ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
الذهاب إلى القناة على Telegram
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች፣ ስንክሳር፣ መዝሙራትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም አስተያየት @Zimaredawitmessanger ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል። ስለሚሰጡን ገንቢ ሃሳብ እናመሰግናለን። YouTube Page - https://bit.ly/2O1Z3d8 Facebook Page - https://www.fb.com/l/6lp1kJRRR
إظهار المزيد2025 عام في الأرقام

166 278
المشتركون
-2324 ساعات
+187 أيام
-1430 أيام
أرشيف المشاركات
Photo unavailableShow in Telegram
የአንድ መጎናጸፊያ መግዣ ለመሙላት 9,390 ብር ይቀረናል።
ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር
🏦 1000142059022
❤ 25🕊 3
ይዌድስዋ
ይዌድስዋ ስዋ መላእክት ለማርያም /2/
በውስተ ውሳጤ መንጦላዕት ወይብልዋ
በሓኪ ማርያም ሐዳስዩ ጣዕዋ /2/
የአእላፋት ዝማሬ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ይዌድስዋ_2018_የአእላፋት_ዝማሬ_መዝሙር_በጃን_ያሬድ_ኅብረ_ዝማሬ_የተዘመረ.mp32.83 MB
❤ 98🕊 4🔥 2🥰 2
Photo unavailableShow in Telegram
እግዚአብሔር ይመስገን። 🎉🎉🎉
እንኳን ደስ አላችሁ ለአንድ የገጠር ቤተ ክርስቲያን የሚሆን የአንድ ጽንሐሕ መግዣ ብር እና የአንድ መጎናጸፊያ ደግሞ ግማሽ ብር ሰብስበን ጨርሰናል።
እስካሁን 39,260 ብር ደርሰናል።
🕯️የአንድ ጽንሐሕ ዋጋ = 13,000 ብር
⛪️የአንድ መጎናጸፊያ ዋጋ = 40,000
የአንድ መጎናጸፊያ መግዣ ለመሙላት 13,740 ብር ይቀረናል። እያንዳንዷ ብር እዚህ ጋር ትልቅ ዋጋ አላት።
አስራታችሁን፣ ለቁርስ ለምሳ ታጠፉት የነበረውን ገንዘብ ለገጠር አብያተ ክርስቲያናት አገልግሎት የሚውል መጎናጸፊያ እና ጽንሐሕ ገዝተን እንስጥ። እስከ ታኅሣሥ 14 ቀን ድረስ ቃል መግባት ትችላላችሁ።
መባችሁን እግዚአብሔር ይቀበላችሁ።
ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር
🏦 1000142059022
የአገልግሎቱን ሁኔታ ተረድታችሁ ጽንሐሕ እና መጎናጸፊያ በተመጣጣኝ ዋጋ የምታስረክቡ ነጋዴዎች ካላችሁ በዚህ @Zimaredawitmessanger ላይ መልዕክት ያስቀምጡልን።
የደረስንበትን እዚሁ አሳውቃለው።
❤ 51🕊 2
Photo unavailableShow in Telegram
እንኳን ደስ አላችሁ ለአንድ የገጠር ቤተ ክርስቲያን አንድ ጽንሐሕ መግዣ ብር ሰብስበን ጨርሰናል። እግዚአብሔር ይመስገን። 🎉🎉🎉
