ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
رفتن به کانال در Telegram
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች፣ ስንክሳር፣ መዝሙራትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም አስተያየት @Zimaredawitmessanger ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል። ስለሚሰጡን ገንቢ ሃሳብ እናመሰግናለን። YouTube Page - https://bit.ly/2O1Z3d8 Facebook Page - https://www.fb.com/l/6lp1kJRRR
نمایش بیشتر2025 سال در اعداد

166 287
مشترکین
-2324 ساعت
+187 روز
-1430 روز
آرشیو پست ها
Photo unavailableShow in Telegram
ሁለት ቀን ብቻ ቀረን!
የደረስንበት 94,723 ብር
የሚያስፈልገን 119,000 ብር
የቀረን 24,277 ብር ብቻ
ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር
🏦 1000142059022
ሁላችሁም በቀረችን ቀን በመረባረብ የአቅማችሁን እንድትለግሱ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።
❤ 44
እግዚአብሔርን አመስግኑት
እግዚአብሔርን አመስግኑት
ሥራ ግሩም ድንቅ ነው በሉት
እግዚአብሔርን እመስግኑት
ስራህ ግሩም ድንቅ ነው በሉት
አዝሠማይን ያለ ምሰሶ ምድርንም ያለ መሰረት ያጸናው እርሱ ነው ሥራህ ድንቅ ነው በሉት
አዝየባህርንም ጥልቀት የመጠነ ዳርቻዋን የወሰነ እግዚአብሔርን አመስግኑ ሥራ ግሩም ድንቅ ነው በሉት
አዝማእበል ንፋሱን የሚገስጽ ፍጥረቱ ለስሙ የሚታዘዝ ትጉህ እረኛ ድካም የሌለበት እግዚአብሔርን ሥራህ ድንቅ ነው በሉት
አዝንጹሐ ባህርይ ነው ሁሉን የሚገዛ የነገስታት ንጉስ አልፋና ኦሜጋ ዘለዓለም እርሱ ነው የማይለወጥ እግዚአብሔር ስራህ ድንቅ ነው በሉት
አዝጥበብን የሚሰጥ ጥበበኛ ፍርድ የማያጎድል እውነተኛ ዳኛ እንደ እርሱ ያለ ከቶ አይገኝም እግዚአብሔር ግሩም ነው ለዘልዓለም የአእላፋት ዝማሬ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
audio1766424028464.mp33.92 MB
❤ 110🥰 7🕊 2😍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ሁለት ቀን ብቻ ቀረን!
የደረስንበት 93,223 ብር
የሚያስፈልገን 119,000 ብር
ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር
🏦 1000142059022
ሁላችሁም በቀረችን ቀን በመረባረብ የአቅማችሁን እንድትለግሱ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።
