል" ብለዋል። የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት በ2023 ባወጣው መረጃ ኮንጎ ብቻዋን 25 ትሪሊየን ዶላር የሚያወጣ የማዕድን ክምችት አላት። ግጭቱ ያለበት የምስራቃዊ ኮንጎም በማዕድን የበለፀገ እንደሆነ እና ታጣቂው ጭምር በህገወጥ መንገድ አውጥቶ ራሱን የሚያጠናክርበት እንደሆነ ይታወቃል። ዘገባው ከቢቢሲ እና አልጄዚራ የተገኘ ነው። 😀   |   @tikvahethmagazine
Show all...
❤ 50🤣 25😢 15👎 4
Photo unavailableShow in Telegram
‼️ ይፍጠኑ ‼️ á‰ áˆ˜áˆ€áˆ ሳር ቤት ቫቲካን ኢምባሲ አካባቢ ‼️ # ቴምር ሪልስቴት ከ8 በላይ ሳይቶችን ጥንቅቅ አድርገን አስረክበን አሁን ደግሞ ሳርቤት ቫቲካን ኢምባሲ አካባቢ ለሽያጭ ያወጣናቸው አፓርትመንቶች   ➤ 100% ለሚከፍሉ 35% ቅናሽ 👉 ባለ 2 መኝታ = 81ካሬ = 6ሚሊዮን 👉 ባለ 2 መኝታ = 106ካሬ = 7.9ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 139ካሬ = 10.3ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 152ካሬ = 11.3ሚሊዮን ➤ በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ) 👉 81ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 9.3ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (1.8ሚሊዮን) 👉 106ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 12.1ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (2.4ሚሊዮን) 👉 139ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 15.9ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (3.1ሚሊዮን) ⊊ ቀሪውን 80%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት። ⊊ 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፤ ከከፈሉት ላይ ከ15 -25% ቅናሽ አዘጋጅተናል። ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን ☎️+251980782850
Show all...
❤ 26
Photo unavailableShow in Telegram
አሜሪካ ከዚህ ቀደም ለተማሪዎች ቪዛ ለመስጠት የጀመረችውን የአመልካቾችን የማህበራዊ ሚዲያ መፈተሽ ወደ H-1B ቪዛ ልታሰፋ ነው። የትልልቀ ክህሎት እና ሙያ ባለቤቶች ወደ አሜሪካ ለሾል ሲያቀኑ የሚሰጣቸው የH-1B ቪዛ ከዚህ በኋላ ሲሰጥ የማህበራዊ ሚዲያቸው እንደሚታይ ተገልጿል። የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት የዚህ ቪዛ አመልካቾች የማህበራዊ ሚዲያቸውን ወደ "public" እንዲቀይሩ ያዘዘ ሲሆን የአሜሪካን ብሄራዊ ጥቅም የሚጎዳ ተግባር እንዳልፈፀሙ ይታያል ብሏል። የH-1B ቪዛ የአሜሪካ ተቋማት በተለይ በህክምና፣ ቴክኖሎጂ እና ፋይናንስ ላይ ልዩ ችሎታ ያላቸውን የውጪ ሃገራት ዜጎች እንዲቀጥሩ የሚፈቅድላቸው ሲሆን ከማህበራዊ ሚዲያ ፍተሻው በተጨማሪ አመልካቾች በኦንላይን ደህንነት፣ በሃቅ ማጣራት፣ በመረጃ ማዛባት፣ በይዘት ቁጥጥር እና ሌሎችም ተያያዥ ስራዎች ላይ ስለመሰራታቸውም ይታያል ተብሏል። አሜሪካ ከዚህ በፊት በተራድኦ ድርጅቷ በኩል የሚደረጉ የመረጃ መዛባትን መከላከልና የሃቅ ማጥራት ስራዎችን ትደግፍ እንደነበር ሲታወስ አሁን ላይ ግለሰቦቹ በነዚህ ዘርፎች መስራታቸው ቪዛ ለመሰጠት መታየቱ ግርምትን አጭሯል። አሜሪካ በአንድ ወቅት ትደግፋቸው የነበሩትን እነዚህ ተግባራት ሃሳብን በነፃነት መግለፅን የሚገድቡ የሳንሱር ተግባር እንደሆኑ ማስረጃ ካለ አመልካቾች ቪዛ ይከለከላሉ ብላለች። የትራምፕ አስተዳደር እነዚህን ተግባራት ከሃሳብን በነፃነት የመግለፅ ተፃራሪ አድርጎ የሚመለከታቸው ሲሆን ትራምፕ ወደ ቢሮ ከተመለሱ በኋላ የፌደራል ሳንሱርን ማገዳቸው ሲታወስ፣ የውጪ ጉዳይ ቢሮውም የማህበራዊ ሚዲያ ይዘቶች ላይ ቁጥጥር እንዲደረግ ጫና የሚያደርጉ የውጪ ዜጎች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ እንደሚያደርግ መግለፁ ይታወሳል። ዘገባው የአልጄዚራ ነው። 😀   |   @tikvahethmagazine
Show all...