እስካሁን 25,310 ብር ደርሰናል።
አሁን ደሞ የመጎናጸፊያ ማሰባሰብ ጀምረናል። ለአንድ መጎናጸፊያ ገና 27,690 ብር ይቀረናል። እያንዳንዷ ብር እዚህ ጋር ትልቅ ዋጋ አላት።
🕯️የአንድ ጽንሐሕ ዋጋ = 13,000 ብር
⛪️የአንድ መጎናጸፊያ ዋጋ = 40,000
ለቁርስ ለምሳ ታጠፉት የነበረውን ገንዘብ ለገጠር አብያተ ክርስቲያናት አገልግሎት የሚውል መጎናጸፊያ እና ጽንሐሕ ገዝተን እንስጥ። እስከ ታኅሣሥ 14 ቀን ድረስ ቃል መግባት ትችላላችሁ።
መባችሁን እግዚአብሔር ይቀበላችሁ።
ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር
🏦 1000142059022
የአገልግሎቱን ሁኔታ ተረድታችሁ ጽንሐሕ እና መጎናጸፊያ በተመጣጣኝ ዋጋ የምታስረክቡ ነጋዴዎች ካላችሁ በዚህ @Zimaredawitmessanger ላይ መልዕክት ያስቀምጡልን።
የደረስንበትን እዚሁ አሳውቃለው።
❤ 73
Photo unavailableShow in Telegram
እንኳን ደስ አላችሁ ለአንድ የገጠር ቤተ ክርስቲያን አንድ ጽንሐሕ መግዣ ብር ሰብስበን ጨርሰናል። እግዚአብሔር ይመስገን። 🎉🎉🎉
እስካሁን 17,110 ብር ደርሰናል።
አሁን ደሞ የመጎናጸፊያ ማሰባሰብ ጀምረናል። ለአንድ መጎናጸፊያ ገና 35,890 ብር ይቀረናል። እያንዳንዷ ብር እዚህ ጋር ትልቅ ዋጋ አላት።
🕯️የአንድ ጽንሐሕ ዋጋ = 13,000 ብር
⛪️የአንድ መጎናጸፊያ ዋጋ = 40,000
ለቁርስ ለምሳ ታጠፉት የነበረውን ገንዘብ ለገጠር አብያተ ክርስቲያናት አገልግሎት የሚውል መጎናጸፊያ እና ጽንሐሕ ገዝተን እንስጥ። እስከ ታኅሣሥ 14 ቀን ድረስ ቃል መግባት ትችላላችሁ።
መባችሁን እግዚአብሔር ይቀበላችሁ።
ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር
🏦 1000142059022
የአገልግሎቱን ሁኔታ ተረድታችሁ ጽንሐሕ እና መጎናጸፊያ በተመጣጣኝ ዋጋ የምታስረክቡ ነጋዴዎች ካላችሁ በዚህ @Zimaredawitmessanger ላይ መልዕክት ያስቀምጡልን።
የደረስንበትን እዚሁ አሳውቃለው።
❤ 11😍 3🕊 2
Photo unavailableShow in Telegram
እንደምን አደራችሁ?
እግዚአብሔር ይመስገን እስካሁን 12,110 ብር ደርሰናል። አንድ ጽንሐሕ ለመግዛት 890 ብር ይቀረናል ፤የመጎናጸፊያው ገና አልተነካም። እያንዳንዷ ብር እዚህ ጋር ትልቅ ዋጋ አላት።
🕯️የአንድ ጽንሐሕ ዋጋ = 13,000 ብር
⛪️የአንድ መጎናጸፊያ ዋጋ = 40,000
ለቁርስ ለምሳ ታጠፉት የነበረውን ገንዘብ ለገጠር አብያተ ክርስቲያናት አገልግሎት የሚውል መጎናጸፊያ እና ጽንሐሕ ገዝተን እንስጥ።
መባችሁን እግዚአብሔር ይቀበላችሁ።
ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር
🏦 1000142059022
የአገልግሎቱን ሁኔታ ተረድታችሁ ጽንሐሕ እና መጎናጸፊያ በተመጣጣኝ ዋጋ የምታስረክቡ ነጋዴዎች ካላችሁ በዚህ @Zimaredawitmessanger ላይ መልዕክት ያስቀምጡልን።
