352 768
订阅者
-4824 小时
+967 天
+1 45930 天
帖子存档
照片不可用在 Telegram 中显示
#WolaitaSodoUniversity
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛው እና በሳምንት መጨረሻ ፕሮግራም በሁለተኛ እና በሦስተኛ ዲግሪ ለመማር አመልክታችሁ ተቀባይነት ያገኛችሁ አመልካቾች ምዝገባ የሚካሔደው ህዳር 08 እና 09/2018 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል፡፡
የምዝገባ ቦታ፡-
➻በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ያለፋችሁ፦ በህክምና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ (ሆስፒታል ግቢ) ሬጅስትራር ጽ/ቤት
➻ በማኅበራዊ ሳይንስ ዘርፍ ያለፋችሁ፦ በማኅበራዊና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ዋናው ግቢ ( Block 12) ሬጅስትራር ጽ/ቤት
➻ በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ያለፋችሁ፦ በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ዋና ግቢ (Block 21) ሬጅስትራር ጽ/ቤት
➻ በግብርና ዘርፍ ያለፋችሁ፦በግብርና ኮሌጅ ዋናው ግቢ (Block 26) ሬጅስትራር ጽ/ቤት
➻ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ዘርፍ ያለፋችሁ፦ በዋናው ሬጅስትራር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 እና 12
➻ በትምህርትና ባህል ጥናት ዘርፍ ያለፋችሁ፦ በትምህርትና ባህል ጥናት ኮሌጅ (Block 03) ሬጅስትራር ጽ/ቤት
➻ በህግ ዘርፍ ያለፋችሁ፦ በህግ ትምህርት ቤት ሬጅስትራር ጽ/ቤት
➻ በእንስሳት ህክምና ዘርፍ ያለፋችሁ፦ በእንስሳት ህክምና ት/ት ቤት ሬጅስትራር ጽ/ቤት
➻ በኮሚፒውተር ዘርፍ ያለፋቹ፡
በIOT ካምፓስ ሬጅስትራር ጽ/ቤት
➻ በኢንጂነሪንግ ዘርፍ ያለፋችሁ፦ በ IOT ካምፓስ ሬጅስትራር ጽ/ቤት
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➻ የትምህርት ማስረጃ ዋናውና ኮፒውን፣
➻ የቅርብ ጊዜ ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➻ ኦፊሽያል ትራንስክሪፕት ለወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በፖ.ሳ.ቁ. 138 ማስላክ፣
➻ በመንግሥት ስፖንስር የተደረጋችሁ ከሆነ የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ ማቅረብ ይሮርባችኋል፡፡
@tikvahuniversity
❤ 175👎 30👍 16🙏 11👏 8😱 4🥰 2😢 2
照片不可用在 Telegram 中显示
#MoE
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከሚወስዱ ተማሪዎች መካከል ከ15 እስከ 20 በመቶ የሚሆኑትን ወደ ዩኒቨርሲቲ እንዲያልፉ ማድረግ የሚቻል ከሆነ “በጣም ትልቅ” ውጤት መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተናገሩ።
አንድም ተማሪ ለዩኒቨርሲቲ ማሳለፍ ካልቻሉ እና ጉዳት ከደረሰባቸው ትምህርት ቤቶች መካከል 700 ያህሉ ተለይተው “የክትትል” እና “እገዛ” ስራ ከአንድ ወር በኋላ እንደሚጀመርላቸው ሚኒስትሩ ገልፀዋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ይህን ያሉት፤ የመስሪያ ቤታቸውን የሩብ ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት፣ ስራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበበት ወቅት ነው።
