ch
Feedback
Addis Ababa Education Bureau

Addis Ababa Education Bureau

前往频道在 Telegram

ይህ ቻናል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቴሌግራም ቻናል ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የተከናወኑ እንዲሁም ሀገራዊ ፣ አህጉራዊ እና አለማቀፋዊ የትምህርት መረጃዎች ተደራሽ የሚደረጉበት ነው፡፡

显示更多
2025 年数字统计snowflakes fon
card fon
150 232
订阅者
无数据24 小时
+677
+34630
帖子存档
የቀጠለ…. ማስታወቂያ! (መስከረም 28/2018 ዓ.ም) መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
显示全部...
52👍 10👎 3
ማስታወቂያ! (መስከረም 28/2018 ዓ.ም) መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
显示全部...
23👍 8👎 2
የሰው ሃብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በአዋጅ ቁጥር 87/2017 ላይ ያተኮረ ስልጠና ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡ (መስከረም 28/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሰው ሃብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት አዲስ በተሻሻለው በአዋጅ ቁጥር 87/2017 ላይ ያተኮረ ስልጠና መስጠት ጀምሯል፡፡ ስልጠናው በዋናነት በተለያየ ጊዜ የሚወጡና ማሻሻያ የሚደረግባቸው አዋጆች ደንቦችና መመሪያዎች ላይ ሰራተኛው በቂ ግንዛቤ እንዲይዝና መብትና ግዴታውን እንዲያውቅ ያደርጋል ያሉት የሰው ሃብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ስዩም በቀለ በተለያየ ጊዜ በአመት ፈቃድ ዲሲፕሊንና ቅሬታ አቀራረብ መንገዶችና የሚተዳደርበትን ህግና ደንብ ጠንቅቀው እንዲያውቁና በየጊዜው የሚነሱ የግልጽነት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ግንዛቤ ያስጨብጣል ብለዋል፡፡ ስልጠናው በ3 ዙር ለአጠቃላይ የቢሮው ሰራተኞች የሚሰጥ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ ሕግ ባለሙያ በሆኑት አቶ በቃሉ ከበደ አማካኝነት እየተሰጠ መሆኑን ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
显示全部...
21👎 5👍 4🔥 2
(መስከረም 28/2018 ዓ.ም) መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
显示全部...
28
የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የ2018 ዓ.ም የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ። (መስከረም 28/2018 ዓ.ም) በግምገማው የክፍለ ከተማ የመረጃና ቴክኖሎጂ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን በመርሀግብሩ የዳይሬክቶሬቱና የተመረጡ ክፍለ ከተሞች እቅድ አፈጻጸም ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታዬ ወልደ ኪዳን የዛሬው መርሀግብር በ2018 ዓ.ም አንደኛ ሩብ አመት የተማሪ ምዝገባ መረጃ ማደራጀትን ጨምሮ በዘርፉ የተለያዩ ተግባራት መከናወናቸውን ጠቁመው በከተማ አስተዳደሩ የ2018 ዓ.ም የመደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ መረጃ ተደራጅቶ ለሚመለከተው አካል ተደራሽ መደረጉን በመግለጽ የማታ ተማሪዎች እና የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች መረጃም በአግባቡ ተደራጅቶ ሪፖርቱ ለሚመለከተው አካል እንዲደርስ ክፍለከተሞች ተገቢውን ድጋፍና ክትትል ማድረግ የሚጠበቅባቸው መሆኑን አስገንዝበዋል። ዳይሬክተሩ አያይዘውም ስራ ክፍሉ ከየትምህርት ተቋማቱ ፈጣን መረጃ ለመሰብሰብ ቅጽ ማዘጋጀቱን ገልጸው በቀጣይ ከክፍለ ከተማ የመረጃ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች ጋር በቅጹ ዙሪያ በመግባባት ከየተቋማቱ ፈጣን መረጃዎችን በመሰብሰብ ለተለያዩ አገልግሎቶች የማዋል ስራ እንደሚሰራ አመላክተዋል። በመርሀግብሩ የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ቡድን መሪ አቶ ደስታ አብረሀም የዳይሬክቶሬቱን የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበው ውይይት ተካሂዷል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
显示全部...
28👍 4👏 2
显示全部...
15😁 3
显示全部...
👍 6 1
显示全部...
👍 3 1
显示全部...
