ch
Feedback
Addis Ababa Education Bureau

Addis Ababa Education Bureau

前往频道在 Telegram

ይህ ቻናል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቴሌግራም ቻናል ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የተከናወኑ እንዲሁም ሀገራዊ ፣ አህጉራዊ እና አለማቀፋዊ የትምህርት መረጃዎች ተደራሽ የሚደረጉበት ነው፡፡

显示更多
2025 年数字统计snowflakes fon
card fon
150 232
订阅者
无数据24 小时
+677
+34630
帖子存档
ኢትዮዽያ ችላለች! (መስከረም 4/2018 ዓ.ም) ኢትዮዽያ የድል አድራጊዎች ፣ የአሸናፊዎች ምድር ! መላዉ አዲስ አበባ ለዳግማዊዉ የአድዋ ታላቅ ድል ክብር ከሌሊት አንስቶ ወደ መስቀል አደባባይ በከፍተኛ የድል አድራጊነት ስሜት በነቂስ እየተመመ ይገኛል። #ሕዳሴ #GERD #Ethiopia #AddisAbaba. ከንቲባ አዳነች አቤቤ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
显示全部...
48👎 11🤣 9👏 5😁 3🥰 1
照片不可用在 Telegram 中显示
150K followers Thank you! (መስከረም 3/2018 ዓ.ም) መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
显示全部...
56👍 37👎 8
照片不可用在 Telegram 中显示
50K followers Thank you! (መስከረም 3/2018 ዓ.ም) መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
显示全部...
照片不可用在 Telegram 中显示
50K followers Thank you! (መስከረም 3/2018 ዓ.ም) መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
显示全部...
😁 1
照片不可用在 Telegram 中显示
የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት ነገ ይፋ ይሆናል። (መስከረም 3/2018 ዓ.ም) በ2017 የትምህርት ዘመን የተሰጠው የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት በነገው ዕለት ይፋ ይሆናል። የትምህርት ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፤ የፈተና ውጤቱን አስመልክቶ በነገው ዕለት ከ10 ሰዓት ጀምሮ ለመገናኛ ብዙሃን ማብራሪያ ይሰጣል። የ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ መሰጠቱ ይታወሳል። በተፈጥሮ ሳይንስና በማህበራዊ ሳይንስ በአጠቃላይ 608 ሺህ 742 ተማሪዎች ተመዝግበው 581 ሺህ 905 ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸው ይታወሳል። ከተፈታኞቹ መካከልም 134 ሺህ 828 ተማሪዎች በበይነ መረብ የተፈተኑ ሲሆን፤ ቀሪዎቹ ተማሪዎች ደግሞ በወረቀት ተፈትነዋል። ፈተናው በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በተቋቋሙ 216 የመፈተኛ ማዕከላት በበይነ መረብ በአራት ዙር እንዲሁም በወረቀት በሁለት ዙር ተሰጥቷል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
显示全部...
