አዲስ ነገር መረጃ
الذهاب إلى القناة على Telegram
#አዲስ_ነገር_መረጃ #መረጃዎች_በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ Addis Ababa , Ethiopia Buy Ads : https://telega.io/?r=UbutLo2z #ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇 @Addisnegermereja_bot
إظهار المزيد2025 عام في الأرقام

103 076
المشتركون
-9224 ساعات
-3717 أيام
+21730 أيام
أرشيف المشاركات
Photo unavailableShow in Telegram
የሩሲያ ጀነራል በሞስኮ መገደላቸው ተነገረ፡፡
በመኪና ውስጥ በተጠመደ ቦምብ ጀነራሉ ህይወታቸውን ማጣታቸውን የአር ቲ ዘገባ ያሳያል፡፡
የሩሲያ የምርመራ ኮሚቴ ከፍተኛው ጀነራል ህይዎታቸውን ማጣታቸውን ከማረጋገጡም ባሻገር ምርመራውን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
በደቡባዊ የከተማዋ ክፍል በርካታ ተሸከርካሪዎች ወድመዋል፤አሽከርካሪም ተጎድቷል፡፡
ሌተናንት ጀነራል ፋኒል ሳርቫሮቭ የኦፕሬሽናል ስልጠና መሪ እንደነበሩም ተነግሯል፡፡
የግድያው ሁኔታ ምንድን ነው የሚለውን የደህንነት ኃይሎች አሁንም በማጣራት ላይ ናቸው ተብሏል፡፡
የዩክሬን የኢንተለጀንስ አገልግሎት በጉዳዪ ላይ እጁ ሊኖርበት ይችላል የሚል ጥርጣሬም ሞስኮ አላት፡፡
ሳርቫሮቭ በመከላከያው ውስጥ ለከፍተኛ ባለሙያዎች ስልጠናን በማዘጋጀት እንዲሁም የተለያዩ ኃላፊነቶችን በመውሰድ የሚታወቁ ነበሩ፡፡
@Addisinsider_ETH
@Addisinsider_ETH
❤ 19😢 10👏 2
Photo unavailableShow in Telegram
ወርቅ በአለም አቀፍ ገበያ ላይ ከፍተኛ ዋጋ ታየበት
ዛሬ በአለም አቀፍ ገበያ የወርቅ ዋጋ ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍተኛ ዋጋ እየተሸጠ ነው ።
ሮይተርስ እንደዘገበው፣ ለዋጋው መጨመር ዋነኛው ምክንያት የአሜሪካ የፌደራል መጠባበቂያ የወለድ ምጣኔን ይቀንሳል የሚለው ጠንካራ ግምት ነው።
የአንድ ወቄት ወርቅ ዋጋ 4,383.76 ዶላር በመድረስ አዲስ ታሪክ አስመዝግቧል።
ባለፈው ሳምንት የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ በአሜሪካ የሥራ ገበያ ላይ የታየው ድክመት እና የዋጋ ግሽበት መቀነስ ማዕከላዊ ባንኩ የገንዘብ ፖሊሲውን ለማላላት ምቹ ሁኔታ ፈጥሮለታል።
በጂኦፖለቲካዊ ውጥረቶች፣ በንግድ ግጭቶች እና በሚቀጥለው የፈረንጆቹ ዓመት የወለድ ምጣኔ ይቀንሳል በሚል ግምት ሳቢያ የወርቅ ዋጋ በዚህ የፈረንጆቹ ዓመት በ67 በመቶ ጨምሯል።
ቀደም ብሎ በጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ የወርቅ ዋጋ ከፍተኛ ቅናሽ አሳይቶ የነበረ ሲሆን፣ በወቅቱ የአንድ ወቄት ወርቅ ዋጋ ወደ 4,130.40 ዶላር ዝቅ ብሎ ነበር።
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤ 15👍 2🔥 2🤣 2
በኮንትራክሽን ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ሰራተኞች ለተለያዩ ጉዳቶች ተጋላጭ መሆናቸው በጥናት ተመላከተ
በአዲስ አበባ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ሰራተኞች ለተለያዩ ጉዳቶች ተጋላጭ መሆናቸው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥናት አመላከተ።
ዩኒቨርስቲው ባጠናው ጥናት 5 መቶ 62 የአምራች ፣ የአገልግሎት ሰጪና ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪዎች ተካተውበታል።
