ar
Feedback
Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ

Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ

الذهاب إلى القناة على Telegram

እንኳን ደህና መጡ‼ 📌ማስታወቂያ ለማሰራት👉 @WasuMohammed 📌 ቻናሉን ለመቀላቀል 👉 @Wasulife ከልብ አመሰግናለሁ♥🙏

إظهار المزيد
2025 عام في الأرقامsnowflakes fon
card fon
242 186
المشتركون
-96724 ساعات
+9 9047 أيام
+19 31230 أيام
أرشيف المشاركات
Photo unavailableShow in Telegram
ከቃል በላይ ያስረከብናቸው ከ 8 በላይ ሳይቶች ማሳያ ናቸው #ቴምርሪልስቴት አሁን ደግሞ በተለያዩ ሳይቶቻችን ላይ እስከ 35% ልዩ ቅናሽ ላይ ነን #ይፍጠኑ ‼️ተክለሀይማኖት ሆስፒታል ፊት ለፊት 🎯የክፍያ አማራጭ 70/30 👉3 መኝታ 110ካሬ ሙሉ ክፍያ 8,547,000 ብር 🎯ቀስ ብሎ መክፈል ለሚፈልግ 👉3 መኝታ 110ካሬ      10%ቅድመ ክፍያ 1,210,000ብር      ሙሉ ክፍያ 12,100,000ብር ‼️ሀይሌጋርመንት African CDC ፊት ለፊት   🎯የክፍያ አማራጭ 70/30 👉3 መኝታ 139ካሬ 10,216,500ብር ሙሉ ክፍያ 🎯ቀስ ብሎ መክፈል ለሚፈልግ 👉 ባለ 3መኝታ (139ካሬ) ሙሉ ክፍያ = 14,595,000ብር ቅድመ ክፍያ = 10% (1,459,500ብር ) ‼️አያት 🎯 65/35 የክፍያ አማራጭ 👉3 መኝታ 111 ካሬ ሙሉ ክፍያ 7,936,500ብር 🎯ቀስ ብሎ መክፈል ለሚፈልግ 👉3 መኝታ 111ካሬ 10% ቅድመ ክፍያ 1,221,000ብር ሙሉ ክፍያ 12,210,000ብር ‼️አያት ፈረስ ቤት 🎯ቀስ ብሎ መክፈል ለሚፈልግ 👉3 መኝታ 108ካሬ 6,669,000ብር ሙሉ ክፍያ 6,669,000ብር ሙሉ ክፍያ 🎯ቀስ ብሎ መክፈል ለሚፈልግ 👉3 መኝታ 108ካሬ 10%ቅድመ ክፍያ ሙሉ ክፍያ 10,260,000ብር ቅድመ ክፍያ 1,026,000ብር     #ልብይበሉ ቀሪውን 90% ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት * 40% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ 20%_35% ቅናሽ አዘጋጅተናል                ለበለጠ መረጃ ይደውሉ        👇👇👇👇👇👇      +251939770177      +251996856273 https://t.me/TemerRealEstateSalesConsultant WhatsApp. https://wa.me/251939770177
إظهار الكل...
24👏 3
Photo unavailableShow in Telegram
በባይራክታር ከዕይታ ወሰን በላይ የሆነ የአየር-ለ-አየር ሚሳኤል ጥቃት ተከናወነ‼ የአገሪቱ ብሔራዊ ሰው አልባ ተዋጊ አውሮፕላን የሆነው ባይራክታር ኪዚልኤልማ በአይነቱ የመጀመሪያው በመሆን ከዕይታ ወሰን በላይ የሆነ የአየር-ለ-አየር ሚሳኤል ጥቃት በተሳካ ሁኔታ ማከናወኑን የመከላከያ ኩባንያው ባይካር (Baykar) ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። በሲኖፕ ግዛት አቅራቢያ ጥቁር ባህር ላይ በተካሄደው ሙከራ አውሮፕላኑ በአገር ውስጥ የተገነባውን ጎክዶጋን ሚሳኤል ከክንፉ ስር በመተኮስ በፍጥነት የሚንቀሳቀስ ኢላማ ጄትን በተሳካ ሁኔታ አውድሟል። ጥቃቱ የተመራው በሰው አልባው አውሮፕላን ሲስተሞች ውስጥ በተዋሃደው የአሰልሳን ሙራድ AESA ራዳር አማካኝነት ነው። የባይካር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሃሉክ ባይራክታር "በብሔራዊ አውሮፕላን፣ በብሔራዊ ራዳር እና በብሔራዊ ሚሳኤል፣ የአየር-ለ-አየር ፍልሚያ ሰንሰለት ውስጥ ያለውን እያንዳንዱን ትስስር ሙሉ በሙሉ በአገር ውስጥ አቅም ጨርሰናል ይህ ኩራት የሕዝባችን ነው" ብለዋል። የቱርክ መከላከያ ሚኒስቴር ኪዚልኤልማ በዓለም የመጀመሪያው ሰው አልባ ተዋጊ ጄት በመሆን በጀት የሚንቀሳቀስ የአየር ላይ ኢላማን ከዕይታ ወሰን በላይ ሚሳኤል በመጠቀም ማጥፋቱን አሞግሷል። ሚኒስቴሩ "እኛ የወታደሮች አገር እንደመሆናችን መጠን ለልጆቻችን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ግስጋሴዎችን መምራታችንን እንቀጥላለን" ብሏል።(nejmudinawel)
إظهار الكل...
