ar
Feedback
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

الذهاب إلى القناة على Telegram

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች፣ ስንክሳር፣ መዝሙራትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም አስተያየት @Zimaredawitmessanger ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል። ስለሚሰጡን ገንቢ ሃሳብ እናመሰግናለን። YouTube Page - https://bit.ly/2O1Z3d8 Facebook Page - https://www.fb.com/l/6lp1kJRRR

إظهار المزيد
2025 عام في الأرقامsnowflakes fon
card fon
166 278
المشتركون
-2324 ساعات
+187 أيام
-1430 أيام
أرشيف المشاركات
ማስታወቂያ! የ2018 አዳዲስ ዲዛይኖቻችንን ለእናንተ ለውድ ደንበኞቻችን ውብ በሆነ መልኩ ሰርተን በማቅረብ ላይ እንገኛለን። ከፊታችን ለሚመጣው የጥምቀት በዓልም ለእናንተ በጣም በቅናሽ ለማድረስ እየሰራን እንገኛለን፡፡ ዲዛይነሮቻችንም እናንተን ለማስደሰት እየሰሩ ይገኛሉ፡፡  ትዕዛዝ መቀበል ጀምረናል፡፡ ማዘዝ የምትፈልጉ ማህበራት ለእናንተ ልዩ ቅናሽ (Package) አዘጋጅተናል፡፡ ከእናንተ የሚጠበቀው ቀደም ብላቹ ማዘዝ ብቻ ነው፡፡ ክፍለ ሀገር የምትገኙ ደንበኞቻችን እንደ ከዚህ ቀደሙ ትዕዛዝ የሚቀበሉ ሰዎችን ስለመደብን ለአገልግሎት ጥራትና ለተደራሽነት ዝግጁ ሆነን እየሰራን ነው፡፡  KABA Digital Print 0965875219 / 0922501999 Join አድርጉ 👇👇👇 https://t.me/KABAPrint https://t.me/KABAPrint
إظهار الكل...
45😍 4🥰 2
Photo unavailableShow in Telegram
ሁለት ቀን ብቻ ቀረን! የደረስንበት 94,723 ብር የሚያስፈልገን 119,000 ብር የቀረን 24,277 ብር ብቻ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 🏦 1000142059022 ሁላችሁም በቀረችን ቀን በመረባረብ የአቅማችሁን እንድትለግሱ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።
إظهار الكل...
45
እግዚአብሔርን አመስግኑት እግዚአብሔርን አመስግኑት ሥራ ግሩም ድንቅ ነው በሉት እግዚአብሔርን እመስግኑት ስራህ ግሩም ድንቅ ነው በሉት
አዝ
ሠማይን ያለ ምሰሶ ምድርንም ያለ መሰረት ያጸናው እርሱ ነው ሥራህ ድንቅ ነው በሉት
አዝ
የባህርንም ጥልቀት የመጠነ ዳርቻዋን የወሰነ እግዚአብሔርን አመስግኑ ሥራ ግሩም ድንቅ ነው በሉት
አዝ
ማእበል ንፋሱን የሚገስጽ ፍጥረቱ ለስሙ የሚታዘዝ ትጉህ እረኛ ድካም የሌለበት እግዚአብሔርን ሥራህ ድንቅ ነው በሉት
አዝ
ንጹሐ ባህርይ ነው ሁሉን የሚገዛ የነገስታት ንጉስ አልፋና ኦሜጋ ዘለዓለም እርሱ ነው የማይለወጥ እግዚአብሔር ስራህ ድንቅ ነው በሉት
አዝ
ጥበብን የሚሰጥ ጥበበኛ ፍርድ የማያጎድል እውነተኛ ዳኛ እንደ እርሱ ያለ ከቶ አይገኝም እግዚአብሔር ግሩም ነው ለዘልዓለም የአእላፋት ዝማሬ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
إظهار الكل...
audio1766424028464.mp33.92 MB
112🥰 7🕊 2😍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ሁለት ቀን ብቻ ቀረን! የደረስንበት 93,223 ብር የሚያስፈልገን 119,000 ብር ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 🏦 1000142059022 ሁላችሁም በቀረችን ቀን በመረባረብ የአቅማችሁን እንድትለግሱ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።
إظهار الكل...