👍 3 1
照片不可用在 Telegram 中显示
የሪሜዲያል መግቢያ ነጥብ ትምህርት ሚኒስቴር በ2018 የትምህርት ዘመን የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎችን በተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ትምህርት መስኮች ከ49.5% በታች ያስመዘገቡ ነገር ግን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የሚያሟሉ ተማሪዎች የ Remedial ፕሮግራም ተጠቃሚ መሆናቸውን አሳውቋል። 1. በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 33% ከመቶ እና ከዚያ የተቆረጠ መሆኑን። 2. ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግስት ተቋማት (ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) የ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥቡን ያሟሉ ብቻ እንደሚሆኑ ገልጿል። የትምህርት ሚ/ር
显示全部...
25
የልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም የተማሪዎችን ውጤት መሻሻልን መነሻ ያደረገ ሲምፖዚየም አካሄደ። (መስከረም 27/2018 ዓ.ም) በሲምፖዚሙ የሂሳብና እንግሊዝኛ ውጤት ማሻሻያ ስትራቴጂ በ2017 የነበረውን አፈጻጸም በተመለከተ የዳሰሳ ጥናት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። በሲምፖዚየሙ ንግግር ያደረጉት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ የተማሪዎች ውጤት እንዲሻሻል ሁሉም የትምህርት ባለድርሻ አካላት በትምህርቱ ዘርፍ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ገልጸው በተለይም በሂሳብና በእንግሊዝኛ ትምህርቶች ላይ ተማሪዎችን በመርዳት ለሌሎች ትምህርቶች መሠረት እንዳጥሉ መስራት ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍራኦል ሞሲሳ እንደተናገሩት እንደሀገር ብልጽግናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ትምህርት ያለው ፋይዳ ትልቅ መሆኑን ገልጸው የተማሪዎችን የትምህርት ውጤት በማሳደግ ተማሪዎች ለሀገራቸው ብልጽግና መረጋገጥ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል። አቶ ፍራኦል አክለውም የተማሪዎችን የትምህርት አቀባበል ውጤታማ እንዲሆን ለሂሳብና እንግሊዝኛ ትምህርቶች ትኩረት በመስጠት ሁለቱ ትምህርቶች ላይ ተማሪዎች ብቁ ሆነው በሌሎች ትምህርቶች ውጤታማ እንዲሆኑ ልንሰራ ይገባል ብለዋል። የመድረኩ ተሳታፊዎዎች እንደተናገሩት ሲምፖዚየሙ የተማሪዎች ውጤት እንዲሻሻል ማን ምን ማድረግ እንዳለበት ግንዛቤ ያገኙበት መሆኑን ገልጸው ተማሪዎች ውጤታቸው እንዲሻሻል የክትትል ስራ በተጠናከረ መልኩ ልናከናውን ይገባል ብለዋል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
显示全部...
45
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት የ 2018 ትምህርት ዘመን 1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን ግምገማ አካሄዱ:: (መስከረም 27/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት የ2018 ትምህርት ዘመን 1ኛ ሩብ ዓመት የቁልፍና አበይት ተግባራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት አካሂደዋል:: በውይይቱ የቢሮው ማኔጅመንት አባላት የተገኙ ሲሆን የእቅድና በጀት ዝግጅት ክትትል ግምገማ ዳይሬክተር በሆኑት አቶ ጌታሁን ለማ አማካኝነት በሩብ አመቱ የተከናወኑ ቁልፍና አበይት ተግባራት እቅድ አፈፃፀም እንዲሁም ሥራዎቹ ሲከናወኑ የነበሩ ጥንካሬዎች፣ ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ መፍትሄዎች በሪፖርቱ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ እቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱ ቀደም ሲል በየሥራ ክፍሉና በየዘርፉ ግምገማ የተካሄደ መሆኑን ገልፀው ሪፖርቱ የዝግጅት ምዕራፍ ስራው በተቀመጠው እቅድ መሰረት በስኬት የተጠናቀቀ መሆኑን ያሳያል ብለዋል:: አክለውም በጋራ ውይይቱ የተነሱ ሀሳቦች ተካተው በቀጣይ ለፕሮሰስ ካውንስል እና ጠቅላላ ሰራተኛ ውይይት እንደሚቀርብ መሆኑን ተናግረዋል :: መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
显示全部...
