ar
Feedback
ATC NEWS

ATC NEWS

الذهاب إلى القناة على Telegram

#ADDIS_ABABA : ETHIOPIA ለመልዕክት 👇🏻 @mujaabot For Advertisement👇🏿 @atcads

إظهار المزيد
2025 عام في الأرقامsnowflakes fon
card fon
127 433
المشتركون
-6624 ساعات
-2667 أيام
-76830 أيام
أرشيف المشاركات
Photo unavailableShow in Telegram
#MoE ትምህርት ሚኒስቴር በተለያዩ የሙያ ዘርፎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀው የመምህርነት ሙያን መቀላቀል ለሚፈልጉ የአንድ ዓመት ስልጠና ሊሰጥ ነው፡፡ ስልጠናው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ በተመረጡ አምስት ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል፡፡ የምዝገባ መስፈርት፦ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቁና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በሚሰጡ የትምህርት ዓይነቶች እና ተዛማጅነት ባላቸው የትምህርት መስኮች በመምህርነት ሙያ መሰልጠን የሚፈልጉ የምዝገባ ጊዜ ከዛሬ ህዳር 16/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት የምዝገባ ቦታ ከስር በተገለፁ በተመረጡ አምስት ዩኒቨርሲቲዎች በኦንላይን በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚሰጡ የትምህርት አይነቶችና ተዛማጅ የትምህርት መስኮችን ዝርዝር ለማግኘት https://shorturl.at/N8e0s ላይ በመግባት “አማራጭ የመምህራን ስልጠና ትምህርት አይነቶች” የሚለውን በማውረድ ማግኘት ይችላሉ፡፡ የዩኒቨርሲቲ መመዝገቢያ ሊንኮች፦ ➫ ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ፦ https://forms.gle/JZG12devyUvDe3v6 ➫ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ፦ https://docs.google.com/.../1FAIpQLSfQcnu1ThO.../viewform... ➫ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ፦ https://portal.hu.edu.et/Home/AvailablePrograms ➫ ጅማ ዩኒቨርሲቲ፦ https://portal.ju.edu.et ➫ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፦ https://forms.gle/6t1BNV9S67oXwzBv9 የስልጠና ፕሮግራሙ በአንድ ዓመት የሚጠናቀቅ ሲሆን፤ በቀን መርሐግብር የሚማሩ ተማሪዎች የትምህርት ወጪያቸው ሙሉ ለሙሉ በመንግሥት እንደሚሸፈን ተገልጿል። ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉 እስከ 30% በተሻለ ዋጋ የተሻለ ጉዞ በYango ይጓዙ
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
#UniversityOfGondar በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ህዳር 29 እና 30/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ ትምህርት የሚጀምረው ታህሳስ 01/2018 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል። የምዝገባ ቦታ፦ የሁሉም ተማሪዎች ምዝገባ በአጼ ፋሲል ግቢ ይከናወናል። ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ የ12ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ መጠኑ 3×4 የሆነ ሁለት ፎቶግራፍ፣ ➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና ትራስ ልብስ፡፡ ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
#SamaraUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ሠመራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ህዳር 25 እና 26/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ መጠኑ 3×4 የሆነ ስምንት ፎቶግራፍ፣ ➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ ➫ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡ ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
#WoldiaUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ታህሳስ 06 እና 07/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ ትምህርት የሚጀምረው ታህሳስ 08/2018 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል። ➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ መጠኑ 3×4 የሆነ የቅርብ ጊዜ አራት ፎቶግራፍ፣ ➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ ➫ ብሔራዊ መታወቂያ (Fayda)፣ ➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡ ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
‎ ‎የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ የማበልፀጊያ ማዕከላት ጥምረት (Ethiopian University Incubation Center Alliance - EUICA) ተመስርቷል። የዩኒቨርሲቲዎች ‎የማበፀጊያ ማዕከላት በግብርና፣ በዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በጤና፣ በቱሪዝም፣ በአየር ንብረት እና በሌሎችም የፈጠራ ሥራዎች አበርክቷቸውን ለማሳደግ የጥምረቱ መመስረት ጉልህ ድርሻ ይኖረዋል ተብሏል። ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
#TVTI ለ2018 የትምህርት ዘመን በደረጃ VII (የሁለተኛ ዲግሪ) እና በደረጃ VI (የመጀመሪያ ዲግሪ) ትምህርት በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት እንድትሰለጥኑ በክልሎች ተመልምላችሁ ስም ዝርዝራችሁ የተላከ ሰልጣኞች ምዝገባ ከህዳር 15-17/2018 ዓ.ም መሆኑን ኢንስቲትዩቱ አሳውቋል። ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
إظهار الكل...