የደረስንበትን እዚሁ አሳውቃለው።
❤ 38
ታኅሣሥ 6
ቅድስት አርሴማ(ቅዳሴ ቤቷ)
እናታችን ቅድስት አርሴማን በምን እንመስላታለን? እርሷ በአድማስ ላይ ተቀምጦ እንደሚያበራ እንቁ ናትና ክብሯ ብዙ ነው።
መድኃኒታችን ክርስቶስ በወንጌል እንዳለው "በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሠወር አይቻላትምና። "(ማቴ. ፭፥፲፩) የሰማዕቷ ሕይወት በፊታችን እንደ ብርሃን ተገልጦ ይታያል። ቅድስት አርሴማ እንደ ልጅ ወላጆቿን በመታዘዝ ደስ ያሰኘች ቡርክት ናት። ቅድስት አርሴማ ይህ ቀረሽ የማይሏት ውብ ናት።
ቅድስት አርሴማ ድንግል ናት። ቅድስት አርሴማ ባሕታዊት ጻድቅ ናት። ቅድስት አርሴማ ኃያል ሰማዕት ናት። ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ፦ አበው በትውፊት እንደ ነገሩን ቅዱሱ ጐርጐርዮስ የታላቋ ሰማዕት ቅድስት አርሴማ ትልቅ ወንድም ነው። በዜና ሰማዕታት ተጽፎ እንደሚገኘው በዚያ የመከራ ዘመን ቅዱስ ጐርጐርዮስ ሦስት ኃላፊነቶች ነበሩበት፦
፩.ቅድስት አርሴማን ጨምሮ ደናግሉን ማጽናት፤
፪.ትምሕርተ ቤተ ክርስቲያንን በሚገባ ማጥናት፤
፫.የሚመጣውን መከራ ለመቀበል ራሱን ማዘጋጀት። ቅዱሱ ሦስቱንም ኃላፊነቶች በሚገባ በመወጣቱ ከራሱ አልፎ ለሌሎቹ አርአያ መሆን ቻለ። ያቺን ንጽሕት አርበኛ ቅድስት አርሴማንም አጽንቶ የደናግሉ መሪ አደረጋት።
መከራው ገፍቶ እስከ መጣበት ጊዜ በአንድ የደናግል ገዳም ውስጥ ሆነው ይጸልዩ፣ ይጾሙ፣ ገዳማዊ ሥራንም ይሠሩ ነበር። ለዚህም ነው ቅድስት አርሴማና ቅዱስ ጐርጐርዮስን ጻድቃን የምንላቸው። በኋላ ግን ማኅደረ ሰይጣን ዲዮቅልጢያኖስ በመልኳ ተማርኮ ቅድስት አርሴማን ካላገባሁ በማለቱ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ድንግሏን አርሴማን ጨምሮ ክርስቲያኖችን ይዞ ወደ አርማንያ ተሰደደ።
በአርማንያም በአንድ ገዳም ውስጥ ተደብቀው በጾምና በጸሎት ለጥቂት ጊዜ ቆዩ። ነገር ግን ረሃብ ፈጃቸው። የሚላስ የሚቀመስ ነገር በአካባቢው ባለ መኖሩ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ወደ ከተማ ለመውጣት ተገደደ። በዚያም በድርጣድስ ቤተ መንግሥት ውስጥ ባርነት ተቀጠረ። በሚያገኛት ገንዘብም ወገኖቹን ይረዳ ነበር። መከራው ግን አለቀቃቸውም።
ርጉም ዲዮቅልጢያኖስ ቅዱሳኑ ወደ አርማንያ መሔዳቸውን ስለ ሰማ ይዞ እንዲልክለት ድርጣድስን ላከው። ድርጣድስ ግን ቅድስት አርሴማን ባያት ጊዜ ከውበቷ የተነሳ መታገስ ባለመቻሉ "ካላገባሁሽ" አላት። ድንግሊቱ ግን "እኔ የክርስቶስ ሙሽራ ነኝ፤ አይሆንም።" አለችው። ሊያስፈራራት ሞከረ። ዓይኗ እያየ ደናግሉን ጨፈጨፋቸው። አልሳካልህ ቢለው በአደባባይ በግድ ሊያገባት ቢሞክር እጁን ጠምዝዛ በሰው ሁሉ ፊት መሬት ላይ ጣለችው።
