fa
Feedback
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

رفتن به کانال در Telegram

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች፣ ስንክሳር፣ መዝሙራትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም አስተያየት @Zimaredawitmessanger ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል። ስለሚሰጡን ገንቢ ሃሳብ እናመሰግናለን። YouTube Page - https://bit.ly/2O1Z3d8 Facebook Page - https://www.fb.com/l/6lp1kJRRR

نمایش بیشتر
2025 سال در اعدادsnowflakes fon
card fon
166 277
مشترکین
-2324 ساعت
+187 روز
-1430 روز
آرشیو پست ها
Photo unavailableShow in Telegram
እግዚአብሔር ይመስገን። 🎉🎉🎉 እንኳን ደስ አላችሁ ለአንድ የገጠር ቤተ ክርስቲያን የሚሆን የአንድ ጽንሐሕ መግዣ ብር እና የአንድ መጎናጸፊያ ደግሞ ግማሽ ብር ሰብስበን ጨርሰናል። እስካሁን 39,260 ብር ደርሰናል። 🕯️የአንድ ጽንሐሕ ዋጋ = 13,000 ብር ⛪️የአንድ መጎናጸፊያ ዋጋ = 40,000 የአንድ መጎናጸፊያ መግዣ ለመሙላት 13,740 ብር ይቀረናል። እያንዳንዷ ብር እዚህ ጋር ትልቅ ዋጋ አላት። አስራታችሁን፣ ለቁርስ ለምሳ ታጠፉት የነበረውን ገንዘብ ለገጠር አብያተ ክርስቲያናት አገልግሎት የሚውል መጎናጸፊያ እና ጽንሐሕ ገዝተን እንስጥ። እስከ ታኅሣሥ 14 ቀን ድረስ ቃል መግባት ትችላላችሁ። መባችሁን እግዚአብሔር ይቀበላችሁ። ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 🏦 1000142059022 የአገልግሎቱን ሁኔታ ተረድታችሁ ጽንሐሕ እና መጎናጸፊያ በተመጣጣኝ ዋጋ የምታስረክቡ ነጋዴዎች ካላችሁ በዚህ @Zimaredawitmessanger ላይ መልዕክት ያስቀምጡልን። የደረስንበትን እዚሁ አሳውቃለው።
نمایش همه...
51🕊 2
Photo unavailableShow in Telegram
እንኳን ደስ አላችሁ ለአንድ የገጠር ቤተ ክርስቲያን አንድ ጽንሐሕ መግዣ ብር ሰብስበን ጨርሰናል። እግዚአብሔር ይመስገን። 🎉🎉🎉 እስካሁን 25,310 ብር ደርሰናል። አሁን ደሞ የመጎናጸፊያ ማሰባሰብ ጀምረናል። ለአንድ መጎናጸፊያ ገና 27,690 ብር ይቀረናል። እያንዳንዷ ብር እዚህ ጋር ትልቅ ዋጋ አላት። 🕯️የአንድ ጽንሐሕ ዋጋ = 13,000 ብር ⛪️የአንድ መጎናጸፊያ ዋጋ = 40,000 ለቁርስ ለምሳ ታጠፉት የነበረውን ገንዘብ ለገጠር አብያተ ክርስቲያናት አገልግሎት የሚውል መጎናጸፊያ እና ጽንሐሕ ገዝተን እንስጥ። እስከ ታኅሣሥ 14 ቀን ድረስ ቃል መግባት ትችላላችሁ። መባችሁን እግዚአብሔር ይቀበላችሁ። ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 🏦 1000142059022 የአገልግሎቱን ሁኔታ ተረድታችሁ ጽንሐሕ እና መጎናጸፊያ በተመጣጣኝ ዋጋ የምታስረክቡ ነጋዴዎች ካላችሁ በዚህ @Zimaredawitmessanger ላይ መልዕክት ያስቀምጡልን። የደረስንበትን እዚሁ አሳውቃለው።
نمایش همه...
73
Photo unavailableShow in Telegram
እንኳን ደስ አላችሁ ለአንድ የገጠር ቤተ ክርስቲያን አንድ ጽንሐሕ መግዣ ብር ሰብስበን ጨርሰናል። እግዚአብሔር ይመስገን። 🎉🎉🎉 እስካሁን 17,110 ብር ደርሰናል። አሁን ደሞ የመጎናጸፊያ ማሰባሰብ ጀምረናል። ለአንድ መጎናጸፊያ ገና 35,890 ብር ይቀረናል። እያንዳንዷ ብር እዚህ ጋር ትልቅ ዋጋ አላት። 🕯️የአንድ ጽንሐሕ ዋጋ = 13,000 ብር ⛪️የአንድ መጎናጸፊያ ዋጋ = 40,000 ለቁርስ ለምሳ ታጠፉት የነበረውን ገንዘብ ለገጠር አብያተ ክርስቲያናት አገልግሎት የሚውል መጎናጸፊያ እና ጽንሐሕ ገዝተን እንስጥ። እስከ ታኅሣሥ 14 ቀን ድረስ ቃል መግባት ትችላላችሁ። መባችሁን እግዚአብሔር ይቀበላችሁ። ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 🏦 1000142059022 የአገልግሎቱን ሁኔታ ተረድታችሁ ጽንሐሕ እና መጎናጸፊያ በተመጣጣኝ ዋጋ የምታስረክቡ ነጋዴዎች ካላችሁ በዚህ @Zimaredawitmessanger ላይ መልዕክት ያስቀምጡልን። የደረስንበትን እዚሁ አሳውቃለው።
نمایش همه...
