ch
Feedback
Tikvah-University

Tikvah-University

前往频道在 Telegram
2025 年数字统计snowflakes fon
card fon
352 889
订阅者
-2224 小时
+1617
+1 84730
帖子存档
照片不可用在 Telegram 中显示
📢 ሰልጥነው ይቀጠሩ! የሥራ ዘርፎች፦ ✔️ Customer Service ✔️ Call Center Agent ✔️ Sales and Marketing ✔️ Social Media Management 2ኛ ዙር ምዝገባ ተጀምሯል! 🔔 የአንድ ወር ስልጠና ወስደው የሥራ ባለቤት ይሁኑ! ውስን ቦታ ነው ያለን! ተከታዩን ሊንክ በመጠቀም ይመዝገቡ👇 https://forms.gle/zSmdnuLY6mbv72H46 ☎️ ይደውሉ 👉 0977448467 Geez and Pan African Education and Skills
显示全部...
28👍 3
照片不可用在 Telegram 中显示
ተራዝሞ የነበረው ጋምቤላ ፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ከታህሳስ 12-15/2018 ዓ.ም መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። ለበለጠ መረጃ የጋምቤላ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር 0911590938 በመደወል መጠየቅ ትችላላችሁ። ከከተማው ወደ ዩኒቨርሲቲው የምትሄዱበትን ትራንስፖርት ለማመቻቸት እንዲረዳ ጋምቤላ የምትደርሱበትን ቀን እና ሰዓት አስቀድማችሁ በተጠቀሰው ስልክ ቁጥር እንድታሳውቁ ሚኒስቴሩ ጠይቋል። @tikvahuniversity
显示全部...
75👎 10👍 5😱 3😢 2
照片不可用在 Telegram 中显示
#MoE የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የ2018 ዓ.ም የመረጃ አሰባሰብ (HEMIS) ያለበት ሁኔታ እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሪፎርም ሥራዎችን የተመለከተ የምክክር መድረክ በትምህርት ሚኒስቴር ተዘጋጅቷል። መድረኩ ታህሳስ 14 እና 15/2018 ዓ.ም ይካሔዳል። በዚህም ስማችሁ ከላይ በምስሉ የተዘረዘሩ ተቋማት፣ የተቋም ባለቤት/የበላይ አመራር እና ከተገለፀው ሥራ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው አንድ ባለሙያ የተቋሙን የተሟላ መረጃና ለሥራ የሚሆን ላፕቶፕ በመያዝ ታህሳስ 14/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 በትምህርት ሚኒስቴር ትንሹ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንድትገኙ ጥሪ ተላልፏል። @tikvahuniversity
显示全部...
57👍 6🙏 1
照片不可用在 Telegram 中显示
በቀጣይ ራስ ገዝ ሆነው የሚቋቋሙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ለሚያደርጉት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ግብዓት የሚሆን የሽግግር ረቂቅ መመሪያ ላይ ምክክር ተደረገ። በመጪው ዓመት ራስ ገዝ ለመሆን እየሠሩ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች፥ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተጀመረው ራስ ገዝ የመሆን ሂደት የተገኙ ተሞክሮዎች እና ፈተናዎችን በመለየት በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) አሳስበዋል። በመድረኩ ለመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የራስ ገዝነት ሽግግር የተዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ ውይይት ተደርጎበታል። ረቂቅ ሰነዱ ለራስ ገዝነት ሽግግር የሚያበቁ መስፈርቶችና ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች የተካተቱበት ሲሆን፤ ዩኒቨርሲቲዎች በዚህ ረቂቅ መመሪያ እየተመዘኑ ሽግግር የሚያደርጉ መሆኑ ተገልጿል። በመድረኩ በቀጣይ ራስ ገዝ በመሆን ለሚቋቋሙ ዩኒቨርሲቲዎች ተሞክሮ እንዲሆን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የራስ ገዝነት ሽግግርን የተመለከተ የዳሰሳ ጥናት ቀርቦ ወይይት ተደርጎበታል። @tikvahuniversity
显示全部...