155🖕 13🥰 6🤔 6😁 4🙏 4
ትምህርት ቤቶች እንዲሰጥ መደረጉን የገለፁት አቶ ሰማሀኝ በቀን መማር ያልቻሉትንም በማታ ትምህርት እንዲከታተሉ ሰፊ ሥራ መሰራቱን ገልፀዋል :: ትምህርት ቤት ደረጃን ለማሳደግ በያዝነው አመታዊ እቅድ መሰረት ትኩረት ሰጥተን ሰፊ ሥራዎች አከናውነናል ሲሉ የገለፁት ትምህርት ፅ /ቤት ኃላፊው ብቁ መምህራንን ከማፍራት አንፃርም ለመምህራንና ሱፐርቫይዘሮች ስልጠና መሰጠቱን አብራርተዋል :: 32 ኛው የትምህርት ጉባኤም ያሉብንን ጉድለቶች በማየት ቀጣይ ስራችንን አጠናክረን ለማከናወን አቅም ይፈጥርልናል ብለዋል :: በጉባኤው ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፈቃዱ ባስተላለፉት መልእክት ቂርቆስ ክፍለ ከተማ በ 2017 የትምህርት ዘመን ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡን አስታውሰው የተገኘው ውጤት በብዙዎች ጥረት የተገኘ መሆኑን በመረዳት የትምህርት አካላት ሁሉ በቀጣይም በሂሳብና እንግሊዘኛ ትምህርት ላይ ሰፊ ትኩረት በመስጠት በትብብር መሥራት እንዲሁም በ2018 የትምህርት ዘመንም የተማሪዎች ውጤት በማላቅ ፣ መጠነ ማቋረጥን በመቀነስ ወደ ቀጣይ ክፍል የሚያልፉ ውጤታማ ተማሪዎች ቁጥር በማሳደግ ረገድ ትልቅ ሥራ የሚጠበቅበት ዓመት መሆኑን ልብ ማለት ይገባል ብለዋል:: አቶ ጥላሁን አያይዘውም  የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ውጤት ለማሻሻል ያላችሁን አቅም አሟጣችሁ በመጠቀም የተማሪ ውጤታማነትን በማሻሻል የተቀመጡ ስትራቴጂክ ውጤቶችን በተግባር ላይ በማዋል እንዲሁም መምህራንን ሱፐርቫይዘሮችንና የትምህርት አመራሩን ማብቃት ሰላማዊ መማር ማስተማር ሥራ ላይ ትኩረት ሰጥታችሁ መስራት ይገባል ብለዋል። በጉባኤው የክፍለ ከተማው ትምህርት ፅህፈት ቤት የ2017 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀምና  የ2018 ዓ.ም እቅድና የትኩረት አቅጣጫዎች የቀረበ ሲሆን በአመቱ የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ አካላት እውቅና ተሰጥቷል:: መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
显示全部...
39😁 4
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት  “በዕውቀት እና ክህሎት የበቃ ትውልድ በማፍራት ኢትዮጵያን የብልፅግና ተምሳሌት እናደርጋታለን!” በሚል መሪ ሀሳብ 32ኛውን የትምህርት ጉባኤ አካሂዷል፡፡ (መስከረም 3/2018 ዓ.ም) በትምህርት ጉባኤው  የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፅ /ቤት ኃላፊ አቶ አደፍርስ ኮራ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ   ፣ የክፍለ ከተማው ትምህርት ፅ /ቤት ሀላፊ አቶ ሰማሀኝ አስታጥቄ ፣ የክፍለ ከተማና ወረዳ አመራሮች ፣ የተማሪ ወላጅ ህብረት እና   የትምህርት አመራሮች ፣ መምህራን ተማሪዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በጉባኤው ተሳትፈዋል፡፡ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ /ቤት ኃላፊ አቶ ሰማሀኝ አስታጥቄ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጭት የሆነው አባይ ግድብ በይፋ በተመረቀበት ማግስት ፣ አዲስ አበባን እንደስሟ አዲስ እንዲሁም ትምህርት ቤቶችን ሳቢና ማራኪ እንዲሆኑ ያስቻለው የአዲስ አበባ ኮሪደር ልማት ሥራዎች ተጠናክረው ለስራ የዋሉበት ብሎም በትምህርት ዘርፉ ውጤታማ የሆንንበት ወቅት ላይ መገኘታችን ጉባኤያችንን ልዩ ያደርገዋል ብለዋል :: አክለውም በክፍለ ከተማው የሚሰጠውን ትምህርት ውጤታማ ለማድረግ በ2017 የትምህርት ዘመን በተቀመጠ የትኩረት አቅጣጫ መሰረት ሰፊ ሥራ መሰራቱን ገልፀው ተማሪዎችን በቅድመ አንደኛ በመካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ወደ ትምህርት ቤት ለማምጣት ሰፊ ቅስቀሳ መሰራቱን ጠቅሰው በትምህርት ዘመኑ በክፍለ ከተማው የትምህርት ሽፋን ተደራሽነት ላይ በተሰራው ስራ ትልቅ ውጤት መመዝገቡን ገልፀዋል። የትምህርት ቤቶች ደረጃ ለማሻሻል ፣ ተማሪዎች ትምህርትን በጥራት እንዲያገኙ የቴክኖሎጂ ግብዓት በማሟላት እንዲሁም ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች ተገቢ ትምህርት እንዲያገኙ በሁሉም
显示全部...
