አዲስ ነገር መረጃ
前往频道在 Telegram
#አዲስ_ነገር_መረጃ #መረጃዎች_በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ Addis Ababa , Ethiopia Buy Ads : https://telega.io/?r=UbutLo2z #ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇 @Addisnegermereja_bot
显示更多2025 年数字统计

103 076
订阅者
-9224 小时
-3717 天
+21730 天
帖子存档
መረጃ‼️
የኢትዮጵያ የግል ድብልቅ የትራንስፖርት ወይም መልቲ ሞዳል አገልግሎት ሠጪ ኩባንያዎች ጅቡቲ ወደብ ላይ ደረሠኝ እንዳይቆርጡ የወደቡ ባለስልጣናት በድንገት ማገዳቸው በግል ኩባንያዎቹ የሎጅስቲክ ትራንስፖርት ዘርፍ ላይ ከባድ ችግር መፍጠሩን ፎርቹን ዘግቧል።
የጅቡቲ የወደብ አስተዳደር፣ ከእንግዲህ በወደቡ ላይ ደረሠኝ መቁረጥ የሚችሉት የንግድ መርከብ ባለቤቶች የሆኑ የትራንስፖርት አገልግሎት ሠጪ ኩባንያዎች ብቻ ናቸው ማለቱን ዘገባው ጠቅሷል።
በዚህ አዲስ መመሪያ ሳቢያ፣ የግል ትራንስፖርት ኩባንያዎች የካርጎ ጭነቶችን ከወደብ ማውጣት እንዳልቻሉ ዘገባው አመልክቷል።
በኢትዮጵያ እና ጅቡቲ መካከል ቀደም ሲል የተፈረመው የወደብ አጠቃቀም ስምምነት የጊዜ ገደቡ ያለፈ ሲኾን፣ ስምምነቱን በድጋሚ ለማደስ ንግግ እየተደረገ ይገኛል ተብሏል።
የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ የመሩት ልዑካን ቡድን፣ ባለፈው ሳምንት ወደ ጅቡቲ ተጉዞ ከአገሪቱ ባለሥልጣናት ጋር መነጋገሩ አይዘነጋም።
መንግሥት ለግል የድብልቅ ትራንስፖርት አገልግሎት ሠጪ ኩባንያዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ፍቃድ የሠጠው ከአንድ ዓመት በፊት ሲሆን፣ ቀደም ሲል ዘርፉን በብቸኝነት ተቆጣጥሮት የቆየው መንግሥታዊው የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክ ድርጅት ነበር።
Via : ዋዜማ
@Addis_News
@Addis_News
❤ 16🤪 3
照片不可用在 Telegram 中显示
የይዞታ ማረጋገጫ የሌላቸው ይዞታዎች ታክስ እንዲከፈልባቸው የሚያስገድድ ሕግ ተዘጋጀ
የይዞታ ማረጋገጫ የሌላቸው ነገር ግን በይዞታው ጥቅም የሚያገኙ፣ የንብረት ታክስ እንዲከፍሉ የሚያስገድድ ሞዴል ረቂቅ የንብረት ታክስ አዋጅመዘጋጀቱ ተነገረ።
ረቂቅ አዋጁን የገንዘብ ሚኒስቴር ከገቢዎች፣ ከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ጋር ማዘጋጀቱ ተገልጿል።
ለሁሉም ክልሎችና ለሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የተላከው ሞዴክ የንብረት ታክስ ህጉ በሊዝ ይዞታ ስሪትም ሆነ ከይዞታ ስሪት ውጪ በሚተዳደር ማንኛውም የቦታ መጠቀሚያ የሚጣልና የሚሰበሰብ መሆኑ ተገልጿል።