24
ቂርቆስ ክፍለ ከተማ የትምህርት ቤቶች የማስ ስፖርት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡ (መስከረም 27/2018 ዓ.ም) ንቅናቄው "ብቁና ንቁ ትውልድ ለማፍራት እንተጋለን!" በሚል መሪ ቃል የተከናወነ ሲሆን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለተማሪዎች የአዕምሮ እድገት አስተዋፅኦው የጎላ በመሆኑ ያንን ታሳቢ ያደረገ የማስ ስፖርት መርሀ-ግብር እንደሆነ በመድረኩ ላይ ተገልፁዋል፡፡ በመርሀ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱና የክፍለ ከተማው ትምህርት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሰማኸኝ አስታጥቄ በዋሊያ ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት አስጀምረዋል፡፡ በመድረኩ ከከተማ እስከ ወረዳ ያሉ አመራሮች የትምህርት ባለሙያዎች፣ሱፐርቫይዘሮች፣ የትምህርት ቤቱ መምህራን፣ የአስተዳደር ሠራተኞችና ተማሪዎች ተሳትፈዋል። ይህ የማስ ስፖርት በሁሉም ትምህርት ቤቶች ዘወትር ማክሰኞ እና ሐሙስ ማለዳ የሚካሄድ መሆኑ ተመላክቷል፡፡ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
显示全部...
26👍 4🖕 3👎 1
በንፋስ ስልክ ላፍቶ የትምህርት ቤቶች የማስ ስፖርት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡ (መስከረም 27/2018 ዓ.ም) በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ "ብቁና ንቁ ትውልድ ለመፍጠር እንተጋለን!" በሚል መሪ ሃሳብ የትምህርት ቤቶች የማስ ስፖርት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሂዷል። በሲቢስቴ ነጋሲ ቅድመ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተካሄደው ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት እና ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት በጋራ የተዘጋጀ ነው። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳምሶን መለሰ ትምህርት ለአንድ ሀገር ሁለንተናዊ እድገትና ብልጽግና መሰረት እንደመሆኑ ከተማ አስተዳደሩ ለትምህርት ሴክተሩ ውጤታማነት ልዩ ትኩረት የሰጠ መሆኑን ጠቅሰው የአካል ብቃት እንቅስቃሴውም ተማሪዎች ብቁና ንቁ እንዲሆኑ የሚያስችል ነው ብለዋል። የትምህርት ቤቶች የማስ ስፖርት መርሃ ግብር ቀጣይነት ያለውና ሁሌም በየሳምንቱ ማክሰኞና ሀሙስ የሚከናወን መሆኑን የጠቀሱት አቶ ሳምሶን ለተግባራዊነቱ ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት መወጣት እንዳለባቸው ገልፀዋል። የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በላይ ነጋሽ የአካል ብቃት እንቅስቃሴው ተማሪዎች በአካልና በአዕምሮ ዳብረው በትምህርታቸው ላይ ውጤታማ እንዲሆኑ በማድረግ ረገድ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው ሳይቆራረጥ ማክሰኞና ሃሙስ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ላይ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
显示全部...
26🔥 1
በጉለሌ ክፍለ ከተማ የተማሪዎች የማለዳ የአካል ብቃት እንቅስቀሴ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር በእንጦጦ አንባ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተካሄደ። (መስከረም 27/2018 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የተማሪዎች የማለዳ አካል ብቃት እንቅስቃሴ ማስጀመሪያ መርሀግብር በእንጦጦ አምባ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት "ብቁ እና ንቁ ትውልድ ለመፍጠር እንተጋለን!" በሚል መሪ ሀሳብ ተካሂዷል፡፡ በስፖርታዊ እንቅስቃሴው ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊ አማካሪ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ፤ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሳሙዔል ተገኝ የትምህርት ቤቱ መምህራን፣ አመራሮችና ተማሪዎች ተሳትፈዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊ አማካሪ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማስጀመሪያ መርሃግብሩ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በሁሉም ደረጃ ያሉ ተማሪዎች በአካዳሚክ እውቀታቸው የበቁ እንዲሆኑ ብቻ ሳይሆን በአካል ብቃታቸው የበቁ እና ጤንነታቸው የተጠበቀ የነገ ሃገር ተረካቢ ትውልድ ለማፍራት በሁሉም ትምህርት ቤቶች ምቹ የስፖርት ሜዳ እንዲኖር በማድረግ የትምህርት ሰዓት በማይነካ በሳምንት 2 ቀናት የማስ ስፖርት እንቅስቃሴ ተግባራዊ እንዲደረግ በርካታ ተግባራት መከናወናቸው በመግለጽ በቀጣይም በጥብቅ ዲሲፕሊን እንዲመራ አሳስበዋል፡፡ በመርሀግብሩ የተገኙ እንግዶችና ተማሪዎች በስፖርታዊ እንቅስቃሴው የተሳተፉ ሲሆን የስፓርት እንቅስቃሴው በሳምንት 2 ጊዜ ጠዋት ጠዋት ማክሰኞና ሐሙስ በሁሉም በትምህርት ቤቶች በቋሚነት የሚካሄድ መሆኑና በትምህርትና በወጣቶችና ስፖርት ቢሮዎች መካከል በጋራ የሚከናወን መሆኑ ተገልጿል፡፡
显示全部...
