TIKVAH-MAGAZINE
رفتن به کانال در Telegram
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። #ኢትዮጵያ ያግኙን +251913134524
نمایش بیشتر2025 سال در اعداد

194 396
مشترکین
-5024 ساعت
-1767 روز
-81830 روز
آرشیو پست ها
Photo unavailableShow in Telegram
መቀመጫውን በቻይና ያደረገ ባንክ በቢሾፍቱ ለሚገነባው ግዙፍ ኤርፖርት የፋይናንስ ድጋፍ ሊሰጥ ነው።
ቻይና መቀመጫውን ያደረገው ባንክ ስሙ ያልተገለፀ ሲሆን ለኤርፖርቱ ግንባታ 500 ሚሊየን ዶላር ፋይናንስ ይሰጣል ተብሏል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው በሞሮኮ እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ ኢንቨስትመንት ፎረም የባንኩን ስም ሳይጠቅሱ ፋይናንሱ መገኘቱን የተናገሩ ሲሆን ይህም አለም አቀፍ የፋይናንስ ሰጪዎች በፕሮጀክቱ ላይ ለመሳተፍ ያላቸውን ፍላጎት ያሳየ ነው ብለዋል።
ከ10 ቢሊየን ዶላር በላይ ይፈጃል ተብሎ የሚጠበቀው የቢሾፍቱ ኤርፖርት ግንባታን በተመለከተ ከመካከለኛው ምስራቅ፣ ቻይና፣ ህንድ፣ አውሮፓና ሰሜን አሜሪካ እየተደረጉ ያሉ የፋይናንስ ማሰባሰብ ሂደቶች ጥሩ ላይ መሆናቸውንም ዋና ስራ አስፈፃሚው ገልፀዋል።
አቶ መስፍን ጣሰው 90 በመቶው የአየር መንገዱ ገቢ በውጪ ምንዛሬ መሆኑን አንስተው በኢትዮጵያ የተደረገው የውጪ ምንዛሬ ፖሊሲ ለውጥ በደንብ ተፅዕኖ እንዳላሳደረባቸውና የአዲሱን ኤርፖርት ኢንቨስትመንት በተመለከተ የውጪ ምንዛሬ ስጋት እንደሌለ ተናግረዋል።
በሁለት ዙር ግንባታው ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቀው የቢሾፍቱ ኤርፖርት ግንባታን በተመለከተ ከዚህ ቀደም አሜሪካም ፍላጎቷን መግለጿ ይታወሳል።
አህጉራዊው የአፍሪካ ልማት ባንክም ለኤርፖርቱ ግንባታ ከሚያስፈልገው 10 ቢሊየን ዶላር ውስጥ 8 ቢሊየን ዶላሩን እንዲያሰባስብ ኃላፊነት እንደተሰጠው የሚታወስ ሲሆን 500 ሚሊየን ዶላርም ፋይናንስ ለማድረግ መወሰኑ ይታወሳል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኤርፖርቱ በሚሰራበት ቦታ ያሉ ሰዎችን ወደ ሌላ ቦታ ለማዘዋወር 350 ሚሊየን ዶላር አውጥቶ ግንባታዎችን ያከናወነ ሲሆን በዚህ ወርም ግንባታው ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል።
የመጀመሪያ ዙር ግንባታው በ2022 የሚጠናቀቀው ኤርፖርት ሙሉ ለመሉ ሲጠናቀቅ ከ110 ሚሊየን በላይ መንገደኞችን በአመት ማስተናገድ ይችላል።
ዘገባው ከኢኮፊን ኤጀንሲ የተገኘ ነው።
😀 | @tikvahethmagazine
Photo unavailableShow in Telegram
‼️ ይፍጠኑ
‼️ በመሀል ሳር ቤት ቫቲካን ኢምባሲ አካባቢ ‼️
# ቴምር ሪልስቴት ከ8 በላይ ሳይቶችን ጥንቅቅ አድርገን አስረክበን አሁን ደግሞ ሳርቤት ቫቲካን ኢምባሲ አካባቢ ለሽያጭ ያወጣናቸው አፓርትመንቶች
➤ 100% ለሚከፍሉ 35% ቅናሽ
👉 ባለ 2 መኝታ = 81ካሬ = 6ሚሊዮን
👉 ባለ 2 መኝታ = 106ካሬ = 7.9ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 139ካሬ = 10.3ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 152ካሬ = 11.3ሚሊዮን
➤ በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ)
👉 81ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 9.3ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (1.8ሚሊዮን)
👉 106ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 12.1ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (2.4ሚሊዮን)
👉 139ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 15.9ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (3.1ሚሊዮን)
⩩ ቀሪውን 80%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት።
⩩ 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፤ ከከፈሉት ላይ ከ15 -25% ቅናሽ አዘጋጅተናል።
ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን
☎️+251980782850
❤ 14
Photo unavailableShow in Telegram
መረጃ የሚፈለግበትን መንገድ የቀየረው ኤ.አይ
ከጥቂት ዓመታት በፊት ሰዎች ስለሆነ ነገር መረጃ ሲፈልጉ እንደ ጎግል ወይም ዩቲዩብ ያሉ መተግበሪያዎችን መጠቀማቸው የተለመደ ነበር። ከ3 አመታት ወዲህ ግን ሰዎች መረጃ ሲፈልጉ ወደ ቻት ጂፒቲ መሰል አማራጮች ማምራት ይቀናቸዋል።
በ2022 በተዋወቀ በወራት ውስጥ 100 ሚሊየን ሳምንታዊ ተጠቃሚዎች የደረሰው ቻት ጂፒቲ በአሁኑ ወቅት ብዙ ተጠቃሚዎች ካላቸው የዓለማችን መተግበሪያዎች አንዱ መሆን ችሏል።
በ2025 በአሜሪካ ከሚገኙ አዋቂዎች መካከል 34 በመቶው ቻት ጂፒቲ ሲጠቀሙ፤ እድሜያቸው ከ30 ዓመት በታች ከሆኑት መካከል 58 በመቶዎቹ ሞክረውታል።
60 በመቶ የሚሆኑት አሜሪካውያን መተግበሪያውን መረጃ ለመፈለግ የሚጠቀሙ ሲሆን ዕድሜያቸው ከ30 አመት በታች ከሆኑት ደግሞ 70 በመቶዎቹ ለዚሁ አገልግሎት እንደሚጠቀሙ ተገልጿል።
ለአመታት ሰዎች መረጃ ለመፈለግ ጎግልን በዋነኝነት ይጠቀሙ የነበሩ ሲሆን አሁን ግን መረጃን ለመፈለግና ነገሮች ምን እንደሆኑ ለማወቅ ሰዎች ፊታቸውን ወደ ቻት ጂፒቲ እያዞሩ ይገኛሉ።
በአሜሪካ በተሰራ ጥናት ከዚህ በፊት ጎግልን ለተለያዩ መረጃዎች ይጠይቁ ከነበሩ ሰዎች መካከል 55 በመቶዎች አሁን ቻትጂፒቲ ወይም ጄሚናይን እንደሚጠቀሙ ያሳያል።
ሰዎች አሁንም ጎግልን መጠቀም ያላቆሙ ሲሆን፥ ቀጥታ ማብራሪያ ለሚፈልጉባቸው ጉዳዮች ግን በዋነኝነት የሰው ሰራሽ አስተውሎት መተግበሪያዎችን ይጠቀማሉ።
ጎግልም ሁኔታውን ተረድቶ በመፈለጊያው ላይ "AI SUMMARY" ያካተተ ሲሆን ከሶስት አመት በፊት በሚሰራበት መንገድም እየሰራ አይደለም።
ጥናቶች፥ ለዜና ምንጮች ከጎግል መፈለጊያ የሚመጡ ፍለጋዎች በ2024 ከነበሩበት 2.3 ቢሊየን በ2025 ወደ 1.7 ቢሊየን እንደቀነሱ አሳይተው በሰው ሰራሽ አስተውሎት መተግበሪያዎች የሚደረጉ የዜና ፍለጋዎች በአንድ አመት ውስጥ ከ56% ወደ 69% መጨመራቸውን ጠቁመዋል።
በአሁኑ ወቅት ከ2.7 ቢሊየን በላይ ተጠቃሚዎች ያሉት ዩቲዩብ እንኳን በዚህ የተጠቃ ሲሆን ሰዎች ወደ ዩቲዩብ የሚያመሩት መጀመሪያ ከቻት ጂፒቲ ጋር ንግግር አድርገው ተጨማሪ የቪዲዮ ማብራሪያዎችን ሲፈልጉ ነው ተብሏል።
የሶፍትዌር መሃንዲሶችም ከቻት ጂፒቲ መምጣት ቀድሞ ይጠቀሙ የነበሯቸውን ድረ-ገፆች መጠቀም ቀንሰው ስራቸውን ከሰው ሰራሽ አስተውሎት ጋር በመተባበር እያከናወኑ ይገኛሉ።
ቻት ጂፒቲ ምንም እንኳን በሦስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ነገሮችን ባይተካም ሰዎች መረጃን የሚፈልጉበትን አዲስ መንገድ ግን አምጥቷል።
Source ፡ The Conversation
#IsItAI
#Concepthub #InterNews #EU
Via @ConceptHubeth
- Tikvah Magazine | @tikvahethmagazine
❤ 115👍 6👎 4😢 4🤯 2
Photo unavailableShow in Telegram
በኬንያ የትልልቅ ድርጅቶች ስራ አስፈፃሚዎች ከመምህራን በ214 እጥፍ የተሻለ ክፍያ ያገኛሉ ተባለ።
የኬንያ አስር ግዙፍ ድርጅቶች ዋና ስራ አስፈፃሚዎች በአማካይ ከኬንያ መምህራን በ214 እጥፍ የተሻለ ክፍያ እንደሚያገኙ ኦክስፋም ኬንያ አስታውቋል።
ኦክስፋም አክሎም፥ ለዋና ስራ አስፈፃሚዎቹ የሚደረገው አማካይ የክፍያ ጭማሪ ከአስተማሪዎቹ የ6 አመት ደመወዝ ጋር እኩል መሆኑንም ገልጿል።
በተጨማሪ በኦክስፋም ሪፖርት በኬንያ የሚገኙ 125 ሃብታሞች ከ77 በመቶው ወይም 42.6 ሚሊየን ህዝብ የበለጠ ሃብት እንዳላቸው ተመላክቷል።
ከ2019-2023 ባለው ጊዜም 1% የሚሆኑት ሃብታሞች የሃገሪቱን ሁለት አምስተኛ ሃብት እንደያዙና የነዚህ 1% ሃብታሞች ሃብት ከቀሩት 99% አንፃር በእጥፍ ማደጉ ተነግሯል።
እነዚህ 1% ሃብታሞችም የሃገሪቱን የፋይናንስ ሃብት 78% መያዛቸው ሲነገር ከ2015 ወዲህም በከፍተኛ ድህነት የሚኖሩ ሰዎች ቁጥር በ7 ሚሊየን መጨመሩ ተነግሯል።
በ125ቱ የኬንያ ሃብታሞች የተያዘው ሃብት ወደ 100 ሽልንግ የመገበያያ ገንዘብ ቢቀየር ሙሉ የናይሮቢ ግዛትን እንደሚሸፍን የኦክስፋም ሪፖርት አሳይቷል።
ዘገባው ከ ዘ ኬንያ ታይምስ የተወሰደ ነው።
Tikvah Magazine | @tikvahethmagazine
❤ 51😢 28🤔 4👍 1👎 1
Photo unavailableShow in Telegram
አሜሪካ ከ19 ሃገራት የመጡ ሰዎች የግሪን ካርድ ሁኔታ ላይ ምርመራ ጀመረች።
አሜሪካ በኋይት ሃውስ አቅራቢያ ጥቃት ተፈፅሞ 2 የብሔራዊ ዘቦቿ ከተገደሉ በኋላ ምርመራ ጀምራለች። የትራምፕ አስተዳደር ከ19 ሃገራት የመጡ ዜጎች የቋሚ መኖሪያ ፈቃድ/ ግሪን ካርድ ሁኔታ እንዲፈተሽ አዟል።
ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ በ2021 ከአፍጋኒስታን ወደ አሜሪካ የገባ ግለሰብ የታሰረ ሲሆን ትራምፕ ከጥቃቱ በኋላ ከአፍጋኒስታን የሚመጡ የኢሚግሬሽን ሂደቶችንም አቋርጠዋል።
የግሪን ካርዳቸው እንዲታይ የተደረጉ ሃገራት ዜጎች መካከል ከአፍጋኒስታን በተጨማሪ የኤርትራ፣ሶማሊያ፣ሊቢያ፣ ኢራን፣ የመን፣ ኩባ እና ቬኔዙዌላ ዜጎች አሉበት።
ትራምፕ ከጥቃቱ በኋላ "ከሶስተኛው አለም የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን" በቋሚነት አቆማለሁ ያሉ ሲሆን ለሃገራቸው ዜጋ ላልሆኑ ሰዎች የሚደረግን የፌደራል መንግስት ጥቅምም አቆማለው ብለዋል።
የግሪን ካርድ ሁኔታው ፍተሻ ከተካሄደ በኋላ ምን እንደሚደረግ ያልታወቀ ሲሆን በርካቶች ግን በገፍ የማባረር እርምጃ ሊወሰድ እንደሚችል ሰግተዋል።
ዘገባው የDW ነው።
Tikvah Magazine | @tikvahethmagazine
❤ 33👎 16👍 4🤷♀ 2
ዩኒሳ (UNISA) 12ኛውን የምርቃት ሥነ-ስርዓት አከናወነ።
የደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ (UNISA) የኢትዮጵያ ሪጅናል የትምህርት ማዕከል በዛሬው ዕለት 12ኛ ዙር የምርቃት ሥነ-ስርዓት በድምቀት አከናውኗል።
በዚህም 64 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት የተመረቁ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 58 ያህሉ በፒኤችዲ ዲግሪ ነተመረቁ ናቸው።
የሥነ-ስርዓቱ ላይ የዩኒሳ የዩኒሰ ፕሪንሲፓል እና ምክትል ቻንስለር ፕሮፌሰር ፑሌንግ ሌንካቡላ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የደቡብ አፍሪካ ሪፐብሊክ ኤምባሲ ተወካዮች እና የዩኒሳ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
የUNISA የኢትዮጵያ ሪጅናል ማዕከል በ2007 ዓ.ም በኢትዮጵያ እና በደቡብ አፍሪካ መንግስታት መካከል በተፈረመው የሁለትዮሽ የትብብር ስምምነት መሰረት የተቋቋመ ሲሆን እስካሁን 1,163 ተማሪዎችን (629 ዶክትሬት፣ 382 ማስተርስ) ማስመረቅ ችሏል።
አብዛኛዎቹ ተመራቂዎች የዩኒቨርሲቲ መምሀራን እና ባለሙያዎች ሲሆኑ፣ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዘርፎች በአመራርነት በማገልገል ላይ ይገኛሉ።
እንዲሁም ዩኒሳ በምርምር፣ በትምህርት ዘርፍ እና በሳይንስ ልማት ከኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በቅርበት ይሰራል።
የአፍሪካ መሪ የርቀት እና የኢ-ለርኒንግ (ODeL) ተቋም የሆነው ዩኒሳ፣ በ152ኛ ዓመቱ በመለው አሀጉሪቱ ተደራሽ እና ጥራት ያለው ትምሀርትን በመስጠት ፈር ቀዳጅ ሆኖ ቀጥሏል።
(Advertorial)
❤ 32🤣 3👎 1
Photo unavailableShow in Telegram
‼️ ይፍጠኑ
‼️ በመሀል ሳር ቤት ቫቲካን ኢምባሲ አካባቢ ‼️
# ቴምር ሪልስቴት ከ8 በላይ ሳይቶችን ጥንቅቅ አድርገን አስረክበን አሁን ደግሞ ሳርቤት ቫቲካን ኢምባሲ አካባቢ ለሽያጭ ያወጣናቸው አፓርትመንቶች
➤ 100% ለሚከፍሉ 35% ቅናሽ
👉 ባለ 2 መኝታ = 81ካሬ = 6ሚሊዮን
👉 ባለ 2 መኝታ = 106ካሬ = 7.9ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 139ካሬ = 10.3ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 152ካሬ = 11.3ሚሊዮን
➤ በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ)
👉 81ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 9.3ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (1.8ሚሊዮን)
👉 106ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 12.1ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (2.4ሚሊዮን)
👉 139ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 15.9ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (3.1ሚሊዮን)
⩩ ቀሪውን 80%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት።
⩩ 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፤ ከከፈሉት ላይ ከ15 -25% ቅናሽ አዘጋጅተናል።
ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን
☎️+251980782850
❤ 23
Photo unavailableShow in Telegram
ኡጋንዳ በአሁኑ ጊዜ ጦርነት ከሌለባቸው ሃገራት የሚመጡ ሰዎችን እንደ ስደተኛ እንደማትመለከታቸው አስታወቀች።
ኡጋንዳ ጦርነት ከሌለባቸው ሃገራት የሚመጡ ሰዎችን እንደ ስደተኛ እንደማታይ ስትገልጽ እነዚህ ሃገራትሞ ኢትዮጵያ ፣ ሶማሊያና ኤርትራ ናቸው ተብሏል።
ለ2 ሚሊየን የቀረቡ ስደተኞችን እያስተናገደች ያለችው ኡጋንዳ የድጋፍ እጥረት የገጠማት ሲሆን የስደተኞቹ መብዛት ሃብትና አገልግሎቷ ላይ ጫና እየፈጠረ ነው።
ኡጋንዳ ከተመድ የስደተኞች ኮሚሽን በአመት 240 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ታገኝ እንደነበር ገልፃ አሁን ይህ ድጋፍ ከ100 ሚሊየን ዶላር በታች መሆኑን ገልፃ በዚህ አመት 18 ሚሊየን ዶላር ብቻ መቀበሏን አስታውቃለች።
ኡጋንዳ ስደተኞችን መቀበሏን እንደማታቆም ገልፃ ከሶስቱ ሃገራት ከዚህ በኋላ የሚመጡ ዜጎችን ግን እንደ ስደተኛ እንደማትቀበል ገልፃለች።
በአሁኑ ጊዜ በስደተኝነት ተመዝግበው ያሉ የሶስቱ ሃገራት ዜጎች ግን በስደተኝነት ተመዝግበው ይቀጥላሉ ብላለች።
ዘገባው የ DW Africa ነው።
Tikvah Magazine | @tikvahethmagazine
🤣 112❤ 82🕊 9🤔 8😢 3
Photo unavailableShow in Telegram
በጊኒ ቢሳው ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ተፈጸመ።
በጊኒ ቢሳው የሚገኙ ወታደራዊ አመራሮች ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት በመፈፀም የሃገሪቱን ፕሬዚዳንት ኡማሮ ሲሶኮን አስረዋል።
ወታደራዊ አመራሮቹ በሃገሪቱ ብሔራዊ ጣቢያም ቀርበው እሁድ የተካሄደውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ማገዳቸውን ገልፀዋል።
በተጨማሪ ሁሉንም የጊኒ ቢሳው ድንበሮች የዘጉ ሲሆን የሰዓት እላፊም አስቀምጠዋል።
ጊኒ ቢሳው ባለፈው እሁድ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫዋን ያካሄደች ሲሆን ውጤቱ በዛሬው እለት ይፋ ይደረጋል ተብሎ እየተጠበቀ ነበር።
ከመፈንቅለ መንግስቱ በኋላ ከፕሬዚዳንቱ በተጨማሪ የፕሬዚዳንቱ የምርጫ ተፎካካሪ የነበሩት ዲያዝ እና ለእርሳቸው ድጋፍ ሲሰጡ የነበሩት የቀድሞ የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስተር ፔሬራም ታስረዋል።
ወታደሮቹ የጦሩን አዛዥ ጀነራል ና ንታንና ምክትላቸውን ጀነራል ቱሬንም ማሰራቸው ተሰምቷል።
ጊኒ ቢሳው ከቅኝ ግዛት ነፃ ከወጣች በኋላ ባለፉት 50 አመታት 9 የመፈንቅለ መንግስት ተግባራትንና ሙከራዎችን አስተናግዳለች።
የ2 ሚሊየን ሰዎች መኖሪያዋ ሃገር ሰፊ የባህር ዳርቻ ሲኖራት ለአደንዛዥ እፅ ዝውውር የተመቸች ስትሆን ተመድም "narco-state" የሚለውን ስያሜ ሰጥቷታል።
መፈንቅለ መንግስት ፈፃሚዎቹም መፈንቅለ መንግስቱን የፈፀሙት በእፅ አዘዋዋሪዎች የሚደገፉ ፖለቲከኞችን ሴራ ለመቀልበስ እንደሆነ ገልፀዋል።
ዘገባው የቢቢሲ ነው።
- Tikvah Magazine | @tikvahethmagazine
❤ 72🤣 27👏 8💔 4👎 3🤷♂ 2
Photo unavailableShow in Telegram
ኦፕንኤአይ በ2030 ቻትጂፒቲን ከሚጠቀሙት መካከል 220 ሚሊየን ያህሉ በክፍያ ይጠቀማሉ ብሎ እንደሚጠብቅ ገለጸ።
ኦፕንኤአይ የሰው ሰራሸ አስተውህሎት መተግበሪያውን ከሚጠቀሙ ሳምንታዊ 2.6 ቢሊየን ተጠቃሚዎች መካከል 8.5% ወይም 220 ሚሊየን ያህሉ በ2030 በክፍያ ይጠቀማሉ ብሎ እንደሚጠብቅ ገልጿል።
በአሁኑ ጊዜ የቻትጂፒቲን የፕላስ አገልግሎቱን 20 ዶላር በወር እንደዚሁም የፕሮ አገልግሎቱን በወር 200 ዶላር እየከፈሉ የሚጠቀሙ 35 ሚሊየን ተጠቃሚዎች እንዳሉም ተመላክቷል።
በዚህ አመት መጨረሻ አመታዊ ገቢው 20 ቢሊየን ዶላር ይደርሳል ተብሎ የሚጠበቀው ኦፕንኤአይ በዚህ አመት የመጀመሪያው 6 ወር ለምርምርና ለተያያዙ ወጪዎች ከ2.5 ቢሊየን ዶላር በላይ ፈሰስ አድርጓል።
ዘገባው የሮይተርስ ነው።
Tikvah Magazine | @tikvahethmagazine
❤ 33🤣 11
Photo unavailableShow in Telegram
‼️ይፍጠኑ ሱቅ ሽያጭ ፒያሳ ላይ ጨርሰናል የመጨረሻው ሱቅ ብቻ ነው የቀረው
#ቴምርሪልስቴት
🎯 ታማኝነት እና የግንባታ ጥራት መለያችን ነው ለዚሆም ማሳያ ከ 7 በላይ ሳይቶችን በታማኝነት ሰርተን አስረክበናል.