141👏 30👍 21😍 6😱 3🔥 2🎉 2😢 1
Ads መሳቅ ከፈለጉ ብቻ ወደ እኛ ኑ አርሂቡ ብለናል‼ እኛ ጋር የምትመጡት ዘና ለማለትና ለመሳቅ ብቻ ነው።ግን ሰብስክራይብ ማድረግ እንዳይረሳ። https://youtu.be/arxRKpyulvE ለቀጣይ ለበለጠ መዝናናት ከፈለጋችሁ ብቻ Subscribe አድርጉን።ሊንኩ ከስር ተቀምጧል። 👇   👇    👇   👇 https://youtube.com/@mewamedia?si=WqTGSX0f_-rUm3ua Mewa Media የሳቅ ምንጭ
إظهار الكل...
17👍 3
"...ነፃ ሕክምና የማይሰጡ ተቋማት እና ሐኪሞች በሕግ ይጠየቃሉ"የመንገድ ደህንነት እና መድኅን ፈንድ በትራፊክ አደጋ ጉዳት ደርሶበት ወደ ሕክምና ተቋማት ያመራ ማንኛውም ሰው እስከ 15 ሺሕ ብር የሚደርስ አስቸኳይ የነፃ ሕክምና አገልግሎት እንዲያገኝ የሚፈቅደውን መመሪያ ተግባራዊ የማያደርጉ ተቋማት እና ባለሙያዎች በሕግ ይጠየቃሉ ተብሏል። የመንገድ ደህንነት እና መድኅን ፈንድ አገልግሎት እንዳስታወቀው፤ የመንግሥትም ሆነ የግል የሕክምና ተቋማት ጉዳት ደርሶበት የሚመጣን ማንኛውም ግለሰብ በነፃ የመርዳት ግዴታ ቢኖርባቸውም አንዳንድ ተቋማት በመመሪያው የታዘዘውን አሰራር ተግባራዊ እያደረጉ አይደለም፡፡ "መመሪያውን ተላልፈው የተገኙ የሕክምና ባለሙያዎች እና ተቋማቱ እርምጃ ይወሰድባቸዋል" ሲሉ ማስጠንቀቂያ የሰጡት የአገልግሎቱ የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪ አቶ ሱራፌል ብርሃኑ፤ ሁሉም የሕክምና ተቋማት ለትራፊክ አደጋ ተጎጂዎች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ አስቸኳይ የሕክምና እርዳታ መስጠት እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተውበታል። ይህ ግዴታ የተቀመጠው ከ2005 ዓ.ም. ጀምሮ እንደሆነ ያስታወሱት አስተባባሪው፤ በወቅቱ የወጣው ተቋማቱ እስከ 2 ሺሕ ብር የሚደርስ ሕክምና በነጻ እንዲሰጡ የሚያዘው መመሪያ ተሻሽሎ ወደ 15 ሺሕ ብር መሻሻሉን ለአሐዱ ሬዲዮ ተናግረዋል። አስተባባሪው አቶ ሱራፌል፤ "ምንም እንኳን ሥልጠና እና መመሪያ በተደጋጋሚ ቢሰጥም፣ ጥቂት የማይባሉ የጤና ተቋማት 'ሕጉን አላውቀውም' የሚል ምክንያት አገልግሎቱን ከመስጠት መቆጠባቸው ለቅጣት ይዳርጋቸዋል" ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ተመሳሳይ ጥፋት የተገኘባቸው ሕግን የማያከብሩ ተቋማትን በወጡ ደንብና መመሪያዎች መሠረት ተጠያቂ ለማድረግም ለሕግ አስከባሪ አካላት ሥልጠና እንደሚሰጥ አብራርተዋል። የጤና ተቋማት ለነፃ አስቸኳይ ሕክምና ያወጡት ወጪ ተመላሽ እንደሚደረግ ያስረዱት አቶ ሱራፌል፤ ፈንዱ ይህንን ነፃ አስቸኳይ ሕክምና ለማስፈጸም የሚያስችል ገንዘብ የሚያሰባስበው ከራሱ መዋጮ በተጨማሪ ከኢንሹራንስ ኩባንያዎች እንደሆነ ተገልጿል። የተሰበሰበው ገንዘብ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለተጎጂዎች ድጋፍ ይውላል ተብሏል።(አሐዱ ሬዲዮ)
إظهار الكل...