33
ታኅሣሥ ፲፬ /14/
በዚች ቀን ከፍ ከፍ ካለች ከመኑፍ ከተማ ቅዱስ ስምዖን በሰማዕትነት አረፈ። እርሱም በእስላሞች ዘመን ከመሳፍንቶቻቸው ከአንዱ ጋር ተከራከረና ቅዱስ ስምዖን ረቶ አሳፈረው ያም እስላም ወደ መሳፍንቱ አለቃ ሒዶ ይህ ስምዖን የእስላሞችን ሃይማኖት ያቃልላል ብሎ ወነጀለው ስለዚህም ይዘው በጽኑዕ ሥቃይ አሠቃዩት ከዚያም በኋላ ራሱን በሰይፍ ቆረጡት የሰማዕትነት አክሊልን በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ዳግመኛም በዚችም ቀን ቅዱሳን አባ ብሑርና አረጋዊ ሚናስ በሰማዕትነት አረፉ። በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦  መጽሐፈ ስንክሳር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
إظهار الكل...
111🕊 14
ከሰማዩ ከፍታ ከሰማዩ ከፍታ ከፍ ብላ ጽዮን በሰገነት ላይ ተቀምጣ ድንግል በክብር በግርማ ትኖራለች አጊጣ /2/ አይን ከሞላባቸው ከኪሩቤል ክንፋቸው ከበዛ ከሱራፌል ከሊቃናቱ ሁሉ ትበልጣለች እሳተ መለኮትን በሆዱዋ ስለተሸከመች
አዝ
ከንጉሱ በስተቀኝ ከዙፋኑ ንግስቲቱ ቆማለች በየቀኑ የቃል ኪዳን ቀሚሷን ተጐናጽፋ የምትማልድልን ድንግል ናት የሁላችን ተስፉ
አዝ
በብርሀን ወንበር ላይ ተቀምጣለች ጨረቃን ከእግሯ በታች ተጫምታለች የቅድስናን ውበት ተሸልማ የምታብረቀርቀው እርሷ ናት የልዑል ከተማ
አዝ
ከዕብራውያን ሴቶች ተለይታ ከሔዋን ዘሮች ሁሉ ታየች ጐልታ ሰባቱን መቅረዝ ልጇ ያበራል ስጋዋን ተዋህዶ በፍቅር እኛኑ መስሏል የአእላፋት ዝማሬ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
إظهار الكل...
ከሰማዩ_ከፍታ_ዘማሪ_ገብረዮሐንስ_ገብረጻድቅ_2018_የአእላፋት_ዝማሬ_መዝሙር_በጃን_ያሬድ_ኅ.mp34.79 MB
59🕊 3
إظهار الكل...