26
በልደታ ክፍለ ከተማ የተማሪዎች የማለዳ የአካል ብቃት እንቅስቀሴ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር በደጃች ባልቻ ሁለተኛና መሰናዶ ትምህርት ቤት ተካሄደ። (መስከረም 27/2018 ዓ.ም) ብቁና ንቁ ትውልድ ለማፍራት እንተጋለን! በሚል መሪ ሀሳብ በልደታ ክፍለ ከተማ የተማሪዎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር ተካሂዳል፡፡ የልደታ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍራኖል ሞሲሳ በከተማ አቀፍ የትምህርት ቤቶች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መጀመሩን ገልፀው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የተማሪዎችን ጤና ከመጠበቅ ባለፈ በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ያደርጋል ብለዋል። በአካል ብቃት እንቅስቃሴው ላይ የተሳተፉ የትምህርት ቤቱ መምህራኖች፣ ተማሪዎች ፣ የአስተዳደር ሠራተኞች እና አመራሮችን የልደታ ክ/ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ ወጣት ክብረዓለም ደምሴ አመስግነዋል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
显示全部...
13👍 1🥰 1😁 1
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ በበኩላቸው በትምህርት ውጤት ላይ ብቻ ሳይሆን በአካል ብቁና ንቁ የሆኑ ተማሪዎችን በማፍራት ስራ ውስጥ የስፖርት መምህራን ትልቅ ሀላፊነት እንዳለባቸው እንዲሁም ንቅናቄው አመቱን ሙሉ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ለ15 ደቂቃ የሚከናወን መሆኑን ገልፀዋል። በትምህርትና በወጣቶችና ስፖርት ቢሮዎች መካከለል በጋራ የሚከናወኑ ስራዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉ እንደሚሆኑ ተናግረዋል፡፡ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
显示全部...
11👍 1👎 1
የተማሪዎች የማለዳ የአካል ብቃት እንቅስቀሴ ማስጀመሪያ ከተማ አቀፍ መርሀ ግብር በዳግማዊ ሚኒሊክ ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጀ ትምህርት ቤት ተካሄደ፡፡ (መስከረም 27/2018 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአራዳ ክፍለከተማ በሚገኘው ዳግማዊ ሚኒሊክ ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጀ ትምህርት ቤት የተማሪዎች የማለዳ የአካል ብቃት እንቅስቀሴ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር "ብቁ እና ንቁ ትውልድ ለመፍጠር እንተጋለን!" በሚል መሪ ሀሳብ ተካሄዳል፡፡ የአካል ብቃት እንቅስቃሴውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት እና ወጣቶችና ስፓርት ቢሮዎች በጋራ ያዘጋጁት ሲሆን በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ ፣ የክፍለ ከተማዉ ትምህርትና ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ሀላፊዎች ፣ የወረዳ ባለሙያዎችና አመራሮች ፣ የትምህርት ቤቱ መምህራን፣ አመራሮችና ተማሪዎች ተሳተፊ ሆነዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ ባስተላለፉት መልዕክት ተማሪዎች በአካልና በአዕምሮ ብቁ እንዲሆኑ ለማድረግ ስፖርታዊ እንቅስቀሴዎች ትልቅ አበርክቶ እንዳላቸው ገልጸው ስፖርት ግንኙነትን ለማጠናከርና ለአብሮነት የሚኖረው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የስፓርት እንቅስቃሴው በየሳምንቱ 2 ጊዜ ጠዋት ጠዋት ማክሰኞና ሐሙስ በሁሉም በትምህርት ቤቶች በቋሚነት የሚካሄድ መሆኑን ገልፀዋል። ሀላፊው አክለውም የስፓርት ማስጀመሪያ ንቅናቄው በዛሬው እለት በሁሉም ክፍለ ከተማዎች የሚካሄድ መሆኑን ገልፀዋል።
显示全部...
13👍 2👎 1
显示全部...
23👍 6🔥 1
የከተማ ግብርና በጃራ አባገዳ ቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጀ ትምህርት ቤት (መስከረም 26/2018 ዓ.ም) መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
显示全部...
38👏 6🥰 5👎 2🤮 1