እጅግ ስላፈረ አስገረፋት፣ አሰቃያት፣ ዓይኗንም አወጣ። በመጨረሻም አንገቷን አስቆርጦ ከሰማዕታቱ ጋር ተራራ ላይ ጣላት። ከነገር ሁሉ በኋላ ድርጣድስና ባለሟሎቹ ለአደን በሔዱበት ርኩስ መንፈስ ወደ አውሬነት (እሪያነት) ቀየራቸው። የንጉሡ እንስሳ (አውሬ) መሆን በአርማንያ ታላቅ ድንጋጤን ፈጠረ። የንጉሡ እኅት ስታለቅስ በራእይ "ለእመ ኢያዕረግምዎ ለጐርጐርዮስ አልብክሙ ድኂን - ጐርጐርዮስን ከተቀበረበት ካላወጣችሁት አትድኑም።" አላቸው። ወዲያውም ቆፍረው አወጡት። ቅዱሱ እንደ ወጣ ዕረፍትን አልፈለገም።
ለአሥራ አምስት ዓመታት ቀባሪ አጥቶ የተበተነውን የቅድስት አርሴማንና የሰማዕታቱን አጽም ሰብስቦ በክብር አኖረው። ድርጣድስና ባለሟሎቹንም ወደ በርሃ ሒዶ ፈወሳቸው። የሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ አጽም በአሥራ አራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከሌሎች ሰማዕታት አጽም ጋር ኢትዮጵያ እንደ መጣ አባቶቻችን በትውፊት ነግረውናል። ለዚህም ነው ቡርክቷ እናታችን ከሌሎች ሃገራት ለይታ ለኢትዮጵያውያን ልዩ ፍቅር ያላት።
በዋናው ገዳሟ (ወሎ /ኩላማሶ/ ስባ ውስጥ የሚገኝ ነው።) ጨምሮ ስሟ በተጠራበት ሁሉ ኃይልን ታደርጋለችና። ነገር ግን ወንድሞቼና እኅቶቼ በቅድስቷ እናታችን ስም የሚነግዱ ሥጋውያን ሰዎች በዝተዋልና እንጠንቀቅ። የሰማዕቷ ክብር ብዙ ነውና በሕልም ላይ ብቻ አንታመን። አባ እንጦንስ እንዳሉት "በሕልሙ የሚታመን ሰው ከንቱ ነውና።" (መዝ. ፸፭፥፭)
በዚህ ዕለት ከሰማዕቷ ጋር የመንፈስ እናቷን ቅድስት አጋታን ልናስባት ይገባናል። ይህች እናት እመ ምኔት ስትሆን ቅድስት አርሴማን ታስተምራት፣ ታጸናት፣ ከጐኗም ትቆምላት ነበር። ረሃቧን፣ ጥሟን፣ ስደቷን፣ መከራዋንም ሁሉ አብራት ተሳትፋለች። በፍጻሜውም አብራት ተሰይፋለች። ይህች ዕለት ለቅድስት አርሴማና ለተከታዮቿ ሰማዕታት የፍልሰትና የቅዳሴ ቤት መታሰቢያ ናት።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
❤ 193🕊 7🥰 2
ወደ ማደሪያው ገብቼ
ወደ ማደሪያው ገብቼ ልስገድ ለእግዚአብሔር
ምስጋናንም ላቅርብ ስለ ስሙ ክብር
አድርጎልኛልና አመሰግነዋለሁ በዐፀደ መቅደሱም እሰግድለታለሁ
ከፊቱ ለመቆም ማልጄ እነሣለሁ /2/
እዝበመከራዬ ቀን ሆኖኛል መከታ ቤቱ ተገኝቼ በፍጹም ደስታ የከንፈሬን ፍሬ ልሠዋ በእልልታ /2/
አዝአሥር አውታር ባለው በዳዊት በገና በመላእክቱ ፊት ለማቅረብ ምስጋና የአፌንም ነገር ሰምተኸኛልና /2/
አዝለስሙ ልንበርከክ ለእርሱ እንደሚገባ ስዕስቴን ልፈጽም ላቅርበለት መብዓ ወደ አደባባዩ በምስጋና ልግባ /2/
እዝአሸበሽባለሁ ድምፄን አሰምቼ በቤተ መቅደሱ ሌሊት ተገኝቼ እንደ ካህናቱ እጆቼን ዘርግቼ /2/ የአእላፋት ዝማሬ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ወደ_ማደሪያው_ገብቼ_ዘማሪ_ቀሲስ_ወንድወሰን_በቀለ_2018_የአእላፋት_ዝማሬ_መዝሙር_በጃን.mp34.16 MB