1
ሰባቱ መንጦላይት ሰባቱ መንጦላይት ወዴት ተጋረዱ ሰባቱ መብራቶች ወዴት ተሰናዱ ታናሽ ሙሽራ ነሽ የአሥራ አምስት ዓመት በአንቺ ላይ ሲፈጸም እንግዳ ሥርዓት
አዝ
አንዴ እየታጠቀ አንዴም እየፈታ ገብርኤል ሲያበስርሽ በፍጹም ሰላምታ ይኩነኒ ብለሽ ስትቀበይው መለኮት እንዴት ነው የተዋሐደው ይህን ባሰብኩ ቁጥር ልቤ ይመሰጣል ከዚህ በላይ ፍቅርስ እንዴት ይገለጣል   
አዝ
ሁሉን የሚወስን ባንቺ ተወሰነ ከሦስቱ አካል አንዱ ቃልም ሥጋ ሆነ ስፋት እና ጥበት ሰማይ እና ምድር ባንቺ ተገናኙ ገባሪና ግብር ይህን ባሰብኩ ቁጥር ልቤ ይመሰጣል ከዚህ በላይ ፍቅርስ እንዴት ይገለጣል
አዝ
እንዴት ቢመርጥሽ ነው እንዴት ቢያከብርሽ ትናንት እና ዛሬን ያገናኘብሽ ምልዐትና ወሰን ግዝፈትና ርቀት ባንቺ ተዋሐዱ ፈጣሪና ፍጥረት ይህን ባሰብኩ ቁጥር ልቤ ይመሰጣል ከዚህ በላይ ፍቅርስ እንዴት ይገለጣል     
አዝ
ምስጢር ሊመረምር ይወጣል ኀሊና ያልፋል ይሻገራል ከሰማይ ደመና ነገር ግን አይችልም ምንም ቢገሠግሥ ከመሰወሪያው ዘንድ ከልጅሽም ሊደርስ ስለዚህ አቅቶት ደክሞት ይመለሳል መልክዐ ውዳሴሽን በአድናቆት ያደርሳል የአእላፋት ዝማሬ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
إظهار الكل...
ሰባቱ_መንጦላዕት_ዘማሪ_ቀሲስ_ምንዳዬ_ብርሃኑ_2018_የአእላፋት_ዝማሬ_መዝሙር_በጃን_ያሬድ.mp34.91 MB
151🕊 11🥰 8😍 2
የቀረን ሶስት ቀን ብቻ ነው። ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል አገልግሎት ማድረስ ስላለብን ቀድመን ገዝተን መላክ አለብን።
አንድ እህታችን የቀጣይ ወር አስራቷን ከሰው ተበድራ ሰጥታናለች።
ቅዱስ ገብርኤል አብዝቶ ይስጥልን።
إظهار الكل...
71
Photo unavailableShow in Telegram
እግዚአብሔር ይመስገን። 🎉🎉🎉 እንኳን ደስ አላችሁ እስካሁን 90,873 ብር ደርሰናል። ለአንድ የገጠር ቤተ ክርስቲያን የሚሆን የሶስት ጽንሐሕ እና የአንድ መጎናጸፊያ መግዣ ብር ሰብስበን ጨርሰናል። 🕯️የአንድ ጽንሐሕ ዋጋ = 13,000 ብር ⛪️የአንድ መጎናጸፊያ ዋጋ = 40,000 ለሁለተኛ መጎናጸፊያ መግዣ የሚሆን ለመሙላት 28,127 ብር ብቻ ይቀረናል። እያንዳንዷ ብር እዚህ ጋር ትልቅ ዋጋ አላት። አስራታችሁን ያላወጣችሁ፣ ለቁርስ ለምሳ ታጠፉት የነበረውን ገንዘብ ለገጠር አብያተ ክርስቲያናት አገልግሎት የሚውል መጎናጸፊያ እና ጽንሐሕ ገዝተን እንስጥ። እስከ ታኅሣሥ 14 ቀን ድረስ ቃል መግባት ትችላላችሁ። መባችሁን እግዚአብሔር ይቀበላችሁ። ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 🏦 1000142059022 የደረስንበትን እዚሁ አሳውቃለው።
إظهار الكل...