156🙏 43👍 8👏 6😱 5🏆 3🎉 1
Photo unavailableShow in Telegram
ዶ/ር አብዱ ዶ/ር ሙሀመድ እና ጓደኞቻቸው ሪልስቴት ደሴ ስልክ  0937411111           0938411111 ሊንክ: https://t.me/+ACPCPoXDK4JlMjA0
إظهار الكل...
8
Photo unavailableShow in Telegram
“ከ 11 ሰዓት ተኩል በፊት ከቢሮ ለሚወጣ የመንግሥት ሠራተኛ የትራንስፖርት አገልግሎት አይሰጥም” የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ለመንግሥት ሠራተኞች በነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙት የፐብሊክ ሰርቪስ የትራንስፖርት አውቶብሶችን በሥራ መውጫ ሰዓት ከ 11 ሰዓት ተኩል በፊት መጠቀም እንደማይቻል የአዲስ አበባ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ አስታውቋል። ቢሮ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው “የመንግሥት የሥራ ሰዓት ከመድረሱ በፊት” ባሶቹን የሚጠቀሙ ሠራተኞች በመኖራቸው መሆኑን አስታውቋል። በቢሮ ተጽፎ ለሁሉም ክፍለከተማዎች በተሰራጨው ደብዳቤ ላይ፤ “የመንግሥት ሠራተኞች የሥራ ሰዓትን በአግባቡ ሥራ ላይ እንዲያውሉ መንግሥት የፐብሊክ ትራንስፖርት አገልግሎት በማመቻቸቱ እና አብዛኛው ሠራተኛ ተጠቃሚ በመሆኑ ከእንግልት መትረፉን” ይገልፃል። ኢትዮቲዩብ የተመለከተው ደብዳቤ የመንግሥት ሠራተኛው ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚ መሆኑ “ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዲያገኝ” ስለማድረጉ ያትታል። ሆኖም ባሶቹ የሥራ መውጫ ሰዓት ከመድረሱ በፊት ሠራተኛውን እንደሚጭኑ ተነግሯል። ይህ ተግባር “በመንግሥት ሥራ ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ እንደሚገኝ ቢሮ አስታውቋል። በዚህ ሳቢያ የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አውቶብሶች “በተመደቡበት የመነሻ ቦታ ሠራተኞችን ከሰዓት ከ 11:45 በኋላ መጫን እንዲጀምሩ” ለሁሉም ክፍለክተማ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ጽሕፈት ቤት መመሪያ ተላልፏል። ሁሉም የፐብሊክ ትራንስፖርት ተጠቃሚ ይህን የሰዓት ለውጥ በመገንዘብ ከ 11 ሰዓት ተኩል በፊት ከመሥሪያ ቤቱ እንዳይወጣ ቢሮ አሳስቧል። በዚህ ረገድ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችም ሠራተኞቻቸው በአግባቡ እንዲቆጣጠሩ በተጻፈው ደብዳቤ ላይ ተመላክቷል።
إظهار الكل...