Repost from TgId: 1401419976
Photo unavailableShow in Telegram
#1Days 1 ቀን ቀረዉ 🏃‍♂🏃‍♂ የ ተለያዩ ድርጅቶችን ኔትዎርክ ሰብራችሁ ምትገቡበት የ RED TEAMING ስልጠና ምዝገባ ጥቂት ሰዓታት ቀሩት በ ኢትዮጵያ 🇪🇹 የመጀመርያ የሆነዉን እድል ከማለፉ በፊት ተጠቀሙበት❤️ ➡️አሁኑኑ ይመዝገቡ: https://course.geezsecurity.com/course/gtcrt ለበለጠ መረጃ👇👇 Contact Us ✅ @geezsecsupport 📞 +251953537820 📬 info@geezsecurity.com #GTCRT @geeztechgroup
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
#DebreTaborUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ህዳር 25 እና 26/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ስምንት መጠኑ 3×4 የሆነ ፎቶግራፍ፣ ➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ ➫ ብሔራዊ መታወቂያ (Fayda)፣ ➫ የሌሊት አልባሳት እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
إظهار الكل...
የትምህርት ሚኒስትሩ በሲንጋፖር አምባሳደር የተመራ የልዑካን ቡድንን ተቀብለው አነጋገሩ። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የሲንጋፖር አምባሳደርንና በሲንጋፖር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ጉዳይ ኃላፊን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። በዚሁ ጊዜ ክቡር ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓቱን በማሻሻል ፍትሃዊና ጥራት ያለው ትምህርትን ለሁሉም ዜጎች ለመስጠት እየወሰደቻቸው ያሉ የሪፎርም ተግባራትን ለልኡካን ቡድኑ ገልፀዋል። በተለይም ኢትዮጵያ በጀመረቻቸው አዳዲስ የልማት እቅዶች እንደ ፔትሮ ኬሚካል፣ ማዕድን ልማት፣ ቱሪዝም፣ ኒውክለር ሳይንስ እና በመሳሰሉት የትምህርት መስኮች ላይ በትብብር የመስራት ፍላጎት እንዳለ አንስተዋል። የልዑካን ቡድኑን የመሩት አምባሳደር H.E Aselverjah በበኩላቸው ሲንጋፖር ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትብብር የበለጠ አጠናክራ በመቀጠል በቴክኖሎጂ ልውውጥ፣ በአቅም ግንባታ፣ በሥርዓተ ትምህርትና ነጻ የትምህርት እድል በመስጠት ረገድ በትብብር መስራት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል። ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
#Digital_ID በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የምትወስዱ ተማሪዎች የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ እንድታወጡ ይጠበቃል። ማንኛውም ተማሪ የመልቀቂያ ፈተናውን ለመውሰድ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ሊኖረው እንደሚገባ ትምህርት ሚኒስቴር መወሰኑ ይታወሳል። በመሆኑም በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ የሆናችሁ ተማሪዎች በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ማውጫ ማዕከል በመመዝገብ መታወቂያውን ማውጣት ይኖርባችኋል። ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
إظهار الكل...