ሆኖም የተመዘገበ የባለቤትነት መብት በሌለበት ጊዜ ታክስ መክፈሉ ብቻ ባለይዞታ እንዳማያደርግና በሌሎች ህጎች የሚወሰዱ እርምጃዎችን እንደማያስቀር ተገልጿል።
በከተማው ቦታ መጠቀሚያ መብት ላይ የሚጣለው ታክስ ምጣኔ ታክስ የሚከፈልበት ዋጋ ላይ 0 ነጥብ 2 በመቶ በታችና ከአንድ በመቶ በታች በማይበልጥ ሁኔታ ተግባራዊ እንደሚደረግ፣ ከተሞች አግባብነት ያላቸውን ህጎች መሰረት በማድረግ በባዶ ቦታ ላይ ከፍተኛ የታክስ ተመን ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸው ሰፍሯል።
በሌላ በኩል ዝቅተኛ ገቢ ላለው አንድ ቤተሰብ በመኖሪያነት የሚያገለግል የከተማ ቦታ፣ ህንጻና የቦታ ማሻሻያ ከንብረት ታክስ ነጻ መደረጉ ተገልጿል።
በተመሳሳይ የሀይማኖት ተቋማት ለአምልኮና ለመካነ መቃብር አገልግሎት የሚጠቀሙባቸው ንብረቶች ፣ ለህብረተሰቡ ነጻ ማህበራዊ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች ለአገልግሎቱ የሚጠቀሙባቸው ንብረቶች ከታክስ ነጻ ናቸው ተብሏል።
@seledadotio
@seledadotio
❤ 18🤣 7😨 3
“ትግስታችን አልቋል”ህወሓት‼️
በምርጫ ቦርድ የተሰረዘው ህወሓት ሳምንታዊ መልዕክት በሚል ባወጣው መግለጫ፣ ትዕግሴት አልቋል ብሏል፡፡ የፌደራል መንግሥቱን የወነጀለው ህወሓት፣ በተደጋጋሚ ያቀረበው ጥሪ ምላሽ አለማግኘቱን ገልጿል፡፡
በፕሪቶሪያ የተደረሰውን ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ በተደጋጋሚ ጥሪ ባቀርብም ምላሽ እያገኘ አይለም ያለው ህወሓት፣ ከዚህ በኋላ አልታገስም ብሏል። ቡድኑ በመግለጫው ለዘላቂ ሰላም መስፍን ቁርጠንነት ቢኖረኝም፣ የትግራይ ህዝብን ለማጥፋት የሚደረጉ ሴራዎችን አልታገስም ብሏል፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት “የትግራይ ህዝብን በተለያዩ መንገዶች የዘር ማጥፋት ዘመቻውን ቀጥሏል” በማለት የወነጀለው ህወሓት፣ ትግራይ ያለው የሰብአዊ ቀውስ መባባሱን ጠቁሟል። ለዚህም አስታኮ ማስጠንቀቂያ አዘል መግለጫ ያወጣበትን የህጻጽ ተፈናቃዮ ረሃብ ያነሳ ሲሆን፣ የፕሪቶሪያው ስምምነት ባለመተግበሩ ትግራይ ተደራራቢ ቀውስ እያስተናገደች ነው ብሏል፡፡
ይሁን እንጂ ትግራይ ለገጠማት ቀውስ የፌደራል መንግሥቱን ተጠያቂ የሚያደርገው ራሱ ህወሓት ተፈናቃዮች የፖለቲካ መያዛ በማድረግ ይወነጀላል፡፡ ከህወሓት በተቃራኒ የቆሙ በርካታ የትግራይ ፖለቲካ ኃይሎች ተፈናቃዮች ለችግር የተጋለጡት ሰብዓዊነት እና ፖለቲካ በመቀላቀሉ ነው ይላሉ፡፡
ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ በትግራይ ሕዝብ ላይ እየተፈጸመ ነው ያለውን “የዘር ማጥፋት” ወንጀል ለመከላከል ጥረት እያደረገ አለመሆኑን አመልክቷል። ህወሓት በመግለጫው ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ተገቢውን ዕርምጃ መውሰድ አለበት ያለ ሲሆን፣ ትዕግስትም ልክ አለው በማለት አሳስቧል።
