ch
Feedback
Addis Ababa Education Bureau

Addis Ababa Education Bureau

前往频道在 Telegram

ይህ ቻናል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቴሌግራም ቻናል ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የተከናወኑ እንዲሁም ሀገራዊ ፣ አህጉራዊ እና አለማቀፋዊ የትምህርት መረጃዎች ተደራሽ የሚደረጉበት ነው፡፡

显示更多
2025 年数字统计snowflakes fon
card fon
150 232
订阅者
无数据24 小时
+677
+34630
帖子存档
የከተማ ግብርና በትምህርት ተቋማት ግቢ ተግባራዊ በማድረግ የመማር ማስተማሩን ተጨባጭነት ከማረጋገጥ ባሻገር የምርት አቅርቦት ላይ መሻሻል እየፈጠረ ይገኛል። (መስከረም 15/2018 ዓ.ም) በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የኢትዩ-ጃፓን ህዳሴ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በከተማ ግብርና የለማ የበቆሎ ሰብል በመሰብሰብ ስራ የተሰራ ሲሆን የትምህርት ቤቱ አስተዳደር፣ መምህራን እና ተማሪዎች በሌማት ትሩፋት ስራ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛሉ። በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ በሚገኙ በትምህርት ተቋማት ውስጥ እየተተገበረ የሚገኘው የከተማ ግብርና ውጤት በማስመዝገብ ላይ ይገኛል። የክ/ከተማዉ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አህመድ ኡርጎ፣ የክ/ከተማዉ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ከበደ ድሪባ፣ የወረዳ 2 አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አዱኛ ዘነበ፣ መምህራን እና ተማሪዎች እንዲሁም የትምርት ቤቱ ርዕሰ መምህርና የአስተዳደር ሰራተኞች በተገኙበት መልዕክት የተላለፈ ሲሆን በቀጣይ የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብና ተማሪዎችን በማስተባበር በአመት ሁለቴ ለማምረትና ለአካባቢው ማህበረሰብም ተሞክሯቸውን ለማካፈል መዘጋጀታቸው ተገልፀዋል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
显示全部...
38
የትምህርት ስራ ለትምህርት ዘርፉ ብቻ የሚተው ሳይሆን የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ የሚጠይቅ በመሆኑ ሁሉም የበኩሉን ሚና መወጣት አለበት ብለዋል፤ እነዚህን ግብአቶች በጥንቃቄ በመያዝ ተማሪዎች እንዲጠቀሙባቸው በማሳሰብ በዛሬው እለት የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ድርጅት ላደረገው ልዩ ድጋፍ ላቅ ያለ ምስጋና አቅረበዋል። በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የወረዳው ዋና ስራ አስፈጻማ ወ/ሮ ነይማ ሉባ ይህን ድጋፍ ላደረገው ተቋም ላቅ ያለ ምስጋና በማቅረብ የትምህርት ስራ የሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የሚጠይቅ በመሆኑ ለነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ የሚደረጉ ድጋፎች የነገዋን ኢትዮጵያ መገንባት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የተቋሙ ማርኬቲንግ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደምስ ተቋሙ በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች የማህበራዊ ኃላፊነቱን በተለያዩ ዘርፎች እየተወጣ ሲሆን በቀጣይም በትምህርት ዘርፉ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አስረድተዋል። መርሀግብሩ የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት ሎጂስቲክ አባላት ፣ የከተማ የክፍለ ከተማ ፣ የወረዳ አመራሮች እንዲሁም የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ተገኝቷል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
显示全部...