58👎 18👍 2👏 2🥰 1
照片不可用在 Telegram 中显示
#ETA ሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ2018 ዓ.ም የተመዘገቡ አዲስ ተማሪዎቻቸውን ዝርዝር መረጃ እንዲልኩ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ጠይቋል። ተቋማቱ ፈቃድ በተሰጣቸው የትምህርት መስኮች፣ የትምህርት ደረጃ፣ መርሐግብር እና ካምፓስ በ2018 ዓ.ም የመዘገቧቸውን አዲስ ተማሪዎች ብቻ ከዚህ በፊት በባለሥልጣኑ በተላከው ቅጽ መሰረት ዝርዝር መረጃውን እስከ ታህሳስ 25/2018 ዓ.ም በሶፍት እና በሃርድ ኮፒዎች እንዲልኩ ባለሥልጣን መስሪያቤቱ አሳስቧል። @tikvahuniversity
显示全部...
24
照片不可用在 Telegram 中显示
📢 ሰልጥነው ይቀጠሩ! የሥራ ዘርፎች፦ ✔️ Customer Service ✔️ Call Center Agent ✔️ Sales and Marketing ✔️ Social Media Management 2ኛ ዙር ምዝገባ ተጀምሯል! 🔔 የአንድ ወር ስልጠና ወስደው የሥራ ባለቤት ይሁኑ! ውስን ቦታ ነው ያለን! ተከታዩን ሊንክ በመጠቀም ይመዝገቡ👇 https://forms.gle/zSmdnuLY6mbv72H46 ☎️ ይደውሉ 👉 0977448467 Geez and Pan African Education and Skills
显示全部...
19🙏 2
照片不可用在 Telegram 中显示
#ማስታወሻ በ2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ትምህርታችሁን በመከታተል ላይ የምትገኙ ተማሪዎች የፋይዳ መታወቂያ ማውጣት ይጠበቅባችኋል። የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ ያላደረጋችሁ በከተማዋ የምትገኙ የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ቅዳሜ እና እሑድ በሁሉም የምዝገባ ጣቢያዎች በመገኘት ምዝገባ በማድረግ መታወቂያውን መውሰድ ትችላላችሁ። @tikvahuniversity
显示全部...
👎 55 46👍 2😱 2👏 1
照片不可用在 Telegram 中显示
#ጥቆማ #HawassaUniversity የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዳዬ ካምፓስ ፍላጎትና ብቃት ያላቸው መመህራንን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል። ➤ የሥራ መደብ፦ መምህራን ➤ ተፈላጊ ባለሙያዎች ብዛት፦ 04 ➤ ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፦ ሁለተኛ ዲግሪ ➤ የሥራ ልምድ፦ ዜሮ ዓመት እና በላይ ➤ የሥራ ቦታ፦ ዳዬ ከተማ (ከሃዋሳ ከተማ 130 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ) የመመዝገቢያ ቀናት፦ ለሥራ መደቡ በትምህርት ሚኒስቴር የተቀመጠውን መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 (ሰባት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በዋናው ግቢ የብቃትና ሰው ኃይል አስተዳደር ሥራ አስፈፃሚ ቢሮ እና በዳዬ ካምፓስ የብቃትና ሰው ኃይል አስተዳደር ሥራ አስፈፃሚ ቢሮ 2ኛ ፎቅ በአካል በመገኘት ወይም በተወካይ አማካይነት መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል። @tikvahuniversity
显示全部...