11😍 3🕊 2
Photo unavailableShow in Telegram
እንደምን አደራችሁ? እግዚአብሔር ይመስገን እስካሁን 12,110 ብር ደርሰናል። አንድ ጽንሐሕ ለመግዛት 890 ብር ይቀረናል ፤የመጎናጸፊያው ገና አልተነካም። እያንዳንዷ ብር እዚህ ጋር ትልቅ ዋጋ አላት። 🕯️የአንድ ጽንሐሕ ዋጋ = 13,000 ብር ⛪️የአንድ መጎናጸፊያ ዋጋ = 40,000 ለቁርስ ለምሳ ታጠፉት የነበረውን ገንዘብ ለገጠር አብያተ ክርስቲያናት አገልግሎት የሚውል መጎናጸፊያ እና ጽንሐሕ ገዝተን እንስጥ። መባችሁን እግዚአብሔር ይቀበላችሁ። ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 🏦 1000142059022 የአገልግሎቱን ሁኔታ ተረድታችሁ ጽንሐሕ እና መጎናጸፊያ በተመጣጣኝ ዋጋ የምታስረክቡ ነጋዴዎች ካላችሁ በዚህ @Zimaredawitmessanger ላይ መልዕክት ያስቀምጡልን። የደረስንበትን እዚሁ አሳውቃለው።
نمایش همه...
38
​​​​ታኅሣሥ 6 ቅድስት አርሴማ(ቅዳሴ ቤቷ) እናታችን ቅድስት አርሴማን በምን እንመስላታለን? እርሷ በአድማስ ላይ ተቀምጦ እንደሚያበራ እንቁ ናትና ክብሯ ብዙ ነው።  መድኃኒታችን ክርስቶስ በወንጌል እንዳለው "በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሠወር አይቻላትምና። "(ማቴ. ፭፥፲፩) የሰማዕቷ ሕይወት በፊታችን እንደ ብርሃን ተገልጦ ይታያል። ቅድስት አርሴማ እንደ ልጅ ወላጆቿን በመታዘዝ ደስ ያሰኘች ቡርክት ናት። ቅድስት አርሴማ ይህ ቀረሽ የማይሏት ውብ ናት። ቅድስት አርሴማ ድንግል ናት። ቅድስት አርሴማ ባሕታዊት ጻድቅ ናት። ቅድስት አርሴማ ኃያል ሰማዕት ናት። ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ፦ አበው በትውፊት እንደ ነገሩን ቅዱሱ ጐርጐርዮስ የታላቋ ሰማዕት ቅድስት አርሴማ ትልቅ ወንድም ነው። በዜና ሰማዕታት ተጽፎ እንደሚገኘው በዚያ የመከራ ዘመን ቅዱስ ጐርጐርዮስ ሦስት ኃላፊነቶች ነበሩበት፦ ፩.ቅድስት አርሴማን ጨምሮ ደናግሉን ማጽናት፤ ፪.ትምሕርተ ቤተ ክርስቲያንን በሚገባ ማጥናት፤ ፫.የሚመጣውን መከራ ለመቀበል ራሱን ማዘጋጀት። ቅዱሱ ሦስቱንም ኃላፊነቶች በሚገባ በመወጣቱ ከራሱ አልፎ ለሌሎቹ አርአያ መሆን ቻለ። ያቺን ንጽሕት አርበኛ ቅድስት አርሴማንም አጽንቶ የደናግሉ መሪ አደረጋት።  መከራው ገፍቶ እስከ መጣበት ጊዜ በአንድ የደናግል ገዳም ውስጥ ሆነው ይጸልዩ፣ ይጾሙ፣ ገዳማዊ ሥራንም ይሠሩ ነበር። ለዚህም ነው ቅድስት አርሴማና ቅዱስ ጐርጐርዮስን ጻድቃን የምንላቸው። በኋላ ግን ማኅደረ ሰይጣን ዲዮቅልጢያኖስ በመልኳ ተማርኮ ቅድስት አርሴማን ካላገባሁ በማለቱ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ድንግሏን አርሴማን ጨምሮ ክርስቲያኖችን ይዞ ወደ አርማንያ ተሰደደ። በአርማንያም በአንድ ገዳም ውስጥ ተደብቀው በጾምና በጸሎት ለጥቂት ጊዜ ቆዩ። ነገር ግን ረሃብ ፈጃቸው። የሚላስ የሚቀመስ ነገር በአካባቢው ባለ መኖሩ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ወደ ከተማ ለመውጣት ተገደደ። በዚያም በድርጣድስ ቤተ መንግሥት ውስጥ ባርነት ተቀጠረ። በሚያገኛት ገንዘብም ወገኖቹን ይረዳ ነበር። መከራው ግን አለቀቃቸውም። ርጉም ዲዮቅልጢያኖስ ቅዱሳኑ ወደ አርማንያ መሔዳቸውን ስለ ሰማ ይዞ እንዲልክለት ድርጣድስን ላከው። ድርጣድስ ግን ቅድስት አርሴማን ባያት ጊዜ ከውበቷ የተነሳ መታገስ ባለመቻሉ "ካላገባሁሽ" አላት። ድንግሊቱ ግን "እኔ የክርስቶስ ሙሽራ ነኝ፤ አይሆንም።" አለችው። ሊያስፈራራት ሞከረ። ዓይኗ እያየ ደናግሉን ጨፈጨፋቸው። አልሳካልህ ቢለው በአደባባይ በግድ ሊያገባት ቢሞክር እጁን ጠምዝዛ በሰው ሁሉ ፊት መሬት ላይ ጣለችው። እጅግ ስላፈረ አስገረፋት፣ አሰቃያት፣ ዓይኗንም አወጣ። በመጨረሻም አንገቷን አስቆርጦ ከሰማዕታቱ ጋር ተራራ ላይ ጣላት። ከነገር ሁሉ በኋላ ድርጣድስና ባለሟሎቹ ለአደን በሔዱበት ርኩስ መንፈስ ወደ አውሬነት (እሪያነት) ቀየራቸው። የንጉሡ እንስሳ (አውሬ) መሆን በአርማንያ ታላቅ ድንጋጤን