2025 年数字统计

194 402
订阅者
-5024 小时
-1767 天
-81830 天
帖子存档
照片不可用在 Telegram 中显示
በባለፈው አመት የአለማችን ግዙፎቹ የጦር መሳሪያ አምራቾች ገቢ በ5.9% መጨመሩ ተነገረ።
በአለማችን ላይ እየበዛ የመጣውን ጦርነት ተከትሎ የምድራችን ትላልቆቹ የጦር መሳሪያ ሻጮች ገቢ ባለፈው አመት በ5.9 በመቶ ጨምሯል ተብሏል።
የስቶኮልም የሰላም ጥናት ተቋም 100 የሚሆኑ የአለማችን ትላልቆቹ የጦር መሳሪያ አምራቾች ገቢ በ2024 ወደ 679 ቢሊየን ዶላር መድረሱንና ይህም የተመዘገበ ከፍተኛው ገቢ መሆኑን ገልጿል።
ሃገራት ከፍተኛ የሚባል በጀትን በመከላከያ ላይ ማውጣታቸውም የድርጅቶቹ ገቢ እንዲጨምር ምክንያት ሆኗል።
አብዛኞቹ የጦር መሳሪያ አምራች ድርጅቶች በአሜሪካና አውሮፓ የሚገኙ ናቸው።
ዘገባው የአሶሽየትድ ፕረስ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
😢 66❤ 47🤔 9
照片不可用在 Telegram 中显示
#Update
የጃኮብ ዙማ ልጅ ዱዱዚሌ ዙማ ከሳምንታት በፊት 17 ወንዶችን ለሩሲያ ጦርነት መልምላለች ከተባለች በኋላ ከፓርላማ አባልነቷ በገዛ ፈቃዷ ለቃለች።
በአባቷ ጃኮብ ዙማ የሚመራው ፓርቲ ለሩሲያ በተመለመሉ ወጣቶች ዙሪያ ምንም ተሳትፎ የለኝም ያለ ሲሆን ለወጣቶቹ ቤተሰቦች ድጋፍ አደርጋለሁ ብሏል።
ዱዱዚሌ ዙማ ወጣቶቹን ለሩሲያ መመልመሏን ያስታወቀችውና ክስ የመሰረተችው እህቷ ስትሆን ፖሊስም ምርመራ መጀመሩን አስታውቋል።
ዘገባው የዘ ኢንዲፔንደንት ነው።
👋 | @tikvahethmagazine
❤ 33👍 13🤣 4
照片不可用在 Telegram 中显示
የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ በሃገራቸው ያሉ ቤተክርስቲያናትን ወቅሰዋል።
የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ አንዳንድ ቤተክርስቲያናት እምነትን ከማስተማር ይልቅ ዜጎችን መበዝበዝ ተያይዘዋል በማለት እያደገ የመጣውን የቤተክርስቲያን ቁጥር ተችተዋል።
ባለፈው ነሐሴ ወር ሩዋንዳ የጤና እና ደህንነት መመሪያዎች አላሟሉም ያለቻቸውን 4000 ቤተክርስቲያናት ዘግታለች።
ሩዋንዳ የቤተክርስቲያን ቁጥር እየጨመረ ያለው አንዳንድ የቤተክርስቲያን መስራቾች የግል ጥቅማቸውን ለመጨመር በማሰባቸው ነው ብላለች።
በተጨማሪም ሐሰተኛ ትምህርቶችን በማስፋፋት የግል የፋይናንስ ጥቅማቸውን የሚያስቀድሙና ከአባሎች ንብረት የሚወስዱ መስራቾች በዝተዋል ነው የተባለው።
ፕረዚዳንት ፖል ካጋሜ፥ የሃይማኖት ተቋማት ትርፍ ከመፈለግ በትምህርት፣ ጤና እና ማኅበረሰባዊ ለውጥ ላይ ትኩረት ማድረግ አለባቸው ሲሉ ገልጸዋል።
ዘገባው የ DW ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 168👍 64👏 31🤔 4🙏 3🤷♂ 2🤝 2🤣 1
照片不可用在 Telegram 中显示
ያልተመጣጠነው የደሞዝ ልዩነት
በአለም አቀፍ ደረጃ የድርጅቶች ዋና ስራ አስፈፃሚዎች ከ2019 ወዲህ ክፍያቸው በ50 በመቶ ሲጨምር የመደበኛ ሰራተኞች ክፍያ ግን የጨመረው በ0.9% ብቻ ነው።
አማካይ የድርጅቶች ዋና ስራ አስፈፃሚዎች ክፍያ በ2019 ከነበረበት 2.9 ሚሊየን ዶላር በ2024 4.3 ሚሊየን ዶላር ደርሷል።
አየርላንድ እና ጀርመን ለዋና ስራ አስፈፃሚዎች ከፍተኛ አማካይ ክፍያ የሚከፈልባቸው ሃገራት ሲሆኑ በ2024 በአማካይ በቅደም ተከተል 6.7 ሚሊየን ዶላርና 4.7 ሚሊየን ዶላር አመታዊ ክፍያ ይከፈላል።
በደቡብ አፍሪካ ይህ አማካይ የዋና ስራ አስፈፃሚዎች ክፍያ 1.6 ሚሊየን ዶላር ይደርሳል።
በየጊዜው በድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚዎች እና በመደበኛ ሰራተኞች መካከል ያለው የደመወዘ እድገትና ክፍያ እየሰፋ የመጣ ሲሆን እንደ ኦክስፋም ያሉ ድርጅቶች በነዚህ ሃብታሞች ላይ የሚጣለው ታክስ እንዲጨምር ጥሪ እያደረጉ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