32
ታሕሳስ ፲፫ /13/
በዚችም ቀን ከላይኛው ግብጽ ቅዱስ አባት አብራኮስ አረፈ። ይህም ቅዱስ ዕድሜው ሃያ ዓመት ሲሆን መንኵሶ መልካም የሆነ ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለ። ሰይጣንም ከእርሱ ጋር በመጣላት በተሸነፈና በደከመ ጊዜ በእርሱም ላይ ምንም ምን ማድረግ ባልተቻለው ጊዜ ፊት ለፊት ተገልጦ መጥቶ “እነሆ ከዚህ ዕድሜህ ሌላ ኀምሳ ዓመት ቀረህ አለው።” በዚህም ወደ ስንፍና ሊጥለው ወዶ ነው። ሽማግሌውም እንዲህ ብሎ መለሰለት “አሳዘንከኝ እኔ ሌላ መቶ ዓመት እኖር ዘንድ ስለ አሰብኩ ቸል ብያለሁ አንተ እንዳልከውም ከሆነ ከቀድሞው እጅግ አብዝቼ እጋደል ዘንድ ይገባኛል።” ከዚህም በኋላ ተጋድሎውንና በገድል መጸመዱን አበዛ ሰባ ዓመታትም ከተጋደለ በኋላ በዚያች ዓመት አረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦  መጽሐፈ ስንክሳር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
إظهار الكل...
132🕊 10🥰 1
የጥበብ ሰዎች መጡ ሰማይና ምድር የማይወስኑት ተወስኖ አየነው በጠባብ ደረት ዘጠና ዘጠኙን መላእክትን ትቶ አገኘነው ዛሬ በበረት ተኝቶ የጥበብ ሰዎች መጡ /2/ ሰምተውት በዜና እያበራላቸው ኮከብ እንደፋና /2/
አዝ
ድንግል እመቤቴ ሰላምታ ይድረስሽ ለአምላክ ወገኖች መመኪያቸው የሆንሽ ከአንቺ ተወለደ የዓለም መድኀን ኲነኔን አጥፍቶ ክብሩን ሊያወርሰን
አዝ
ጌታችን ሲወለድ በቤተልሔም /2/ ሐዘን ተደምስሶ ሰፈነ ሰላም /2/ እንጨቶች አፈሩ ፍሬ በረከት ወንዞች ሁሉ ሆኑ ማርና ወተት
አዝ
ሰብአ ሰገል መጡ ሊሰግዱ በሙሉ የእስራኤል ንጉሥ ወዴት ነው እያሉ እጅ መንሻውን ሰጡት እንደየሥርዓቱ ዕጣነን ለክህነት ወርቁን ስመንግሥቱ የአእላፋት ዝማሬ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
إظهار الكل...
የጥበብ ሰዎች መጡ.mp310.74 MB
107🥰 8🕊 2
እስከ ታኅሣሥ 16 ጠዋት ብቻ ነው የምንሰበስበው። እንደው በእግዚአብሔር ስም የምጠይቃችሁ ነገር ግን አንድ መጎናጸፊያ ብንጨምር መልካም ነበር። እነዚህን የገጠር አብያተ ክርስቲያናት ከእግዚአብሔር ውጪ የሚመለከታቸው ሌላ ማንም የለም። ስለዚህ ለታቦተ ሕጉ አንድ መጎናጸፊያ ብቻ በቂ አይደለም። ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 🏦 1000142059022 እስካሁን በስውር የሰጣችሁን በሙሉ እግዚአብሔር አምላክ አብዝቶ በግልጥ ይመልስላችሁ።
إظهار الكل...
55
የአማልክት አምላክ ተወለደ የአማልክት አምላክ ተወለደ /2/ መድኀኔዓለም የጌቶች ጌታ ተወለደ  መድንኔዓለም ከድንግል ማርያም በቤተልሔም ተወለደ አማኑኤል
አዝ
መጣ ወረደ ተወለደ አማኑኤል ክብሩን አዋርዶ ተወለደ አማኑኤል በበረት ተኛ ተወለደ አማኑኤል ትሕትናን ወደ ተወለደ አማኑኤል ጌታ ተወልዷል ተወለደ አማኑኤል ከድንግል ማርያም ተወለደ አማኑኤል ጠብን አርቆ ተወለደ አማኑኤል ሊሰጠን ሰላም ተወለደ አማኑኤል
አዝ
የዲያብሎስን ተወለደ አማኑኤል ሥልጣኑነ ሊሽር ተወለደ አማኑኤል ሰወን ለፊታ ተወለደ አማኑኤል ከኀጢአት እስር ተወለደ አማኑኤል ይኸው ተወልዷል ተወለደ አማኑኤል በከብቶች በረት ተወለደ አማኑኤል አልፋ ዖሜጋ ተወለደ አማኑኤል አሞላከ አማልክት ተወለደ አማኑኤል
አዝ
አናመስግነው ተወለደ አማኑኤል እንደ መላእክት ተወለደ አማኑኤል ተወልዷልና ተወለደ አማኑኤል የዓለም መድኃኒት ተወለደ አማኑኤል ቃል ሥጋ ሆነ ተወለደ አማኑኤል ከድንግል ማርያም ተወለደ አማኑኤል የጌቶች ጌታ ተወለደ አማኑኤል መድኃኔዓለም ተወለደ አማኑኤል የአእላፋት ዝማሬ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
إظهار الكل...