🎯ፒያሳ አደዋዐ0 ላይ በ5.9 ሚሊየን ብር የመጨረሻው 1 ሱቅ ብቻ ቀረን
**ከፍተኛ የሆነ የኪራይ ገቢ ያላቸው ሱቆች
👉ግራውንድ ፍሎር ላይ
ጠቅላላ ዋጋ : 5.9 ሚሊየን ብር
ቅድመ ክፍያ: 2.8 ሚሊየን ብር
🏬 G +5 ሞል 4790 ካሬ ላይ ያረፈ
- 2 ቤዝመንት የመኪና ማቆሚያ
- ከሞሉ ፊት ለፊት 10,500 መኪናዎችን ማቆም የሚችል የመኪና ተርሚናል መንግሥት አስጋንብቶ እያጠናቀቀ ነው , ይህም ለሱቁ ትልቅ የሰው ፍሰት እንዲኖረው ያደርጋል.
ለበለጠ መረጃ
👇👇👇👇👇👇
+251980782850
❤ 18👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
Prompt Engineering? ምንድነው ?
ጄኔሬቲቭ ኤ.አይ (Generative Ai) ከተዋወቀ በኋላ ሰዎች በብዛት ኤ.አይ መተግበሪያዎችን መረጃ ለማግኘት፣ ጥያቄዎችን ለመጠየቅ፣ ዝርዝር ነገሮችን ለማሳጠርና ግልጽ ለማድረግና ለብዙ ጉዳዮች እየተጠቀሟቸው ይገኛል።
እነዚህ አገልግሎቶች በነጻ ሁሉም ሰው በብዛት የሚጠቀማቸው ቢሆኑም ለሁሉም ሰው እኩል አገልግሎት ይሰጣሉ ማለት ግን አይደለም።
ታዲያ ለሰዎች የሚሰጠው ምላሽ ላይ ያለው ልዩነት ከምን የሚመነጭ ነው ?
ኤ.አይ ሞዴሎች ለሚሰጡት ምላሽ ተገቢውን ጥያቄ፣ ወይም መረጃውን ሊረዱበት በሚችለው መንገድ ማቅረብ የተሻለ ምላሽ እንድናገኝ ይረዳናል። ይህንን ተግባር ወይም ሞያ "Prompt Engineering " ብለን እንጠራዋለን።
ግልጽ ትዕዛዞችን ማስተላለፍ መቻል፣ መጠየቅ ስለምንፈልገው ጥያቄ የተገደበ እና በአጭሩ የተብራራ መረጃ መስጠት፣ በሚሰጡን ምላሾች ላይ ተደጋጋሚ ማሻሻያዎችን መጠየቅ፥ የተሻለ ምላሽ ለማግኘት ከሚጠቅሙን መካከል ይጠቀሳሉ።
በተጨማሪም፥ በአንድ ጊዜ አንድ ርዕሰ ጉዳይ ነጥሎ (ትኩረት አድርጎ) መጠየቅ፤ ምሳሌዎችን ማቅረብ፤ መረጃዎች ቅደም ተከተላቸውን ጠብቀው አንዲቀመጡ ትዕዛዝ ማስቀመጥ፤ በምን አይነት መልኩ ምላሹን እንደምንፈልገው በግልጽ መግለጽ ጥራት ያለው ምላሽ እንድናገኝ ያግዙናል።
ምን ጥንቃቄ ማድረግ አለብን ?