❤ 96👎 15👍 6🤣 5
Photo unavailableShow in Telegram
የኬንያ መንግስት በሳፋሪኮም ውስጥ ያለውን ድርሻ ሊሸጥ ነው። ኬንያ በሳፋሪኮም ውስጥ ያላትን የ15% ድርሻ ለደቡብ አፍሪካው ቮዳኮም በ1.6 ቢሊየን ዶላር ልትሸጥ ነው። ውሳኔው በኬንያ የፋይናንስ ሚኒስትር ይፋ ሲሆን የመንግስት ድርጅቶችን በመሸጥ ገንዘብ ማግኘትም ምክንያት ነው ተብሏል። የኬንያ መንግስት 40 በመቶ ገቢውን እዳ ለመክፈል እያዋለው ሲሆን ይህ ሽያጭም ይህንኑ ታሳቢ ያደረገ ነው። ቮዳኮም የሳፋሪኮምን የ39.9% ባለድርሻ ሲሆን የኬንያ የፋይናንስ ሚኒስትር ከሳፋሪኮም ሽያጭ የሚገኘው ገንዘብ ያለ ተጨማሪ ብድር በመንገድ፣ በኃይል እንደዚሁም በኤርፖርት ስራ ኢንቨስት ለማድረግ ወደተቋቋሙት የብሔራዊ መሰረተ ልማት ፈንድና የሃብት ፈንድ( Sovereign Wealth Fund) ይገባል ብሏል። የሳፋሪኮም ሽያጭ የፓርላማ ውሳኔ ብቻ ቀርቶታል ሲባል በተጨማሪም በቀጣይ አመት በኬንያ ነዳጅ የማሰራጨት ስራ የሚሰራው መንግስታዊ ተቋም ድርሻ ለህዝብ መሸጥ ይጀምራል። ግዢው በፓርላማ ከፀደቀ ቮዳኮም የሳፋሪኮምን 55 በመቶ ድርሻ ሲይዝ፣ የኬንያ መንግስት ድርሻ ወደ 20 በመቶ ይቀንሳል። ቀሪው 25 በመቶ ድርሻ ደግሞ በተለያዩ ኢንቨስተሮች የተያዘ ይሆናል። ዘገባው የሮይተርስ ነው። @TikvahethMagazine
Show all...
❤ 54😢 7👍 5🤔 4👏 2🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
የካሳንቺስ አዲሱ ፕሮጀክታችን ከካሬ 80,000 ብር ጀምሮ ሽያጭ ጀምረናል!!! እስከ ታህሳስ 29 ብቻ የሚቆይ ከፍተኛ ታላቅ ቅናሽ! 🏡 የቤቶች መጠን • 1 መኝታ – 97.18 ካሬ • 2 መኝታ – 120.97 ካሬ • 3 መኝታ – 176.00 ካሬ …እና ሌሎችም ብዙ አማራጮች ይገኛሉ! 💰 15% ቅድመ ክፍያ ብቻ በመክፈል ቀሪውን በሶስት አመት የሚከፍሉት! 📩 ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ይደውሉ +251936002200 093 080 7780 info@pvtcenter.com Private Center Real Estate — Your Foundation Stone for Success
Show all...