በቋሚ ኮሚቴው የትምህርት ዘርፍ ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ታደሰ ጌጡ፤ በ2017 የትምህርት ዘመን ለዩኒቨርሲቲ የማለፊያ ነጥብ ያመጡ ተማሪዎች ካለፈው ዓመት አንጻር መሻሻል የታየበት ቢሆንም አፈጻጸሙ “አሁንም ዝቅተኛ” መሆኑን ተናግረዋል። ባለፈው ዓመት ተማሪዎቻቸውን ካስፈተኑ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 40 በመቶ ያህሉ አንድም ተማሪ ማሳለፍ አለመቻላቸውንም በተጨማሪነት ጠቅሰዋል።
“ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ ማሳለፍ የማይችሉት ለምንድን ነው?” ሲሉ የቋሚ ኮሚቴ አባሉ የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችን ጠይቀዋል። “በተከታታይ አንድም ተማሪ በማያሳልፉ እና አነስተኛ ቁጥር በሚያሳልፉ ትምህርት ቤቶች ላይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለምን ተጠያቂነትን ማረጋገጥ አልቻለም?” ሲሉም ተያያዥ ጥያቄ አቅርበዋል።
በቀጣይ ዓመታት ከ12ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል በጣም ብዙዎቹ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናዎችን አልፈው ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ይገባሉ የሚል “ግምት” እንዳለ የትምህርት ሚኒስትሩ አንስተዋል። ይሁንና ሚኒስትሩ “በጣም ጥሩ ትምህርት ያስተምራሉ” የሚባሉ እንደ ፊንላንድ ያሉ ሀገራትን በምሳሌነት በማንሳት፤ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎች ምጣኔ በእነዚህ ሀገራት ጭምር ትንሽ መሆኑን አመልክተዋል።
በፊንላንድ ለአራት ዓመት የዲግሪ ትምህርት ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡት ተማሪዎች ብዛት “22 በመቶ” መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሩ፤ የተቀረሩት “በስፋት እና በጥራት የቴክኒክ እና ሙያ ትምህርት” የሚማሩ መሆናቸውን ለፓርላማ አባላቱ አስገንዝበዋል። በኢትዮጵያ ባለፉት ባለፉት 20 ዓመት የተለመደው በገፍ የማሳለፍ ሁኔታ “normal” ተደርጎ መወሰድ እንደሌለበት እና ይህ አስተሳሰብ መስተካከል የሚገባው እንደሆነ አጽንኦት ሰጥተዋል።
“ከሌሎች ሀገሮች ተሞክሮ ተነስተን ካየነው፤ ምናልባት 20 በመቶ ከደረሰ በጣም ትልቅ ነው። በእኛ አይነት ሀገሮች ከ15 እስከ 20 በመቶ ባለው range ውስጥ ማሳለፍ ከቻልን ከዚያ ኢኮኖሚው የሚፈልገው የskill level መድረስ እንችላለን” ያሉት የትምህርት ሚኒስትሩ፤ “እኛ ምኞታችን ሄደን ሄደን እዚያ 15፣ 20 በመቶ አካባቢ ለመድረስ ነው። ስለዚህ ከዚያ አንጻር ባለፉት ሶስት ዓመታት ያሳየነውን እድገት ስናይ፤ ለራሳችንም የገረመን በጣም ከፍተኛ እመርታ ነው የመጣው” ሲሉ የውጤት መሻሻሉን አሞካሽተዋል።
“ስር የሰደደ ችግር ያለባቸው” እና “የተጎዱ” 700 ትምህርት ቤቶች መለየታቸውን አመልክተዋል። ከማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ለእነዚህ ትምህርት ቤቶች “ክትትል” እና “እገዛ” እንዲደረግ ስምምነት ላይ መደረሱን የገለጹት ሚኒስትሩ፤ ስራው በአንድ ወር በኋላ እንደሚጀምር ተናግረዋል። #ኢትዮጵያ_ኢንሳይደር
@tikvahuniversity
❤ 107👎 21😢 4🥰 3👍 2🙏 1
照片不可用在 Telegram 中显示
የኮምፒውተር ፕሮግራሚንግ እና ዳታቤዝ (Computer Programming and Database) ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን!
👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 C++, Java እና Python ፕሮግራሞች ከመሰረታዊ ደረጃ እስከ Advanced Level በጋራ የሚሰጡበት
👉 ፕሮጀክቶችን እየሠሩ የሚሰለጥኑበት
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
የበለጠ ይጠብቁ ...
💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥
Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute
TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
❤ 43🙏 1
照片不可用在 Telegram 中显示
#DireDawaUniversity
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ህዳር 20 እና 21/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3×4 መጠን የሆነ ፎቶግራፍ፣
➫ የብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) FAN No.፣
➫ ከአካባቢው የአየር ሁኔታ ጋር የሚስማማ እንሶላ እና ትራስ ልብስ፡፡
(ተጨማሪ መረጃ ከምስሉ ይመልከቱ።)
@tikvahuniversity
❤ 151🙏 27👏 14👍 10😢 3
照片不可用在 Telegram 中显示
#OdaBultumUniversity
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ህዳር 25 እና 26/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
የምዝገባ ቦታ፦
በዩኒቨርሲቲው አዲሱ ካምፓስ
ትምህርት የሚጀምረው ህዳር 29/2018 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ፓስፖርት መጠን የሆነ ስምንት ፎቶግራፍ፣
➫ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ፣ ብርድ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
@tikvahuniversity
❤ 116👎 8😱 6👍 1👏 1
#ጥቆማ
የእንግሊዘኛ ቋንቋ ምዘና ፈተና (IELTS) በቀጣይ ሳምንት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ይሰጣል፡፡
ብሪቲሽ ካውንስል ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የ'IELTS' ፈተና ህዳር 13/2018 ዓ.ም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ይሰጣል፡፡
በዕለቱ ሁለት አይነት የ'IELTS' ፈተናዎች (IELTS Academic and IELTS General Training) የሚሰጡ ሲሆን፤ ፈተናውን መውሰድ የሚፈልጉ አመልካቾች ምዝገባ ተጀምሯል።
ኦንላይን ይመዝገቡ 👇
https://ethiopia.britishcouncil.org/exam/ielts
ለተጨማሪ መረጃ፦ 0925629589
@tikvahuniversity
❤ 62👍 6👎 1😱 1
照片不可用在 Telegram 中显示
#ያኔት_ኮሌጅ
በ6 ኪሎ ካምፖስ እና በሰፈረ ሰላም ካምፓስ የ2018 ዓ.ም ምዝገባ ጀምረናል!
BSc Fields of Study:
→ BSc in Medical Laboratory Science
→ Bachelor of Pharmacy
→ BSc in Nursing
TVET Programs:
→ Nursing
→ Medical Laboratory
→ Pharmacy
→ Accounting and Finance
የCPD ማዕከል አገልግሎት
☎️ 0929969696/ 0996828282
አድራሻ፦
መሳለሚያ ሰፈረ ሰላም ንጉሴ ቱሩፊ ህንፃ
6 ኪሎ ካምፓስ ያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት አጠገብ
Telegram: @Yanet6kiloc
❤ 40
照片不可用在 Telegram 中显示
#HaramayaUniversity
በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የድኅረ-ምረቃ ትምህርት የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች የኦንላይን ምዝገባ ህዳር 11 እና 12/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።
በቅጣት ምዝገባ፦ ህዳር 15 እና 16/2018 ዓ.ም
ለምዝገባ ስትሔዱ የትምህርት ማስረጃዎች እና የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ መያዝ ይኖርባችኋል።
@tikvahuniversity
❤ 68😱 3👍 1
照片不可用在 Telegram 中显示
በወለጋ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኢንስቲትዩት የ2018 ዓ.ም የፖስት ቤዚክ የመጀመሪያ ዓመት አመልካች ተማሪዎች ምዝገባ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡
የምዝገባ ጊዜው በቅርቡ በዩኒቨርሲቲው የማኅበራዊ ትስስር ገጾች ይፋ ይደረጋል ተብሏል፡፡
@tikvahuniversity
❤ 33
照片不可用在 Telegram 中显示
ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በ TEFL የሦስተኛ ዲግሪ ትምህርት መስጠት ጀምሯል።
Teaching English as a Foreign Language/TEFL በPhD መሰጠት መጀመሩ፣ ዩኒቨርሲቲው ብቁ የሆኑ መምህራንን በመስኩ ለማፍራት የጀመረውን ጉዞ የሚያጠናክር ነው ተብሏል።
@tikvahuniversity
❤ 28
照片不可用在 Telegram 中显示
ለእናንተ ብቻ ተብለው የተዘጋጁትን የበሽ ጥቅሎች በመግዛት በሽ ሽልማት በየቀኑ፣ በየሳምንቱ ያግኙ! 🎉🎉🎉
ወደ *777*0# ይደውሉ ወይም በM-PESA የበሽ ጥቅል ይግዙ!