የአማልክት_አምላክ_ተወለደ_ዘማሪ_ፍቃዱ_አማረ_2018_የአእላፋት_ዝማሬ_መዝሙር_በጃን_ያሬድ.mp35.12 MB
79🕊 1
Photo unavailableShow in Telegram
እግዚአብሔር ይመስገን። 🎉🎉🎉 ጉዞ ወደ ሁለተኛ መጎናጸፊያ የሶስት ጽንሐሕ እና የአንድ መጎናጸፊያ መግዣ ብር ሰብስበን ጨርሰናል። 🕯️የአንድ ጽንሐሕ ዋጋ = 13,000 ብር ⛪️የአንድ መጎናጸፊያ ዋጋ = 40,000
إظهار الكل...
27
እስከ ታኅሣሥ 16 ጠዋት ብቻ ነው የምንሰበስበው። እንደው በእግዚአብሔር ስም የምጠይቃችሁ ነገር ግን አንድ መጎናጸፊያ ብንጨምር መልካም ነበር። እነዚህን የገጠር አብያተ ክርስቲያናት ከእግዚአብሔር ውጪ የሚመለከታቸው ሌላ ማንም የለም። ስለዚህ ለታቦተ ሕጉ አንድ መጎናጸፊያ ብቻ በቂ አይደለም። ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 🏦 1000142059022 እስካሁን በስውር የሰጣችሁን በሙሉ እግዚአብሔር አምላክ አብዝቶ በግልጥ ይመልስላችሁ።
إظهار الكل...
11
Photo unavailableShow in Telegram
እግዚአብሔር ይመስገን። 🎉🎉🎉 እንኳን ደስ አላችሁ እስካሁን 75,173 ብር ደርሰናል። ለአንድ የገጠር ቤተ ክርስቲያን የሚሆን የሁለት ጽንሐሕ እና የአንድ መጎናጸፊያ መግዣ ብር ሰብስበን ጨርሰናል። 🕯️የአንድ ጽንሐሕ ዋጋ = 13,000 ብር ⛪️የአንድ መጎናጸፊያ ዋጋ = 40,000 ለሶስተኛ ጽንሐሕ መግዣ የሚሆን ለመሙላት የሚቀረን 3,900 ብር ብቻ ነው። እያንዳንዷ ብር እዚህ ጋር ትልቅ ዋጋ አላት። አስራታችሁን ያላወጣችሁ፣ ለቁርስ ለምሳ ታጠፉት የነበረውን ገንዘብ ለገጠር አብያተ ክርስቲያናት አገልግሎት የሚውል መጎናጸፊያ እና ጽንሐሕ ገዝተን እንስጥ። እስከ ታኅሣሥ 14 ቀን ድረስ ቃል መግባት ትችላላችሁ። መባችሁን እግዚአብሔር ይቀበላችሁ። ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 🏦 1000142059022 የደረስንበትን እዚሁ አሳውቃለው።
إظهار الكل...
