es
Feedback
አዲስ ነገር መረጃ

አዲስ ነገር መረጃ

Ir al canal en Telegram

#አዲስ_ነገር_መረጃ #መረጃዎች_በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ Addis Ababa , Ethiopia Buy Ads : https://telega.io/?r=UbutLo2z #ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇 @Addisnegermereja_bot

Mostrar más
2025 año en númerossnowflakes fon
card fon
103 231
Suscriptores
-9224 horas
-3717 días
+21730 días
Archivo de publicaciones
Photo unavailableShow in Telegram
" ህወሓት ከተፈናቃዮች ሳይቀር በማስገደድ ወርሀዊ የፓርቲ መዋጮ እየጠየቀ ነው " - ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ፓርቲ  " በትግራይ በጠበንጃ የሚመራ የፓለቲካ ሀይል ስልጣን ላይ ተቀምጧል " ሲል ክስ አሰማ። ህወሓት ከተፈናቃዮች ሳይቀር በማስገደድ ወርሀዊ የፓርቲ መዋጮ እየጠየቀ ነው ያለው ፓርቲው በእንዳስላሰ-ሽረ የተፈናቃዮች የማቆያ ማእከል የሆነውን በማስረጃ አቅርቧል። በማቆያ ማእከሉ የነበሩት የ6 ልጆች አባት ተፈናቃይ በህወሓት የፓርቲ  ወርሃዊ ክፍያ እንዲከፈሉ ይጠየቃሉ ይላል ፓርቲው። አባትየው " እኔ የፓርቲ አባል አይደለሁም ፤ ብሆንም በዚህ ወቅት የመክፈል አቅም የለኝም " በማለት እንደመለሱ ገልጿል። " የፓርቲ አባል አይደለሁም ወርሃዊ መዋጮ አልከፍልም " ያሉት አባት በህወሓት አባላት በፕላስቲክ የተሰራ ቤታቸው ፈርሶ ከመጠለያ ማእከሉ እንዲባረሩ መደረጋቸው ፓርቲው አሳውቋል። ፓርቲው በትግራይ ህዝብ ጫንቃ በጠበንጃ የሚያዝ የፓለቲካ ሀይል ተጭኗል ቢልም ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ሳይመለሱ የክልሉ ግዛታዊ አንድነት ሳይረጋገጥ ምርጫ መካሄድ የለበትም ሲል አሳስቧል። @Addis_Reporter @Addis_Reporter
Mostrar todo...
25😢 12👏 5🤣 2
Photo unavailableShow in Telegram
የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ አገልግሎትን ለመግዛት በርካታ ሀገራት ጥያቄ ማቅረባቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩገሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አገልግሎቱን ለተለያዩ ሀገራት በክፍያ ለማቅረብ ድርድሮች በመደረግ ላይ መሆናቸውን ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ይፋ ባደረጉበት መድረክ ላይ አስታውቀዋል። 🪪 ዛምቢያን ጨምሮ በፍርድ ቤቶች፣ በኢትዮ ቴሌኮም እና በሞሰብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እየተሰጡ ያሉ ግልጋሎቶችን የጎበኙ በርካታ ሀገራት የግዢ ጥያቄ ማቅረባቸውንም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተናገሩት። ብዙዎቹ የአፍሪካ ሀገራት ከሌሎች የውጭ ሀገራት የሚገዟቸው አገልግሎቶች እየተዘጉባቸው መሆኑን ተከትሎ “የአፍሪካን እንጠቀም የሚል ሐሳብ እየተፈጠረ” መምጣቱንም ገልጸዋል። የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ አገልግሎት እስካሁን ከ30 ሚሊዮን በላይ ህዝብን መመዝገቡና እስከ ሰኔ ወር ድረስ 90 ሚሊዮን ለማድረስ እየተሠራ መሆኑን በመድረኩ ላይ ተገልጿል ሲል የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ ዘግቧል። @seledadotio @seledadotio
Mostrar todo...