ኤ.አይ ሞዴሎች ትክክለኛ ምላሽ ላይሰጡን ስለሚችሉ መረጃዎችን እንደወረደ ከመጠቀም ተቆጥበን ምላሾቹን ማንበብ፣ ደግሞ ማጣራትና ይዘቱን መፈተሽ ያስፈልጋል።
በተጨማሪም፥ ኤ.አይ ሞዴሎች አሰራራቸው ምላሽ ለመስጠት ነው። ስለዚህ የምንጠይቀው ጥያቄ ግልጽ ባይሆንም ምላሽ ይሰጣሉ።
መረጃ በሌላቸው ጉዳይ ላይም የቅዠት መረጃ (AI hallucinations) ይሰጣሉ። ስለዚህ በሚሰጡን ምላሾች ላይ ማጣራት፤ መልሶ መጠየቅ እና በሌሎች መረጃዎች መደገፍ ያስፈልጋል።
#IsItAI
#Concepthub #InterNews #EU
Via @ConceptHubeth
- Tikvah Magazine | @tikvahethmagazine
❤ 73🤣 7👍 6👎 1🤯 1
Photo unavailableShow in Telegram
ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በአፋር ክልል የሚገኘው የኤርታሌ እሳተ ገሞራ ድጋሚ ከፈነዳ በኋላ የፍንዳታው ጭስ ቀይ ባህርን ተሻግሮ ቻይና ደርሷል።
በፍንዳታው ወቅት ጭስ እና ሰልፈር ዳይኦክሳይድ እስከ 14 ኪሎሜትር ከፍታ ድረስ የወጣ ሲሆን ጭሱ ቀይ ባህርን ተሻግሮ ሰሜን ምዕራብ ህንድ ከደረሰ በኋላ ዛሬ የህንድን አየር ክልል በመልቀቅ ወደ ቻይና እያመራ ነው ተብሏል።
ጭሱ በሰዓት ከ120-130 ኪሎሜትር በሆነ ፍጥነት እየሄደ እንደሆነ የተገመተ ሲሆን ወትሮውንም በመጥፎ አየር ለምትታወቀው ዴሊህ ከተማም ስጋት ሆኗም ነበር።
የሜትሮዎሎጂ ባለሙያዎች ግን ጭሱ ከ25,000-45,000 ጫማ ከፍታ ውስጥ እየተጓዘ በመሆኑ መሬት ላይ የአየር ብክለት ተፅዕኖው እምብዛም አይደለም ሲሉ ገልጸዋል።
የህንድ የሜትሮዎሎጂ ተቋምም የጭሱ ተፅዕኖ በዴሊህ ከተማ ላይ ብዙም አይቆይም ሲል አስታውቆም ነበር።
በዚህው የኤርታሌ ፍንዳታ ጭስ የተነሳም በርካታ በረራዎች ተሰርዘው የቆዩ ሲሆን ጭሱ የሳተላይት ተግባራትንና የበረራ ስራዎችን በጊዜያዊነት ተስተጓጉለዋል።
ኤይር ኢንዲያ፥ በጭሱ የተነሳ 11 በረራዎችን ሲሰርዝ የህንድ የሲቪል አቪየሽን ተቋምም አብራሪዎች ከጭሱ ጋር በተያያዘ የገጠማቸው ነገር ካለ ሪፖርት እንዲያደርጉ ጠይቆ፤ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶም ነበር።
የፍንዳታው ጭስም በዛሬው ዕለት የህንድ የአየር ክልልን ሙሉ ለሙሉ በመልቀቅ ወደ ቻይና እንዳመራ የህንድ የሜትሮዎሎጂ ተቋም ገልጿል።
የዘገባው ምንጮች ቢቢሲ፣ ሂንዱስታን ታይምስና ኢንዲያ ቱደይ ናቸው።
@TikvahethMagazine
❤ 102🤣 67😢 8👍 6🤯 3🙏 3🤷♂ 1
Photo unavailableShow in Telegram
በአፍሪካ የአሜሪካ ጦር ማዘዣ በዚህ አመት በሶማሊያ መቶኛውን የአየር ጥቃት ፈፅሟል።
አሜሪካ በሳምንቱ መጨረሻ በሶማሊያ በጎሊስ ተራራማ አካባቢ የአየር ጥቃት የፈፀመች ሲሆን ጥቃቱ በዚህ አመት በሶማሊያ የፈፀመችው 100ኛ የአየር ጥቃትም ሆኗል።
ይህ የጥቃት ቁጥርም ከባለፈው አመት በእጅጉ የጨመረ ሲሆን በአሜሪካ ጦር በሶማሊያ በአንድ አመት ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የአየር ጥቃት የፈፀመችበትን የ2019 እ.ኤ.አ 63 የአየር ጥቃቶችንም በልጧል።
አሜሪካ በሶማሊያ እየፈፀመች ያለችው አልሸባብን ኢላማ ያደረገ የአየር ጥቃትም በካሪቢያን ከጀመረችው የዕፅ አዘዋዋሪዎች ጥቃት በልጧል ተብሏል።
ከመስከረም ወር መጀመሪያ ጀምሮ አሜሪካ በካሪቢያን በሚገኙ የአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪዎች ላይ 21 የአየር ጥቃቶችን የፈፀመች ሲሆን በሶማሊያ ግን በዚሁ ወቅት 28 ጥቃቶችን ፈፅማለች።
አሜሪካ ከአልሸባብ በተጨማሪ በአሁኑ ጊዜ 60 በመቶ የሶማሊያ ዜጋ ያልሆኑና 1500 ተዋጊዎች ባሉት በሶማሊያ በሚገኘው በአይኤስአይኤስ ላይ የአየር ጥቃት እየፈፀመች ትገኛለች።
ዘገባው ከStripes የተወሰደ ነው።
@TikvahethMagazine
❤ 61👎 7🤔 2
Photo unavailableShow in Telegram
#SocialMedia
በርካታ የማኅበራዊ ሚዲያ ተቋማት በሰዎች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚያደርስ የሚያሳዩ መረጃዎች እያሏቸው በመደበቃቸው መከሰሳቸው ተሰምቷል።
ከዚህ ውስጥ ሜታ፥ ፌስቡክና ኢንስታግራም የሰዎችን የአዕምሮ ጤና እንደሚጎዱ የሚያሳየውን የራሱን ጥናት ደብቋል ተብሏል።
ሜታ፥ በ2020 ጥናት ካስጠና በኋላ ለሳምንት ፌስቡክ መጠቀም ያቆሙ ሰዎች የጭንቀት፣ የፍራቻ እና የብቸኝነት ስሜታቸው መቀነሱን ካሳወቁና የተቋሙ ምርቶች የሰዎችን፤ በተለይም የወጣቶችን የአዕምሮ ጤና እየጎዱ መሆኑ ከታወቀ በኋላ ጥናቱን መደበቁ ተሰምቷል።
