2025 年数字统计

150 232
订阅者
无数据24 小时
+677 天
+34630 天
帖子存档
የልዩ ፍላጎትና የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ለ1ኛ ደረጃ አይነስውራን ተማሪዎች የተዘጋጀ የብሬል መጽሐፍ እና የመምህር መምሪያ በማስገምገም ላይ መሆኑን አስታወቀ።
(መስከረም 20/2018 ዓ.ም) የብሬል መጽሐፍ ግምገማው በከተማ አስተዳደሩ ከሚገኙ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ብቃታቸው ተረጋግጦ በተመረጡ አይነስውር መምህራን እና ከቢሮው ጉዳዩ በሚመለከታቸው የስርአተ ትምህርት ባለሙያዎች እየተካሄደ መሆኑን ከስራ ክፍሉ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የልዩፍላጎትና የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገመቺስ ፍቃዱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ልዩ ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች ፍትሐዊ ትምህርት ተደራሽ ለማድረግ የተለያዩ ተጨባጭ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ላይ መሆኑን ጠቁመው በዛሬው እለት መካሄድ የጀመረው የ1ኛ ደረጃ የብሬል መጽሐፍ ግምገማ አይነስውራን ተማሪዎች በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ከተማ አስተዳደሩ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ማሳያ መሆኑን አመላክተዋል።
ዳይሬክተሩ አያይዘውም የብሬል መጽሐፍ ግምገማው ሲጠናቀቅ የሚሰጡ የማስተካከያ ሀሳቦችን በማካተት ታትመው ለተማሪዎች ተደራሽ የሚደረጉ መሆኑን ገልጸው ቀደም ሲል ለ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች የተዘጋጁ የብሬል መጽሐፍት እና የመምህሩ መምሪያ በተመሳሳይ መገምገሙን አስረድተዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 32👍 1
የትምህርት መረጃ ዝግጅት ፣ የትምህርት ቴክኖሎጂ ልማት እና የግብአት አቅርቦትና ስርጭት ዘርፍ የ3 ወራት እቅድ አፈጻጸሙን ገመገመ፡፡
(መስከረም 20/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት መረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ፣ የትምህርት ቴክኖሎጂ ልማትና አስተዳደር እና የግብአት አቅርቦትና ስርጭት ዳይሬክቶሬቶች ቁልፍ ውጤት አመላካች ( KPI ) እና ሪፎርም ተግባራት ለማከናወን በእቅድ ካስቀመጧቸው ተግባራት ውስጥ የተከናወኑ ዋና ዋና ሥራዎች የ3 ወር አፈፃፀም ሪፖርት የቢሮው ምክትል ቢሮ ኃላፊና ዘርፉ ኃላፊ አቶ ሳምሶን መለሰ በተገኙበት ተገምግሟል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ ሳምሶን መለሰ ሶስቱም ዳይሬክቶሬቶች ተመጋጋቢ ተግባራት የሚፈፅሙ ከመሆኑ አንፃር በጋራ ስራቸውን መገምገም በስራው ላይ ሁሉም በቂ ግንዛቤ እንዲይዙ ዕድል ይፈጥራል ብለዋል፡፡ አያይዘውም የተነሱ ሀሳቦች በቀጣይ ትኩረት ሰጥተን እንድንሰራ ግብዓት የሚሆኑ ናቸዉ ብለው የየስራ ክፍሎቹ ሪፖርት ላይ በጥንካሬ የተነሱ ሥራዎችን አጠናክሮ ለመቀጠልና በክፍተት የተነሱትን ፈጥኖ ማስተካከል እንደሚገባ ገልጸው ባለሙያዎቹና ዳይሬክቶሬቶቹ በሥራ ክፍላቸው እየሰሩ ያሉትን ቅንጅቶችና የስራ ውጤቶች አጠናከረው እንዲቀጥሉ አበረታተዋል:: በተጨማሪም በቀሪ ዘጠኝ ወራት ሊከናወኑ የሚገቡ ስራዎች ላይ የስራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡
በሪፖርቱ የትምህርት መረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ፤ የትምህርት ቴክኖሎጂ ልማትና አስተዳደር እና የግብአት አቅርቦትና ስርጭት ዳይሬክቶሬቶች በ3 ወራት ውስጥ ያከናወኗቸውን ዋና ዋና ስራዎች አቅርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
በውይይቱ ላይ በሶስቱ ዳይሬክቶሬቶች የሚገኙ ዳይሬክተሮች ፤ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡
❤ 43👍 1
የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡
(መስከረም 19/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሰኞ ማለዳ ከስራ ሰዓት መግቢያ በፊት የሚያዘጋጀው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር በዛሬው እለት የተካሄደ ሲሆን በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስነ ጥበባት ትምህርት ባለሙያ የሆኑት አቶ ቱጁባ በየነ የባህል አስፈላጊነት በትውልድ ግንባታ ላይ በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በመድረኩ ማጠቃለያ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ ባህል ለትውልድ ግንባታ ትልቅ መሰረት የሚጥል መሆኑን ገልጸው ወሩ የቱሪዝም ወር እንደመሆኑ መጠን ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በጋራ በመሆኑን በትምህርት ቤቶች ላይ ተንቀሳቃሽ አውደ ርዕዮች እየተከናወኑ የሚገኙ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 47🔥 2
ቴክኖሎጂን ለትምህርት ስርአቱ ኣጋዥ መሳሪያ በማድረግ አሉታዊ ተጽእኖዎችን መቀነስ ይገባል፡፡
(መስከረም 17/2018 ዓ.ም)
https://youtu.be/qcJvQukrN1Q
❤ 33
照片不可用在 Telegram 中显示
እንኳን ለመስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
Baga Ayyaanaa Masqalaan nagaan isin ga'e!