84🤣 54👏 12👍 9🏆 4😢 2😍 2
Photo unavailableShow in Telegram
📍አድራሻ - በመሀል ከተማ በኮሊደር ልማቷ ባሸበረቀችው  ለቡ ማብራት-ሀይል 💥ሊኖሩበት ቢፈልጉ ሰላሚዊ መንደር፣ ሊያከራዩት ቢያስቡ በጥሩ ወጋ እና መልሰው እንኳን ቢሸጡት በደንብ የሚያተርፉበት!! 💥ስቱዲዮ (59 ካሬ) በ 260ሺህ ብር 💥ባለ አንድ መኝታ (77.3ካሬ) በ 341ሺህ ብር 💥ባለ ሁለት መኝታ (127.2ካሬ) በ 561ሺህ ብር 💥ባለ ሦስት መኝታ (150.5 ካሬ) በ 664ሺህ ብር 💥 ባለ አራት መኝታ (194 ካሬ) በ 855 ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ብቻ 💥 እንዲሁም እስከ 295ካሬ ስፋት ያላቸው ፔንትሃውስ ቤቶችን በምቹ አከፋፈል በተመጣጣኝ ዋጋ ከኛ ያገኛሉ በተጨማሪም  ከ27 - 190 ካሬ ስፋት ያላቸው ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ የንግድ ቦታዎችን እንደምርጫዎ አቀርብንሎት! ✍️ በ10% ቅድመ ክፍያ ብቻ ✍️ ከ 60% የባንክ ብድርጋር እስከ 25 ዓመት ✍️ በተጨማሪም እስከ 35%  እንደ አከፋፈሎ ልዩ ቅናሽ ይደረግሎታል ✍️ ሁሉም ቤቶች ተጨማሪ የሰራተኛ ክፍል, ስቶር እና የላውንድሪ ክፍሎች ያሏቸው። ✍️ መንደራችን በውስጥ የያዛቸው ልዩ ልዩ የጋራ መገልገያዎች: 💥 አራት የመንገደኞች እና አንድ የእቃ አሳንሰር 💥 አምስት የዋና ገንዳዋች 💥 አስተማማኝ ና ደህንነቱ የተጠበቀ ሰፊ የመኪና ማቆሚያ 💥 የኤሌክትሪክ መኪና ኃይል መሙያ መሳሪያ 💥 ለተለያዩ ዝግጅቶች የሚሆን የጋራ ቦታ 💥 የቆሻሻ መጣያ (Garbage shooter) 💥 ዘመናዊ የገበያ ማዕከሎች @Dmcreales ለበለጠ መረጃ ☎️ 0940625843
إظهار الكل...
31👍 1👏 1
‹‹ከተቀመጠው ስታንዳርድ በላይ የሚለቁ ይታገዳሉ›› ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች የሚለቁትን በካይ ጋዝ ለመቆጣጠር የሚያስችል መሣሪያ እንዲገጥሙ ሊደረግ መሆኑን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ከዕፅዋት የሚዘጋጅ የአውሮፕላን ነዳጅ ለመጠቀም የሚያስችል ዘላቂ የአቪዬሽን ነዳጅ ላይ የተሠራ የአዋጭነት ጥናት ሪፖርት ኅዳር 18 ቀን 2018 ዓ.ም. ሲያቀርብ የተገኙት የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)፣ በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች የሚለቁት በካይ ጋዝ ምን ያህል መሆን እንዳለበት የሚወስን ስታንዳርድ መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡ ሚኒስቴሩ ስታንዳርዱን ያዘጋጀው ከኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ጋር መሆኑንና አሽከርካሪዎች በተዘጋጀው ስታንዳርድ መሠረት የማይጠቀሙ ከሆነ እንደሚታገዱ፣ በተለይም ለረዥም ጊዜ ያገለገሉና ሞተራቸው ያረጀ ተሽከርካሪዎች የሚለቁት በካይ ጋዝ ከፍተኛ በመሆኑ ካላስተካከሉ እንደሚታገዱ አስታውቀዋል፡፡ ‹‹ተሽከርካሪዎች የሚለቁት የጋዝ መጠን በሕጉ ከተቀመጠው በላይ መብለጥ እንደሌለበት መጠኑን ያስቀመጠ የሕግ ድንጋጌ ተዘጋጅቷል፡፡ ይህ ሕግ ሥራ ላይ መዋሉ በካይ ጋዝ እንዲቀንስ ያደርጋል ማለታቸው ሪፖርተር ዘግቧል።
إظهار الكل...
159👍 26👏 16😱 12😍 8😁 5💩 4🏆 4🎉 3🔥 1
አክሱም ፅዮን‼ "የፕሪቶሪያ ስምምነት ተግባራዊ አለማድረግ የትግራይን ህዝብ ችግር የበለጠ አሳሳቢ አድርጎታልና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጫና ሊያሳድርበት ይገባል።"ሲሉ ብፁዕ አቡነ ሰላማ በዛሬው የአክሱም ፂዮን ማርያም ባዕል ላይ መናገራቸው ተሰምቷል።ጀኔራል ታደሰም ወረደም ተመሳሳይ መልዕክት ማስተላለፋቸው ተነግሯል።ዓመታዊው የአክሱም ህዳር ፅዮን በዓል ዛሬ ድምቀት ተከብሯል።
إظهار الكل...
147😁 53👍 9🙉 9🕊 7👏 6🏆 5🔥 3😍 3🤡 1
Photo unavailableShow in Telegram
ዛሬ አዲስ አበባ አንድ ኪሎ ቀይ ሽንኩርት ከ20 እስከ 30 ብር እየተሸጠ ነው።ከወር በፊት እስከ 130 ብር ሲሸጥ እንደነበር ይታወሳል።
إظهار الكل...