39
照片不可用在 Telegram 中显示
#ጥቆማ 👨‍🏫👩‍🏫 ለ2018 ፍሬሽማን ተማሪዎች በሙሉ! 📌 ለ Final Exam ዝግጅት በ A+ Tutorial Class❗️ ለምን A+ Tutorial ን ምርጫዎ ያደርጋሉ❓ 📝 በፍሬሽማን ትምህርቶች ላይ እያንዳንዱን ምዕራፍ በሚገባ የሚያብራሩ፣ ቁልፍ ሀሳቦችን በቀላሉ ለመያዝ የሚያግዙ፣ ለመረዳት ግልፅ የሆኑና ሞጁሉን በፍጥነት ለመረዳት የሚያግዙ በአማርኛ የተብራሩ ቲቶርያሎችን ያገኛሉ፡፡ ➤ በእያንዳንዱ ኮርስ ከ300 በላይ ጥያቄዎችን ከነማብራሪያቸው ያገኛሉ፣ ➤ በእያንዳንዱ ቲቶርያል Quiz ይወሰወዳሉ፣ ➤ ያለፉ ዓመታት Mid እና Final Exam ያገኛሉ። ለመመዝገብ 👉🏼 @Aplusstutorialbot ለማንኛውም ጥያቄ 👉🏼 @ContactAplusbot የቴሌግራም ቻናላችን 👉🏼 @Aplustutorialofficial ©A+ Tutorial Class
显示全部...
30👍 5
照片不可用在 Telegram 中显示
Animation and Visual Effect ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን! 👉 Blender ሶፍትዌርን በመጠቀም 3D አኒሜሽን መስራትን፣ After Effect በመጠቀም 2D Animation መስራትን እና Cinema 4Dን በአንድ ላይ አካቶ የሚሰጥ 👉 በተለያዩ መድረኮች ላይ ራስዎትን የበለጠ የሚያስተዋውቁበት 👉 ልምድ ባላቸው የአኒሜሽን ባለሙያዎች የሚሰጥ ስልጠና ☎️ 0906777799 / 0906777755 አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ የበለጠ ይጠብቁ ... 💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥 Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
显示全部...
25🥰 2😱 1
照片不可用在 Telegram 中显示
#ጥቆማ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም በኅብረተሰብ ጤና ትምህርት የፒኤችዲ ፕሮግራም (PhD in Public Health) ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡ የምዝገባ ጊዜ፦ ከታህሳስ 09-25/2018 ዓ.ም የፈተና/Synopsis ማቅረቢያ ቀናት፦ ጥር 07 እና 08/2018 ዓ.ም ለመመዝገብ ተከታዩን ሊንክ ይጠቀሙ 👇 https://portal.sphmmc.edu.et/Web/Announcement (ዝርዝር መስፈርቶችን ለማግኘት የኮሌጁን ድረ-ገፅ https://sphmmc.edu.et/ ይጎብኙ፡፡) @tikvahuniversity
显示全部...
67👍 3😱 1
照片不可用在 Telegram 中显示
#ጥቆማ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም በኅብረተሰብ ጤና ትምህርት የፒኤችዲ ፕሮግራም (PhD in Public Health) ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡ የምዝገባ ጊዜ፦ ከታህሳስ 09-25/2018 ዓ.ም የፈተና/Synopsis ማቅረቢያ ቀናት፦ ጥር 07 እና 08/2018 ዓ.ም ለመመዝገብ ተከታዩን ሊንክ ይጠቀሙ 👇 https://portal.sphmmc.edu.et/Web/Announcement (ዝርዝር መስፈርቶችን ለማግኘት የኮሌጁን ድረ-ገፅ https://sphmmc.edu.et/ ይጎብኙ፡፡) @tikvahuniversity
显示全部...
15🙏 2
照片不可用在 Telegram 中显示
የምስራች 🎊 ከዛሬ ጀምሮ ለየት ያለ የጥሪ ማሳመሪያ ሙዚቃ መጋበዝ ይችላሉ! አገልግሎቱን ለማግኘት ወደ *722# እንደውል! #SafaricomEthiopia #MPESASafaricom #furtheraheadtogether
显示全部...