11👏 1
የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክ አገልግሎት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት በእድገት በህብርት ቅድመ 1ኛና አንደኛ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ ድጋፎችን አደረገ። (መስከረም 15/2018 ዓ.ም) በትምህርት ቤቱ በመገኘት የማጣቃሻና አጋዥ መጽሀፍ ፣ የስፖርት ቁሳቁስ ፣ እንዲሁም የተለያዩ የሙዚቃ ክዋኔ ማስተማሪያ ግባቶችን ድጋፍ አድርገዋል። በድጋፍ ስነ_ስራዓቱ ላይ የተገኙት የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰማኝ አስታጥቄ መንግስት ለትምህርት ሴክተሩ በሰጠው ልዩ ትኩረት ሰፊ ተግባራት እየተከናወነ ሲሆን በዚህም ሰፊ ለውጥ መምጣቱን አስታውቀዋል፤ በተለይም የተማሪ ውጤትና ስነ-ምግባር ሊያሻሽሉ የሚችሉ የተማሪዎች ምገባ፣ የተማሪዎች ሙሉ ግብአት አቅርቦት ፣ የትምህርት ቤቶች ግቢ ለመምህራን ፣ ለተማሪዎችና ለትምህርት ቤቱ ስታፍ ምቹና ማራኪ በማድረግ ፣ የትምህርት ውስጣዊ ብቃትን ሊያረጋግጡ የሚችሉ ስራዎች የተሰሩ ሲሆን በዚህም በነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ላይ ተጨባጭ ለውጥ መመዝገቡን ገልጸዋል።
显示全部...
17
ዳይሬክተሩ አክለውም ተማሪዎቹን እንደየጉዳት አይነታቸው ለይቶ በትምህርት፤በባህሪና ማህበራዊ ህይወታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ማብቃት ከሰልጣኝ ባለሙያዎች እንደሚጠበቅ ተናግረዋል፡፡   ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥቁር አንበሳ ሕፃናት እና ታዳጊ ወጣቶች አእምሮ ጤና ስፔሻሊስት የሆኑት ዶክተር ፍቅርተ ግርማ ልዩ ፍላጎት ያላቸው ልጆችን ለመለየት የሚጠቅሙ ዘዴዎች እና ከልየታ በኋላ  ለማገዝ የሚጠቅሙ ነጥቦች ላይ ትኩረት ያደረገ እንዲሁም  ከልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ንባብ፣ ባህሪ ፣ተግባቦት ፣ አካል ጉዳት እና መሰል ጉዳዮች ጋር ተያይዞ በአቶ ፀጋዬ ሁንዴ አማካኝነት በቀረበ ሰነድ  ስልጠናው ተሰጥቷል፡፡ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ያሉ የልዩ ፍላጎት ባለሙያዎች እና ቡድን መሪዎች ፣ ተዘዋዋሪ መምህራን እና ከሁሉም ክፍለከተሞች የተውጣጡ በልዩ ፍላጎት ትምህርት አሰጣጥ ላይ የተሻለ አፈፃፀም ያላቸው ርዕሰ መምህራን ስልጠናውን እንደወሰዱ ያገኘነው መረጃ ያሳያል :: መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
显示全部...
16
የልዩ ፍላጎት አካቶ እና ጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ዳይሬክቶሬት የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ልየታ ላይ ስልጠና ሰጠ :: (መስከረም 15/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የልዩ ፍላጎት አካቶ እና ጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ዳይሬክቶሬት የልዩ ፍላጎት ተማሪዎችን በየጉዳት አይነታቸው ለመለየት የሚያስችል ስልጠና ለሚመለከታቸው ባለሙያዎች በመስጠት ላይ መሆኑን አሳውቋል :: የልዩ ፍላጎት አካቶ እና ጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ዳይሬክተር አቶ ገመቺስ ፈቃዱ በስልጠናው ማስጀመሪያ ላይ ተገኝተው እንዳሉት በቢሮው የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ቤታቸው እንዳይቀሩ እና ትምህርት እንዲያገኙ የመማሪያ ክፍሎችን እንዲሁም የትምህርት ቁሳቁሶችን እያሟላ መቆየቱን ተናግረው በ2017 የትምህርት ዘመንም ከ34ሺ በላይ ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎችን ልየታ በማድረግ እና በ12 ምድቦች በመለየት ትምህርት ሲሰጥ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡ ስልጠናው በልዩ ፍላጎት ትምህርት አሰጣጥ ላይ በተደረገ ድጋፍና ክትትል መሰረት የታዩ እጥረቶችን ለመቅረፍና በ2018 ትምህርት ዘመን ቅበላ ለተደረገላቸውና ነባር የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ትምህርቱን ለሚሰጡ አካላት ብቁ እንዲሆኑ መዘጋጀቱን የገለጹት አቶ ገመቺስ ከስልጠናው በኋላም አስፈላጊውን ልየታ በማድረግ እንደጉዳት አይነታቸው ተገቢ የሆነ ትምህርት የሚሰጡ የሚደግፉና የሚያበቁ መምህራን እንዲኖሩ ስልጠናው ትልቅ ድጋፍ ያደርጋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
显示全部...