32🤪 20👏 3😢 2🤣 2💯 1
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የግብር ከፋዮችን የባንክ አካውንት የመዘጋት ሥልጣን ገደበ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ፣ የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ያለምንም የላቀ አመራር ፈቃድ የግብር ከፋዮችን የባንክ ሂሳብ (አካውንት) እንዳይዘጉ የሚከለክል አዲስ መመሪያ ማውጣቱን አስታወቀ። ይህ እርምጃ በዘፈቀደ የሚወሰዱ እርምጃዎችን ለመቀነስና የንግዱን ማህበረሰብ እንቅስቃሴ ለመጠበቅ የታለመ ነው። የቢሮው ኃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ ከከፍተኛ ግብር ከፋዮች ጋር ባደረጉት የምክክር መድረክ ላይ እንደገለጹት፣ ከዚህ ቀደም በኦዲተሮች የግል ውሳኔ ወይም በጥቃቅን የሂሳብ ስህተቶች ምክንያት አካውንቶች መታገዳቸው በንግዱ ማህበረሰብ ላይ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጉዳት ሲያደርስ ቆይቷል። @Addis_News @Addis_News
Mostrar todo...
17👏 8
Photo unavailableShow in Telegram
🇪🇹💸💸📱 በOnline ስራ በቀን ከ 2ሺ ብር ጀምሮ የሚሰሩበት ድንቅ የስልክ መትግበሪያ (Application)። ዳውንሎድ አርገው ተመዝግበው ከቤትዎ ሆነው ስራ ይጀምሩ። 💥💰በቀላሉ ከታች ባለው ሊንክ አፑን ዳውንሎድ በማድረግ መስራት እና መጠቀም ትችላላችሁ። ✅Download ለማድረግ 👇👇👇👇👇👇👇 https://play.google.com/store/apps/details?id=com.habeshanjobs.habeshanjobs
Mostrar todo...
7🤣 5
" በቂ የጸጥታ አካላት በአስቸኳይ ይሰማሩ " - ኢሰመኮ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከኅዳር 28 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በጋምቤላ ክልል ኢታንግ ልዩ ወረዳ፣ በጋምቤላ ወረዳ (አቦል)፣ በጋምቤላ ከተማ እና በዙሪያው ባሉ አካባቢዎች የተፈጠረውን ግጭትና የጸጥታ መደፍረስ ተከትሎ የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችና ሥጋቶችን እየተከታተለ መሆኑን አሳውቋል። እስካሁን ባሰባሰበው መረጃ በጋምቤላ ከተማ የጋምቤላ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት አዛዥ የነበሩት ዋና ኢንስፔክተር ኡመድ ኡጁሉ መገደልን ተከትሎ በከተማውና በአካባቢው ባሉት ወረዳዎችና ቀበሌዎች ግጭት ተፈጥሮ በተለያዩ አከባቢዎች የተኩስ ልውውጥ ሲካሄድ መቆየቱን ገልጿል። በዚህም ሳቢያ የሰዎች ሕይወት መጥፋቱንና የአካል ጉዳት መድረሱን፣ የሰዎችን እና የመጓጓዣ አማራጮችን እንቅስቃሴ የሚገድብ የሰዓት እላፊ በክልሉ መንግሥት መጣሉን፤ ባንኮችንና የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን ጨምሮ በርካታ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አገልግሎት ማቋረጣቸውን እንደተገነዘበ አመልክቷል። በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች የተፈጠረውን ግጭትና የሰላም መደፍረስ በፍጥነት በማስቆም በሰዎች በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደኅንነት፣ ከቦታ ቦታ የመዘዋወር፣ የንብረት፣ የሥራ እንዲሁም ሌሎች ሰብአዊ መብቶች ላይ ተጨማሪ ጥሰቶች እንዳይደርሱ ለመከላከል በቂ የጸጥታ አካላት በአስቸኳይ እንዲሰማሩ እንዲደረግ ኢሰመኮ አሳስቧል። " በክልሉ በተለያዩ ጊዜያት የሚፈጠሩ ግጭቶችን በዘላቂነት ለማስቆም፣ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ እና ወደፊት ተመሳሳይ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እንዳይከሰቱ ለመከላከል የፌዴራሉ እና የክልሉ መንግሥታት ተገቢ እርምጃዎችን ሊወስዱ ይገባል " ብሏል። በአካባቢው ተሰሚነት ያላቸው የሀገር ሽማግሌዎችን እንዲሁም የሃይማኖት እና የማኅረሰብ መሪዎችን በማሳተፍ ውይይቶችና ዕርቆች እንዲካሄዱ እንዲሁም ከአጋር ድርጅቶችና ባለድርሻዎች ጋር በትብብር በመሥራት ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ተገቢውን ሕክምና እና ካሳ እንዲያገኙ እንዲሁም እንዲቋቋሙ ማድረግ ይገባል ሲልም ገልጿል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ @Addis_News @Addis_News
Mostrar todo...