በዚህም 1 መቶ 2 ኢንዲስትሪዎች ውስጥ 76 ነጥብ 8 በመቶ ከአምራች ዘርፍ፣ ከኮንስትራክሽን ዘርፍ ሁሉም፣ ከአገልግሎት ዘርፍ ደግሞ 25 ነጥብ 9 በመቶ እየሰሩ ያሉበት የስራ ሁኔታ፣ ሠራተኞችን በከፍተኛ ደረጃ ለአደጋ አጋላጭ ነው ተብሏል።
በእያንዳንዱ የጤና ችግር ላይ ከ1 ሺህ 5 መቶ እስከ 2 ሺህ በተደረገ ጥናት፣ 34 ነጥብ 3 በመቶ አምራች ኢንዱስትሪዎች ፣ 25 ነጥብ 2 በመቶ በአገልግሎት ዘርፍ ፣ 23 ነጥብ 1 በመቶ ደግሞ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ሰራተኞች የመተንፈሻ አካላት በሽታ ምልክቶች እንደተገኘባቸው ተጠቅሷል።
በተጨማሪም 58 በመቶ የአምራች ኢንዲስትሪዎች ፣ 69 ነጥብ 9 በመቶ የአገልግሎት ፣ 65 ነጥብ 5 በመቶ የኮንስትራክሽን ሰራተኞች የአንገት ፣ የጀርባ የጡንቻ መገጣጠሚያ የጤና ችግር እንዳጋጠማቸው ተገልጿል።
እያንዳንዱ የኢንዱስትሪ የስራ ቦታ ደህንነትና የጤና ፖሊሲ ሊኖረው ይገባል የተባለ ሲሆን ጥናቱን መሰረት በማድረግ በጉዳዩ ላይ ደረጃውን የጠበቀ ስልጠና መስጠት የሚያስችል መመሪያ መዘጋጀቱም ተገልጿል።
በዓለም የስራ ድርጅት ሪፖርት መሰረት በአለም አቀፍ ደረጃ በስራ ምክንያት በየአመቱ ከ2 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ሰራተኞች ሲሞቱ፣ ከ270 ሚሊየን በላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት ፣ ከ160 ሚሊየን ቀላል የአካል ጉዳት ይዳረጋሉ።
ዘገባው የሪፖርተር ነው
@Addis_News
@Addis_News
❤ 12
Photo unavailableShow in Telegram
♨️ እንኳን ደስ አላችሁ ለመላው ስራ ፈላጊ ኢትዮጲያዊያን!
-----------------------------------
✅ Make Money Online In Ethiopia 🇪🇹 ✅
በቀን 3000 ብር የሚከፍል ዌብሳይት
15,000- በላይ ክፍት ቦታዎች በ0 አመት እና በልምድ
🔺የትምህርት አይነት: በተለያዩ ዲፓርትመንቶች
🔺የስራ ልምድ: በ 0 ዓመትና በልምድ
🔺 የቅጥር ሁኔታ: በቋሚ ቅጥር
🔺 ብዛት: 15,000+ በላይ
🔺ደሞዝ: በቀን 3000 ብር
🛑 ፈጥነው ታች ባለው ሊንክ ስራውን ይጀምሩ
⁉️ ማሳሰቢያ:- VPN ወይም Psiphon መጠቀም ይኖርባችሗል
👇👇👇👇Apply Now👇👇👇👇👇
👇👇👇👇
https://reportervacancy.com/make-money-onlinejobs-for-beginners-2025/
--------Follow Our Website--------
👇👇👇👇👇👇
https://reportervacancy.com
----------Join Our Telegram-------
👇👇👇👇👇
https://t.me/reporter_vacancy
❤ 2
Photo unavailableShow in Telegram
ኢሎን ማስክ ገንዘብ መቆጠብ አያስፈልግም፣ AI ድህነትን ታሪክ ያደርገዋል አሉ
ታዋቂው ቢሊየነር ኢሎን ማስክ የሰው ሰራሽ አስተውሎት እና የሮቦቲክስ ቴክኖሎጂ እድገት ወደፊት ድህነትን ሙሉ በሙሉ እንደሚያጠፋና ሰዎች ለወደፊት ህይወታቸው የሚያደርጉትን የገንዘብ ቁጠባ አስፈላጊነት እንደሚያስቀረው ገለጹ።
ማስክ በቅርቡ በኤክስ (X) ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት፣ ወደፊት "ሁለንተናዊ ከፍተኛ ገቢ" የሚባል ስርዓት እንደሚመጣ ተንብየዋል። ይህም ማለት በቴክኖሎጂ አማካኝነት የሚመነጨው ሀብትና ምርት ለሰው ልጆች ሁሉ በበቂ ሁኔታ ስለሚተርፍ፣ ባህላዊው የስራ ባህል አስፈላጊነቱ ቀርቶ ስራ በሰዎች ፍላጎት ላይ ብቻ የተመሰረተ ምርጫ ይሆናል ብለዋል።
ይህ አስተያየት የተሰጠው ታዋቂው የኢንቨስትመንት ባለሙያ ሬይ ዳሊዮ ለወጣት አሜሪካውያን አዲስ የቁጠባ አካውንት መከፈት አለበት በሚል ላቀረቡት ሃሳብ ምላሽ ነው።
