ch
Feedback
Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

前往频道在 Telegram

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

显示更多
2025 年数字统计snowflakes fon
card fon
228 606
订阅者
-14224 小时
-1 0407
-4 59630
帖子存档
照片不可用在 Telegram 中显示
መጥተናል ገባ ገባ በሉማ…! "…ዘወትር በየሳምንቱ በእለተ ሐሙስ በኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ የምናቀርብላችሁ ሳምንታዊ መርሀ ግብራችን አሁን ጀምሯል። የዛሬውንም ዝግጅታችንን፦ በ የዛሬው ዝግጅታችን ከዘመዴ ጋር 👉በዩቱብ /YouTube ♦https://www.youtube.com/live/PM5bE40s7pA?si=nd399JWK15cOPKFZ 👉በፌስቡክ Facebook ♦facebook.com/ethiobeteseb 👉    በቲውተር / Twitter ♦https://twitter.com/EBeteseb 👉 ቴሌግራም / Telegram ♦https://t.me/ethiobeteseb "…ሻሎም !  ሰላም !
显示全部...
🙏 279 137👍 98🔥 6🤯 6🤔 4😱 3🏆 3🕊 2
照片不可用在 Telegram 中显示
"…እነሆ፥ በአገሩ ውስጥ እረኛ አስነሣለሁ፤ እርሱም የጠፋውን አያስብም፥ የባዘነውን አይፈልግም፥ የተሰበረውን አይጠግንም፤ የዳነውንም አይቀልብም፥ ነገር ግን የሰባውን ሥጋ ይበላል፥ ሰኰናውንም ይቀለጣጥማል። መንጋውን ለሚተው ለምናምንቴ እረኛ ወዮለት! ሰይፍ በክንዱና በቀኝ ዓይኑ ላይ ይሆናል፤ ክንዱም አጥብቃ ትደርቃለች፥ ቀኝ ዓይኑም ፈጽሞ ትጨልማለች። ዘካ 11፥ 16-17 "…እንደምን አደራችሁ? "…እንደምን አረፈዳችሁ? "…እንደምን ዋላችሁ? "…እንደምን አመሻችሁ? "…መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
显示全部...
star reaction 2🙏 947 236👍 117💔 59🕊 20😡 9😱 6 4🤔 3
照片不可用在 Telegram 中显示
መልካም… "…የእኔ የዛሬው ርእሰ አንቀጽ ያነበባችሁትን የመሰለ ነበር። ይሄ የእኔ ምልከታ ነው። አሁን ደግሞ አሰብንና ወደብን በተመለከተ  የእናንተን ዕይታና ምልከታ የምናነብበት ጊዜ ነው። ከአሁኗ ደቂቃ ጀምሮ እስከ እኩለለ ሌሊት ድረስ የእናንተን ጣፋጭም ሆነ መራራ፣ ማርም ሆነ ሬት፣ ሬት የሚል ነገር ግን በጨዋ ደንብ ተዘጋጅቶ የሚሰጥ አስተያየት ስንኮመኩም እናመሻለን። • ጀምሩ… ✍✍✍
显示全部...
star reaction 5 530👍 196🏆 38🙏 33😡 13 10🔥 7🕊 6💔 3
👆⑤✍✍✍ የተቆረጠ ሃውልት በመሃል አሩሲ ተክላ፣ ድርሰቱን ኤርትራዊው ተስፋዬ ገብረ እባብ እንዲደርሰው አድርጋ፣ እነ አቢይ አሕመድ፣ እነ አባዱላ ገመዳ ቆመው ያሠሩት ሃውልት፣ በትምህርት ካሪኩለም ውስጥ ገብቶ ዐማራ ጡትህን ቆረጠው እያሉ እያስተማሩት አሳድገው፣ ትምህርት ቤቶች በተማሪ የጉብኝት መርሀ ግብር ተዘጋጅቶላቸው አኖሌ ድረስ እንዲሄዱ ተደርገው፣ የኦሮሞ ሕጻናት ቂም በቀል ይዘው እንዲያድጉ ተደርገው ዛሬ እነዚያ ሕጻናት አድገው ነው በአሩሲ ዐማራ ሲያዩ በማረድ የተበቀሉ እንዲመስላቸው የተደረገው። እናም ዐማራ አሁን በመኖርና ባለመኖር፣ በኅልውና ጉዳይ እየደከመ፣ እየታገለ ስለሆነ አታስቸግሩት። ደግሞም ስሙ አያምርም። ደመ መራራም ነው። ዐመድ አፋሽም ነው ዐማራ። ታስታውሱ እንደሆነ ኤርትራና ኦሮሙማ ትግራይ ገብተው ቢዘርፉ፣ ቢገድሉ፣ ቢደፍሩ የተወገዘው፣ የተሰደበው፣ ሂሳብ እናወራርዳለን የተባለው ግን በቦታው ያልነበረው ዐማራው ነው። ኦሮሞ እየገረፈው ትግሬ ይዝት የነበረው በዐማራ ላይ ነበር። ጌታቸው ረዳ ትግሬን አስጨፍጭፎ ሄዶ የተለጠፈው ድንክ፣ ማይም ሲለው ከነበረው ከአቢይ አሕመድ ዘንድ ነው። እናም ዐማራ የቤት ሥራህን ዝም ብለህ ሥራ። የማቴዎስ ወንጌል ምእ 10፥ 16 ን ኑረው። መጀመሪያ የሚቀድመው ኅልውናህ ነው። ብልጼዎች ግን ይቅናችሁ። ከግድቡ ወደ ወደቡ መልካም ጉዞ ይሁንላችሁ። በፍጹም በእኔ በኩል ምንም አይነት እንቅፋት የሚሆን ቃል አላወጣባችሁም። ብቻ ራሳችሁን ችላችሁ ውረሩ፣ ስፈሩ። በጓሮ በር እየመጣችሁ አትነዝንዙን። ደርሶ ሀገር ወዳድ ሌላውን ባንዳ ለማድረግ አትድከሙ። አቋሜ ይኸው ነው። እኔንም ዐማራን ለዛሬ ተፋቱን። ከቻላችሁ በኦሮሚያ የምታርዱትን ዐማራ ራሩለት። አይ ካላችሁም እሱም እንደ ዐማራ ክልሉ ነቅቶ ራሱን ለመከላከል እስኪቆርጥ ድረስ ግረፉት። በብላሽ፣ በነፃ መታረድ እስኪያቆም ድረስ ቆንጥጡት። ሌላ ምን ይባላል። "…በተረፈ አቢይ አሕመድ ኤርትራ ገብቶ ሲፈተፍት፣ ዓረቦቹ ፊት ሄዶ ሲፈራረም ጀግና፣ ሀገር ወዳድ ተብሎ የሚያመሰግን የጎንደር ስኳድና የግንቦት ሰባት የብርሃኑ ነጋ ግርፍ ሁላ፣ አቢይ አሕመድ ኤርትራን ጋብዞ ትግሬን ሲጨፈጭፍ ጀግና ጎበዝ ሲል የነበረ ገተት ሁላ፣ ጄነራል በለው ጥርሱ የተተከለለት ዶር ዳኛቸው፣ ይሄ ነገር የሀገር ሉዓላዊነት የሚጥስ ተግባር ነው የሚሉ ኢትዮጵያውያንን በወያኔነት እየፈረጀ ከሻአቢያ ጋር በአንድ ፖፖ ካልተጸዳዳን፣ በአንድ ግልገል ሱሪ ካልተጠቀምን እያለ ሲያሸማቅቀን የኖረ መንጋ፣ ነውረኛ ሁላ፣ የኤርትራ ፍቅር፣ የሻአቢያ ውለታን ከፍለን አንጨርሰውም ሲለኝ የነበረ ቀፈታም ሁላ፣ ዛሬ ደርሶ ዐማራው ከመቼ ወዲያ ነው በብሔራዊ ጥቅም፣ በሉዓላዊነት ጉዳይ እንዲህ ወደ ኋላ ያለው?  ብሎ አጉል ልፈላሰፍ ቢል ጥፋ ከዚህ ነው የምለው። ተመልከቱ ልብም በሉ አያሌው መንበርም ሆነ ይድነቃቸው ታደለ ዐማራ ስላልሆኑ የዐማራን መፈናቀል፣ የዐማራን መሞት አይዘግቡም። ድምጽ አይሆኑም። ዐማራ ኤርትራ ገብቶ ከአቢይ ጋር ካልተዋጋ ግን ሞተን እንገኛለን ነው የሚሉት። አያሌው መንበር የሚደግፋቸው የጎንደር ፋኖ ፋፍዴኖቹ፣ እነ ደረጄም ጥይት የሚሰጣቸው ሻአቢያ ነው። አያሌው መንበር ግን ጓ ብሎ ሀገር ይያዝ የሚለው ሻአቢያ ለእነ ሀብቴ፣ ለእነ ምሬ፣ ለእነ ደሳለኝ እና ለእነ ዘመነ ጥይት ስትሰጥ ነው። እስክንድር በገሃድ አሰብን፣ ወደብን አንጠይቅም ብሎ ሻአቢያን ሲለማመጥ እስክንድር የእነሱ ስለሆነ ክንፍ የሌለው መልአክ ነው። እኔ ደጋፊው ባልሆንም ጄነራል ተፈራ ማሞ ግን አቢይ ሰሜኖቹን ሊያጠፋ ነውና ልንነቃ ይገባል ሲል አገር ይያዝልኝ ብሎ አዋራ ማስነሳት። ይሄን እርድና እዚያው በጸበልህ አባቴ። ከእነ ዘመነ እስክንድር ይሻለኛል ትላለህ። ዘመነም፣ እስክንድርም ጥይት የሚቀበሉት ግን ከሻአቢያ ነው። ምነው ከሥጋው ጦመኛ ነኝ ከመረቁ ስጡኝ አላችሁሳ። የአሰብም፣ የወደብም ጉዞ የሚቃወም ዐማራ ያለ አይመስለኝም። ግን ዐማራ እያለ ያለው መጀመሪያ ከወደቡ በፊት መጨፍጨፌን ገድቡ ነው እያለ ያለው። • ስላነበባችሁኝ በድጋሚ አመሰግናለሁ። • ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ ከራየን ወንዝ ማዶ።
显示全部...