14
ምግብና የስርዓተ ምግብ ጉድለት በተማሪ አካላዊና አእምሮአዊ እድገት ላይ ውስንነት የሚያስከትል መሆኑን ያብራሩት ምክትል ቢሮ ኃላፊው ለተማሪ ጤና አስፈላጊ የሆኑ ንጥረ ነገሮች የያዘ እንዲሁም የተማሪ ፍላጎት እና የመጋቢ እናቶች የመመገብ አቅም ባማከለ መልኩ የምግብ ዝርዝሩን ለማዘጋጀትና ለማስተግበር ቢሮው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ እንደሚሰራ ተናግረዋል:: አያይዘውም የወረደውን የምግብ ዝርዝር በአግባቡ ተግባራዊ በማድረግ ለልጆቻችን ውጤት መሻሻል ሀላፊነታችንን እንወጣ በማለት አሳስበዋል:: የምገባ ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር ወ/ሮ ስንታየሁ ማሞ በበኩላቸው የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም ሲጀመር አንድም ተማሪ በምግብ እጥረት ምክንያት ከትምህርት መቅረት የለበትም በሚል አላማ የትምህርት ቤት የምገባ ስርዓት መጀመሩን ገልፀው አሁን ላይ ተማሪዎችን ከመመገብ ባለፈ በምግብ ጥራትና ጠቀሜታ እንዲሁም አገልግሎት ማሻሻል ላይ መወያየታችን የምገባ ሥርዓቱ ምን ያህል ከፍ እንዳለ ያሳያል ብለዋል:: አክለውም ይህንን የምገባ ስርዓት በ2018 ትምህርት ዘመን በተሻለ ትግበራ ለማስቀጠል ገንቢ የሆኑ ሀሳቦች በማንሳት የምገባ ሥርዓቱ የታለመለትን አላማ እንዲያሳካ ሙያዊ አስተያየት በመውሰድ ቁጥጥር ለሚያደርጉ ባላሙያዎች አቅም የሚሆን ሀሳብ ከጋራ ውይይቱ የሚጠበቅ መሆኑን አብራርተዋል:: መጋቢ እናቶችና የሚመለከታቸው ባለሙያዎችም የተጣለባቸውን ትልቅ ኃላፊነት ለመወጣት በጋራ ውይይት የተወሰነ የምግብ ዝርዝር ሳይጓደል ለተማሪዎች እንዲያቀርቡ አሳስበዋል:: በውይይቱ በምገባ ኤጀንሲ የትምህርት ቤት ስርዓተ ምግብ ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ይግዛው አየለ የተማሪዎች የምገባ ስርዓት ምግብ ዝርዝር (Menu) የያዘ ሰነድ አቅርበዋል:: በተሳታፊዎችም ግብዓት የሚሆኑ ነጥቦች ተነስተው ውይይት ተደርጎበታል:: መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
显示全部...
39👍 6
የ2018 ትምህርት ዘመን የተማሪ ምገባ ምግብ ዝርዝርን (Menu) አስመልክቶ ውይይት ተካሄደ:: (መስከረም 15/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2018 ትምህርት ዘመን የተማሪ ምገባ ምግብ ዝርዝር (Menu) አስመልክቶ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳምሶን መለሰ ፣ የምገባ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ስንታየሁ ማሞ ፣ የአዲስ አበባ ወ.ተ. ማህበር ሰብሳቢ አቶ ሐሰን ሺፋ ፣ የአዲስ አበባ ምግብ መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን እና የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ባለሙያዎች ፣ የክፍለከተማ ቡድን መሪና ባለሙያዎች እንዲሁም መጋቢ እናቶች በተገኙበት ውይይት ተካሂዷል :: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳምሶን መለሰ በውይይቱ መክፈቻ ተገኝተው የ2018 ትምህርት ዘመን የተማሪ ውጤት ለማሻሻል በከተማ አስተዳደሩና ትምህርት ቢሮ እየተሰሩ ካሉ ሥራዎች አንዱ የተማሪዎች ምገባ መሆኑን ገልፀው የተማሪዎች የምገባ ስርዓት ምግብ ዝርዝር (Menu) በትምህርት ቤቶች ወረደና ትግበራ የተጀመረ በመሆኑ የቀረበው የምግብ ዝርዝር ላይ መጨመርና መሻሻል ያለባቸውን ምግቦች ለማሻሻል የምግብ ዝርዝር ክለሳ ማስፈለጉን አብራርተዋል ::
显示全部...