ማስክ የሬይ ዳሊዮ ሃሳብ በጎ ቢሆንም፣ ቴክኖሎጂው ግን ህብረተሰቡ ስለ ገቢ፣ ስለ ስራ እና ስለ ፋይናንስ ዋስትና ያለውን አመለካከት መሰረታዊ በሆነ መልኩ እንደሚቀይረው አፅንኦት ሰጥተዋል።
በተጨማሪም ማስክ ማሽኖች አብዛኛውን ስራ በሚረከቡበት በዚያ ዘመን፣ የሰው ልጅ የህይወት ትርጉሙን እንዴት ሊያገኝ እንደሚችል ትልቅ ጥያቄ መሆኑን ጠቁመዋል።
ቴክኖሎጂው መሰረታዊ ፍላጎቶችን ከማሟላት ባለፈ ለሁሉም ሰው የተትረፈረፈ ህይወት እንደሚያመጣ ቢገልጹም፣ ተቺዎች ግን ይህ ቴክኖሎጂ የሚያመጣው ሀብት ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ለሁሉም ስለመድረሱ ጥርጣሬያቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።
@seledadotio
@seledadotio
❤ 30🥱 3
Photo unavailableShow in Telegram
የኢትዮጵያዊቷ የቲክቶክ ንግስት ድል በአፍሪካ መድረክ!
ዩቲ ናስ (Yuti Nass) በዩጋንዳ ካምፓላ በተካሄደው Iconic African Awards ላይ በሁለት ታላላቅ ዘርፎች አሸናፊ በመሆን የሀገራችንን ስም በአህጉር አቀፍ ደረጃ አስጠርታለች።
በድል የተረከበቻቸው ዘርፎች፡-
1. Iconic Influencer of the Year: በአፍሪካ ደረጃ የዓመቱ ተጽዕኖ ፈጣሪ።
2. Iconic TikToker of the Year (East Africa): በምስራቅ አፍሪካ የዓመቱ ምርጥ ቲክቶከር።
ዩቲ ሽልማቷን ስትቀበል እንደገለጸችው፣ ይህ ስኬት የኢትዮጵያውያን ሁሉ ኩራት ነው። ቀደም ሲል በህዝብ ድምፅ ቀዳሚ የነበረችው ዩቲ፣ አሁን ሽልማቷን በይፋ በመረከብ ድሏን አድምቃለች።
ከሀገር ውስጥ የቲክቶክ ሽልማት እስከ አህጉራዊው መድረክ ስኬቷን የቀጠለችው ዩቲ ናስ፣ ለሀገራችን የጥበብ ዘርፍ ሌላው ትልቅ ትርፍ ሆናለች።
@Addisinsider_ETH
@Addisinsider_ETH
❤ 47🤪 6
Photo unavailableShow in Telegram
በአፍሪካ ዋንጫ መክፈቻ አሰተናጋጇ ሞሮኮ ኮሞሮስን 2 ለ0 አሸነፈች
ትናንት ምሽት አራት ሰዓት በተካሄደው ጨዋታ ብራሂም ዲያዝ እና ኤል ካቢ ለአትላስ አንበሶቹ ጎሉን አስቆጥረዋል።
የኮሞሮስ ቡድን ግብ ጠባቂ ያኒክ ፓንዶር ፍፁም ቅጣት በማዳን እና ግብ የሚሆኑ ኳሶችን በማዳን ጥሩ ጥረት አድርጓል።
@Addis_News
@Addis_News
🔥 9❤ 6
00:37
Video unavailableShow in Telegram
🌟🌟ታላቅ የበዓል ቅናሽ በካሬ 78,000 ብር
✅እንዲሁም ሙሉ ክፍያ ለሚከፊል በካሬ 54,800
🔷 በ10 % ቅድመ ክፍያ
🔷 50 % የባንክ ብድር የተመቻቸለት
📍Location እንግሊዝ ኢንባሲ አጠገብ ውብ እይታ (Top View) ያላቸው ቤቶች በሽያጭ ላይ እንገኛለን
👉ከባለ 2 መኝታ- ባለ4 መኝታ
✅ ህንፃው ላይ ያሉ ተጨማሪ አገልግሎትች
👉5 ሰፋፊ ሊፍት /elevator
👉የቆሻሻ መጣያ/garbage chute
👉አውቶማቲክ ጀኔረተር/ automatic generator
👉ሰገነት/terrace
👉የመኪና ማቆምያ/car parking
👉 ጂም , እስፖ
👉 የዋና ገንዳ
👉 የልጆች መጫወታ
✨ባለ 2 መኝታ
138 ካሬ
157.3 ካሬ
163.6 ካሬ
✨ባለ 3 መኝታ
152.4 ካሬ
158.1 ካሬ
187.6 ካሬ
211.5 ካሬ
✨ባለ 4 መኝታ
240.7 ካሬ
258.4 ካሬ
📞 ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
0973559591
0919489575
Telegram -@Homef17
7.49 MB
❤ 3
እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን በነገዱ ውስጥ በመላእክት ሁሉ ላይ በብዙ ክብር ሾመው፡፡
ቅዱስ ሚካኤል በዚህ ሁሉ ልዕልና ላይ ትሕትናን ደርቦ የያዘ በጸሎቱ ተማጽኖ በተራዳኢነት አምኖ ለሚለምነው ሁሉ ፈጥኖ በመድረስ ከአጋንንት ሠራዊተ ተንኰል የሚያድን ነው፡፡ ሚካኤል የሥሙ ትርጓሜ በዕብራይስጥ “ማንነው እንደ እግዚአብሔር?” ማለት ነው፡፡