❤ 20😢 2🕊 2🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
በደቡብ ሱዳን የእርዳታ አውሮፕላን ከተጠለፈ በኋላ መገኘቱ ተነገረ። ንብረትነቱ የወንጌላዊት ክርስቲያን የእርዳታ ቡድን የሆነው አውሮፕላን በታጠቀ ግለሰብከተጠለፈ በኋላ አብራሪው ወደ ቻድ እንዲበር ተደርጎ ነበር። አውሮፕላኑ የህክምና ቁሳቁሶችን ጭኖ እንደነበር ሲዘገብ ታጣቂው አውሮፕላኑ ውስጥ ቀድሞ ገብቶ መደበቁ ተነግሯል። ግለሰቡ ለምን ወደ ቻድ መብረር እንደፈለገ ያልተገለፀ ሲሆን አብራሪው አውሮፕላኑ ነዳጅ እንደሚያስፈልገው ከነገረው በኋላ ዋኡ በተባለች ከተማ ማሳረፉና ጠላፊው መያዙ ተነግሯል። ግለሰቡ በጁባ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት የሚገኝ የአየር ቻርተር ድርጅት ልብስ ለብሶ ነበር ሲባል ድርጅቱ እንደዚህ አይነት ሰራተኛ እንደሌለው አሳውቋል። ባለፈው ሳምንት የተመሳሳይ የእርዳታ ድርጅት አውሮፕላን የምግብ እርዳታ ጭኖ ሲጓዝ ተከስክሶ በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ ሶስቱም ሰዎች መሞታቸውም ተጠቅሷል። ዘገባው የአሶሽየትድ ፕረስ ነው። 😀   |   @tikvahethmagazine
Show all...
❤ 69🤣 21😢 11👍 5
Photo unavailableShow in Telegram
ተመድ የ2026 በጀቱን በ577 ሚሊየን ዶላር ይቀንሳል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በ2026 የ15.1% የበጀት ቅነሳ እንደሚደረግና የሰራተኞቹ ቁጥርም በ18.8% እንደሚቀንስ ተናግረዋል። ዋና ፀሃፊው የተመድ የ2026 በጀት 3.24 ቢሊየን ዶላር እንደሚሆንና ከ2025 አንፃር በ577 ሚሊየን ዶላር ቅናሽ እንደሚኖር ተናግረዋል። አሜሪካ፣ ቻይና፣ ሩሲያና ሜክሲኮ መክፈል የሚጠበቁባቸውን ክፍያዎች ያልፈፀሙ ሃገራት ናቸው ሲባል ይህም  ለበጀት እጥረቱ ምክንያት ነው ተብሏል። ጉተሬዝ የፍልስጤም ስደተኞችን የሚደግፈው UNRWA ምንም አይነት ቅነሳ እንዳይደረግበት አዝዣለሁም ብለዋል። ተመድ የአባል ሃገራቱ ያልከፈሉት አጠቃላይ ክፍያ 1.59 ትሪሊየን ዶላር መድረሱን ገልፆ 2681 የስራ ቦታዎችንም እንደሚቀንስ አስታውቋል። ተመድ የልዩ የፖለቲካ ተልዕኮዎች በጀትን በ21.6 በመቶ የቀነሰ ሲሆን አንዳንድ ተልዕኮዎቹ ሊቋረጡ እንደሚችሉም አስታውቋል። የተለያዩ ቢሮዎቹን ከኒውዮርክ ለማዞር ያቀደው ተመድ በኒውዮርክ ያሉትን ሁለት ሊዞች በ2027 እንደሚያቋርጥና ይህም ከ2029 ጀምሮ 24 ሚሊየን ዶላር በአመት እንደሚያድን ዋና ፀሃፊው ገልፀዋል። ዘገባው የአልጄዚራ ነው። 😀   |   @tikvahethmagazine
Show all...
