ru
Feedback
Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

Открыть в Telegram

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Больше
2025 год в цифрахsnowflakes fon
card fon
228 585
Подписчики
-14224 часа
-1 0407 дней
-4 59630 день
Архив постов
👆⑤✍✍✍ …"…ዱባይ ዓረብ መሩ የኦሮሞ ብልጽግናው የአቢይ አገዛዝም መውደቁ እንደሁ አይቀርም። የጊዜ ጉዳይ ነው። ኔፓል የተጀመረው የወጣቶች ዐመጽ እና ተቃውሞ ማዳጋስካር ገብቶ፣ አገዛዙን ወደ ዱባይ አስፈርጥጦ፣ ካሜሮን ተሻግሮ ቀውጢ እየፈጠረ፣ አሁን ላይ ጎረቤት ሀገር ታንዛኒያ ደርሷል። በታንዛኒያና በኢትዮጵያ መሃል ያለው ኬንያ ነው። የታንዛኒያ መንግሥት እንደለመደው ጥቁቶችን ገድዬ ተቃውሞውን አስቆመዋለሁ ብሎ ፎክሮ በጥቂቱ 700 ታንዛኒያውያን ቢገድልም እንዲያውም ሕዝቡ ብሶበት አደባባይ ግልብጥ ብሎ በመውጣት በኑሮ የደቀቀው ሕዝብ፣ እኛንም ግደሉንና ገላግሉን በማለት አገዛዙን አስጨንቆ፣ ወታደሩን ከጎን አሰልፎ ሥርዓቱን በአናቱ ተክሎ ነፃ ሊወጣ ከጫፍ ደርሶ ነው ያለው። ከማዳጋስካር የተነሳው የለውጥ ፈላጊ ወጣቶች ዐመጽ ታንዛኒያ ደርሷል። በታንዛኒያና በኢትዮጵያ መካከል የምትገኘው ኬንያ ብቻ ናት። የኢትዮጵያው ከማዳጋስካሩም፣ ከታንዛኒያውም፣ ከኔፓሉም የሚለየው ዐመፁ በድንጋይ አለመሆኑ ነው። ዐመጹ በጥይት ነው። ኦሮሙማውም ከወዲሁ ሸኔ የሚባለውን ኃይል አዲስ አበባ ዙሪያ አስፍሯል። መውረዳችን ካልቀረ በማለት በኦሮሚያና በአዲስ አበባ ቅርስ ለማውደም፣ ንፁሐንን በጅምላ ለመጨፍጨፍ በዝግጅት ላይ ናቸው። በሸገር ሲቲ በሚባለው በቀን በጠራራ ፀሐይ ሲሯሯጡ የሚታዩት ኦነግ ሸኔዎች ለዚሁ ጭፍጨፋ ተብለው የተዘጋጁ ናቸው። በባሌ፣ በኤርትራ፣ በሱማሊያ የሰለጠነው አራጅ የወሀቢያ ቡድን ደግሞ በአሩሲ የጀመረውን የዘር ማጽዳት በሀረርጌ፣ በባሌና በጅማ፣ በወለጋም ለማጣጧፍ እያሟሟቀ ነው። "…አዎ ከባድ ግዜ ከፊታችን መጥቷል። ደቡብ ሱዳን የሰለጠነ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአክራሪ የወሀቢይ እስላም ቡድን በቤንሻንጉል ጉሙዝ ካማሽ ዞን በኩል ወደ ወለጋ በብዛት እየገባ መሆኑ ተነግሯል። በሱዳን የጅምላ ጭፍጨፋ እንደሚፈጽመው እንደ አረመኔው የዱባይ ቅጥረኛው ሀሚቲው ቡድን ያለ ጨካኝ ነው። የሚገድሉት ብሔር ሳይለዩ ኦርቶዶክሱን ብቻ ነው። የሚያወሩት አረብኛ ሲሆን ትንሽ ትንሽ ኦሮሚኛ እንደሚያወሩ ነው የሚነገረው። አሁን ላይ ከፍተኛ ውጊያ በዚያ አካባቢ እየተካሄደ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ የኦሮሞ ብልፅግና ብአዴንን በማዘዝ ወደ አሰብ እንዳንሄድ፣ ሻአቢያን እንዳንበቀል እንቅፋት የሆነን ፋኖ ነው ብላችሁ ሚሊሻ፣ ፖሊሱን ከፋኖ ጋር አጋጥሙልኝ በማለት ያዘዘ ሲሆን፣ ብአዴንም የታዘዘውን ቢፈጽምም ልባሙ ዐማራ ግን መሳሪያውን እንደያዘ ፋኖን እየተቀላቀለ ነው። በኦሮሚያ ደግሞ ሕዝቡን ሰብስበው ዐማራ መጣልህ፣ በዘመናት ተጋድሎ ከእጃችን የገባውን ሥልጣን ነጥቆ ሊወስድብህ ነው። ተነሥተህ የማትዋጋ ከሆነ፣ በብዙ ነገር የተከፋ፣ ቂም የቋጠረ ኃይል ስለሆነ እየመጣ ያለው እንደ ሩዋንዳ የዘር ፍጅት ነው የሚፈጸምብህ፣ ተነሥ፣ ታጠቅ፣ ዐማራ ሥልጣን እንዳይዝ ዝመት፣ ተዋጋ እያሉት እንደሆነም ተሰምቷል። የሆነው ሆኖ ይሄ ሥርዓት ያበቃለት ሥርዓት ነው። አወዳደቁም ከሁሉ የከፋ ነው። ይደፈርሳል። ግን ደግሞ ይጠራል። • ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ ከራየን ወንዝ ማዶ።
Показать все...
star reaction 3 685🙏 168👍 147🏆 23🤯 7🕊 5👌 4😡 4 3😱 3🤔 2
👆④✍✍✍ …ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ አለመቻል። ዘመድ ጥየቃ፣ ለልቅሶም ቢሆን ገጠር መሄድ አለመቻል የመጣው በዘመነ ኦሮሞ ነው። በዘመነ ዐማራ 1ዶላር 1 ብር ነበር። አሁን 1 ዶላር 200 መቶ። ነዳጅ ላይ አምስት ሳንቲም ጨመረ ብሎ ዘውዳዊውን ሥርዓት የገረሰሰው የሻአቢያ፣ የትግሬና የኦሮሞ አቢዮት አሁን ላይ ነዳጅን በሊትር 120 ብር እየሸጠ አጨሰው ሕዝቡን። በዘመነ ዐማራ በ600 ብር ደሞዝ ውኃ፣ መብራት፣ ስልክ፣ የቤት ኪራይ፣ የቤት ቀለብ አስቤዛ ችለህ እንደ ዲታ ትኖር ነበር። በዘመነ ኦሮሙማ እግርህን ትበላታለህ። የመቶ ሚልዮን ብር በአናትህ ላይ የሚነዳው ቄሮ ብቻ ነው። አለቀ።     "…አሁን አገዛዙ የዳጎን ሐውልት ነው። የዳጎን ሐውልት ለኤሎፍላውያን አምላክ ነው። ታቦተ ጽዮን ስትመጣ ግን አመድ ነው የሆነው። አቢይ በላይ ሲያዩት ንጉሥ ነው፤ በፋኖ ዘንድ ግን ገለባ ነው። አወዳዳቁም የከፋ ነው። እስካሁን የሄደበት አካሄድ ስሕተት መሆኑን አምኖ ሌላ መፍትሔ በማምጣት ፈንታ አሁንም የበለጠውን የስሕተት ገደል መርጧል። በጀት፣ በድሮን፣ በመድፍ ያልቀለበሰውን በኦሮሚያ ልዩ ኃይል እቀለብሰው ይሆናል ብሎ በአርባ ዙር ያሰለጠነውን ሠራዊት ወደ ዐማራ ቀጠናዎች አስገብቷል። ይህ እብደት ነው። ያለ ሓሳብ በተዘረፈ ብር ጥሬ ሥጋ በመብላት ጥይት በባዶ ሜዳ እንደመተኮስ ቀላል አይደለም። በእኔ ግምት ይህ የእግዚአብሔር እጅ ያለበት ይመስለኛል፤ በኦሮሚያ የዐማራ እናቶችን ያረደው የሽመልስ አብዲሳን ቅልብ ጦር ፈጣሪ ዐማራ መንደር ድረስ ሰተት አድርጎ አስገብቶለት አራጁ በእጅን ራሱ ዐማራው ተበቅሎት ፍርድ ሰጥቶት በዚያው እንዲቀበር በተዘዋዋሪ የፈረደለት ነው የሚመስለኝ። "…አቢይን እስካሁን የተዋጋው የፋኖ ማዕበል ነው። በፐርሰንት ቢለካ 2% እንኳ የማይሞላ የፋኖ ኃይል። ያውም በውስጡ ከዚህቹ ለመከፋፈል የሚጋጋጡ በበዙበት፣ በጎጃም፣ በጎንደር፣ በወሎ የተሰገሰጉ፣ በሸዋ የተሰነቀሩ ባንዳዎች ሞልተውበትም ቢሆን በጥቂት ኃይል ነው መክቶ እያደባየ የሚገኘው። ባንዳው ብቻውን እየቀረ ነው። በወሎ ብአዴኖች በቁም ያሠሩት ኮሎኔል ፈንታሁን ሙሐባው ከማስረሻ ሰጤ ጋር ሲቀር፣ ጎንደር እነ ደረጄ ሰሞኑን የሚያበስሩን ብሥራት የሚጠበቅ ሆኖ ወደ አንድነት እየመጣ ነው። የሸዋውም እስክንድር አንቆ የያዘው የላይኛው የእነ መከታው ቡድን ሲቀር በአብዛኛው ታች ያለው ፋኖ ያለወረቀት ተዋሕዶ በአንድነት መዋደቅ የጀመረ ነው። የጎጃሙ ነው አደገኛው። መሰሪው፣ ሾተላዩ። እሱም ቢሆን የጊዜ ጉዳይ ነው ብቻውን ይቀራል። የጎጃም የበላይ ዘለቀ ልጆችም ወደፊት ይመጣሉ። እናም አቢይ አሁን በያዘው አቋም ግን የፋኖ ሳይሆን የሕዝብ ማዕበል ያጥለቀልቀዋል። በጥላቻ የሰከረው የሽመልስ አብዲሳ ልዩ ኃይል ሕዝቡን ከፋኖ አይለይም። ከእስካሁኑ ጭፍጨፋ በበለጠ ሕዝብ ይጨፈጨፋል። በመድፍ፣ በጀት፣ በድሮን የዐማራ ከተሞችን ያወድማል። ለዚህም ይልማ መርዳሳ ዝግጅቱን ጨርሷል። ፋኖ ቅንጣት ታህል ጉዳት አያገኘውም። አገዛዙ ግን ይህን እያወቀ ዐማራን እንደ ጋዛ ሊያደርጋት ተዘጋጅቷል። አቢይ መገንዘብ ያልቻለው፣ እስራኤል በጋዛ ያን ያህል ውድመት አድርሳ ሐማስን ያላሸነፈች፤ የታገቱትንም በሠራዊቷ ያላስለቀቀች መሆኑን ነው። አቢይም ፋኖን ማሸነፍ ቀርቶ ካለበት ኢንች ፈቀቅ ማድረግ አይችልም። የሕዝብ ማዕበል ይነሳል፤ የአቢይን አራጅ ሠራዊት በዱላ፣ በመጥረቢያ፣ በማጭድ፣ እጁ ላይ ባገኘው መሣሪያ ይውጠዋል። ፋኖ የሚታጠቀውን መሣሪያ ሕዝቡ ይታጠቀዋል። ውድቀቱም ይፋጠናል። አወዳደቁም የከፋ ነው የሚሆነው። ብቻውን ሳይሆን በስሙ ብዙ ወንጀል የሠራበትን የኦሮሞን ሕዝብም ይዞ ነው የሚወድቀው። አቢይ ሆይ የአንተን ስሕተት የኦሮም ሕዝብም ያወራርደዋል። እናም ምክሬ ሳይመሽ የኦሮሞ ሕዝብ ከዐማራ ወንድምህ ጎን የምትቆምበት አጋርነትህን የምታሳይበት የመጨረሻው ወቅት አሁን ነው። ለወደፊት ህልውናህ ስትል ዕወቅበት። አይጥ በበላ ዳዋ ተመታ እንዳይሆን ፍጠን። የአቢይ ውድቀት ይዞህ እንዳይጠፋ ተጠንቀቅ። መራር ነው ግን እውነት ነው ዋጠው። "…ዐማራን ወደብ ላመጣ ነው፣ ቀይ ባህርን ልመልስልህ ነውና አትውጋኝ አትበለው። ኤርትራንም በወልቃይት በኩል ስትፈልግ በዛላንበሳ በሽሬ ሞክራት፣ ውረራት፣ በአፋር በኩልም ቅርብ ነው። ስታርደው፣ ስትገፍፈው፣ ስታሸማቅቀው፣ አዲስ አበባ እንዳትገባ ስትለው፣ ወራሪ፣ ሰፋሪ ስትለው፣ በድሮን፣ በቦንብ ስትጨፈጭፈው ውለህ የምታድረውን ዐማራ አሁን ላይ ደርሰህ አንድ ጊዜ መዋጋቱን እናቁምና አሰብን፣ ወደቡን እናምጣው ናና ተከተለኝ አትበለው። ፊንፊኔን ኬኛ፣ ጎጃም ኬኛ፣ ጎንደር ኬኛ፣ አክሱም ኬኛ፣ ወሎን ኬኛ ስትል ቆይተህ አሁን ድንገት ደርሰህ አሰብ የኢትዮጵያ ነው ብለህ አትጃጃል ጋሽ ኬኛ። አዎ አይደለም አሰብ ኤርትራም የኢትዮጵያ አካል ናት። ይሄን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከጠላት፣ ከባንዳ በቀር ያምናል። በዘመነ ኦሮሞ፣ በሁሉም ኬኛ ዘመን አሰብ የኢትዮጵያ ነው ብትል የሚሰማህ የለም። ይልቅ ደሞዝ፣ የቤት ኪራይ፣ አበል እከፍልሃለሁ እና ለፊንፊኔ ፖሊስነት ለ30 ዙር ኑና ሰልጥኑ ብለህ በማስታወቂያ የምትጠራቸውን የሊሙ ሰቃ የአባ ገዳ ልጆች ይዘህ ንካው። ለጊዜው የዐማራ ወደቡ አራት ኪሎ ብቻ ነው። መንገዱን ጨርቅ ያድርግልህ ብሎሃል ዐማራ። ሀሚቲንና አቢይን የምትረዳው ኤምሬትስ በሱዳንና በአሩሲ አላህ ወአክበር እያለ እናትን ከእነ ልጆቿ ጨፍጭፎ የሚበላ አራጅ ቡልጉ ጭራቅ ተከትሎ ኤርትራ የሚዘምት የለም። እነ የትነበርክ ተድላም አድቡ፣ ተኝታችሁ ከርማችሁ ዐማራ ላይ አታናፉ። ዐማራ የቤት ሥራ አለበት። የምትፈርስ ሀገር ላዩ ላይ ወድቃ ቢያንስ በፍርስራሹ እንዳይቀበር የመከላከል አቅሙን ማጎልበት፣ ከዚያም አለፍ ሲል ከዚህ ፀረሰው የሰው ቡልጉ ሥርዓት ኢትዮጵያን አይደለም ቀጠናውን መታደግ አለበት። እናም እረፉ። የአቢይ አገዛዝ ይወድቃል። ማዳጋስካር፣ ካሜሮን፣ አሁን ታንዛኒያ የደረሰው ሕዝባዊ ዐመጽ ብልጽግና የተባለን ሁሉ ከፋኖ በፊት ቆረጣጥሞ ይበላዋል። መራራ ጉዲና ያለውም ቃል ይፈጸማል። የራበው ሕዝብ መንግሥቱን ይበላዋል። አከተመ። …👇④✍✍✍
Показать все...