📲 የM-PESA መተግበሪያን አሁኑኑ ያውርዱ፦ https://onelink.to/ewsb22
የቴሌግራም ቦታችን 👇
https://t.me/official_safaricomet_bot
#SafaricomEthiopia
#MPESASafaricom
#furtheraheadtogether
#besh
❤ 15🥰 1🙏 1
照片不可用在 Telegram 中显示
ከነገ ህዳር 06/2018 ዓ.ም ጀምሮ በሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት (Sage Training Institute) ቲክቶክ ቀጥታ ስርጭት (Live) ላይ ከጠዋቱ 01:30 እስከ ምሽቱ 01:30 በመግባት ጥያቄዎችን በመመለስ ዕለታዊ 500 ብር እና ሳምንታዊ 5000 ብር ይሸልሙ።
ስለውድድሩ ዝርዝር ህግ ለማግኝት የቲክቶክ አካውንታችንን ይከተሉን።
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Facebook: https://www.facebook.com/sagetraininginstitute
Instagram: https://www.instagram.com/sage_training_institute/
Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute
Tiktok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
❤ 45👏 4👍 1
照片不可用在 Telegram 中显示
#JinkaUniversity
ጂንካ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ለተመደቡ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲው ከጥቂት ቀናት በፊት ጥሪ ማድረጉ ይታወቃል።
ይሁን እንጂ የምዝገባው ጥሪ ላልተወሰን ጊዜ የተራዘመ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።
በመሆኑም በቀጣይ በሌላ ማስታወቂያ ጥሪ እስከሚደረግላቹ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁ ዩኒቨርሲቲው ጠይቋል።
@tikvahuniversity
❤ 94👏 90😢 28👎 18😱 9🙏 2
照片不可用在 Telegram 中显示
#DillaUniversity
በዲላ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛው ፕሮግራም የሁለተኛ እና የሦስተኛ ዲግሪ ትምህርት ለመማር አመልክታችሁ ተቀባይነት ያገኛችሁ አመልካቾች ምዝገባ የሚካሔደው ህዳር 09 እና 10/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡
የምዝገባ ቦታ
➫ በህክምናና ጤና ሳይንስ ዘርፍ ያለፋችሁ፦ በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ግቢ (ሆስፒታል ግቢ) ሬጅስትራር ፅ/ቤት
➫ በማኅበራዊ ሳይንስ ዘርፍ ያለፋችሁ፦ በኦዳያኣ ግቢ ዋና ሬጅስትራር ህንፃ ቁጥር 609
➫ በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ያለፋችሁ፦ ነባሩ ግቢ ሬጅስትራር ፅ/ቤት
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒውን፣
➫ የቅርብ ጊዜ ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➫ Official Transcript ለዲላ ዩኒቨርሲቲ በፖ.ሳ.ቁ. 419 ወይም በኢ-ሜይል አድራሻ registrar@du.edu.et ማስላክ፣
➫ በመንግሥት ስፖንሰር የተደረጉ ከሆነ የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርብዎታል፡፡
@tikvahuniversity
❤ 160👎 64😢 11🙏 8👍 2👏 1😱 1
照片不可用在 Telegram 中显示
#ጥቆማ