❤ 45👍 8😢 7👎 3🙏 2
Photo unavailableShow in Telegram
በአመት 5.6 ሚሊየን ፓስፖርቶችን የማምረት አቅም ያለው ፋብሪካ ወደመጠናቀቅ መቃረቡ ተነገረ። በቦሌ ለሚ ሁለት የኢንዱስትሪ ፓርክ እየተሰራ ያለውና 12,000 ስኩዌር ሜትር ቦታ ላይ ያረፈው እንደዚሁም የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በባለድርሻነት የተሳተፈበት የፓስፖርት እና የመታወቂያ ማምረቻ ወደመጠናቀቁ ተቃርቧል ተብሏል። ፋብሪካው በፈረንጆቹ 2026 መጀመሪያ ይጠናቀቃል ሲባል ሙሉ ለሙሉ ወደ ሾል ሲገባም በአመት 5.6 ሚሊየን ፓስፖርት እና 28 ሚሊየን የመታወቂያ እና የባንክ ካርዶችን የማምረት አቅም ይኖረዋል ተብሏል። ማምረቻው ለ200 ሰዎች የስራ እድል እንደሚፈጥር ሲጠበቅ በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ማምረቱ የሚኖርን የመታወቂያ ማጭበርበር ይቀንሳል ተብሎ ይጠበቃል። ከዚህ በፊት የፓስፖርት ህትመት በውጪ ሃገራት መከናወኑ የኢትዮጵያ ፓስፖርት በማይገባቸው ሰዎች እጅ እንዲገኝ ምክንያት መሆኑ እንደዚሁም የውጪ ምንዛሬ እንደሚያስወጣና ተገልጋዮችን እንደሚያጉላላ በተደጋጋሚ መነገሩ ሲታወስ በሃገር ውስጥ መመረት መጀመሩ ከደህንነት በተጨማሪ አገልግሎትን በጊዜ ለመስጠት ያስችላል ተብሏል። ዘገባው የአዲስ ፎርቹን ነው። 😀   |   @tikvahethmagazine
Show all...
❤ 71👍 43🤣 18🤔 7🤷‍♂ 6👎 3
Photo unavailableShow in Telegram
የካሳንቺስ አዲሱ ፕሮጀክታችን ከካሬ 80,000 ብር ጀምሮ ሽያጭ ጀምረናል!!! እስከ ታህሳስ 29 ብቻ የሚቆይ ከፍተኛ ታላቅ ቅናሽ! 🏡 የቤቶች መጠን • 1 መኝታ – 97.18 ካሬ • 2 መኝታ – 120.97 ካሬ • 3 መኝታ – 176.00 ካሬ …እና ሌሎችም ብዙ አማራጮች ይገኛሉ! 💰 15% ቅድመ ክፍያ ብቻ በመክፈል ቀሪውን በሶስት አመት የሚከፍሉት! 📩 ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ይደውሉ +251936002200 093 080 7780 info@pvtcenter.com Private Center Real Estate — Your Foundation Stone for Success
Show all...
👎 6❤ 4
Photo unavailableShow in Telegram
የሰው ሰልሽ አስተውሎት ቻትቦቶች በግጥም መልክ ሲጠየቁ የደህንነት ህጎችን እንደሚዘነጉ አዲስ ጥናት አመላከተ። በጣልያን የሚገኙ ተመራማሪዎች መጥፎ የሆኑ "prompts"በግጥም መልክ ቻትቦቶችን በመጠየቅ የደህንነት ሁኔታዎችን ማለፍ ይቻላል ብለዋል። በጥናቱ የጎግል፣ የኦፕንኤአይ እና የኤክስኤአይን ቻትቦቶች ጨምሮ 25 ብዙ ተጠቃማ ያላቸው ቻትቦቶች ተካተው ነበር። በጥናቱ እነዚህ የኤአይ ሞዴሎች 62 በመቶ ለሚሆኑት በግጥም ለቀረቡ ተገቢ ያልሆኑ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል። ተገቢ ባልሆኑት ጥያቄዎች ውስጥ የጥላቻ ንግግር፣ የወሲብ፣ ራስን ስለመግደል እና መሳሪያ እንዴት እንደሚሰራ የሚሉትን በግጥም መልክ መጠየቅ ሲገኙበት የኦፕንኤአዩ GPT-5 nano ለየትኛውም መጥፎ ጥያቄ ምላሽ አለመስጠቱ በአንፃሩ የጎግሉ Gemini 2.5 pro ለሁሉም መልስ መስጠቱ ተነግሯል። ተመራማሪዎቹ የሰው ሰልሽ አስተውሎት ሞዴሎቹ በመደበኛ ሁኔታ ሾር እና በተለመደው የቋንቋ አፃፃፍ መሰልጠናቸው በግጥም መልክ ተገቢ ያልሆኑ ጥያቄዎችን ሲጠየቁ ምላሽ እንዲሰጡ ምክንያት ሆኗል ያሉ ሲሆን ለተቋማቱ የጥናቱን ሰነድ እንዲመለከቱና እንዲያስተካክሉ መላካቸውን ገልፀዋል። ዘገባው ከዩሮኒውስ የተገኘ ነው። #IsitAi? 😀   |   @tikvahethmagazine
Show all...