👍 113 36👏 20🥱 4😱 3
Photo unavailableShow in Telegram
Ads መሳቅ ከፈለጉ ብቻ ወደ እኛ ኑ አርሂቡ ብለናል‼ እኛ ጋር የምትመጡት ዘና ለማለትና ለመሳቅ ብቻ ነው።ግን ሰብስክራይብ ማድረግ እንዳይረሳ። https://youtu.be/arxRKpyulvE ለቀጣይ ለበለጠ መዝናናት ከፈለጋችሁ ብቻ Subscribe አድርጉን።ሊንኩ ከስር ተቀምጧል። 👇   👇    👇   👇 https://youtube.com/@mewamedia?si=WqTGSX0f_-rUm3ua Mewa Media የሳቅ ምንጭ
إظهار الكل...
16🥰 2
Photo unavailableShow in Telegram
አማራ ክልል ከመንግስት ጋር መሳሪያ አንስተው ግጭት ውስጥ ከገቡ የፋኖ መሪዎች መካከል ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ ትናንት ምሽት እጁን ለመንግስት የፀጥታ ኃይሎች መስጠቱን የወጡ መረጃዎች አመልክተዋል። በፋኖ መዋቅር ራሱን የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት/አፋህድ) በማለት የሚጠራው አደረጃጀት ትናንት ምሽት ባወጣው መግለጫ ማስረሻ ሰጤ እና መሥፍን አባተ (መስፍን ከፈለኝን) ከአመራርነት ማገዱን አሳውቆ ነበር። በአማራ ክልል የተቀሰቀሰው ግጭት ሶስት አመት ሊሆነው ወራት ቀርተውታል።በግጭቱ በርካታ የክልሉ ነዋሪዎች ህይወታቸውንና ኃብት ንብረታቸው አጥተዋል።ጉዳቱ በትውልዶች የመማር ማስተማር ሂደት ከፍተኛ ኪሳራን ማድረሱ ሲዘገብ መቆየቱ ይታወሳል።
إظهار الكل...
159👍 46🤣 26🕊 10👏 6🤪 5😢 4😱 3🎉 2🔥 1
ኮሜዲያን ወንደሠን አውራሪስ በድንገተኛ ህመም ህይወቱ ማለፉ ታውቋል።ወንዶሰን በርካታ የኮሜዲ ስራዎች ላይ ታወቂ ነበር።ለቤተሰቦቹ መጽናናትን እመኛለሁ።።
إظهار الكل...
😢 126😭 75 30💔 19😱 11👍 4
Photo unavailableShow in Telegram
ኤርባስ ኩባንያ በ6 ሺሕ ኤርባስ-320 የመንገደኞች አውሮፕላኖች ላይ የኮምፒውተር እክል እንዳገኘ ማሳወቁን ተከትሎ፣ በዓለም ዙሪያ በርካታ በረራዎች ተስተጓጎሉ። ኩባንያው፣ አውሮፕላኑ ለጸሐይ ጨረር በሚጋለጥበት ወቅት የበረራ ተቆጣጣሪ ኮምፒውተሩ የአውሮፕላኑን ከፍታ ለማስላት የሚጠቀምበት መተግበሪያ እክል እንደሚገጥመው መረዳቱን ገልጧል። ኾኖም 5 ሺሕ 100 አዳዲስ የኤርባስ-320 አውሮፕላኖች በሦስት ሰዓታት ውስጥ የኮምፒውተር መተግበሪያቸውን ማሻሻል እንደሚችሉ ኩባንያው የገለጠ ሲኾን፣ ቀሪዎቹ 900 አውሮፕላኖች ግን ኮምፒውተራቸውን ሙሉ በሙሉ መቀየር አለባቸው ብሏል። የአውሮፕላኑ የኮምፒውተር መተግበሪያ ለችግር መጋለጡ የታወቀው፣ ባለፈው ጥቅምት ወር ከአሜሪካ ወደ ሜክሲኮ በመጓዝ ላይ የነበረ ኤርባስ-320 አውሮፕላን ከፍታውን ከሳተ በኋላ ነው። Via Fontenina Wasu Mohammed - Mereja
إظهار الكل...
