uz
Feedback
ATC NEWS

ATC NEWS

Kanalga Telegram’da o‘tish

#ADDIS_ABABA : ETHIOPIA ለመልዕክት 👇🏻 @mujaabot For Advertisement👇🏿 @atcads

Ko'proq ko'rsatish
2025 yil raqamlardasnowflakes fon
card fon
127 423
Obunachilar
-6624 soatlar
-2667 kunlar
-76830 kunlar
Postlar arxiv
Photo unavailableShow in Telegram
#MoE ትምህርት ሚኒስቴር ሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመጀመሪያ መንፈቀ-ዓመት መረጃን በተዘጋጀው የከፍተኛ ትምህርት የመረጃ ስርዓት (HEMIS) እንዲያስገቡ አሳስቧል፡፡ በትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጡሹኔ በቀን ህዳር 16/2018 ዓ.ም ተፈርሞ ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተላከ ሰርኩላር፥ ሁሉም ተቋማት መረጃቸውን በተዘጋጀው ሲስተም ላይ የማስገባት ግዴታ እንዳለባቸው ይገልጻል። በመሆኑም የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያው መንፈቀ-ዓመት ሁሉም መረጃዎች ተሟልተውና በየተቋሙ አመራር ተረጋግጠው እስከ ታህሳስ 25/2018 ዓ.ም በሲስተሙ (http://hemis.ethernet.edu.et) እንዲያስገቡ ጠይቋል፡፡ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ይህን ተከታትሎ የማስፈፀም ኃላፊነት እንደተሰጠው የተገለፀ ሲሆን፤ መረጃውን የማያስገቡ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመንግሥት በሚሰጡ አገልግሎቶች እንደማይስተናገዱ ተጠቁሟል። ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉 እስከ 30% በተሻለ ዋጋ የተሻለ ጉዞ በYango ይጓዙ
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
#WerabeUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ወራቤ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ታህሳስ 02 እና 03/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ ከ8ኛ ክፍል ጀምሮ ያሉ የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣ ➫ መጠኑ 3×4 የሆነ ሁለት ፎቶግራፍ፣ ➫ ብሔራዊ መታወቂያ (Fayda)፣ ➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ ➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡ ከህዳር 21 እስከ ታህሳስ 01/2018 ዓ.ም ድረስ registrar.wru.edu.et የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም የተጠየቁ መረጃዎችን እንድትሞሉ ይጠበቅባችኋል። ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
#MoE ትምህርት ሚኒስቴር በተለያዩ የሙያ ዘርፎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀው የመምህርነት ሙያን መቀላቀል ለሚፈልጉ የአንድ ዓመት ስልጠና ሊሰጥ ነው፡፡ ስልጠናው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ በተመረጡ አምስት ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል፡፡ የምዝገባ መስፈርት፦ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቁና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በሚሰጡ የትምህርት ዓይነቶች እና ተዛማጅነት ባላቸው የትምህርት መስኮች በመምህርነት ሙያ መሰልጠን የሚፈልጉ የምዝገባ ጊዜ ከዛሬ ህዳር 16/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት የምዝገባ ቦታ ከስር በተገለፁ በተመረጡ አምስት ዩኒቨርሲቲዎች በኦንላይን በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚሰጡ የትምህርት አይነቶችና ተዛማጅ የትምህርት መስኮችን ዝርዝር ለማግኘት https://shorturl.at/N8e0s ላይ በመግባት “አማራጭ የመምህራን ስልጠና ትምህርት አይነቶች” የሚለውን በማውረድ ማግኘት ይችላሉ፡፡ የዩኒቨርሲቲ መመዝገቢያ ሊንኮች፦ ➫ ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ፦ https://forms.gle/JZG12devyUvDe3v6 ➫ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ፦ https://docs.google.com/.../1FAIpQLSfQcnu1ThO.../viewform... ➫ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ፦ https://portal.hu.edu.et/Home/AvailablePrograms ➫ ጅማ ዩኒቨርሲቲ፦ https://portal.ju.edu.et ➫ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፦ https://forms.gle/6t1BNV9S67oXwzBv9 የስልጠና ፕሮግራሙ በአንድ ዓመት የሚጠናቀቅ ሲሆን፤ በቀን መርሐግብር የሚማሩ ተማሪዎች የትምህርት ወጪያቸው ሙሉ ለሙሉ በመንግሥት እንደሚሸፈን ተገልጿል። ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉 እስከ 30% በተሻለ ዋጋ የተሻለ ጉዞ በYango ይጓዙ
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
#UniversityOfGondar በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ህዳር 29 እና 30/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ ትምህርት የሚጀምረው ታህሳስ 01/2018 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል። የምዝገባ ቦታ፦ የሁሉም ተማሪዎች ምዝገባ በአጼ ፋሲል ግቢ ይከናወናል። ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ የ12ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ መጠኑ 3×4 የሆነ ሁለት ፎቶግራፍ፣ ➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና ትራስ ልብስ፡፡ ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
#SamaraUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ሠመራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ህዳር 25 እና 26/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ መጠኑ 3×4 የሆነ ስምንት ፎቶግራፍ፣ ➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ ➫ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡ ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
#WoldiaUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ታህሳስ 06 እና 07/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ ትምህርት የሚጀምረው ታህሳስ 08/2018 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል። ➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ መጠኑ 3×4 የሆነ የቅርብ ጊዜ አራት ፎቶግራፍ፣ ➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ ➫ ብሔራዊ መታወቂያ (Fayda)፣ ➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡ ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
‎ ‎የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ የማበልፀጊያ ማዕከላት ጥምረት (Ethiopian University Incubation Center Alliance - EUICA) ተመስርቷል። የዩኒቨርሲቲዎች ‎የማበፀጊያ ማዕከላት በግብርና፣ በዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በጤና፣ በቱሪዝም፣ በአየር ንብረት እና በሌሎችም የፈጠራ ሥራዎች አበርክቷቸውን ለማሳደግ የጥምረቱ መመስረት ጉልህ ድርሻ ይኖረዋል ተብሏል። ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
#TVTI ለ2018 የትምህርት ዘመን በደረጃ VII (የሁለተኛ ዲግሪ) እና በደረጃ VI (የመጀመሪያ ዲግሪ) ትምህርት በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት እንድትሰለጥኑ በክልሎች ተመልምላችሁ ስም ዝርዝራችሁ የተላከ ሰልጣኞች ምዝገባ ከህዳር 15-17/2018 ዓ.ም መሆኑን ኢንስቲትዩቱ አሳውቋል። ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Hammasini ko'rsatish...
Repost from TgId: 1401419976
Photo unavailableShow in Telegram
#1Days 1 ቀን ቀረዉ 🏃‍♂🏃‍♂ የ ተለያዩ ድርጅቶችን ኔትዎርክ ሰብራችሁ ምትገቡበት የ RED TEAMING ስልጠና ምዝገባ ጥቂት ሰዓታት ቀሩት በ ኢትዮጵያ 🇪🇹 የመጀመርያ የሆነዉን እድል ከማለፉ በፊት ተጠቀሙበት❤️ ➡️አሁኑኑ ይመዝገቡ: https://course.geezsecurity.com/course/gtcrt ለበለጠ መረጃ👇👇 Contact Us ✅ @geezsecsupport 📞 +251953537820 📬 info@geezsecurity.com #GTCRT @geeztechgroup
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
#DebreTaborUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ህዳር 25 እና 26/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ስምንት መጠኑ 3×4 የሆነ ፎቶግራፍ፣ ➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ ➫ ብሔራዊ መታወቂያ (Fayda)፣ ➫ የሌሊት አልባሳት እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
Hammasini ko'rsatish...
የትምህርት ሚኒስትሩ በሲንጋፖር አምባሳደር የተመራ የልዑካን ቡድንን ተቀብለው አነጋገሩ። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የሲንጋፖር አምባሳደርንና በሲንጋፖር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ጉዳይ ኃላፊን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። በዚሁ ጊዜ ክቡር ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓቱን በማሻሻል ፍትሃዊና ጥራት ያለው ትምህርትን ለሁሉም ዜጎች ለመስጠት እየወሰደቻቸው ያሉ የሪፎርም ተግባራትን ለልኡካን ቡድኑ ገልፀዋል። በተለይም ኢትዮጵያ በጀመረቻቸው አዳዲስ የልማት እቅዶች እንደ ፔትሮ ኬሚካል፣ ማዕድን ልማት፣ ቱሪዝም፣ ኒውክለር ሳይንስ እና በመሳሰሉት የትምህርት መስኮች ላይ በትብብር የመስራት ፍላጎት እንዳለ አንስተዋል። የልዑካን ቡድኑን የመሩት አምባሳደር H.E Aselverjah በበኩላቸው ሲንጋፖር ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትብብር የበለጠ አጠናክራ በመቀጠል በቴክኖሎጂ ልውውጥ፣ በአቅም ግንባታ፣ በሥርዓተ ትምህርትና ነጻ የትምህርት እድል በመስጠት ረገድ በትብብር መስራት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል። ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
#Digital_ID በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የምትወስዱ ተማሪዎች የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ እንድታወጡ ይጠበቃል። ማንኛውም ተማሪ የመልቀቂያ ፈተናውን ለመውሰድ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ሊኖረው እንደሚገባ ትምህርት ሚኒስቴር መወሰኑ ይታወሳል። በመሆኑም በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ የሆናችሁ ተማሪዎች በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ማውጫ ማዕከል በመመዝገብ መታወቂያውን ማውጣት ይኖርባችኋል። ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Hammasini ko'rsatish...