star reaction 3 795👍 274🙏 50🕊 22😡 15🏆 12👌 10🔥 8🤔 7 3 2
👆④✍✍✍ …የዐማራ የሆኑትን ጥንታውያን ቅርሶችና ሀብቶች ሊያወድሙ ይችላሉ። ኦርቶዶክሳዊ ነው የሚባለውን የሰሜኑን ክፍል ኤርትራንና ትግራይን ጨምሮ ከዐማራ ጋር ለማውደም ጽንፈኞቹ የጴንጤና የወሀቢያ እስላሞች ይተባበራሉ። እናም ሰሜነኞቹ ከወዲሁ በሚገባ መሬት ረግጠው ካላሰቡ በቀር የሚመጣው ጊዜ ባይሸነፉ እንኳ ቀላል የሚሆንላቸው አይመስለኝም። "…ቀይ ባህርን ሲወስዱብን ማን እንደሰጣቸው፣ እንዴት እንዳጣነው የተቀመጠ ሰነድ አላገኘንም። በፓርላማ ከሆነ ብለን ፈለግን ምንም ዓይነት ሰነድ አላገኘንም። የተፈረሙ ሰነዶችን ፈለግን አንዳችም መረጃ አላገኘንም። እናም ቀይ ባሕርን እንዴት እንደወሰዱብንና እንዴት ወደባችንን እንዳጣን አናውቅም" በማለት አቢይ ትናንት የተናገረውን ስሰማ ሰውየው አቢይ ሆነ እንጂ ሌላ ሰው ቢናገረው ኑሮ ቢያሻኝ ሻምፓኝ ከፍቼ ስጨፍር አልያም ሻማ አብርቼ ስጸልይ ነበር የማድረው። ግን የተናገረው ፀረ ኢትዮጵያው፣ ፀረ ሰው፣ ጨካኙ፣ አውሬው አቢይ አሕመድ ስለሆነ አልሞቀኝ አልበረደኝም። ነገ ሙልጭ አድርጎ በፈጣጣው አላልኩም፣ አልተናገርኩም ብሎ ለመካድ ሰከንድ የማይፈጅበት የሐሰት አባት ስለተናገረው ሚዛኔ የተዛባ ነው የሚሆነው። እንጂ ንግግሩስ ሃቅ አለው። በመለስ ዜናዊ ፊርማ ነው ኤርትራን ያጣናት፣ አሰብን የወሰዱብን የሚባለውም ሳክስ ነበር ማለት ነው። በጨበጣ ሀገር ተቆርሶ ነው የተወሰደብን ማለት ነው። መለስ ዜናዊም አስር ጊዜ እየወጣ ወደብ ሸቀጥ ነው፣ ከገበያ ላይ እንደ ሽንኩርት፣ እንደ ቲማቲም የምንገዛው ሸቀጥ ነው እያለ እነ ጌታቸው ረዳ ሳይቀሩ እየወጡ ይቦተረፉብን የነበረው ሁላ ውሸት እንደሆነ፣ ወደቡ ከኢትዮጵያ የተገነጠለው በኢትዮጵያ ሀብት ታላቋ ትግራይ ስትመሰረት ያኔ ለእሷ እንዲያገለግል ታስቦ የታችኞቹ ትግሬዎች ለላይኛዎቹ ትግሬዎች በአደራ መልክ ያስቀመጡት እንደሆነ ይሰማኛል። እናም በዚህ መጠን በድፍረት አቢይ መናገሩን ተቃዋሚ አይደለሁም። "…እንግዲህ በሞቅታ ተነግሮ ሕዝብን ጮቤ አስረግጦ፣ ልክ የሶማሊያው ወደብ ተገኘ የተባለ ዕለት "እግዚአብሔር ይመስገን የወደብ ባለቤት ሆንን" በማለት ሲጨፍር ኋላ ላይ እግርህን ብላ ብለው እስከዛሬ ስለበርበራ ወደብ ትንፍሽ እንደማይሉት ሁላ አሁንም እንደዚያው ከሆነ ልናይ ኋላ ብለን ተርተንባቸው እናልፋለን። እንዲያውም የአቢይ አሕመድ የፓርላማ ግልፅ የወረራ ዲስኩር ተጠያቂነትን የሚያመጣና ጫና የሚፈጥርበት መስሎ ከታየው አጀንዳውን ለማስተንፈስ ሲል የተለያዩ አስቂኝም፣ ዘግናኝም አጀንዳዎች ተፈብርከው ሊበተኑልን ይችላሉ። ለምሳሌ ቀላሉና አጀንዳ ማስቀየሻው ነገር በኢትዮጵያ ዐማሮችን እና ኦርቶዶክሳውያንን በገፍ በግፍ መግደል፣ ማረድ ነው። ለዚህ ደግሞ በኦሮሚያ ክልል ለእርድ የተዘጋጁ ሚልዮን ዐማሮችና ኦርቶዶክሳውያን ተዘጋጅተው የሞታቸውን ቀን ይጠባበቃሉ። እናም በኦሮሚያ ኦርቶዶክሳውያን በገፍ ይታረዳሉ። ይጨፈጨፋሉ። የወሀቢይ እስላምም በአገዛዙ ድጋፍ እየታገዘ በኢትዮጵያው እስላም ላይ ይዘምታል። በዐማራ ክልል ድሮን በድሮን ሆኖ ጭፍጨፋ ይጀመራል። የለንደን ፋኖም አቢይ ፓርላማ ላይ ስሙን ያለነገር አላነሳውም እና ለንደኖች ልክ እንደ ዲሲው ግብረ ኃይል በሰርጎ ገቦች ወይ ይፈረካከሳሉ አልያም እንደ ወርቅ ነጥረው ይወጣሉ። እሱን በቅርቡ የምናየው ነው። በጎጃም እና በጎንደር መካከል ሰሜን ጎጃም የሚለው አጀንዳ ተመዝዞ ጎንደርና ጎጃም እንዲነታረክ ይደረጋል። ጫጫታ እንዳይበዛ የጎጃሙ ሸንጎ ቅባታሙ የእነ አረጋ ቡድን መንግሥታዊ ሥልጣኑን ተጠቅሞ አቢይ አሕመድ ሹም ሽር እንዲያደርግ አስገድዶ ሥልጣን ለጎንደሬዎች አሰጥቶ በመለጎም ትኩሳቱ እያበረደ እንዲቆይ ይደረጋል። የኦርቶዶክሳውያን እርድና ጭፍጨፋ ግን በሚዘገንን ሁኔታ በገፍ እንሰማ ይሆናል። እንደመካነ ሠላሙ በኦሮሚያ ለሚታረደው ኦርቶዶክሳዊ መንግሥታዊ መግለጫ እንዳትጠብቁ። ትሰሙታላችሁ። "…እናም ወንድም ዓለሜ ወደ ኋላ ተመልሼ ስነግርህ እኔ የማውቃት ኢትዮጵያ የጥንቷን ነው። ሙሉዋን ኢትዮጵያ። በባሌም ሆነ በቦሌ የሆነ ቀን በሴራ እንዲለያይ የተደረገው ወንድማማች ሕዝብ ሴረኞቹ ሲጠፉ፣ ሲከሽፉም አንድ ላይ የሚሆን ነው ብዬ በተስፋ የምጠባበቅ ሰው ነኝ። ኤርትራና ኢትዮጵያ ታረቁ የተባለ ዕለት በአስመራም በኢትዮጵያም የነበረውን የሕዝብ ደስታ ማስታወሱ እኮ በቂ ነው። ኢሳይያስ አፈወርቂ ከመሞቱ በፊት፣ በወያኔ ሴራ በግድ ሀገር እንዲሆን የፈረዱበትን ኤርትራን በይፋ ከኢትዮጵያ ጋር በዐዋጅ ቀላቅሎ ንስሀ ገብቶ ቢሞት ሁላ ነው የምመኘው። እንደዚያ ቢያደርግ ደግሞ ዓረቦቹም፣ ምዕራባውያኑም፣ የታች ሰፈር ትግሬዎችም የሚፈቅዱለት አይመስለኝም። ተዋርዶ ከሚሞት በሕይወት ሳለ የነጣጠላቸውን ሕዝቦች አንድ አድርጎ በክብር ቢያልፍ ለእሱም ንስሀ ይሆነው ነበር። ነገር ግን ያደርገዋል ተብሎም አይጠበቅም። ሥራው ያውጣው። "…ቀይ ባህር ከተመለሰ፣ ወደብም ከኖረን ግን እስከዛሬ ድረስ በ8 ዓመታት ውስጥ ከእልቂት በቀር፣ ችግኝ በመትከል ሰውን ከመቅበርም በቀር ምንም ዓይነት ሌጋሲ ስለሌለው በከፍተኛ የአእምሮ ስቃይ ውስጥ የሚገኘው አቢይ አሕመድ ከችግኙ ቀጥሎ ወደቡ ሌጋሲ ይሆነው ነበር የሚሉ መተርጉማንም አሉ። እናም እሱ ባያዝበትም እንኳ ለወደቡ ቢታገል አልነቅፈውም። ሆኖም ግን ዓባይን ተሻግሮ አዲስ አበባ መግባት የተከለከለውን ዐማራ ለወደብ፣ ለግድብ ብሎ ተዋጋልኝ ማለት ግን ነውር ነው የሚሆነው። እስከዛሬ ወራሪ፣ ጠቅላይ፣ ኢትዮጵያን በኃይል፣ በጉልበት የፈጠረ፣ ነፍጠኛ እየተባለ ሲወቀስ የኖረው ዐማራ አሁን ደግሞ ኦሮሞን ከዳር ሆኖ እንዲያይ ነው የምመክረው። የዐማራ የእስከዛሬ ድካሙ፣ ሀገር አንድ ለማድረግ የደከመው ድካም በኦሮሞና በትግሬ ዘንድ አልተወደደለትም። ጡት ቆራጭ፣ ነፍጠኛ እየተባለ ትግሬ በመሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ የተሠራ…👇④✍✍✍
显示全部...
387👍 147🔥 9🏆 8🙏 5 4🕊 4😡 4
👆③ ✍✍✍ …የሚል ታዛዥ ተገኝቶ ነው? "…መቼም የብልጽግና አገዛዝ ቡና ሽጦ ዕዳ እንደማይከፍላቸው እያወቁ እኮ ነው እነ አይኤምኤፍ የቢሊዮን ዶላር ብድሮች በላይ በላዩ ሲያሸከሙት የምናየው። ሀገሪቱን ዓይናችን እያየ እየሟሸሸች እኮ ነው። አሁን በዶላር በብድር ዕዳ እስከ አንገታችን እንድንዘፈቅ አድርገውናል። 1 የአሜሪካ ዶላር 160 ብር በባንክ እንዲዘረዘር አድርገዋል። አንድ ሊትር ነዳጅ 120 ብር እንዲሸጥ አድርገዋል። ኑሮው ከመወደዱ የተነሣ አውቶቡስ እንኳ ከተማ ውስጥ በ20 ብር ትኬት እንደሚቆረጥ እየሰማን ነው። ኩንታል ጤፍ 20ሺ፣ ደረቅ እንጀራ 30ብር፣ አንድ እንቁላል ስንት እንደገባ ባላውቅም ሁሉም ነገር የተወደደው ዶላር ተበድሮ ድሮንና ቦንብ ለሚሸምተው አቢይ አሕመድ በገፍ እየሰጡት ስለሆነ ነው። አሁን ላይ ቴሌውንም፣ ባንኩንም፣ አየር መንገዱም ተሽጦ የምንመልሰው አይደለም የዕዳው ክምር። ምንአልባትም አንድ ቀን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮጵላኖች ለሥራ ወጥተው በዚያው በረፉባቸው ሀገራት በዕዳ ተይዘው ላይመለሱ ሁላ ይችላሉ የሚሉም አሉ። እናም ይሄንን የብድር ተራራ ለመናድ የሚቻለው ውድ ማዕድናትን ለአበዳሪዎቹ አሳልፎ በመስጠት ብቻ ነው። "…ሱማሌላንድ ሀገር ስትሆን የምሥራቁ መዓድን በሱማሌላንድ በኩል ይወጣል። በዚያ ወደብም አለ። አሰብ ወደብ የሚያስፈልገው ደግሞ ለወልቃይቱ ፖታሽ፣ ለአዲ ዳውሮው ወርቅ ነው። ጅቡቲ ደግሞ ወደቡ ሩቅ ነው። ቅርቡ አሰብ ነው። እናም ከትግራይ የሚታፈሰው ወርቅ እና ከወልቃይት የሚታፈሰዉን ፖታሽ ዕዳ መክፈያ ሆኖ እየተዛቀ ከኢትዮጵያ ለማውጣት ከጦር መንደርነቱ ባሻገር ወደቡ የግድ አስፈላጊ ነው የሚሆነው። ማዕድናቱን ወዳየ ሀገራቸው በሚያወጡበት ወቅት በመሃል ላይ ምንም ዓይነት ፍተሻ፣ የየትኛውም ሀገር ኬላ መኖር የለበትም። ስለዚህ ሱማሌላንድና አሰብ ላይ ነፃ ወደብ ያስፈልጋቸዋል ማለት ነው። በዚህም ምክንያት በዕቅዳቸው መሠረት ለኢትዮጵያ በጥቂት ዓመታት ውስጥ በብድር መልክ የሚሰጥ እስከ 17 ቢልዮን ዶላር  የሚደርስ ብር መመደባቸው ነው የሚነገረው። ወደቡም ቢሆን በስም የኢትዮጵያ ሆኖ በተግባር ግን የእነሱ አድርገው መጨረሳቸውንም በለሆሳስ የሚያወሩም አሉ። ለዚህ ዓላማ መሳካት ደግሞ ከአቢይ አሕመድ የተሻለ ተመራጭ እንደማያገኙም ተረድተዋል። አሁን ላይ የአቢይ አገዛዝ ወደብ አልፈልግም ቢል እንኳን አስገድደው እና አስፈራርተውም ዓላማቸውን ከማሳካት ወደ ኋላ አይሉም የሚሉም አሉ። "…ግብፅ ምናምን ጓ ትላለች የሚባለው ብላኔ ነው። ጆካ ነው። ግብፅ የምዕራባውያኑ አጀንዳ ማስፈጸሚያ፣ ዓረቦቹን የሚቆጣጠሩበት ሪሞት ኮንትሮላቸው ናት። አሜሪካ የዓባይ ግድብ የተገደበው በራሳችን ብር ነው ስትል መልስ የሰጠ አንድም ባለሥልጣን ከኢትዮጵያ ወገን የለም። ልክ ግድቡ በኢትዮጵያ ስም በኢትዮጵያ ተገንብቶ ለእነ ግብፅ እንዲመች ተደርጎ እንደተገነባው ሁሉ አሁንም የቀይ ባሕር የአሰብ ወደብ ጉዳይም ከዚሁ አይዘልም። የህዳሴ ግድብ በተጠናቀቀ ማግስት የመብራት ዋጋ ይቀንስልኛል፣ ይረክስልኛል ብሎ ይጠብቅ የነበረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጭራሽ ምንድነው የገጠመው? አቢይ አሕመድ የመብራት ክፍያን 400% መጨመሩ ነው የተነገረው። ወደቡም ከዚህ የተለየ ይሆናል ብዬ አልጠብቅም። ለወደቡ ቋምጣ የተቀመጠች ናት የምትባለው የተባበሩት አረብ ኤምሬትስም ሌላኛዋ ውጋት ናት። ኤምሬትስ በአፍሪካ ጉዳይ በተለይ በኢትዮጵያና በሱዳን የውስጥ ጉዳይ ገብታ መፈትፈት ከጀመረች ሰነባብታለች። ለገነት መግቢያ ለነፍሷ ሳይሆን በአቢይ አሕመድ በኩል መጨረሻውን የማናውቀው በቢልዮን የሚቆጠር ዶላር እያፈሰሰችብንም ነው። የሱዳኑን ሄሚቲን እና የኢትዮጵያውን አቢይ አሕመድን ወጥራ ነው የምትረዳው። ዶላርም፣ ድሮንም፣ ጥይትም፣ ቦንብም ትለግሳለች። በገፍም ታቀርባለች። አልቡሁራን ከኢሳይያስ ጋር ነው። ሄሚቲ ከአቢይና ከኤምሬትስ ጋር "…ልክ እስራኤል የፍልስጤም ጋዛን ቀጥቅጣ ሽባ አድርጋ እንደተቆጣጠረችው ሁሉ ኢትዮጵያም ኤርትራ ሻአቢያን ቀጥቅጣ አሰብን እንድትቆጣጠር የማርያም መንገድ ሊሰጧት ይችላሉ። ኤርትራ ብትከስ የምትሄደው ወደ ተባበሩት መንግሥታት ዘንድ ነው። በተባበሩት መንግሥታት ውስጥ ደግሞ ወሳኞቹ ከአቢይ አሕመድ ጀርባ ያሉት ጎምቱዎቹ ኃያላን መንግሥታት ናቸው። እናም አቢይ በዚያ በኩል ገልማጭም፣ ተቆጬ ገሳጭም እንደማይኖርበት ከታወቀ አሰብ ለመግባት ጠዋት 2:00 ሰዓት ጉዞ ቢጀምር ምሳ ሰዓት ቀይ ባሕር ውኃው ጋር ደርሶ ዓሣ አስግሮ፣ ጠብሶ ከመብላት የሚያቆመው ኃይል ያለ አይመስለኝም። እነ ጣልያን፣ እነ ሳዑዲ አረቢያም ጓ ቢሉ እንኳ ከአማሪካው ፕሬዘዳንት ከአባ እንደልቡ ከትራንፕ ፊት የመቆም፣ የመገዳደርም አቅም ያላቸው አይመስለኝም። "…ወልቃይት። አቢይ ወልቃይትን ለትግሬዎቹም፣ ለዐማሮቹም ሳይሰጥ ልክ እንደ ድሬደዋ እና አዲስ አበባ በፌደራል መንግሥቱ ሥር አስቀምጦ ትግሬና ዐማራን ዘላለም ሊያናቁርበት ነው የሚፈልገው። አሁን ባለው ሁኔታ የአብይ ኃይል በዚህ በኩል ሰብሮ ወደ ኤርትራ ለ መግባት የሚሞክር አይመስለኝም። ምዕራባውያኑም ደግሞ በዚያ ያለውን የፖታሽ መአድን ክምችቱን አጥብቀው ይፈልጉታል። አሰብ ወደብ የሚፈለገውም ከላይ እንደተባለው ለሽሬው፣ ለአዲ ዳሮው ወርቅና ለወልቃይቱ ፖታሽ ሲባል ነው። ሰሊጥ፣ ጥጥ ምናምን የሚባለውን እርሱት። እሱን እነ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ እየሸጡት በጀት አልባዋን ወልቃይት ለሀኪም እና ለአስተማሪ፣ ለተከዜ ዘብ ደሞዝ የሚከፍሉበት ነው። አንገምት ከተባለና በሃላል ግምታችንን እንናገር ከተባለ አሁን ላይ እንደ ትናንቱ የፓርላማ አያያዙ ከሆነ አቢይ አሕመድ በአሜሪካ ስውር ድጋፍ የኦሮሚያ ሚሊሻንም ቢሆን ይዞ ኤርትራን ይወራል። በአንዷ እስራኤልእነ ጋዟም ሆኑ ሊባኖስ፣ ሶሪያ፣ ኢራንም በአሜሪካ ድጋፍ ዶግ አመድ እንደተደረጉት ኤርትራም ቢሆን በዚያው አግባብ በኤምሬትስ ድሮን፣ በምዕራባውያኑ ይሁንታ ዶግ አመድ ልትሆን ትችላለች። ሩሲያ፣ ቻይና፣ ኢራን፣ ሰሜን ኮሪያ ኤርትራን ማገዝ የሚሞክሩ አይመስለኝም። እንጃ ግን ምን እንደሚፈጠር። እናም አብይ አህመድ ወደቡንም ሆነ ባህሩን የሚይዘው ለኢትዮጵያ ሳይሆን ለቀጣሪዎቹ ነው። ልክ እንደ አባይ ግድብ ማለት ነው። አሜሪካ ግድቡ በገንዘብ ስለተሠራ እኛ ነው እንዳለችን ሁሉ ኋላም አብይ አህመድ እና ሻአቢያ ከተዋጉ በኋላ እነ አሜሪካ አሸማጋይ ሆነው ይገቡና አንተም ተው አንተም ተው ብለው ቀይ ባህርንም ወደቡንም በበላይነት ይቆጣጠሩታል። ፈረንሳይ ጅቡቲን እንደምትቆጣጠረው ማለት ነው። "…እዚህ ላይ የዐማራ ፋኖም በታሪክ አጋጣሚ ሌላ ሚዘን ማስጠበቂያ ዕድል እጁ ገብቶለታል። እንዲያ ነው እንዲህ ነው ብሎ በአደባባይ የሚነገርም ባይሆን ጥሩ አጋጣሚ እንደተፈጠረለት ግን ለመገመት አይከብድም። የትግሬ ፖለቲከኞችን መቼም ባላምንም ምዕራባውያኑ ግን ከትግሬዎቹ በተሻለ መልኩ የሚታዘዛቸው ካገኙ ከእነርሱ ጋር የሚንገላወዱበት ምክንያት የሚኖር አይመስለኝም። አቢይ አሕመድ ጦርነቱን ለማሸነፍ ከሱዳን ሃሚቲ በድሮን ኤርትራን የሚደበድብለት ከሆነ አቢይ አሕመድ 70 ኪሎሜትር ሩጦ አሰብ መግባት አያቅተውም። አቢይ አሕመድ በዚህ ሙቀት አሰብ ገብቶ የአሸናፊነት ሰርተፊኬቱን ምዕራባውያኑ ከሰጡትና እንደተባለው አሰብን ካጸደቁለት አቢይ ከአሰብ መልስ ወደ ዐማራ ክልል ተመልሶ ውጊያ ብቻውን አይጀምርም። የጥቅም ጉዳይ ነውና ፋኖን የአሸባሪነት ታፔላ ለጥፎ ከስሶ በአየርና በምድር ሊዘምቱበት ሁላ ይችላሉ። እግረ መንገዳቸውንም…👇③✍✍✍
显示全部...