❤ 122🕊 6🥰 4🔥 2
Photo unavailableShow in Telegram
💰እስካሁን 2,542 ብር ደርሰናል። አንድ ጽንሐሕ ለመግዛት 10,458 ብር ይቀረናል ፤የመጎናጸፊያው ገና አልተነካም። እያንዳንዷ ብር እዚህ ጋር ትልቅ ዋጋ አላት።
ለቁርስ ለምሳ ታጠፉት የነበረውን ገንዘብ ለገጠር አብያተ ክርስቲያናት አገልግሎት የሚውል መጎናጸፊያ እና ጽንሐሕ ገዝተን እንስጥ።
መባችሁን እግዚአብሔር ይቀበላችሁ።
ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር
🏦 1000142059022
የደረስንበትን ነገ እዚሁ አሳውቃለው።
❤ 54🥰 4
Photo unavailableShow in Telegram
እስካሁን 1,092 ብር ደርሰናል። አንድ ጽንሐሕ ለመግዛት 11,908 ብር ይቀረናል። መባችሁን እግዚአብሔር ይቀበላችሁ።
ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር
🏦 1000142059022
❤ 38😍 4🥰 3
Photo unavailableShow in Telegram
እስካሁን 400 ብር ደርሰናል።
መባችሁን እግዚአብሔር ይቀበላችሁ።
ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር
🏦 1000142059022
❤ 36
Photo unavailableShow in Telegram
እስካሁን 400 ብር ደርሰናል።
መባችሁን እግዚአብሔር ይቀበላችሁ።
ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር
🏦 1000142059022
Repost from ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
እግዚአብሔር ቢወድ እና ቢፈቅድ ለፊታችን ታኅሣሥ 19 የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል መጎናጸፊያ እና ጽንሐሕ ገዝተን ለአንድ የገጠር ቤተ ክርስቲያን ለመላክ አስበናል።
ጥሩ የሚባለው አንዱ መጎናጸፊያ ዋጋ 40ሺህ እና ከዚያ በላይ የሚባል ሲሆን ጽንሐሕ ደግሞ ከ13ሺ ጀምሮ ይጠራል።
በዚህም መሰረት እግዚአብሔር የረዳችሁ የፈቀደላችሁ እና የአቅማችሁን አስተዋጾ ማድረግ የምትፈልጉ በ @Zimaredawitmessanger ወይም +251 70 340 8851 ላይ መልዕክት ያስቀምጡልን። ከ1 ብር ጀምሮ የአቅማችሁን እርዳታ ማድረግ ትችላላችሁ። እኔ እንደ አንድ ክርስቲያን የዚህን ወር አስራቴን ለእነዚህ ሊዘጉ ለደረሱ የገጠር ቤተ ክርስቲያን ሰጥቻለው።
እግዚአብሔር ፈቅዶ ያሰብነው ገንዘብ ከሞላ ለዚህ በጎ ተግባር ከተሳተፋችሁ እና አ.አ ከምትኖሩ ወንድም እህቶች ጋር በጋራ የምንገዛ ሲሆን የተገዛበትን ደረሰኝ እዚሁ ለእናንተ የምናቀርብ ይሆናል።
ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር
🏦 1000142059022
❤ 70🔥 4
ሃሌ ሉያ በሰማያት ላለው
ሃሌ ሉያ በሰማያት ላለው