15🤣 2
Photo unavailableShow in Telegram
4
የሠራዊት ጌታ የልዑል እግዚአብሔር አገልጋይ መላዕክት” 🙏 የስሙ ትርጓሜ “እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው” ማለት ነው። ድርሳነ ሩፋኤል ላይ ተጽፎ እደምናገኘው 7 ሊቃነ መላዕክት ሲኖሩ አለቃቸው ቅዱስ ሚካኤል ነውከእግዚአብሔር ዙፋን ስር ትዕዛዝ በወጣ ግዜ ኪሩቤል ተቀብለው ለሱራፌል ያስተላልፋሉ፤ ሱራፌልም ለሚካኤልና ለገብርኤል ለሩፋኤልም ያደርሳሉ፡፡ ሚካኤል ለፍጥረቱ በጎም ይሁን ክፉ ትዕዛዙን ይፈጽሙ ዘንድ መላዕክትን ያዛቸዋል፤ ኪሩቤልና ሱራፌል መላዕክቱም ሁሉ አቤቱ የእጅህን ስራ አታጥፋ እያሉ ቀንና ማታ ይለምናሉ። የመላዕክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ከዲያቢሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ እግዚአብሔር ይገስፅህ አለው እንጂ የስድብን ቃል አልተናገረውም ሲባል ሰምተናል፡፡ ሊቀ ነብያት ሙሴ እጅግ ታዛዥና የዋህ ስለነበርና ከነዓንን ለማየት ወደ ናባው ተራራ ሲወጣ 2 መላዕክት በአረጋውያን ተመስለው መቃብር ሲቆፍሩ ቢያይ ላግዛቹ ብሎ መቆፈሪያውን ተቀበላቸው፡፡ በመጨረሻ “ሰውየው በአንተ ልክ ነውና እስቲ ገብተህ ለካልን” አሉት፡፡ እሱም በየዋህነቱ ጉድጓዱ ውስጥ ገብቶ እንደተኛ እንደ እንቅልፍ አሸልቦት በዚያው ዐረፈ፤ መላዕክቱም ቀበሩት። እስራኤላዊያን ሙሴን እጅግ ስለሚወዱት የሙሴን መቃብር እንደ ጣዖት እንዳያመልኩት እግዚአብሔር የሙሴን መቃብር ሰወረው፤ ነገር ግን ጠላት ዲያቢሎስ ሊያሳያቸው በመነሳቱ ቅዱስ ሚካኤል ተቃወመው፡፡ በመጨረሻም ቅዱስ ሚካኤል ዲያቢሎስን እግዚአብሔር ይገስጽህ ብሎ ከእርሱም ሰወረበት። በሐዋርያው ይሁዳ መልዕክት ቁጥር 8 የሚገኘው ቃል የቅዱስ ሚካኤልን ትዕግስት ያሳያል፡፡ ዳግመኛም አይሁድ ጌታን ሲሰቅሉት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በቁጣ ሰይፉን አወጣ፤ ቅዱስ ሚካኤል ግን በአይሁድ ስራ አዝኖ፣ ፈጣሪን ፍጡራን ሲሰቀሉት የትዕግስቱንና የፍቅሩን ብዛት እያየ በአርምሞና በትዕግስት አያቸው ይላል ድርሳኑ። መላዕክቱ በክንፋቸው የእግዚአብሔር ስም ስለተፃፈበት ህዝቡን ይጠብቃሉ፤ የመላዕክቱን ስም የመጨረሻውን ፊደል ስናይ ኤል ብሎ ይጨርሳል፡፡ ሚካ-ኤል ገብር-ኤል ኡራ-ኤል፡፡ ይህም “ስሜ በሱ ላይ ነውና” እንደሚል የእግዚአብሔር የምህረት ስም ስለሆነና በክንፎቻቸው ስለተፃፉ መላዕክቱ ይጠብቁናል። “በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለአንተ ያዛቸዋል፤ እግርህም በድንጋይ እንዳይሰናከል በእጆቻቸው ያነሱሃል” ተብሎም በመዝሙር 90÷11 ተጽፋልና አህዛብን ጭምር ያለጊዜያቸው እንዳይሞቱ መላዕክት ይጠብቋቸዋል!!! ቅዱስ ሚካኤል ሰኔ 12 ቀን ዲያቢሎስን ጥሎ በምትኩ ሊቀ መላዕክት ሆኖ የተሾመበትና አፎምያንም የረዳበት ቀን ስለሆነ በታላቅ ሥርዓት ይከበራል። ህዳር 12 ሕዝበ እስራኤልን በክንፎቹ ጥላ ከበረሃው ፀሐይ ከልሎ ከግብጽ ምድር እየመራና እየጠበቀ ከንዓን ያገባቸው እለት ነው። በትንቢተ ዳንኤል 10÷13 እና 10÷21 ደግሞ የስሙ ትርጉም እግዚአብሔር ዳኛዬ ነው የተባለው ነብዩ ቅዱስ ዳንኤልም ስለ ቅዱስ ሚካኤል እንዲህ ሲናገር ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ፣ በተዘጋ ጉድጓድ ሲያጽናናው ደግሞ “ከሚካኤል በቀር የሚያጽናናኝ የለም” አለ፡፡ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙር 33÷7 “የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸውማል” ይለናል፡፡ በዓለም ፍፃሜም ስለህዝቡ የሚቆመው ሚካኤል ይነሳል። በማለትረ በምዕራፍ 12÷1 ጽፎልናል፡፡ በራዕይ 8÷3 “የቅዱሳኑ ፀሎት ከዕጣኑ ጢስ ጋር ከመልአኩ እጅ ወደ እግዚአብሔር ፊት ወጣ” ተብሎ እንደተጻፈውም መላዕክት የቅዱሳኑን ጸሎት ወደ እግዚአብሔር ያሳርጋሉ፡፡ ገዳማውያንም የእግዚአብሔርን ቸርነት የመላእክቱን አማላጅነት አምነው ዘወትር በጸሎት ይተጋሉ። ገዳማቸውን እየረዳን በዓታቸውን እያጠናን የበረከታቸው ተካፋይ እንሁን፡፡ ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ 1000442598391 ወይም አቢሲኒያ ባንክ 141029444 ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957
Mostrar todo...
36👍 3
Photo unavailableShow in Telegram
28🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ማሳሰቢያ! በጋምቤላ ከተማ እና በዙሪያው ባሉ አካባቢዎች ተጨማሪ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንዳይፈፀሙ ለመከላከል “በቂ የጸጥታ አካላት ሊሰማሩ ይገባል“ ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሳሰበ። ኢሰመኮ ዛሬ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ ከኅዳር 28 ቀን ጀምሮ በጋምቤላ ክልል ኢታንግ ልዩ ወረዳ፣ በጋምቤላ ወረዳ (አቦል)፣ በጋምቤላ ከተማ እና በዙሪያው ባሉ አካባቢዎች የተፈጠሩ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችና ሥጋቶችን እየተከታተለ መሆኑን አስታውቋል። በጋምቤላ ከተማ አስተዳደር የጋምቤላ ከተማ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አዛዥ የነበሩት ዋና ኢንስፔክተር ኡመድ ኡጁሉ መገደልን ተከትሎ በከተማውና በአካባቢው ባሉት ወረዳዎችና ቀበሌዎች ግጭት መፈጠሩን የገለፀው ኢሰመኮ በተለያዩ አከባቢዎች የተኩስ ልውውጥ እንደነበር ገልጿል። ከዚህም በተጨማሪ ኢሰመኮ በአሀዝ ሳይጠቅስ የሰዎች ሕይወት መጥፋቱንና የአካል ጉዳት መድረሱን አስታውቋል። የሰዎችን እና የመጓጓዣ አማራጮችን እንቅስቃሴ የሚገድብ የሰዓት እላፊ በክልሉ መንግሥት መጣሉን የገለፀው ኢሰመኮ ባንኮችንና የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን ጨምሮ በርካታ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አገልግሎት ማቋረጣቸውን ይፋ አድርጓል። “የፌዴራሉ እና የክልሉ መንግሥታት ተገቢ እርምጃዎችን ሊወስዱ ይገባል“ ያለው ኢሰመኮ፤ “በግጭቶችና ጥቃቶች ላይ ተሳታፊ የሆኑ ቡድኖች እና ግለሰቦች ላይ ተገቢ የወንጀል ምርመራ እና ተጠያቂነትን የማረጋገጥ ጥረቶች የበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥል“ ሲልም አሳስቧል። @Addisinsider_ETH @Addisinsider_ETH
Mostrar todo...