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ በተለያዩ የትምህርት መስኮች መምህራንን አወዳድሮ በክልሉ ውስጥ በሚገኙ ወረዳዎች መድቦ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
የመመዝገቢያ መስፈርቶች፦
➫ ከመንግሥት ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ ፕሮግራም በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቀ/የተመረቀች፣
➫ ከዚህ በፊት በክልሉ በቋሚነት ቅጥር ያልፈፀመ/ያልፈፀመች፣
➫ ክልሉ በሚመድብዎት ቦታ ለመስራት ፍቃደኛ የሆነ/የሆነች፣
➫ የመምህርነት ሙያ ክህሎት (PGDT) ስልጠና ላጠናቀቁ ቅድሚያ ይሰጣል፡፡
አመልካቾች ማስታወቂያው ከወጣበት ህዳር 04/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት አምስት የሥራ ቀናት የትምህርት ማስረጃችሁን ከማመለስ ኮፒ ጋር በመያዝ ዘወትር በስራ ሰአት በክልሉ ትምህርት ቢሮ በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፦ 011577752063
@tikvahuniversity
❤ 63😢 3👍 1
照片不可用在 Telegram 中显示
እንኳን ደስ አላችሁ! 🎉💵
ሰኞ ህዳር 1/2018 ዓ.ም የ11ኛው ዙር ዕድለኞች ዕጣ አወጣጥ በቲክቶክ እና በፌስቡክ ገፃችን ላይ በቀጥታ ስናስተላልፍ በነበረው መሰረት የ100,000 ብር ዕድለኞች ከአዳማ ሆነዋል።
ማን ያውቃል ቀጣይ እርስዎ ሊሆኑ ይችላሉ! የበሽ ጥቅል እየገዛን እንንበሽበሽ! 🥳🎉🎉
📲 የM-PESA መተግበሪያን አሁኑኑ ያውርዱ 👇🏽
https://onelink.to/ewsb22
የቴሌግራም ቦታችን 👇🏽
https://t.me/official_safaricomet_bot
ወደ *777*0# ይደውሉ ወይም በM-PESA የበሽ ጥቅል ይግዙ!
#SafaricomEthiopia
#MPESASafaricom
#furtheraheadtogether
#Besh100Winner
❤ 28👏 3👍 1😱 1
照片不可用在 Telegram 中显示
#DebarkUniversity
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ህዳር 25 እና 26/2018 ዓ.ም እንዲሁም በቅጣት ህዳር 29/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
ትምህርት የሚጀምረው ህዳር 29/2018 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ መጠኑ 3×4 የሆነ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣
➫ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ፣ ብርድ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
@tikvahuniversity
❤ 136👍 17👎 8🙏 3😱 2
照片不可用在 Telegram 中显示
ትምህርት ሚኒስቴር በዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና (Exit Exam) ውጤታማነት ላይ ጥናት እያካሔደ ነው፡፡
ጥናቱ በሦስት ወራት ውስጥ ተጠናቆ ይፋ እንደሚደረግ በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡
መንግሥት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በመጀመሪያ ዲግሪ ለሚመረቁ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ከሰኔ 2015 ዓ.ም ጀምሮ እየሰጠ እንደሚገኝ ይታወቃል።
እስከ 250 ሺህ የሚደርሱ ተማሪዎች በዓመት ሁለት ጊዜ የሚሰጠውን ፈተና እየወሰዱ መሆኑን የገለፁት መሪ ስራ አስፈጻሚው፤ ፈተናው ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት መቅሰም የሚጠበቅባቸውን ክህሎት እና እውቀት ለመፈተሽ ያለመ መሆኑን ገልፀዋል።