ዓለማትን ፈጥሮ ለሚንዛው
ዘምራለሁ እቀኝለታለሁ
ጌትነቱን ክብሩን አደንቃለሁ
አዝገናና ነው ክብርን የተመላ ድንቅ የሚያደርግ የለም ከእርሱ ሌላ ጉልበት ሁሉ ለስሙ ይሰግዳል ከአማልክት እርሱን ማን ይመስላል
አዝበልብሱ ዘርፍ መቅደሱ ተሞልቶ ስለ ክብሩ በገናው ተቃኝቶ ምስጋናችን በዕጣኑ ጢስ ሲያርግ ይመስጣል ያ የሰማዩ ሰርግ
እዝሲቀኝለት ዳዊት በማሕሌት ቅዱስ ሲሉ ሱራፌል በኀብረት ከዙፋኑ ምሕረት ይታወጃል በምድራችን ሰላም ፍቅር ይሰፍናል
አዝመሠወሪያው የእሳት ነበልባል ነው ሠረገላው ነፋስ ደመና ነው የእግዚአብሔር ሰልፍ የጸና ግንብ ነው ስሚፈሩት ኀይልና ብርታት ነው የአእላፋት ዝማሬ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ሃሌ_ሉያ_በሰማያት_ላለው_ዘማሪት_ለምለም_ከበደ_2018_የአእላፋት_ዝማሬ_መዝሙር_በጃን_ያሬድ.mp34.38 MB
❤ 110🕊 6
ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው
ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው
በመጠቅለያም ጠቀለለችው
የለምና ስፍራ ለእግዶች ማረፊያ
ግርግም አስተኛችው በከብቶች ማደሪያ/2/
አዝጨነቃት ጠበባት የዳዊት ከተማ የጌታ መወለድ ታምሩ ሲሰማ ወረደ መላአኩ ምስራች ሊያወራ የህፃኑ ክብር በምድር አበራ ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ ማይነገር ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር/2/
አዝሰባሰገል መጡ ከሩቅ ምስራቅ ሀገር ወርቅ እጣን ከርቤዉን ለርሱ ለመገበር በእናቱም እቅፍ አገኙት ህፃኑን ለዓለም ተናገሩ ንጉስ መወለዱን ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ ማይነገር ማርያምም በልቧ ትጠብቀዉ ነበር/2/
አዝየይሁዳ ምድር ምስጋናን ተሞላ ንጉስ መቷል እና ከናዝሬት ገሊላ ተዐምሩን ትናገር ቤተልሔም ታውራ ዝማሬ ሲውጣት ተረስቶ ቆጠራ ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ ማይነገር ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር/2/
አዝየማይታይ ታየ ተዳሰሰ እንደሰው በጠባቡ ደረት ማንን እንመስለው ገረማት ጥበቡ ታናሿን ሙሽራ ተዋህዷል እና ቃል ከሥጋ ጋራ ይህ ሚሰጢር ግሩም ነው ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር/2/ የአእላፋት ዝማሬ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ድንግል_ፈጣሪዋን_ወለደችው_ዘማሪ_ቴዎድሮስ_ዮሴፍ_2018_የአእላፋት_ዝማሬ_መዝሙር_በጃን_ያሬ.mp36.11 MB
❤ 158🕊 7😍 7🔥 5🥰 5
እግዚአብሔር ቢወድ እና ቢፈቅድ ለፊታችን ታኅሣሥ 19 የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል መጎናጸፊያ እና ጽንሐሕ ገዝተን ለአንድ የገጠር ቤተ ክርስቲያን ለመላክ አስበናል።