star reaction 1 502👍 137🙏 42🏆 13🕊 8🔥 3😡 3 2🤔 2🤯 2
👆③✍✍✍ …ለዐማራ ፋኖ እጅ እየሰጠ አብሮ ለመታገል ቃል እየገባ ነው። "…ለማንኛውም የሰሜን ኢትዮጵያው ሕዝብ በጥንካሬ፣ በሥነ ልቡና፣ በወኔ፣ በውጣ ውረድ ችግርን በመጋፈጥ ለዘመናት የቆየ ከፍተኛ የሆነ ልምድ ያከበተና የአመራርና የመዋጋት አቅሙም ላለፉት  ሺህ ዘመናት የዳበረና የበለጸገም ነው። በሽምቅ ውጊያ፣ በቆረጣ፣ በፊት ለፊት ውጊያ፣ ስቦ በመምታትም እጅግ የተካነ ነው። ጦርነትን በስሜት ሳይሆን በስሌት የሚመራ፣ ወደ ጦርነት ከመግባቱ በፊት አሸንፎ የሚገጥም አደገኛ ሕዝብ ነው። ዐማራው መንግሥት እንኳ ባይኖር ራሱን በጎበዝ አለቃ አደራጅቶ ራስን የመከላከል የዳበረ ልምድም ያለው ድንቅ ሕዝብም። በሰብአዊ ርኅራሄው፣ በምርኮ አያያዝ፣ ለሰው ልጆች ባለው እኩልነትና ነጻነት፣ በሚሰጠው ፍቅር ጠላት እሱን ከመፍራት ይልቅ ጠላቱን እንደ ዱር እንስሳ አላምዶ ወዳጅ ማድረግን የሚችልበት ሕዝብ ነው። ለዚህ ነው የአቢይ አሕመድ ሠራዊት ወደ ዐማራ ግዛት ገብቶ እንደ እንቧይ ካብ እየተናደ ወደ ዐማራ ፋኖ እየተመመ፣ እየጎረፈም ያለው። ይህ የዳበረ የዐማራ ጠባይና ስብዕና ነው አሁን ላይ ዐማራን ጠላቱን እየቀነሰለት ወዳጅም እያበዛለት ለዐማራ የፋኖም የጀርባ አጥንት እየሆነለት የመጣው። "…የፋኖ አደረጃጀት በካምፕ፣ በቦታ፣ በድንበር የተወሰነ ሳይሆን በጎጥ፣ በቀበሌ፣ በወረዳ፣ በአውራጃ፣ በክፍለ ሀገር፣ በመላው ዐማራ የመላ በመሆኑ አገዛዙ በቀላሉ ለመቆጣጠር አያስችለውም። ሌላኛው የፋኖ ጥንካሬ የመልክዐ ምድር ጠቀሜታ ነው። በየሰፈሩ የተበተነው ሠራዊት በቀላሉ ይጠቃል። በየሰፈሩ የሚረወረው የድሮን ቦንብ፣ የሚተኮሰው መድፍና ሞርታር በቀላሉ ይባክናል። ወጪው ደግሞ የማይቀመስ ነው። መቼም ከሱዳንና ከኢትዮጵያ ተዝቆ በሚሄድላት ወርቅ፣ እንዲሁም ዓረቦችን አረብ መስላ በማዳከም አዲሷ የዓረብ ቅኝ ገዢ የሆነችው ኤምሬትስና ቱርክ ለጥቅማቸው ሲሉ በገፍ የሚያቀርቡለት ቦንብና ድሮን ከነ ቴክኒሽያኖቹ በገፍ ስላሉት ነው እንጂ ወጪው በኢትዮጵያ አቅም የማይቀመስ ነበር የሚሆነው። እንዲያም ሆኖ በ10 ሚልዮን አንድ የድሮን ቦንብ 2 አህያ፣ አንድ በሬ፣ ትምህርት ቤት፣ ጤና ጣቢያ፣ እናትና ልጅ መግደሉ አልቀረም። በእስከአሁኑ ድካማቸው የፋኖን ኃይል ሊያጠቁ አልቻሉም። ወታደር ይመረቃል፣ ይመረቃል፣ በገፍ ወደ ክልሉ ይገባል። ነገር ግን የገባው ቤርሙዳ እንደገቡ መርከቦች ሰምጠው ከመቅረት በቀር ሌላ አማራጭ የሌላቸው ሆነዋል። ወታደሩ በቲክቶክ ይፎክራሉ፣ በአካል ይኮመተራሉ። አሁን ላይ በዐማራ ግዛት የተበተነው ሠራዊት በማያውቀው ሸለቆ፣ ተራራ፣ ሰፈር፣ ቀበሌ ገብቶ እንደ ሰም ቀልጦ እየቀረ ነው። የዐማራ ፋኖ መውጫ መግቢያውን ስለሚያውቅ፣ የቦረቀበት ሸለቆ፣ ጋራና ሸንተረር በመሆኑ መቶውን የአቢይ አሕመድ ሠራዊት ሁለት የዐማራ ፋኖ እንደ ከፍት ይነዳዋል፣ ይደመስሰዋልም። ፋኖ በልምድ ያካበተውን የተኩስ ችሎታ በሥልጠና አዳብሮ አንዲት ጥይት መሬት አትወድቅም፤ ቅንድብ ነው የምትላጨው። "…ይህን በየሰፈሩ የተዋቀረን ዘመናዊ የፋኖ አደረጃጀት እንኳን ማሸነፍ ለመደራደርም ቢሆን አሁን ላይ አዳጋች ነው። በሳምንት ውስጥ ሱሪውን፣ ቀበቶውንም እናስፈታዋለን የተባለው ዐማራ የመከላከያውን ሱሪም፣ ቀበቶም እያስፈታ ታየ። ሦስት ጠምንጃ ይዞ መንግሥት መገልበጥ አይቻልም የተባለለት ዐማራ ዛሬ ላይ በአርፒጂ ያደባየው ጀመር። ሺ ዓመት ብትዋጉንም አታሸንፉንም የተባለ ዐማራ በሁለት ዓመት ፍርክርኩን አወጣው። 10 ቢልዮን ዶላር መድቤ እዋጋቸዋለሁ ያለውን አቢይ አሕመድን 10 ቢልዮን ዶላር ለማግኘት አይኤምኤፍ እግር ስር ተደፍቶ ውሎ እንዲያድርም አደረገው። 1ዶላር በብላክ ለ200 ብር ፈሪ የሚዘረዘር ሆኖ ተገኘ። አንድ ሊትር ነዳጅ 120 ብር መቅዳት ግድ ሆነ። ኑሮ ሰማይ፣ ጣራ ነካ። ይሄ ሁሉ የዐማራ ፋኖ በአገዛዙ ላይ ባሳረፈው ጡጫ ምክንያት የመጣ ኪሳራ ነው። አንድ የዐማራ ልጅ በአስተዳደጉ እንደ መደበኛ ትምህርት ከእናት አባቱ፣ ከማኅበረሰቡ የሚወስደው ሥልጠና አለ። ከስም አወጣጡ ጀምሮ ብንመለከት አሸናፊ፣ መክት፣ ንጉሡ፣ መኳንንት፣ ከበደ እየተባለ ነው የሚጠራው። ተሸንፎ ከቤት የመጣ ልጅ ምግብ አይሰጠውም። ሥነ ልቦናው በጥንካሬ ነው የሚገነባው። በራሱ የሚኮራ ትግራይ ላይ የካሌብን፣ የአብርሃን፣ የአጽብሃን፣ የምኒልክን፣ የሳባን፣ የዐጼ ዮሐንስን ታሪክ ተግቶ ነው የሚያድገው። ወሎ ላይ የላሊበላን፣ የነራስ ካሳን ታሪክ ይጠጣል። ጎንደር የፋሲልን፣ የቴዎድሮስን ወኔ የተላበሰ ነው። ጎጃም የበላይ ዘለቀን፣ የንጉሥ ተክለ ሃይማኖትን ታሪክ ይጎናጸፋል። ሸዋ ላይ የዐፄ ዘርዓ ያዕቆብን፣ የዐፄ ዳዊትን፣ የዳግማዊ ምኒልክን ታሪክ ይዋኝበታል። በዚህ የሕሊና ውቅር የተመሠረተን የዐማራ ፋኖ በቀላሉ ማሸነፍ ሕልም ነው የሚሆነው። "…የአገዛዙ ሠራዊት በተቃራኒው በጥላቻ ያበደ፣ ከኢትዮጵያ ታሪክ የተነጠለ፣ ማንነት ፍለጋ የሚንከራተት፣ ሥነ ልቦናው የተጎዳ፣ ያየው ሁሉ የሚያምረው፣ ማውደም እንጂ መገንባት የማይችል፣ የትላንት ማንነትህ ተነጥቋል ተብሎ ያደገ፤ መንጠቅ መቀማትን እንደ ባህል የሚቆጥር፣ በቀላሉ የያዘውን መሣሪያ የሚያስነጥቅ፣ መማረክን እንደ ባህል የሚቆጥር፣ ርእዮተ ዓለም የሌለው፣ ጭፍን፣ ወሬ ብቻ፣ እንደ ሕፃን በአሻንጉሊት፣ በብልጭልጭ ነገር የሚታለል፣ የሚፈዝ፣ እንደ ሴተኛ አዳሪ ጨለማን እንደ ቡናቤት በመብራት፣ በዲምላይት ማንቦግቦግን ይሄንኑ እንደ እድገት ቁጠሩልኝ፣ ቢርባችሁ፣ ቢጠማችሁም በመናፈሻና በፓርኮቹ ውስጥ እየተንሸራሸራችሁ አየር ብሉና ኑሩ የሚል ቀሽም፣ በተንኮል ከኢትዮጵያ ተነጥሎ ያደገ በመሆኑ አገዛዙን ክስረት አድርሶበታል። "…ሌላው የአገዛዙ ስሕተት የዐማራን ሥነ ልቦና ጠንቅቆ አለማወቁ ነው። ዐማራ ነጻ የሆነ፣ የማንንም ነጻነት የማይቀማ፣ የራሱን የማይሰጥ፣ የሰውን የማይወስድ፣ በእኩልነት፣ በፍትሐዊነት የሚያምን፣ ጭቆናን ፈጽሞ የማይቀበል ብቻ ሳይሆን አምርሮ የሚጸየፍ ጭምር። ለጠብም የማይመች ሕዝብ ነው። መሸነፍንማ ፈጽሞ  የማይወድ ብቻ ሳይሆን የሚያስቀጣው ጭምር ነው። ሞቶ ካልሆነ በቀር በሕይወት እያለ የማይማረክም ነው ዐማራ። ዐማራ ሲበዛ በቀለኛ ነው፤ ደም ሳይመልስ እንቅልፍ አይወስደውም። አባቱን ሰው የገደለበት ልጅ ደም መላሽ ተብሎ ነው የሚጠራው። በምድር ላይ ካሉ ጦረኛ ሕዝቦች የሰሜኑ ሕዝብ አንደኛ ነው። ሁለተኛ እስራኤላውያን ናቸው። እንዲያው ውኃ ቀጠነ ብሎ ዘው ብሎ ጦርነት ውስጥ የሚገባ ሕዝብም አይደለም ዐማራ። ኢትዮጵያን ለብዙ ዓመታት የገዛ፣ በክብርም ያቆያት ነው ዐማራ። በሃይማኖት፣ በባህል የዳበረን ሕዝብ በፍፁም በቀላሉ ማንበርከክ አይቻልም። በሕዝቡ ብዛት፣ በሚኖርበት የምድሩ ቆዳ ስፋት ሲታይ ዐማራ በመላው ኢትዮጵያ ይገኛል። ከዐማራ የተነጠለችን ኢትዮጵያ እያየናት ነው። በዲፕሎማሲ፣ በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ፣ በእድገት አሁን በዘመነ ኦሮሙማ የት ነው ያለቸው? ጅቡቲ የምትንቃት፣ ሱማሌ የምታሾፍባት፣ ትናንት በራሷ በኢትዮጵያ ድጋፍ የተፈጠሩት ደቡብ ሱዳንና ኤርትራ ግዛቶቿን ወርረው የሚይዙባት። ኬንያ የምትፀየፋት። የዓለም መንግሥታት የማይጎበኟት። ምኖቹ ላይ ጣለሽ ብለው ወዳጆቿ ሁሉ የሚያለቅሱላት ሀገር ነው የሆነችው። ማርያምን ኢትዮጵያንማ ዐማራ ይምራት። ትግሬም መርቷት ያተረፍነውን አይተናል። ስደት፣ ዝሙት፣ ግሉምትና፣ ሌብነት፣ በዘር መከፋፈል ነው ያተረፍነው። ኦሮሞም ይኸው እየመራት አይተናል፣ የዘር ጭፍጨፋ፣ ግድያ፣ ሰው አግቶ ሚልዮኖች መጠየቅ፣ የጉቦ ሕጋዊ መሆን፣ የነውር ጌጥ መሆን፣…👇③✍✍✍
Показать все...
star reaction 135 480🙏 103👍 101🏆 14🕊 7 5🔥 3🤔 3🤯 3 2
👆②✍✍✍ …ገፊ ምክንያቶች ዐማራው ፋኖ የሚል ኃይል እንዲፈጥር ትልቅ እድል ከፈተለት። እግዚአብሔር ይመስገን። "…ዐማራው በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በማእከላዊ መንግሥት ላይ አመጸ። አቢይ በተሳሳተ ስሌት፣ በዕውቀት ማነስ በምዕራባውያን ጫና፣ የፕሪቶርያውን ስምምነት ፈርሞ ሕወሓትን በለመደው የቁማር ፖለቲካ ከጎኑ አሰልፎ ሕወሓት እግረ መንገዷን በቅሏን ትበቀል ዘንድ በመወትወት፣ በመደለል ትግሬን በሌሎች እንዳደቀቀው ዐማራንም በትግሬና በኤርትራ ለማድቀቅ አሰበ። ትጥቅ ፍቱ በማለት ዐማራ ላይ ጦርነት ዐወጀ። ሕወሓትን ያሸነፋት አቢይ ሳይሆን ዐማራው እንደሆነ ሕወሓት በደንብ ስለገባት ድምጿን አጥፍታ አቅሟንም ዐውቃ ከቤቷ ሳትወጣ፣ ከሰፈሯም ሳትንቀሳቀስ ፀባይ ገዝታ ተቀመጠች። የኤርትራው ሻአቢያም የኦሮሞዎቹ አካሄድ ስለደበረው አይመለከተኝም፣ ከዐማራ ጋር አልነካካም ብሎ ኢግኖር ገጨው። ፖለቲካ ቁማር ነው። በቁማር ዓለም ደግሞ ማን ምርጥ ቁማር ተጫወተ ሳይሆን ቁማሩን ማን በላው፣ ጠቀለለው የሚለው ነው። እናም እኔ ዓባይ ማዶ ተሻግሬ ዐማራን ቁማር በልቼዋለሁ በማለት በአደባባይ በወንፊቱ ሽመልስ አብዲሳ በኩል ተነግሮ በእኔ በዘመድኩን በቀለ በኩል ለሕዝብ ይፋ የሆነበትን የኦሮሙማውን ቁማር ሴራ የሰማችው ህወሓት ብር ቢሰጣት፣ ሚሊንየም አዳራሽ አሸንዳን ጨፍሪበት ተብላ በአዳነች አበቤ እንክብካቤ ቢደረግላት። የጥፋት መሃንዲሱን አቦይ ስብሃት ነጋንና በጦርነቱ የተማረኩትን ወያኔዎች በሙሉ ፈትቼላችኋላሁ ብሎ እጅመንሻ ቢያቀርብ ወያኔ ሞኝህን ፈልግ ብላ እሷም እንደ ሻአቢያ ኦሮሙማውን ኢግኖር ገጭታው ብቻህን ተወጣው በማለት እንዲያውም ለምን ዐማራና አቢይ ሲፋለሙ ከሩቅ ሆኜ አልመለከትም በማለት ከዳር ቆማ ማጤን ጀመረች። ተባብረው የወጓት በጦር ሲቀራደዱ እሷ በደስታ እየሰከረች ተመለከተች። በአቢይ ጅልነትና ማይምነት ምክንያት ዋና አጋሩ የሆነውን ዐማራን ያጣውን አቢይን እያመሰገነች ራሷን እያሻሻጠች አገገመች። አቢይ በወቅቱ አብረውት የነበሩትን ሁሉ ሲያጣ፣ ከዳያስጶራው ጋር ሲቆራረጥ፣ ከዚያም አልፎ ከዋናው አጋሩ ከሻአቢያ ጋር እሳትና ጭድ ሲሆኑ እያየች አፈር ልሳ ተነሣች። በጁንታው ጦርነት ወቅት ከአቢይ አገዛዝ ጋር ኢትዮጵያን ብለው የተሰለፉ ክልሎች፣ ቤርቤረሰቦች ለአቢይ ጀርባቸውን ሰጡት። የደቡብ የጴንጤ ፓስተሮች፣ የኦሮሞ የጴንጤና የወሀቢያ እስላም ሓላፊዎች ብቻ አቢይ ከወደቀ እኛም ያበቃልናል በሚል ሰበብ በአደባባይ እየቀሰቀሱ የደቡብና የኦሮሞ ወጣቶች ብቻ በግዳጅ፣ በአፈሳ ጭምር ወደ ዐማራ ክልል ከማዝመታቸው በቀር ሁሉም በዐማራ ጉዳይ ጀርባውን ነው የሰጠው። ሰልፍ የሚወጣ የለም፣ ስንቅ ለሠራዊቱ የሚያቀብል የለም። ሠራዊቱ ደጀን ሕዝብ የለውም። አቢይን ጨምሮ በወያኔ ላይ ከስድብ አንስቶ እስከማዋረድ የሚደርስ መግለጫ ይሰጡ የነበሩት እነባጫ ደበሌ፣ እነአዳነች አበቤ፣ የድሬደዋው ከንቲባ፣ የደቡብ፣ የጋንቤላ፣ የቤኒሻንጉል አስተዳዳሪዎች ዐማራን ወጥተው እንደ ትግሬዋ ሂዊ ለመሳደብ አልሞከሩም። በቃ ዐማራ ይችላል። ቢሮክራሲውም ጠንካራ ነው። ያስፈራል። ይሄን ሁሉ ሳያገናዝብ ነው በጎንደር ስኳድ፣ በጎጃም አገው ሸንጎ፣ በፀረ ዐማራ የኦሮሞ ፖለቲከኞችና በእነ ዳንኤል ክብረት ምክርና አይዞህ ባይነት አቢይ ዐማራን በቀላሉ ትጥቅ አስፈታለሁ ብሎ ዘው ብሎ ዐማራ ግዛት ገብቶ ከፋኖ ጉያ ተወሽቆ በዚያው ሟሙቶ የቀረው። ፋኖም አንድ ጥይት ሲተኮስ ሽምጥ የሚጋልበው መከላከያን በጁንታው ጦርነት ጊዜ አጠገቡ ሆኖ በደንብ የሚያውቀው ተቋም በመሆኑ ምንም ጭንቀት አልገባውም፣ አላሳሰበውም፣ አላስፈራውምም። ውጤቱም ይኸው ባለፉት ሁለት ዓመታት ወደ ዐማራ ቀጠናዎች የሚገባ ሠራዊት እንጂ የሚወጣ ባለመኖሩ ታይቷል። "…ፋኖ ቀለቡን ከእናት እና ከአባቱ፣ ትጥቁን ደግሞ ከጠላቱ በመበጀት፣ አገዛዙ ላይ በኢኮኖሚ፣ በሰው ኃይል፣ በፕሮፓጋንዳ፣ በወጪ ኪሳራ በማድረስ ራሱን በውጊያ፣ በትጥቅ፣ ከታች ወደ ላይ በመደራጀት፣ በመሰብሰብ፣ የውስጥ ባንዳን በማጥራት፣ ስሕተቱን ከስር ከስር በማረም የመንግሥትነትን ቁመና በመላበስ፣ ነጻ ቀጠና በማስፋት፣ የዐማራ ብልፅግና ተብዬውን የብአዴንን አመራር የማይላወስ፣ ወገቡን የተመታ ጩኸት ብቻ የሚሰማ ውሻ በማድረግ ለመደራደርም ለማሸነፍም የማይመች የእሳት አሎሎ፣ የብረት ቆሎ ሆኖ አሁን ካለበት ቁመና ደረሰ። የፋኖ ጥንካሬ የራሱ ብቻ ሳይሆን የአገዛዙም ስሕተት ነው። በመጀመሪያ የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል እንዲሉ አገዛዙ ወጣቶችን መረሸን፣ ሴቶችን መድፈር፣ አዛውንቶችን ማሰር፣ ቀሳውስትን መግደል ጀመረ። በዚህ ስሕተቱ ወጣቱ ተገፍቶ የፋኖን ትግል በገፍ ተቀላቀለ። ሕዝቡም መከላከያን እንደ ኢትዮጵያ ሠራዊት ሳይሆን እንደ ግራዚያኒ፣ እንደ ደርቡሽ፣ እንደ ግራኝ አህመድ አድርጎ ተመለከተው። ከፋኖ ጎን እንዲሰለፍ አስገደደው። በወለጋና በመተከል ያየውን ጭካኔ በየደጁ እስኪበቃው ተመለከተ። ማዳበሪያ ይሰጠንና አምርተን ሀገር እንቀልብ ብለው በጨዋ ደንብ በሰላማዊ ሰልፍ የጠየቁ የዐማራ ገበሬዎችን "የጅራፍ ቦለጢቀኞች" በማለት አላገጠባቸው። ከሚታረዱት በተጨማሪ አዲስ አበባ ለመግባት የሚታገቱት፣ ታግተውም በኦሮሚያ ባንክ በሰው ሚልዮን ብር የሚጠየቁት ዐማሮች ይህንና ይህን የመሰለውን የኦሮሙማውን አፓርታይድ ሥርዓት ሲመለከቱ "የሕዝብ ልብ" ሸፈተ። ሕፃናቱ፣ አዛውንቱ ፋኖ ፋኖ አለ። አገዛዙ በራሱ ፈቃድ የሕዝብን ወገንተኝነት አጣ። ሠራዊቱ ደጀን የሌለው፣ በሕዝብ ዘንድ የተጠላ፣ ዐይንህን ለአፈር የሚባል ሆነ። አሁን ላይ ሠራዊቱ ሕዝብን አያምንም፤ ሕዝብም ሠራዊቱን አያምንም። ይህ የአቢይ ስሕተት ነው ለዐማራ ፋኖ ዋና የ ጥንካሬ ምንጭ የሆነው። "…ሌላው፣ መከላከያው ሀገራዊ ስሜት የሌለው ግማሹ የታፈሰ፣ ግማሹ በጥላቻ የሰከረ፣ ዓላማ ቢስ፣ የመዋጋት ብቃት ሞራል የሌለው፣ በፍርኃት የተዋጠ፣ በማያውቀው ነገር እና ሠፈር ለሠፈር የሚንከራተት፣ በቀላሉ የሚጠቃ፣ የሚማረክ፣ የሚኮበልል፣ መሣሪያውን ለፋኖ የሚያስረክብ፣ የአገዛዙን የጦር መጋዘን የሚያራቁት፣ የፋኖን የትጥቅ ፍላጎት በቀላሉ የሚያሟላ ስለሆነ ፋኖን ከሽምቅ ውጊያ ወደ ፊት ለፊት መደበኛ ውጊያ አሳደገው። በሌላ በኩል፣ የአቢይ ጀነራሎች ችሎታ ማነስ፣ በሙስና መዘፈቅ፣ በመሣሪያ ንግድና በሰዎች ሕገ ወጥ ዝውውር መሰማራት፣ የአንድ ብሔር የበላይነት ጎልቶ መታየት፣ እርስ በርስ አለመተማመን፣ በሚካሄደው ጦርነት አለማመን፣ ጊዜን ጠብቆ መክዳት፣ የግል ጥቅምን ማሳደድ፣ መረጃን በቀላሉ ለፋኖ ማሾለክ፣ ውጊያን ማበላሸት፣ በሁለት ቢላ መብላት፣ አንድ እግራቸውን ከአቢይ አንድ እግራቸውን ከፋኖ በማድረግ የአገዛዙ ሠራዊት በደፈጣና በውጊያ፣ በምርኮና በኩብለላ እንዲያልቅ በማድረግ የዐማራ ፋኖ በአጭር ጊዜ ውስጥ ራሱን ግዙፍ ጠንካራ ወሳኝ ኃይል ሆኖ እንዲገለፅ ረድቶታል። አቢይ ዐማራ እና ልምድ ያላቸው ሆነው ብአዴኖች እንኳ ቢሆኑ ብሎ የሚጠረጥራቸውን እንኳ የማይምር መሆኑ፣ ሕዝብ ይወዳቸዋል፣ ያዳምጣቸዋል፣ የሕዝብ ተቆርቋሪዎች ይሆናሉ ያላቸውን በሙሉ በመግደል፣ በማሰር፣ በማባረር፣ ጡረታ በሚል በማሰናበት አስወገደ። በምትካቸው የተሾሙትም በሆዳቸው እንጂ በራሳቸው የማያስቡትንና ሞግዚት የሚያስፈልጋቸውን ሾሞ ሲያለቅስ የሚያለቅሱ፣ ሲስቅ የሚስቁ አቅመ ቢሶች፣ የፖለቲካ ዐይነ ስውራን፣ ጀነራሎች ቁጭ ብድግ የሚያሰኟቸው ድኩማን በመሆናቸው ፋኖ እንዲጠነክር አድርጎታል። ፋኖን ይመክታል የተባለው ሚሊሻና አድማ በታኝ አሁን ልብ ወደ መግዛት እየተመለሰ ነው። በገፍም…👇②✍✍✍
Показать все...
star reaction 1 510👍 142🙏 47🏆 16🕊 6🔥 3 2
"ርእሰ አንቀጽ" • የአቢይ አወዳደቅ "…አቢይ ዋና ችሎታው ማስመሰል ሲሆን የወረሰውም ከአባቱ ከሕወሓት ነው። ነገር ግን የሕወሓት ትወና ብልኃት፣ ጮሌነትና ጥንቃቄ የተሞላበት፣ ትወናው በስውር የሚከናወን ነው። በተቃራኒው የአቢይ ትወና በሸፍጥ፣ በገሐድ፣ በጅልነት፣ በማይምነት የሚፈጸም ድንጋይ ዳቦ ነው የሚል ቂልነት የተጠናወተው፣ የተቀደደ ስልቻ ይመስል በሽመልስ አብዲሳ በኩል የሚያንዘረዝር ወንፊት፣ መቆጣጠሪያ የሌለው አቁማዳ፣ ካልተነፈሰ የሚፈነዳ የሚመስለው፣ ከዚህ በፊት የመምራትም ሆነ የማስተዳደር ልምድ የሌለው ጥራዝ ነጠቅ፣ በአጋጣሚ ሥልጣን ከእጁ የገባ፣ የታሪክና የዕውቀት ደሀ፣ የሥልጣን ጥመኛ፣ የማንነት ቀውስ የተጠናወተው፣ ካየው ሰፋሪ፣ ሁሉ ኬኛ ባይ፣ ያልሰከነ ዛር፣ ቀምቶ፣ ወንብዶ፣ ሸፍቶ፣ ዋሽቶ ሲበላ ሲቀማ የኖረ ወፈፌ በመሆኑ ሀገርን በቅጡ አይረዳም። ሥልጣን እንዴት ማቆየትና ማሻገር እንዳለበት አያውቅም፤ ችሎታም የለውም። ከጎኑ ያሰለፋቸው ሰዎችም የተለያየ ዓላማ ያነገቡ ናቸው፤ በዕውቀትም ከእሱ ያነሱ ናቸው። ኢትዮጵያን የምታህል ታላቅ፣ በዓለም የተከበረች፣ የተፈራች፣ ልዩ ስፍራ የሚሰጣትን ሀገር ይቅርና የአንዲት አነስተኛ መንደር ዕድር እንኳ መምራት የማይችሉ ደካሞች ናቸው። አማካሪዎቹ የራስ ማንነት የተጫናቸው፣ ግላዊ ሰብእና የሚያስጨንቃቸው ተዋናዮች፣ ዘፋኞች፣ ሞዴላ ሞዴሎች ናቸው። እንደ ዳንኤል ክብረት ያሉ በዲፕሎማ የእነዋሪ ተለማማጅ መምህር፣ የሰውን ታሪክና ሥራ በመቀማት የሚኩራሩም ቀማኞች ሁሉ ናቸው አጠገቡ የኮለኮሏቸው። "…ብታምኑም ባታምኑም ከፈለጋችሁ ይህን ርእሰ አንቀጽ ለታሪክ አስቀምጡት። የአቢይ ፍጻሜ እጅግ በጣም የከፋ ነው የሚሆነው። የእሱ ውድቀት ከሁሉ እጅግ ከባድ ነው። የእሱ ውድቀት እንደ ግርማዊ ቀዳማዊ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ አይደለም። የእሱ ውድቀት እንደ ደርጉ መንግሥቱ ኃይለማርያም አደይለም። የእሱ ውድቀት እንደ ወያኔ ሕወሓት እንደ መለስ ዜናዊ እንደ ስብሃት ነጋ የዓድዋው ስርወ መንግሥት ያለ አወዳደቅም አይሆንም። የእሱ ከሁሉ የከፋ ነው። ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት እንዳለው "…ሁሉ ዐመፁ በአንድነትም ረከሱ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም፤ አንድም ስንኳ የለም። ጕሮሮአቸው የተከፈተ መቃብር ነው፥ በምላሳቸው ሸነገሉ፤ ከከንፈራቸው በታች የእባብ መርዝ አለ፤ አፋቸው መርገምንና መራራን ተሞልቶአል፤ ደምን ለማፍሰስ እግራቸው ፈጣን ነው፤ ጥፋትና ጕስቍልና በመንገዳቸው አለ፥ የሰላምን መንገድ አላወቁአትምና፤ እግዚአብሔርን መፍራት በዓይናቸው ፊት የለም።) መዝ፥ 14፥ 3-6 …እንዳለ ነቢዩ ሁሉም አንድ ሆኖ የደነቆረበትና የወነጀለበት ጊዜ ነውና አወዳደቁም ሲታሰብ ያስፈራል። ጊዜው ታጣቂዎች እንደ አሸን የፈሉበት፣ የሕግ የበላይነት የተናደበት፣ ዝቅም ያለበት፣ ወሮ በላ ዘራፊ ቀማኛ ዱርዬ የሰፈር ሽፍታ የበዛበት፣ ዘመነ መሳፍንትን የሚያስንቅ ጊዜ ነው። በዐፄ ኃይለ ሥላሴ ውድቀት እሳቸውና ሥርዓቱ ብቻ ነበር ተለይተው የወደቁት። የዘውዳዊው ሥርዓት በዚያ መልክ መውደቅ ደስ ባያሰኝም ሀገሪቱ ግን ቀጥላለች፤ በደርግም ጊዜ አመራሮቹን ወያኔ ገሚሱን እንዲሰደዱ አድርጋ፣ ገሚሱን ገድላ ቀሪዎቹን በወኅኒ ቤት ዘብጥያ አቆይታ፣ የሞተው ሞቶ በሕይወት ከቆዩት መካከልም በምህረት ነፃ ወጥተው እስከአሁን በነፃነት የሚንቀሳቀሱ ሁሉ አሉ። ደርግ ወደቀ መንግሥትና ሀገር ግን ቀጠለ። በሕወሓትም እንደዚያው ነው። የወያኔ አመራሮች እህል ውኃቸው ሲያልቅ ገሚሱ ተሰደደ፣ ገሚሱ ጫካ ገባ፣ ገሚሱ ወደ ትግራይ ተሰደደ፣ ጥቂቶች ከዚያም ከዚህም እየተጫወቱ መሃል ላይ ቀሩ። ጥቂት የማይባሉትም በኤርትራና በኦሮሞ ብልጽግና ተገደሉ። አሁን ግን ሀገራችን እንደ ሦስቱም መንግሥታት አይደለም የምትሆን የሚመስለው። መለኮታዊ ጣልቃገብነት ከሌለ በቀር ሀገሪቱ ከአቢይ ጋር አብራ የመንኮታኮት አደጋ ነው ከፊቷ የተጋረጠባት። "…አቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን እንደመጣ በቀላሉ የመምራት ዕድል ያለ መስሎት በመርገጥ፣ በመደፍጠጥ፣ በመጨፍጨፍ፣ ሰጥ ለጥ አድርጎ የኦሮሙማን ፍላጎት ለማሳካት በበላይነትም ለማስጓዝ አቅዶ የሄደበት ርቀት አሁን ላይ የሌለ እና ከማይወጣበት ቅርቃር ውስጥ ከቶታል። አሁን ያለውን ሁኔታ አስቀድሞ ተረድቶ ቢሆን ኖሮ በእርግጠኝነት አቢይ አሕመድ ፈጽሞ አይሞክረውም ነበር። የሰሜኑ ጦርነት ለአቢይም፣ ለፋኖም፣ ለሕወሓትም ያልተገመተ ክስተት አሳይቷቸዋል። ሕወሓት በተነሳበት ተቃውሞ በአሜሪካ ግፊት በቀላሉ ከአራት ኪሎ ወደ መቀሌ ሲዛወር የሕዝብን ቁጣ አብርዶ፣ አስተማማኝ ኃይል ገንብቶ፣ እፎይታ ወስዶ፣ ብሔር ብሔረሰቦች የሚለውን አሰልፎ፣ አቢይን ፈንቅሎ መልሶ አራት ኪሎ እንዲደላደል ነበር። ግን የሆነው ግልባጩ ነው። አቢይ ወያኔ ራሷ ጠፍጥፋ በአምሳሏ የፈጠረቻቸውን ብሔር ብሔረሰቦችን ከራሷ ቀምቶ፣ እነሱኑ ጠመንጃ አስይዞ አሰልፎ ከጎረቤት በወያኔ ላይ የ20 ዓመት ቂም ይዛ ምቹ ቀን ትጠብቅ የነበረችዋን ኤርትራን ጨምሮ የሕወሓትን ወንጀል በእጥፍ አባዝቶ በከፍተኛ ቅስቀሳ የሕወሓትን ሕልም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አመከነ። ሕወሓት አሁን የሚጮኸው ስለ አራት ኪሎ አይደለም ስለ ሕልውናው እንጂ። አከተመ። "…የሰሜኑ ጦርነት ለአቢይ አሕመድ የፈጠረለት ስሜት ቢኖር እንዴት በቀላሉ ጦርነት ማሸነፍ እንደሚችል ነው። ሰማይ የደረሰው ፈርኦን ናቡከደነፆሩ ሕወሓት በዚህ ደረጃ መውደቁን ሲመለከት ጦርነትን ዋና የስልጣኑ ማቆያ ቁልፍ ጉዳይ አድርጎ መቁጠር ነው የጀመረው። ሕወሓት በኢትዮጵያውያን ላይ በፈጸመችው ግፍ በሕወሓት ላይ ቂም የነበረው ሁላ ያን ቂሙን ይወጣ ዘንድ በብሔራዊ ቴሌቭዥን እና ራዲዮ፣ በጋዜጣ፣ በፓርላማ፣ በዘፈንና በድራማ፣ በሰልፍ ጭምር እየተቀሰቀሰ ሙሉ ኢትዮጵያ ተሰልፎ ሕወሓት የወጋበትን ምስጢር አለማወቁም ነው ዳግመኛ ከዐማራም ጋር ብዋጋ ልክ እንደ ሕወሓት ጀማውን አንቀሳቅሼ ልክ አገባዋለሁ ብሎ በተሳሳተ ስሌትና ቀመር እንዲንቀሳቀስ አደረገው። ትግሬን አግዝፎ፣ ዐማራን ንቆ አቅልሎ ገባበት። መግባት ግን እንደ መውጣት ቀላል አልሆነለትም። የዐማራው ምድር ረግረግ ሆኖ ዋጠው። ሰለቀጠው። ኢትዮጵያንም በሁሉ ነገር ሽባ አደረጋት። እነ ብርሃኑ ጁላ፣ እነ ባጫ ደበሌ፣ እነ ሽመልስ አብዲሳ፣ እነ አዳነች አበቤ፣ አማካሪዎቹ እነ ዳንኤል ክብረት በተረት፣ በፉከራ፣ በማዋረድ፣ በማቅለል ያላግጡበት የነበረ ዐማራ ዛሬ ሁላቸውንም ሳይለንት ሙድ ላይ ቆልፎ አስቀመጣቸው። አሞሌ ጨው የለ፣ ጃዊሳ፣ ኩይሳ፣ ፈይሳ፣ ጃርት የለ፣ ሽፍታ፣ ፅንፈኛ… ዝም። ጭጭ። "…የሰሜኑ ጦርነት ለዐማራው ኃይል ደግሞ የፈጠረው ስሜት ከሕወሓትም ከአቢይም የተለየ ነው። አይደለም ጠብመንጃ በትር እንኳ በእጁ እንዳይዝ የተከለከለው ዐማራ የሕወሓት ወሎን አልፋ ደብረ ሲና መድረስ ያስጨነቀው ኦሮሙማ በብአዴን በኩል ተዋጋልኝና በምትኩ ከህወሓት የምትማርከውን መሳሪያ ማርከህ እስከ አፍንጫህ ድረስ ታጠቅ ተባለ። እግዚአብሔርም የተገፋውን ዐማራ በጥበብ አገዘው። ከዘመነ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ጀምሮ እስከ ዘመነ አቢይ አሕመድ ድረስ የላሸቀው ዐማራም ወኔው ተቀሰቀሰ። አቢይ በዐማራው ላይ ሊያደርግ ያሰበውን ጭፍጨፋ ዐማራው በሰሜኑ ጦርነት በቅርበት ከመከላከያ ጎን በመሆን ተረዳ። ለወደፊት ራሱን ማዘጋጀት እንዳለበትም ወሰነ። በወለጋ፣ በመተከል የተደረገው የዐማራ ጭፍጨፋ፣ ከማእከላዊ መንግሥቱ የዐማራው በገፍ መገለል፣ የነሽመልስ አብዲሳ የኦሮሞ ቦለጢቀኞች በሙሉ የሰበርናቸውና ዓባይን ተሻግረን ቁማር በላናቸው ቀረርቶ፣ በሌሎችም…👇①✍✍✍
Показать все...