❤ 33
ታኅሣሥ ፲፬ /14/በዚች ቀን ከፍ ከፍ ካለች ከመኑፍ ከተማ ቅዱስ ስምዖን በሰማዕትነት አረፈ። እርሱም በእስላሞች ዘመን ከመሳፍንቶቻቸው ከአንዱ ጋር ተከራከረና ቅዱስ ስምዖን ረቶ አሳፈረው ያም እስላም ወደ መሳፍንቱ አለቃ ሒዶ ይህ ስምዖን የእስላሞችን ሃይማኖት ያቃልላል ብሎ ወነጀለው ስለዚህም ይዘው በጽኑዕ ሥቃይ አሠቃዩት ከዚያም በኋላ ራሱን በሰይፍ ቆረጡት የሰማዕትነት አክሊልን በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ዳግመኛም በዚችም ቀን ቅዱሳን አባ ብሑርና አረጋዊ ሚናስ በሰማዕትነት አረፉ። በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
❤ 111🕊 14
ከሰማዩ ከፍታ
ከሰማዩ ከፍታ ከፍ ብላ ጽዮን
በሰገነት ላይ ተቀምጣ
ድንግል በክብር በግርማ ትኖራለች አጊጣ /2/
አይን ከሞላባቸው ከኪሩቤል
ክንፋቸው ከበዛ ከሱራፌል
ከሊቃናቱ ሁሉ ትበልጣለች
እሳተ መለኮትን በሆዱዋ ስለተሸከመች
አዝከንጉሱ በስተቀኝ ከዙፋኑ ንግስቲቱ ቆማለች በየቀኑ የቃል ኪዳን ቀሚሷን ተጐናጽፋ የምትማልድልን ድንግል ናት የሁላችን ተስፉ
አዝበብርሀን ወንበር ላይ ተቀምጣለች ጨረቃን ከእግሯ በታች ተጫምታለች የቅድስናን ውበት ተሸልማ የምታብረቀርቀው እርሷ ናት የልዑል ከተማ
አዝከዕብራውያን ሴቶች ተለይታ ከሔዋን ዘሮች ሁሉ ታየች ጐልታ ሰባቱን መቅረዝ ልጇ ያበራል ስጋዋን ተዋህዶ በፍቅር እኛኑ መስሏል የአእላፋት ዝማሬ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ከሰማዩ_ከፍታ_ዘማሪ_ገብረዮሐንስ_ገብረጻድቅ_2018_የአእላፋት_ዝማሬ_መዝሙር_በጃን_ያሬድ_ኅ.mp34.79 MB
❤ 59🕊 3
ሰባቱ መንጦላይት
ሰባቱ መንጦላይት ወዴት ተጋረዱ
ሰባቱ መብራቶች ወዴት ተሰናዱ
ታናሽ ሙሽራ ነሽ የአሥራ አምስት ዓመት
በአንቺ ላይ ሲፈጸም እንግዳ ሥርዓት
አዝአንዴ እየታጠቀ አንዴም እየፈታ ገብርኤል ሲያበስርሽ በፍጹም ሰላምታ ይኩነኒ ብለሽ ስትቀበይው መለኮት እንዴት ነው የተዋሐደው ይህን ባሰብኩ ቁጥር ልቤ ይመሰጣል ከዚህ በላይ ፍቅርስ እንዴት ይገለጣል
አዝሁሉን የሚወስን ባንቺ ተወሰነ ከሦስቱ አካል አንዱ ቃልም ሥጋ ሆነ ስፋት እና ጥበት ሰማይ እና ምድር ባንቺ ተገናኙ ገባሪና ግብር ይህን ባሰብኩ ቁጥር ልቤ ይመሰጣል ከዚህ በላይ ፍቅርስ እንዴት ይገለጣል
አዝእንዴት ቢመርጥሽ ነው እንዴት ቢያከብርሽ ትናንት እና ዛሬን ያገናኘብሽ ምልዐትና ወሰን ግዝፈትና ርቀት ባንቺ ተዋሐዱ ፈጣሪና ፍጥረት ይህን ባሰብኩ ቁጥር ልቤ ይመሰጣል ከዚህ በላይ ፍቅርስ እንዴት ይገለጣል
አዝምስጢር ሊመረምር ይወጣል ኀሊና ያልፋል ይሻገራል ከሰማይ ደመና ነገር ግን አይችልም ምንም ቢገሠግሥ ከመሰወሪያው ዘንድ ከልጅሽም ሊደርስ ስለዚህ አቅቶት ደክሞት ይመለሳል መልክዐ ውዳሴሽን በአድናቆት ያደርሳል የአእላፋት ዝማሬ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ሰባቱ_መንጦላዕት_ዘማሪ_ቀሲስ_ምንዳዬ_ብርሃኑ_2018_የአእላፋት_ዝማሬ_መዝሙር_በጃን_ያሬድ.mp34.91 MB