11🤪 2
Photo unavailableShow in Telegram
የሰው ልጅን አስተሳሰብ ወደ ተግባር የሚቀይረው ረቂቅ ቺፕ ይፋ ተደረገ በሳይንሱ ዓለም ከፍተኛ መነቃቃትን የፈጠረውና ቢአይኤስሲ (BISC) ተብሎ የሚጠራው አዲስ የአእምሮ ውስጥ ቺፕ በታህሳስ 2025 በይፋ ለዓለም ቀርቧል። ይህ ቴክኖሎጂ ከሰው ፀጉር በበለጠ የሚቀጥን ሲሆን ያለምንም የሚታይ ገመድ ወይም የውጭ መሣሪያ የሰውን ልጅ የውስጥ ሃሳብ በቀጥታ ወደ ተግባር የመተርጎም ልዩ አቅም አለው። በኔቸር ኤሌክትሮኒክስ (Nature Electronics) ላይ የወጣው ይሄው ጥናት እንደሚያመለክተው መሣሪያው በአእምሮ እና በኮምፒውተር መካከል ያለውን ግንኙነት እጅግ ፈጣንና ስውር በሆነ መንገድ ያከናውናል። ቺፑ በአእምሮ ውስጥ የሚፈጠሩ የኤሌክትሪክ ምልክቶችን በሰው ሰራሽ አስተውሎት በመታገዝ ወደ እንቅስቃሴ የሚቀይር ሲሆን ይህም በተለይ አካል ጉዳተኞች በሃሳባቸው ብቻ የተለያዩ መሣሪያዎችን እንዲቆጣጠሩ ያስችላቸዋል። ከቀድሞዎቹ ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎች በተለየ መልኩ ይህ ቺፕ በራስ ቅል ላይ ምንም ዓይነት ትልቅ ቀዳዳ ወይም ግዙፍ ሃርድዌር የማይጠይቅ በመሆኑ የቴክኖሎጂውን ስውርነትና ምቾት ወደ ላቀ ደረጃ አሳድጎታል። መረጃዎችን በከፍተኛ ፍጥነትና በገመድ አልባ ዘዴ ወደ ውጭ የሚያስተላልፈው ይህ ግኝት በሰው ልጅ እና በዲጂታል ዓለም መካከል ያለውን ልዩነት የሚያጠብ ታላቅ የፈጠራ ውጤት ተብሎ ተመዝግቧል። @seledadotio @seledadotio
Mostrar todo...
31😢 16🤔 5🤣 5
Photo unavailableShow in Telegram
መረጃ‼️ በቲክቶክ የፈጠራ ስራዎች እና በባህል ጥበቃ ዙሪያ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሰጠ ማብራሪያ‼️ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቲክቶክ ማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ዙሪያ በሰጡት አዲስ ማብራሪያ፣ ወጣቶች ቴክኖሎጂውን ለፈጠራ ስራዎችና ለኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እንዲያውሉት መንግስት ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታወቁ። ይሁን እንጂ፣ ይህ ነፃነት * የሀገሪቱን ባህል፣ * ወግና * እሴቶች በጣሰ መልኩ መሆን እንደሌለበት በጥብቅ አሳስበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው፤ ወጣቶች ከውጭው ዓለም የሚመጡ ተጽዕኖዎችን ሲቀበሉ "ጠቃሚውን ብቻ" በመለየት መሆን እንዳለበት ጠቁመው፣ ከኢትዮጵያ ስርአት ውጪ የሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ "መመከርና መገሰጽ" አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። ቀጣዩ ትውልድ ሊታሰብበት ይገባል፤ መልካሙን ብቻ ማሳየት የሁላችንም ኃላፊነት ነው" ሲሉም ተናግረዋል። @sheger_press @sheger_press
Mostrar todo...