57😱 8🥰 7🙏 3🏆 3🙈 3👍 2😢 2👌 2💔 2👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
ከቃል በላይ ያስረከብናቸው ከ 8 በላይ ሳይቶች ማሳያ ናቸው #ቴምርሪልስቴት አሁን ደግሞ በተለያዩ ሳይቶቻችን ላይ እስከ 35% ልዩ ቅናሽ ላይ ነን #ይፍጠኑ ‼️ተክለሀይማኖት ሆስፒታል ፊት ለፊት 🎯የክፍያ አማራጭ 70/30 👉3 መኝታ 110ካሬ ሙሉ ክፍያ 8,547,000 ብር 🎯ቀስ ብሎ መክፈል ለሚፈልግ 👉3 መኝታ 110ካሬ      10%ቅድመ ክፍያ 1,210,000ብር      ሙሉ ክፍያ 12,100,000ብር ‼️ሀይሌጋርመንት African CDC ፊት ለፊት   🎯የክፍያ አማራጭ 70/30 👉3 መኝታ 139ካሬ 10,216,500ብር ሙሉ ክፍያ 🎯ቀስ ብሎ መክፈል ለሚፈልግ 👉 ባለ 3መኝታ (139ካሬ) ሙሉ ክፍያ = 14,595,000ብር ቅድመ ክፍያ = 10% (1,459,500ብር ) ‼️አያት 🎯 65/35 የክፍያ አማራጭ 👉3 መኝታ 111 ካሬ ሙሉ ክፍያ 7,936,500ብር 🎯ቀስ ብሎ መክፈል ለሚፈልግ 👉3 መኝታ 111ካሬ 10% ቅድመ ክፍያ 1,221,000ብር ሙሉ ክፍያ 12,210,000ብር ‼️አያት ፈረስ ቤት 🎯ቀስ ብሎ መክፈል ለሚፈልግ 👉3 መኝታ 108ካሬ 6,669,000ብር ሙሉ ክፍያ 6,669,000ብር ሙሉ ክፍያ 🎯ቀስ ብሎ መክፈል ለሚፈልግ 👉3 መኝታ 108ካሬ 10%ቅድመ ክፍያ ሙሉ ክፍያ 10,260,000ብር ቅድመ ክፍያ 1,026,000ብር     #ልብይበሉ ቀሪውን 90% ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት * 40% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ 20%_35% ቅናሽ አዘጋጅተናል                ለበለጠ መረጃ ይደውሉ        👇👇👇👇👇👇      +251939770177      +251996856273 https://t.me/TemerRealEstateSalesConsultant WhatsApp. https://wa.me/251939770177
إظهار الكل...
26
ከአደጋው የተረፈ ተሳፋሪ የለም ‼ 📌"በእኛ አካባቢ በአንድ አደጋ ሙሉ ተሳፋሪ ህይወቱ ያለፈበት አጋጣሚ ይህ ነው" ፖሊስ በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ጉምቢ ቦርደዴ ወረዳ ትናንት ቅዳሜ 10 ሰዓት፣ በደረሰ የትራፊክ አደጋ አንድ ዶልፊን ያሳፈራቸው 11 ሠዎች ህይወታቸው ማለፉን የምዕራብ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ ዋና መምርያ አስታውቋል። የምዕ/ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ ዋና መምርያ የትራፊክ ደሕንነትና ቁጥጥር አስተባባሪ ምክትል ኢንስፔክተር ዳኙ ሶሪ ለሂርኖዬ እንደተናገሩት ትናንት ህዳር 20 ቀን 2018 ዓም መነሻውን ከሚኤሶ ከተማ ያደረገ የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3-96835 ኦሮ ዶልፊን የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ዘጠኝ ተሣፋሪዎችን አሳፍሮ ወደ አዋሽ ከተማ ሲጓዝ ነበር። ተሸከርካሪው በተቃራኒ መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ጅቡቲ ሲጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-ኤ-11805 ኢቲ የነዳጅ ማመላለሻ ቦቴ ጉምቢ ቦርደዴ ወረዳ ጪቱ ቀበሌ ላይ ፊት ለፊት ተጋጭተዋል። በአደጋው በዶልፊኑ ውስጥ የነበሩ አሽከርካሪውን እና ረዳቱን ጨምሮ የስምንት ወንዶችና የሶስት ሴቶች በአጠቃላይ ተሽከርካሪው ውስጥ የነበሩ ሰዎች በሙሉ ህይወታቸው ማለፉን ገልፀዋል። የአደጋው መንሴ የዶልፊኑ ተሽከርካሪው መስመሩን ለቆ ወደ ተቃራኒ አቅጣጫ በመግባቱ ና ፊት ለፊት ከነዳጅ ጫኝ ቦቴው ጋር በመጋጨቱ ሲሆን የነዳጅ ቦቴ አሽከርካሪው ለግዜው ተሰውሯል። ፖሊስ ከተሽከርካሪው ውስጥ የመንጃ ፈቃዱን ና ሌሎች መረጃዎችን በማግኘቱ ክትትል ላይ መሆኑን ገልፀዋል። የሟቾች አስክሬን ለምርመራ ወደ ሆስፒታል የተላከ ሲሆን በአንድ አደጋ ሙሉ ተሳፋሪ ህይወቱ ያለፈበት አጋጣሚ ከዚህ ቀደም የተመዘገበ እንደሌለ ምክትል ኢንስፔክተር ዳኙ ሶሪ ጨምረው መናገራቸውን መነሃሪያ ዘግቧል።
إظهار الكل...