star reaction 1 567👍 140🙏 43 12🏆 10🕊 8🔥 2🤯 2
መልካም… "…ለትናንት አርብ ተዘጋጅቶ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ወደ ዛሬ የተሸጋገረው ርእሰ አንቀጻችን አሁን ይቀርብና እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ስንወያይበት እናመሻለን። ይህን ከሊቃውንተ ኢትዮጵያ ጋር በነበረኝ ጉባኤ ወቅት የያዝኩትን ማስታወሻ በርእሰ አንቀጽ መልክ አዘጋጅቼ ለእናነተ ለወዳጅ ጓደኞቼ ሳቀርብ ታላቅ ኩራትና ደስታ ነው የሚሰማኝ። "…ከኔፓል የተነሳው የለውጥ ፈላጊ ወጣቶች እምቢተኝነት ማዳጋስካር ገብቶ፣ አምባገኑን በአፍጢሙ ደፍቶ፣ በፈረንሳይ ጀት፣ ወደ ኤምሬትስ አስፈርጥጦ በታላቅ ድል ተጠናቅቋል። አፍሪካ የገባው የለውጥ ፈላጊዎች ዐመጽ በካሜሮን እየጋመ ሲሆን፣ አሁን ደግሞ በምሥራቅ አፍሪካ ታንዛኒያም ሰተት ብሎ ገብቷል። የታንዛኒያው ደግሞ የተለየ ነው። "…በታንዛኒያ ፕሬዘዳንቷ ወሮ ሳሚያ ሱሉሁ በምርጫ 98% ከመቶ አሸንፌአለሁ ብላ በብርቱካን ሚደቅሳ መሳይ ምርጫ ቦርዷ በኩል ዐወጀች። ሕዝቡም እንደ ኢትዮጵያ ሕዝብ " አቤት ውሸት፣ ምንአይነቷ አጭበርባሪ ናት? ትልቅ ሰው ይዋሻል እንዴ? በስመአብ፣ ቢስሚላሂ፣ ጌታ ሆይ ድረስ። ፈጣሪ የአንቺን መጨረሻ ያሳየኝ ብሎ ወደ ቤቱ ገብቶ መተኛትን አልመረጠም። ይልቁንም ግልብጥ ብሎ ነቅሎ አደባባይ ወጣ። ውረጂ፣ አልመረጥንሽም በማለት ሰቅዞ ያዛት። ፕሬዘዳንቷም እንደ ወያኔ፣ እንደ ኦሮሙማው እስቲ ጥቂቶችን ገድዬ ብዙሃኑን በማስደንገጥ አስደንብሬ አመፁን በእንጭጩ ልቅጨው አለችና ሰልፈኛው ላይ ተኩስ ከፈተች። 700 ሰውም ገደለች። ሕዝቡ ግን ጭራሽ ባሰበት። በመላው ሃገሪቱ አደባባይ ወጣ። ፎቶዋን ገንጥሎ እሳት ውስጥ ዶለው። አቃጠለውም። በመጨረሻም ወታደሩ ክፍል መሪዎቹ ኦሮሞ ብቻ ስላልሆኑ የለም፣ የለም ይሄነገር ያበቃለት ነው፣ ከአንዲት ሴት ጎን ቆመን ሀገር ያህል ከምናጣ ከሕዝብ ጎን እንቁም። ግድያም እናቁም በማለት ዜጎቻቸውን መግደል እንዳቆሙ። ከሕዝቡም ጎን ተሰልፈው እንደ ሕዝቡ ሆነው መጨረሻውን እያዩ እንደሆነ ነው እየተነገረ ያለው። "…ልብ በሉ የታንዛንያዋ ፕሬዜዳንት እንደ አቢይ አህመድ አንድ ሚልዮን ትግሬ አልጨፈጨፈችም። ቁጥሩ እስከአሁን ያልተገለጠ በብዙ ሚልዮን የሚቆጠር ዐማራ እንደጨፈጨው ዓይነት ጭፍጨፋ አልፈጸመቺም። ያደረገችው ነገር ቢኖር ልክ እንደወያኔ፣ እንደ ብልፅግናውን ጠልፋ 98% አሸንፌአለሁ ስላለች ብቻ ነው የታንዛኒያ ሕዝብ ከቤቱ ወጥቶ አደባባዩን ሞልቶ ሰማይ ምድሩን እያንቀጠቀጠው የሚገኘው። እንጂ ቤቱ፣ ትዳሩ፣ ንብረቱን፣ ሀገሩን እንደተነጠቀው፣ በሃላል እንደተጨፈጨፈው፣ እንደታረደው እና 120 ሚልዮን ኢትዮጵያዊ ጄኖሳይድ ተፈጽሞበት አይደለም። ልዩነቱ ግን ታንዛኒያውያን ይሄ  "በኃጢአታችን ምክንያት እግዚአብሔር ያመጣብን ቁጣ ነው" ብለው እጃቸውን አጣጥፈው፣ አፋቸውን ለጉመው፣ ወደ ቤተ ክርስቲያንና ወደ መስጊድ በመሄድ ጌታ ሆይ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤልን ሰይፍ አስይዘህ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስን ጦር አስይዘህ ይሄን አረመኔ ገላግልልን አለማለታቸው ብቻ ነው። ወዳጄ ይልቅ እንደ ፋኖ የቅዱሳን መላእክቱን ሰይፍ፣ የሰማእቱን ጦር ይዞ ዓድዋ ድረስ ሄዶ ዘምቶ ድል እንደማድረግ አቡነ ሳዊሮስ እግር ላይ ተደፍቶ የሥርዓት ለውጥ መጠበቅ ኃጢአት ነው። ለማንኛውም ሥርዓቱ ይወድቃል። ሲወድቅ ላያችን ላይ እንዳይወድቅ ምን እናድርግ በሚለው ዙሪያ በጊዜ መወያየት መጀመር መልካም ነው። "…መልካም… አሁን አመስጋኙ አንድ ሺ ሰው ሞልቷል። ለትናንት ተዘጋጅቶ የነበረው ርእሰ አንቀጹን ለዛሬ ልለጥፍላችሁ ነኝ። እስከዚያው የታንዛኒያውን አጫጭር ቪዲዮ እያያችሁ ርእሰ አንቀጹን ለማንበብ፣ አንብቦም በጨዋ ደንብ ሓሳብ ለመስጠት ዝግጁ ናችሁ…? • እስኪ አንድ 100 ያህል ሰው "ዘመዴ ዝግጁ ነነ" ይበል። ✍✍✍
Показать все...
1.76 MB
3.73 MB
7.85 MB
6.39 MB
star reaction 2🙏 520 325👍 141🏆 17 15🔥 5🕊 5🤯 4
Фото недоступноПоказать в Telegram
"…እግዚአብሔር በውስጥዋ ጻድቅ ነው፤ ክፋትን አያደርግም፤ ፍርዱን በየማለዳው ወደ ብርሃን ያወጣል፥ ሳያወጣውም አይቀርም፤ ዓመፀኛው ግን እፍረትን አያውቅም። ሶፎ 3፥5  • እንደምን አደራችሁ? • እንደምን አረፈዳችሁ? • እንደምን ዋላችሁ? • እንደምን አመሻችሁ? • መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
Показать все...
star reaction 3🙏 927 232👍 91🕊 17🏆 6😡 6 3💔 2🤔 1
መልካም… "…ዛሬ በዕለተ አርብ በሳምንቱ መጨረሻ በእኔ በዘመዴ ፔጅ ይቀርብ የነበረው ተጠባቂው ርእሰ አንቀጻችን ከሊቃውንተ ኢትዮጵያ ጋር በነበረን ውይይት ላይ ከተያዘ ማስታወሻ ተውጣጥቶ በግሩም ሁኔታ ተዘጋጅቶ የነበረ ቢሆንም እንደ ድንገት ባየሁት የሱዳን የንጹሐን ጭፍጨፋ ምክንያት በትክክል ማሰብ፣ ጣቶቼንም በትክክል ለማዘዝ በመቸገሬ ምክንያት ሳላቀርብላችሁ ቀርቷል። "…ነገ በጠዋት በዕለተ ቀዳሚት ሰንበት ከጠዋቱ የሥራ መጀመሪያ የምስጋና መርሀ ግብራችን በኋላ ግን ተዘጋጅቶ የተቀመጠ ስለሆነ በቶሎ እለጥፍላችኋለሁ። "…የተባበሩት አረብ ኤምሬት በሱዳን የግመል ነጋዴውን ሀሜቲ የመሀመድ ደጋሎን ፈጥኖ ደራሽ ጨፍጫፊ አሸባሪ ቡድን፣ በኢትዮጵያም የኦሮሞ ብልጽግና ወንጌል ፕሬዘዳንቱን አቢይ አሕመድን ይዛ ንፁሐንን በመጨፍጨፍ፣ በማስጨፍጨፍ፣ ለሀሜቲና ለአቢይ ድሮን ከእነ ኦፕሬተሩ፣ ከነ ቦንቡ፣ ጠመንጃ ከነ ጥይቱ፣ ዶላር በኮንቴነር እየሰጠች እሷ በምትኩ የሱዳንና የኢትዮጵያን ወርቅና መዓድነት ያለከልካይ ትዝቀዋለች፣ ታግዘዋለችም። "…በሱዳን መልካቸው ጠቆር ያሉት ሱዳናውያን እናንተ አረቦች አይደላችሁም ተብለው ለዘር ሳያስቀሩ ጨፍጭፈዋቸዋል። ክርስቲያን ሱዳኒዎችም ከጭፍጨፋው አልተረፉም። አላመለጡም። አላህ ወአክበር እያሉ ፈጣሪያቸውን እያመሰገኑ ነው የፈጇቸው። በተለይ እናቶችና ሕጻናቱ እንዴት አንጀት እንደሚበሉ አትጠይቁኝ። አላሃቸው ግን ምን አይነት ነው በማርያም? አንዲት ሴት እጇን አስረው አንጠልጥለው የሚፈጽሙባትም ግፍ ይዘገንናል። የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕም የሱዳኑን ጭፍጨፋ ሳይጠቅሱ በዓለም ላይ ክርስቲያኖች እና ክርስትና ጥቃት እየደረሰበት ነው በማለት የናይጄሪያው ቢኮ ሃራም ላይ እንደዛቱ ፎክስ ነውስ ለጥፎም አይቻለሁ። "…በኢትዮጵያችን በኦሮሚያ አሩሲ እንደዚሁ እንደ ሱዳኑ ያለ አረመኔያዊ ግፍ ነው የተፈጸመው። ሕፃን ሽማግሌ አልቀራቸውም። ጭፍጭፍ ነው የደረጓቸው። የሱዳኑ በስልክ እየቀረጹ ቀጥታ በቲክቶክና በፌስቡክ ነው የለቀቁት። የበተኑት። የእኛዎቹ እሱን ተከልክለው ሕዝቡ ነው አስከሬንና ዋይታውን ቀርጾ ዓለም ይመልከተን ያለው። የብልጽግና አገዛዝ እስከአሁን ትንፍሽ አላለም። የሱዳኑ ዓለም አቀፍ ጫጫታ ሲበዛበት ዋናውን ጨፍጫፊ በክብር አስረው ወደ ማረፊያ ወስደውታል። የኢትዮጵያዎቹ ማን አባቱ ነው የሚጠይቀን በማለት ጭራሽ ለቢቢሲ "ውሸት ነው" ሐሰት ነው የተጨፈጨፈ የለም በማለት ለሚዲያው ቃላቸውን ሰጥተዋል። "…ሲኖዶሱ ከስንትና ስንት ውትወታ በኋላ "እንደማንም ተራ ነገር በጉዳዩ አዝነናል" የሚል አናዳጅ፣ አብሻቂ መግለጫ ሰጥቷል። የኦሮሞ ብልጽግናን የገጽታ ግንባታ ለመከላከል ሲባልም ገዳዮቹን " ያልታወቁ ኃይሎች" በማለት ዘግበዋል፣ መግለጫም አውጥተዋል። ይሄን ባለቤቱ ያቀለለውን ዐሞሌ የጰንጤ፣ የእስልምናና የኦሮሞ የሃይማኖት ጉባኤ ተብየዎችም "ቤተ ክርስቲያኒቱ የሰጠችውን መግለጫ ዋቢ አድርገው እሷ እንዳለችው "ባልታወቁ ኃይሎች በተወሰደው ግድያ አዝነነናል" የሚል የለበጣ መግለጫ አውጥተዋል። እነ ኢቲቪ፣ ዋልታ፣ አሚኮ፣ ፋና፣ ኦቢኤምም ዝም ጭጭ ብለዋል። ኦኤምኤንም ትንፍሽ አላለም። "…የአሩሲው ሊቀጳጳስ አቡነ ያሬድ ሀገረ ስብከቱ ሄደው አያውቁም። አሁንም አሜሪካ ከርመው አርፈው ነው የመጡት። አሜሪካ የሚገኘው የማኅበረ ቅዱሳኑ ቀሲስ በላቸው የሚመሩት የቅዱስ ዮሐንስ ምእመናን ተራ ገብተው ሲቀልቧቸው ከርመው፣ በመጨረሻም ዶላር ተሸክመው ሀገር ቤት ከገቡ ገና ሳምንት ቢሞላቸው ነው አሉ። በጌታቸው አሰፋ ምክትል በያሬድ አማካኝነት በዘር ኮታ የተሾሙት አቡነ ያሬድ በሥልጣን ዘመናቸው ኦሮሙማው ከወይብላ ማርያም ጀምሮ የሚፈጽመውን ጭፍጨፋ እኔን አትንኩኝ እንጂ ምን አገባኝ በሚል ስሜት በደንታ ቢስነት መንጋውን ማስጨፍጨፋቸውን ቀጥለውበታል። የሚገርመው ነገር አሁን እንኳ ከሞት ተርፈው ሀኪም ቤት ያሉትን ሕጻናት እነ አቡነ ሳዊሮስ፣ ያሬድ መጎብኘት፣ ማጽናናት ሳይፈልጉ በመቅረታቸው ምክንያት የወላይታው ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ ቦታው ድረስ ሄደው ሊያጽናኑ እንደሆነ  ነው የሰማሁት። በረከታቸው ይደርብን። "…እኔን ትንፋሼን አሳጥሮ መጻፍ እስኪያቅተኝ ከፈጣሪዬ ጋር ሲያሟግተኝ የዋለውን ቪድዮ እያያችሁ ነግ በእኔ እያላችሁ እደሩልኝ። በነገራችን ላይ ኤምሬት ለሱዳኑ ሀሚቲ ከደቡብ አሜሪካ ከኮሎምቢያ ቅጥር ነፍሰ ገዳዮችን ዶላር እየከፈለች ሶማሊያ ላይ በተከራየችው ወደቧ በኩል በገፍ እንደምታስገባም ዘገባዎችን እያየሁ ነበር። በዐማራ ክልልም የሚፈነዳውን ቦንብ ድሮን ኦፕሬት የሚያደርጉት ኤምሬት ቀጥራ ያመጣቻቸው ሲሆኑ አስተኳሾቹ ግን ኦፒዎቹ እዚያው ጎጃም፣ ጎንደር፣ ሸዋና ወሎ ያሉ ዐማሮች ናቸው ይባላል። "…ዘመናዊ ቀኝ ገዢ ለመሆን አፍሪካውያንን እየፈጀች ማዕድኑንም ዝቃ አፍሳ እየወሰደች ሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎች እየገነባች፣ ለመዝናናት ደግሞ እኔው ጋር ኑ እያለች በንፁሐን ደም እየተገነባች የምተገኘውም ባቢሎን ኤምሬት ዱባይም እንደሰዶምና ገሞራ መጥፋቷ አይቀርም። ይሄ የጊዜ ጉዳይ ነው። ሱዳኖችም በአቢይ አሕመድ ምክንያት ኢትዮጵያም አብራ ነው የጨፈጨፈችን የሚል ክስ ማቅረብ ጀምረዋል። ይሄ የጠንቋይ የመተት የአስማት ባለዛር የኦሮሞ ብልፅግና መሪ ከሁሉ አጣልቶን ምን ዓይነት መዓት እየጠራብን እንደሆነ ፈጣሪ ይወቅ። • ደኅና እደሩልኝ የነገ ሰው ይበለን። 🙏🙏🙏
Показать все...