❤ 150🕊 11🥰 8😍 2
የቀረን ሶስት ቀን ብቻ ነው።
ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል አገልግሎት ማድረስ ስላለብን ቀድመን ገዝተን መላክ አለብን።
አንድ እህታችን የቀጣይ ወር አስራቷን ከሰው ተበድራ ሰጥታናለች።ቅዱስ ገብርኤል አብዝቶ ይስጥልን።
❤ 71
Photo unavailableShow in Telegram
እግዚአብሔር ይመስገን። 🎉🎉🎉
እንኳን ደስ አላችሁ እስካሁን 90,873 ብር ደርሰናል። ለአንድ የገጠር ቤተ ክርስቲያን የሚሆን የሶስት ጽንሐሕ እና የአንድ መጎናጸፊያ መግዣ ብር ሰብስበን ጨርሰናል።
🕯️የአንድ ጽንሐሕ ዋጋ = 13,000 ብር
⛪️የአንድ መጎናጸፊያ ዋጋ = 40,000
ለሁለተኛ መጎናጸፊያ መግዣ የሚሆን ለመሙላት 28,127 ብር ብቻ ይቀረናል። እያንዳንዷ ብር እዚህ ጋር ትልቅ ዋጋ አላት።
አስራታችሁን ያላወጣችሁ፣ ለቁርስ ለምሳ ታጠፉት የነበረውን ገንዘብ ለገጠር አብያተ ክርስቲያናት አገልግሎት የሚውል መጎናጸፊያ እና ጽንሐሕ ገዝተን እንስጥ። እስከ ታኅሣሥ 14 ቀን ድረስ ቃል መግባት ትችላላችሁ።
መባችሁን እግዚአብሔር ይቀበላችሁ።
ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር
🏦 1000142059022
የደረስንበትን እዚሁ አሳውቃለው።
❤ 31
ታሕሳስ ፲፫ /13/በዚችም ቀን ከላይኛው ግብጽ ቅዱስ አባት አብራኮስ አረፈ። ይህም ቅዱስ ዕድሜው ሃያ ዓመት ሲሆን መንኵሶ መልካም የሆነ ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለ። ሰይጣንም ከእርሱ ጋር በመጣላት በተሸነፈና በደከመ ጊዜ በእርሱም ላይ ምንም ምን ማድረግ ባልተቻለው ጊዜ ፊት ለፊት ተገልጦ መጥቶ “እነሆ ከዚህ ዕድሜህ ሌላ ኀምሳ ዓመት ቀረህ አለው።” በዚህም ወደ ስንፍና ሊጥለው ወዶ ነው። ሽማግሌውም እንዲህ ብሎ መለሰለት “አሳዘንከኝ እኔ ሌላ መቶ ዓመት እኖር ዘንድ ስለ አሰብኩ ቸል ብያለሁ አንተ እንዳልከውም ከሆነ ከቀድሞው እጅግ አብዝቼ እጋደል ዘንድ ይገባኛል።” ከዚህም በኋላ ተጋድሎውንና በገድል መጸመዱን አበዛ ሰባ ዓመታትም ከተጋደለ በኋላ በዚያች ዓመት አረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
❤ 132🕊 10🥰 1
የጥበብ ሰዎች መጡ
ሰማይና ምድር የማይወስኑት
ተወስኖ አየነው በጠባብ ደረት
ዘጠና ዘጠኙን መላእክትን ትቶ
አገኘነው ዛሬ በበረት ተኝቶ
የጥበብ ሰዎች መጡ /2/ ሰምተውት በዜና እያበራላቸው ኮከብ እንደፋና /2/
አዝድንግል እመቤቴ ሰላምታ ይድረስሽ ለአምላክ ወገኖች መመኪያቸው የሆንሽ ከአንቺ ተወለደ የዓለም መድኀን ኲነኔን አጥፍቶ ክብሩን ሊያወርሰን