❤ 69😢 19👍 18👎 10
照片不可用在 Telegram 中显示
መቀመጫውን በቻይና ያደረገ ባንክ በቢሾፍቱ ለሚገነባው ግዙፍ ኤርፖርት የፋይናንስ ድጋፍ ሊሰጥ ነው።
ቻይና መቀመጫውን ያደረገው ባንክ ስሙ ያልተገለፀ ሲሆን ለኤርፖርቱ ግንባታ 500 ሚሊየን ዶላር ፋይናንስ ይሰጣል ተብሏል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው በሞሮኮ እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ ኢንቨስትመንት ፎረም የባንኩን ስም ሳይጠቅሱ ፋይናንሱ መገኘቱን የተናገሩ ሲሆን ይህም አለም አቀፍ የፋይናንስ ሰጪዎች በፕሮጀክቱ ላይ ለመሳተፍ ያላቸውን ፍላጎት ያሳየ ነው ብለዋል።
ከ10 ቢሊየን ዶላር በላይ ይፈጃል ተብሎ የሚጠበቀው የቢሾፍቱ ኤርፖርት ግንባታን በተመለከተ ከመካከለኛው ምስራቅ፣ ቻይና፣ ህንድ፣ አውሮፓና ሰሜን አሜሪካ እየተደረጉ ያሉ የፋይናንስ ማሰባሰብ ሂደቶች ጥሩ ላይ መሆናቸውንም ዋና ስራ አስፈፃሚው ገልፀዋል።
አቶ መስፍን ጣሰው 90 በመቶው የአየር መንገዱ ገቢ በውጪ ምንዛሬ መሆኑን አንስተው በኢትዮጵያ የተደረገው የውጪ ምንዛሬ ፖሊሲ ለውጥ በደንብ ተፅዕኖ እንዳላሳደረባቸውና የአዲሱን ኤርፖርት ኢንቨስትመንት በተመለከተ የውጪ ምንዛሬ ስጋት እንደሌለ ተናግረዋል።
በሁለት ዙር ግንባታው ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቀው የቢሾፍቱ ኤርፖርት ግንባታን በተመለከተ ከዚህ ቀደም አሜሪካም ፍላጎቷን መግለጿ ይታወሳል።
አህጉራዊው የአፍሪካ ልማት ባንክም ለኤርፖርቱ ግንባታ ከሚያስፈልገው 10 ቢሊየን ዶላር ውስጥ 8 ቢሊየን ዶላሩን እንዲያሰባስብ ኃላፊነት እንደተሰጠው የሚታወስ ሲሆን 500 ሚሊየን ዶላርም ፋይናንስ ለማድረግ መወሰኑ ይታወሳል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኤርፖርቱ በሚሰራበት ቦታ ያሉ ሰዎችን ወደ ሌላ ቦታ ለማዘዋወር 350 ሚሊየን ዶላር አውጥቶ ግንባታዎችን ያከናወነ ሲሆን በዚህ ወርም ግንባታው ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል።
የመጀመሪያ ዙር ግንባታው በ2022 የሚጠናቀቀው ኤርፖርት ሙሉ ለመሉ ሲጠናቀቅ ከ110 ሚሊየን በላይ መንገደኞችን በአመት ማስተናገድ ይችላል።
ዘገባው ከኢኮፊን ኤጀንሲ የተገኘ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
照片不可用在 Telegram 中显示
‼️ ይፍጠኑ
‼️ በመሀል ሳር ቤት ቫቲካን ኢምባሲ አካባቢ ‼️
# ቴምር ሪልስቴት ከ8 በላይ ሳይቶችን ጥንቅቅ አድርገን አስረክበን አሁን ደግሞ ሳርቤት ቫቲካን ኢምባሲ አካባቢ ለሽያጭ ያወጣናቸው አፓርትመንቶች
➤ 100% ለሚከፍሉ 35% ቅናሽ
👉 ባለ 2 መኝታ = 81ካሬ = 6ሚሊዮን
👉 ባለ 2 መኝታ = 106ካሬ = 7.9ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 139ካሬ = 10.3ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 152ካሬ = 11.3ሚሊዮን
➤ በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ)
👉 81ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 9.3ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (1.8ሚሊዮን)
👉 106ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 12.1ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (2.4ሚሊዮን)
👉 139ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 15.9ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (3.1ሚሊዮን)
⩩ ቀሪውን 80%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት።