(መስከረም 17/2018 ዓ.ም)
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 35👍 13
የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር መርሃ ግብር በመስቀል አደባባይ በፎቶ
(መስከረም 16/2018 ዓ.ም)
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 78👍 7🙏 5🥰 4👏 4🤔 1
እንኳን ለደመራ እና መስቀል በዓል በሰላም አደረሰን፤ አደረሳችሁ!
የከተማችን ልዩ ድምቀት ለሆነው እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ ሳይንስ እና ባህል ድርጅት (UNESCO) በማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበው የመስቀል ደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ በታላቅ ድምቀት እየተከበረ ነዉ።
ለመላዉ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች እንኳን በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ፤ በዓሉ የአብሮነት፣ የፍቅር እና የሰላም እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ
መልካም በዓል !
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
❤ 57👍 6
የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር መርሃ ግብር ከመስቀል አደባባይ - ፎቶ
(መስከረም 16/2018 ዓ.ም)
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 40👎 4🥰 4😁 1
照片不可用在 Telegram 中显示
"እንኳን ለመስቀል በዓል አደረሳችሁ"
"እውነት አይቀበርም!!..." - ጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ
(መስከረም 16/2018 ዓ.ም) የመስቀል በዓል ሲታሰብ እውነት ተቀብራ እንደማትቀር እናስባለን። መስቀሉ የተቀበረበት ቦታ ተራራ ሠርቶ ነበር። የቀበሩት ሰዎች ከዚህ በኋላ እንደማይወጣ ደምድመው ነበር። አንዳንድ አማኞችም ተስፋ ቆርጠው ነበር።
ጊዜው በረዘመ ቁጥር ቀባሪዎቹ ያሸነፉ መስሏቸው ተደሰቱ። የተቀበረው መስቀልም ታሪክ የሆነ መሰለ።
ብርቱ ሰዎች፣ እውነት ፈላጊ ሰዎች፣ አቧራውን የሚገልጡ፣ ቆሻሻውን የሚያነሡ ሰዎች፣ ሲመጡ ግን መስቀሉ ከተቀበረበት ወጣ።
እውነት አይቀበርም። ጊዜው ሲደርስ አቧራውን አንሥቶ ዐሻራውን ያሳያል። ሐሰቱን እንደ ጉም አትንኖ፣ ሐቁን እንደ ዐለት አግንኖ ያሳያል።
የኢትዮጵያም እውነት እንደዚሁ ነው። የአውራ ዶሮዎች ጩኸት የፀሐይን መውጣት አያስቀረውም። የሌሊት ወፎች ክንፍ የፀሐይን ንጋት አያግደውም። በዚህም ተባለ በዚያ ፀሐይ ትወጣለች።
የኢትዮጵያ እውነት እንደ መስቀሉ ሁሉ አቧራውን ጥሶ፣ አፈሩን አፍልሶ፣ ቆሻሻውን ደርምሶ ይገለጣል። የወጓት ያዩዋታል። ከላይ ሆነው እንዳዩዋት ሁሉ፣ ከታች ሆነው ይገረሙባታል።
በመደመር ደመራ እየተመራን፣ በትጋት እየቆፈርን፣ የኢትዮጵያን ብልጽግና እናወጣዋለን። ይህ ዓመት የኢትዮጵያ ብርሃን ሲወጣ የምናይበት ይሆናል።
በድጋሚ መልካም የደመራና የመስቀል በዓል ይሁንልን።
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
መስከረም 16 ቀን 2018 ዓ.ም
ጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 58🤮 9👍 5😁 3💋 1
ዛሬ በሁሉም ክፍለከተማዎች እና ወረዳዎች ዘውትር በዓል በመጣ ቁጥር እንደምናደርገው የመሰቀልና የኢሬቻ በዓላትን ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋርተናል ።