ፈጠረ። የንጉሡ እኅት ስታለቅስ በራእይ "ለእመ ኢያዕረግምዎ ለጐርጐርዮስ አልብክሙ ድኂን - ጐርጐርዮስን ከተቀበረበት ካላወጣችሁት አትድኑም።" አላቸው። ወዲያውም ቆፍረው አወጡት። ቅዱሱ እንደ ወጣ ዕረፍትን አልፈለገም። ለአሥራ አምስት ዓመታት ቀባሪ አጥቶ የተበተነውን የቅድስት አርሴማንና የሰማዕታቱን አጽም ሰብስቦ በክብር አኖረው። ድርጣድስና ባለሟሎቹንም ወደ በርሃ ሒዶ ፈወሳቸው። የሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ አጽም በአሥራ አራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከሌሎች ሰማዕታት አጽም ጋር ኢትዮጵያ እንደ መጣ አባቶቻችን በትውፊት ነግረውናል። ለዚህም ነው ቡርክቷ እናታችን ከሌሎች ሃገራት ለይታ ለኢትዮጵያውያን ልዩ ፍቅር ያላት።  በዋናው ገዳሟ (ወሎ /ኩላማሶ/ ስባ ውስጥ የሚገኝ ነው።) ጨምሮ ስሟ በተጠራበት ሁሉ ኃይልን ታደርጋለችና። ነገር ግን ወንድሞቼና እኅቶቼ በቅድስቷ እናታችን ስም የሚነግዱ ሥጋውያን ሰዎች በዝተዋልና እንጠንቀቅ። የሰማዕቷ ክብር ብዙ ነውና በሕልም ላይ ብቻ አንታመን። አባ እንጦንስ እንዳሉት "በሕልሙ የሚታመን ሰው ከንቱ ነውና።" (መዝ. ፸፭፥፭) በዚህ ዕለት ከሰማዕቷ ጋር የመንፈስ እናቷን ቅድስት አጋታን ልናስባት ይገባናል። ይህች እናት እመ ምኔት ስትሆን ቅድስት አርሴማን ታስተምራት፣ ታጸናት፣ ከጐኗም ትቆምላት ነበር። ረሃቧን፣ ጥሟን፣ ስደቷን፣ መከራዋንም ሁሉ አብራት ተሳትፋለች። በፍጻሜውም አብራት ተሰይፋለች። ይህች ዕለት ለቅድስት አርሴማና ለተከታዮቿ ሰማዕታት የፍልሰትና የቅዳሴ ቤት መታሰቢያ ናት።  ወስብሐት ለእግዚአብሔር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
نمایش همه...
193🕊 7🥰 2
ወደ ማደሪያው ገብቼ ወደ ማደሪያው ገብቼ ልስገድ ለእግዚአብሔር ምስጋናንም ላቅርብ ስለ ስሙ ክብር አድርጎልኛልና አመሰግነዋለሁ በዐፀደ መቅደሱም እሰግድለታለሁ ከፊቱ ለመቆም ማልጄ እነሣለሁ /2/
እዝ
በመከራዬ ቀን ሆኖኛል መከታ ቤቱ ተገኝቼ በፍጹም ደስታ የከንፈሬን ፍሬ ልሠዋ በእልልታ /2/
አዝ
አሥር አውታር ባለው በዳዊት በገና በመላእክቱ ፊት ለማቅረብ ምስጋና የአፌንም ነገር ሰምተኸኛልና /2/
አዝ
ለስሙ ልንበርከክ ለእርሱ እንደሚገባ ስዕስቴን ልፈጽም ላቅርበለት መብዓ ወደ አደባባዩ በምስጋና ልግባ /2/
እዝ
አሸበሽባለሁ ድምፄን አሰምቼ በቤተ መቅደሱ ሌሊት ተገኝቼ እንደ ካህናቱ እጆቼን ዘርግቼ /2/ የአእላፋት ዝማሬ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
نمایش همه...
ወደ_ማደሪያው_ገብቼ_ዘማሪ_ቀሲስ_ወንድወሰን_በቀለ_2018_የአእላፋት_ዝማሬ_መዝሙር_በጃን.mp34.16 MB
118🕊 6🥰 3🔥 2
Photo unavailableShow in Telegram
💰እስካሁን 2,542 ብር ደርሰናል። አንድ ጽንሐሕ ለመግዛት 10,458 ብር ይቀረናል ፤የመጎናጸፊያው ገና አልተነካም። እያንዳንዷ ብር እዚህ ጋር ትልቅ ዋጋ አላት። ለቁርስ ለምሳ ታጠፉት የነበረውን ገንዘብ ለገጠር አብያተ ክርስቲያናት አገልግሎት የሚውል መጎናጸፊያ እና ጽንሐሕ ገዝተን እንስጥ። መባችሁን እግዚአብሔር ይቀበላችሁ። ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 🏦 1000142059022 የደረስንበትን ነገ እዚሁ አሳውቃለው።
نمایش همه...
54🥰 4
Photo unavailableShow in Telegram
እስካሁን 1,092 ብር ደርሰናል። አንድ ጽንሐሕ ለመግዛት 11,908 ብር ይቀረናል። መባችሁን እግዚአብሔር ይቀበላችሁ። ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 🏦 1000142059022
نمایش همه...
38😍 4🥰 3
Photo unavailableShow in Telegram
እስካሁን 400 ብር ደርሰናል። መባችሁን እግዚአብሔር ይቀበላችሁ። ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 🏦 1000142059022
نمایش همه...