⩩ 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፤ ከከፈሉት ላይ ከ15 -25% ቅናሽ አዘጋጅተናል።
ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን
☎️+251980782850
❤ 14
照片不可用在 Telegram 中显示
መረጃ የሚፈለግበትን መንገድ የቀየረው ኤ.አይ
ከጥቂት ዓመታት በፊት ሰዎች ስለሆነ ነገር መረጃ ሲፈልጉ እንደ ጎግል ወይም ዩቲዩብ ያሉ መተግበሪያዎችን መጠቀማቸው የተለመደ ነበር። ከ3 አመታት ወዲህ ግን ሰዎች መረጃ ሲፈልጉ ወደ ቻት ጂፒቲ መሰል አማራጮች ማምራት ይቀናቸዋል።
በ2022 በተዋወቀ በወራት ውስጥ 100 ሚሊየን ሳምንታዊ ተጠቃሚዎች የደረሰው ቻት ጂፒቲ በአሁኑ ወቅት ብዙ ተጠቃሚዎች ካላቸው የዓለማችን መተግበሪያዎች አንዱ መሆን ችሏል።
በ2025 በአሜሪካ ከሚገኙ አዋቂዎች መካከል 34 በመቶው ቻት ጂፒቲ ሲጠቀሙ፤ እድሜያቸው ከ30 ዓመት በታች ከሆኑት መካከል 58 በመቶዎቹ ሞክረውታል።
60 በመቶ የሚሆኑት አሜሪካውያን መተግበሪያውን መረጃ ለመፈለግ የሚጠቀሙ ሲሆን ዕድሜያቸው ከ30 አመት በታች ከሆኑት ደግሞ 70 በመቶዎቹ ለዚሁ አገልግሎት እንደሚጠቀሙ ተገልጿል።
ለአመታት ሰዎች መረጃ ለመፈለግ ጎግልን በዋነኝነት ይጠቀሙ የነበሩ ሲሆን አሁን ግን መረጃን ለመፈለግና ነገሮች ምን እንደሆኑ ለማወቅ ሰዎች ፊታቸውን ወደ ቻት ጂፒቲ እያዞሩ ይገኛሉ።
በአሜሪካ በተሰራ ጥናት ከዚህ በፊት ጎግልን ለተለያዩ መረጃዎች ይጠይቁ ከነበሩ ሰዎች መካከል 55 በመቶዎች አሁን ቻትጂፒቲ ወይም ጄሚናይን እንደሚጠቀሙ ያሳያል።
ሰዎች አሁንም ጎግልን መጠቀም ያላቆሙ ሲሆን፥ ቀጥታ ማብራሪያ ለሚፈልጉባቸው ጉዳዮች ግን በዋነኝነት የሰው ሰራሽ አስተውሎት መተግበሪያዎችን ይጠቀማሉ።
ጎግልም ሁኔታውን ተረድቶ በመፈለጊያው ላይ "AI SUMMARY" ያካተተ ሲሆን ከሶስት አመት በፊት በሚሰራበት መንገድም እየሰራ አይደለም።
ጥናቶች፥ ለዜና ምንጮች ከጎግል መፈለጊያ የሚመጡ ፍለጋዎች በ2024 ከነበሩበት 2.3 ቢሊየን በ2025 ወደ 1.7 ቢሊየን እንደቀነሱ አሳይተው በሰው ሰራሽ አስተውሎት መተግበሪያዎች የሚደረጉ የዜና ፍለጋዎች በአንድ አመት ውስጥ ከ56% ወደ 69% መጨመራቸውን ጠቁመዋል።
በአሁኑ ወቅት ከ2.7 ቢሊየን በላይ ተጠቃሚዎች ያሉት ዩቲዩብ እንኳን በዚህ የተጠቃ ሲሆን ሰዎች ወደ ዩቲዩብ የሚያመሩት መጀመሪያ ከቻት ጂፒቲ ጋር ንግግር አድርገው ተጨማሪ የቪዲዮ ማብራሪያዎችን ሲፈልጉ ነው ተብሏል።
የሶፍትዌር መሃንዲሶችም ከቻት ጂፒቲ መምጣት ቀድሞ ይጠቀሙ የነበሯቸውን ድረ-ገፆች መጠቀም ቀንሰው ስራቸውን ከሰው ሰራሽ አስተውሎት ጋር በመተባበር እያከናወኑ ይገኛሉ።
ቻት ጂፒቲ ምንም እንኳን በሦስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ነገሮችን ባይተካም ሰዎች መረጃን የሚፈልጉበትን አዲስ መንገድ ግን አምጥቷል።
Source ፡ The Conversation
#IsItAI
#Concepthub #InterNews #EU
Via @ConceptHubeth
- Tikvah Magazine | @tikvahethmagazine
❤ 115👍 6👎 4😢 4🤯 2
照片不可用在 Telegram 中显示
በኬንያ የትልልቅ ድርጅቶች ስራ አስፈፃሚዎች ከመምህራን በ214 እጥፍ የተሻለ ክፍያ ያገኛሉ ተባለ።
የኬንያ አስር ግዙፍ ድርጅቶች ዋና ስራ አስፈፃሚዎች በአማካይ ከኬንያ መምህራን በ214 እጥፍ የተሻለ ክፍያ እንደሚያገኙ ኦክስፋም ኬንያ አስታውቋል።
ኦክስፋም አክሎም፥ ለዋና ስራ አስፈፃሚዎቹ የሚደረገው አማካይ የክፍያ ጭማሪ ከአስተማሪዎቹ የ6 አመት ደመወዝ ጋር እኩል መሆኑንም ገልጿል።
በተጨማሪ በኦክስፋም ሪፖርት በኬንያ የሚገኙ 125 ሃብታሞች ከ77 በመቶው ወይም 42.6 ሚሊየን ህዝብ የበለጠ ሃብት እንዳላቸው ተመላክቷል።
ከ2019-2023 ባለው ጊዜም 1% የሚሆኑት ሃብታሞች የሃገሪቱን ሁለት አምስተኛ ሃብት እንደያዙና የነዚህ 1% ሃብታሞች ሃብት ከቀሩት 99% አንፃር በእጥፍ ማደጉ ተነግሯል።