❤ 75🤣 42😢 3🕊 1
Photo unavailableShow in Telegram
ህንድ የስማርት ስልክ አምራቾች በራሷ የበለፀገውን የሳይበር ደህንነት መተግበሪያ ቀድመው በስልኮቹ እንዲጭኑ አዛለች። የህንድ የቴሌኮም ሚኒስትር የስማርት ስልክ አምራቾች በመንግስት የበለፀገውን የሳይበር ደህንነት መተግበሪያ ቀድመው አዳዲስ በሚያመርቷቸው ስልኮች እንዲጭኑ በሚስጥር መጠየቁ የተነገረ ሲሆን መተግበሪያውን ከስልክ ላይ ማጥፋት አለመቻሉ ደግሞ የግለሰባዊ ደህንነት ጥያቄን አጭሯል። ህንድ እየበዛ ያለውን የማጭበርበር እና የሳይበር ወንጀሎች ለመከላከል እንደዚሁም ሰዎች በተሰረቁ ስልኮች ወንጀሎችን እንዳይፈፅሙ ለመከላከል ይህንን እርምጃ መውሰዷ ተሰምቷል። እንደ አፕልና ሳምሰንግ ያሉ የስልክ አምራቾችም ይህንን መተግበሪያ በአዳዲስ ስልኮች መጫን እንዲጀምሩ የ90 ቀናት የጊዜ ገደብ ሲሰጣቸው እየተመረቱ ባሉ ስልኮች ላይ ደግሞ በሶፍትዌር ማሻሻያ መልክ እንዲጫኑ ለህዝብ ይፋ ባልሆነው ጥያቄ አዛለች። ሳንቻር ሳታሂ የተባለው ይህ መተግበሪያ የሩሲያ ማክስ የተሰኘ መልዕከት መለዋወጫ በስልኮች ላይ ቀድሞ እንዲጫን ባለፈው ነሐሴ ወር ካስገደደች በኋላ የመጣ ነው። ህንድ ይህ መተግበሪያ ባለፈው ጥር ወር ከተለቀቀ በኋላ ከ700,000 በላይ የጠፉ ስልኮች እንዲገኙ ምክንያት ሆኗል ስትል 30 ሚሊየን የሚሆን የማጭበርበር ግንኙነቶችንም አቋርጧል ብላለች። በ2025 በህንድ ከሚገኙት 735 ሚሊየን ስማርት ስልኮች ውስጥ 4.5% ተጠቃሚዎች ያሉት አፕል ህጉ የመንግስት መተግበሪያዎችን ቀድሞ በስልኮች ላይ መጫንን የሚከለክል ሲሆን ሌሎች የስልክ አምራቾች በጉዳዩ ላይ ምላሽ አልሰጡም። ዘገባው የሮይተርስ ነው። 😀   |   @tikvahethmagazine
Show all...