በክርስትና በአይሁድ፣ እንዲሁም በመላዕክት አማላጅነት በሚያምኑ ሃይማኖቶች የመላዕክት ሁሉ አለቃ ተብሎ ይጠራል፡፡ ይህም የከበረ መልአክ ክብር ይገባውና በጌታችን ፊት ስለ ሰው ልጆችና ስለ ፍጥረትም ሁሉ ይለምናል፤ ይማልዳልም፡፡ የቅዱስ ሚካኤል ተአምራቱ ብዙዎች ናቸው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ለቅዱስ ሚካኤል የተሰጠውን ክብርና ባለሟልነት እንዲሁም የሠራቸውን ሥራዎች በስፋት እንመለከታለን፡፡
በኢያሱ 5÷13 እንዲህ ይላል፡፡ “እንዲህም ሆነ ኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ ዓይኑን አንሥቶ ተመለከተ፡፡ እነሆም የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ ነበር፡፡ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህን አለው፡፡ እርሱም አይደለሁም እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁን መጥቻለሁ አለ፡፡ ኢያሱም ወደ ምድር በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደ፡፡ ጌታዬ ለባሪያው የሚነግረው ምንድን ነው አለው፡፡ የእግዚአብሔርም ሠራዊት አለቃም ኢያሱን አንተ የቆምህበት ሥፍራ የተቀደሰ ነውና ጫማህን በፊቱ አውልቅ አለው፡፡ ኢያሱም እንዲሁ አደረገ” ይላል፡፡ ኢያሱ ከኢያሪኮ ጀምሮ ታላላቅ አሕዛብን አጥፍቶ እግዚአብሔር ለአብርሃም፣ ለይስሐቅ፣ ለያዕቆብ የማለላቸውን የተስፋይቱን ምድር ለልጆቻቸው ያወረሳቸው በዚህ የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ ይዞ በተገለጸለት የእስራኤል መሪ በቅዱስ ሚካኤል እገዛ ነው፡፡ መልአኩ በሰው አምሳል ስለተገለጸለት አላወቀውም ነበር፡፡
ከቃሉ እንደምንረዳው ከራሱ ወገን ወይም ከጠላቶቹ ወገን የሆነ አንድ ወታደር መስሎት ነበር፡፡ ያነጋገረውም ያለ ፍርሃት ያለ ጭንቀት ያለድንጋጤ ወታደሮቹን እንደሚያነጋግር ዘና ብሎ ነው፡፡ ሆኖም “ከወገኖችህ ወይም ከጠላቶችህ አይደለሁም እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁን መጥቻለሁ” ሲለው ኢያሱ በፊቱ የቆመው ከሙሴ ሳይለይ እስራኤልን የሚጠብቅ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል መሆኑን ሲረዳ ለመልአኩ ክብር መስጠት ስለሚገባ የአክብሮት ስግደት ሰገደለት፤ “ጌታዬ ለባሪያው የሚነግረው ምንድነው” በማለት በትህትና ጠየቀ፡፡ ጌታዬ ማለቱ የእግዚአብሔርን ክብር ለፍጡር መስጠቱ አይደለም፣ መላእክት የጸጋ ጌቶች ስለሚባሉ እንጂ፡፡ ኢያሱ መልአኩን ጌታዬ ብሎ ከጠራው እኛም ጌታዬ፤ ቅዱስ ሚካኤል ለኔ ለባሪያህ ጸልይልኝ መጥተህ አድነኝ በማለት የአክብሮት የጸጋ ስግደት በመስገድ ብንለምነው፣ ብንታዘዘው ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት አልወጣንም፡፡
መላእክትን ማክበርና መታዘዝ እንደሚገባ እግዚአብሔርም ነግሮናል፡፡ በዘጸ.23÷20-22 “በመንገድህ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ሥፍራ ያገባህ ዘንድ እነሆ እኔ መልአክህን በፊትህ እሰዳለሁ፤ በፊቱ ተጠንቀቁ፤ ቃሉንም አድምጡ፤ ስሜም በእርሱ ስለሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት፤ አንተ ግን ቃሉን ብትሰማ፣ ያልሁህንም ሁሉ ብታደርግ፣ ጠላቶችህን እጣላቸዋለሁ፣ የሚያስጨንቁህንም አስጨንቃቸዋለሁ፣ መልአኬ በፊትህ ይሄዳል” በማለት ለሙሴ ተናግሯል፡፡ ይህ ቃል ለሙሴና ለሕዝቡ ብቻ ተነግሮ ያበቃ ሳይሆን ዛሬም ያለ ወደፊትም የሚቀጥል ነው፡፡