ምንም እንኳን ሜታ በራሱ ያስጠናው ጥናት የማኅበራዊ ሚዲያዎቹ በሰዎች አዕምሮ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደረ መሆኑን ቢያሳይም በኮንግረስ ቀርቦ ምርቶቹ ሴቶች ህፃናትን እንደሚጎዱ በመጠን የመግለፅ አቅም እንደሌለው ገልፆ ነበር።
የሜታ ቃለ-አቀባይ "ጥናቱ የተሰራበት መንገድ ትክክል ስላልሆነ ቆሟል" ያለ ሲሆን ህፃናትን ለመጠበቅ ባለፉት 10 ዓመታት ከቤተሰቦችና ከተመራማሪዎች ጋር በመሆን ለውጥ ያመጣ ሥራ ተሰርቷል ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
ሜታ በተጨማሪ ከ13 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናት መተግበሪያውን እንዲጠቁሙ በማበረታታት እና በትምህርት ቤት እንዲጠቀሙ በመገፋፋት እንደዚሁም የህፃናት ወሲባዊ ይዘቶችን መፍትሄ ባለመስጠት ተከሷል።
ሜታ፥ ጥናቱን በመደበቁና በሌሎችም "ሞትሊይ ራይስ" በተሰኘ ተቋም ፍርድ ቤት ክስ የተመሰረተበት ሲሆን እንደ ጎግል፣ ስናፕቻት፣ ቲክቶክ ያሉትም ምርቶቻቸው የሚያደርሱትን አደጋ ሆን ብለው በመደበቅ ተከሰዋል።
የማኅበራዊ ሚዲያዎቹ የመተግበሪያቸውን ደህንነት ለመከላከል ህፃናት ላይ ለሚሰሩ ተቋማት ገንዘብ ይከፍላሉ ተብለውም ተከሰዋል።
ፍርድ ቤትም ክሱን ከመጪው የፈረንጆቹ ጥር 26 ጀምሮ ማድመጥ ይጀምራል ተብሏል።
ዘገባው የሮይተርስ ነው።
@TikvahethMagazine
❤ 61👏 9🤣 5
Photo unavailableShow in Telegram
‼️ ይፍጠኑ
‼️ በመሀል ሳር ቤት ቫቲካን ኢምባሲ አካባቢ ‼️
# ቴምር ሪልስቴት ከ8 በላይ ሳይቶችን ጥንቅቅ አድርገን አስረክበን አሁን ደግሞ ሳርቤት ቫቲካን ኢምባሲ አካባቢ ለሽያጭ ያወጣናቸው አፓርትመንቶች
➤ 100% ለሚከፍሉ 35% ቅናሽ
👉 ባለ 2 መኝታ = 81ካሬ = 6ሚሊዮን
👉 ባለ 2 መኝታ = 106ካሬ = 7.9ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 139ካሬ = 10.3ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 152ካሬ = 11.3ሚሊዮን
➤ በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ)
👉 81ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 9.3ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (1.8ሚሊዮን)
👉 106ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 12.1ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (2.4ሚሊዮን)
👉 139ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 15.9ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (3.1ሚሊዮን)
⩩ ቀሪውን 80%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት።
⩩ 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፤ ከከፈሉት ላይ ከ15 -25% ቅናሽ አዘጋጅተናል።
ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን
☎️+251980782850
❤ 20👍 1
እርሶ በሚጠቀሙባቸው ማኅበራዊ ሚዲያዎች ባለፉት አንድ ወራት የትኞቹ መረጃዎች በስፋት ሀሰተኛ መረጃዎች የተሰራጨባቸው ነበሩ?Anonymous voting
- 1. ፖለቲካዊ እና ከግጭት ጋር የሚያያዙ መረጃዎች
- 2. የማጭበርበሪያ ስልቶችና ሀሰተኛ የሥራ ማስታወቂያዎች
- 3. አሳሳች የጤና መረጃዎች
- 4. በኤ አይ የተቀነባበሩ ምስሎችና ቪዲዮዎች
Photo unavailableShow in Telegram
ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ኡጋንዳ በህንድ ውቅያኖስ የባህር በር እንደሚኖራት ተናገሩ።
ከቀናት በፊት የኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ኡጋንዳ የህንድ ውቅያኖስ ባለቤት ነች በማለት በባህር አማራጭ ዙሪያ ከኬንያ ጋር ግጭት ሊኖር እንደሚችል ተናግረው ነበር።
የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ" ኡጋንዳ እና ኬንያ ወንድማማቾች ናቸው፤ ኡጋንዳ በኬንያ በኩል የባህር አማራጭ ታገኛለች" ብለዋል።
ሙሴቬኒ እንደ ኢጋንዳ ያሉ ሃገራት የባህር በር ማጣታቸው ምክንያታዊ እንዳልሆነ አንስተው በአፍሪካ ያሉ ፖለቲካዊ ድንበሮች ለንግድና ደህንነት የማይመቹ ናቸውም ብለው ነበር።
ዊሊያም ሩቶ ኡጋንዳ በኬንያ በኩል የባህር በር እንደሚኖራት ከተናገሩ በኋላ የኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ዊሊያም ሩቶን እውነተኛ ፓን አፍሪካኒስት ሲሉ ገልፀዋቸዋል።