ጥሩ የሚባለው አንዱ መጎናጸፊያ ዋጋ 40ሺህ እና ከዚያ በላይ የሚባል ሲሆን ጽንሐሕ ደግሞ ከ13ሺ ጀምሮ ይጠራል።
በዚህም መሰረት እግዚአብሔር የረዳችሁ የፈቀደላችሁ እና የአቅማችሁን አስተዋጾ ማድረግ የምትፈልጉ በ @Zimaredawitmessanger ወይም +251 70 340 8851 ላይ መልዕክት ያስቀምጡልን። ከ1 ብር ጀምሮ የአቅማችሁን እርዳታ ማድረግ ትችላላችሁ። እኔ እንደ አንድ ክርስቲያን የዚህን ወር አስራቴን ለእነዚህ ሊዘጉ ለደረሱ የገጠር ቤተ ክርስቲያን ሰጥቻለው።
እግዚአብሔር ፈቅዶ ያሰብነው ገንዘብ ከሞላ ለዚህ በጎ ተግባር ከተሳተፋችሁ እና አ.አ ከምትኖሩ ወንድም እህቶች ጋር በጋራ የምንገዛ ሲሆን የተገዛበትን ደረሰኝ እዚሁ ለእናንተ የምናቀርብ ይሆናል።
❤ 79🕊 5
ታኅሣሥ ፭ /5/በዚች ቀን የኬልቅዩ ልጅ ታላቅ ነቢይ ናሆም አረፈ። ከስምዖን ነገድ የሆነ ይህ ጻድቅ ነቢይ ከነቢይ ሙሴ በትንቢቱ ዐሥራ ሰባተኛ ነው። በካህኑ ዮዳሄ በነገሥታቱ በኢዮአስ በአሜስያስ በልጁ በኢዝያን ዘመን ትንቢት ተናገረ ስለ ክህደታቸውና ጣዖታትን ስለማምለካቸውም የእስራኤልን ልጆች ገሠጻቸው። እግዚአብሔርም ምንም መሐሪና ይቅር ባይ ምሕረቱም የበዛ ቢሆን ካልተመለሱ ጠላቶቹን ይበቀላቸው ዘንድ እንደአለው ለሚቃወሙትም የፍርድ ቀን እንደሚጠብቃቸው በትንቢቱ ገለጠ። ዳግመኛም ስለ ከበረ የወንጌል ትምህርትና ስለ ሐዋርያት እንዲህ ብሎ ትንቢት ተናገረ የምሥራች የሚናገሩ ሰዎች እግራቸው እነሆ በተራራ ላይ ቁሟል ሰላምንም ይናገራሉ። ስለነነዌም ውኃና እሳት ያጠፉአት ዘንድ እንዳላቸው ትንቢት ተናግሮ እንደቃሉ ሆነ ከዕውነት መንገድ ተመልሰው በበደሉ ሰዎች ላይ እግዚአብሔር በውስጧ ታላቅ ንውጽውጽታ አድርጎ እሳትም አውርዶ እኩሌታዋን አቃጥሏልና። በንስሐ ጸንተው ወደ እግዚአብሔር የተመለሱትን ግን ከክፉ ነገር ከቶ ምንም ምን አልደረሰባቸውም። የትንቢቱንም ወራት ሲፈጽም እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ነቢይ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘለዓለሙአሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
❤ 116🕊 6
Photo unavailableShow in Telegram
ከቃል በላይ ያስረከብናቸው ከ8 በላይ ሳይቶች ማሳያ ናቸው
#ቴምርሪልስቴት #temerproperties #temerrealestate
📞+251912954919
‼️ሳር ቤት ቫቲካን
🎯65/35 አከፍፈል
👉2መኝታ 81ካሬ ሙሉ ክፍያ 6ሚሊዮን
👉2መኝታ 106ካሬ ሙሉ ክፍያ 7.9ሚሊዮን
👉3መኝታ 139ካሬሙሉ ክፍያ 10.3ሚሊዮን
🎯ቀስ ብሎ ለሚከፍል
👉2መኝታ 81ካሬ
20%ቅድመ ክፍያ 1.86ሚሊዮን
ሙሉ ክፍያ 9.3ሚሊዮን
👉2መኝታ 106ካሬ
20% ቅድመ ክፍያ 2.4ሚሊዮን
ሙሉ ክፍያ 12.1ሚሊዮን