ገዳማውያንም ይህን ቃል ታምነው ሌሊትና ቀን ሚካኤል ሆይ አማልደን ይሉታል፡፡ ከጸሎታቸው በረከት እንድንካፈል ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957
❤ 36
Photo unavailableShow in Telegram
ባንኮች የሰራተኞቻቸውን የትምህርት ማስረጃ ትክክለኝነት እንዲያጣሩ ብሄራዊ ባንክ መመሪያ ሰጠ
በተለያዩ የሰራ መስኮች ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች መኖራቸውን የሚያሳይ ፍንጭ መገኘቱን ተከትሎ፣ ብሎም የዲግሪ ወረቀት ሽያጭ እንደነበረ ከተደረሰበት በኋላ፣ ብሔራዊ ባንክ የሀገሪቱ ባንኮች ውስጥ ያሉ ሰራተኞች የትምሕርት ማስረጃ ላይ ማጣራት እንዲደረግ አዟል።
ምንጭ : ዋዜማ
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍 24❤ 14👏 6🤣 4
Photo unavailableShow in Telegram
" ህወሓት ከተፈናቃዮች ሳይቀር በማስገደድ ወርሀዊ የፓርቲ መዋጮ እየጠየቀ ነው " - ሳልሳይ ወያነ ትግራይ
ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ፓርቲ " በትግራይ በጠበንጃ የሚመራ የፓለቲካ ሀይል ስልጣን ላይ ተቀምጧል " ሲል ክስ አሰማ።
ህወሓት ከተፈናቃዮች ሳይቀር በማስገደድ ወርሀዊ የፓርቲ መዋጮ እየጠየቀ ነው ያለው ፓርቲው በእንዳስላሰ-ሽረ የተፈናቃዮች የማቆያ ማእከል የሆነውን በማስረጃ አቅርቧል።
በማቆያ ማእከሉ የነበሩት የ6 ልጆች አባት ተፈናቃይ በህወሓት የፓርቲ ወርሃዊ ክፍያ እንዲከፈሉ ይጠየቃሉ ይላል ፓርቲው።
አባትየው " እኔ የፓርቲ አባል አይደለሁም ፤ ብሆንም በዚህ ወቅት የመክፈል አቅም የለኝም " በማለት እንደመለሱ ገልጿል።
" የፓርቲ አባል አይደለሁም ወርሃዊ መዋጮ አልከፍልም " ያሉት አባት በህወሓት አባላት በፕላስቲክ የተሰራ ቤታቸው ፈርሶ ከመጠለያ ማእከሉ እንዲባረሩ መደረጋቸው ፓርቲው አሳውቋል።
ፓርቲው በትግራይ ህዝብ ጫንቃ በጠበንጃ የሚያዝ የፓለቲካ ሀይል ተጭኗል ቢልም ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ሳይመለሱ የክልሉ ግዛታዊ አንድነት ሳይረጋገጥ ምርጫ መካሄድ የለበትም ሲል አሳስቧል።
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤ 25😢 12👏 5🤣 2
Photo unavailableShow in Telegram
የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ አገልግሎትን ለመግዛት በርካታ ሀገራት ጥያቄ ማቅረባቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩገሩ
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አገልግሎቱን ለተለያዩ ሀገራት በክፍያ ለማቅረብ ድርድሮች በመደረግ ላይ መሆናቸውን ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ይፋ ባደረጉበት መድረክ ላይ አስታውቀዋል።
🪪 ዛምቢያን ጨምሮ በፍርድ ቤቶች፣ በኢትዮ ቴሌኮም እና በሞሰብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እየተሰጡ ያሉ ግልጋሎቶችን የጎበኙ በርካታ ሀገራት የግዢ ጥያቄ ማቅረባቸውንም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተናገሩት።
ብዙዎቹ የአፍሪካ ሀገራት ከሌሎች የውጭ ሀገራት የሚገዟቸው አገልግሎቶች እየተዘጉባቸው መሆኑን ተከትሎ “የአፍሪካን እንጠቀም የሚል ሐሳብ እየተፈጠረ” መምጣቱንም ገልጸዋል።
የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ አገልግሎት እስካሁን ከ30 ሚሊዮን በላይ ህዝብን መመዝገቡና እስከ ሰኔ ወር ድረስ 90 ሚሊዮን ለማድረስ እየተሠራ መሆኑን በመድረኩ ላይ ተገልጿል ሲል የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ ዘግቧል።