61🤪 26🔥 8
Photo unavailableShow in Telegram
ግብፅ ከኢትዮጵያ ጋር 'ምንም ችግር' የለባትም፤ የምትፈልገው በሕዳሴ ግድብ ላይ ሕጋዊ አስገዳጅ ስምምነት ብቻ ነው – አብደል ፈታህ ኤል-ሲሲ የግብፁ ፕሬዝዳንት ይህንን የተናገሩት፣ በሁለተኛው የሩሲያ-አፍሪካ አጋርነት ፎረም የሚኒስትሮች ጉባኤ ከተሳተፉ የአፍሪካ ልዑካን ጋር ባደረጉት ውይይት ነው። ከኢትዮጵያ ጋር ልዩነቶች ቢኖሩም "ግብፅ በጭራሽ ዛቻ ሰንዝራ አታውቅም" ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ አለመግባባቶች በውይይት እና በፖለቲካዊ መፍትሄዎች መፈታት አለባቸው ብለዋል ሲል የሀገሪቱ ሚዲያ ዘግቧል። እሳቸው ይህን ይበሉ እንጂ፣ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሕዳር ወር መጨረሻ ባወጣው መግለጫ፣ ግብጽ የ21ኛውን ክፍለ ዘመን እውነታ ያልተረዱ ማስፈራሪያዎችና ዛቻዎች ኢትዮጵያ ላይ እያቀረበች ነው ሲል ከሷል፡፡ ሚኒስቴሩ "... ባለሥልጣናቱ (የግብጽ) ትኩረቱን በኢትዮጵያ ላይ ብቻ ያልተገደበ የአፍሪካ ቀንድን የማተራመስ ዘመቻ እያካሄዱ ነው.... ኢትዮጵያን በፍጹም ሊያስፈራራት ያልቻለውን ይህን ያረጀ አሠራር የምንሰናበትበት ጊዜ አሁን ነው" ብሏል፡፡ @seledadotio @seledadotio
Mostrar todo...
26🤣 12👍 2😍 2
Photo unavailableShow in Telegram
ዛሬ እና ነገ የሚደረገው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የደሴ በረራ ተቋረጠ‼️ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሁኑ ሰዓት በደሴ እና አካባቢዋ ባለው ለበረራ አመቺ ያልሆነ የአየር ጠባይ ምክንያት፤ ዛሬ እሑድ ታኅሣሥ 12/2018 እና ነገ ሰኞ ወደ ከተማዋ የሚያደርገውን በረራ ለማቋረጥ መገደዱን ለመንገደኞች አሳውቋል። አየር መንገዱ ከሚቲዎሮሎጂ በሚደርሰው መረጃ መሠረት የአየር ጠባዩ እንደተስተካከለ በረራዎቹ ወደመደበኛ አገልግሎታቸው የሚመለሱበት ጊዜ ይገለጻል ብሏል። @seledadotio @seledadotio
Mostrar todo...
15🤔 7👍 6
ቻይና የወሊድ የህክምና ወጪዎችን ሙሉ በሙሉ በነጻ ልታደርግ መሆኑ ተገለጸ የቻይና መንግስት በሀገሪቱ በከፍተኛ ሁኔታ እየቀነሰ የመጣውን የህዝብ ቁጥር ለመታደግ እና የውልደት ምጣኔን ለማሳደግ በማለም ከመጪው 2026 የፈረንጆቹ ዓመት ጀምሮ ማንኛውም ከወሊድ ጋር የተያያዘ የህክምና ወጪ በመንግስት እንዲሸፈን መወሰኑን አስታውቋል። ይህ አዲስ መመሪያ ከቅድመ ወሊድ ምርመራ ጀምሮ እስከ ወሊድ ድረስ ያሉ ማናቸውንም የህክምና አገልግሎቶች ያካተተ ሲሆን ወላጆች ከኪሳቸው ምንም አይነት ክፍያ እንዳይከፍሉ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል። ቻይና በአሁኑ ወቅት የ1.416 ቢሊዮን ህዝብ ባለቤት ብትሆንም በህዝብ ብዛት በህንድ ተበልጣ የዓለማችን ሁለተኛዋ ሀገር ሆና ትገኛለች። የሀገሪቱ የህዝብ ቁጥር ከ2022 ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ማሽቆልቆል የጀመረ ሲሆን ይህ አዝማሚያ እስከ 2025 ድረስ ቀጥሎ ታይቷል። ለዚህ የህዝብ ቁጥር መቀነስ ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው ተብለው የሚጠቀሱት ለበርካታ አስርት ዓመታት ተግባራዊ የነበረው የአንድ ልጅ ብቻ ፖሊሲ፣ የከተማ መስፋፋት እና የልጆች ማሳደጊያ ወጪ በከፍተኛ ሁኔታ መናር ናቸው። መንግስት የወሊድ ወጪን ሙሉ በሙሉ በነጻ ለማድረግ የወሰነውን እርምጃ ተከትሎም ከጃንዋሪ 2026 ጀምሮ በእርግዝና መከላከያ ቁሶች ላይ የ13 በመቶ ታክስ ለመጣል ማቀዱ ተሰምቷል። ቤጂንግ ይህንን ውሳኔ ያስተላለፈችው ወደፊት ሊያጋጥማት የሚችለውን የሰው ኃይል እጥረት ለመከላከል እና የኢኮኖሚ ጥንካሬዋን ለማስቀጠል እንደሆነ የዘርፉ ባለሙያዎች እየገለጹ ይገኛሉ። @seledadotio @seledadotio
Mostrar todo...