446👍 147 9🤔 7🙏 6🏆 6😡 5🔥 3🤯 1👌 1🕊 1
👆②✍✍ ላይ ሆነ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጣቸው ቃለ መጠይቆች ላይ አሜሪካንን እንዳትሸጥ እንዳትለወጥ አድርጎ ቀጥቅጦ ማዋረዱን ያዩ የተመለከቱ ምዕራባውያን ደስ ይሰኛል ተብሎም አይጠበቅም። እናም ወደባችንን ያስነጠቁን አካላት አሁን ላይ ወደቡን መልሰው ባይሰጡንም እነርሱም በጉዳዩ ላይ በቀጥታ ባይገቡበትም በኢትዮጵያ በኩል ግን ከመስመራቸው እንዳፈነገጠ የሚያስቡትን ሻአቢያን ለመቅጣት ወደቡን ከሻአቢያ ተቀብለው በእጃዙር ሊያስተዳድሩት እንደፈለጉት የትናንቱን የአቢይን ፉከራና ድንፋታ ሳይ ብጠረጥር አይፈረድብኝም። እኔን የተሰማኝ ስሜት እንዲህ ያለ ነው። ያውም ዓረቦችን ብቻ ሳይሆን የሃገራችንን የስልጤና የወሃቢይ እስላሞችን ሊያበሳጭ የሚችለውን የፍልስጤሟን ጋዛን አንስቶ ምሳሌም አድርጎ እገሌ ያድነኛል ብሎ ጦርነት መግጠም ውጤቱን ኤርትራውያን ከዚያ እንዲማሩ ጠቅሶ መደስኮሩ በአሜሪካም፣ በእንግሊዝም ሆነ በእስራኤል ከፍተኛ ድጋፍ እንዳለው የሚያሳይ መስሎ ነው የታየኝ። ፍልስጤማውያን የሚያድናቸው የሚታደጋቸውም እንዳላቸው አስበው የነበረ ቢሆንም እስራኤል ኃያል ሆና በአሜሪካ ድጋፍ አዳኞቹንም በመቀጥቀጧ የሚያድናቸው አልተገኘም ነው ያለው አቢይ በትናንትናው የፓርላማ ዲስኩሩ። ለፍልስጤም ኢራን፣ ለዩክሬን ምዕራባውያን አይዞኝ ከማለት በቀር ማንም አላዳናቸውም፣ ማንም አልሞተላቸውም ብሎ ሲፎክር ሳየው ሰውየው ማን ከጀርባው እንዳለ እንድጠረጥር ነው ያደረገኝ። "…እንግዲያውማ ራሺያ ክሬሚያን በመውረሯ ምክንያት ምዕራባውያን ያን ሁሉ ማዕቀብ የጣሉባት ሩሲያን የሰው ሀገር በመውረር ከሰዋት ነው። ኢራቅ ኩዌት ስትገባ ኔቶና አሜሪካ ኢራቅን ዱቄት ያደረጓት ኢራቅን የሰው ሀገር ወርረሻል፣ ድንበርም ጥሰሻል ብለዋት ነው። ቻይና ታይዋንን ጫፏን እንዳትነካት እነ አሜሪካ የሚፋለሙት ለነፍሳቸው ብለው እንዳይደለ ይታወቃል። ነገር ግን እነርሱ ለሚፈልጉት ጉዳይ፣ ለኅልውናቸው የሚጠቅም ከሆነ ወረራ ነው የተባለን ጉዳይ ባለየ፣ ባልሰማም ያልፉታል። እስራኤል ጋዛንና ዌስት ባንክን ስትቆጣጠር የሚቆጣት፣ የሚጠይቃት የሌለው ለዚህ ይመስለኛል። ልክ እንደዚያው ኢትዮጵያም አሰብ ወደብንና ቀይ ባሕርን የእኔ ስትል እስከ አሁን የተነፈሰ የዓለም አቀፍ መንግሥታት ያልታዩት ለዚህ ይመስለኛል። እናም ቀይ ባሕርን ኢትዮጵያ እንድትይዘው፣ አሰብንም እንድትቆጣጠረው ተፈልጓል ብለን ብንገምት ኃጢአት አይሆንብንም። ነገርየው ባይጠራም የማርያም መንገድ ግን ሳያገኝ አይቀርም ባይ ነኝ። "…ልክ እንደ ኤርትራ ሁሉ ታይዋንም እኮ የቻይና ግዛት ነበረች። በሕዝብ ብዛት ቻይና የምትበልጣት ታይዋንን እንደ ራሷ ግዛት ትመለከታታለች እንጂ መሪ ቀይራ፣ ባንዲራ አውርዳ ሀገር ሆና ከመቀጠል አላስቆመቻትም። እንዲያ ብታደርግ እነ አሜሪካ ዝም አይሉም። አሜሪካ ታይዋን የቻይና ግዛት ከምትሆን ካሊፎርኒያ ወደ ቻይና ብትጠቃለል የሚቀላት ሁላ ነው የሚመስለኝ። በሕዝብ ብዛትም ማሸነፍ፣ መጠቅለል አይቻልም። የኢትዮጵያ ሕዝብ በየዓመቱ 3 ሚልዮን ሕዝብ ጨምሮ ያድራል። ይሄ ማለት አንድ ኤርትራ ሕዝብ በየዓመቱ በኢትዮጵያ ይወለዳል ብሎ መፎከርም፣ 5 ሚልዮን ትግሬን በ100 ሚልዮን ኢትዮጵያዊ መዋጥ፣ ባህሩን አድርቆ ዓሳውን እንደ ማጥፋት ያለ ነው ብሎ የኢሳቱ መሳይ መኮንን እንዳወጀው የዘር ማጥፋት አቢይ አሕመድም የዘር ማጥፋት ሊፈጸምብን ነው ብለው ኤርትራውያኑ የዲፕሎማሲ ብልጫ ወስደው ድል እንዲቀዳጁ፣ ኢትዮጵያንም በማይም ንግግር እንድትዋረድ ከማድረግ የዘለለ ምንም ለውጥ አያመጣም። ብቸኛው የብልጽግና አሰብ መግቢያ፣ ቀይ ባሕር ላይ መውጫ መንገዱ አንድና አንድ ብቻ ነው። ድሮ በልጅነታችን የሰፈር ጉልቤ ጎረምሶች የሆነ የሌላ ሰፈር ጎረምሳ መቀጥቀጥ አምሯቸው ነገር ግን በቀጥታ ሄደው ከመጣላት እኛ ደቃቃ ጩጬዎቹን ልከው እንድንተነኩሰው አድርገው ሲያበቁ ምስኪኑ እኛን ሊቆነጥጥና ሊኮረክም ሲሞክር እነርሱ ከኋላ መጥተው አፈር ደቼ እንደሚያበሉት አይነት ነገር ከሌለ በቀር እንዲሁ የሚቻል አይመስለኝም። ሶሪያን፣ ኢራንን፣ ሊባኖስን፣ የመንንና ጋዛን እንድትመታ፣ ራሷን እንድትከላከል እንደተፈቀደላት እንደ እስራኤል እሰይ ደግ አደረገች የሚል ኃይል ከኋላ ከሌለ በቀር እንዲሁ ግርር ተብሎ በድንገቴ ጫጫታ አሰብም፣ ወደብም የሚሞከር አይመስለኝም። ከሆነ ግን ይቅናችሁ። "…የአፍሪካ ቀንድ በቀይ ባሕር በኤደን ባሕረ ሰላጤ ላይ ኃያላኑ ቦታ ያስፈልጋቸዋል። ልክ ፈረንሳይ ጅቡቲን ይዛ ቀንዱን እንደተቆጣጠረችው ሌሎቹም ቦታ ይፈልጋሉ። ከላይ ከሱዳን ጀምሮ ኤርትራ፣ ጅቡቲ፣ ሱማሌላንድና ሱማሌም ሁላቸውም ተሰፍሮባቸዋል። የጦር ሰፈር የሌለውን ጠይቁ። የለም ሁሉም የጦር ሰፈር ገንብተዋል። ሩሲያ፣ አሜሪካ፣ ቻይናም፣ ቱርክም፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬት ሳትቀር ሰፍረዋል። ቱርክማ ሱማሌ ባህሩን አስተዳድሪልኝ ሁላ ብላ እንደሰጠቻት ነው የሚነገረው። ግብፅም እንዲሁ አፍንጫችን ስር ናት። አካባቢው የምድራችን ወሳኝ አካባቢ ስለሆነ ሁላቸውም ይፈልጉታል። ከአካባቢው እንድንርቅ የተደረግነው እኛ ብቻ ነን። በቅርቡም ሱማሌ ላንድም በእነ አሜሪካ ጭምር የሀገርነት ዕውቅና ተሰጥቷት ሀገር መሆኗ የሚቀር አይመስልም። ይሄ የሚሆነውም በምክንያት ነው። አሁን ባለው ሁኔታ ግን  አሜሪካንን ጨምሮ ኃያላኑ የዓለም መንግሥታት የካናዳና የእንግሊዝ መንግሥታት በጋራ በመሆን በመላው ኢትየጵያ ያስጠኑት የውድ ማዕድናት መገኛ ቦታዎች በስፋት እንዳሉ ይነገራል። እነዚህን የማዕድናት መገኛ ቦታዎችን ደግሞ እንዴት መቆጣጠር እንዳለባቸውና  እንዴት መጠቀም እንዳለባቸውም አብረው አጥንተው የጨረሱት ጉዳይ እንደሆነም ይነገራል። በዚህም ምክንያት ኢትዮጵያ የግድ ሳታስፈልጋቸው አልቀረችም የሚሉ መተርጉማንም አሉ። "…ኢትዮጵያ ወደፊት ምዕራባውያኑና ምሥራቃውያኑ አበዳሪ መንግሥታት የሚራኮቱባትም ትመስላለች። የተበደረችውን ደግሞ ቡና ሽጣ መክፈል ስለማትችል በምትኩ ማዕድናቶቿን አውጥተው በመውሰድ ብድራቸውን ሊያጣጡ ይችላሉ። በዚህም መሠረት ለኢትዮጵያ መንግሥት ከወረቀት እኩል ዋጋ ያለውን ዶላር አትመው በመስጠት፣ በማበደርም እነርሱ በምትኩ መዓድኖቿን ዝቀው በዚያ ሊያጣጡ እንደሚችሉም ነው በዘርፉ አጥንተን ወረቀት አለን የሚሉ ወገኖች የሚያሳስቡት። ይሄ አይነቱ አሠራር ደግሞ በእነርሱ ዘንድ የተለመደ ነው። እንኳን ምዕራባውያኑ ይቅርና እነ ቻይናም የሚያደርጉት እንደዚሁ ሆኗል። ብር ያበድራሉ፣ ከዚያ ከአንተ ማዕድናቶችህን አውጥተው በመውሰድ ዕዳህን ክፈል ትባላለህ። በኢትዮጵያም እየሆነ ያለው ይሄው ነው። ያልተማረ፣ ነገን የማያስብ አገዛዝ ትምህርትን እና ዐዋቂን በመግደል ሀገር በደናቁርትና በማይማን እንድትሞላ በቲክቶከርም አጥለቅልቀው የተማረ እና የሚያንሰላስል ዜጋን እያጠፉላቸው፣ ሀኪሞች እንኳ በቅርብ ወደምተገኘው ኡጋንዳ በገፍ እየፈለሱ ሀገር እያጠፋላቸው ስለሆነ ደስተኞች ናቸው። እንዲህያለ ተላላኪ፣ በግልጽ ለአሜሪካ ፈርሜ ለአሜሪካ መዋጋት እፈልጋለሁ የሚል ግለሰብ መሪ አድርገው በኢትዮጵያ መንበረ ሥልጣኑን እንዲቆጣጠር ስላደረጉ ራሳቸውን እንደ እድለኛም ነው የሚቆጥሩት። ሚልዮን ትግሬ የሞተበት፣ ሚልዮን ዐማራ ኦሮሞ የሞተበትን ጦርነት የሚመራ ጨካኝ ቢሆንም እነሱን እስከጠቀማቸው ድረስ ገልማጭ የለበትም። የቡርኪነፋሶው ትራወሬ አልታዘዝ ስላለ እንዴት እየዘመቱበት እንዳለ የሚያይ ሰው አራጁን አቢይ የሚንከባከቡት ጴንጤ ስለሆነ ብቻ ነው ብሎ መደምደም ስህተት ነው የሚሆነው። ሲልኩት ወዴት፣ ሲጠሩት አቤት…👇②✍✍✍
显示全部...