አዝጌታችን ሲወለድ በቤተልሔም /2/ ሐዘን ተደምስሶ ሰፈነ ሰላም /2/ እንጨቶች አፈሩ ፍሬ በረከት ወንዞች ሁሉ ሆኑ ማርና ወተት
አዝሰብአ ሰገል መጡ ሊሰግዱ በሙሉ የእስራኤል ንጉሥ ወዴት ነው እያሉ እጅ መንሻውን ሰጡት እንደየሥርዓቱ ዕጣነን ለክህነት ወርቁን ስመንግሥቱ የአእላፋት ዝማሬ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
የጥበብ ሰዎች መጡ.mp310.74 MB
❤ 107🥰 8🕊 2
እስከ ታኅሣሥ 16 ጠዋት ብቻ ነው የምንሰበስበው። እንደው በእግዚአብሔር ስም የምጠይቃችሁ ነገር ግን አንድ መጎናጸፊያ ብንጨምር መልካም ነበር። እነዚህን የገጠር አብያተ ክርስቲያናት ከእግዚአብሔር ውጪ የሚመለከታቸው ሌላ ማንም የለም። ስለዚህ ለታቦተ ሕጉ አንድ መጎናጸፊያ ብቻ በቂ አይደለም።
ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር
🏦 1000142059022
እስካሁን በስውር የሰጣችሁን በሙሉ እግዚአብሔር አምላክ አብዝቶ በግልጥ ይመልስላችሁ።
❤ 52
የአማልክት አምላክ ተወለደ
የአማልክት አምላክ ተወለደ /2/
መድኀኔዓለም የጌቶች ጌታ ተወለደ
መድንኔዓለም ከድንግል ማርያም
በቤተልሔም ተወለደ አማኑኤል
አዝመጣ ወረደ ተወለደ አማኑኤል ክብሩን አዋርዶ ተወለደ አማኑኤል በበረት ተኛ ተወለደ አማኑኤል ትሕትናን ወደ ተወለደ አማኑኤል ጌታ ተወልዷል ተወለደ አማኑኤል ከድንግል ማርያም ተወለደ አማኑኤል ጠብን አርቆ ተወለደ አማኑኤል ሊሰጠን ሰላም ተወለደ አማኑኤል
አዝየዲያብሎስን ተወለደ አማኑኤል ሥልጣኑነ ሊሽር ተወለደ አማኑኤል ሰወን ለፊታ ተወለደ አማኑኤል ከኀጢአት እስር ተወለደ አማኑኤል ይኸው ተወልዷል ተወለደ አማኑኤል በከብቶች በረት ተወለደ አማኑኤል አልፋ ዖሜጋ ተወለደ አማኑኤል አሞላከ አማልክት ተወለደ አማኑኤል
አዝአናመስግነው ተወለደ አማኑኤል እንደ መላእክት ተወለደ አማኑኤል ተወልዷልና ተወለደ አማኑኤል የዓለም መድኃኒት ተወለደ አማኑኤል ቃል ሥጋ ሆነ ተወለደ አማኑኤል ከድንግል ማርያም ተወለደ አማኑኤል የጌቶች ጌታ ተወለደ አማኑኤል መድኃኔዓለም ተወለደ አማኑኤል የአእላፋት ዝማሬ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
የአማልክት_አምላክ_ተወለደ_ዘማሪ_ፍቃዱ_አማረ_2018_የአእላፋት_ዝማሬ_መዝሙር_በጃን_ያሬድ.mp35.12 MB
❤ 79🕊 1
Photo unavailableShow in Telegram
እግዚአብሔር ይመስገን። 🎉🎉🎉 ጉዞ ወደ ሁለተኛ መጎናጸፊያ
የሶስት ጽንሐሕ እና የአንድ መጎናጸፊያ መግዣ ብር ሰብስበን ጨርሰናል።
🕯️የአንድ ጽንሐሕ ዋጋ = 13,000 ብር
⛪️የአንድ መጎናጸፊያ ዋጋ = 40,000
❤ 27