ዘገባው ከኬንያ ታይምስ የተገኘ ነው።
@TikvahethMagazine
❤ 207👍 40🤣 10🤝 2
Photo unavailableShow in Telegram
#Update
የምያንማር ወታደሮች በማጭበርበሪያ ካምፖች ላይ ባደረጉት ዘመቻ 1590 የውጪ ዜጎችን መያዛቸውን አስታወቁ።
የምያንማር ጦር ከታይላንድ በሚዋሰንበት አካባቢ በሚገኙ የማጭበርበሪያ ካምፖች ለ5 ቀናት ኦፕሬሽን አድርጎ ወደ ምያንማር በህገወጥ መንገድ የገቡ ናቸው ያላቸውን 1590 የውጪ ሃገር ዜጎች ማሰሩን ገልጿል።
በተጨማሪም 2893 ኮምፒውተሮች ፣ 21750 የሞባይል ስልኮች፣ 101 የስታርሊንክ የሳተላይት መቀበያና ሌሎች ለማጭበርበር ተግባራት ይውሉ የነበሩ መሳሪያዎች ተይዘዋል ተብሏል።
ባለፈው ወር አጭበርባሪዎቹ የስታርሊንክ የሳተላይት ኢንተርኔት አገልገሎት እንደሚጠቀሙ ከተነገረ በኋላ ተቋሙ አጭበርባሪዎች ይጠቀሙበት የነበረን 2500 የስታርሊንክ መገልገያዎች ማጥፋቱን መግለፁ ይታወሳል።
ምያንማር በ2021 መፈንቅለ መንግስት ከተፈፀመባትና መረጋጋት ካቃታት በኋላ የአጭበርባሪዎች መናኸሪያ ስትሆን በርካታ የውጪ ሃገር ዜጎችሞ ተታለው ከተወሰዱ በኋላ የራሳቸው ጦር ባላቸው አጭበርባሪዎች ተገደው እንዲሰሩ ይደረጋል።
ተመድ በደቡብ ምስራቅና ምስራቅ እስያ ያሉ አጭበርባሪዎች በ2023 ብቻ 37 ቢሊየን ዶላር አግኝተዋል ያለ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቻይና በምትሰጠው ድጋፍ የተነሳ በካምፖቹ ላይ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል።
ዘገባው የAFP ነው።
@TikvahethMagazine
❤ 53👍 12
Photo unavailableShow in Telegram
ብዙ ወጣቶች የተዘፈቁበት የ"ቨርቹዋል" ቁማር
ከኢንተርኔት መስፋፋት ጋር በተያያዘ እያደጉ ከመጡ ነገሮች አንዱ የ "ቨርቹዋል ቁማር" ነው። ነገሩ በኦንላይን መከናወኑና የክፍያ ሥርዓቶች ዲጂታል መሆናቸው ደግሞ በርካታ ሰዎች እንዲገቡበትና እንዲዘፈቁበት ምክንያት ሆኗል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ዳይሬክተሩ አቶ ደሴ ደጀኔ ለስፖርት ውርርድና ለ4 የሎተሪ አይነቶች ፈቃድ መሰጠቱን አንስተው ሌሎች የቁማር አይነቶች ግን በህግ እንዳልተፈቀዱ ቢያነሱም፥ በርካቶች በተለይ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በቨርቹዋል ጌሞች ህይወታቸውን አበላሽተዋል።
ጫላ ማረማ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ሲሆን በቨርቹዋል ቁማር ከተጠመዱ ወጣቶች ውስጥ አንዱ ነው። ጫላ በመማሪያ ክፍል ውስጥ መምህራንን ከመስማት ይልቅ የሞባይል ዳታ እየገዛ እነዚህን የቨርቹዋል ቁማሮች እንደሚጫወት ይገልፃል።
ጫላ የጀመረው በስፖርት ውርርድ ቢሆንም ከሰዎች ስለ ቨርቹዋል ቁማር ከሰማ በኋላ እንደገባበት ይናገራል።
ወጣቱ ተማሪ ከመማሪያ ክፍል በተጨማሪ ማንበቡን ትቶ ቁማሩን ማሳደዱ ለ16 አመት ሲዘጋጅለት የነበረውን ድግሪ ዋጋ እንዳስከፈለው አንስቶ ሥነ-ልቦናዊ ሁኔታውም ሰዎችን ወደመጥላትና ደስታን ወደ ማጣት ይከታል ይላል።
ጫላ ቤተሰቦቹ ለእሱ ገንዘብ ለመላክ እዳ ውስጥ እንደሚገቡ፣ እሱ ግን ቁማሩን ለመጫወት እንደሚጠቀምበት አንስቶ ከሰዎችም ብድር ውስጥ እንደገባም ይናገራል።
በዚህ የተነሳ ከፍቅረኛው ጋር መለያየቱን፣ ከራሱ ጋር መጋጨቱንና ለሶስት ተከታታይ ዓመታት የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ማለፍ ሳይችል በመቅረቱም የኦንላይን ጌም ህይወቴን አበላሽቶታል ይላል።
እንደ ጫላ ሁሉ በርካታ ወጣቶች በዚህ የቨርቹዋል ጌም የተጠመዱ ሲሆን ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ ሌላ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዓመት ተማሪ በሁሉም ቦታ ቁማሩን እንደሚጫወት ተናግሮ ከቤተሰብ ብር ከማስላክ በተጨማሪ ከጓደኞቹና ከቴሌብር ጭምር እንደተበደረ ይናገራል።
ተማሪዎቹ ከአቋማሪ ድርጅቶች የሚደርሳቸው የቦነስና ሽልማት መልዕክት እንደዚሁም በተፅዕኖ ፈጣሪዎች የሚሰሩ ማስታወቂያዎች ወደቁማሩ እንዲመለሱ እንደሚስባቸው ይናገራሉ።
የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር የህጉ አፈፃፀም ላይ ክፍተቶች እንዳሉ አንስቶ ድጋሚ እንደሚታይ ገልጿል።
የዓለም ጤና ድርጅት ቁማር በኦንላይን መንገድ መቅረቡና በተፅዕኖ ፈጣሪዎች መተዋወቁ እንደሚያስፋፋው ሲገልፅ በነዚህ መንገዶች ወደ ቁማሩ የገቡ ወጣቶች ግን ዛሬም የሰላም እንቅልፍ መተኛት አልቻሉም።
ፅሁፉ ከአዲስ ስታንዳርድ የተገኘ ነው።
@TikvahethMagazine
❤ 181🤣 39😢 23👍 16👎 3🙏 3🕊 3