520👍 160🏆 12 6😡 6🙏 4🕊 4🤯 3🤔 2
"ርእሰ አንቀጽ" "…የዛሬ ሁለት ዓመት አካባቢ አቅም ስላነሰን ኤርትራ ሆይ አግዢን፣ ድረሺልን፣ ለነፍስ እንሆንሻለን ብለው ለምነው፣ አስለምነው፣ ጋብዘው ትግሬን እንድትወጋላቸው፣ እንድታወድምላቸው፣ ኢትዮጵያን እንድትዘርፍላቸው ሕጋዊ ፈቃድ ሰጥተው ጋብዘው አምጥተው ትግሬን አስቀጠቀጡት። በኦሮሙማው አገዛዝ በክብር ተጋብዘው ትግራይ የገቡት ሻአቢያዎችም ከትግራይ ፋብሪካ ነቅለው፣ ተሽከርካሪ፣ ቅርሳ ቅርስ፣ የሆስፒታል የሕክምና መሳሪያ፣ በኢትዮጵያ ስም ተገዝቶ ከሰሜን ዕዝ ጋር በትግራይ ተከማችቶ የነበረ የጦር መሳሪያ ሁላ ዘርፈው እንዲወስዱ ያመቻቹ አካላትበዚያውም እግረ መንገዳቸውን የመለስ ዜናዊ ኔትወርክ የሚባሉትንና በመለስ ዜናዊው የወያኔ ኢህአዴግ አገዛዝ ዘመን ባለሥልጣን የነበሩና በወቅቱ የሻአቢያን አገዛዝ በዓለም መድረክ እንዲገለል፣ ማእቀብ እንዲጣልበት አስደርገው ያደቀቁት ናቸው ከሚባሉት መካከል እንደ አቶ ስዩም መስፍን አይነቶቹን፣ ዓባይ ፀሐዬና ዓባይ ነፍሶ አቶ አስመላሽ ዓይነ ስውሩን ከቤታቸው አውጥተው ግንባር ግንባራቸውን ብለው ገደል ውስጥ ከትተው ጣፋጭ በቀል እንዲበቀሉ ለኤርትራውያን የፈቀደው የአቢይ አሕመዱ አገዛዝ ፣ከዚህም በላይ ደግሞ ከትግራይ ውጪም ቢሆን ትግሬን የሚያውቀው ራሱ ትግሬ ነው በሚል ፍልስፍና   የኢትዮጵያን ትግሬ በተገኘበት በአዲስ አበባ ነሽ በደቡብ በኦሮሚያ፣ በጋምቤላ፣ በቤኒሻንጉል በዐማራ ክልል ሳይቀር ቤት ለቤት እየሄዱ በወያኔ ሰበብ ትግሬ የተባለን በሙሉ ወደ ዘብጥያ በማውረድ፣ በእጃቸው የሚገኝን ሀብት በሙሉ ወርቅ ነሽ ብር ዝርፍ ሙልጭ ግፍፍ በማድረግ በጋራ ሲያሰቃዩአቸው የከረሙ ሁሉ ዛሬ ደርሰው በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግርር ብለው በመምጣት እንደ እስፔስ 1999 ኗ አክተር ማያ ተለውጠው፣ ተቀይረው "ዘመዴ በኤርትራ በአሰብ ወደብ በቀይ ባህር ጉዳይ ምን ትላለህ?" በማለት ሲቸክኩብኝ አያለሁ። ችኮ ሁላ። "…የእኔማ አቋም ግልጽ ነው። አይሸራረፍ፣ አይቆራረስ፣ እንደ ጠላ ቂጣ አየገለባበጥ፣ እንደ እስስት አይቀያየር፣ እንደ ዋሾ፣ እንደ ቀጣፊ አይወሸክት፣ እንደ ዓሣ፣ እንደ ተልባ አይሙለጨለጭ የታወቀ እኮ ነው። ዘመን አይቀይረው፣ ፊት አይቶ፣ ጌዜ ተመልክቶ አይንሸራተት የታወቀ ነው አቋሜ። የእኔ አቋም ሴተኛ አዳሪ አይደለም። ለከፈለው ሁሉ ጭኑን ገልጦ የሚተኛ አቋም የለኝም። መንገደኛ ሁሉ የሚጫወትበት አቋም የለኝ። አለቃ፣ ቀጣሪ፣ ከፋይ የለኝም። ተቆጭ፣ ገልማጭ፣ አፍጣጭም የለኝም። አቋሜ ግልጽ ነው። የእኔ አቋም እንደ ጌታቸው ረዳ፣ እንደ ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ የተልባ ስፍር አቋም አይደለም። ጠዋት ሌላ ማታ ሌላ አቋም የለኝም። ጠዋት ተቆጥቼ ተራግሜም ማታ አልመርቅም። እናም በኤርትራም ሆነ በኢትዮጵያ ጉዳይ፣ በቀይ ባሕርም ሆነ በአሰብ፣ ያውም ምፅዋ ጉዳይ አቋሜ ግልፅ ነው። አንድና አንድ ነው። "…እኔ ዘመዴ 1966 ዓም አብዮቱ ሲፈነዳ አብሬ በፍንዳታው የተወለድኩ የአብዮቱ ዘመን ትውልድ ነኝ። ኢትዮጵያ ወይም ሞት፣ ኢትዮጵያ ትቅደም፣ አቆርቋዧ ይውደም የሚል መፈክር ስስማ ያደግኩ፣ የኢትዮጵያን ሙሉ ካርታ ስመለከት ያደግኩ፣ ገንጣይ አስገንጣይ ወንበዴ፣ የዓረብ ፔትሮ ዶላር ያሰከራቸው የወያኔንና የሻአቢያን ክፋት፣ ከፋፋይነት ስጋት ያደግኩ፣ በትምህርት ቤት ቆይታዬ ስለ እናት ሀገር፣ ስለ አንድነት ግጥም ጽፌ፣ እየተወዳደርኩ ስሸለም የኖርኩ፣ ለኢትዮጵያ ራዲዮ የልጆች ክፍለ ጊዜ ስለ እናት ሀገር ኢትዮጵያ ግጥም ጽፌ ልኬ ስሜ ተጠርቶ ግጥቤ በራዲዮ ተነብቦልኝ ስቦርቅ ያደግኩ፣ በአረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ሰንደቅ ዓላማ ፍቅር ተልክፌ ያደግኩ የዚያ ዘመን ልጅ ነኝ። ዐማራ ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ ጉራጌ የሚባል የዘር ግሳንግስ ሳናውቅ ሰውን በሰውነቱ፣ በኢትዮጵያዊነቱ ብቻ ዐውቀን እንድናድግ የተደረግን የዚያ ዘመን ልጅ ነኝ። እናም እኔ የማውቃት ኢትዮጵያ፣ በአእምሮዬ ውስጥ ታትማ የቀረችው ኢትዮጵያ ያቺ እነ መለስ ዜናዊ፣ እነ ስብሀት ነጋ፣ እነ ደብረ ጽዮን፣ እነ ስዩም መስፍን፣ እነ ስዬ አብርሃ፣ እነ ጻድቃን ገብረ ትንሳኤ፣ እነ ጄነራል ታደሰ ወረደ፣ እነ ሞንጆሪኖ፣ እነ ዓባይ ፀሐዬ የታችኞቹ ትግሬዎች ከላይኛዎቹ ትግሬዎች ጋር ተጠቃቅሰው አንገቷን በሰይፍ ያልቆረጧትን ሙሉዋን፣ የምታምረዋን ኢትዮጵያን ነው የማውቃት። የባህር በርም፣ የባህር ኃይልም፣ ከአንድም 2 ወደቦች የነበሯት ኢትዮጵያን ነው የማውቃት። ያቺ የእኔና የመሰሎቼ ኢትዮጵያ እስከዛሬ ድረስ አልሞተችም። በየትኛውም መልእክቴ ላይ የተቆረጠች፣ ኤርትራ የሌለችበት የኢትዮጵያ ካርታን አጋርቼ አላውቅም። ያውም እየተሰደብኩ። እየተወቀስኩ። እናም እነ ድንገቴ ሆይ ተረጋጉ። "…በተለይ የትናንቱን የአቢይ አሕመድን የፓርላማ ንግግር ሳይ፣ ስመለከት የኤርትራ መወረር፣ የሻአቢያ መውደቅ አይቀሬ መሆኑን ሳይሆን መምሰሉን ነው የታዘብኩት። አቢይ አሕመድ ኤርትራን ለመውረር አረንጓዴ መብራት እንደበራለት፣ ፈቃድም እንደተሰጠው ያረጋገጥኩበት የመሰለኝ ቀን ሆኖ ነው ያየሁት። እንደ ጋዛና እንደ ዩክሬን ትቀጠቀጣታለህ፣ የሚያግዝህ፣ የሚደርስልህ የለም እያለ በፍልስጤማውያን እና በዩክሬናውያን ላይ ሙድ ሲይዝ ሳየው ድፍረቱ ከየት እንደሚመጣ ለመገመት ብዙም አያስቸግርም። ሰሞኑን አንድ ዶክመንተሪ እያየሁ ነበር። ዶክመንተሪውን የሠሩት ነጮች ናቸው። በሀገረ እስራኤል ምስረታ ወቅት የአፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት በተባበሩት መንግሥታት ጉባኤ የድምፅ መሰጠት ወቅት እስራኤል ሀገር ትሁን፣ አትሁን ለሚለው "ድምፀ ተአቅቦ" በማድረጋቸው ምክንያት እስራኤል ቂም ይዛ፣ እነ እንግሊዝም፣ እነ አሜሪካም ይሄ ዘውዳዊ ሥርዓት መገርሰስ አለበት፣ ኢትዮጵያም ከውኃው መራቅ አለባት፣ አዲስ ሀገር ኤርትራ መፈጠር አለባት በማለት ሻአቢያን አደራጅተው፣ ደርግን ፈጥረው፣ ረድተውም፣ ንጉሡን አዋርደው፣ አውርደውም ሥርዓቱንም አፍርሰው፣ ሀገሪቱንም በጦርነት አድቅቀው፣ ልሂቃኖቿንም የተማረውን ክፍል በጅምላ አስረሽነው፣ አስጨፍጭፈው ኢትዮጵያን ከተፈጥሮአዊው የባህር በሯ ቅፍፍ አድረገው አራቋት ሲሉ እያየሁ እንደ አዲስ እየበገንኩ ነበር። በሌላም ቪድዮ እስራኤል ኤርትራ ነፃ ብትወጣም በአረቦቹ ድጋፍ ስለሆነ ነፃ የምትወጣው አረቦቹ ደግሞ ኤርትራን ከተቆጣጠሩ ለእኔ ህልውና አደጋ ይኖረዋል በማለት ኋላ ላይ ደርግን መርዳት ብትጀምርም የአረቦቹ የነዳጅ ብር በልጦ፣ እነርሱ አሸንፈው ባህሩንም፣ ኤርትራንም አሳጡን የሚል ነገርም አይቻለሁ። ሻአቢያ አይደለም ከቀይ ባሕር ያራቀን፣ ወያኔም አይደለም። እኛን የቀሙን፣ ያራቁን፣ ዓረቦቹ እና ኃያላኖቹ ምዕራባውያን ናቸው። አለቀ። ምንም ማለባበስ አያስፈልገውም። "…የየትናንቱም የፓርላማ ውሎ ሳይ ደግሞ አኬሩ ተገለበጠ እንዴ አስብሎኛል። ዓረቦቹ በእስራኤል ተቀጥቅጠው ልክ ስለገቡ፣ ስለገበሩላትም አሁን በኤርትራ ላይ አረቦቹ የማዘዝ ሥልጣን ስለሌላቸው በአቢይ አህመድ በኩል ቀይ ባሕርን በኢትዮጵያ ስም ሊቆጣጠሩ ፈልገው ወስነው ይሆን እንዴም እያልኩ ብቻዬን ሳስብ ነው ያመሸሁት። ምዕራባውያኑም የኤርትራን አገዛዝ አንደ ማስቲካ አኝከው፣ እንደ ሸንኮራም መጥጠው የተፏት መስሎም ነው የተሰማኝ። በተለይ የኢሳይያስ አፈወርቂ የሻአቢያው መንግሥት ባለፈው ጊዜያት ከሩሲያ፣ ከኢራንና ከቻይናም ጋር በመሰለፍ በተለይ ቻይና በሄደ ጊዜ ለአሜሪካ ያልተደረገ አቀበባበል ተደርጎለት ያሳዩት ክብርና በፊታቸው ያገኘው ሞገስ ለምዕራባውያኑ ምቾት ይሰጣል ተብሎም አይታሰብም። በተለይ ኢሳይያስ አፈወርቂ ሩሲያ ሞስኮ በሄደ ጊዜ በጉባኤውም…👇①✍✍✍
显示全部...
593👍 161🙏 39🤯 9🏆 7😡 6 4🕊 4🔥 3
መልካም… "…በወደቡና በቀይ ባሕር ጉዳይ እኔም የዜግነቴን ድርሻ ልወጣ ብዬ አጭር ቃሪያ በሚጥሚጣ የሆነች ርእሰ አንቀጽ አዘጋጅቻለሁ። በተለይ "ዘመዴ ስለ ወደቡ ምንትላለህ? በቀይ ባሕር ጉዳይስ አቋምህ ምንድነው? እያሉ እንጥሌ እስኪወርድ ለሚያደርቁኝ ሰሞነኛ ኢትዮጵያኒስቶችም ቢጥማቸውም ባይጥማቸውም አጭር መልስ አዘጋጅቼላቸዋለሁ። "…ወደቡንና በወደቡ ጉዳይ የዐማራን ተሳትፎ በተመለከተም የራሴን ሃሳብ ለማጋራት ብዕሬን ስዬ ተከስቻለሁ። የወሃቢይ እስላሞችና የብልፅግና ወንጌል አማኞች እየጨፈራችሁ አንብቡኝ፣ ዐማሮችና ኦርቶዶክሳውያን ግን ለአሩሲዋ እመቤት የጥቅምት ግብር የጠንቋይ ልጆቹ መንግሥት ሰውቷችሁ ያው ኀዘን ላይ ናችሁና ከይቅርታ ጋር ከተመቻችሁ ብቻ አንብቡኝ። እግረ መንገዴንም ነፍስ ይማርም ብያለሁ። • ዝግጁ ጓዶች… ?
显示全部...
1.61 MB
3.17 MB
33.72 MB
star reaction 2 705👍 302🙏 91💔 52😡 12 10🕊 8🏆 7🤔 6🤯 5🔥 3
መልካም… "…በወደቡና በቀይ ባሕር ጉዳይ እኔም የዜግነቴን ድርሻ ልወጣ ብዬ አጭር ቃሪያ በሚጥሚጣ የሆነች ርእሰ አንቀጽ አዘጋጅቻለሁ። በተለይ ዘመዴ ስለ ወደቡ ምንትላለህ? በቀይ ባሕር ጉዳይ አቋምህ ምንድነው ለሚሉኝ ሰሞነኛ ኢትዮጵያኒስቶችም አጭር መልስ አዘጋጅቼላቸዋለሁ። "…ወደቡንና የዐማራን ተሳትፎ በተመለከተም የራሴን ሃሳብ ለማጋራት ብዕሬን ስዬ ተከስቻለሁ። የወሃቢይ እስላሞችና የብልፅግና ወንጌል አማኞች እየጨፈራችሁ አንብቡኝ፣ ዐማሮችና ኦርቶዶክሳውያን ግን ለአሩሲዋ እመቤት የጥቅምት ግብር የጠንቋይ ልጆቹ መንግሥት ሰውቷችሁ ያው ኀዘን ላይ ናችሁና ከይቅርታ ጋር ከተመቻችሁ ብቻ አንብቡኝ። እግረ መንገዴንም ነፍስ ይማርም ብያለሁ። • ዝግጁ ጓዶች… ?