36
Photo unavailableShow in Telegram
እስካሁን 400 ብር ደርሰናል። መባችሁን እግዚአብሔር ይቀበላችሁ። ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 🏦 1000142059022
نمایش همه...
እግዚአብሔር ቢወድ እና ቢፈቅድ ለፊታችን ታኅሣሥ 19 የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል መጎናጸፊያ እና ጽንሐሕ ገዝተን ለአንድ የገጠር ቤተ ክርስቲያን ለመላክ አስበናል። ጥሩ የሚባለው አንዱ መጎናጸፊያ ዋጋ 40ሺህ እና ከዚያ በላይ የሚባል ሲሆን ጽንሐሕ ደግሞ ከ13ሺ ጀምሮ ይጠራል። በዚህም መሰረት እግዚአብሔር የረዳችሁ የፈቀደላችሁ እና የአቅማችሁን አስተዋጾ ማድረግ የምትፈልጉ በ @Zimaredawitmessanger ወይም +251 70 340 8851 ላይ መልዕክት ያስቀምጡልን። ከ1 ብር ጀምሮ የአቅማችሁን እርዳታ ማድረግ ትችላላችሁ። እኔ እንደ አንድ ክርስቲያን የዚህን ወር አስራቴን ለእነዚህ ሊዘጉ ለደረሱ የገጠር ቤተ ክርስቲያን ሰጥቻለው። እግዚአብሔር ፈቅዶ ያሰብነው ገንዘብ ከሞላ ለዚህ በጎ ተግባር ከተሳተፋችሁ እና አ.አ ከምትኖሩ ወንድም እህቶች ጋር በጋራ የምንገዛ ሲሆን የተገዛበትን ደረሰኝ እዚሁ ለእናንተ የምናቀርብ ይሆናል። ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 🏦 1000142059022
نمایش همه...
70🔥 4
ሃሌ ሉያ በሰማያት ላለው ሃሌ ሉያ በሰማያት ላለው ዓለማትን ፈጥሮ ለሚንዛው ዘምራለሁ እቀኝለታለሁ ጌትነቱን ክብሩን አደንቃለሁ
አዝ
ገናና ነው ክብርን የተመላ ድንቅ የሚያደርግ የለም ከእርሱ ሌላ ጉልበት ሁሉ ለስሙ ይሰግዳል ከአማልክት እርሱን ማን ይመስላል
አዝ
በልብሱ ዘርፍ መቅደሱ ተሞልቶ ስለ ክብሩ በገናው ተቃኝቶ ምስጋናችን በዕጣኑ ጢስ ሲያርግ ይመስጣል ያ የሰማዩ ሰርግ
እዝ
ሲቀኝለት ዳዊት በማሕሌት ቅዱስ ሲሉ ሱራፌል በኀብረት ከዙፋኑ ምሕረት ይታወጃል በምድራችን ሰላም ፍቅር ይሰፍናል
አዝ
መሠወሪያው የእሳት ነበልባል ነው ሠረገላው ነፋስ ደመና ነው የእግዚአብሔር ሰልፍ የጸና ግንብ ነው ስሚፈሩት ኀይልና ብርታት ነው የአእላፋት ዝማሬ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
نمایش همه...
ሃሌ_ሉያ_በሰማያት_ላለው_ዘማሪት_ለምለም_ከበደ_2018_የአእላፋት_ዝማሬ_መዝሙር_በጃን_ያሬድ.mp34.38 MB
110🕊 6
ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው በመጠቅለያም ጠቀለለችው የለምና ስፍራ ለእግዶች ማረፊያ ግርግም አስተኛችው በከብቶች ማደሪያ/2/
አዝ
ጨነቃት ጠበባት የዳዊት ከተማ የጌታ መወለድ ታምሩ ሲሰማ ወረደ መላአኩ ምስራች ሊያወራ የህፃኑ ክብር በምድር አበራ ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ ማይነገር ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር/2/
አዝ
ሰባሰገል መጡ ከሩቅ ምስራቅ ሀገር ወርቅ እጣን ከርቤዉን ለርሱ ለመገበር በእናቱም እቅፍ አገኙት ህፃኑን ለዓለም ተናገሩ ንጉስ መወለዱን ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ ማይነገር ማርያምም በልቧ ትጠብቀዉ ነበር/2/
አዝ
የይሁዳ ምድር ምስጋናን ተሞላ ንጉስ መቷል እና ከናዝሬት ገሊላ ተዐምሩን ትናገር ቤተልሔም ታውራ ዝማሬ ሲውጣት ተረስቶ ቆጠራ ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ ማይነገር ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር/2/
አዝ
የማይታይ ታየ ተዳሰሰ እንደሰው በጠባቡ ደረት ማንን እንመስለው ገረማት ጥበቡ ታናሿን ሙሽራ ተዋህዷል እና ቃል ከሥጋ ጋራ ይህ ሚሰጢር ግሩም ነው ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር/2/ የአእላፋት ዝማሬ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
نمایش همه...