24👍 4
የሚዲያ ማበልፀግና ስርጭት ዳይሬክተር ወ/ሮ የውብዳር አያሌው ድጋፍና ክትትሉ በ2018 ትምህርት ዘመን የሚሰጥ ትምህርት በሬዲዮን አጀማመርና አተገባበር ምን እንደሚመስል ለማየትና በሚያጋጥሙ ክፍተቶች ላይ ድጋፍ ለማድረግ እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡ ትምህርት በሬዲዮ መምህሩ ክፍል ውስጥ የሚያስተምረውን የትምህርት ይዘት በማገዝ ትምህርቱን የበለጠ ተጨባጭና ተማሪዎች በቀላሉ እንዲረዱት የራሱ ሚና እንዳለው የገለጹት ዳይሬክተሯ ድጋፍና ክትትሉ የሬዲዮ ትምህርት አተገባበር በመንግስትና በግል ትምህርት ቤቶች ያለውን አካሄድ በማየት የታዩ ጉድለቶችን ለማረም እንዲቻል በቂ መረጃ የምናገኝበት ይሆናል ብለዋል፡፡ አክለውም በድጋፍና ክትትሉ የሚሳተፉ ባለሙያዎች ኃላፊነት በተሞላው አግባብ ስራውን እንዲያከናውኑና ለቀጣይ ስራችን መነሻ የሚሆን ግኝት በግብረመልስ አደራጅተው እንዲያቀርቡ ይጠበቃል ብለዋል፡፡ የትምህርት በሬዲዮ ፕሮግራም ስርጭት ጣቢያ ሀላፊ አቶ አብይ ተፈራ እና የአፋን ኦሮሞ ትምህርት በሬዲዮ ፕሮግራም ስርጭት ቡድን መሪ በሆኑት አቶ ሳኔሳ ነጋሹ አማካኝነት በሁለቱም ቋንቋዎች ድጋፍና ክትትል የሚደረግበት ቼክ ሊስት ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል :: በድጋፍና ክትትል ስራው ከ11ዱ ክፍለከተሞች እና ከቢሮው የተውጣጡ ባለሙያዎች እንደሚሳተፉ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፤ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
显示全部...
32👏 2
የሚዲያ ማበልፀግና ስርጭት ዳይሬክቶሬት ድጋፍና ክትትል ለሚያደርጉ ባለሙያዎች ኦረንቴሽን ሰጠ:: (መስከረም 15/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሚዲያ ማበልፀግና ስርጭት ዳይሬክቶሬት የ 2018 ትምህርት ዘመን 1ኛ ሩብ ዓመት ትምህርት በሬዲዮ አጀማመር እና አተገባበርን በተመለከተ ድጋፍና ክትትል ለሚያደርጉ ባለሙያዎች ኦረንቴሽን ሰጥቷል:: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ ቢሮው ትምህርትን በቴክኖሎጂ በማስደገፍ ለማስተማር በርካታ ስራዎች ሲሰራ መቆየቱን ጠቁመው የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል በቢሮው ታቅደው እየተሰሩ ካሉ ተግባራት መካከል ደግሞ የትምህርት በሬዲዮ አንዱና ዋንኛው በመሆኑን ተናግረዋል፡፡ አቶ ዲናኦል በሁሉም የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች ትምህርት በሬዲዮ ስርጭት ማስተግበር ግዴታ መሆኑን አንስተው ይህን ተግባራዊ በማያደርጉ ትምህርት ቤቶች ላይ ተገቢውን ማስተካከያ ማድረግ እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም ትምህርት በሬዲዮን ተደራሽ ለማድረግ የትምህርት አመራሩ መምህራን ሱፐርቫይዘሮችና የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ተሳትፎ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡
显示全部...
14🏆 1
显示全部...