@seledadotio
@seledadotio
❤ 32🤪 20👏 3😢 2🤣 2💯 1
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የግብር ከፋዮችን የባንክ አካውንት የመዘጋት ሥልጣን ገደበ
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ፣ የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ያለምንም የላቀ አመራር ፈቃድ የግብር ከፋዮችን የባንክ ሂሳብ (አካውንት) እንዳይዘጉ የሚከለክል አዲስ መመሪያ ማውጣቱን አስታወቀ። ይህ እርምጃ በዘፈቀደ የሚወሰዱ እርምጃዎችን ለመቀነስና የንግዱን ማህበረሰብ እንቅስቃሴ ለመጠበቅ የታለመ ነው።
የቢሮው ኃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ ከከፍተኛ ግብር ከፋዮች ጋር ባደረጉት የምክክር መድረክ ላይ እንደገለጹት፣ ከዚህ ቀደም በኦዲተሮች የግል ውሳኔ ወይም በጥቃቅን የሂሳብ ስህተቶች ምክንያት አካውንቶች መታገዳቸው በንግዱ ማህበረሰብ ላይ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጉዳት ሲያደርስ ቆይቷል።
@Addis_News
@Addis_News
❤ 17👏 8
Photo unavailableShow in Telegram
🇪🇹💸💸📱 በOnline ስራ በቀን ከ 2ሺ ብር ጀምሮ የሚሰሩበት ድንቅ የስልክ መትግበሪያ (Application)። ዳውንሎድ አርገው ተመዝግበው ከቤትዎ ሆነው ስራ ይጀምሩ።
💥💰በቀላሉ ከታች ባለው ሊንክ አፑን ዳውንሎድ በማድረግ መስራት እና መጠቀም ትችላላችሁ።
✅Download ለማድረግ
👇👇👇👇👇👇👇
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.habeshanjobs.habeshanjobs
❤ 7🤣 5
" በቂ የጸጥታ አካላት በአስቸኳይ ይሰማሩ " - ኢሰመኮ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከኅዳር 28 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በጋምቤላ ክልል ኢታንግ ልዩ ወረዳ፣ በጋምቤላ ወረዳ (አቦል)፣ በጋምቤላ ከተማ እና በዙሪያው ባሉ አካባቢዎች የተፈጠረውን ግጭትና የጸጥታ መደፍረስ ተከትሎ የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችና ሥጋቶችን እየተከታተለ መሆኑን አሳውቋል።
እስካሁን ባሰባሰበው መረጃ በጋምቤላ ከተማ የጋምቤላ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት አዛዥ የነበሩት ዋና ኢንስፔክተር ኡመድ ኡጁሉ መገደልን ተከትሎ በከተማውና በአካባቢው ባሉት ወረዳዎችና ቀበሌዎች ግጭት ተፈጥሮ በተለያዩ አከባቢዎች የተኩስ ልውውጥ ሲካሄድ መቆየቱን ገልጿል።
በዚህም ሳቢያ የሰዎች ሕይወት መጥፋቱንና የአካል ጉዳት መድረሱን፣ የሰዎችን እና የመጓጓዣ አማራጮችን እንቅስቃሴ የሚገድብ የሰዓት እላፊ በክልሉ መንግሥት መጣሉን፤ ባንኮችንና የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን ጨምሮ በርካታ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አገልግሎት ማቋረጣቸውን እንደተገነዘበ አመልክቷል።
በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች የተፈጠረውን ግጭትና የሰላም መደፍረስ በፍጥነት በማስቆም በሰዎች በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደኅንነት፣ ከቦታ ቦታ የመዘዋወር፣ የንብረት፣ የሥራ እንዲሁም ሌሎች ሰብአዊ መብቶች ላይ ተጨማሪ ጥሰቶች እንዳይደርሱ ለመከላከል በቂ የጸጥታ አካላት በአስቸኳይ እንዲሰማሩ እንዲደረግ ኢሰመኮ አሳስቧል።