ድንግል_ፈጣሪዋን_ወለደችው_ዘማሪ_ቴዎድሮስ_ዮሴፍ_2018_የአእላፋት_ዝማሬ_መዝሙር_በጃን_ያሬ.mp36.11 MB
158🕊 7😍 7🔥 5🥰 5
እግዚአብሔር ቢወድ እና ቢፈቅድ ለፊታችን ታኅሣሥ 19 የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል መጎናጸፊያ እና ጽንሐሕ ገዝተን ለአንድ የገጠር ቤተ ክርስቲያን ለመላክ አስበናል። ጥሩ የሚባለው አንዱ መጎናጸፊያ ዋጋ 40ሺህ እና ከዚያ በላይ የሚባል ሲሆን ጽንሐሕ ደግሞ ከ13ሺ ጀምሮ ይጠራል። በዚህም መሰረት እግዚአብሔር የረዳችሁ የፈቀደላችሁ እና የአቅማችሁን አስተዋጾ ማድረግ የምትፈልጉ በ @Zimaredawitmessanger ወይም +251 70 340 8851 ላይ መልዕክት ያስቀምጡልን። ከ1 ብር ጀምሮ የአቅማችሁን እርዳታ ማድረግ ትችላላችሁ። እኔ እንደ አንድ ክርስቲያን የዚህን ወር አስራቴን ለእነዚህ ሊዘጉ ለደረሱ የገጠር ቤተ ክርስቲያን ሰጥቻለው። እግዚአብሔር ፈቅዶ ያሰብነው ገንዘብ ከሞላ ለዚህ በጎ ተግባር ከተሳተፋችሁ እና አ.አ ከምትኖሩ ወንድም እህቶች ጋር በጋራ የምንገዛ ሲሆን የተገዛበትን ደረሰኝ እዚሁ ለእናንተ የምናቀርብ ይሆናል።
نمایش همه...
79🕊 5
ታኅሣሥ ፭ /5/
በዚች ቀን የኬልቅዩ ልጅ ታላቅ ነቢይ ናሆም አረፈ። ከስምዖን ነገድ የሆነ ይህ ጻድቅ ነቢይ ከነቢይ ሙሴ በትንቢቱ ዐሥራ ሰባተኛ ነው። በካህኑ ዮዳሄ በነገሥታቱ በኢዮአስ በአሜስያስ በልጁ በኢዝያን ዘመን ትንቢት ተናገረ ስለ ክህደታቸውና ጣዖታትን ስለማምለካቸውም የእስራኤልን ልጆች ገሠጻቸው። እግዚአብሔርም ምንም መሐሪና ይቅር ባይ ምሕረቱም የበዛ ቢሆን ካልተመለሱ ጠላቶቹን ይበቀላቸው ዘንድ እንደአለው ለሚቃወሙትም የፍርድ ቀን እንደሚጠብቃቸው በትንቢቱ ገለጠ። ዳግመኛም ስለ ከበረ የወንጌል ትምህርትና ስለ ሐዋርያት እንዲህ ብሎ ትንቢት ተናገረ የምሥራች የሚናገሩ ሰዎች እግራቸው እነሆ በተራራ ላይ ቁሟል ሰላምንም ይናገራሉ። ስለነነዌም ውኃና እሳት ያጠፉአት ዘንድ እንዳላቸው ትንቢት ተናግሮ እንደቃሉ ሆነ ከዕውነት መንገድ ተመልሰው በበደሉ ሰዎች ላይ እግዚአብሔር በውስጧ ታላቅ ንውጽውጽታ አድርጎ እሳትም አውርዶ እኩሌታዋን አቃጥሏልና። በንስሐ ጸንተው ወደ እግዚአብሔር የተመለሱትን ግን ከክፉ ነገር ከቶ ምንም ምን አልደረሰባቸውም። የትንቢቱንም ወራት ሲፈጽም እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ነቢይ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘለዓለሙአሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
نمایش همه...
116🕊 6
Photo unavailableShow in Telegram
ከቃል በላይ ያስረከብናቸው ከ8 በላይ ሳይቶች ማሳያ ናቸው #ቴምርሪልስቴት #temerproperties #temerrealestate 📞+251912954919 ‼️ሳር ቤት ቫቲካን 🎯65/35 አከፍፈል 👉2መኝታ 81ካሬ ሙሉ ክፍያ 6ሚሊዮን 👉2መኝታ 106ካሬ ሙሉ ክፍያ 7.9ሚሊዮን 👉3መኝታ 139ካሬሙሉ ክፍያ 10.3ሚሊዮን 🎯ቀስ ብሎ ለሚከፍል 👉2መኝታ 81ካሬ 20%ቅድመ ክፍያ 1.86ሚሊዮን ሙሉ ክፍያ 9.3ሚሊዮን 👉2መኝታ 106ካሬ 20% ቅድመ ክፍያ 2.4ሚሊዮን ሙሉ ክፍያ 12.1ሚሊዮን 👉3መኝታ 139ካሬ 20%ቅድመ ክፍያ 3.1ሚሊዮን ሙሉ ክፍያ 15.9ሚሊዮን ‼️አዋሬ 🎯65/35 አከፍፈል 👉 ባለ 1 መኝታ = 78ካሬ = 5.5ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 117ካሬ = 8.3ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 137ካሬ = 9.7ሚሊዮን 🎯ቀስ ብሎ ለሚከፍል 👉 1መኝታ 78ካሬ 20%ቅድመ ክፍያ 1.7ሚሊዮን ሙሉ ክፍያ = 8.5ሚሊዮን                  👉3 መኝታ 117ካሬ 20%ቅድመ ክፍያ  2.6ሚሊዮን ሙሉ ክፍያ 12.9ሚሊዮን 👉 157ካሬ = 20% ቅድመ ክፍያ 3.4ሚሊዮን ሙሉ ክፍያ = 17.2ሚሊዮን  ❗️ልብይበሉ ቀሪውን 80% በ 15ዙር  ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ  ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት ይሆናል 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ 15%_25% ቅናሽ አዘጋጅተናል ለበለጠ መረጃ 👇👇👇👇👇👇 +251912954919
نمایش همه...