እነዚህ 1% ሃብታሞችም የሃገሪቱን የፋይናንስ ሃብት 78% መያዛቸው ሲነገር ከ2015 ወዲህም በከፍተኛ ድህነት የሚኖሩ ሰዎች ቁጥር በ7 ሚሊየን መጨመሩ ተነግሯል።
በ125ቱ የኬንያ ሃብታሞች የተያዘው ሃብት ወደ 100 ሽልንግ የመገበያያ ገንዘብ ቢቀየር ሙሉ የናይሮቢ ግዛትን እንደሚሸፍን የኦክስፋም ሪፖርት አሳይቷል።
ዘገባው ከ ዘ ኬንያ ታይምስ የተወሰደ ነው።
Tikvah Magazine | @tikvahethmagazine
❤ 51😢 28🤔 4👍 1👎 1
照片不可用在 Telegram 中显示
አሜሪካ ከ19 ሃገራት የመጡ ሰዎች የግሪን ካርድ ሁኔታ ላይ ምርመራ ጀመረች።
አሜሪካ በኋይት ሃውስ አቅራቢያ ጥቃት ተፈፅሞ 2 የብሔራዊ ዘቦቿ ከተገደሉ በኋላ ምርመራ ጀምራለች። የትራምፕ አስተዳደር ከ19 ሃገራት የመጡ ዜጎች የቋሚ መኖሪያ ፈቃድ/ ግሪን ካርድ ሁኔታ እንዲፈተሽ አዟል።
ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ በ2021 ከአፍጋኒስታን ወደ አሜሪካ የገባ ግለሰብ የታሰረ ሲሆን ትራምፕ ከጥቃቱ በኋላ ከአፍጋኒስታን የሚመጡ የኢሚግሬሽን ሂደቶችንም አቋርጠዋል።
የግሪን ካርዳቸው እንዲታይ የተደረጉ ሃገራት ዜጎች መካከል ከአፍጋኒስታን በተጨማሪ የኤርትራ፣ሶማሊያ፣ሊቢያ፣ ኢራን፣ የመን፣ ኩባ እና ቬኔዙዌላ ዜጎች አሉበት።
ትራምፕ ከጥቃቱ በኋላ "ከሶስተኛው አለም የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን" በቋሚነት አቆማለሁ ያሉ ሲሆን ለሃገራቸው ዜጋ ላልሆኑ ሰዎች የሚደረግን የፌደራል መንግስት ጥቅምም አቆማለው ብለዋል።
የግሪን ካርድ ሁኔታው ፍተሻ ከተካሄደ በኋላ ምን እንደሚደረግ ያልታወቀ ሲሆን በርካቶች ግን በገፍ የማባረር እርምጃ ሊወሰድ እንደሚችል ሰግተዋል።
ዘገባው የDW ነው።
Tikvah Magazine | @tikvahethmagazine
❤ 33👎 16👍 4🤷♀ 2
ዩኒሳ (UNISA) 12ኛውን የምርቃት ሥነ-ስርዓት አከናወነ።
የደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ (UNISA) የኢትዮጵያ ሪጅናል የትምህርት ማዕከል በዛሬው ዕለት 12ኛ ዙር የምርቃት ሥነ-ስርዓት በድምቀት አከናውኗል።
በዚህም 64 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት የተመረቁ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 58 ያህሉ በፒኤችዲ ዲግሪ ነተመረቁ ናቸው።
የሥነ-ስርዓቱ ላይ የዩኒሳ የዩኒሰ ፕሪንሲፓል እና ምክትል ቻንስለር ፕሮፌሰር ፑሌንግ ሌንካቡላ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የደቡብ አፍሪካ ሪፐብሊክ ኤምባሲ ተወካዮች እና የዩኒሳ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
የUNISA የኢትዮጵያ ሪጅናል ማዕከል በ2007 ዓ.ም በኢትዮጵያ እና በደቡብ አፍሪካ መንግስታት መካከል በተፈረመው የሁለትዮሽ የትብብር ስምምነት መሰረት የተቋቋመ ሲሆን እስካሁን 1,163 ተማሪዎችን (629 ዶክትሬት፣ 382 ማስተርስ) ማስመረቅ ችሏል።
አብዛኛዎቹ ተመራቂዎች የዩኒቨርሲቲ መምሀራን እና ባለሙያዎች ሲሆኑ፣ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዘርፎች በአመራርነት በማገልገል ላይ ይገኛሉ።
እንዲሁም ዩኒሳ በምርምር፣ በትምህርት ዘርፍ እና በሳይንስ ልማት ከኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በቅርበት ይሰራል።
የአፍሪካ መሪ የርቀት እና የኢ-ለርኒንግ (ODeL) ተቋም የሆነው ዩኒሳ፣ በ152ኛ ዓመቱ በመለው አሀጉሪቱ ተደራሽ እና ጥራት ያለው ትምሀርትን በመስጠት ፈር ቀዳጅ ሆኖ ቀጥሏል።
(Advertorial)
❤ 32🤣 3👎 1
照片不可用在 Telegram 中显示
‼️ ይፍጠኑ
‼️ በመሀል ሳር ቤት ቫቲካን ኢምባሲ አካባቢ ‼️