በዚህ ተግባር የቆየዉን የመደጋገፍ እና ተካፍሎ የመኖር ባህል ከሰዉ ተኮር እሳቤዎቻችን ጋር አቆራኝተን የተቸገሩትን የመርዳት እሴቶቻችንን እያዳበርንበት ነዉ።
ይህንን የበጎ ፈቃድ ተግባር ከጎናችን ሆናችሁ የምትደግፉ ልበ ቀናዎች በሙሉ በተጠቃሚዎች ስም ምስጋናዬ ይድረሳችሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
መልካም የመስቀል ደመራ በዓል
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
❤ 27👍 2👎 1
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አሊ ከማል በበኩላቸው ትምህርት ሰው ተኮር ሥራ በመሆኑ የተለየ የአመራር ጥበብን የሚጠይቅ መሆኑን ገልፀው ስልጠናው በራስ መተማመናቸው የዳበረ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ችግርን የሚፈቱ ዜጎች ለማፍራት የሚችሉ የትምህርት አመራሮችን እውቀት ለማጎልበት ጠቃሚ መሆኑን አብራርተዋል :: ሰልጣኞችም ያለባቸውን ብቁ ዜጋ የማፍራት ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት ስልጠናውን በትኩረት እንዲከታተሉ አሳስበዋል::
በስልጠና መርሐግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ፣ የአፍሪካ አመራር ልቀት አካዳሚ ፕሬዝዳንት አቶ ዛዲግ አብርሀ ፣ የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ ፣ የኢትዮጵያ እና አዲስ አበባ ተ. ወ. ማ ፕሬዝዳንት አቶ ሐሰን ሺፋ ፣ የቢሮ ማኔጅመንት አባላት የተገኙ ሲሆን በስልጠናው የቢሮው ሱፐርቫይዘሮች ፣ የ1ኛ ደረጃ እና 2ኛ ደረጃ ሱፐርቪዥን አስተባባሪዎች ፣ የክፍለ ከተማ የአፋን ኦሮሞ የሱፐርቪዥን አስተባባሪዎች ተሳትፈዋል::
የትምህርት ሀይል በሀገራችን ዕጣ ፈንታ ላይ ያለው አስተዋፅኦ በሚል ርዕሰ ጉዳይ ትኩረት ያደረገ የአቅም ግንባታ ስልጠና የአፍሪካ አመራር ልቀት አመራር አካዳሚ ፕሬዝዳንት በሆኑት አቶ ዛዲግ አብርሀ አማካኝነት ተሰጥቷል ::
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 22👍 8👎 6
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለትምህርት አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ::
(መስከረም 16/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለትምህርት አመራሮች በትምህርት ሀይልና በሀገራችን ዕጣ ፈንታ ላይ ትኩረት ያደረገ የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በስልጠናው መክፈቻ ተገኝተው ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ስልጠናው የትምህርት አመራሩን በአቅም በመገንባት የበቃና የነቃ ትውልድ የሚመራ አመራር እናፈራለን በሚል በ32 ኛው የትምህርት ጉባኤ የትምህርት አመራርን አቅምና ክህሎት ለማሳደግ ቃል በገባነው መሰረት የተዘጋጀ የስልጠና መርሐግብር ነው ሲሉ ገልፀዋል::
የትምህርትን መሰረታዊ ትርጉም በመረዳት በአመለካከትና ክህሎት የተገነባና በመርህ የሚመራ ትውልድ ማፍራት የሚችሉ የትምህርት አመራሮች ለመፍጠር ቢሮው በርካታ ሥራዎች እየሰራ መሆኑን የጠቆሙት ቢሮ ኃላፊው የትምህርት አመራሮች ከስልጠናው የሚገኙ መሰረታዊ ሀሳቦችን በመጨበጥ በመልካም ስነምግባር የታነፁ የዜግነት ኃላፊነት የሚሰማቸው ሀገር አቀፋዊና አለማቀፋዊ እውቀት ያላቸው ልጆች ለማፍራት አቅም የሚፈጥር መሆኑን አብራርተዋል :: አያይዘውም ሰልጣኞች በጥብቅ ዲሲፕሊን ስልጠናውን በመከታተል ከስልጠናው ያገኙትን እውቀት ተግባር ላይ እንዲያውሉት አሳስበዋል::
❤ 25👍 1