41
Repost from TgId: 2131344856
Photo unavailableShow in Telegram
የመጨረሻው የምዝገባ ቀን ኮርሱ ነገ ምሽት 1:00 የሚጀምር ሲሆን ምዝገባ ዛሬ ይጠናቀቃል ••••••••••••••••••••••••••• •  Laptop •  Internet •  በቂ ጊዜ አላችሁ ? አሁኑኑ ተመዝገቡ @Greenbirdtechnology √ በ300 ብር ቅድመ ክፍያ ብቻ √ ጠቅላላ ክፍያ ደግሞ 4500 √  ቤታቹ ሆናቹ ብቻ ብቁ ግራፊክስ ዲዛይነር ሁኑ ደግሞም Video Editing Course ተሸለሙ 1ኛ አሸናፊ 100% በነጻ 2ኛ አሸናፊ 50% በነጻ 3ኛ አሸናፊ 25% በነጻ የኮርስ ቀናት ቅዳሜ ምሽት 1:00 - 3:00 እሑድ ምሽት 1:00 - 3:00 3ኛ ቀን በብዙሃኑ ምርጫ ሆኖ ምሽት 2:00 - 4:00 @greenbirdtechs @greenbirdtechs የለውጥዎ ክንፍ 🔑 🐥
نمایش همه...
42🔥 8😍 7🥰 4
ሰላም ለኪ ሰላም ለኪ /2/ ማርያም ሰላም ለኪ /2/ ሰላም ለዝክርኪ ማርያም ለኪዳንኪ
አዝ
ሰላም ለአንቺ ይሁን የኤልሳቤጥ ደስታ ሰላም ለኪ አምላክ የመረጠሽ የፍጥረት አለኝታ  ሰላም ስኪ የልባችን ደስታ የተገለጠብሽ ሰላም ለኪ የአማኑኤል እናት ምስጋና ይድረስሽ ሰላም ለኪ
አዝ
ንጽሕተ ንጹሐን እንከን የሌለብሽ ሰላሞ ስኪ መዓዛሽ ያማረ ጸጋን የተመላሽ ሰላም ለኪ ልቤ ተመሰጠ ዝናሽን ሲሰማ ሰላም ለኪ ውዴ ሙሽራዬ ብርሃናዊት ሻማ ሰላም ለኪ
አዝ
ስምሽን ለልጅ ልጅ እስኪ እኔ ልናገር ሰላም ለኪ በአንቺ ያገኘሁት አለ ብዙ ነገር ሰላም ለኪ ሰላም ለኪ ድንግል እሰግድልሻለሁ ሰላም ለኪ የአንቺን እናትነት ለዓለም እነግራለሁ ሰላም ለኪ የአእላፋት ዝማሬ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
نمایش همه...
ሰላም_ለኪ_ዘማሪ_ፍቃዱ_አማረ_2018_የአእላፋት_ዝማሬ_መዝሙር_በጃን_ያሬድ_ኅብረ_ዝማሬ_የተ.mp33.87 MB
124🥰 1
ከዚህም በኋላ ሐዋርያ እንድርያስ ርግብን ጠርቶ ዕድሜሽ ስንት ነው አላት እርሷም ስምንት ዓመት ነው አለችው ። እርሱም ለደቀ መዝሙሬ ስለታዘዝሽ ወደ ዱር ሒጂ ለዓለም ሰዎች ከመገዛት ነጻ ሁኚ አላት ወዲያውኑ ሔደች ሕዝቡም ይህን ድንቅ ሥራ አይተው አምነው ሁሉም የክርስትና ጥምቀትን ተጠመቁ ። ከዚህም በኋላ ከእርሳቸው ዘንድ ወጥቶ አክራድ አክሲስ አክሳስያ ሴኒፎሮስም ወደ ተባሉ አገሮች ሒዶ አስተማረ ከሐዋርያ በርተሎሜዎስም ጋር ተገናኝቶ ጋዝሪኖስ ወደ ሚባል አገር በአንድነት ሔዱ የሀገር ሰዎች እግዚአብሔርን ወደ ማወቅ እስከተመለሱ ድረስ ረዳት ከተደረገላቸው ገጸ ከልብ ጋር ገብተው ወንጌልን ሰበኩ ድንቅ ተአምራትንም አደረጉ ። ከዚህም በኋላ ሐዋርያ እንድርያስ ወደ ሌሎች አገሮች ሒዶ አስተማረ በፍጻሜውም ወደ አንዲት አገር ገብቶ ቅዱስ ወንጌልን ሰበከ የዚያች አገርሰዎች ግን እጅግ የከፉ ስለሆኑ ትምህርቱን አልተቀበሉትም ። ከቅዱስ ሐዋርያ እንድርያስም ድንቅ ተአምራትን ስለአዩ ያመኑ አሉ ያላመኑ ግን ወደእነርሱ እንዲመጣና እንዲገድሉት በቅዱስ እንድርያስ ላይ ክፉ ምክርን መክረው በተንኩል ወደርሱ መልእክተኞችን ላኩ መልእክተኞችም ወደ ቅዱስ እንድርያስ ሲደርሱ ማራኪ የሆነ ትምህርቱን ሰሙ ፊቱንም ብርሃን ሁኖ አዩትና ክብር ይግባውና በጌታችን አመኑ ደቀ መዝሙሮችም ሆኑት ወደላኳቸውም አልተመለሱም ። ሁለተኛም በእሳት ሊአቃጥሉት ተማከሩና ተሰብስበው ወደርሱ ሔዱ እርሱ ግን የልባችሁን ክፋት ትታችሁ ትድኑ ዘንድ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እመኑ ይህ ካልሆነ ግን ለእኔ ያላችኋት ይቺ እሳት እናንተን ትበላለች አላቸው ። ቃሉንም ባልሰሙ ጊዜ ከሰማይ እሳት ወርዳ እንድታቃጥላቸው ክብር ይግባውና ጌታችንን ለመነው ወዲያውኑ እሳት ወርዳ አቃጠለቻቸው በዚያች አገር አውራጃዎች ሁሉ ዜናው ተሰማ እጅግም ፈርተው ብዙዎች ክብርይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ ። የጣዖታት አገልጋዮች ግን ይህን ሁሉ ድንቅ ተአምራት አይተው አላመኑም ቅዱስ ሐዋርያ እንድርያስን ሊገድሉት ፈለጉት እንጂ ። ከዚህም በኋላ ተሰብስበው መጡና ቅዱስ ሐዋርያ እንድርያስን ይዘው ወሰዱት ታላቅ ግርፋትንም ገርፈው በከተማው ሁሉ ራቁቱን አዙረው ከወህኒ ቤት ጨመሩት በማግሥቱ የሚሰቅሉትን ሰው ልማዳቸው እንዲሁ ነውና ሰው ሊገድሉ በሚሹ ጊዜ ወስደው በእንጨት ላይ ይሰቅሉታል እስከሚሞትም ድረስ በደንጊያዎች ይወግሩታል ። በዚያችም ሌሊት የተመሰገነ ሐዋርያ አባታችን እንድርያስ እንደ ፊተኞቹ እሳት ወርዳ እንድትበላቸው ክብር ይግባውና ጌታችንን ክርስቶስን ለመነው ክብርይግባውና ጌታችንም ተገለጠለትና ከዚህ ዓለም የምትለይበት ጊዜ ደርሷልና አትዘን አለው ሰላምታም ሰጥቶት ከእርሱ ተሠወረ የተመሰገነ የሐዋርያ እንድርያስም ልቡናው ፈጽማ ደስ አላት ። ንጋትም በሆነ ጊዜ ወስደው በዕንጨት ላይ ሰቀሉት እስከ ሞተ ድረስም በደንጊያዎች ወገሩት አማንያን ሰዎችም መጥተው ሥጋውን ወስደው ገንዘው ቀበሩት ከእርሱም ታላላቅ የሆኑ አስደናቂዎች ተአምራት ተገለጡ ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ በሐዋርያ እንድርያስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን ። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
نمایش همه...
132🕊 9🔥 4
ታህሳስ ፬ /4/
በዚች ቀን የሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ ወንድም የተመሰገነ ቅዱስ ሐዋርያ እንድርያስ በምስክርነት አረፈ ። ለዚህም ቅዱስ ይሰብክ ዘንድ ዕጣው በልዳ ሀገር ወጣ ከእርሷም ብዙዎች በቅዱስ ጴጥሮስ ትምህርት አምነው ነበር አንደበቱ የሚጥም በሥራው ሁሉና በአምልኮቱ የተወደደ ያማረ ደቀ መዝሙሩ ፊልሞና አብሮት ነበር ሐዋርያ እንድርያስም ከፍ ካለ ቦታ ላይ ወጥቶ ጣዕም ባለው አንደበቱ ከቅዱሳት መጻሕፍት እንዲአነብ አዘዘው ። የጣዖታት ካህናትም የሐዋርያ እንድርያስን መምጣት በሰሙ ጊዜ አማልክቶቻቸውን ይረግሙ እንደሆነ ሊጣሏቸው ሽተው የጦር መሳሪያቸውን ይዘው መጡ ። በዚያንም ጊዜ ፊልሞና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከወርቅና ከብር የሰው እጅ ሥራ የሆኑ የአሕዛብ አማልክቶቻቸው አፍ አላቸው አይናገሩም፣ ዐይን አላቸው አያዩም፣ ጆሮ አላቸው አይሰሙም፣ አፍንጫ አላቸው አያሸቱም፣ እጅ አላቸው አይዳስሱም፣ እግር አላቸው አይሔዱም፣ በጉሮሮአቸውም አይናገሩም፣ የሚሠሩአቸውና የሚኣምኑባቸው ሁሉ እንደእነርሱ ይሁኑ እያለ ሲያነብ ሰሙት ስለ ቃሉ ጣዕምና ስለ ንባቡ ማማር ልባቸው ከክህደት ማሠሪያ ተፈታ ወደ ቤተ ክርስቲያንም ገብተው ከሐዋርያ እንድርያስ እግር በታች ሰገዱ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስም አመኑ እርሱም የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት አስተምሮ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው ከእሳቸውም ጋር ጣዖትን ከሚያመልኩ ውስጥ ብዙዎች አምነው ተጠመቁ ። በዚያ ወራትም እንዲህ ሆነ በልዳ አገር አቅራቢያ ስሙ ዮሐንስ የሚባል አንድ ቄስ ነበረ ለእርሱም አንድ ልጅ አለው እርሱም ከባልንጀራው ጋር ሲጫወት በድንገት ገደለው የሟች አባትም ልጄን የገደለ ልጅህን አሳልፈህ ስጠኝ ሲል ቀሲስ ዮሐንስን ያዘው ቀሲስ ዮሐንስም የሀገር ሰዎችን ሔጄ ሐዋርያ እንድርያስን እስከማመጣው ዋስ ሁኑኝ እርሱ የሞተውን ያነሣልኛልና ብሎ ለመናቸው እነርሱም በተዋሱት ጊዜ ቀሲስ ዮሐንስ ወደ ሐዋርያ እንድርያስ ሒዶ ችግሩን