የመውጫ ፈተናውን ውጤታማነት በመገምገምና በቀጣይ መሰራት ያለበትን ሥራ በመለየት የአፈጻጸም ወጥነትን ለማረጋገጥ እየተደረገ ያለው ጥናት በቀጣይ ሦስት ወራት ተጠናቆ ይፋ ይደረጋል ብለዋል። #ኢዜአ
@tikvahuniversity
👎 130❤ 82👍 29😱 8😢 6🙏 1
照片不可用在 Telegram 中显示
ትምህርት ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ መንግሥታዊ ያልሆኑ የትምህርት ተቋማት የሚመሩበት አዲስ ረቂቅ ደንብ አዘጋጅቷል፡፡
ረቂቅ ደንቡ በተለይ በውጭ ሀገር ማኅበረሰቦች ለሚቋቋሙ ትምህርት ቤቶች አስገዳጅ መስፈርቶችን አስቀምጧል።
በውጭ ሀገር ማኅበረሰብ የተቋቋሙ ትምህርት ቤቶች ከጠቅላላ በጀታቸው ውስጥ 30% የሚሆነው ከሀገራቸው መንግሥት ድጋፍ ማግኘታቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ቀሪውን 70% ደግሞ ራሳቸው መሸፈን የሚችሉ መሆናቸውን የሚያሳይ ማረጋገጫ እንዲያቀርቡ ረቂቁ እንደሚያስገድድ የካፒታል ጋዜጣ ዘገባ ያሳያል፡፡ ይህ የፋይናንስ ማረጋገጫ በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና አግባብ ባለው የሰነዶች ማረጋገጫ ባለሥልጣን ተረጋግጦ መቅረብ እንዳለበት ረቂቁ ያመለክታል።
ለትምህርት ማህበረሰቡና ባለድርሻ አካላት አስተያየት ክፍት በተደረገው ረቂቅ ደንብ፤ መንግሥታዊ ያልሆኑ የትምህርት ተቋማት የአገሪቱን የትምህርት ህግ፣ የመምህራን ብቃት፣ የተማሪዎች መብት እና የትምህርት ደረጃን ጨምሮ ሌሎች ተያያዥ ህጎችን ማክበር እንደሚጠበቅባቸው ተገልጿል።
ተቋማቱ የራሳቸው የሆነ የገንዘብ ምንጭ (ከተማሪዎች ክፍያ፣ ከስጦታ ወይም ከኢንቨስትመንት ትርፍ) እና ነጻ አስተዳደር ያለው ድርጅታዊ አወቃቀር ሊኖራቸው ይገባል። የክፍያ ጭማሪ ለማድረግ ከሦስት ወራት በፊት ተጠቃሚዎችን ማወያየት እንደሚኖርባቸው ያስገድዳል።
መንግሥታዊ ያልሆኑ የአጠቃላይ ትምህርት ተቋማት፣ ሚኒስቴሩ በሚያወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት እንደገና መመዝገብ እንዳለባቸው ተመላክቷል።
ትምህርት ሚኒስትሩ አዲሱ ደንብ የመንግሥታዊ ያልሆኑ ትምህርት ተቋማትን ምዝገባ፣ ዕውቅና እና ቁጥጥር በአጠቃላይ ትምህርት አዋጅ ቁጥር 1368/2017 መሠረት የሚያከናውን መሆኑን ገልጿል። #Capital
@tikvahuniversity
❤ 61👍 6
照片不可用在 Telegram 中显示
ሰቨን ስታር ጤና ሳይንስ እና ቢዝነስ ኮሌጅ
የበርካታ ዓመታት የማስተማር ልምድ ባላቸው የዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሐኪሞች የተመሰረተ ኮሌጅ!
🔔 ለ2018 ዓ.ም ምዝገባ ጀምረናል!
በዲግሪ የጤና መርሐግብሮች
➫ ነርሲንግ ➫ ፐብሊክ ሄልዝ
➫ ፋርማሲ ➫ ሚድዋይፈሪ
➫ ሜዲካል ላብራቶሪ ሳይንስ
➫ ሜዲካል ራዲዮሎጂ ቴክኖሎጂ
በዲግሪ የቢዝነስ መርሐግብሮች (በቀን እና በማታ)
➫ አካውንቲንግና ፋይናንስ
➫ ማርኬቲንግ ማኔጅመንት
➫ ቢዝነስ ማኔጅመንት
➫ ሰው ሀብት አስተዳደር
በጤና በደረጃ-4 መርሐግብሮች
➫ በፋርማሲ ➫ በላብራቶሪ
➫ በነርሲንግ ➫ በሚድዋይፈሪ
➫ በሜዲካል ራዲዮግራፊ
በቢዝነስ በደረጃ-4 መርሐግብሮች
➫ በአካውንቲንግና ፋይናንስ
➫ በማርኬቲንግና ሴልስ ማኔጅመንት
በሪሚዲያል መርሐግብር
⏩ ፈጥነው ይመዝገቡ!
አድራሻ፡-
አዲስ አበባ፣ ፒያሳ አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን፣ ከባቡር ትኬት መቁረጫው ፊት ለፊት
☎️ 0982373737 / 0965686819
❤ 13👏 2