# ቴምር ሪልስቴት ከ8 በላይ ሳይቶችን ጥንቅቅ አድርገን አስረክበን አሁን ደግሞ ሳርቤት ቫቲካን ኢምባሲ አካባቢ ለሽያጭ ያወጣናቸው አፓርትመንቶች
➤ 100% ለሚከፍሉ 35% ቅናሽ
👉 ባለ 2 መኝታ = 81ካሬ = 6ሚሊዮን
👉 ባለ 2 መኝታ = 106ካሬ = 7.9ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 139ካሬ = 10.3ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 152ካሬ = 11.3ሚሊዮን
➤ በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ)
👉 81ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 9.3ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (1.8ሚሊዮን)
👉 106ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 12.1ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (2.4ሚሊዮን)
👉 139ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 15.9ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (3.1ሚሊዮን)
⩩ ቀሪውን 80%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት።
⩩ 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፤ ከከፈሉት ላይ ከ15 -25% ቅናሽ አዘጋጅተናል።
ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን
☎️+251980782850
❤ 23
照片不可用在 Telegram 中显示
ኡጋንዳ በአሁኑ ጊዜ ጦርነት ከሌለባቸው ሃገራት የሚመጡ ሰዎችን እንደ ስደተኛ እንደማትመለከታቸው አስታወቀች።
ኡጋንዳ ጦርነት ከሌለባቸው ሃገራት የሚመጡ ሰዎችን እንደ ስደተኛ እንደማታይ ስትገልጽ እነዚህ ሃገራትሞ ኢትዮጵያ ፣ ሶማሊያና ኤርትራ ናቸው ተብሏል።
ለ2 ሚሊየን የቀረቡ ስደተኞችን እያስተናገደች ያለችው ኡጋንዳ የድጋፍ እጥረት የገጠማት ሲሆን የስደተኞቹ መብዛት ሃብትና አገልግሎቷ ላይ ጫና እየፈጠረ ነው።
ኡጋንዳ ከተመድ የስደተኞች ኮሚሽን በአመት 240 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ታገኝ እንደነበር ገልፃ አሁን ይህ ድጋፍ ከ100 ሚሊየን ዶላር በታች መሆኑን ገልፃ በዚህ አመት 18 ሚሊየን ዶላር ብቻ መቀበሏን አስታውቃለች።
ኡጋንዳ ስደተኞችን መቀበሏን እንደማታቆም ገልፃ ከሶስቱ ሃገራት ከዚህ በኋላ የሚመጡ ዜጎችን ግን እንደ ስደተኛ እንደማትቀበል ገልፃለች።
በአሁኑ ጊዜ በስደተኝነት ተመዝግበው ያሉ የሶስቱ ሃገራት ዜጎች ግን በስደተኝነት ተመዝግበው ይቀጥላሉ ብላለች።
ዘገባው የ DW Africa ነው።
Tikvah Magazine | @tikvahethmagazine
🤣 112❤ 82🕊 9🤔 8😢 3
照片不可用在 Telegram 中显示
በጊኒ ቢሳው ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ተፈጸመ።
በጊኒ ቢሳው የሚገኙ ወታደራዊ አመራሮች ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት በመፈፀም የሃገሪቱን ፕሬዚዳንት ኡማሮ ሲሶኮን አስረዋል።
ወታደራዊ አመራሮቹ በሃገሪቱ ብሔራዊ ጣቢያም ቀርበው እሁድ የተካሄደውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ማገዳቸውን ገልፀዋል።
በተጨማሪ ሁሉንም የጊኒ ቢሳው ድንበሮች የዘጉ ሲሆን የሰዓት እላፊም አስቀምጠዋል።
ጊኒ ቢሳው ባለፈው እሁድ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫዋን ያካሄደች ሲሆን ውጤቱ በዛሬው እለት ይፋ ይደረጋል ተብሎ እየተጠበቀ ነበር።
ከመፈንቅለ መንግስቱ በኋላ ከፕሬዚዳንቱ በተጨማሪ የፕሬዚዳንቱ የምርጫ ተፎካካሪ የነበሩት ዲያዝ እና ለእርሳቸው ድጋፍ ሲሰጡ የነበሩት የቀድሞ የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስተር ፔሬራም ታስረዋል።