እስከ ታኅሣሥ 16 ጠዋት ብቻ ነው የምንሰበስበው። እንደው በእግዚአብሔር ስም የምጠይቃችሁ ነገር ግን አንድ መጎናጸፊያ ብንጨምር መልካም ነበር። እነዚህን የገጠር አብያተ ክርስቲያናት ከእግዚአብሔር ውጪ የሚመለከታቸው ሌላ ማንም የለም። ስለዚህ ለታቦተ ሕጉ አንድ መጎናጸፊያ ብቻ በቂ አይደለም።
ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር
🏦 1000142059022
እስካሁን በስውር የሰጣችሁን በሙሉ እግዚአብሔር አምላክ አብዝቶ በግልጥ ይመልስላችሁ።
❤ 11
Photo unavailableShow in Telegram
እግዚአብሔር ይመስገን። 🎉🎉🎉
እንኳን ደስ አላችሁ እስካሁን 75,173 ብር ደርሰናል። ለአንድ የገጠር ቤተ ክርስቲያን የሚሆን የሁለት ጽንሐሕ እና የአንድ መጎናጸፊያ መግዣ ብር ሰብስበን ጨርሰናል።
🕯️የአንድ ጽንሐሕ ዋጋ = 13,000 ብር
⛪️የአንድ መጎናጸፊያ ዋጋ = 40,000
ለሶስተኛ ጽንሐሕ መግዣ የሚሆን ለመሙላት የሚቀረን 3,900 ብር ብቻ ነው። እያንዳንዷ ብር እዚህ ጋር ትልቅ ዋጋ አላት።
አስራታችሁን ያላወጣችሁ፣ ለቁርስ ለምሳ ታጠፉት የነበረውን ገንዘብ ለገጠር አብያተ ክርስቲያናት አገልግሎት የሚውል መጎናጸፊያ እና ጽንሐሕ ገዝተን እንስጥ። እስከ ታኅሣሥ 14 ቀን ድረስ ቃል መግባት ትችላላችሁ።
መባችሁን እግዚአብሔር ይቀበላችሁ።
ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር
🏦 1000142059022
የደረስንበትን እዚሁ አሳውቃለው።
❤ 35🔥 1😍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ታሕሳስ ፲፪ /12/በዚችም ዕለት የከበረ አባት የዋልድባው አባ ሳሙኤል የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው። ለዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም እስጢፋኖስ የእናቱ ስም አመተ ማርያም ነው። እነርሱም በዘመድ የከበሩ ደጎች ናቸው በአክሱም ምድርም ወለዱት በአደገ ጊዜም የቤተ ክርስቲያንን መጻሕፍት አስተማሩት አባቱና እናቱም በሞቱ ጊዜ ወደ ደብረ በንኰል ገዳም ወደ አባ አድኃኒ ሒዶ የምንኲስና ልብስን ለብሶ በጾምና በጸሎት እየተጋደለ ኖረ። አንበሶችና ነብሮች የሚያስፈሩም አራዊት ሁሉ ወደርሱ በመምጣት ይሰግዱለታል የእግሮቹን ትቢያ ይልሱ ነበር። በአንዲት ዕለትም በጐዳና ሲጓዝ ታላቅ ወንዝን ውኃው መልቶ አገኘ መጽሐፍና እሳትም ከእርሱ ጋር ነበረ ጸሎትንም አድርጎ ወደ ውኃው ገባ ውኃውም ዋጠውና ወደታች አወረደው በእግዚአብሔርም ኃይል ወደማዶ በጣለው ጊዜ መጽሐፉ ሳይደመሰስ እሳቱም ሳይጠፋ አገኘው። ከዚህም በኋላ ብዙ ደቀ መዛሙርት ወደርሱ ተሰበሰቡ በተጋድሎም ተጠመዱ ከእርሳቸውም የመጀመሪያው አባ ዘሩፋኤል ነው። የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ውዳሴዋን ሲያነብ ክንድ ያህል ከምድር ወደ ላይ ከፍ ከፍ ይላል እምቤታችን ማርያምም ወደርሱ መጥታ የሚያበራ ዕንቁንና ንጹሕ ዕጣንን ሰጠችው። ፍልሰቱም ሲቀርብ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በክንፎቹ ተሸክሞ አወጣው የሰማያዊት ኢየሩሳሌምን ተድላዋን ሁሉ አሳየው ወደ ልዑል እግዚአብሔርም ዙፋን ፊት አቅርቦት ስሙን ለሚጠራ መታሰቢያውንም ለሚያደርግ ቃል ኪዳን ተቀበለ ወደ በዓቱም ሲመለስ ለደቀ መዛሙርቱ ነገራቸው ከዚህም በኋላ በሰላም በፍቅር አረፈ። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
❤ 183🕊 14
ዮም ፍስሐ ኮነ
ዮም ፍስሐ ኮነ ፍስሐ ኮነ
በእንተ ልደቱ ለመድኃኒነ
ዛሬ ሆነ ደስታችን ሆነ ደስታችን
ተወልዶአልና መድኀኒታችን
አዝየያዕቆብ ኮከብ ፍስሐ ኮነ የዳዊት ሆድ ፍሬ ፍስሐ ኮነ የአብርሃም ተስፋ ፍስሐ ኮነ ተፈጸመ ዛሬ ፍስሐ ኮነ የሰው ልጆች ሁሉ ፍስሐ ኮነ በአንድነት ተነሡ ፍስሐ ኮነ መድኀኒት ተወልዶአል ፍስሐ ኮነ እልል በሉ ለእሱ ፍስሐ ኮነ
አዝአንቺ ቤተልሔም ፍስሐ ኮነ የዳዊት ከተማ ፍስሐ ኮነ ተንቀሽ አትቀሪም ፍስሐ ኮነ ተብለሽ ባድማ ፍስሐ ኮነ የብርሃን ድንኳን ፍስሐ ኮነ ባንቺ ተተከለ ፍስሐ ኮነ ጎዳናሽ አበራ ፍስሐ ኮነ ሰማይን መሰለ ፍስሐ ኮነ
አዝአረኞች ሆይ ስሙ ፍስሐ ኮነ ተአምር ልንገራችሁ ፍስሐ ኮነ ቤተ ልሔም ሒዱ ፍስሐ ኮነ በጎቹን ትታችሁ ፍስሐ ኮነ በፍጥነት ገስግሡ ፍስሐ ኮነ ማንም ሳይቀድማችሁ ፍስሐ ኮነ ለዓለም የሚበቃ ፍስሐ ኮነ በግ ታገኛላችሁ ፍስሐ ኮነ
አዝድንቅ መካር ኃያል ፍስሐ ኮነ የሰላም አለቃ ፍስሐ ኮነ ተወልዶ ሲገለጥ ፍስሐ ኮነ ዕንባችን አበቃ ፍስሐ ኮነ የእኛ መድኀኔዓስም ፍስሐ ኮነ ተወልደህ ወለደኽን ፍስሐ ኮነ ስምህ ይቀደስ ፍስሐ ኮነ
አዝመላእክት ዘመሩ ፍስሐ ኮነ ሔሮድስ ተጨነቀ ፍስሐ ኮነ አህያ ገዢውን ፍስሐ ኮነ አሞላኩን አወቀ ፍስሐ ኮነ ኮከብ መንገድ መራ ፍስሐ ኮነ ነገሥታት ሰገዱ ፍስሐ ኮነ የዚህ ድንቅ ሕፃን ፍስሐ ኮነ ልዩ ነው መንገዱ ፍስሐ ኮነ
አዝእሳት ተሸክማ ፍስሐ ኮነ እሳት የወለደች ፍስሐ ኮነ እሳትን ታቅፋ ፍስሐ ኮነ እሳት ያሳደገች ፍስሐ ኮነ ዕፀ ጳጦስ ሆና ፍስሐ ኮነ በሲና ያያት ፍስሐ ኮነ አምላክን የቻለች ፍስሐ ኮነ ድንግል ማርያም ናት ፍስሐ ኮነ የአእላፋት ዝማሬ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ዮም_ፍስሐ_ኮነ_2018_የአእላፋት_ዝማሬ_መዝሙር_በጃን_ያሬድ_ኅብረ_ዝማሬ_የተዘመረ.mp35.77 MB
❤ 167🕊 6🔥 3
Photo unavailableShow in Telegram
እግዚአብሔር ይመስገን። 🎉🎉🎉
እንኳን ደስ አላችሁ እስካሁን 71,737 ብር ደርሰናል። ለአንድ የገጠር ቤተ ክርስቲያን የሚሆን የሁለት ጽንሐሕ እና የአንድ መጎናጸፊያ መግዣ ብር ሰብስበን ጨርሰናል።
🕯️የአንድ ጽንሐሕ ዋጋ = 13,000 ብር