" በክልሉ በተለያዩ ጊዜያት የሚፈጠሩ ግጭቶችን በዘላቂነት ለማስቆም፣ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ እና ወደፊት ተመሳሳይ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እንዳይከሰቱ ለመከላከል የፌዴራሉ እና የክልሉ መንግሥታት ተገቢ እርምጃዎችን ሊወስዱ ይገባል " ብሏል።
በአካባቢው ተሰሚነት ያላቸው የሀገር ሽማግሌዎችን እንዲሁም የሃይማኖት እና የማኅረሰብ መሪዎችን በማሳተፍ ውይይቶችና ዕርቆች እንዲካሄዱ እንዲሁም ከአጋር ድርጅቶችና ባለድርሻዎች ጋር በትብብር በመሥራት ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ተገቢውን ሕክምና እና ካሳ እንዲያገኙ እንዲሁም እንዲቋቋሙ ማድረግ ይገባል ሲልም ገልጿል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
@Addis_News
@Addis_News
❤ 15🤣 2
የሠራዊት ጌታ የልዑል እግዚአብሔር አገልጋይ መላዕክት” 🙏
የስሙ ትርጓሜ “እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው” ማለት ነው። ድርሳነ ሩፋኤል ላይ ተጽፎ እደምናገኘው 7 ሊቃነ መላዕክት ሲኖሩ አለቃቸው ቅዱስ ሚካኤል ነውከእግዚአብሔር ዙፋን ስር ትዕዛዝ በወጣ ግዜ ኪሩቤል ተቀብለው ለሱራፌል ያስተላልፋሉ፤ ሱራፌልም ለሚካኤልና ለገብርኤል ለሩፋኤልም ያደርሳሉ፡፡ ሚካኤል ለፍጥረቱ በጎም ይሁን ክፉ ትዕዛዙን ይፈጽሙ ዘንድ መላዕክትን ያዛቸዋል፤ ኪሩቤልና ሱራፌል መላዕክቱም ሁሉ አቤቱ የእጅህን ስራ አታጥፋ እያሉ ቀንና ማታ ይለምናሉ። የመላዕክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ከዲያቢሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ እግዚአብሔር ይገስፅህ አለው እንጂ የስድብን ቃል አልተናገረውም ሲባል ሰምተናል፡፡ ሊቀ ነብያት ሙሴ እጅግ ታዛዥና የዋህ ስለነበርና ከነዓንን ለማየት ወደ ናባው ተራራ ሲወጣ 2 መላዕክት በአረጋውያን ተመስለው መቃብር ሲቆፍሩ ቢያይ ላግዛቹ ብሎ መቆፈሪያውን ተቀበላቸው፡፡
በመጨረሻ “ሰውየው በአንተ ልክ ነውና እስቲ ገብተህ ለካልን” አሉት፡፡ እሱም በየዋህነቱ ጉድጓዱ ውስጥ ገብቶ እንደተኛ እንደ እንቅልፍ አሸልቦት በዚያው ዐረፈ፤ መላዕክቱም ቀበሩት። እስራኤላዊያን ሙሴን እጅግ ስለሚወዱት የሙሴን መቃብር እንደ ጣዖት እንዳያመልኩት እግዚአብሔር የሙሴን መቃብር ሰወረው፤ ነገር ግን ጠላት ዲያቢሎስ ሊያሳያቸው በመነሳቱ ቅዱስ ሚካኤል ተቃወመው፡፡ በመጨረሻም ቅዱስ ሚካኤል ዲያቢሎስን እግዚአብሔር ይገስጽህ ብሎ ከእርሱም ሰወረበት። በሐዋርያው ይሁዳ መልዕክት ቁጥር 8 የሚገኘው ቃል የቅዱስ ሚካኤልን ትዕግስት ያሳያል፡፡ ዳግመኛም አይሁድ ጌታን ሲሰቅሉት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በቁጣ ሰይፉን አወጣ፤ ቅዱስ ሚካኤል ግን በአይሁድ ስራ አዝኖ፣ ፈጣሪን ፍጡራን ሲሰቀሉት የትዕግስቱንና የፍቅሩን ብዛት እያየ በአርምሞና በትዕግስት አያቸው ይላል ድርሳኑ።
መላዕክቱ በክንፋቸው የእግዚአብሔር ስም ስለተፃፈበት ህዝቡን ይጠብቃሉ፤ የመላዕክቱን ስም የመጨረሻውን ፊደል ስናይ ኤል ብሎ ይጨርሳል፡፡ ሚካ-ኤል ገብር-ኤል ኡራ-ኤል፡፡ ይህም “ስሜ በሱ ላይ ነውና” እንደሚል የእግዚአብሔር የምህረት ስም ስለሆነና በክንፎቻቸው ስለተፃፉ መላዕክቱ ይጠብቁናል። “በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለአንተ ያዛቸዋል፤ እግርህም በድንጋይ እንዳይሰናከል በእጆቻቸው ያነሱሃል” ተብሎም በመዝሙር 90÷11 ተጽፋልና አህዛብን ጭምር ያለጊዜያቸው እንዳይሞቱ መላዕክት ይጠብቋቸዋል!!! ቅዱስ ሚካኤል ሰኔ 12 ቀን ዲያቢሎስን ጥሎ በምትኩ ሊቀ መላዕክት ሆኖ የተሾመበትና አፎምያንም የረዳበት ቀን ስለሆነ በታላቅ ሥርዓት ይከበራል። ህዳር 12 ሕዝበ እስራኤልን በክንፎቹ ጥላ ከበረሃው ፀሐይ ከልሎ ከግብጽ ምድር እየመራና እየጠበቀ ከንዓን ያገባቸው እለት ነው።