25
32ኛው ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ የተቀመጡ 13 የትኩረት መስኮችን መሰረት በማድረግ በ2018 ዓ.ም የትምህርት አመት በክፍለ ከተማው የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል። የየካ ክፍለከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መገርሳ ገላና በበኩላቸው ሀገራችን የጀመረችው የብልጽግና ጉዞ ውጤታማ የሚሆነው በዕውቀት እና ክህሎት የበቃ ትውልድ በማፍራት እንደመሆኑ የጉባኤው ተሳታፊዎች የክፍለከተማውን የ2017 ዓ.ም አፈጻጸም በመገምገም በ2018ዓ.ም የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር እንዲሻሻል የሚያስቀምጡት አቅጣጫ ውጤታማ እንዲሆን የክፍለከተማው አስተዳደር አስፈላጊውን ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን አመላክተዋል። የየካ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፈይሳ ወዳጆ በክፍለ ከተማው በ2017 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 98.6% ያህሉ 50 በመቶ እና በላይ በማምጣት ወደ 7ኛ ክፍል ከመዘዋወራቸው ባሻገር 93% የሚሆኑ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች 50 በመቶ እና በላይ አስመዝግበው ወደ 9ኛ ክፍል ማለፋቸውን እና ለዚህ ውጤት መመዝገብ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ከፍተኛ አስተዋጽአ ማበርከቱን ጠቅሰው የዛሬው ጉባኤ በ2017 ዓ.ም የነበሩ አፈጻጸሞችን በመገምገም በ2018ዓ.ም የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ አቅጣጫ የሚቀመጥበት መሆኑን አስታውቀዋል። በመርሀግብሩ ማጠቃለያ በ2017 ዓ.ም በክፍለ ከተማው የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ተማሪዎች እና የትምህርት ተቋማት እንዲሁም ለበርካታ አመታት ላገለገሉ አንጋፋ መምህራን ዕውቅና ተሰቷል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
显示全部...
36👍 10👎 2
የየካ ክፍለከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት ቤት 32 ኛውን የትምህርት ጉባኤ በዕውቀት እና ክህሎት የበቃ ትውልድን በማፍራት ኢትዮጵያን ተምሳሌት ሀገር እናደርጋለን በሚል መሪ ቃል የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት አካሄደ። (መስከረም 3/2018 ዓ.ም) በጉባኤው የጽህፈት ቤቱ የ2017ዓ.ም አፈጻጸም እና የ2018 ዓ.ም እቅድ በመረጃና ቴክኖሎጂ ቡድን መሪው አቶ አውግቸው አበባው እንዲሁም በክፍለ ከተማው በ2017 ዓ.ም የተመዘገበ የተማሪ ውጤት ትንተና በጽህፈት ቤቱ የስርአተ ትምህርት ቡድን መሪ አቶ አዱኛው ባምላኩ እና በአፋን ኦሮሞ ሱፐርቫይዘር አቶ ዘሪሁን ለታ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ እና የጉባኤው የክብር እንግዳ አቶ ዲናኦል ጫላ በመርሀግብሩ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት ቤት ቢሮው በ2017ዓ.ም የበጀት አመት የተማሪዎች ውጤት ማሻሻልን ጨምሮ በቁልፍ ተግባራት አመላካች እና የሪፎርም ስራዎች አፈጻጸምን መሰረት አድርጎ ባካሄደው ምዘና ከፍተኛ ውጤት አስመዝግበው ዕውቅና ከተሰጣቸው ተቋማት መካከል አንዱ መሆኑን ጠቁመው የጉባኤው ተሳታፊዎች በቅርቡ በተካሄደው
显示全部...