8👍 1
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ በበኩላቸው 38ኛውን የዓለም ቱሪዝም ቀንን ምክንያት በማድረግ ተንቀሳቃሽ ኤግዚቢሽን መዘጋጀቱን ገልጸው ተማሪዎች የሀገራቸዉን ታሩክ እንዲያውቁ እንዲረዱና እንደ ሀገር እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎችን በማወቅ ለሌላው እንዲያሳውቁ ትልቅ እድል የሚፈጥር መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ሀላፊው አክለዉም በትምህርት ቤቶች የሚገኙ ክበባት እንዲጠናከሩም መደላደልን ይፈጥራል ብለዋል፡፡ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
显示全部...
16👍 5
38ኛውን የዓለም ቱሪዝም ቀንን ምክንያት በማድረግ ተንቀሳቃሽ ኤግዚቢሽን በዳግማዊ ሚኒሊክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከፈተ፡፡ (መስከረም 15/2018 ዓ.ም) በኤግዚቢሽኑ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ላይ የቱሪዝም ሚኒስትር ክብርት ሰላማዊት ካሳ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ክቡር ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ መኔጅመንት አባላት ፣ ተማሪዎች ፣ መምህራንና ርዕሳነ መምህራን ተሳትፈዋል፡፡ በመክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት የቱሪዝም ሚኒሰትር ክብርት ሰላማዊት ካሳ አንደገለጹት የዛሬ ተማሪዎች የነገ በሁሉም መስክ ሀገራቸውን የሚያገለግሎ ዜጎች በመሆናቸው ስለ ሀገራቸው የባህል፣ የታሪክ፣ ተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ሀብቶች እንዲያውቁ እና ሀገሩን የሚውድ ትውልድ ለመፍጠር ተንቀሳቀሽ አውደ ርዕይ እንደተዘጋጀ አንስተዋል። ዛሬ በይፋ በዳግሜዊ ሚኒሊክ ት/ቤት ለትምህርት ቤት ማህበረሰብ ለጉብኝት ያቀረብናቸው እና በቀጣዩ ሳምንታትም በጥቁር አንበሳ 2ኛ ደረጃ ተ/ቤት፣ በጄ.ታደሰ ብሩ ት/ቤት በመጨረሻም በቦሌ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለእይታ የሚቀርቡት ጠቁመዋል። ኤግዚቢሽን መዘጋጀት በመዝሙራችን የምንዘምረውን የሚዳስሱና የማይዳሰሱ የኢትዮጵያን የቱሪዝም መስህቦች እና ሀብቶች ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፤ የአገር ውስጥ ቱሪዝምን፤ የባህል ቅርስ፣ ግንዛቤ መፍጠር አንደሆነ አብራርተዋል። ይህ ዝግጅት በሚኒስቴር መስሪያቤቱ በአዲስ አበባ ት/ቢሮ እና የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን ጋር አንደተዘጋጀ ገልጸዋል።
显示全部...
33👍 1
የኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ ብፁእ አቡነ ሳዊሮስ ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ብፁህ አቡነ ዲዎስቆሮስ እንዲሁም የአ/አ አገረ ስብከት ሊቀ ዻዻስ ብፁህ አቡነ ህርያቆስ እና የመስቀል በአል አዘጋጅ ኮሚቴ በተገኙበት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና ከከተማዉ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች ጋር በበአሉ ቅድመ ዝግጅት እና በከተማዉ አስተዳደር ስለሚደረገዉ ድጋፍ ዙሪያ ተወያይተዋል ። የመስቀል ደመራ በአል መስቀል አደባባይን ጨምሮ በ 2375 ደብሮችና ቦታዎች ላይ የሚከበር መሆኑ በመጥቀስ ሃይማኖታዊ ቱፊቱን እና ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ በደመቀና ባማረ መልኩ እንዲከበር የከተማዉ አስተዳደር ከማእከል እስከ ወረዳ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን በመግለፅ አባቶች እና የኮሚቴዉ አባላት እየተረገ ላለዉ ድጋፍ ምስጋናቸዉን አቅርበዋል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዉይይቱ የበአሉ ዋና ባለቤትና በአሉን የምትመራዉ ፣ የምታስተባብረዉ የኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ብትሆንም የመስቀል ደመራ በአል ከፍተኛ ቁጥር ያለዉ ህዝብ በአደባባይ የሚያከብረዉ የአገር ሀብት ፣የከተማችን ድምቀት ፣ የቱሪዝም መስህብ ነዉ ያሉ ሲሆን ሃይማኖታዊ ቱፊቱን እና እሴቱን በጠበቀ መልኩ በድምቀት እንዲከበር፣ አብሮትን በሚያጠናክር መልኩ እና በሰላም እንዲጠናቀቅ ለሌሎችም የአደባባይ ክብረ በአላት የሚያደርገዉን ድጋፍ የከተማዉ አስተዳደር እያደረገ ይገኛል ብለዋል ። (መስከረም 14/2018 ዓ.ም) መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
显示全部...