⛪️የአንድ መጎናጸፊያ ዋጋ = 40,000
ለሶስተኛ ጽንሐሕ መግዣ የሚሆን ለመሙላት 7,263 ብር ይቀረናል። እያንዳንዷ ብር እዚህ ጋር ትልቅ ዋጋ አላት።
አስራታችሁን ያላወጣችሁ፣ ለቁርስ ለምሳ ታጠፉት የነበረውን ገንዘብ ለገጠር አብያተ ክርስቲያናት አገልግሎት የሚውል መጎናጸፊያ እና ጽንሐሕ ገዝተን እንስጥ። እስከ ታኅሣሥ 14 ቀን ድረስ ቃል መግባት ትችላላችሁ።
መባችሁን እግዚአብሔር ይቀበላችሁ።
ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር
🏦 1000142059022
የአገልግሎቱን ሁኔታ ተረድታችሁ ጽንሐሕ እና መጎናጸፊያ በተመጣጣኝ ዋጋ የምታስረክቡ ነጋዴዎች ካላችሁ በዚህ @Zimaredawitmessanger ላይ መልዕክት ያስቀምጡልን።
የደረስንበትን እዚሁ አሳውቃለው።
Photo unavailableShow in Telegram
ታሕሳስ ፲፩ /11/
በዚች ቀን የግብጽ ደቡብ ከሆነ ከመጺል አውራጃ ከሬስ ከተማ ሰዎች ወገን የሆነ ቅዱስ አባት አባ በኪሞስ አረፈ።
እርሱም የአባቱን በጎች የሚጠብቅ ነበር ዕድሜውም 12 ዓመት ሲሆነው የእግዚአብሔር መልአክ በጐልማሳ አምሳል ተገለጠለትና ሒደን እንመነኵስ ዘንድ ትሻለህ አለው። ሁለቱም ተስማምተው ወደ አስቄጥስ ገዳም ተጓዙ አባ በኪሞስም በዚያ መነኮሰ። በዚያም ሃያ አራት ዓመታትን ኖረ።
በአንድ ወቅትም አባ ሲኖዳ በራእይ ምሰሶ አየና ይህ ታላቅ ምሰሶ ምንድን ነው ብሎ ደነገጠ የእግዚአብሔርም መልአክ ተገልጦ ይህ አባ በኪሞስ ነው አለው።ከዚያችም ቀን በፊት ከቶ አላየውም ነበር በተገናኙም ጊዜ እርስበርሳቸው ሰላምታ ተሰጣጡ።
ዳግመኛም በአንዲት ቀን በአንድነት ሲጓዙ የሞተ ሰው ራስ አገኙ አባ ሲኖዳም በበትሩ ነቅነቅ አደረገውና ምውት ሆይ ያየኸውን ትነግረንና ታስረዳን ዘንድ ተነሣ አለው በዚያን ጊዜ ነፍሱ ወደ ዐፅሙ ተመልሳ ሥጋ ለብሶ ተነሣና ሰገደላቸው በሲኦል የሚሠራውንም ሁሉ በየወገናቸውም በውስጧ የሚሠቃዩትን እርሱም አረማዊ እንደሆነ ነገራቸው። በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ያመኑ ትእዛዙን ግን ያልጠበቁ በአሕዛብ ሥራና በአረማውያን ርኵስት የኖሩ ከእኛ በታች የሚኖሩ ክርስቲያኖች አሉ አለ ቅዱሳኑም ተመልሰህ ተኛ አሉት ወዲያውኑ እንደ ቀድሞው ሆነ።
ዕረፍቱም በቀረበ ጊዜ በሆድ ዝማ ሕመም ጥቂት ታመመ።
ቅዱሳንን በአንድነት ወደርሱ ሲመጡ ባያቸው ጊዜ ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ።መላእክትም ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት እያመሰገኑ አሳረጓት። መላ ዕድሜውም ሰባ ዓመት ሆነ 12 ዓመት በዓለም ውስጥ 58 ዓመት በምንኵስና ሥራ ኖረ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
❤ 126🕊 6🥰 5