21
显示全部...
10👍 3👎 3
"ኢትዮጵያ ትችላለች" በሚል መሪ ቃል የታላቁን ህዳሴ ግድብ የ14 ዓመት ጉዞ የሚያስቃኝ የፎቶ እና የስዕል አውደ ርዕይ በአድዋ ድል መታሰቢያ ተከፈተ፡፡ (መስከረም 3/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የታላቁን የህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ አስመልክቶ በከተማ ደረጃ በማዘጋጀት የፎቶ እና የስዕል አውደ ርዕይ በአድዋ ድል መታሰቢያ ለእይታ ክፍት አድረጓል። በዚህ በተዘጋጀዉ የፎቶ እና የስዕል አውደ ርዕይ መክፈቻ ስነስርዓት ላይ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር ዓባይ፣የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ፣ናየታላቁ የኢትዮጽያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ዋና ስራ አስፈፃሚ አረጋዊ በርሔ(ዶ/ር ፣ እና ሌሎች ከፍተኛ የፈሬደራልና የከተማ ክፍተኛ የመንግስት አመራሮች ተገኝተዋል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
显示全部...
26👎 4👏 2😁 2🥰 1
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት መስከረም 5 የሚጀምረዉን የ2018 ትምህርት ዘመንን ምክንያት በማድረግ ትምህርት ቤቶችን ፅዱ እና ማራኪ ፤ ለመማር ማስተማር ሂደት ምቹ እንዲሆኑ ለማድረግ የፅዳት ንቅናቄ አካሄደ። (መስከረም 3/2018 ዓ.ም) በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ መስከረም 5 የሚጀምረዉን የ2018 ትምህርት ዘመንን ምክንያት በማድረግ በካራ ቆሬ ቅድመ አንደኛ ፣ አንደኛ ፣ መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በዛሬዉ እለት የፅዳት ንቅናቄ ተካሄዳል። በፅዳት ንቅናቄ መርሀ ግብሩ ላይ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራርሮች ፣ ርዕሳነ መምህራን ፣ የአካባቢዉ ነዋሪዎች ፣ የፅዳት ባለሞያዎች ፣ የተማሪ መጋቢ እናቶች ተገኝተዋል። የክፍለ ከተማዉ የትምህርት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ገነነ ዘዉዴ በዚህ ወቅት ባሳለፍነዉ በጀት ዓመት በክፍለ ከተማዉ በሚገኙ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ሳምንታዊ የፅዳት ንቅናቄዎች መካሄዳቸዉን አስታዉሰዉ በዛሬዉ እለት የምናካሄደዉ የፅዳት ንቅናቄ የፊታችን ሰኞ የሚጀመረዉን የ2018 የትምህርት ዘመን ለተማሪዎች በአጠቃላይ ለመማር ማስተማር ምቹ ለማድረግ ነው ብለዋል። አቶ ዳኛቸው አበበ የክፍለ ከተማው ስራ አስኪያጅ ፅህፈት ቤት ሀላፊ በበኩላቸው ተማሪዎች በፅዱ አካባቢ የመማር መብቶቻቸውን ለማስጠበቅ ሰፊ ስራ መሰራቱን ገልፀው በትምህርት ቤቶች የምናካሄደው ሳምንታዊ የፅዳት ንቅናቄ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ መግለጻቸዉን ከክፍለ ከተማው ያገኘነው መረጃ ያሳያል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
显示全部...