2.40 MB
2.77 MB
4.49 MB
14.07 MB
3.17 MB
829🙏 241💔 143👍 98🤔 12 11🏆 9🕊 8👌 7🔥 3😱 2
ከደጋው መብረቅ ኮር የተሰጠ የአንድነት ብሥራት መግለጫ የአማራ ሕዝብ በአሁኑ ጊዜ ሞት ከጥላው የቀረበ መሆኑንና የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር የአገዛዙ ኃይልና አማራ ጠል ኃይሎች በአማራው አንገት ላይ ያለማቋረጥ ሠይፍ እያሳረፉ ያሉበት ጊዜ መሆኑን ለአፍታም እንኳን የማንዘነጋው ጉዳይ ነው። አማራን በሌሎች ወገን ሕዝቦች ለማስጠላት የተኬደበት ርቀትም ረጅም ነው፤ በቢሮክራቲክ ተቋማት፣ በፖለቲካዊ ሹመት፣ በዲፕሎማሲው ረገድ ሳይቀር አማራው ከፍተኛ በደል እየደረሰበት ይገኛል፡፡ የአማራ ፋኖን ትግል በድል ለመቋጨት የአማራ የህልውና ታጋዮች አንድነት ወሳኝ ነው፡፡ እኛ የአማራ ፋኖዎች ወደ በረሃ የወረድነው፣ ቤታችንን ዘግተን ዱር ቤቴ ያልነው፣ የአማራ ሕዝብ ላለፉት ዘመናት በጎበጠ የፖለቲካ ትርክት ምክንያት ተገዳይና ተሳዳጅ መሆኑ እንዲያበቃ፣ ነጻነቱን እንዲያገኝ ነው። እኛን ከክፋት ሠሪዎች ጋር ፊት ለፊት በጠመንጃ አፈሙዝ እንድንጋፈጥ ያደረገን ወገናችንን በሀገሩ ላይ ከእኩልነት ደረጃ አውርደው በሕልውና ጥያቄ ቅርቃር ውስጥ ስላስገቡት ነው። የአማራ ሕዝብ የህልውናና የፍትሕ ትግል በሞራል፣ በሰብአዊነት፣ በሃይማኖት፣ በማኅበራዊና ዓለም አቀፋዊ የሕግ ሚዛኖች ሁሉ ፍትሓዊ ብቻ ሳይሆን ሰው ሆኖ መፈጠር የሚያስከትለውን ራስን በክብር የመጠበቅ ተፈጥሮአዊ እዳን የመክፈል የማይቀር ትግል ነው። ታላቁ ሰማዕት ፕ/ር አሥራት ወልደየስ “አማራ የለም” ለሚሉ ጠላቶች ምላሽ ሲሰጡ “አማራ የለም ትላላችሁ፤ ለመግደል ስትፈልጉት ግን ታገኙታላችሁ” እንዳሉት ጠላቶቻችን በጅምላ ሊጨፈጭፉን የሚፈልጉን ሕዝቦች ነን፡፡ ይኸውም ከወለጋ እስከ ባሌ፣ ከሞያሌ እስከ ማይካድራ ድረስ የተደረገ የትላንት ታሪክና እስከ ዛሬ የቀጠለ በአለም ፊት በገሃድ እየተፈጸመ ያለ ሐቅ ነው፡፡ ጠላቶቻችን መርጠው የማይገድሉን፣ በጋራ የዘመቱብን፣ በአማራነታችን ብቻ በጅምላ የሚፈጁን ከሆነ እኛ በአንድነት በመሠለፍ ትግላችንን ከድል ምዕራፍ ለማድረስ የሚያግደን ምናለ? ሥልጣን ነውን? ገዳይ በበዛበት፣ ሕዝባችን ዕለት ዕለት እየሞተ ባለበት ሁኔታ የትኛው ሥልጣን አጓጉቶን ነው? ዝና እና ሕዝበኝነት ነውን? ሕዝባችን በሞትና በስደት መከራ በሚያይበት ሀገር ላይ ሆነን እኛ ታጋዮች ስለ ምን ዝና መናገር እንችላለን? ፍትሕ በተጓደለበት ሕዝባችን ፊት ስለምን ዝና ልናወራ እንችላለን? ኃብትና ገንዘብ ነውን? ለመሞት ወስነን ዱር ቤቴ ያልን መቼና እንዴት በምን ሁኔታ ልንሞት እንደምንችል እያወቅን ኃብትና ገንዘብ ምናችን ነው? ለአንድነታችን እንቅፋት የሚሆንብን ምክንያት ሁሉ ከሕዝባችን ክብርና ሕልውና በታች ነው፡፡ ሆኖም ግን ሰበብ በማብዛት አንድ ላይ ለመቆም የሚቆዝም ቢኖር ከጠላቶቻችን ጋር የተሰለፈ አልያም ለግል ፍላጎቱ ያደረ ነውና ባንዳ መሆኑን በዚህ እናውቀዋለን። ስለሆነም እኛ ቀደም ሲል የአማራ ፋኖ ወሎ ቤተ-አምሓራ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አመራሮች ከአፋብኃ ምሥራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ አመራሮች ጋር በአማራ ሕዝብ የትግል መስመር፣ መዳረሻ ዓላማና ግብ፣ መዋቅራዊ የግንኙነት መስመር፣ የትብብርና የአጋርነት ማዕቀፍ ላይ ባደረግነው ተከታታይ ጥብቅ ውይይት በዝርዝር ከተወያየን በኋላ ከዚህ ቀደም የነበሩ ቅሬታዎችን በወንድማዊ ይቅርታ በመዝጋት ፍጹም መግባባት ላይ ደርሰናል፡፡ በመሆኑም ይህ መግለጫ ከተሰጠበት ከዛሬ ጥቅምት 21 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ የደጋው መብረቅ ኮር በሚል አምስት ክፍለ ጦሮችን የያዘ አደረጃጀት ያለው ግዙፍ ኃይል አደራጅተን በአፋብኃ ምሥራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ጋር በመዋሐድ በአንድ መዋቅር ለመታገል መስማማታችንን አንድነታችንን ለምትናፍቁ ወገኖቻችን ስናበሥር በታላቅ ደስታ ነው። በደጋው መብረቅ ኮር የተካተቱ ክፍለጦሮች:- 1. ፅናት ክፍለጦር 2. ደጀን ክፍለጦር (የቀድሞው የደጋው መብረቅ ክ/ጦር) 3. አንሻ ሰይድ ክፍለጦር 4. ሰንጥቅ ክፍለጦር 5. ቀኝ-አዝማች ተበጀ ክፍለጦር እንዲሁም በሻለቃ አደረጃጀት ያሉ ሀይሎችን ያካተተ ኮር መሆኑን ለመላው የትግሉ ደጋፊ እና ታጋዩ መግለፅ እንፈልጋለን። የደጋው መብረቅ ኮር አመራሮች እና ኃላፊነታቸው ከዚህ በታች በተገለጸው መሠረት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ ሰብሳቢ ……………………… አርበኛ ኃብቴ አባቡ ወታደራዊ አዛዥ ……………. አርበኛ ተመስገን አለባቸው ምክትል ወታደራዊ አዛዥ …... አርበኛ ማረጉ አስፋው ፖለቲካ ጉዳይ ኃላፊ ………… አርበኛ መ/ር ብርሃን አረጋ ዘመቻ ኃላፊ …………………. አርበኛ አስፌ አበጋዝ ም/ል ዘመቻ………………………. አርበኛ ጨለፍ ተስፋው ሎጂስቲክስ …………….…….. አርበኛ መሳፍንት ደሴ ቃል አቀባይ ………………….. አርበኛ መ/ር መኩሪያ አጋዥ ፋይናንስ ……………………… አርበኛ 10 አለቃ ሙላቱ ሰጠ ም/ል ፋይናንስ...................አርበኛ ፍቅር አራጌ የሰው ኃብት አስተዳደር …….. አርበኛ መካሽ የኋላው መረጃና ደህንነት ……………. *** ስልጠና መምሪያ ……………. አርበኛ 100 አለቃ ሲሳይ ም/ል ስልጠና መምሪያ.......አርበኛ ጋሻው ቢያርጎ ሕግ ክፍል ..............አርበኛ 100አለቃ ፈለቀ ጌትነት ህክምና መምሪያ……………………… አርበኛ ዶ/ር መላኩ የሻነው ወታደራዊ አስተዳደር …………………… አርበኛ ናቲ ውዱ ም/ል ወታደራዊ አስተዳደር...............አርበኛ ውበት ደምሴ ሚዲያ ክፍል………………………. አርበኛ እሸቱ አባተ ኦርዲናንስ ................................አርበኛ ሙሉጌታ አሻግር ሴቶች ጉዳይ ………………… ፋኒት መቅደስ ብርሃን የሕዝብ አስተዳደር …………… አርበኛ መኩሪያ ፈንቴ ወታደራዊ እቅድና ስትራቴጂ … አርበኛ አወቀ ብዙአየሁ የኮር ልዩ ዘመቻ ……………………. አርበኛ አበበ ቢራራ የኮር ም/ል ልዩ ዘመቻ..................አርበኛ ኪዳን ወዳጄ ኦዲትና ኢንስፔክሽን ………….. አርበኛ አንደበት ወረታ የኮር አማካሪ ………………….. አርበኛ አለሙ ገላው የኮር ም/ል አማካሪ.............አርበኛ እንዳለማው ፈጠነ ግዥ …………………………… አርበኛ አለበል ተካልኝ ወታደራዊ አደረጃጀት ………….. አርበኛ ሻለቃ ወንድሙ፡ ም/ል ወታደራዊ አደረጃጀት ...........አርበኛ ሻምበል ደመቀ እንየው በዚህ አጋጣሚ በተለያዩ የአማራ ቀጠናዎች የምንገኝ ፋኖዎች ለድል የምንበቃውና የወገናችንን ግፍ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በፍጥነት እንዲያከትም የምናደርገው በአንድነትና በመተባበር መታገል ስንችል ብቻ ነው፡፡ ዛሬ የታወጀው አንድነት በወሎ ቀጠና ይሁን እንጂ አገዛዙ የሀገር በጀት ይዞ ያለ እረፍት በገፍ እያሰለጠነ የሚልከውን የጠላት ኃይል የክተት ጦርነት መክቶ ድል ለማድረግ በሌሎችም የአማራ ቀጠናዎች በልዩነት የምትገኙ የፋኖ አደረጃጀቶች ወደ አንድነት እንድትመጡ ያስፈልጋልና ወንድማዊ ጥሪያችንን ለማስተላለፍ እንወዳለን፡፡ በመጨረሻም፣ በተፈጠረው አንድነት የተሰማንን ከፍተኛ ደስታ እየገለጽን በቀጣይ የሚጠብቀን ትግል ውጣ ውረድ ያለበትና ከፍተኛ መሥዋዕትነትን የሚጠይቅ በመሆኑ መላው የአማራ ልጆች ሁለንተናዊ ድጋፋችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡ ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! በአፋብኃ ምሥራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር ጥቅምት 21 ቀን 2018 ዓ.ም.
Показать все...
star reaction 2 1 358🙏 323👍 225🏆 22🕊 18🔥 15 13😡 9👌 8🤯 3
"…እግዚአብሔር ፈጽሞ ያረጋጋቸው ዘንድ ስለ አዘኑና ስለ ተከዙ ሰዎች እንማልዳለን። "…ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ወገን ስለ ሞቱ_ሰዎች እግዚአብሔር የዕረፍት ቦታ ይሰጣቸው ዘንድ እንማልዳለን። በእንተ ቅድሳት። • እንደምን አደራችሁ? • እንደምን አረፈዳችሁ? • እንደምን ዋላችሁ? • እንደምን አመሻችሁ? • መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
Показать все...
3.93 MB
star reaction 3 794🙏 503💔 129👍 95🕊 15 13🔥 10😡 7🏆 6🤯 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
"…እንዲህ በየቦታው፣ በየተራራ ሸንተረሩ የሚያልቀው የደሀ ኢትዮጵያውያን ልጆች ናቸው። አገዛዙ እንደሆነ ምንም ደንታ የለውም። ቢያንስ እንኳ ለሟች ወታደሮች ቤተሰብ እርማቸውን እንዲያወጡ መርዶ እንኳን አይነግርም። ከትግራዩ ጦርነት ጀምሮ አሁን ከዐማራ ፋኖ ጋር እየተካሄደ እስካለው ጦርነት እንደ ቅጠል የሚረግፉት ወታደሮች መጨረሻቸው ምን ይሆን…? "…ዐማራስ ምን ያድርግ? ወታደሮቹ ወንድሞቹ እንደሆኑ ያውቃል። ቢተዋቸው አይለቁት። ከቤቱ ከመንደሩ መጥተው ነው እየገደሉት ያሉት። ዳር ድንበር መጠበቅ፣ ማስከበር የነበረበት አገዛዝ ወታደሩን ሁሉ በገዛ ሀገሩ ሕዝብ ላይ አዘመተው። ይኸው እንደ ሱዳን ደርቡሽ፣ እንደ ሱማሌ አልሸባብ፣ እንደ ኤርትራው ሻአቢያ ጠላት ያልሆነ የሀገር ልጅ በአንድ ፀረ ሰላም፣ ፀረ ሀገር ግለሰብ ምክንያት እንደ ቅጠል በየቦታው ይረግፋል። ብርሃኑ ነጋ ተማሪ ይጥላል። ብርሃኑ ጁላ የወደቁትን ተማሪዎች ይቀበላል። በ3 ወር የለብለብ ሥልጠና ወታደር ነህ ተብሎ ይላካል። በመጨረሻም እንዲህ የአሞራ ቀለብ ይሆናል? ግን እስከመቼ…? አንድ እግር በርበሬ መንቀል አቅቷችሁ ለብልቦ፣ ለብልቦ አቃጥሎ ፈጃችሁ።
Показать все...
star reaction 1 782👍 297💔 186🙏 55🤔 23🕊 15👌 11🏆 8🔥 7 5😱 4
Фото недоступноПоказать в Telegram
መጥተናል ገባ ገባ በሉማ…! "…ዘወትር በየሳምንቱ በእለተ ሐሙስ በኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ የምናቀርብላችሁ ሳምንታዊ መርሀ ግብራችን አሁን ጀምሯል። የዛሬውንም ዝግጅታችንን፦ በ የዛሬው ዝግጅታችን ከዘመዴ ጋር 👉በዩቱብ /YouTube ♦https://www.youtube.com/live/PM5bE40s7pA?si=nd399JWK15cOPKFZ 👉በፌስቡክ Facebook ♦facebook.com/ethiobeteseb 👉    በቲውተር / Twitter ♦https://twitter.com/EBeteseb 👉 ቴሌግራም / Telegram ♦https://t.me/ethiobeteseb "…ሻሎም !  ሰላም !
Показать все...
🙏 279 137👍 98🔥 6🤯 6🤔 4😱 3🏆 3🕊 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
"…እነሆ፥ በአገሩ ውስጥ እረኛ አስነሣለሁ፤ እርሱም የጠፋውን አያስብም፥ የባዘነውን አይፈልግም፥ የተሰበረውን አይጠግንም፤ የዳነውንም አይቀልብም፥ ነገር ግን የሰባውን ሥጋ ይበላል፥ ሰኰናውንም ይቀለጣጥማል። መንጋውን ለሚተው ለምናምንቴ እረኛ ወዮለት! ሰይፍ በክንዱና በቀኝ ዓይኑ ላይ ይሆናል፤ ክንዱም አጥብቃ ትደርቃለች፥ ቀኝ ዓይኑም ፈጽሞ ትጨልማለች። ዘካ 11፥ 16-17 "…እንደምን አደራችሁ? "…እንደምን አረፈዳችሁ? "…እንደምን ዋላችሁ? "…እንደምን አመሻችሁ? "…መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
Показать все...
star reaction 2🙏 947 236👍 117💔 59🕊 20😡 9😱 6 4🤔 3
Фото недоступноПоказать в Telegram
መልካም… "…የእኔ የዛሬው ርእሰ አንቀጽ ያነበባችሁትን የመሰለ ነበር። ይሄ የእኔ ምልከታ ነው። አሁን ደግሞ አሰብንና ወደብን በተመለከተ  የእናንተን ዕይታና ምልከታ የምናነብበት ጊዜ ነው። ከአሁኗ ደቂቃ ጀምሮ እስከ እኩለለ ሌሊት ድረስ የእናንተን ጣፋጭም ሆነ መራራ፣ ማርም ሆነ ሬት፣ ሬት የሚል ነገር ግን በጨዋ ደንብ ተዘጋጅቶ የሚሰጥ አስተያየት ስንኮመኩም እናመሻለን። • ጀምሩ… ✍✍✍
Показать все...
star reaction 5 530👍 196🏆 38🙏 33😡 13 10🔥 7🕊 6💔 3
👆⑤✍✍✍ የተቆረጠ ሃውልት በመሃል አሩሲ ተክላ፣ ድርሰቱን ኤርትራዊው ተስፋዬ ገብረ እባብ እንዲደርሰው አድርጋ፣ እነ አቢይ አሕመድ፣ እነ አባዱላ ገመዳ ቆመው ያሠሩት ሃውልት፣ በትምህርት ካሪኩለም ውስጥ ገብቶ ዐማራ ጡትህን ቆረጠው እያሉ እያስተማሩት አሳድገው፣ ትምህርት ቤቶች በተማሪ የጉብኝት መርሀ ግብር ተዘጋጅቶላቸው አኖሌ ድረስ እንዲሄዱ ተደርገው፣ የኦሮሞ ሕጻናት ቂም በቀል ይዘው እንዲያድጉ ተደርገው ዛሬ እነዚያ ሕጻናት አድገው ነው በአሩሲ ዐማራ ሲያዩ በማረድ የተበቀሉ እንዲመስላቸው የተደረገው። እናም ዐማራ አሁን በመኖርና ባለመኖር፣ በኅልውና ጉዳይ እየደከመ፣ እየታገለ ስለሆነ አታስቸግሩት። ደግሞም ስሙ አያምርም። ደመ መራራም ነው። ዐመድ አፋሽም ነው ዐማራ። ታስታውሱ እንደሆነ ኤርትራና ኦሮሙማ ትግራይ ገብተው ቢዘርፉ፣ ቢገድሉ፣ ቢደፍሩ የተወገዘው፣ የተሰደበው፣ ሂሳብ እናወራርዳለን የተባለው ግን በቦታው ያልነበረው ዐማራው ነው። ኦሮሞ እየገረፈው ትግሬ ይዝት የነበረው በዐማራ ላይ ነበር። ጌታቸው ረዳ ትግሬን አስጨፍጭፎ ሄዶ የተለጠፈው ድንክ፣ ማይም ሲለው ከነበረው ከአቢይ አሕመድ ዘንድ ነው። እናም ዐማራ የቤት ሥራህን ዝም ብለህ ሥራ። የማቴዎስ ወንጌል ምእ 10፥ 16 ን ኑረው። መጀመሪያ የሚቀድመው ኅልውናህ ነው። ብልጼዎች ግን ይቅናችሁ። ከግድቡ ወደ ወደቡ መልካም ጉዞ ይሁንላችሁ። በፍጹም በእኔ በኩል ምንም አይነት እንቅፋት የሚሆን ቃል አላወጣባችሁም። ብቻ ራሳችሁን ችላችሁ ውረሩ፣ ስፈሩ። በጓሮ በር እየመጣችሁ አትነዝንዙን። ደርሶ ሀገር ወዳድ ሌላውን ባንዳ ለማድረግ አትድከሙ። አቋሜ ይኸው ነው። እኔንም ዐማራን ለዛሬ ተፋቱን። ከቻላችሁ በኦሮሚያ የምታርዱትን ዐማራ ራሩለት። አይ ካላችሁም እሱም እንደ ዐማራ ክልሉ ነቅቶ ራሱን ለመከላከል እስኪቆርጥ ድረስ ግረፉት። በብላሽ፣ በነፃ መታረድ እስኪያቆም ድረስ ቆንጥጡት። ሌላ ምን ይባላል። "…በተረፈ አቢይ አሕመድ ኤርትራ ገብቶ ሲፈተፍት፣ ዓረቦቹ ፊት ሄዶ ሲፈራረም ጀግና፣ ሀገር ወዳድ ተብሎ የሚያመሰግን የጎንደር ስኳድና የግንቦት ሰባት የብርሃኑ ነጋ ግርፍ ሁላ፣ አቢይ አሕመድ ኤርትራን ጋብዞ ትግሬን ሲጨፈጭፍ ጀግና ጎበዝ ሲል የነበረ ገተት ሁላ፣ ጄነራል በለው ጥርሱ የተተከለለት ዶር ዳኛቸው፣ ይሄ ነገር የሀገር ሉዓላዊነት የሚጥስ ተግባር ነው የሚሉ ኢትዮጵያውያንን በወያኔነት እየፈረጀ ከሻአቢያ ጋር በአንድ ፖፖ ካልተጸዳዳን፣ በአንድ ግልገል ሱሪ ካልተጠቀምን እያለ ሲያሸማቅቀን የኖረ መንጋ፣ ነውረኛ ሁላ፣ የኤርትራ ፍቅር፣ የሻአቢያ ውለታን ከፍለን አንጨርሰውም ሲለኝ የነበረ ቀፈታም ሁላ፣ ዛሬ ደርሶ ዐማራው ከመቼ ወዲያ ነው በብሔራዊ ጥቅም፣ በሉዓላዊነት ጉዳይ እንዲህ ወደ ኋላ ያለው?  ብሎ አጉል ልፈላሰፍ ቢል ጥፋ ከዚህ ነው የምለው። ተመልከቱ ልብም በሉ አያሌው መንበርም ሆነ ይድነቃቸው ታደለ ዐማራ ስላልሆኑ የዐማራን መፈናቀል፣ የዐማራን መሞት አይዘግቡም። ድምጽ አይሆኑም። ዐማራ ኤርትራ ገብቶ ከአቢይ ጋር ካልተዋጋ ግን ሞተን እንገኛለን ነው የሚሉት። አያሌው መንበር የሚደግፋቸው የጎንደር ፋኖ ፋፍዴኖቹ፣ እነ ደረጄም ጥይት የሚሰጣቸው ሻአቢያ ነው። አያሌው መንበር ግን ጓ ብሎ ሀገር ይያዝ የሚለው ሻአቢያ ለእነ ሀብቴ፣ ለእነ ምሬ፣ ለእነ ደሳለኝ እና ለእነ ዘመነ ጥይት ስትሰጥ ነው። እስክንድር በገሃድ አሰብን፣ ወደብን አንጠይቅም ብሎ ሻአቢያን ሲለማመጥ እስክንድር የእነሱ ስለሆነ ክንፍ የሌለው መልአክ ነው። እኔ ደጋፊው ባልሆንም ጄነራል ተፈራ ማሞ ግን አቢይ ሰሜኖቹን ሊያጠፋ ነውና ልንነቃ ይገባል ሲል አገር ይያዝልኝ ብሎ አዋራ ማስነሳት። ይሄን እርድና እዚያው በጸበልህ አባቴ። ከእነ ዘመነ እስክንድር ይሻለኛል ትላለህ። ዘመነም፣ እስክንድርም ጥይት የሚቀበሉት ግን ከሻአቢያ ነው። ምነው ከሥጋው ጦመኛ ነኝ ከመረቁ ስጡኝ አላችሁሳ። የአሰብም፣ የወደብም ጉዞ የሚቃወም ዐማራ ያለ አይመስለኝም። ግን ዐማራ እያለ ያለው መጀመሪያ ከወደቡ በፊት መጨፍጨፌን ገድቡ ነው እያለ ያለው። • ስላነበባችሁኝ በድጋሚ አመሰግናለሁ። • ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ ከራየን ወንዝ ማዶ።
Показать все...
star reaction 3 795👍 274🙏 50🕊 22😡 15🏆 12👌 10🔥 8🤔 7 3 2
👆④✍✍✍ …የዐማራ የሆኑትን ጥንታውያን ቅርሶችና ሀብቶች ሊያወድሙ ይችላሉ። ኦርቶዶክሳዊ ነው የሚባለውን የሰሜኑን ክፍል ኤርትራንና ትግራይን ጨምሮ ከዐማራ ጋር ለማውደም ጽንፈኞቹ የጴንጤና የወሀቢያ እስላሞች ይተባበራሉ። እናም ሰሜነኞቹ ከወዲሁ በሚገባ መሬት ረግጠው ካላሰቡ በቀር የሚመጣው ጊዜ ባይሸነፉ እንኳ ቀላል የሚሆንላቸው አይመስለኝም። "…ቀይ ባህርን ሲወስዱብን ማን እንደሰጣቸው፣ እንዴት እንዳጣነው የተቀመጠ ሰነድ አላገኘንም። በፓርላማ ከሆነ ብለን ፈለግን ምንም ዓይነት ሰነድ አላገኘንም። የተፈረሙ ሰነዶችን ፈለግን አንዳችም መረጃ አላገኘንም። እናም ቀይ ባሕርን እንዴት እንደወሰዱብንና እንዴት ወደባችንን እንዳጣን አናውቅም" በማለት አቢይ ትናንት የተናገረውን ስሰማ ሰውየው አቢይ ሆነ እንጂ ሌላ ሰው ቢናገረው ኑሮ ቢያሻኝ ሻምፓኝ ከፍቼ ስጨፍር አልያም ሻማ አብርቼ ስጸልይ ነበር የማድረው። ግን የተናገረው ፀረ ኢትዮጵያው፣ ፀረ ሰው፣ ጨካኙ፣ አውሬው አቢይ አሕመድ ስለሆነ አልሞቀኝ አልበረደኝም። ነገ ሙልጭ አድርጎ በፈጣጣው አላልኩም፣ አልተናገርኩም ብሎ ለመካድ ሰከንድ የማይፈጅበት የሐሰት አባት ስለተናገረው ሚዛኔ የተዛባ ነው የሚሆነው። እንጂ ንግግሩስ ሃቅ አለው። በመለስ ዜናዊ ፊርማ ነው ኤርትራን ያጣናት፣ አሰብን የወሰዱብን የሚባለውም ሳክስ ነበር ማለት ነው። በጨበጣ ሀገር ተቆርሶ ነው የተወሰደብን ማለት ነው። መለስ ዜናዊም አስር ጊዜ እየወጣ ወደብ ሸቀጥ ነው፣ ከገበያ ላይ እንደ ሽንኩርት፣ እንደ ቲማቲም የምንገዛው ሸቀጥ ነው እያለ እነ ጌታቸው ረዳ ሳይቀሩ እየወጡ ይቦተረፉብን የነበረው ሁላ ውሸት እንደሆነ፣ ወደቡ ከኢትዮጵያ የተገነጠለው በኢትዮጵያ ሀብት ታላቋ ትግራይ ስትመሰረት ያኔ ለእሷ እንዲያገለግል ታስቦ የታችኞቹ ትግሬዎች ለላይኛዎቹ ትግሬዎች በአደራ መልክ ያስቀመጡት እንደሆነ ይሰማኛል። እናም በዚህ መጠን በድፍረት አቢይ መናገሩን ተቃዋሚ አይደለሁም። "…እንግዲህ በሞቅታ ተነግሮ ሕዝብን ጮቤ አስረግጦ፣ ልክ የሶማሊያው ወደብ ተገኘ የተባለ ዕለት "እግዚአብሔር ይመስገን የወደብ ባለቤት ሆንን" በማለት ሲጨፍር ኋላ ላይ እግርህን ብላ ብለው እስከዛሬ ስለበርበራ ወደብ ትንፍሽ እንደማይሉት ሁላ አሁንም እንደዚያው ከሆነ ልናይ ኋላ ብለን ተርተንባቸው እናልፋለን። እንዲያውም የአቢይ አሕመድ የፓርላማ ግልፅ የወረራ ዲስኩር ተጠያቂነትን የሚያመጣና ጫና የሚፈጥርበት መስሎ ከታየው አጀንዳውን ለማስተንፈስ ሲል የተለያዩ አስቂኝም፣ ዘግናኝም አጀንዳዎች ተፈብርከው ሊበተኑልን ይችላሉ። ለምሳሌ ቀላሉና አጀንዳ ማስቀየሻው ነገር በኢትዮጵያ ዐማሮችን እና ኦርቶዶክሳውያንን በገፍ በግፍ መግደል፣ ማረድ ነው። ለዚህ ደግሞ በኦሮሚያ ክልል ለእርድ የተዘጋጁ ሚልዮን ዐማሮችና ኦርቶዶክሳውያን ተዘጋጅተው የሞታቸውን ቀን ይጠባበቃሉ። እናም በኦሮሚያ ኦርቶዶክሳውያን በገፍ ይታረዳሉ። ይጨፈጨፋሉ። የወሀቢይ እስላምም በአገዛዙ ድጋፍ እየታገዘ በኢትዮጵያው እስላም ላይ ይዘምታል። በዐማራ ክልል ድሮን በድሮን ሆኖ ጭፍጨፋ ይጀመራል። የለንደን ፋኖም አቢይ ፓርላማ ላይ ስሙን ያለነገር አላነሳውም እና ለንደኖች ልክ እንደ ዲሲው ግብረ ኃይል በሰርጎ ገቦች ወይ ይፈረካከሳሉ አልያም እንደ ወርቅ ነጥረው ይወጣሉ። እሱን በቅርቡ የምናየው ነው። በጎጃም እና በጎንደር መካከል ሰሜን ጎጃም የሚለው አጀንዳ ተመዝዞ ጎንደርና ጎጃም እንዲነታረክ ይደረጋል። ጫጫታ እንዳይበዛ የጎጃሙ ሸንጎ ቅባታሙ የእነ አረጋ ቡድን መንግሥታዊ ሥልጣኑን ተጠቅሞ አቢይ አሕመድ ሹም ሽር እንዲያደርግ አስገድዶ ሥልጣን ለጎንደሬዎች አሰጥቶ በመለጎም ትኩሳቱ እያበረደ እንዲቆይ ይደረጋል። የኦርቶዶክሳውያን እርድና ጭፍጨፋ ግን በሚዘገንን ሁኔታ በገፍ እንሰማ ይሆናል። እንደመካነ ሠላሙ በኦሮሚያ ለሚታረደው ኦርቶዶክሳዊ መንግሥታዊ መግለጫ እንዳትጠብቁ። ትሰሙታላችሁ። "…እናም ወንድም ዓለሜ ወደ ኋላ ተመልሼ ስነግርህ እኔ የማውቃት ኢትዮጵያ የጥንቷን ነው። ሙሉዋን ኢትዮጵያ። በባሌም ሆነ በቦሌ የሆነ ቀን በሴራ እንዲለያይ የተደረገው ወንድማማች ሕዝብ ሴረኞቹ ሲጠፉ፣ ሲከሽፉም አንድ ላይ የሚሆን ነው ብዬ በተስፋ የምጠባበቅ ሰው ነኝ። ኤርትራና ኢትዮጵያ ታረቁ የተባለ ዕለት በአስመራም በኢትዮጵያም የነበረውን የሕዝብ ደስታ ማስታወሱ እኮ በቂ ነው። ኢሳይያስ አፈወርቂ ከመሞቱ በፊት፣ በወያኔ ሴራ በግድ ሀገር እንዲሆን የፈረዱበትን ኤርትራን በይፋ ከኢትዮጵያ ጋር በዐዋጅ ቀላቅሎ ንስሀ ገብቶ ቢሞት ሁላ ነው የምመኘው። እንደዚያ ቢያደርግ ደግሞ ዓረቦቹም፣ ምዕራባውያኑም፣ የታች ሰፈር ትግሬዎችም የሚፈቅዱለት አይመስለኝም። ተዋርዶ ከሚሞት በሕይወት ሳለ የነጣጠላቸውን ሕዝቦች አንድ አድርጎ በክብር ቢያልፍ ለእሱም ንስሀ ይሆነው ነበር። ነገር ግን ያደርገዋል ተብሎም አይጠበቅም። ሥራው ያውጣው። "…ቀይ ባህር ከተመለሰ፣ ወደብም ከኖረን ግን እስከዛሬ ድረስ በ8 ዓመታት ውስጥ ከእልቂት በቀር፣ ችግኝ በመትከል ሰውን ከመቅበርም በቀር ምንም ዓይነት ሌጋሲ ስለሌለው በከፍተኛ የአእምሮ ስቃይ ውስጥ የሚገኘው አቢይ አሕመድ ከችግኙ ቀጥሎ ወደቡ ሌጋሲ ይሆነው ነበር የሚሉ መተርጉማንም አሉ። እናም እሱ ባያዝበትም እንኳ ለወደቡ ቢታገል አልነቅፈውም። ሆኖም ግን ዓባይን ተሻግሮ አዲስ አበባ መግባት የተከለከለውን ዐማራ ለወደብ፣ ለግድብ ብሎ ተዋጋልኝ ማለት ግን ነውር ነው የሚሆነው። እስከዛሬ ወራሪ፣ ጠቅላይ፣ ኢትዮጵያን በኃይል፣ በጉልበት የፈጠረ፣ ነፍጠኛ እየተባለ ሲወቀስ የኖረው ዐማራ አሁን ደግሞ ኦሮሞን ከዳር ሆኖ እንዲያይ ነው የምመክረው። የዐማራ የእስከዛሬ ድካሙ፣ ሀገር አንድ ለማድረግ የደከመው ድካም በኦሮሞና በትግሬ ዘንድ አልተወደደለትም። ጡት ቆራጭ፣ ነፍጠኛ እየተባለ ትግሬ በመሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ የተሠራ…👇④✍✍✍
Показать все...