58👍 13👎 3👏 2
የስርአተ ትምህርት ማበልጸጊያና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዘንድሮ ለ20ኛ ጊዜ ለሚከበረው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በተዘጋጀ መሪ እቅድ ዙሪያ ኦረንቴሽን ሰጠ። (መስከረም 14/2018 ዓ.ም) ኦረንቴሽኑ ለክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት የስርአተ ትምህርት ትግበራ አስተባባሪዎች የተሰጠ ሲሆን በመርሀግብሩ የስርአተ ትምህርት ማበልጸጊያና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ታለማ መሪ እቅዱን አቅርበው ውይይት ተካሂዷል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርአተ ትምህርት ማበልጸጊያና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ታለማ ዘንድሮ ለ20ኛ ጊዜ የሚከበረውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በትምህርት ሴክተሩ በድምቀት ለማክበር ከወዲሁ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን መሪ እቅዱን ባቀረቡበት ወቅት ገልጸው ክፍለ ከተሞች በቀረበው እቅድ መነሻ የራሳቸውን እቅድ በማዘጋጀት ቀኑ በየትምህርት ተቋማቱ በድምቀት እንዲከበር መስራት እንደሚገባቸው አመላክተዋል። 20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ ትምህርት ተቋማት ህገመንግስቱን እና የፌደራል ስርአቱን መሰረት ያደረገ የተማሪዎች የጥያቄና መልስ ውድድርን ጨምሮ በተለያዩ መርሀግብሮች እንደሚከበር ተገልጿል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
显示全部...
30👍 4👏 3
የቢሮው የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የዘርፉን የ2017ዓ.ም አፈጻጸም እና የ2018 ዓ.ም እቅድ ገመገመ። (መስከረም 14/2018 ዓ.ም) በመርሀግብሩ የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት የዘርፉ አስተባባሪዎች እና የፈተና ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን በፕሮግራሙ የተመረጡ ክፍለ ከተሞች ሪፖርት እንዲሁም የዳይሬክቶሬቱ የ2017ዓ.ም አፈጻጸም እና የ2018 ዓ.ም እቅድ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ በለጠ ንጉሴ በ2017 ዓ.ም የበጀት አመት ለተማሪዎች ስታንዳርዱን የጠበቀ የብቃት መለኪያ በማዘጋጀት ፈተና እንዲሰጥ ከማድረግ ባሻገር ውጤቱን በመተንተን ለሚመለከተው ባለድርሻ አካል ተደራሽ ማድረግን ጨምሮ የተለያዩ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸው የዛሬው ውይይት በዘርፉ የተከናወኑ ተግባራትን በመገምገም በ2018ዓ.ም የትምህርት አመት የተሻለ ስራ ለመስራት የሚያስችል መሆኑን አመላክተዋል። የቢሮው የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ቡድን መሪ አቶ ተሾመ በበኩላቸው በ2017 ዓ.ም የትምህርት አመት የነባር እና አዳዲስ የ6ኛ፣8ኛ እና 12ኛ ክፍል አስፈታኝ ትምህርት ቤቶችን መረጃ በማደራጀት እና የተመዘገቡ ተማሪዎችን ብዛት በማጥራት ፈተናውን በአግባቡ እንዲወስዱ መደረጉን ገልጸው በ2018 ዓ.ም የዘርፉን እቅድ በማዘጋጀት ወደ ተግባር መገባቱን አስታውቀዋል። በውይይቱ ማጠቃለያ ከቢሮ ጀምሮ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ በ2017 ዓ.ም በዘርፉ የነበሩ አፈጻጸሞችን በጥንካሬ እና በድክመት በመገምገም በ2018 ዓ.ም የተሻለ ስራ ለመስራት ከወዲሁ በቂ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ አቅጣጫ ተቀምጧል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
显示全部...