32😁 1
በባልቻ አባነብሶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የፅዳት ዘመቻ ንቅናቄ ተካሄደ። (መስከረም 3/2018 ዓ.ም) በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 በሚገኘው ባልቻ አባነብሶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት "ጽዱ እና ውብ በሆነ ስፍራ የመማር መብት አለኝ!" በሚል መሪ ሀሳብ የፅዳት ዘመቻ ንቅናቄ ተካሄዳል። ትምህርት ቤቶች የትውልድ ማነፅያ ስፍራ እንደመሆናቸው ሁሌም ፅዱ፣ ውብና ማራኪ መሆን አለባቸው ያሉት የልደታ ክፍለ ከተማ ምክትል ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አራርሳ ድሪባ ዘውትር የትምህርት ተቋማት ፅዳት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ሲሉ ገልፀዋል። በፅዳት ዘመቻው የአዲስ አበባ ከተማ የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ም/ዳይሬክተር አቶ ሳዲቅ ሽኩር እንዳሉት በከተማ አስተዳደሩ በተሠጠው አቅጣጫ መሠረት ፅዳትን ባህል ያደረገ ትውልድ እንዲሁም ውብና ለመማር ማስተማሩ ሂደት ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር የፅዳት የግንዛቤ ማስጨበጫና የፅዳት ዘመቻ ማድረግ እጅግ ወሳኝ በመሆኑ ሁሉም አካል ሀላፊነቱን መወጣት ይኖርበታል ብለዋል። በፅዳት ዘመቻው የአዲስ አበባ ከተማ የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ም/ዳይሬክተር አቶ ሳዲቅ ሽኩር ፣ የልደታ ክፍለ ከተማ ምክትል ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አራርሳ ድሪባ ፣ የልደታ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደረጄ ትሬቦ ፣ የፅዳት አባሳደሮች ፣ አርቲስቶች ፣ የክ/ከተማና የወረዳ አመራሮች ፣ ሰላም ሰራዊት ፣ የአከባቢው ነዋሪዎች፣ ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ፣ ደንብ ኦፊሰር ፣ ወጣት ማህበር ፣ ሴት ማህበር እና የፅዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ሰራተኞች መሳተፋቸዉን ከክፍለ ከተማው ያገኘነው መረጃ ያሳያል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
显示全部...
25👎 7👍 6😁 2🔥 1👌 1
显示全部...
33👍 6👎 3
በህብረት ችለናል በሚል መሪ ቃል ከ300ሺህ በላይ የመዲናዋ ነዋሪዎች የተሳተፉበት የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፕሮግራም ተካሄደ። (መስከረም 2/2017 ዓ.ም) የታላቁ የህዳሴ ግድብ መጠናቀቁን ምክንያት በማድረግ በህብረት ችለናል በሚል መሪ ቃል ከ300ሺህ በላይ የመዲናዋ ነዋሪዎች የተሳተፉበት የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፕሮግራም በመስቀል አደባባይ ተካሄደ። በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፕሮግራሙ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ፣የብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻን ጨምሮ ከ300ሺ በላይ ነዋሪዎች ተገኝተዋል። የአባይ ግድብ ኢትዮጵያዊያን በህብረት አንድ ላይ ስንቆም የማናሳካው ፕሮጀክት የማንፈፅመው ገድል እንደሌለ ለዓለም ያሳየንበት ድንቅ ታሪክ መሆኑን ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ ገልጸዋል። የሕዳሴ ግድብ ከትንሽ እስከ ትልቅ ከሀብታም እስከ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ኢትዮጵያውያን በጋራ ያሳኩት መሆኑን ያወሱት ምክትል ከንቲባው የህዳሴው ግድብ መጠናቁ ለሀገራችን ከሚሰጠው ኢኮኖሚያዊ ተጠቀሜታ ባሻገር በህብረተሰቡ ዘንድ የእርስ በእርስ ግንኙነትን ያጠናክራል ብለዋል። የኢትዮጵያውያን የላብ ፣ የደም እና የእንባ መስዋዕትነት የከፈሉበት ስለመሆኑም ማስታወስ ያሻል ያሉት አቶ ጃንጥራር የአባይ ግድብ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ለ14 ዓመታት የአዲስ አበባ ነዋሪ እና አመራሩ ላበረከተው አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
显示全部...