Repost from TgId: 1401419976
Photo unavailableShow in Telegram
🧑‍💻 #GTCRT v1 – Intermediate Cyber RED TEAM Training 📣 ⚡️ የመካከለኛ ደረጃ የ Red Teaming ኮርስ – ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ☄️ ⚡️ Course Highlights 🩷 Duration: 3 Months 🩷 Difficulty: Intermediate to Advanced ✅ Key Modules You'll Master: ✅ External Reconnaissance (Passive & Active) ✅ Initial Access (Phishing, Weaponization, Delivery) ✅ Pivoting and Tunneling ✅ Privilege Escalation (Windows & Linux) ✅ Lateral Movement & Persistence ✅ AD Exploitation & Domain Dominance ✅ OpSec & Evasion Techniques ✅ Full-Scope Attack Path Simulation within AWS LAB 👑 Ideal for: ✔️Aspiring Penetration Testers ✔️SOC Analysts moving to Offensive Security ✔️System/Network Admins hardening their environments ✔️Anyone ready to Think Like an Adversary Register Now: https://course.geezsecurity.com/course/gtcrt ለበለጠ መረጃ👇👇 Contact Us ✅ @geezsecsupport 📞 +251953537820 📬 info@geezsecurity.com #GTCRT @geeztechgroup
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ስቴም ማዕከል የዩኒቨርሲቲው መደበኛ ተማሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የ2018 ዓ.ም የሳምንት መጨረሻ ፕሮግራም አስጀምሯል። ፕሮግራሙ መደበኛ ተማሪዎች የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነሪንግ እና ሂሳብ (STEM) ክህሎቶች እነዲያጎለብቱ ለማድረግ የሚያስችል ነው ተብሏል። ሰልጣኝ ተማሪዎቹ ከዩኒቨርሲቲው ኮሌጆች/ትምህርት ቤቶች የተመለመሉ ሲሆኑ፤ መሰረታዊ የኮምፒውተር፣ የኤሌክትሮኒክስ፣ ሮቦቲክስ እና ኮዲንግ ክህሎቶች ለማጎልበት የሚያስችሉ ስልጠና እንደሚሰጣቸው ተገልጿል፡፡ ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
إظهار الكل...
Repost from TgId: 1401419976
00:53
Video unavailableShow in Telegram
Red Team Engagement❤️ አሁኑኑ ተመዝገቡ: https://course.geezsecurity.com/course/gtcrt ለበለጠ መረጃ👇👇 Contact Us ✅ @geezsecsupport 📞 +251953537820 📬 info@geezsecurity.com #GTCRT @geeztechgroup
إظهار الكل...
6.16 MB
Photo unavailableShow in Telegram
#AssosaUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ታህሳስ 02 እና 03/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። ትምህርት ታህሳስ 04/2018 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል። ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና 2 ኮፒ፣ ➫ የ12ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና 2 ኮፒ፣ ➫ ስምንት መጠኑ 3×4 የሆነ ፎቶግራፍ፣ ➫ ብሔራዊ መታወቂያ ፋይዳ (National ID)፣ ➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ ➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡ ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
#WolloUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ወሎ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ህዳር 25 እና 26/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። የምዝገባ ቦታ፦ ➫ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በኮምቦልቻ ግቢ ➫ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በደሴ ግቢ ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የ8ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ የ12ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና 2 ኮፒ፣ ➫ አራት መጠኑ 3×4 የሆነ ፎቶግራፍ፣ ➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ልብስ፡፡ ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
#BuleHoraUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባ ህዳር 29 እና 30/2018 ዓ.ም የሚከናወን መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። ትምህርት ታህሳስ 01/2018 ዓ.ም ይጀመራል ተብሏል፡፡ ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና 2 ኮፒ፣ ➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና 2 ኮፒ፣ ➫ ስምንት 3x4 መጠን የሆነ ፎቶግራፍ፣ ➫ የብሔራዊ መታወቂያ ፋይዳ (National ID) ፣ ➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ፣ ➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡ ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
#ETA የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት በትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ተገምግሞ ተቀባይነት ያገኘን ስርዓተ ትምህርት በመከተል ትምህርት እንዲሰጡ አሳስቧል፡፡ ማንኛውም ከፍተኛ ትምህርት ተቋም የሀገሪቱን የትምህርት ፖሊሲ ተከትሎ በተዘጋጀ ስርዓተ ትምህርት ተማሪ መቀበል፣ ማስተማር እና ማስመረቅ እንዳለበት ባለሥልጣኑ ገልጿል፡፡ ይህን የተላለፈ ተቋም በትምህርት መስኩ ለሁለት ዓመት አዲስ ተማሪ እንዳይቀበል ቅጣት እንደሚጣልበታል እና ስርዓተ ትምህርቱን ያልተከተለ የትምህርት መስክ እንዲዘጋ እንደሚደረግም ተመላክቷል፡፡ ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
إظهار الكل...