31
አለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማህበር (IATA) የወጣው አዲስ መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በተለያዩ አገራት ወደ ውጭ መላክ ሳይቻል የተያዘው የአየር መንገዶች የገንዘብ መጠን አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። በተለይም በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ያለው የገንዘብ መጠን መጨመሩን ሪፖርቱ ጠቁሟል። በተቋሙ መረጃ መሠረት፣ በኢትዮጵያ ወደ ውጭ ሳይላክ የቆየው የገንዘብ መጠን 54 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ደርሷል። ይህም ባለፈው ዓመት ጥቅምት 2024 ላይ ከነበረበት 43 ሚሊዮን ዶላር የ11 ሚሊዮን ዶላር ጭማሪ አሳይቷል። በጎረቤት ሀገር ኤርትራ በኩል የተያዘው የገንዘብ መጠን ደግሞ 78 ሚሊዮን ዶላር የደረሰ ሲሆን፣ ይህም አገሪቱን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ገንዘብ ከያዙ ሀገራት 6ኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል። ኢትዮጵያ በ2024 አጋማሽ ላይ የብርን ዋጋ በገበያ እንዲወሰን ማድረጓን ተከትሎ፣ የተያዘው ገንዘብ ከ149 ሚሊዮን ዶላር ወደ 43 ሚሊዮን ዶላር ዝቅ ብሎ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ላይ አሃዙ በድጋሚ ማደግ መጀመሩ ተመልክቷል። በዓለም ዙሪያ በድምሩ 1.2 ቢሊዮን ዶላር የተከማቸ ሲሆን፣ 89 በመቶው የሚገኘው በሚከተሉት 10 አገራት ውስጥ ነው ። በተለይ በቀዳሚነት አልጄሪያ 307 ሚሊዮን ዶላር ፣ ሞዛምቢክ 91 ሚሊዮን ዶላር ኤርትራ ደግሞ 78 ሚሊዮን ዶላር በስምንተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘዉ ኢትዮጵያ ደግሞ 54 ሚሊዮን ዶላር መድረሱ ተነግሯል። Via Capital Newspaper @Addis_News @Addis_News
Mostrar todo...
12🤪 3
Photo unavailableShow in Telegram
ዛሬ በመላው ዓለም የአጭር ሴቶች ቀን እልል ብሎ እየተከበረ ነው! ይህ ቀን አጭርነታቸውን በኩራት እና በልዩ ውበታቸው የሚያከብሩበት ልዩ አጋጣሚ ነው። ለውብ እና ደማቅ አጫጭር ሴቶች ሁሉ፣እንኳን ለዚህ ልዩ የኩራት እና የደስታ ቀን በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ እንላለን! በአጭርነታችሁ ኩሩ፣ ውበታችሁም ልዩ ነው! የምታቋትን አጭር ሴት " Mention " እያደረጋችሁ እንኳን አደረሳችሁ በሏችሁ መልካም በዓል @seledadotio @seledadotio
Mostrar todo...