በትንቢተ ዳንኤል 10÷13 እና 10÷21 ደግሞ የስሙ ትርጉም እግዚአብሔር ዳኛዬ ነው የተባለው ነብዩ ቅዱስ ዳንኤልም ስለ ቅዱስ ሚካኤል እንዲህ ሲናገር ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ፣ በተዘጋ ጉድጓድ ሲያጽናናው ደግሞ “ከሚካኤል በቀር የሚያጽናናኝ የለም” አለ፡፡ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙር 33÷7 “የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸውማል” ይለናል፡፡ በዓለም ፍፃሜም ስለህዝቡ የሚቆመው ሚካኤል ይነሳል። በማለትረ በምዕራፍ 12÷1 ጽፎልናል፡፡ በራዕይ 8÷3 “የቅዱሳኑ ፀሎት ከዕጣኑ ጢስ ጋር ከመልአኩ እጅ ወደ እግዚአብሔር ፊት ወጣ” ተብሎ እንደተጻፈውም መላዕክት የቅዱሳኑን ጸሎት ወደ እግዚአብሔር ያሳርጋሉ፡፡
ገዳማውያንም የእግዚአብሔርን ቸርነት የመላእክቱን አማላጅነት አምነው ዘወትር በጸሎት ይተጋሉ። ገዳማቸውን እየረዳን በዓታቸውን እያጠናን የበረከታቸው ተካፋይ እንሁን፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957
❤ 38👍 3
Photo unavailableShow in Telegram
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ማሳሰቢያ!
በጋምቤላ ከተማ እና በዙሪያው ባሉ አካባቢዎች ተጨማሪ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንዳይፈፀሙ ለመከላከል “በቂ የጸጥታ አካላት ሊሰማሩ ይገባል“ ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሳሰበ።
ኢሰመኮ ዛሬ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ ከኅዳር 28 ቀን ጀምሮ በጋምቤላ ክልል ኢታንግ ልዩ ወረዳ፣ በጋምቤላ ወረዳ (አቦል)፣ በጋምቤላ ከተማ እና በዙሪያው ባሉ አካባቢዎች የተፈጠሩ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችና ሥጋቶችን እየተከታተለ መሆኑን አስታውቋል።
በጋምቤላ ከተማ አስተዳደር የጋምቤላ ከተማ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አዛዥ የነበሩት ዋና ኢንስፔክተር ኡመድ ኡጁሉ መገደልን ተከትሎ በከተማውና በአካባቢው ባሉት ወረዳዎችና ቀበሌዎች ግጭት መፈጠሩን የገለፀው ኢሰመኮ በተለያዩ አከባቢዎች የተኩስ ልውውጥ እንደነበር ገልጿል።
ከዚህም በተጨማሪ ኢሰመኮ በአሀዝ ሳይጠቅስ የሰዎች ሕይወት መጥፋቱንና የአካል ጉዳት መድረሱን አስታውቋል።
የሰዎችን እና የመጓጓዣ አማራጮችን እንቅስቃሴ የሚገድብ የሰዓት እላፊ በክልሉ መንግሥት መጣሉን የገለፀው ኢሰመኮ ባንኮችንና የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን ጨምሮ በርካታ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አገልግሎት ማቋረጣቸውን ይፋ አድርጓል።
“የፌዴራሉ እና የክልሉ መንግሥታት ተገቢ እርምጃዎችን ሊወስዱ ይገባል“ ያለው ኢሰመኮ፤ “በግጭቶችና ጥቃቶች ላይ ተሳታፊ የሆኑ ቡድኖች እና ግለሰቦች ላይ ተገቢ የወንጀል ምርመራ እና ተጠያቂነትን የማረጋገጥ ጥረቶች የበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥል“ ሲልም አሳስቧል።
@Addisinsider_ETH
@Addisinsider_ETH
❤ 11🤪 2