👉3መኝታ 139ካሬ
20%ቅድመ ክፍያ 3.1ሚሊዮን
ሙሉ ክፍያ 15.9ሚሊዮን
‼️አዋሬ
🎯65/35 አከፍፈል
👉 ባለ 1 መኝታ = 78ካሬ = 5.5ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 117ካሬ = 8.3ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 137ካሬ = 9.7ሚሊዮን
🎯ቀስ ብሎ ለሚከፍል
👉 1መኝታ 78ካሬ
20%ቅድመ ክፍያ 1.7ሚሊዮን
ሙሉ ክፍያ = 8.5ሚሊዮን
👉3 መኝታ 117ካሬ
20%ቅድመ ክፍያ 2.6ሚሊዮን
ሙሉ ክፍያ 12.9ሚሊዮን
👉 157ካሬ =
20% ቅድመ ክፍያ 3.4ሚሊዮን
ሙሉ ክፍያ = 17.2ሚሊዮን
❗️ልብይበሉ ቀሪውን 80% በ 15ዙር ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት ይሆናል
30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ 15%_25% ቅናሽ አዘጋጅተናል
ለበለጠ መረጃ
👇👇👇👇👇👇
+251912954919
❤ 41
Repost from TgId: 2131344856
Photo unavailableShow in Telegram
የመጨረሻው የምዝገባ ቀን
ኮርሱ ነገ ምሽት 1:00 የሚጀምር
ሲሆን ምዝገባ ዛሬ ይጠናቀቃል
•••••••••••••••••••••••••••
• Laptop
• Internet
• በቂ ጊዜ
አላችሁ ?
አሁኑኑ ተመዝገቡ
@Greenbirdtechnology
√ በ300 ብር ቅድመ ክፍያ ብቻ
√ ጠቅላላ ክፍያ ደግሞ 4500
√ ቤታቹ ሆናቹ ብቻ
ብቁ ግራፊክስ ዲዛይነር ሁኑ
ደግሞም Video Editing Course
ተሸለሙ
1ኛ አሸናፊ 100% በነጻ
2ኛ አሸናፊ 50% በነጻ
3ኛ አሸናፊ 25% በነጻ
የኮርስ ቀናት
ቅዳሜ ምሽት 1:00 - 3:00
እሑድ ምሽት 1:00 - 3:00
3ኛ ቀን በብዙሃኑ ምርጫ ሆኖ
ምሽት 2:00 - 4:00
@greenbirdtechs
@greenbirdtechs
የለውጥዎ ክንፍ 🔑 🐥
❤ 42🔥 8😍 7🥰 4
ሰላም ለኪ
ሰላም ለኪ /2/ ማርያም ሰላም ለኪ /2/
ሰላም ለዝክርኪ ማርያም ለኪዳንኪ
አዝሰላም ለአንቺ ይሁን የኤልሳቤጥ ደስታ ሰላም ለኪ አምላክ የመረጠሽ የፍጥረት አለኝታ ሰላም ስኪ የልባችን ደስታ የተገለጠብሽ ሰላም ለኪ የአማኑኤል እናት ምስጋና ይድረስሽ ሰላም ለኪ
አዝንጽሕተ ንጹሐን እንከን የሌለብሽ ሰላሞ ስኪ መዓዛሽ ያማረ ጸጋን የተመላሽ ሰላም ለኪ ልቤ ተመሰጠ ዝናሽን ሲሰማ ሰላም ለኪ ውዴ ሙሽራዬ ብርሃናዊት ሻማ ሰላም ለኪ
አዝስምሽን ለልጅ ልጅ እስኪ እኔ ልናገር ሰላም ለኪ በአንቺ ያገኘሁት አለ ብዙ ነገር ሰላም ለኪ ሰላም ለኪ ድንግል እሰግድልሻለሁ ሰላም ለኪ የአንቺን እናትነት ለዓለም እነግራለሁ ሰላም ለኪ የአእላፋት ዝማሬ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ሰላም_ለኪ_ዘማሪ_ፍቃዱ_አማረ_2018_የአእላፋት_ዝማሬ_መዝሙር_በጃን_ያሬድ_ኅብረ_ዝማሬ_የተ.mp33.87 MB
❤ 124🥰 1