Repost from TgId: 1401419976
Photo unavailableShow in Telegram
After Exploiting a Company and Got Inital Access the Next Step is moving to the internal network for that you have to know how to tunnel and pivot using the jump host. Register And Learn Now: https://course.geezsecurity.com/course/gtcrt ለበለጠ መረጃ👇👇 Contact Us ✅ @geezsecsupport 📞 +251953537820 📬 info@geezsecurity.com #GTCRT @geeztechgroup
إظهار الكل...
የተማሪዎቹ ጥያቄ ምንድነው ? " ውሳኔው ተቀባይነት የሌለው ነው " - ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የ3ኛ ዓመት ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ ለ1 ዓመት የማስተማር አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስገድደው መመሪያ በ2019 የትምህርት ዘመን ተግባራዊ መሆን ይጀምራል መባሉን መዘገቡ ይታወቃል። ውሳኔው በሚመለከት ለምክር ቤት አባላት ቀርበው ያብራሩት የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)  " ለመምህራን የሚቀርበው ጥቅማጥቅምና ደመወዝ በቂ አለመሆን ለመምህራን እጥረት ምክንያት እንደሆነ " አስረድተዋል። ይህም አዲስ መምህራንን በበቂ ሁኔታ ለማፍራት አስቸጋሪ እንዳረገው ተገልጿል። ይህንንም ለመቅረፍ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት ሲሰጡ፣ የበለጠ የመምህርነት ሙያ ፍቅር ሊያጎለብቱ እንደሚችሉም መገለጹን ተከትሎ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዘንድ ውሳኔው ከፍተኛ ቅሬታ ፈጥሯል። ጉዳዩ ከተሰማበት ቀን አንስቶ በተለያዩ የሃገሪቱ ዩንቨርስቲዎች መነጋገሪያ የሆነው ይህ ውሳኔ በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ተቃውሞ ለማሰማት ሰልፍ ማድረጋቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከተማሪዎች ሰምቷል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከበርካታ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ስለጉዳዩ በማነጋገር እንደተረዳው ጉዳዩን በሚዲያ ላይ ከመስማት በቀር በአሁኑ ሰዓት የሦስተኛ ዓመት ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ ተማሪዎች የሚቀጥለው አመት የማስተማር አገልግሎት ስለመስጠታቸው ከዩኒቨርሲቲያቸው በኩል የተገለጸላቸው ነገር የለም። ከሃዋሳ ፣ ባህርዳር፣ ወለጋ፣ አምቦ፣ ደምቢ ዶሎ፣ መደወላቡ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ድሬዳዋ፣ ሐዋሳ ፣ ደብረ ብርሃን እንዲሁም ከአርባምንጭ ዩንቨርሲቲዎች ያነጋገርናቸው ተማሪዎች ጉዳዩን በመደናገጥ መስማታቸውን ገልጸው ውሳኔውን ግራ አጋቢ ሲሉ ገልጸውታል። ተማሪዎቹ በሰጡን ቃል " በጉዳዩ ላይ ጥርት ያለ የሰማነው ነገር የለም እንዴት እንደምንሄድ፣ ሰርቪሱን በምን አይነት መንገድ እንደምንሰጥ ያወቅነው ነገር የለም ጉዳዩ ግራ አጋቢ ሆኖብናል " ነው ያሉት። ቃላቸውን የሰጡን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ውሳኔውን እንዲሰሙበት ከተደረገበት ጊዜ፣ በተለያዩ አካባቢዎች ያለውን የሰላም ሁኔታ እንዲሁም ከትምህርት ቆይታቸው ርዝመት አንጻር በማቅረብ ጉዳዩን " ተቀባይነት የሌለው " ሲሉ ገልጸውታል። ቲክቫህ ያነጋገራቸው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በዝርዝር ምን አሉ ? " መሃል ላይ ገብተን ነው የተነገረን /ይህ ሃሳብ የመጣው ፣አማራጭ እንኳን ማየት የማንችልበት ሁኔታ ላይ ነው ውሳኔውን የሰማነው አንድ አመት ቀልድ አይደለም ለእኛ። በጣም ቅሬታ አለን ካለው ሃገራዊ ሁኔታ አንጻር ክልል ላይ ሄዳቹ ታስተምራላቹ የተባለው ነገር ተቀባይነት የለውም ሰላም የሰፈነበት ሁኔታ ላይ አይደለም ያለነው። ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት መስጠቱ ግዴታ ነው ከተባለም እንደ አማራጭ የትምህርት ቆይታችንን ጨርሰን ካጠናቀቅን በኋላ ቢሆን የተሻለ ነበር ፣የግዴታ ሦስተኛ አመት ላይ ከተባለ አንድ አመት ሙሉ ሌላ ቦታ ውለን ድጋሚ ወደ ትምህርት ልንመለስ ነው ይህ ደግሞ አግባብ አይደለም። በጉዳዩ ላይ ጥርት ያለ የሰማነው ነገር የለም እንዴት እንደምንሄድ፣ ሰርቪሱን በምን አይነት መንገድ እንደምንሰጥ ያወቅነው ነገር የለም ጉዳዩ ግራ አጋቢ ሆኖብናል። ለመቀበል ትንሽ ከብዶናል የእኛ ባች በርካታ ለውጦችን ያየ ነው ፣ ሬሚዲያል የተጀመረበት ነው ከሦስት እና ከአራት አመት በፊት ፍሬሽማን ኮርስ ተጀምሮ የሦስት አመት ዲግሪ ወደ አራት ከፍ አለ አሁን ደግሞ አገልግሎት ይጀምራል ከተባለ አምስት እና ስድስት አመት ልንቆይ ነው ማለት ነው። ከትምህርት አለም ርቀን ድጋሚ ወደ ትምህርት አለም መመለስ ማለት ከባድ ነው የዲፓርትመንት ኮርሶች ተያያዥ ኮርሶች ስለሆኑ አንድ አመት መስክ ላይ ቆይቶ በድጋሚ ወደ ትምህርት መመለስ የዩኒቨርሲቲ ቆይታችንን ከባድ ያደርግብናል። መውጫ ፈተና ያለብን ከመሆኑም አኳያ የንባብ ጊዜያችንን የሚያጣብብ በመሆኑ ለመቀበል ከብዶናል። አገልግሎቱን ብንቀበለው እንኳን ለምሳሌ የህክምና ተማሪዎች ኢንተርንሺፕ እየወጡ ነገር ግን የሚመረቁበት አመት አይገፋም የእኛም ቢሆን ደስ የሚለን ተመሳሳዩን መንገድ ነው። ' ታስተምራላቹ ' ከተባለ እንኳን የትኞቹ ተማሪዎች እና ምን አይነት የአቅም ደረጃ ላይ ያሉት ያስተምራሉ የሚለው ግልጽ አይደለም። ሁሉም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለክረምት እረፍት ሦስት ወር ከሰኔ ጀምሮ እስከ ነሐሴ እናርፋለን ይህንን ሦስት ወር አገልግሉ በተባልንበት ቦታ ሁሉ አገልግለን በቀጣይ አመት ወደ ትምህርታችን መመለስ ነው የምንፈልገው። ካለቀ በኋላ አስተምሩ ብንባል በበጎ ፈቃድ ወጥተን በደስታ እናገለግላለን ነገር ግን አንድ አመት ተገፍቶ ከሆነ ግን ከትምህርቱ መንፈስ እንወጣለን። ዛሬ ነገ ይመረቅልኛል ብሎ የሚጠብቅ ወላጅ አንድ አመት ተጨምሯል ስትላቸው ተስፋቸው እያጠረ ይመጣል አብዛኛው የዩኒቨርሲቲ ተማሪ የደሃ ልጅ ነው በደሃ ቤተሰብ ላይ አንድ አመት መጨመር በጣም ይከብዳል። በምን አይነት መንገድ ተገምግሞ እዚህ ሃሳብ ላይ እንደተደረሰ ባይገባንም በውሳኔው ደስተኞ አይደለንም የምደባ ቦታችንም አሳስቢ ነው "ሲሉ ገልጸዋል ። በጉዳዩ ዙሪያ እስካሁን ከትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠ ተጨማሪ ማብራሪያ የለም። ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
إظهار الكل...
1.69 MB