ወታደሮቹ የጦሩን አዛዥ ጀነራል ና ንታንና ምክትላቸውን ጀነራል ቱሬንም ማሰራቸው ተሰምቷል።
ጊኒ ቢሳው ከቅኝ ግዛት ነፃ ከወጣች በኋላ ባለፉት 50 አመታት 9 የመፈንቅለ መንግስት ተግባራትንና ሙከራዎችን አስተናግዳለች።
የ2 ሚሊየን ሰዎች መኖሪያዋ ሃገር ሰፊ የባህር ዳርቻ ሲኖራት ለአደንዛዥ እፅ ዝውውር የተመቸች ስትሆን ተመድም "narco-state" የሚለውን ስያሜ ሰጥቷታል።
መፈንቅለ መንግስት ፈፃሚዎቹም መፈንቅለ መንግስቱን የፈፀሙት በእፅ አዘዋዋሪዎች የሚደገፉ ፖለቲከኞችን ሴራ ለመቀልበስ እንደሆነ ገልፀዋል።
ዘገባው የቢቢሲ ነው።
- Tikvah Magazine | @tikvahethmagazine
❤ 72🤣 27👏 8💔 4👎 3🤷♂ 2
照片不可用在 Telegram 中显示
ኦፕንኤአይ በ2030 ቻትጂፒቲን ከሚጠቀሙት መካከል 220 ሚሊየን ያህሉ በክፍያ ይጠቀማሉ ብሎ እንደሚጠብቅ ገለጸ።
ኦፕንኤአይ የሰው ሰራሸ አስተውህሎት መተግበሪያውን ከሚጠቀሙ ሳምንታዊ 2.6 ቢሊየን ተጠቃሚዎች መካከል 8.5% ወይም 220 ሚሊየን ያህሉ በ2030 በክፍያ ይጠቀማሉ ብሎ እንደሚጠብቅ ገልጿል።
በአሁኑ ጊዜ የቻትጂፒቲን የፕላስ አገልግሎቱን 20 ዶላር በወር እንደዚሁም የፕሮ አገልግሎቱን በወር 200 ዶላር እየከፈሉ የሚጠቀሙ 35 ሚሊየን ተጠቃሚዎች እንዳሉም ተመላክቷል።
በዚህ አመት መጨረሻ አመታዊ ገቢው 20 ቢሊየን ዶላር ይደርሳል ተብሎ የሚጠበቀው ኦፕንኤአይ በዚህ አመት የመጀመሪያው 6 ወር ለምርምርና ለተያያዙ ወጪዎች ከ2.5 ቢሊየን ዶላር በላይ ፈሰስ አድርጓል።
ዘገባው የሮይተርስ ነው።
Tikvah Magazine | @tikvahethmagazine
❤ 33🤣 11
照片不可用在 Telegram 中显示
‼️ይፍጠኑ ሱቅ ሽያጭ ፒያሳ ላይ ጨርሰናል የመጨረሻው ሱቅ ብቻ ነው የቀረው
#ቴምርሪልስቴት
🎯 ታማኝነት እና የግንባታ ጥራት መለያችን ነው ለዚሆም ማሳያ ከ 7 በላይ ሳይቶችን በታማኝነት ሰርተን አስረክበናል.
🎯ፒያሳ አደዋዐ0 ላይ በ5.9 ሚሊየን ብር የመጨረሻው 1 ሱቅ ብቻ ቀረን
**ከፍተኛ የሆነ የኪራይ ገቢ ያላቸው ሱቆች
👉ግራውንድ ፍሎር ላይ
ጠቅላላ ዋጋ : 5.9 ሚሊየን ብር
ቅድመ ክፍያ: 2.8 ሚሊየን ብር
🏬 G +5 ሞል 4790 ካሬ ላይ ያረፈ
- 2 ቤዝመንት የመኪና ማቆሚያ
- ከሞሉ ፊት ለፊት 10,500 መኪናዎችን ማቆም የሚችል የመኪና ተርሚናል መንግሥት አስጋንብቶ እያጠናቀቀ ነው , ይህም ለሱቁ ትልቅ የሰው ፍሰት እንዲኖረው ያደርጋል.
ለበለጠ መረጃ
👇👇👇👇👇👇
+251980782850
❤ 18👍 1
照片不可用在 Telegram 中显示
Prompt Engineering? ምንድነው ?
ጄኔሬቲቭ ኤ.አይ (Generative Ai) ከተዋወቀ በኋላ ሰዎች በብዛት ኤ.አይ መተግበሪያዎችን መረጃ ለማግኘት፣ ጥያቄዎችን ለመጠየቅ፣ ዝርዝር ነገሮችን ለማሳጠርና ግልጽ ለማድረግና ለብዙ ጉዳዮች እየተጠቀሟቸው ይገኛል።
እነዚህ አገልግሎቶች በነጻ ሁሉም ሰው በብዛት የሚጠቀማቸው ቢሆኑም ለሁሉም ሰው እኩል አገልግሎት ይሰጣሉ ማለት ግን አይደለም።
ታዲያ ለሰዎች የሚሰጠው ምላሽ ላይ ያለው ልዩነት ከምን የሚመነጭ ነው ?
ኤ.አይ ሞዴሎች ለሚሰጡት ምላሽ ተገቢውን ጥያቄ፣ ወይም መረጃውን ሊረዱበት በሚችለው መንገድ ማቅረብ የተሻለ ምላሽ እንድናገኝ ይረዳናል። ይህንን ተግባር ወይም ሞያ "Prompt Engineering " ብለን እንጠራዋለን።
ግልጽ ትዕዛዞችን ማስተላለፍ መቻል፣ መጠየቅ ስለምንፈልገው ጥያቄ የተገደበ እና በአጭሩ የተብራራ መረጃ መስጠት፣ በሚሰጡን ምላሾች ላይ ተደጋጋሚ ማሻሻያዎችን መጠየቅ፥ የተሻለ ምላሽ ለማግኘት ከሚጠቅሙን መካከል ይጠቀሳሉ።
በተጨማሪም፥ በአንድ ጊዜ አንድ ርዕሰ ጉዳይ ነጥሎ (ትኩረት አድርጎ) መጠየቅ፤ ምሳሌዎችን ማቅረብ፤ መረጃዎች ቅደም ተከተላቸውን ጠብቀው አንዲቀመጡ ትዕዛዝ ማስቀመጥ፤ በምን አይነት መልኩ ምላሹን እንደምንፈልገው በግልጽ መግለጽ ጥራት ያለው ምላሽ እንድናገኝ ያግዙናል።
ምን ጥንቃቄ ማድረግ አለብን ?
ኤ.አይ ሞዴሎች ትክክለኛ ምላሽ ላይሰጡን ስለሚችሉ መረጃዎችን እንደወረደ ከመጠቀም ተቆጥበን ምላሾቹን ማንበብ፣ ደግሞ ማጣራትና ይዘቱን መፈተሽ ያስፈልጋል።
በተጨማሪም፥ ኤ.አይ ሞዴሎች አሰራራቸው ምላሽ ለመስጠት ነው። ስለዚህ የምንጠይቀው ጥያቄ ግልጽ ባይሆንም ምላሽ ይሰጣሉ።
መረጃ በሌላቸው ጉዳይ ላይም የቅዠት መረጃ (AI hallucinations) ይሰጣሉ። ስለዚህ በሚሰጡን ምላሾች ላይ ማጣራት፤ መልሶ መጠየቅ እና በሌሎች መረጃዎች መደገፍ ያስፈልጋል።
#IsItAI
#Concepthub #InterNews #EU
Via @ConceptHubeth
- Tikvah Magazine | @tikvahethmagazine
❤ 73🤣 7👍 6👎 1🤯 1
照片不可用在 Telegram 中显示
ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በአፋር ክልል የሚገኘው የኤርታሌ እሳተ ገሞራ ድጋሚ ከፈነዳ በኋላ የፍንዳታው ጭስ ቀይ ባህርን ተሻግሮ ቻይና ደርሷል።
በፍንዳታው ወቅት ጭስ እና ሰልፈር ዳይኦክሳይድ እስከ 14 ኪሎሜትር ከፍታ ድረስ የወጣ ሲሆን ጭሱ ቀይ ባህርን ተሻግሮ ሰሜን ምዕራብ ህንድ ከደረሰ በኋላ ዛሬ የህንድን አየር ክልል በመልቀቅ ወደ ቻይና እያመራ ነው ተብሏል።
ጭሱ በሰዓት ከ120-130 ኪሎሜትር በሆነ ፍጥነት እየሄደ እንደሆነ የተገመተ ሲሆን ወትሮውንም በመጥፎ አየር ለምትታወቀው ዴሊህ ከተማም ስጋት ሆኗም ነበር።
የሜትሮዎሎጂ ባለሙያዎች ግን ጭሱ ከ25,000-45,000 ጫማ ከፍታ ውስጥ እየተጓዘ በመሆኑ መሬት ላይ የአየር ብክለት ተፅዕኖው እምብዛም አይደለም ሲሉ ገልጸዋል።
የህንድ የሜትሮዎሎጂ ተቋምም የጭሱ ተፅዕኖ በዴሊህ ከተማ ላይ ብዙም አይቆይም ሲል አስታውቆም ነበር።
በዚህው የኤርታሌ ፍንዳታ ጭስ የተነሳም በርካታ በረራዎች ተሰርዘው የቆዩ ሲሆን ጭሱ የሳተላይት ተግባራትንና የበረራ ስራዎችን በጊዜያዊነት ተስተጓጉለዋል።
ኤይር ኢንዲያ፥ በጭሱ የተነሳ 11 በረራዎችን ሲሰርዝ የህንድ የሲቪል አቪየሽን ተቋምም አብራሪዎች ከጭሱ ጋር በተያያዘ የገጠማቸው ነገር ካለ ሪፖርት እንዲያደርጉ ጠይቆ፤ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶም ነበር።
የፍንዳታው ጭስም በዛሬው ዕለት የህንድ የአየር ክልልን ሙሉ ለሙሉ በመልቀቅ ወደ ቻይና እንዳመራ የህንድ የሜትሮዎሎጂ ተቋም ገልጿል።
የዘገባው ምንጮች ቢቢሲ፣ ሂንዱስታን ታይምስና ኢንዲያ ቱደይ ናቸው።
@TikvahethMagazine
❤ 102🤣 67😢 8👍 6🤯 3🙏 3🤷♂ 1
照片不可用在 Telegram 中显示
በአፍሪካ የአሜሪካ ጦር ማዘዣ በዚህ አመት በሶማሊያ መቶኛውን የአየር ጥቃት ፈፅሟል።
አሜሪካ በሳምንቱ መጨረሻ በሶማሊያ በጎሊስ ተራራማ አካባቢ የአየር ጥቃት የፈፀመች ሲሆን ጥቃቱ በዚህ አመት በሶማሊያ የፈፀመችው 100ኛ የአየር ጥቃትም ሆኗል።
ይህ የጥቃት ቁጥርም ከባለፈው አመት በእጅጉ የጨመረ ሲሆን በአሜሪካ ጦር በሶማሊያ በአንድ አመት ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የአየር ጥቃት የፈፀመችበትን የ2019 እ.ኤ.አ 63 የአየር ጥቃቶችንም በልጧል።
አሜሪካ በሶማሊያ እየፈፀመች ያለችው አልሸባብን ኢላማ ያደረገ የአየር ጥቃትም በካሪቢያን ከጀመረችው የዕፅ አዘዋዋሪዎች ጥቃት በልጧል ተብሏል።
ከመስከረም ወር መጀመሪያ ጀምሮ አሜሪካ በካሪቢያን በሚገኙ የአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪዎች ላይ 21 የአየር ጥቃቶችን የፈፀመች ሲሆን በሶማሊያ ግን በዚሁ ወቅት 28 ጥቃቶችን ፈፅማለች።
አሜሪካ ከአልሸባብ በተጨማሪ በአሁኑ ጊዜ 60 በመቶ የሶማሊያ ዜጋ ያልሆኑና 1500 ተዋጊዎች ባሉት በሶማሊያ በሚገኘው በአይኤስአይኤስ ላይ የአየር ጥቃት እየፈፀመች ትገኛለች።
ዘገባው ከStripes የተወሰደ ነው።
@TikvahethMagazine
❤ 61👎 7🤔 2
照片不可用在 Telegram 中显示
#SocialMedia