35🔥 1😍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ታሕሳስ ፲፪ /12/
በዚችም ዕለት የከበረ አባት የዋልድባው አባ ሳሙኤል የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው። ለዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም እስጢፋኖስ የእናቱ ስም አመተ ማርያም ነው። እነርሱም በዘመድ የከበሩ ደጎች ናቸው በአክሱም ምድርም ወለዱት በአደገ ጊዜም የቤተ ክርስቲያንን መጻሕፍት አስተማሩት አባቱና እናቱም በሞቱ ጊዜ ወደ ደብረ በንኰል ገዳም ወደ አባ አድኃኒ ሒዶ የምንኲስና ልብስን ለብሶ በጾምና በጸሎት እየተጋደለ ኖረ። አንበሶችና ነብሮች የሚያስፈሩም አራዊት ሁሉ ወደርሱ በመምጣት ይሰግዱለታል የእግሮቹን ትቢያ ይልሱ ነበር። በአንዲት ዕለትም በጐዳና ሲጓዝ ታላቅ ወንዝን ውኃው መልቶ አገኘ መጽሐፍና እሳትም ከእርሱ ጋር ነበረ ጸሎትንም አድርጎ ወደ ውኃው ገባ ውኃውም ዋጠውና ወደታች አወረደው በእግዚአብሔርም ኃይል ወደማዶ በጣለው ጊዜ መጽሐፉ ሳይደመሰስ እሳቱም ሳይጠፋ አገኘው። ከዚህም በኋላ ብዙ ደቀ መዛሙርት ወደርሱ ተሰበሰቡ በተጋድሎም ተጠመዱ ከእርሳቸውም የመጀመሪያው አባ ዘሩፋኤል ነው። የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ውዳሴዋን ሲያነብ ክንድ ያህል ከምድር ወደ ላይ ከፍ ከፍ ይላል እምቤታችን ማርያምም ወደርሱ መጥታ የሚያበራ ዕንቁንና ንጹሕ ዕጣንን ሰጠችው። ፍልሰቱም ሲቀርብ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በክንፎቹ ተሸክሞ አወጣው የሰማያዊት ኢየሩሳሌምን ተድላዋን ሁሉ አሳየው ወደ ልዑል እግዚአብሔርም ዙፋን ፊት አቅርቦት ስሙን ለሚጠራ መታሰቢያውንም ለሚያደርግ ቃል ኪዳን ተቀበለ ወደ በዓቱም ሲመለስ ለደቀ መዛሙርቱ ነገራቸው ከዚህም በኋላ በሰላም በፍቅር አረፈ። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦  መጽሐፈ ስንክሳር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
إظهار الكل...
183🕊 15
ዮም ፍስሐ ኮነ ዮም ፍስሐ ኮነ ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደቱ ለመድኃኒነ ዛሬ ሆነ ደስታችን ሆነ ደስታችን ተወልዶአልና መድኀኒታችን
አዝ
የያዕቆብ ኮከብ ፍስሐ ኮነ የዳዊት ሆድ ፍሬ ፍስሐ ኮነ የአብርሃም ተስፋ ፍስሐ ኮነ ተፈጸመ ዛሬ ፍስሐ ኮነ የሰው ልጆች ሁሉ ፍስሐ ኮነ በአንድነት ተነሡ ፍስሐ ኮነ መድኀኒት ተወልዶአል ፍስሐ ኮነ እልል በሉ ለእሱ ፍስሐ ኮነ
አዝ