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤ 32🤣 10😢 3
የጭካኔ ጥግ!!!! በአዲስ አበባ ሰሚት ጠፍቶ ሲፈለግ የነበረው የ7 አመቱ ህፃን ተገድሎ የካ ጫካ ውስጥ ተገኘ
ቀብሩ ዛሬ ተፈፅሟል።
ቤተሰቦቹ የ7 ዓመቱ ህፃን ሀበን ካሱ ከአዲስ አበባ፣ ሰሚት እሁድ ታህሳስ 5/2018 ዓም ከቤት እንደወጣ አለመመለሱን በመግለፅ በእግር በፈረስ፣በፖሊስ በማህበራዊ ሚዲያም በመንገር ትንሹን ልጅ አስፈለጉ።
ይገኛል የሚለው ተስፋ ይዘው ፣በሌላ በኩልም ተገድሎ ይሆን ፣አውሬ በልቶት ይሆን ፣ ሰው ሰውሮት ይሆን? ሌላም ሌላም በውስጣቸው እየዞረ ከሳምንት ጭንቀት በኋላ የትንሹ ልጅ ሬሳ በሰው ተገድሎ ክብር እንዴለለው ፍጡር ጫካ ውስጥ ተጥሎ ተገኘ።
ፖሊስ የህጻኑን መገደል ዛሬ ጠዋት ለቤተሰቦቹ ያረዳ ሲሆን ቤተሰቦቹም ለአስክሬን ምርመራ በሆስፒታል ይገኝ የነበረውን አስክሬን በመረከብ ስርአተ ቀብሩን ፈጽመዋል።
ስርአተ ቀብሩ በዛሬው ዕለት 8:30 ሰሚት በሚገኘው ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።
ተጠርጣሪው ህጻኑን ቀደም ብሎ ገድሎት ለቤተሰቦቹ በመደወል በገንዘብ ሲደራደር ነበር ተብሏል።
ይህ ተጠርጣሪ በፖሊስ ተይዞ ምርመራ እየተደረገበት ነው።
😢 63❤ 20💔 13🙏 4👍 2
በንብረት ምክንያት በተፈጠረ አለመግባባት ወንድማቸውን በጩቤ ወግተው የገደሉት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ
የእናት እና አባታችንን ንብረት ብቻህን ለምን ታስተዳደራለህ በማለት ወንድማቸውን የገደሉት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ።
በምስራቅ ባሌ ዞን ፖሊስ ዋና መምርያ የወንጀል ምርመራ ክፍል ሃላፊ ዋና ኢንስፔክተር አሻግሬ ጥላሁን እንደገለጹት ጥበቡ ድሪባ፣ መብራቱ ዲሪባ እና ሀብታሙ ዲሪባ የተባሉት ሶስት ወንድማማቾች ከአንድ አባትና እናት የተወለዱ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በምስራቅ ባሌ ዞን ጊኒር ወረዳ አቃሸት ቀበሌ ሲሆን እንደማንኛውም ልጅ ሶስቱ ወንድማማቾች፣ በልጅነታቸው አንዱ ለአንዱ በመተጋገዝ የወጣትነት እድሜ ክልል ውስጥ ገብተው እያሉ ታላቅ ወንድም ቀድሞ ትዳር ይመሰርታል። በዚህም አባት እናት ታላቅ ወንድምን ለንብረታቸው ተቆጣጣሪ በማድረግ ሁለት ታናሽ ወንድሞች ለታላቅ ታዘው እንዲያድጉ ያደርጋሉ። የወንድማማቾቹ አባት በተፈጥሮ ህመም በሞት ይለያሉ።
የቤተሰብ ሙሉ ንብረትን ሃላፊነት ለታላቅ ወንድማቸው መሰጠት ያላስደሰታቸው ሁለቱ ወንድማማቾች እናታቸውን እኛስ ምንም አይነት ሃላፊነት የለንም በማለት እናታቸውን ማስቸገር እንደጀመሩ ነው የተገለፀው።