ሁሉ ነገረው ። ሐዋርያ እንድርያስም ቀሲስ ዮሐንስን እንዲህ አለው ከእኔ ዘንድ የሚጠመቁ ብዙ ሕዝቦች ስላሉ ከአንተ ጋር እሔድ ዘንድ አይቻለኝም ግን ደቀ መዝሙሬ ፊልሞና አብሮህ ይሒድ እርሱ የሞተውን ያስነሣልሃል አለው ። ሐዋርያ እንድርያስም ከቄሱ ጋር ሒዶ የሞተውን ያስነሣለት ዘንድ ፊልሞናን አዘዘው ወደ ከተማውም ሲቀርቡ ቄሱንና ፊልሞናን ሰዎች በከተማው ውስጥ ሁከት ሁኗልና አገረ ገዥው እንዳይገድላችሁ ወደ ከተማ አትግቡ አሏቸው ። ፊልሞናም እንዲህ አለ እኔ የመምህሬን ትእዛዝ መተላለፍ አልችልም የሞተውን ለማንሣት እሔዳለሁ እንጂ መኰንኑ ቢገድለኝም መምህሬ እንድርያስ መጥቶ እኔንም አስቀድሞ የሞተውንም ያስነሣናል ። ሲገባም መኰንኑን ኒቆሮስን ተገናኘውና ፊልሞና እንዲህ አለው ሀገርን ለምን ታጠፋለህ የሾሙህ ከክፉ ነገር ሁሉ ሀገርን ልትጠብቅ አይደለምን መኰንኑም ይህ ሰው ነፍሰ ገዳይ ይመስላል አለ ወታደሮችንም ይዛችሁ ሰቅላችሁ ግረፉት አላቸው ወታደሮችም ይገርፉት ዘንድ ይዘው ሰቀሉት ። ፊልሞናም ኒቆሮስ የተባለውን መኰንን እንዲህ አለው የበደልኩት በደል ሳይኖርለምን ሰቅለህ ትገርፈኛለህ እኔ ታናሽ ብላቴና ስሆን ደቀ መዝሙሩን እኔን ሰቅለው ሲገርፉኝ ይመለከት ዘንድ ለመምህሬ እንድርያስ ማን በነገረው አለ ። ወደ ወታደሮችም ፊቱን መልሶ እንዲህ አላቸው ከውስጣችሁ የሚራራና የሚያዝንልኝ የለምን በመሰቀልና በመገረፍ እንዳለሁ ሒዶ ለመምህሬ እንድርያስ ስለ እኔ ይነግረው ዘንድ አለ ከቃሉ ጣዕም የተነሣ ወታደሮች ተሰብስበው መጥተው አለቀሱ ። በዚያንም ጊዜ አዕዋፍ ሁሉ መጥተው እኛን ላከን ብለው ተናገሩት ድምቢጥ ቀርባ እኔ በአካሌ ቀላል ነኝና እኔን ላከኝ አለችው አንቺስ አመንዝራ ነሽ ከወገንሽ በመንገድ አንዱን ያገኘሽ እንደሆነ ከርሱ ጋር ትጫወቺአለሽ ፈጥነሽ አትመለሽም አላት ከዚህም በኋላ ቁራ ቀርቦ እኔን ላከኝ አለው ፊልሞናም እንዲህ አለው አንተም በቀድሞ ዘመን በተላክህ ጊዜ ለአባታችን ኖኅ የመልእክቱን መልስ አልመለስክም አለው ። ፊልሞና ግን ርግብን ጠርቶ እንዲህ አላት እግዚአብሔር የዋሂት ብሎ ስም ያወጣልሽ ከኣዕዋፍ ሁሉ የተመረጥሽ ወገን አንቺ ለአባታችን ኖኅ በመርከብ ውስጥ ሳለ መልካም ዜና አድረሰሽለታልና አባታችን ጻድቅ ኖኅም ባርኮሻልና አሁንም ወደ ልዳ ከተማ ወደ መምህሬ እንድርያስ ሔደሽ ንገሪው ሰቅለው እየገረፉኝ ነውና ወደ እኔ ወደ ደቀ መዝሙሩ ፊልሞና ይመጣ ዘንድ ። በዚያን ጊዜ ርግብ ሒዳ ለሐዋርያ እንድርያስ ነግራ የመልእክቱን መልስ ይዛ ተመለሰች የተባረከች ርግብም ለፊልሞና መምህርህ እንድርያስ እኔ እመጣለሁና አይዞህ በርታ ብሎሃል አለችው ። በዚያንም ጊዜ ርግብ በሰው ቋንቋ ለፊልሞና ስትነግረው ኒቆሮስ መኰንን ሰማት እጅግም አደነቀ ፈጥኖ ተነሥቶም ራሱ በእጁ ፊልሞናን ፈትቶ ከተሰቀለበት አወረደው ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም አመነ ። ሰይጣን ግን ቀና በመኰንኑ ሚስት ልቡና አድሮ አሳበዳትና ልጅዋን ገደለች አገልጋዮቹም ሒደው የሆነውን ሁሉ ለመኰንኑ ነገሩት ፊልሞናም አትፍራ አይዞህ አለው ። ከዚህም በኋላ ርግብን ጠርቶ ወደ መኰንኑ ቤት ሒጂ እንዳይሸበሩ በጸጥታ እንዲቆዩ ንገሪያቸው አላት ርግቢቱም ሒዳ ፊልሞና እንዳዘዛት ለሕዝቡ ነገረቻቸው ሕዝቡም ርግቢቱ በሰው ቃል ስትናገር በሰሙ ጊዜ እጅግ አድንቀው ፊልሞና ወዳለበት ተሰበሰቡ ። በዚያንም ጊዜ ሐዋርያ እንድርያስ ደረሰ አስቀድሞ የሞተውን ያስነሣው ዘንድ ደቀ መዝሙሩ ፊልሞናን አዘዘው እርሱም ክብር ይግባውና ወደ ጌታችን በመጸለይ ከሞት አስነሣው ሁለተኛም ወደ መኰንኑ ቤት ሔዱ ሐዋርያ እንድርያስም የመኰንኑን ልጅ እናቱ የገደለችውን አስነሣው የመኰንኑንም ሚስት አዳናት ከእርሷ የወጣውንም ያንን ጋኔን ይዞ በሰው ሁሉ ፊት ምድርን ከፍቶ ወደ ጥልቅ አዘቅት አሰጠመው ።
نمایش همه...
84🕊 7