18
የትምህርት ግብዓት ፍላጎት አቅርቦትና ስርጭት በግብአት አቅርቦትና ስርጭት ዘርፍ ላይ የተከናወኑ ሥራዎች ሪፖርት በአቶ አሸናፊ ደጀኔ እንዲሁም ዳይሬክቶሬቱ በምገባ ዘርፍ ያከናወናቸው ተግባራት በአቶ ተክለማርቆስ  ዳኘ ቀርቦ የተከናወኑ ሥራዎች ሪፖርት እና የድጋፍና ክትትል ግብረመልስ ውጤት ላይ በተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል :: በውይይቱ የክፍለከተማ የዘርፉ ቡድን መሪዎች እና ባለሙያዎች እንዲሁም የዳይሬክቶሬቱ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል :: መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
显示全部...
15
የትምህርት ግብአት አቅርቦትና ስርጭት ዳይሬክቶሬት የ1ኛ ሩብ ዓመት ሥራ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ :: (መስከረም 14/2018 ዓ.ም) የትምህርት ግብአት አቅርቦትና ስርጭት ዳይሬክቶሬት የዳይሬክቶሬቱን የ2018 ትምህርት ዘመን የዝግጅት ምዕራፍ ሥራ አፈፃፀም እና 1ኛ ሩብ ዓመት ሥራ አፈፃፀም ላይ የተደረገ ድጋፍና ክትትል ግብረ መልስ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል :: የትምህርት ግብአት አቅርቦትና ስርጭት ዳይሬክተር ወ /ሮ ምስራቅ ብርሀነመስቀል በውይይቱ ላይ በመገኘት እንዳሉት በ 1ኛ ሩብ ዓመት በዳይሬክቶሬቱ የተሰሩ ሥራዎችን ውጤታማነት ለማስጠበቅ ግምገማ በማድረግ እና አቅጣጫ እየሰጠን ስናከናውን ቆይተናል ሲሉ አብራርተው : አሁንም በነበረን የስራ አፈፃፀም ላይ በጋራ የምናደርገው ውይይት የትምህርት ተሳትፎና ውጤታማነትን ማረጋገጥ የሚያስችል ቁመና ለመያዝ አቅም ይፈጥርልናል ብለዋል :: ዳይሬክተሯ አክለውም የሚቀርቡ ሪፖርቶች ከአምና የተሻለ ጥንካሬዎችን ለማስቀጠል ብሎም የታዩ ጉድለቶች እንዳይደገሙ ለማረምና በቼክሊስቱ በታየው ውጤት መሰረት ቀጣይ ስራችንን በምን መልኩ መስራት አለብን የሚለው ላይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያስችለናል ብለዋል :: የውይይቱ ተሳታፊዎችም ቀጣይ ስራችንን በስኬት ለማጠናቀቅ የሚያስችል ግንዛቤ እንደሚፈጥር በማሰብ በውይይቱ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ አሳስበዋል ::
显示全部...
19👍 1🔥 1😁 1
የትምህርት ግብዓት ፍላጎት አቅርቦትና ስርጭት በግብአት አቅርቦትና ስርጭት ዘርፍ ላይ የተከናወኑ ሥራዎች ሪፖርት በአቶ አሸናፊ ደጀኔ እንዲሁም ዳይሬክቶሬቱ በምገባ ዘርፍ ያከናወናቸው ተግባራት በአቶ ተክለማርቆስ  ዳኘ ቀርቦ የተከናወኑ ሥራዎች ሪፖርት እና የድጋፍና ክትትል ግብረመልስ ውጤት ላይ በተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል :: በውይይቱ የክፍለከተማ የዘርፉ ቡድን መሪዎች እና ባለሙያዎች እንዲሁም የዳይሬክቶሬቱ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል :: መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
显示全部...
照片不可用在 Telegram 中显示
ማስታወቂያ ለፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት መምህርነት የተመዘገባችሁ መምህራን እና የትምህርት ቤት ዳይሬክተሮች ፤ ለፈተና የተመረጣችሁ ዝርዝራችሁን በተጠቀሰው ሊንክ፤  ለመምህራን፤ https://sbs.moe.gov.et/career/check-status  ለር/መምህራን፤ https://sbs.moe.gov.et/directors/check-status በመግባት ማየት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን የፈተና ቀን ወደፊት የሚገለፅ ይሆናል። ትምህርት ሚኒስቴር
显示全部...
30👎 8