❤ 46👎 7👍 6
Photo unavailableShow in Telegram
ኤይርባስ A320 በተሰኘው አውሮፕላኑ የተወሰኑ አውሮፕላኖች ላይ የጥራት ችግር እንዳለ አስታወቀ። ግዙፉ የአውሮፕላን አምራች ኤይርባስ A320 በተሰኘው የአውሮፕላን ሞዴሉ የተወሰኑ አውሮፕላኖች ላይ የቀረበለት የሜታል ፓነል ላይ የጥራት ችግር መኖሩን ገልፆ በዚህ የጥራት ችግር የተጠቁ አውሮፕላኖች ጥቂት መሆናቸውንና ምርመራ መጀመሩን ገልጿል። ኤይርባስ ይህንን ካስታወቀ በኋላ የአክሲዮን ገበያው በ10% መቀነሱ ተዘግቧል። ኤይርባስ በዚህ አመት 820 አውሮፕላኖችን ለማቅረብ ያቀደ ሲሆን ይህንን እቅዱን ለማሳካት በዚህ ወር ብቻ 160 አውሮፕላኖችን ማቅረብ ይጠበቅበታል። በሳምንቱ መጨረሻ 6000 የሚሆኑ የA320 አውሮፕላኖች የሶፍትዌር ችግር ገጥሟቸው ነበር ሲባል የአውሮፓ ተቆጣጣሪዎች ለበረራ ቁጥጥር ወሳኝ የሆነው መረጃ በፀሃይ ጨረር የተነሳ ሊበላሽ እንደሚችል በመጠቆም ማስጠንቀቂያ ሰጥተው ነበር። ከዛ በኋላ በርካታ አየር መንገዶች የሶፍትዌር ማሻሻያ በማድረግ በረራቸውን መቀጠላቸው ተሰምቷል። የአሁኑ የጥራት ችግር ከዚህ ጋር ተዳምሮ ኤይርባስ እቅዱን እንዳያሳካ ሊያደርገው ይችላል ተብሏል። ዘገባው የቢዝነስ ኢንሳይደር አፍሪካ ነው። 😀   |   @tikvahethmagazine
Show all...
❤ 34👍 6🕊 2🙏 1
Photo unavailableShow in Telegram
የካሳንቺስ አዲሱ ፕሮጀክታችን ከካሬ 80,000 ብር ጀምሮ ሽያጭ ጀምረናል!!! እስከ ታህሳስ 29 ብቻ የሚቆይ ከፍተኛ ታላቅ ቅናሽ! 🏡 የቤቶች መጠን • 1 መኝታ – 97.18 ካሬ • 2 መኝታ – 120.97 ካሬ • 3 መኝታ – 176.00 ካሬ …እና ሌሎችም ብዙ አማራጮች ይገኛሉ! 💰 15% ቅድመ ክፍያ ብቻ በመክፈል ቀሪውን በሶስት አመት የሚከፍሉት! 📩 ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ይደውሉ +251936002200 093 080 7780 info@pvtcenter.com Private Center Real Estate — Your Foundation Stone for Success
Show all...
❤ 12👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ በሃገሯ ለ16ኛ ጊዜ የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ ማብቃቱን አውጃለች። ከህክምና ተቋም የመጨረሻው ታካሚ ከወጣ በኋላ በነበሩት 42 ቀናት ምንም አዲስ ሰው በበሽታው አለመያዙን ተከትሎ ኮንጎ ወረርሽኙ ማብቃቱን አውጃለች። በሽታው ለመጀመሪያ ጊዜ በ1976 ከተከሰተ በኋላ ለ16ኛ ጊዜ በተቀሰቀሰው ወረርሽኝ 64 ሰዎች በኢቦላ ተይዘው 45 ሰዎች መሞታቸውም ተዘግቧል። በሽታውን ለመቆጣጠር ከ47500 በላይ ሰዎች ክትባት መውሰዳቸው ሲነገር የአለም ጤና ድርጅትም በቁሳቁስና በባለሙያ ድጋፍ አድርጎ ነበር። 😀   |   @tikvahethmagazine
Show all...