显示全部...
1.61 MB
3.17 MB
33.72 MB
18💔 3
照片不可用在 Telegram 中显示
“…በሰማይ ስማ አድርግም በባሪያዎችህም ላይ ዳኛ ሁን፤ በበደለኛውም ላይ ፍረድ፥ መንገዱንም በራሱ ላይ መልስበት፤ ንጹሑን አጽድቀው፥ እንደ ጽድቁም ክፈለው።” 1ኛ ነገ 8፥32 "…እንደምን አደራችሁ? "…እንደምን አረፈዳችሁ? "…እንደምን ዋላችሁ? "…እንደምን አመሻችሁ? "… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
显示全部...
star reaction 4🙏 944 252👍 108🕊 17🏆 10😡 5 2🔥 2
• በኦሮሚያ የኦርቶዶክሳውያን ጭፍጨፋ ቀጥሏል… "…በገድለ ዮሐንስ፣ የ ካናዳ ሀገረ ስብከት ለማንኛው ሊቀጳጳስ ይሰጥ፣ በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት፣ በበጀት፣ በመንፈሳዊ በዓል አከባበር፣ በጉዞ ማኅበራት ጉዳይ፣ በኮሪደር ልማቱና በዓባይ በሕዳሴው ግድብ መጠናቀቅ ላይ አጀንዳ ይዞ ሲነጋገር የከረመው የኢትዮጵያው ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባውን ጨርሶ ትናንት መግለጫ በሰጠ ማግስት፣ አቢይ አሕመድም ቀይ ባህር እዘምታለሁ፣ ወደብም፣ አሰብንም አመጣለሁ ባለ ማግስት በኦሮሚያ ክልል በምሥራቅ አርሲ ዞን በሽርካ ወረዳ በትናንትናው ዕለት ሰኞ ጥቅምት 18/2018 ዓም ምሽቱ 4:00 ሰዓት አከባቢ ልዩ ቦታው ዘምባባ አርሴማ በሚባል ስፍራ ላይ ኦርቶዶክሳውያን በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውና ሌሎች ደግሞ ታግተው መወሰዳቸው ተነግሯል። "…ሰሞኑን በደብረ ወገግ አሰቦት ቅድስት ሥላሴ ገዳምም ገሚሱን አርደው፣ ገሚሱን አግተው በሚልዮን የሚቆጠር ብር እየጠየቁ መሆናቸው የተነገረ ሲሆን የእነ አቡነ ሳዊሮሷ ቤተ ክህነት የመንግሥታቸውን ገፅታ ስለሚያበላሽ ዜናው እንዳይነገር ጫና ሲፈጥሩ እንደነበርም ተሰምቷል። "…በአሩሲው ጭፍጨፋ ላይ ጨፍጫፊዎቹን ከየቤታቸው በማውጣት በአደባባይ የረሸኗቸው ሲሆን ርሸናውን የፈጸሙትም በኦህዴድኦነግ/ብልጽግና መዋቅር የሚደገፉ እና ራሳቸውን "የኦሮሞ እስላማዊ መንግሥት" ብለው የሚጠሩ ኃይሎች መሆናቸውም ተገልጿል። አስከአሁን ከተጨፈጨፉት ኦርቶዶክሳውያን መሃል… ፩፥ ማሙሽ ደበበ ~ ዕድሜ ~ 30 ፪፥ ትግስት ጅማ  ~ ዕድሜ ~ 50 ፫፣ ግዛው ከተማ ~  ዕድሜ ~40 ሲሆኑ ሥርዐተ ቀብራቸውም በዛሬው ዕለት ጥቅምት 18/02/2018 ዓም በዚያወወ በዘምባባ ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን መፈጸሙም ተዘግቧል።  "… ከተጨፈጨፉት ሌላም የእስላማዊ መንግሥቱ ታጣቂዎች… ፩፦ አስታጥቄ ደርቤ ፪፥ ከተማ ተክሉ ፫፥ በኃይሉ አበባየሁ ፭፦ ሲሳይ ከተማ …የተባሉ ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች ታግተው መወሰዳቸው ተነግሯል። "…ከሀጂ ሙፍቲ ሞት በኋላ በኃይለኛው ድቀት የገጠመው መንግሥታዊው የወሃቢያ እስላም ቡድን ከዚህ የበለጠም የማስደንገጥ ተግባራትን ሊፈጽም እንደሚችልም እየተነገረ ነው። ሰሞኑን በሰሜን ሸዋ መርሀ ቤቴ አካባቢ ከፋኖ ጋር ይፋለም ዘንድ የላኩት ባህር ኃይል፣ አየር ወለድ እና ሪፐብሊካን የተባሉት የአገዛዙ ወታደሮች አይሆኑ ሆነው መደምሰሳቸው ብስጭት የፈጠረበት አገዛዙ ከዚህ የባሰም ጭፍጨፋ በኦርቶዶክሳውያን ላይ ሊፈጽም እንደሚችል ስለሚገመት ኦርቶዶክሳውያን ከኦሮሚያ ቤተ ክህነቱ ከአቡነ ሳዊሮስ አስተዳደር ምንም ዓይነት ተስፋ ሳይጠብቅ ራሱን ለመከላከል ቢሞክር መልካም እንደሚሆንለት የሚመክሩም ብዙዎች ናቸው። "…ሰሞኑን በብዙ መልኩ ኪሳራ ላይ የወደቀው አገዛዝ እንደ ሩዋንዳ ያለ የጅምላ ጭፍጨፋ ሊፈጽም ስለሚችል አሁንም ሕዝቡ ራሱን ለመከላከል እንደ ሁልጊዜው ይዘጋጅ ዘንድ ምክሬን አላቋርጥም። በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ርካሹ የዐማራ ነገድ እና ኦርቶዶክሳውያኑ እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል። የሀገሪቱ ሕግ አውጪ፣ ሕግ ተርጓሚና ሕግ አስፈጻሚው ክፍል በሙሉ ጽንፈኛ የወሃቢይ እስላሞችና አክራሪ ፀረ ኦርቶዶክስ ኃይላት ስብስብ መሆናቸው ይታወቃል። እናም ኦርቶዶክሳውያኑ እንደ ዜጋ ተቆጥረው ሕጋዊ ከለላና ጥበቃ የሚያደርግላቸው መንግሥት እንደሌለ ዐውቀው እንደ ኢራቅ ክርስቲያች ራሳቸውን አደራጅተው ከፈጽሞ መጥፋት ራሳቸውን እንዲታደጉ እመክራለሁ። • የሚሰማም፣ የሚታደግም ሲጠፋ እንዴት ይጨንቃል በማርያም። ብዕር አይታዘዝ፣ እጅ አይታዘዝ፣ ጣትህ አይንቀሳቀስ፣ ፍዝዝ ብቻ።
显示全部...
19.44 MB
33.72 MB
star reaction 4 789💔 482👍 194🙏 66😡 43🔥 25🤔 18🕊 15🤯 12🏆 10 9
照片不可用在 Telegram 中显示
"…ከእግረኞች ጋር በሮጥህ ጊዜ እነርሱ ቢያደክሙህ፥ ከፈረሶች ጋር መታገል እንዴት ትችላለህ? ኤር 12፥ 5 …በቅድሚያ…  ከሁሉም በፊት… "…ቤትህን አስተካክል" 2ኛ ነገ 20፥1 "…እንደምን አደራችሁ? "…እንደምን አረፈዳችሁ? "…እንደምን ዋላችሁ? "…እንደምን አመሻችሁ? "…መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
显示全部...
star reaction 3🙏 983 267👍 129🕊 13👌 12🏆 10😡 10 7🤔 7🤯 6
照片不可用在 Telegram 中显示
“…ምላሱን ከሚያጣፍጥ ይልቅ ሰውን የሚገሥጽ በኋላ ሞገስ ያገኛል።” ምሳ 28፥23 "…እንደምን አደራችሁ? "…እንደምን አረፈዳችሁ? "…እንደምን ዋላችሁ? "…እንደምን አመሻችሁ? "…መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
显示全部...
star reaction 3🙏 1 023 281👍 118🕊 21🏆 17😡 15 4💔 3🔥 1
照片不可用在 Telegram 中显示
• ጀምረናል ገባ ገባ በሉ…! • አላችሁ አይደል…?
显示全部...
star reaction 2👍 471 131🙏 47👌 12🔥 9 8😡 6🤔 5🕊 3🏆 3