84😢 57😭 34🔥 3😱 3😍 3👍 2🏆 2🙊 2🥰 1
Photo unavailableShow in Telegram
ዶ/ር አብዱ ዶ/ር ሙሀመድ እና ጓደኞቻቸው ሪልስቴት ደሴ ስልክ  0937411111           0938411111 ሊንክ: https://t.me/+ACPCPoXDK4JlMjA0
إظهار الكل...
4
የ2025 የቲክቶክ ክሬቲቭ አዋርድ ሽልማት ትናንት ምሽት ተካሂዷል። 📌የዘንድሮው መድረክ በሶስት ዘርፎች ትልቁን ክብር ያገኘው አዶናይ ሲሆን የአመቱ ምርጥ ቲክቶከር፣ አነቃቂ አዶናይ እና የአመቱ ላይፍ ስታይል አሸናፊ ተብሎ ተመርጧል። 📌በጤና እና ማህበራዊ ጠቀሜታ ዘርፍ፣ ዶክተር ዐቢይ ታደሰ የህክምና ይዘት ተሸላሚና የማህበራዊ ኃላፊነት ተሸላሚ የሚሉትን ሽልማቶች ጠርጓል። 📌የመድረኩ ሌላኛዋ ባለብዙ ሽልማት አሸናፊ ዩቲ ናስ ናት። Life Time አሸናፊ፣ የስማይል ቻሌንጅ አሸናፊ እና ምርጥ አለባበስ በሴት የሚሉትን ክብር አግኝታለች። 📌ሌሎች ዋና አሸናፊዎች፦ ዶሚኔት ኑሪ (ምርጥ ወንድ ኮሜዲ)፣ ንጹ (ምርጥ ሴት ኮሜዲ)፣ ብሩክ ኒውስ (ብሩክ ጫላ) (የኢንፎርማቲቭ አሸናፊ)፣ ናሆም ፎንቲ (ላይቭ ስትሪመር) እና መምህር ዳኒ (የ STEM አሸናፊ) ይገኙበታል። 🏆 ትልልቅ አሸናፊዎች (Multiple Wins): 1. አዶናይ: የአመቱ ምርጥ ቲክቶከር፣ አነቃቂ አዶናይ፣ የአመቱ ላይፍ ስታይል አሸናፊ። 2. ዩቲ ናስ: Life Time አሸናፊ፣ የስማይል ቻሌንጅ አሸናፊ፣ ምርጥ አለባበስ በሴት። 3. ዶክተር ዐቢይ ታደሰ: የህክምና ይዘት ተሸላሚ፣ የማህበራዊ ኃላፊነት በመወጣት ተሸላሚ። * የመዝናኛ እና ኮሜዲ አሸናፊዎች: 4. ዶሚኔት ኑሪ: የአመቱ ምርጥ ወንድ ኮሜዲ። 5. ንጹ: የአመቱ ሴት ኮሜዲ ተሸላሚ። 6. ዳዊት ታዬ: የአመቱ ምርጥ ዳንሰኛ ተሸላሚ። 7. ፓትሮን: ምርጥ ሚመር ተሸላሚ። ዕውቀት እና መረጃ አቅራቢዎች: 8. ብሩክ ኒውስ (ብሩክ ጫላ): የኢንፎርማቲቭ አሸናፊ። 9. መምህር ዳኒ: የአመቱ የ STEM አሸናፊ። 10. አቢ: የስፖርት መረጃ ይዘት አሸናፊ። * ልዩ ይዘትና ላይቭ: 11. ናሆም ፎንቲ: የላይቭ ስትሪመር ተሸላሚ። 12. ቤንጂ: የአመቱ አጭር ፊልም አሸናፊ። 13. የአመቱ ምርጥ ሪቪው ይዘት ተሸላሚ። 14. ሰያ: የአመቱ የጉዞ ተሸላሚ። * ቻሌንጅ እና ተስፋ: 15. በረከት ታደሰ (ቤኪ 4kilo): የአመቱ የጭላሎ ቻሌንጅ አሸናፊ። 16. ባምሌ: ተስፋ የተጣለበት ቲክቶከር። ፎቶ:- kira_designs
إظهار الكل...