በርካታ የማኅበራዊ ሚዲያ ተቋማት በሰዎች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚያደርስ የሚያሳዩ መረጃዎች እያሏቸው በመደበቃቸው መከሰሳቸው ተሰምቷል።
ከዚህ ውስጥ ሜታ፥ ፌስቡክና ኢንስታግራም የሰዎችን የአዕምሮ ጤና እንደሚጎዱ የሚያሳየውን የራሱን ጥናት ደብቋል ተብሏል።
ሜታ፥ በ2020 ጥናት ካስጠና በኋላ ለሳምንት ፌስቡክ መጠቀም ያቆሙ ሰዎች የጭንቀት፣ የፍራቻ እና የብቸኝነት ስሜታቸው መቀነሱን ካሳወቁና የተቋሙ ምርቶች የሰዎችን፤ በተለይም የወጣቶችን የአዕምሮ ጤና እየጎዱ መሆኑ ከታወቀ በኋላ ጥናቱን መደበቁ ተሰምቷል።
ምንም እንኳን ሜታ በራሱ ያስጠናው ጥናት የማኅበራዊ ሚዲያዎቹ በሰዎች አዕምሮ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደረ መሆኑን ቢያሳይም በኮንግረስ ቀርቦ ምርቶቹ ሴቶች ህፃናትን እንደሚጎዱ በመጠን የመግለፅ አቅም እንደሌለው ገልፆ ነበር።
የሜታ ቃለ-አቀባይ "ጥናቱ የተሰራበት መንገድ ትክክል ስላልሆነ ቆሟል" ያለ ሲሆን ህፃናትን ለመጠበቅ ባለፉት 10 ዓመታት ከቤተሰቦችና ከተመራማሪዎች ጋር በመሆን ለውጥ ያመጣ ሥራ ተሰርቷል ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
ሜታ በተጨማሪ ከ13 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናት መተግበሪያውን እንዲጠቁሙ በማበረታታት እና በትምህርት ቤት እንዲጠቀሙ በመገፋፋት እንደዚሁም የህፃናት ወሲባዊ ይዘቶችን መፍትሄ ባለመስጠት ተከሷል።
ሜታ፥ ጥናቱን በመደበቁና በሌሎችም "ሞትሊይ ራይስ" በተሰኘ ተቋም ፍርድ ቤት ክስ የተመሰረተበት ሲሆን እንደ ጎግል፣ ስናፕቻት፣ ቲክቶክ ያሉትም ምርቶቻቸው የሚያደርሱትን አደጋ ሆን ብለው በመደበቅ ተከሰዋል።
የማኅበራዊ ሚዲያዎቹ የመተግበሪያቸውን ደህንነት ለመከላከል ህፃናት ላይ ለሚሰሩ ተቋማት ገንዘብ ይከፍላሉ ተብለውም ተከሰዋል።
ፍርድ ቤትም ክሱን ከመጪው የፈረንጆቹ ጥር 26 ጀምሮ ማድመጥ ይጀምራል ተብሏል።
ዘገባው የሮይተርስ ነው።
@TikvahethMagazine
❤ 61👏 9🤣 5
照片不可用在 Telegram 中显示
‼️ ይፍጠኑ
‼️ በመሀል ሳር ቤት ቫቲካን ኢምባሲ አካባቢ ‼️
# ቴምር ሪልስቴት ከ8 በላይ ሳይቶችን ጥንቅቅ አድርገን አስረክበን አሁን ደግሞ ሳርቤት ቫቲካን ኢምባሲ አካባቢ ለሽያጭ ያወጣናቸው አፓርትመንቶች
➤ 100% ለሚከፍሉ 35% ቅናሽ
👉 ባለ 2 መኝታ = 81ካሬ = 6ሚሊዮን
👉 ባለ 2 መኝታ = 106ካሬ = 7.9ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 139ካሬ = 10.3ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 152ካሬ = 11.3ሚሊዮን
➤ በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ)
👉 81ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 9.3ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (1.8ሚሊዮን)
👉 106ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 12.1ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (2.4ሚሊዮን)
👉 139ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 15.9ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (3.1ሚሊዮን)
⩩ ቀሪውን 80%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት።
⩩ 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፤ ከከፈሉት ላይ ከ15 -25% ቅናሽ አዘጋጅተናል።
ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን
☎️+251980782850
❤ 20👍 1