387👍 147🔥 9🏆 8🙏 5 4🕊 4😡 4
👆③ ✍✍✍ …የሚል ታዛዥ ተገኝቶ ነው? "…መቼም የብልጽግና አገዛዝ ቡና ሽጦ ዕዳ እንደማይከፍላቸው እያወቁ እኮ ነው እነ አይኤምኤፍ የቢሊዮን ዶላር ብድሮች በላይ በላዩ ሲያሸከሙት የምናየው። ሀገሪቱን ዓይናችን እያየ እየሟሸሸች እኮ ነው። አሁን በዶላር በብድር ዕዳ እስከ አንገታችን እንድንዘፈቅ አድርገውናል። 1 የአሜሪካ ዶላር 160 ብር በባንክ እንዲዘረዘር አድርገዋል። አንድ ሊትር ነዳጅ 120 ብር እንዲሸጥ አድርገዋል። ኑሮው ከመወደዱ የተነሣ አውቶቡስ እንኳ ከተማ ውስጥ በ20 ብር ትኬት እንደሚቆረጥ እየሰማን ነው። ኩንታል ጤፍ 20ሺ፣ ደረቅ እንጀራ 30ብር፣ አንድ እንቁላል ስንት እንደገባ ባላውቅም ሁሉም ነገር የተወደደው ዶላር ተበድሮ ድሮንና ቦንብ ለሚሸምተው አቢይ አሕመድ በገፍ እየሰጡት ስለሆነ ነው። አሁን ላይ ቴሌውንም፣ ባንኩንም፣ አየር መንገዱም ተሽጦ የምንመልሰው አይደለም የዕዳው ክምር። ምንአልባትም አንድ ቀን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮጵላኖች ለሥራ ወጥተው በዚያው በረፉባቸው ሀገራት በዕዳ ተይዘው ላይመለሱ ሁላ ይችላሉ የሚሉም አሉ። እናም ይሄንን የብድር ተራራ ለመናድ የሚቻለው ውድ ማዕድናትን ለአበዳሪዎቹ አሳልፎ በመስጠት ብቻ ነው። "…ሱማሌላንድ ሀገር ስትሆን የምሥራቁ መዓድን በሱማሌላንድ በኩል ይወጣል። በዚያ ወደብም አለ። አሰብ ወደብ የሚያስፈልገው ደግሞ ለወልቃይቱ ፖታሽ፣ ለአዲ ዳውሮው ወርቅ ነው። ጅቡቲ ደግሞ ወደቡ ሩቅ ነው። ቅርቡ አሰብ ነው። እናም ከትግራይ የሚታፈሰው ወርቅ እና ከወልቃይት የሚታፈሰዉን ፖታሽ ዕዳ መክፈያ ሆኖ እየተዛቀ ከኢትዮጵያ ለማውጣት ከጦር መንደርነቱ ባሻገር ወደቡ የግድ አስፈላጊ ነው የሚሆነው። ማዕድናቱን ወዳየ ሀገራቸው በሚያወጡበት ወቅት በመሃል ላይ ምንም ዓይነት ፍተሻ፣ የየትኛውም ሀገር ኬላ መኖር የለበትም። ስለዚህ ሱማሌላንድና አሰብ ላይ ነፃ ወደብ ያስፈልጋቸዋል ማለት ነው። በዚህም ምክንያት በዕቅዳቸው መሠረት ለኢትዮጵያ በጥቂት ዓመታት ውስጥ በብድር መልክ የሚሰጥ እስከ 17 ቢልዮን ዶላር  የሚደርስ ብር መመደባቸው ነው የሚነገረው። ወደቡም ቢሆን በስም የኢትዮጵያ ሆኖ በተግባር ግን የእነሱ አድርገው መጨረሳቸውንም በለሆሳስ የሚያወሩም አሉ። ለዚህ ዓላማ መሳካት ደግሞ ከአቢይ አሕመድ የተሻለ ተመራጭ እንደማያገኙም ተረድተዋል። አሁን ላይ የአቢይ አገዛዝ ወደብ አልፈልግም ቢል እንኳን አስገድደው እና አስፈራርተውም ዓላማቸውን ከማሳካት ወደ ኋላ አይሉም የሚሉም አሉ። "…ግብፅ ምናምን ጓ ትላለች የሚባለው ብላኔ ነው። ጆካ ነው። ግብፅ የምዕራባውያኑ አጀንዳ ማስፈጸሚያ፣ ዓረቦቹን የሚቆጣጠሩበት ሪሞት ኮንትሮላቸው ናት። አሜሪካ የዓባይ ግድብ የተገደበው በራሳችን ብር ነው ስትል መልስ የሰጠ አንድም ባለሥልጣን ከኢትዮጵያ ወገን የለም። ልክ ግድቡ በኢትዮጵያ ስም በኢትዮጵያ ተገንብቶ ለእነ ግብፅ እንዲመች ተደርጎ እንደተገነባው ሁሉ አሁንም የቀይ ባሕር የአሰብ ወደብ ጉዳይም ከዚሁ አይዘልም። የህዳሴ ግድብ በተጠናቀቀ ማግስት የመብራት ዋጋ ይቀንስልኛል፣ ይረክስልኛል ብሎ ይጠብቅ የነበረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጭራሽ ምንድነው የገጠመው? አቢይ አሕመድ የመብራት ክፍያን 400% መጨመሩ ነው የተነገረው። ወደቡም ከዚህ የተለየ ይሆናል ብዬ አልጠብቅም። ለወደቡ ቋምጣ የተቀመጠች ናት የምትባለው የተባበሩት አረብ ኤምሬትስም ሌላኛዋ ውጋት ናት። ኤምሬትስ በአፍሪካ ጉዳይ በተለይ በኢትዮጵያና በሱዳን የውስጥ ጉዳይ ገብታ መፈትፈት ከጀመረች ሰነባብታለች። ለገነት መግቢያ ለነፍሷ ሳይሆን በአቢይ አሕመድ በኩል መጨረሻውን የማናውቀው በቢልዮን የሚቆጠር ዶላር እያፈሰሰችብንም ነው። የሱዳኑን ሄሚቲን እና የኢትዮጵያውን አቢይ አሕመድን ወጥራ ነው የምትረዳው። ዶላርም፣ ድሮንም፣ ጥይትም፣ ቦንብም ትለግሳለች። በገፍም ታቀርባለች። አልቡሁራን ከኢሳይያስ ጋር ነው። ሄሚቲ ከአቢይና ከኤምሬትስ ጋር "…ልክ እስራኤል የፍልስጤም ጋዛን ቀጥቅጣ ሽባ አድርጋ እንደተቆጣጠረችው ሁሉ ኢትዮጵያም ኤርትራ ሻአቢያን ቀጥቅጣ አሰብን እንድትቆጣጠር የማርያም መንገድ ሊሰጧት ይችላሉ። ኤርትራ ብትከስ የምትሄደው ወደ ተባበሩት መንግሥታት ዘንድ ነው። በተባበሩት መንግሥታት ውስጥ ደግሞ ወሳኞቹ ከአቢይ አሕመድ ጀርባ ያሉት ጎምቱዎቹ ኃያላን መንግሥታት ናቸው። እናም አቢይ በዚያ በኩል ገልማጭም፣ ተቆጬ ገሳጭም እንደማይኖርበት ከታወቀ አሰብ ለመግባት ጠዋት 2:00 ሰዓት ጉዞ ቢጀምር ምሳ ሰዓት ቀይ ባሕር ውኃው ጋር ደርሶ ዓሣ አስግሮ፣ ጠብሶ ከመብላት የሚያቆመው ኃይል ያለ አይመስለኝም። እነ ጣልያን፣ እነ ሳዑዲ አረቢያም ጓ ቢሉ እንኳ ከአማሪካው ፕሬዘዳንት ከአባ እንደልቡ ከትራንፕ ፊት የመቆም፣ የመገዳደርም አቅም ያላቸው አይመስለኝም። "…ወልቃይት። አቢይ ወልቃይትን ለትግሬዎቹም፣ ለዐማሮቹም ሳይሰጥ ልክ እንደ ድሬደዋ እና አዲስ አበባ በፌደራል መንግሥቱ ሥር አስቀምጦ ትግሬና ዐማራን ዘላለም ሊያናቁርበት ነው የሚፈልገው። አሁን ባለው ሁኔታ የአብይ ኃይል በዚህ በኩል ሰብሮ ወደ ኤርትራ ለ መግባት የሚሞክር አይመስለኝም። ምዕራባውያኑም ደግሞ በዚያ ያለውን የፖታሽ መአድን ክምችቱን አጥብቀው ይፈልጉታል። አሰብ ወደብ የሚፈለገውም ከላይ እንደተባለው ለሽሬው፣ ለአዲ ዳሮው ወርቅና ለወልቃይቱ ፖታሽ ሲባል ነው። ሰሊጥ፣ ጥጥ ምናምን የሚባለውን እርሱት። እሱን እነ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ እየሸጡት በጀት አልባዋን ወልቃይት ለሀኪም እና ለአስተማሪ፣ ለተከዜ ዘብ ደሞዝ የሚከፍሉበት ነው። አንገምት ከተባለና በሃላል ግምታችንን እንናገር ከተባለ አሁን ላይ እንደ ትናንቱ የፓርላማ አያያዙ ከሆነ አቢይ አሕመድ በአሜሪካ ስውር ድጋፍ የኦሮሚያ ሚሊሻንም ቢሆን ይዞ ኤርትራን ይወራል። በአንዷ እስራኤልእነ ጋዟም ሆኑ ሊባኖስ፣ ሶሪያ፣ ኢራንም በአሜሪካ ድጋፍ ዶግ አመድ እንደተደረጉት ኤርትራም ቢሆን በዚያው አግባብ በኤምሬትስ ድሮን፣ በምዕራባውያኑ ይሁንታ ዶግ አመድ ልትሆን ትችላለች። ሩሲያ፣ ቻይና፣ ኢራን፣ ሰሜን ኮሪያ ኤርትራን ማገዝ የሚሞክሩ አይመስለኝም። እንጃ ግን ምን እንደሚፈጠር። እናም አብይ አህመድ ወደቡንም ሆነ ባህሩን የሚይዘው ለኢትዮጵያ ሳይሆን ለቀጣሪዎቹ ነው። ልክ እንደ አባይ ግድብ ማለት ነው። አሜሪካ ግድቡ በገንዘብ ስለተሠራ እኛ ነው እንዳለችን ሁሉ ኋላም አብይ አህመድ እና ሻአቢያ ከተዋጉ በኋላ እነ አሜሪካ አሸማጋይ ሆነው ይገቡና አንተም ተው አንተም ተው ብለው ቀይ ባህርንም ወደቡንም በበላይነት ይቆጣጠሩታል። ፈረንሳይ ጅቡቲን እንደምትቆጣጠረው ማለት ነው። "…እዚህ ላይ የዐማራ ፋኖም በታሪክ አጋጣሚ ሌላ ሚዘን ማስጠበቂያ ዕድል እጁ ገብቶለታል። እንዲያ ነው እንዲህ ነው ብሎ በአደባባይ የሚነገርም ባይሆን ጥሩ አጋጣሚ እንደተፈጠረለት ግን ለመገመት አይከብድም። የትግሬ ፖለቲከኞችን መቼም ባላምንም ምዕራባውያኑ ግን ከትግሬዎቹ በተሻለ መልኩ የሚታዘዛቸው ካገኙ ከእነርሱ ጋር የሚንገላወዱበት ምክንያት የሚኖር አይመስለኝም። አቢይ አሕመድ ጦርነቱን ለማሸነፍ ከሱዳን ሃሚቲ በድሮን ኤርትራን የሚደበድብለት ከሆነ አቢይ አሕመድ 70 ኪሎሜትር ሩጦ አሰብ መግባት አያቅተውም። አቢይ አሕመድ በዚህ ሙቀት አሰብ ገብቶ የአሸናፊነት ሰርተፊኬቱን ምዕራባውያኑ ከሰጡትና እንደተባለው አሰብን ካጸደቁለት አቢይ ከአሰብ መልስ ወደ ዐማራ ክልል ተመልሶ ውጊያ ብቻውን አይጀምርም። የጥቅም ጉዳይ ነውና ፋኖን የአሸባሪነት ታፔላ ለጥፎ ከስሶ በአየርና በምድር ሊዘምቱበት ሁላ ይችላሉ። እግረ መንገዳቸውንም…👇③✍✍✍
Показать все...
446👍 147 9🤔 7🙏 6🏆 6😡 5🔥 3🤯 1👌 1🕊 1
👆②✍✍ ላይ ሆነ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጣቸው ቃለ መጠይቆች ላይ አሜሪካንን እንዳትሸጥ እንዳትለወጥ አድርጎ ቀጥቅጦ ማዋረዱን ያዩ የተመለከቱ ምዕራባውያን ደስ ይሰኛል ተብሎም አይጠበቅም። እናም ወደባችንን ያስነጠቁን አካላት አሁን ላይ ወደቡን መልሰው ባይሰጡንም እነርሱም በጉዳዩ ላይ በቀጥታ ባይገቡበትም በኢትዮጵያ በኩል ግን ከመስመራቸው እንዳፈነገጠ የሚያስቡትን ሻአቢያን ለመቅጣት ወደቡን ከሻአቢያ ተቀብለው በእጃዙር ሊያስተዳድሩት እንደፈለጉት የትናንቱን የአቢይን ፉከራና ድንፋታ ሳይ ብጠረጥር አይፈረድብኝም። እኔን የተሰማኝ ስሜት እንዲህ ያለ ነው። ያውም ዓረቦችን ብቻ ሳይሆን የሃገራችንን የስልጤና የወሃቢይ እስላሞችን ሊያበሳጭ የሚችለውን የፍልስጤሟን ጋዛን አንስቶ ምሳሌም አድርጎ እገሌ ያድነኛል ብሎ ጦርነት መግጠም ውጤቱን ኤርትራውያን ከዚያ እንዲማሩ ጠቅሶ መደስኮሩ በአሜሪካም፣ በእንግሊዝም ሆነ በእስራኤል ከፍተኛ ድጋፍ እንዳለው የሚያሳይ መስሎ ነው የታየኝ። ፍልስጤማውያን የሚያድናቸው የሚታደጋቸውም እንዳላቸው አስበው የነበረ ቢሆንም እስራኤል ኃያል ሆና በአሜሪካ ድጋፍ አዳኞቹንም በመቀጥቀጧ የሚያድናቸው አልተገኘም ነው ያለው አቢይ በትናንትናው የፓርላማ ዲስኩሩ። ለፍልስጤም ኢራን፣ ለዩክሬን ምዕራባውያን አይዞኝ ከማለት በቀር ማንም አላዳናቸውም፣ ማንም አልሞተላቸውም ብሎ ሲፎክር ሳየው ሰውየው ማን ከጀርባው እንዳለ እንድጠረጥር ነው ያደረገኝ። "…እንግዲያውማ ራሺያ ክሬሚያን በመውረሯ ምክንያት ምዕራባውያን ያን ሁሉ ማዕቀብ የጣሉባት ሩሲያን የሰው ሀገር በመውረር ከሰዋት ነው። ኢራቅ ኩዌት ስትገባ ኔቶና አሜሪካ ኢራቅን ዱቄት ያደረጓት ኢራቅን የሰው ሀገር ወርረሻል፣ ድንበርም ጥሰሻል ብለዋት ነው። ቻይና ታይዋንን ጫፏን እንዳትነካት እነ አሜሪካ የሚፋለሙት ለነፍሳቸው ብለው እንዳይደለ ይታወቃል። ነገር ግን እነርሱ ለሚፈልጉት ጉዳይ፣ ለኅልውናቸው የሚጠቅም ከሆነ ወረራ ነው የተባለን ጉዳይ ባለየ፣ ባልሰማም ያልፉታል። እስራኤል ጋዛንና ዌስት ባንክን ስትቆጣጠር የሚቆጣት፣ የሚጠይቃት የሌለው ለዚህ ይመስለኛል። ልክ እንደዚያው ኢትዮጵያም አሰብ ወደብንና ቀይ ባሕርን የእኔ ስትል እስከ አሁን የተነፈሰ የዓለም አቀፍ መንግሥታት ያልታዩት ለዚህ ይመስለኛል። እናም ቀይ ባሕርን ኢትዮጵያ እንድትይዘው፣ አሰብንም እንድትቆጣጠረው ተፈልጓል ብለን ብንገምት ኃጢአት አይሆንብንም። ነገርየው ባይጠራም የማርያም መንገድ ግን ሳያገኝ አይቀርም ባይ ነኝ። "…ልክ እንደ ኤርትራ ሁሉ ታይዋንም እኮ የቻይና ግዛት ነበረች። በሕዝብ ብዛት ቻይና የምትበልጣት ታይዋንን እንደ ራሷ ግዛት ትመለከታታለች እንጂ መሪ ቀይራ፣ ባንዲራ አውርዳ ሀገር ሆና ከመቀጠል አላስቆመቻትም። እንዲያ ብታደርግ እነ አሜሪካ ዝም አይሉም። አሜሪካ ታይዋን የቻይና ግዛት ከምትሆን ካሊፎርኒያ ወደ ቻይና ብትጠቃለል የሚቀላት ሁላ ነው የሚመስለኝ። በሕዝብ ብዛትም ማሸነፍ፣ መጠቅለል አይቻልም። የኢትዮጵያ ሕዝብ በየዓመቱ 3 ሚልዮን ሕዝብ ጨምሮ ያድራል። ይሄ ማለት አንድ ኤርትራ ሕዝብ በየዓመቱ በኢትዮጵያ ይወለዳል ብሎ መፎከርም፣ 5 ሚልዮን ትግሬን በ100 ሚልዮን ኢትዮጵያዊ መዋጥ፣ ባህሩን አድርቆ ዓሳውን እንደ ማጥፋት ያለ ነው ብሎ የኢሳቱ መሳይ መኮንን እንዳወጀው የዘር ማጥፋት አቢይ አሕመድም የዘር ማጥፋት ሊፈጸምብን ነው ብለው ኤርትራውያኑ የዲፕሎማሲ ብልጫ ወስደው ድል እንዲቀዳጁ፣ ኢትዮጵያንም በማይም ንግግር እንድትዋረድ ከማድረግ የዘለለ ምንም ለውጥ አያመጣም። ብቸኛው የብልጽግና አሰብ መግቢያ፣ ቀይ ባሕር ላይ መውጫ መንገዱ አንድና አንድ ብቻ ነው። ድሮ በልጅነታችን የሰፈር ጉልቤ ጎረምሶች የሆነ የሌላ ሰፈር ጎረምሳ መቀጥቀጥ አምሯቸው ነገር ግን በቀጥታ ሄደው ከመጣላት እኛ ደቃቃ ጩጬዎቹን ልከው እንድንተነኩሰው አድርገው ሲያበቁ ምስኪኑ እኛን ሊቆነጥጥና ሊኮረክም ሲሞክር እነርሱ ከኋላ መጥተው አፈር ደቼ እንደሚያበሉት አይነት ነገር ከሌለ በቀር እንዲሁ የሚቻል አይመስለኝም። ሶሪያን፣ ኢራንን፣ ሊባኖስን፣ የመንንና ጋዛን እንድትመታ፣ ራሷን እንድትከላከል እንደተፈቀደላት እንደ እስራኤል እሰይ ደግ አደረገች የሚል ኃይል ከኋላ ከሌለ በቀር እንዲሁ ግርር ተብሎ በድንገቴ ጫጫታ አሰብም፣ ወደብም የሚሞከር አይመስለኝም። ከሆነ ግን ይቅናችሁ። "…የአፍሪካ ቀንድ በቀይ ባሕር በኤደን ባሕረ ሰላጤ ላይ ኃያላኑ ቦታ ያስፈልጋቸዋል። ልክ ፈረንሳይ ጅቡቲን ይዛ ቀንዱን እንደተቆጣጠረችው ሌሎቹም ቦታ ይፈልጋሉ። ከላይ ከሱዳን ጀምሮ ኤርትራ፣ ጅቡቲ፣ ሱማሌላንድና ሱማሌም ሁላቸውም ተሰፍሮባቸዋል። የጦር ሰፈር የሌለውን ጠይቁ። የለም ሁሉም የጦር ሰፈር ገንብተዋል። ሩሲያ፣ አሜሪካ፣ ቻይናም፣ ቱርክም፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬት ሳትቀር ሰፍረዋል። ቱርክማ ሱማሌ ባህሩን አስተዳድሪልኝ ሁላ ብላ እንደሰጠቻት ነው የሚነገረው። ግብፅም እንዲሁ አፍንጫችን ስር ናት። አካባቢው የምድራችን ወሳኝ አካባቢ ስለሆነ ሁላቸውም ይፈልጉታል። ከአካባቢው እንድንርቅ የተደረግነው እኛ ብቻ ነን። በቅርቡም ሱማሌ ላንድም በእነ አሜሪካ ጭምር የሀገርነት ዕውቅና ተሰጥቷት ሀገር መሆኗ የሚቀር አይመስልም። ይሄ የሚሆነውም በምክንያት ነው። አሁን ባለው ሁኔታ ግን  አሜሪካንን ጨምሮ ኃያላኑ የዓለም መንግሥታት የካናዳና የእንግሊዝ መንግሥታት በጋራ በመሆን በመላው ኢትየጵያ ያስጠኑት የውድ ማዕድናት መገኛ ቦታዎች በስፋት እንዳሉ ይነገራል። እነዚህን የማዕድናት መገኛ ቦታዎችን ደግሞ እንዴት መቆጣጠር እንዳለባቸውና  እንዴት መጠቀም እንዳለባቸውም አብረው አጥንተው የጨረሱት ጉዳይ እንደሆነም ይነገራል። በዚህም ምክንያት ኢትዮጵያ የግድ ሳታስፈልጋቸው አልቀረችም የሚሉ መተርጉማንም አሉ። "…ኢትዮጵያ ወደፊት ምዕራባውያኑና ምሥራቃውያኑ አበዳሪ መንግሥታት የሚራኮቱባትም ትመስላለች። የተበደረችውን ደግሞ ቡና ሽጣ መክፈል ስለማትችል በምትኩ ማዕድናቶቿን አውጥተው በመውሰድ ብድራቸውን ሊያጣጡ ይችላሉ። በዚህም መሠረት ለኢትዮጵያ መንግሥት ከወረቀት እኩል ዋጋ ያለውን ዶላር አትመው በመስጠት፣ በማበደርም እነርሱ በምትኩ መዓድኖቿን ዝቀው በዚያ ሊያጣጡ እንደሚችሉም ነው በዘርፉ አጥንተን ወረቀት አለን የሚሉ ወገኖች የሚያሳስቡት። ይሄ አይነቱ አሠራር ደግሞ በእነርሱ ዘንድ የተለመደ ነው። እንኳን ምዕራባውያኑ ይቅርና እነ ቻይናም የሚያደርጉት እንደዚሁ ሆኗል። ብር ያበድራሉ፣ ከዚያ ከአንተ ማዕድናቶችህን አውጥተው በመውሰድ ዕዳህን ክፈል ትባላለህ። በኢትዮጵያም እየሆነ ያለው ይሄው ነው። ያልተማረ፣ ነገን የማያስብ አገዛዝ ትምህርትን እና ዐዋቂን በመግደል ሀገር በደናቁርትና በማይማን እንድትሞላ በቲክቶከርም አጥለቅልቀው የተማረ እና የሚያንሰላስል ዜጋን እያጠፉላቸው፣ ሀኪሞች እንኳ በቅርብ ወደምተገኘው ኡጋንዳ በገፍ እየፈለሱ ሀገር እያጠፋላቸው ስለሆነ ደስተኞች ናቸው። እንዲህያለ ተላላኪ፣ በግልጽ ለአሜሪካ ፈርሜ ለአሜሪካ መዋጋት እፈልጋለሁ የሚል ግለሰብ መሪ አድርገው በኢትዮጵያ መንበረ ሥልጣኑን እንዲቆጣጠር ስላደረጉ ራሳቸውን እንደ እድለኛም ነው የሚቆጥሩት። ሚልዮን ትግሬ የሞተበት፣ ሚልዮን ዐማራ ኦሮሞ የሞተበትን ጦርነት የሚመራ ጨካኝ ቢሆንም እነሱን እስከጠቀማቸው ድረስ ገልማጭ የለበትም። የቡርኪነፋሶው ትራወሬ አልታዘዝ ስላለ እንዴት እየዘመቱበት እንዳለ የሚያይ ሰው አራጁን አቢይ የሚንከባከቡት ጴንጤ ስለሆነ ብቻ ነው ብሎ መደምደም ስህተት ነው የሚሆነው። ሲልኩት ወዴት፣ ሲጠሩት አቤት…👇②✍✍✍
Показать все...