🤪 35 26🤣 6💯 1
Photo unavailableShow in Telegram
በአሜሪካ አንዲት ሴት በልጆቿ አስተዳደግ እና በቀለብ ክርክር ምክንያት ሁለቱን የቀድሞ ባሎቿን በአንድ ቀን ገደለች ኪቢቲኤክስ ሰሞኑ እንደዘገበው ​በአሜሪካ ፍሎሪዳ ግዛት የምትኖረው የ54 ዓመቷ ሱዛን አቫሎን  ሁለቱን የቀድሞ ባሎቿን በአንድ ቀን በመግደሏ በቁጥጥር ስር ውላለች። ከሁለቱ የቀድሞ ትዳሮቿ አምስት ልጆች ያሏት አቫሎን፣ ከቀድሞ ባሎቿ ጋር በልጆች አስተዳደግ እና በቀለብ ክፍያ ዙሪያ ክርክር ነበራት ​በዚህም መሰረት፣ አቫሎን ልጆቿን ለሚያሳድገው የቀድሞ ባሏ መክፈል ከነበረባት 4,000 ዶላር ገደማ የቀለብ ዕዳ ውስጥ የተወሰነውን ባለመክፈሏ ምክንያት የመንጃ ፈቃዷ ሊሰረዝ እንደሚችል ስጋት ገብቷት ነበር። ከቀድሞ ባሎቿ ጋር መስማማት ያቃታት አቫሎን፣ በመጀመሪያ ታምፓ ውስጥ የሚኖረውን የቀድሞ ባሏን  በጥይት ተኩሳ ገድላለች። ​በዚያው ዕለት ከሰዓት በኋላ ደግሞ ብሬደንተን  የሚኖረው ሌላኛው የቀድሞ ባሏ ቤት ሄደች። ከምግብ ቤት ምግብ ይዛ በመምጣት በሩን እንዲከፍትላት ጠየቀችው። በሩን ሲከፍትላትም ተኩሳ አቆሰለችው፤ እሱም ሆስፒታል ከገባ በኋላ ህይወቱ አለፈ። ፖሊሶች ስለ ቀድሞ ባሏ ሊያነጋግሯት ሲመጡ "የትኛውን የቀድሞ ባሌን?" ስትል ጠየቀች። ፖሊሶቹ በወቅቱ የሚያውቁት ስለ ብሬደንተኑ ግድያ ብቻ ነበር። አቫሎን ይህን ጥያቄ ካነሳች በኋላ ፖሊሶች በታምፓ የሚገኘውን የሌላኛውን ባሏን አድራሻ ሲፈልጉ እሱም መገደሉን አረጋገጡ። Fidel post @Addis_News @Addis_News
Mostrar todo...
20🤣 7😢 3
01:08
Video unavailableShow in Telegram
👉 ከ8 በላይ ሳይቶችን ገንብቶ ያስረከበው ቴምር ፕሮፐርቲ አሁንም በድጋሜ አዳዲስ ሳይቶችን ለሽያጭ አቅርቧል ። 📍 ሳር ቤት #በ35%ቅናሽ! (በ100% ክፍያ) 👉 ባለ 2 መኝታ = 81ካሬ = 5.7ሚ 👉 ባለ 2 መኝታ = 106ካሬ = 7.9ሚ 👉 ባለ 3 መኝታ = 139ካሬ = 10.3ሚ 👉 ባለ 3 መኝታ = 153ካሬ = 11.4ሚ #በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ) 👉 81ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 9.3ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (1.8ሚሊዮን) 👉 106ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 12.1ሚ                  ቅድመ ክፍያ = 20% (2.4ሚሊዮን) 👉 139ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 15.9ሚ                  ቅድመ ክፍያ = 20% (3.1ሚሊዮን) 📍 አዋሬ #በ35%ቅናሽ! (በ100% ክፍያ) 👉 ባለ 1 መኝታ = 78ካሬ = 5.5ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 117ካሬ = 8.3ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 137ካሬ = 9.7ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 145ካሬ = 10.3ሚሊዮን #በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ) 👉 78ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 8.5ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (1.7ሚሊዮን) 👉 135ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 14.8ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (2.9ሚሊዮን) 👉 157ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 17.2ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (3.4ሚሊዮን) ⩩ ቀሪውን 80%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት። ⩩ 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፤ ከከፈሉት ላይ ከ15 -25% ቅናሽ አዘጋጅተናል። ለበለጠ መረጃ ;- 0940464607 0994003949
Mostrar todo...
25.16 MB
4👏 2
🎯🎯 ያልተኖረ 🎯🎯 አዲስ ፊልም   ታህሳስ 13 ሰኞ በታላቁ ብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ ከ ቀኑ 11:30 ጀምሮ በቀይ ምንጣፍ ስነ-ስርዓት ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ ሚዲያዎች እና የኪነ - ጥበብ ባለሙያዎች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ይመረቃል። ታህሳስ 17፣18፣19 ደግሞ በተመረጡ ሲኒማ ቤቶች በታላቅ ድምቀት ይመረቃል። ፊልሙን ያቀረበው ናዲ መልቲ ሚዲያ በቅርቡ ሌሎችም ትላልቅ ፊልሞችን እንደሚያቀርብ ገልፅዋል #ያልተኖረ
Mostrar todo...
4
1