30👎 3
#ExitExamUpdates በጥር ወር 2018 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የሚወስዱ እጩ ተመራቂዎች ምዝገባ ከታህሳስ 06/2018 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ እንደሚገኝ ይታወቃል። ፈተናውን ለመጀመሪያ ጊዜ የምትወስዱ እጩ ተመራቂዎች ምዝገባችሁን በተቋም ደረጃ በተጠቀሱት ቀናት አድርጋችሁ መረጃችሁ በምትማሩበት ከፍተኛ ትምህርት ተቋም አማካኝነት ለትምህርት ሚኒስቴር የሚላክ ይሆናል፡፡ ⏩ የክፍያ ጉዳይ፦ ቴሌብር በመጠቀም Payment የሚለውን በመጫን ከዛም Education fee የሚውን በመንካት ከሚመጡ ዝርዝሮች "Educational Assessment and Examinations Service" የሚለውን በመጫን የፈተና አስተዳደር ክፍያ 750 ብር መፈፀም ይጠበቅባችኋል፡፡ (ምስል 2) ⏩ የመውጫ ፈተናውን በድጋሜ የምወስዱ አመልካቾች ምዝገባ የምታደርጉት በራሳችሁ ነው 👉🏽 https://exam.ethernet.edu.et ⏩ የመፈተኛ Password እና የመግቢያ ትኬት የፈተና ጊዜው ሲደርስ የሚሰጣችሁ ይሆናል፡፡ ⏩ Username የረሳችሁ forgot username በመጠቀም ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ ⏩ ከዚህ ቀደም በተለያየ ሁኔታ ከአንድ ጊዜ በላይ ከተመዘገባችሁ ሲስተሙ ሁሉንም Username ያሳያል፤ አንዱን በቻ ይዛችሁ መመዝገብ ይኖርባችኋል፡፡ @tikvahuniversity
显示全部...
153👍 40🙏 18👎 8👏 4😱 3🥰 1😢 1
照片不可用在 Telegram 中显示
#ጥቆማ #BahirDarUniversity የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ፍላጎትና ብቃት ያላቸው የምህንድስና ባለሙያዎችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል። ➤ የሥራ መደብ፦ የህክምና 3D ቴክኖሎጂ ኢንጂነሮች እና ሳይንቲስቶች ➤ ተፈላጊ ባለሙያዎች ብዛት፦ 03 ➤ ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፦ የመጀመሪያ ዲግሪ ➤ የሥራ ልምድ፦ ዜሮ ዓመት ➤ የቅጥር ሁኔታ፦ በኮንትራት ➤ የሥራ ቦታ፦ ባህር ዳር የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው፦ ታህሳስ 22/2018 ዓ.ም ፍላጎት ያላችሁ አመልካቾች አስፈላጊ የትምህርት ማስረጃዎችን በኢሜይል አድራሻ gmkim111@gmail.com በመላክ ማመልከት ትችላላችሁ ተብሏል፡፡ @tikvahuniversity
显示全部...
21👍 1😢 1🙏 1
照片不可用在 Telegram 中显示
የሦስት ወር መሰረታዊ የኮምፒውተር (Basic Computer) ስልጠና ነገ ቅዳሜ ታህሳስ 11/2018 ዓ.ም ይጀመራል! 👉 Microsoft Word, Excel, Access, PowerPoint, Publisher እና ሌሎች የኮምፒውተር አጠቃቀሞችን አካቶ የሚሰጥ ስልጠና ☎️ 0906777799 / 0906777755 አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
显示全部...
42🙏 1
照片不可用在 Telegram 中显示
የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ ተመዝግበዋል? ጤና ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ17 የጤና ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀው የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች በታህሳስ 2018 ዓ.ም የብቃት ምዘና ፈተና ይሰጣል፡፡ በመሆኑም አዲስ እንዲሁም ነባር የመንግሥት እና የግል ተቋማት ተመዛኞች በኦንላይን http://hpe.moh.gov.et/hple ላይ በመግባት እንድትመዘገቡ አሳስቧል፡፡ የኦንላይን ምዝገባ ጊዜ የሚያበቃው፦ እሑድ ታህሳስ 12/2018 ዓ.ም ከተጠቀሰው የምዝገባ ጊዜ በኋላ ምንም ዓይነት የምዝገባ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን የገለፀው ሚኒስቴሩ፤ በተጠቀሱት ቀናት እንድትመዘገቡና ሲስተሙ የሚሰጣችሁን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) የያዘ ስሊፕ Print አድርጋችሁ መያዝ እንዳለባችሁ ገልጿል፡፡ ስትመዘገቡ በመረጣችሁት የፈተና ጣቢያ በፈተናው ወቅት እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡ ተመዛኞች ምዝገባውን ለማካሔድ የዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ግዴታ በመሆኑ፣ የፋይዳ መለያ ልዩ ቁጥር (FIN) በትክክል እንድታስገቡ አሳስቧል፡፡ @tikvahuniversity
显示全部...