520👍 160🏆 12 6😡 6🙏 4🕊 4🤯 3🤔 2
"ርእሰ አንቀጽ" "…የዛሬ ሁለት ዓመት አካባቢ አቅም ስላነሰን ኤርትራ ሆይ አግዢን፣ ድረሺልን፣ ለነፍስ እንሆንሻለን ብለው ለምነው፣ አስለምነው፣ ጋብዘው ትግሬን እንድትወጋላቸው፣ እንድታወድምላቸው፣ ኢትዮጵያን እንድትዘርፍላቸው ሕጋዊ ፈቃድ ሰጥተው ጋብዘው አምጥተው ትግሬን አስቀጠቀጡት። በኦሮሙማው አገዛዝ በክብር ተጋብዘው ትግራይ የገቡት ሻአቢያዎችም ከትግራይ ፋብሪካ ነቅለው፣ ተሽከርካሪ፣ ቅርሳ ቅርስ፣ የሆስፒታል የሕክምና መሳሪያ፣ በኢትዮጵያ ስም ተገዝቶ ከሰሜን ዕዝ ጋር በትግራይ ተከማችቶ የነበረ የጦር መሳሪያ ሁላ ዘርፈው እንዲወስዱ ያመቻቹ አካላትበዚያውም እግረ መንገዳቸውን የመለስ ዜናዊ ኔትወርክ የሚባሉትንና በመለስ ዜናዊው የወያኔ ኢህአዴግ አገዛዝ ዘመን ባለሥልጣን የነበሩና በወቅቱ የሻአቢያን አገዛዝ በዓለም መድረክ እንዲገለል፣ ማእቀብ እንዲጣልበት አስደርገው ያደቀቁት ናቸው ከሚባሉት መካከል እንደ አቶ ስዩም መስፍን አይነቶቹን፣ ዓባይ ፀሐዬና ዓባይ ነፍሶ አቶ አስመላሽ ዓይነ ስውሩን ከቤታቸው አውጥተው ግንባር ግንባራቸውን ብለው ገደል ውስጥ ከትተው ጣፋጭ በቀል እንዲበቀሉ ለኤርትራውያን የፈቀደው የአቢይ አሕመዱ አገዛዝ ፣ከዚህም በላይ ደግሞ ከትግራይ ውጪም ቢሆን ትግሬን የሚያውቀው ራሱ ትግሬ ነው በሚል ፍልስፍና   የኢትዮጵያን ትግሬ በተገኘበት በአዲስ አበባ ነሽ በደቡብ በኦሮሚያ፣ በጋምቤላ፣ በቤኒሻንጉል በዐማራ ክልል ሳይቀር ቤት ለቤት እየሄዱ በወያኔ ሰበብ ትግሬ የተባለን በሙሉ ወደ ዘብጥያ በማውረድ፣ በእጃቸው የሚገኝን ሀብት በሙሉ ወርቅ ነሽ ብር ዝርፍ ሙልጭ ግፍፍ በማድረግ በጋራ ሲያሰቃዩአቸው የከረሙ ሁሉ ዛሬ ደርሰው በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግርር ብለው በመምጣት እንደ እስፔስ 1999 ኗ አክተር ማያ ተለውጠው፣ ተቀይረው "ዘመዴ በኤርትራ በአሰብ ወደብ በቀይ ባህር ጉዳይ ምን ትላለህ?" በማለት ሲቸክኩብኝ አያለሁ። ችኮ ሁላ። "…የእኔማ አቋም ግልጽ ነው። አይሸራረፍ፣ አይቆራረስ፣ እንደ ጠላ ቂጣ አየገለባበጥ፣ እንደ እስስት አይቀያየር፣ እንደ ዋሾ፣ እንደ ቀጣፊ አይወሸክት፣ እንደ ዓሣ፣ እንደ ተልባ አይሙለጨለጭ የታወቀ እኮ ነው። ዘመን አይቀይረው፣ ፊት አይቶ፣ ጌዜ ተመልክቶ አይንሸራተት የታወቀ ነው አቋሜ። የእኔ አቋም ሴተኛ አዳሪ አይደለም። ለከፈለው ሁሉ ጭኑን ገልጦ የሚተኛ አቋም የለኝም። መንገደኛ ሁሉ የሚጫወትበት አቋም የለኝ። አለቃ፣ ቀጣሪ፣ ከፋይ የለኝም። ተቆጭ፣ ገልማጭ፣ አፍጣጭም የለኝም። አቋሜ ግልጽ ነው። የእኔ አቋም እንደ ጌታቸው ረዳ፣ እንደ ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ የተልባ ስፍር አቋም አይደለም። ጠዋት ሌላ ማታ ሌላ አቋም የለኝም። ጠዋት ተቆጥቼ ተራግሜም ማታ አልመርቅም። እናም በኤርትራም ሆነ በኢትዮጵያ ጉዳይ፣ በቀይ ባሕርም ሆነ በአሰብ፣ ያውም ምፅዋ ጉዳይ አቋሜ ግልፅ ነው። አንድና አንድ ነው። "…እኔ ዘመዴ 1966 ዓም አብዮቱ ሲፈነዳ አብሬ በፍንዳታው የተወለድኩ የአብዮቱ ዘመን ትውልድ ነኝ። ኢትዮጵያ ወይም ሞት፣ ኢትዮጵያ ትቅደም፣ አቆርቋዧ ይውደም የሚል መፈክር ስስማ ያደግኩ፣ የኢትዮጵያን ሙሉ ካርታ ስመለከት ያደግኩ፣ ገንጣይ አስገንጣይ ወንበዴ፣ የዓረብ ፔትሮ ዶላር ያሰከራቸው የወያኔንና የሻአቢያን ክፋት፣ ከፋፋይነት ስጋት ያደግኩ፣ በትምህርት ቤት ቆይታዬ ስለ እናት ሀገር፣ ስለ አንድነት ግጥም ጽፌ፣ እየተወዳደርኩ ስሸለም የኖርኩ፣ ለኢትዮጵያ ራዲዮ የልጆች ክፍለ ጊዜ ስለ እናት ሀገር ኢትዮጵያ ግጥም ጽፌ ልኬ ስሜ ተጠርቶ ግጥቤ በራዲዮ ተነብቦልኝ ስቦርቅ ያደግኩ፣ በአረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ሰንደቅ ዓላማ ፍቅር ተልክፌ ያደግኩ የዚያ ዘመን ልጅ ነኝ። ዐማራ ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ ጉራጌ የሚባል የዘር ግሳንግስ ሳናውቅ ሰውን በሰውነቱ፣ በኢትዮጵያዊነቱ ብቻ ዐውቀን እንድናድግ የተደረግን የዚያ ዘመን ልጅ ነኝ። እናም እኔ የማውቃት ኢትዮጵያ፣ በአእምሮዬ ውስጥ ታትማ የቀረችው ኢትዮጵያ ያቺ እነ መለስ ዜናዊ፣ እነ ስብሀት ነጋ፣ እነ ደብረ ጽዮን፣ እነ ስዩም መስፍን፣ እነ ስዬ አብርሃ፣ እነ ጻድቃን ገብረ ትንሳኤ፣ እነ ጄነራል ታደሰ ወረደ፣ እነ ሞንጆሪኖ፣ እነ ዓባይ ፀሐዬ የታችኞቹ ትግሬዎች ከላይኛዎቹ ትግሬዎች ጋር ተጠቃቅሰው አንገቷን በሰይፍ ያልቆረጧትን ሙሉዋን፣ የምታምረዋን ኢትዮጵያን ነው የማውቃት። የባህር በርም፣ የባህር ኃይልም፣ ከአንድም 2 ወደቦች የነበሯት ኢትዮጵያን ነው የማውቃት። ያቺ የእኔና የመሰሎቼ ኢትዮጵያ እስከዛሬ ድረስ አልሞተችም። በየትኛውም መልእክቴ ላይ የተቆረጠች፣ ኤርትራ የሌለችበት የኢትዮጵያ ካርታን አጋርቼ አላውቅም። ያውም እየተሰደብኩ። እየተወቀስኩ። እናም እነ ድንገቴ ሆይ ተረጋጉ። "…በተለይ የትናንቱን የአቢይ አሕመድን የፓርላማ ንግግር ሳይ፣ ስመለከት የኤርትራ መወረር፣ የሻአቢያ መውደቅ አይቀሬ መሆኑን ሳይሆን መምሰሉን ነው የታዘብኩት። አቢይ አሕመድ ኤርትራን ለመውረር አረንጓዴ መብራት እንደበራለት፣ ፈቃድም እንደተሰጠው ያረጋገጥኩበት የመሰለኝ ቀን ሆኖ ነው ያየሁት። እንደ ጋዛና እንደ ዩክሬን ትቀጠቀጣታለህ፣ የሚያግዝህ፣ የሚደርስልህ የለም እያለ በፍልስጤማውያን እና በዩክሬናውያን ላይ ሙድ ሲይዝ ሳየው ድፍረቱ ከየት እንደሚመጣ ለመገመት ብዙም አያስቸግርም። ሰሞኑን አንድ ዶክመንተሪ እያየሁ ነበር። ዶክመንተሪውን የሠሩት ነጮች ናቸው። በሀገረ እስራኤል ምስረታ ወቅት የአፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት በተባበሩት መንግሥታት ጉባኤ የድምፅ መሰጠት ወቅት እስራኤል ሀገር ትሁን፣ አትሁን ለሚለው "ድምፀ ተአቅቦ" በማድረጋቸው ምክንያት እስራኤል ቂም ይዛ፣ እነ እንግሊዝም፣ እነ አሜሪካም ይሄ ዘውዳዊ ሥርዓት መገርሰስ አለበት፣ ኢትዮጵያም ከውኃው መራቅ አለባት፣ አዲስ ሀገር ኤርትራ መፈጠር አለባት በማለት ሻአቢያን አደራጅተው፣ ደርግን ፈጥረው፣ ረድተውም፣ ንጉሡን አዋርደው፣ አውርደውም ሥርዓቱንም አፍርሰው፣ ሀገሪቱንም በጦርነት አድቅቀው፣ ልሂቃኖቿንም የተማረውን ክፍል በጅምላ አስረሽነው፣ አስጨፍጭፈው ኢትዮጵያን ከተፈጥሮአዊው የባህር በሯ ቅፍፍ አድረገው አራቋት ሲሉ እያየሁ እንደ አዲስ እየበገንኩ ነበር። በሌላም ቪድዮ እስራኤል ኤርትራ ነፃ ብትወጣም በአረቦቹ ድጋፍ ስለሆነ ነፃ የምትወጣው አረቦቹ ደግሞ ኤርትራን ከተቆጣጠሩ ለእኔ ህልውና አደጋ ይኖረዋል በማለት ኋላ ላይ ደርግን መርዳት ብትጀምርም የአረቦቹ የነዳጅ ብር በልጦ፣ እነርሱ አሸንፈው ባህሩንም፣ ኤርትራንም አሳጡን የሚል ነገርም አይቻለሁ። ሻአቢያ አይደለም ከቀይ ባሕር ያራቀን፣ ወያኔም አይደለም። እኛን የቀሙን፣ ያራቁን፣ ዓረቦቹ እና ኃያላኖቹ ምዕራባውያን ናቸው። አለቀ። ምንም ማለባበስ አያስፈልገውም። "…የየትናንቱም የፓርላማ ውሎ ሳይ ደግሞ አኬሩ ተገለበጠ እንዴ አስብሎኛል። ዓረቦቹ በእስራኤል ተቀጥቅጠው ልክ ስለገቡ፣ ስለገበሩላትም አሁን በኤርትራ ላይ አረቦቹ የማዘዝ ሥልጣን ስለሌላቸው በአቢይ አህመድ በኩል ቀይ ባሕርን በኢትዮጵያ ስም ሊቆጣጠሩ ፈልገው ወስነው ይሆን እንዴም እያልኩ ብቻዬን ሳስብ ነው ያመሸሁት። ምዕራባውያኑም የኤርትራን አገዛዝ አንደ ማስቲካ አኝከው፣ እንደ ሸንኮራም መጥጠው የተፏት መስሎም ነው የተሰማኝ። በተለይ የኢሳይያስ አፈወርቂ የሻአቢያው መንግሥት ባለፈው ጊዜያት ከሩሲያ፣ ከኢራንና ከቻይናም ጋር በመሰለፍ በተለይ ቻይና በሄደ ጊዜ ለአሜሪካ ያልተደረገ አቀበባበል ተደርጎለት ያሳዩት ክብርና በፊታቸው ያገኘው ሞገስ ለምዕራባውያኑ ምቾት ይሰጣል ተብሎም አይታሰብም። በተለይ ኢሳይያስ አፈወርቂ ሩሲያ ሞስኮ በሄደ ጊዜ በጉባኤውም…👇①✍✍✍
Показать все...
593👍 161🙏 39🤯 9🏆 7😡 6 4🕊 4🔥 3