Repost from TgId: 1401419976
Photo unavailableShow in Telegram
🧑‍💻 #GTCRT v1 – Intermediate Cyber RED TEAM Training 📣 ⚡️ የመካከለኛ ደረጃ የ Red Teaming ኮርስ – ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ☄️ ⚡️ Course Highlights 🩷 Duration: 3 Months 🩷 Difficulty: Intermediate to Advanced ✅ Key Modules You'll Master: ✅ External Reconnaissance (Passive & Active) ✅ Initial Access (Phishing, Weaponization, Delivery) ✅ Pivoting and Tunneling ✅ Privilege Escalation (Windows & Linux) ✅ Lateral Movement & Persistence ✅ AD Exploitation & Domain Dominance ✅ OpSec & Evasion Techniques ✅ Full-Scope Attack Path Simulation within AWS LAB 👑 Ideal for: ✔️Aspiring Penetration Testers ✔️SOC Analysts moving to Offensive Security ✔️System/Network Admins hardening their environments ✔️Anyone ready to Think Like an Adversary Register Now: https://course.geezsecurity.com/course/gtcrt ለበለጠ መረጃ👇👇 Contact Us ✅ @geezsecsupport 📞 +251953537820 📬 info@geezsecurity.com #GTCRT @geeztechgroup
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ስቴም ማዕከል የዩኒቨርሲቲው መደበኛ ተማሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የ2018 ዓ.ም የሳምንት መጨረሻ ፕሮግራም አስጀምሯል። ፕሮግራሙ መደበኛ ተማሪዎች የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነሪንግ እና ሂሳብ (STEM) ክህሎቶች እነዲያጎለብቱ ለማድረግ የሚያስችል ነው ተብሏል። ሰልጣኝ ተማሪዎቹ ከዩኒቨርሲቲው ኮሌጆች/ትምህርት ቤቶች የተመለመሉ ሲሆኑ፤ መሰረታዊ የኮምፒውተር፣ የኤሌክትሮኒክስ፣ ሮቦቲክስ እና ኮዲንግ ክህሎቶች ለማጎልበት የሚያስችሉ ስልጠና እንደሚሰጣቸው ተገልጿል፡፡ ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Hammasini ko'rsatish...
Repost from TgId: 1401419976
00:53
Video unavailableShow in Telegram
Red Team Engagement❤️ አሁኑኑ ተመዝገቡ: https://course.geezsecurity.com/course/gtcrt ለበለጠ መረጃ👇👇 Contact Us ✅ @geezsecsupport 📞 +251953537820 📬 info@geezsecurity.com #GTCRT @geeztechgroup
Hammasini ko'rsatish...
6.16 MB
Photo unavailableShow in Telegram
#AssosaUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ታህሳስ 02 እና 03/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። ትምህርት ታህሳስ 04/2018 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል። ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና 2 ኮፒ፣ ➫ የ12ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና 2 ኮፒ፣ ➫ ስምንት መጠኑ 3×4 የሆነ ፎቶግራፍ፣ ➫ ብሔራዊ መታወቂያ ፋይዳ (National ID)፣ ➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ ➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡ ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
#WolloUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ወሎ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ህዳር 25 እና 26/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። የምዝገባ ቦታ፦ ➫ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በኮምቦልቻ ግቢ ➫ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በደሴ ግቢ ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የ8ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ የ12ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና 2 ኮፒ፣ ➫ አራት መጠኑ 3×4 የሆነ ፎቶግራፍ፣ ➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ልብስ፡፡ ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
#BuleHoraUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባ ህዳር 29 እና 30/2018 ዓ.ም የሚከናወን መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። ትምህርት ታህሳስ 01/2018 ዓ.ም ይጀመራል ተብሏል፡፡ ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና 2 ኮፒ፣ ➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና 2 ኮፒ፣ ➫ ስምንት 3x4 መጠን የሆነ ፎቶግራፍ፣ ➫ የብሔራዊ መታወቂያ ፋይዳ (National ID) ፣ ➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ፣ ➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡ ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Hammasini ko'rsatish...