አንቺ ቤተልሔም ፍስሐ ኮነ የዳዊት ከተማ ፍስሐ ኮነ ተንቀሽ አትቀሪም ፍስሐ ኮነ ተብለሽ ባድማ ፍስሐ ኮነ የብርሃን ድንኳን ፍስሐ ኮነ ባንቺ ተተከለ ፍስሐ ኮነ ጎዳናሽ አበራ ፍስሐ ኮነ ሰማይን መሰለ ፍስሐ ኮነ
አዝ
አረኞች ሆይ ስሙ ፍስሐ ኮነ ተአምር ልንገራችሁ ፍስሐ ኮነ ቤተ ልሔም ሒዱ ፍስሐ ኮነ በጎቹን ትታችሁ ፍስሐ ኮነ በፍጥነት ገስግሡ ፍስሐ ኮነ ማንም ሳይቀድማችሁ ፍስሐ ኮነ ለዓለም የሚበቃ ፍስሐ ኮነ በግ ታገኛላችሁ ፍስሐ ኮነ
አዝ
ድንቅ መካር ኃያል ፍስሐ ኮነ የሰላም አለቃ ፍስሐ ኮነ ተወልዶ ሲገለጥ ፍስሐ ኮነ ዕንባችን አበቃ ፍስሐ ኮነ የእኛ መድኀኔዓስም ፍስሐ ኮነ ተወልደህ ወለደኽን ፍስሐ ኮነ ስምህ ይቀደስ ፍስሐ ኮነ
አዝ
መላእክት ዘመሩ ፍስሐ ኮነ ሔሮድስ ተጨነቀ ፍስሐ ኮነ አህያ ገዢውን ፍስሐ ኮነ አሞላኩን አወቀ ፍስሐ ኮነ ኮከብ መንገድ መራ ፍስሐ ኮነ ነገሥታት ሰገዱ ፍስሐ ኮነ የዚህ ድንቅ ሕፃን ፍስሐ ኮነ ልዩ ነው መንገዱ ፍስሐ ኮነ
አዝ
እሳት ተሸክማ ፍስሐ ኮነ እሳት የወለደች ፍስሐ ኮነ እሳትን ታቅፋ ፍስሐ ኮነ እሳት ያሳደገች ፍስሐ ኮነ ዕፀ ጳጦስ ሆና ፍስሐ ኮነ በሲና ያያት ፍስሐ ኮነ አምላክን የቻለች ፍስሐ ኮነ ድንግል ማርያም ናት ፍስሐ ኮነ የአእላፋት ዝማሬ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
إظهار الكل...
ዮም_ፍስሐ_ኮነ_2018_የአእላፋት_ዝማሬ_መዝሙር_በጃን_ያሬድ_ኅብረ_ዝማሬ_የተዘመረ.mp35.77 MB
167🕊 6🔥 3
Photo unavailableShow in Telegram
እግዚአብሔር ይመስገን። 🎉🎉🎉 እንኳን ደስ አላችሁ እስካሁን 71,737 ብር ደርሰናል። ለአንድ የገጠር ቤተ ክርስቲያን የሚሆን የሁለት ጽንሐሕ እና የአንድ መጎናጸፊያ መግዣ ብር ሰብስበን ጨርሰናል። 🕯️የአንድ ጽንሐሕ ዋጋ = 13,000 ብር ⛪️የአንድ መጎናጸፊያ ዋጋ = 40,000 ለሶስተኛ ጽንሐሕ መግዣ የሚሆን ለመሙላት 7,263 ብር ይቀረናል። እያንዳንዷ ብር እዚህ ጋር ትልቅ ዋጋ አላት። አስራታችሁን ያላወጣችሁ፣ ለቁርስ ለምሳ ታጠፉት የነበረውን ገንዘብ ለገጠር አብያተ ክርስቲያናት አገልግሎት የሚውል መጎናጸፊያ እና ጽንሐሕ ገዝተን እንስጥ። እስከ ታኅሣሥ 14 ቀን ድረስ ቃል መግባት ትችላላችሁ። መባችሁን እግዚአብሔር ይቀበላችሁ። ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 🏦 1000142059022 የአገልግሎቱን ሁኔታ ተረድታችሁ ጽንሐሕ እና መጎናጸፊያ በተመጣጣኝ ዋጋ የምታስረክቡ ነጋዴዎች ካላችሁ በዚህ @Zimaredawitmessanger ላይ መልዕክት ያስቀምጡልን። የደረስንበትን እዚሁ አሳውቃለው።
إظهار الكل...
star reaction 1 67😍 3🔥 2