57👍 19👎 9👀 1
አዲስ አመትን ከወገኖቻችን ጋር ! (መስከረም 1/2018 ዓ.ም) ወትሮም እንደምናደርገዉ አዲስ አመትን በከተማችን በሚገኙ 26 የምገባ ማዕከላት ጧሪ ፣ ደጋፊ ከሌላቸዉ አቅመ ደካምች ፣ በጉብዝናቸዉ ወራት ለአገራቸዉ ዉለታ ከዋሉ አረጋዉያን ፣ የአካል ጉዳተኞች እና ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ተጋላጭ ከሆኑ ወገኖቻችንን ጋር መአድ ማጋራት አብረን አክብረናል። መልካም አዲስ አመት ፈጣሪ ኢትዮዽያንና ሕዝቦቿን ይባርክ! ከንቲባ አዳነች አቤቤ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
显示全部...
126👎 7👍 3
እንኳን ለ2018 ዓ.ም በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፤ አደረሰን በ2017 በርካታ ስኬቶች አግኝተን፣ የኢትዮጵያ መጪ ብሩህ ዘመን ገላጭ የሆነውን ታላቁን የህዳሴ ግድብ ግንባታ በማስመረቅ ወደ 2018 ዓ.ም በድል ታጅበን እየተሻገርን ነው። አዲሱ የ2018 ዓመት የእቅዶቻችንን ፍሬዎችን የምናይበት፣ አዳዲስ መልካም የተግባር ዘሮችን የምንዘራበት፤ በትጋት እና በቁርጠኝነት ለሕዝባችን የገባነውን ቃል የምንፈጽምበት አመት እንዲሆን እመኛለሁ!! መላው ኢትዮዽያዊያን ፣የከተማችን ነዋሪዎች እንኳን ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ምርቃትና ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ !! መልካም አዲስ ዓመት አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የደስታ እና የስኬት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ። በድጋሚ መልካም አዲስ ዓመት ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ
显示全部...
92👍 9👎 7
የዘንድሮውን ዘመን ስናበቃ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓቱን የጠበቀ እና ቀልጣፋ መሆኑን ለማረጋገጥ የነበረን ቁርጠኝነት እንደቀጠለ ነው። መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከፌደራል አገልግሎቶች ወደ ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች እየተስፋፋ ይገኛል። በአዲሱ አመት ዋዜማ በአስራ ሶስት ተቋማት አንድ መቶ ሰባት የከተማ አስተዳደር አገልግሎቶችን የሚሰጠውን የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ተመልክተናል። ይኽ አገልግሎት አሰጣጥን የመልካም አስተዳደር የድንጋይ ማዕዘን የማድረግ እና ዜጎች ወቅቱን የጠበቀ፣ ግልጽ እና ተደራሽ አገልግሎት የማረጋገጥ ቁርጠኝነታችንን የሚያንፀባርቅ ነው። በአዲሱ አመት ገና ብዙ ማዕከላት ይኖሩናል። በድጋሚ መልካም አዲስ አመት። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
显示全部...
66👍 7😴 3👎 2😁 2
照片不可用在 Telegram 中显示
መልካም አዲስ ዓመት BARA HAARAA GAARII! HAPPY NEW YEAR (ጳጉሜ 5/2017 ዓ.ም) እንኳን ለ2018 የትምህርት ዘመን አደረሳችሁ! BAGA BARA BARNOOTAA 2018 TIIN ISIN GA'E! አዲሱ ዓመት የሰላም ፣ የጤና ፣ የፍቅር ፣ የስኬትና የብልፅግና እንዲሆንልዎ እንመኛለን! BARRI HAARAAN:- KAN NAGAA, KAN FAYYAA, KAN JAALALAA, KAN MILKAA'INAA FI KAN BADHAADHINAA AKKA ISINIIF TA'U HAWWINA! መልካም በዓል! AYYAANA GAARII! መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
显示全部...
84👍 25👎 4