116👍 12🙏 5👎 4👏 1
照片不可用在 Telegram 中显示
እንኳን ደስ አላችሁ! 🎉💵 ሰኞ ታህሳስ 6/2018 ዓ.ም 16ኛው እና የመጨረሻው ዙር ዕጣ አወጣጥ በቲክቶክ እና በፌስቡክ ገፆቻችን ላይ በቀጥታ ስናስተላልፍ በነበረው መሰረት የ1000,000 ብር ዕድለኞች ከሮቤ እና ሎጊያ ሆነዋል። 📲 የM-PESA መተግበሪያን አሁኑኑ ያውርዱ፦ https://onelink.to/ewsb22 የቴሌግራም ቦታችን 👉🏽 https://t.me/official_safaricomet_bot #SafaricomEthiopia #MPESASafaricom #furtheraheadtogether #besh
显示全部...
19👎 9
#ነፃ_የትምህርት_ዕድል የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ኮሌጅ በኖርዌይ የልማትና ትብብር ድርጅት የገንዘብ ድጋፍ ባስጀመራቸው በስነ ትምህርት የሁለተኛ ዲግሪ በሒሳብ እና በሳይንስ ስነ ማስተማር (MED in Educational Sciences: Teaching of Mathematics and MED in Educational Sciences: Teaching of Science Subjects) ፕሮግራሞች ከየካቲት 2018 ዓ.ም ጀምሮ ነፃ የትምህርት ዕድል አመልካቾችን ተቀብሎ ለማስተማር ይፈልጋል። አመልካቾች ልታሟሏቸው የሚገቡ፦ ➫ የ2ኛ ዲግሪ የመግቢያ ፈተና (NGAT) ማለፍ፣ ➫ የመጀመሪያ ዲግሪ በባዮሎጅ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስ እና ሂሳብ ትምህርት መስኮች፣ ➫ የማስተማር ልምድ ያላችሁ አመልካቾች ቅድሚያ ይሰጣችኋል፡፡ በፕሮግራሞቹ ተቀባይነት ለሚያገኙ አመልካቾች ነፃ የትምህርት ዕድሉ በዋናነት የሚሸፍነው ለዩኒቨርሲቲው የሚከፈለውን የትምህርት ክፍያ (Tuition Fee) እና የምርምር ገንዘብ ሲሆን፤ መጠነኛ ወርሃዊ የኪስ ገንዘብም ይታሰብላችኋል ተብሏል፡፡ አመልካቾች ዩኒቨርሲቲው ለ2018 ዓ.ም ሁለተኛ ሴሚስተር በሚያወጣው ማስታወቂያ የማመልከቻ ጊዜ ሰሌዳ መሰረት ማመልከቻችሁን ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ ለበለጠ መረጃ፦ 0929402311 / 0918766232 @tikvahuniversity
显示全部...
139👎 15🙏 6👍 5🥰 5👏 1
照片不可用在 Telegram 中显示
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተቋርጦ የነበረውን መደበኛ የመምህራን የሥራ ቦታ ዝውውር በቅርቡ ያስጀምራል፡፡ መምህራን፣ ርዕሰ መምህራን እና ሱፐርቫይዘሮች ከታህሳስ 30/2018 ዓ.ም እስከ ጥር 10/2018 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት የዝውውር ፎርም እንደሚሞሉ ተገልጿል። ዝውውሩ ገቢራዊ ከመሆኑ በፊት ዝውውሩን ለማስፈፀም ተሻሽሎ በተዘጋጀ መመሪያ ላይ በዘርፉ ለሚገኙ ባለሙያዎች ስልጠና የሚሰጥ መሆኑ ታውቋል፡፡ @tikvahuniversity
显示全部...
29👍 1