👏 56❤ 22👍 4🤔 2🙏 2🕊 1
Photo unavailableShow in Telegram
ቭላድሚር ፑቲን የቻይና ዜጎች ያለ ቪዛ ወደ ሩሲያ እንዲገቡ የሚፈቅደ አዋጅ ፈርመዋል። የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የቻይና ዜጋ የሆኑ ቱሪስቶች፣ የቢዝነስ ሰዎች፣ የስፖርት ሰዎች፣ የአካዳሚ ሰዎችና አርቲስቶች ወደ ሩሲያ ያለ ቪዛ ገብተው ለ30 ቀናት መቆየት እንዲችሉ ወስነዋል። ቻይናም ለሩሲያ ዜጎች ተመሳሳይ ነፃ ፈቃድ ከባለፈው መስከረም ወር ጀምራ የሰጠች ሲሆን ይህ የነፃ ቪዛ አገልግሎት እስከ መጪው መስከረም 2026 ይቆያል ተብሏል። በአዲሱ የፑቲን ውሳኔ በሎጅስቲክስ እና ትራንስፖርት ዘርፍ የሚሰሩ ሰዎችና የረጅም ጊዜ ተማሪዎች አልተካተቱም። ሩሲያና ቻይና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግንኙነታቸውን ማጥበቅ ሲቀጥሉ በተለይ ሩሲያ በዩክሬን ጦርነት የተነሳ በምዕራባውያኑ ተደጋጋሚ ማዕቀብ ከተጣለባት በኋላ ከቤጂንግ ጋር ያላትን ወታደራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እያጠበቀች ትገኛለች። ዘገባው የሮይተርስ ነው። 😀   |   @tikvahethmagazine
Show all...
❤ 85👍 26🤣 9
Photo unavailableShow in Telegram
አሜሪካ ድንበር ተሻጋሪ ክፍያዎችን በተመለከተ ማስጠንቀቂያ ሰጠች። የአሜሪካ የፋይናንስ ወንጀሎች መረብ በህገወጥ መንገድ የተገኘ ገንዘብ ድንበር ተሻግሮ ሊላክ ስለሚችል ይህንን የገንዘብ ዝውውር ለሚያሳልጡ ተቋማት ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል። እነዚህ ተቋማት ከ2,000 ዶላር በላይ የሆነ ድንበር ተሻጋሪ ክፍያ ሲፈፀም ህጋዊ ካልሆነ ቅጥር የተገኘና ከህገወጥ ተግባር ጋር የተያያዘ ነው ብለው ከጠረጠሩ ሪፖርት ማድረግ አለባቸው ተብሏል። አሜሪካ በየአመቱ ከ72 ቢሊየን ዶላር በላይ ገንዘብ ከሃገር ውጪ ያሉ ሰዎችን ለማገዝ በሬሚታንሰ መልክ ይወጣል ብትልም ሌሎች አነስተኛ መጠን ያላቸው ገንዘቦች ግን ሽብርተኝነት እና ወንጀልን ለመደገፍ ይላካሉ ብላለች። አሜሪካ ይህ ቁጥጥር በህጋዊ መንገድ በአሜሪካ የሚኖሩ ሰዎችን አይመለከትም ያለች ሲሆን የፋይናንስ ተቋማትና የገንዘብ አዘዋዋሪዎች ተጨማሪ ማብራሪያዎችን እንዲከታተሉ አዛለች። ዘገባው ከዳዋን አፍሪካ የተገኘ ነው። 😀   |   @tikvahethmagazine
Show all...
❤ 32🤷‍♂ 2👎 2🕊 2
Photo unavailableShow in Telegram
‼️ ይፍጠኑ ‼️ á‰ áˆ˜áˆ€áˆ ሳር ቤት ቫቲካን ኢምባሲ አካባቢ ‼️ # ቴምር ሪልስቴት ከ8 በላይ ሳይቶችን ጥንቅቅ አድርገን አስረክበን አሁን ደግሞ ሳርቤት ቫቲካን ኢምባሲ አካባቢ ለሽያጭ ያወጣናቸው አፓርትመንቶች   ➤ 100% ለሚከፍሉ 35% ቅናሽ 👉 ባለ 2 መኝታ = 81ካሬ = 6ሚሊዮን 👉 ባለ 2 መኝታ = 106ካሬ = 7.9ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 139ካሬ = 10.3ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 152ካሬ = 11.3ሚሊዮን ➤ በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ) 👉 81ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 9.3ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (1.8ሚሊዮን) 👉 106ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 12.1ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (2.4ሚሊዮን) 👉 139ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 15.9ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (3.1ሚሊዮን) ⊊ ቀሪውን 80%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት። ⊊ 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፤ ከከፈሉት ላይ ከ15 -25% ቅናሽ አዘጋጅተናል። ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን ☎️+251980782850
Show all...
❤ 15