135👍 13💩 11🔥 5👌 3😍 3🥰 2👏 2😱 2😢 2 1
Photo unavailableShow in Telegram
🏢እጅግ ውብ እና ዘመናዊ አፓርትመንቶችን በ CMC በመሪ በአያት በዞን 3 እንዲሁም በአያት ዞን 8ና በካሳንቺስ የሚገኙ ሳይቶቻችን ✅ ግንባታቸው 85% የደረሱ        📌CMC ሚካኤል ወሰን       📌 አያት ዞን 2 ❇️ የካሬ አማራጭ      📌ባለ 1 መኝታ      📌 ባለ 2 መኝታ.     📌 ባለ 3 መኝታ     📌 ባለ 4 መኝታ ✅ አዲስ የሚጀመሩ በ3 አመት የሚረከቡት       📌 መሪ 1       📌አያት ዞን 3      📌 ካሳንቺስ       📌 ልደታ ❇️ አከፋፈል * የመኖሪያ ቤቱን አጠቃላይ ዋጋ 15% ቅድመ ክፍያ ብቻ በመክፈል የቤት ባለቤት ያደርጎታል፤ ✅በብድር ለሚከፍሉ የቤቱን  60% እስከሚረከቡ ይከፍላሉ ቀሪውን 40% ተረክበው  እስከ 30 አመት እየኖሩበት ይከፍላሉ ✅የቅናሽ አማራጮች እንደአከፋፈሎ ከ 8- 20%  የሚደርሱ ቅናሾችም አሉን   ❇️ ርክክብ * ቤትዎን ሲረከቡ በከፊልም ሆነ በሙሉ ግንባታ የመረከብ መብትዎ እንደተጠበቀ ነው። ❇️ ቤትዎን ዛሬ ገዝተዉ ነገ ይክፈሉ።   ለበለጠ መረጃ  በቀጥታ @lilye በቴሌግራም ወይም በዋትሳፕ ☎️+251945158152       +251977806111
إظهار الكل...
27👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
Update የአፍሪቃ ህብረት ጊኒ ቢሳዎን ከህብረቱ አባልነት አገደ‼ ህብረቱ ውሳኔውን ያሳለፈው ፕሬዚዳንት ኡማሮ ሲስኮ ኢምባሎ በመፈንቅለ መንግስት ከስልጣን ከተወገዱ ከሁለት ቀናት በኋላ ነው። የጊኒ ቢሳዎ ወታደራዊ ኃይል ባለፈው ረቡዕ ፕሬዚዳንቱን ከስልጣን ማስወገዱን አስታውቋል። ሊቀመንበሩ ማህሙድ አሊ የሱፍ እንዳሉት የአፍሪካ ህብረት ጊኒ ቢሳውን ከአባልነቷ በፍጥነት ለማገድ ወስኗል።በወታደሮች የተፈጸመው መፈልቅለ መንግስት በምዕራብ አፍሪቃዊቷ ሀገር የተደረገው የምርጫ ውጤት በቅርቡ ይፋ ይደረጋል ተብሎ በሚጠበቅበት ወቅት መሆኑን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል። የጊኒ ቢሳዎ ወታደራዊ ሁንታ አዛዡ ጄነራል ሆርታ ንታምን ለአንድ ኦመት የሽግግር መንግስቱ ፕሬዚደንት አድርጎ ሾሟል። ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ በቁጥጥር ስር የነበሩት ፕሬዚዳንት ኡማሮ ሲስኮ ኢምባሎ በድርድር ወደ ሴኔጋል እንዲሸሹ መደረጋቸውን ዘገባው አመልክቷል። በምርጫው አሸንፌያለሁ የሚሉት የተቃዋሚው ፕሬዚዳንታዊ እጩ ፈርናንዶ ዲያስ "ደህንነታቸው ተጠብቆ"  በሀገሪቱ ውስጥ በአንድ ስፍራ ተደብቀው እንደሚገኙ ለዜና ምንጩ ተናግረዋል። የምዕራብ አፍሪካ ኢኮኖሚክ ማህበረሰብ (ECOWAS) ሀገሪቱን “ከሁሉም ውሳኔ ሰጪ አካላት” ማገዱ ይታወሳል።ጊኒ ቢሳዎ ከጥቂት አታት ወዲህ የወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ሰለባ የሆነች ሌላዋ ምዕራብ አፍሪቃዊ ሀገር ኾናለች።Via DW
إظهار الكل...
116😁 23👏 12🙏 9👍 7😱 6🔥 2🥰 2