የሁለቱ ልጆቻቸው ከታላቁ ጋር የገቡትን ቅራኔ ለመፍታት እናት ታላቅየው ከሚያስተዳድረው መሬት የተወሰነው እንዲሰጣቸው ተስማምተው ጥበቡ ለሁለቱ ወንድሞቹ ያለውን መሬት ከፍሎ ይሰጣቸዋል።
ይሁን እና በዚህ ደስተኛ እንዳልሆኑ እና አብላጫውን የወሰደው እሱነው በማለት ቂም ቋጥረው ይቆያሉ። በዚህም መስከረም 17 ቀን 2018 ዓም የመስቀል በዓል እለት መጠጥ የጠጡት ወንድማማቾች ምሽት 12:30 ላይ ታላቅ ወንድማቸውን ወላጅ እናታቸው ጋር ቆይቶ ወደ ቤቱ ሲመለስ ጠብቀው ፀብ በማንሳት በያዙት ስለታም ጩቤ ሆድ እቃውን በመውጋት ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ሕይወቱ እንዲያልፍ ያደርጋሉ።
የአካባቢው ሰዎች ወዲያው ለፖሊስ ጉዳዩን ይጠቁማሉ ። ፖሊስም የሟችን አስክሬን በማንሳት ለአስክሬን ምርመራ ወደ ሆስፒታል በመላክ የድርጊት ፈፃሚዎች ሁለቱ ወንድማማቾች መሆናቸው ባገኘው ተጨባጭ መረጃ ተከታትሎ በቁጥጥር ስር ያውላቸዋል።
የምርመራ መዝገባቸውንም በአስክሬን እና በሌሎች ማስረጃዎች በማጠናከር ለአቃቢ ሕግ ይልካል። ዓቃቢ ህግም ከፖሊስ የተላከውን መዝገብ ተመልክቶ በከባድ የሰው መግደል ወንጀል ክስ ይመሰርታል።
በአቃቢ ህግ የተመሰረተውን ክስ የተመለከተው የምስራቅ ባሌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሕዳር 23 ቀን 2018 ዓም በዋለው ችሎት ተከሳሾቹ ጥፋተኛ መሆናቸው በሙሉ ማስረጃ በመረጋገጡ አንደኛ ተከሳሽ መብራቱ ዲሪባ በእድሜ ልክ እስራት ሁለተኛ ተከሳሽ ሃብታሙ ዲሪባ በሃያ አምስት አመት እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ ማስተላለፉን ዋና ኢንስፔክተር አሻግሬ ጥላሑን ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
Dagu
@Addis_News
@Addis_News
❤ 15😢 7
ነገደ መናብርት የሚባሉትን መላእክት የሚመራቸው አለቃ ነው
አባ ጊዮርጊስ ዘጋሰጫ በሰዓታቱ “ጽርሐ አርያም አዳራሹ፤ የትጉሃን መኖሪያ ቦታው የሚኾን እግዚአብሔር ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ ተብሎ በአንድነት በሦስትነት ይመሰገናል፤ ካህናተ ሰማይ በዙሪያው ይቆማሉ፤ በዙፋኑ ፊት እየሰገዱ አክሊሎቻቸውን ያወርዳሉ፤ እሳትነቱ በሚበርቅ፣ ጊዜ እንዳይመታቸው ይንቀጠቀጣሉ” ይላል፡፡ ቅዱስ ኤጲፋንዮስም በመጽሐፈ አክሲማሮስ “በራማ ሰማይ የሚገኘውን ሁለተኛውን ዐሥሩን ነገድ መናብርት ሲላቸው አለቃቸው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፤ እነዚኽም ረቂቅ የኾነ የመብረቅ ጋሻ የእሳት ጦር ይዘው ከነፋስ ይልቅ የፈጠኑ ሲኾኑ በራማ በሁለተኛው ክፍል ላይ አስፍሯቸዋል፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል ከሚመራው ከዚኽ ነገድ 24ቱ ካህናተ ሰማይ ወጥተዋል፡፡” ይለናል፡፡ በ720 ዓ.ዓ ዐሥሩ ነገደ እስራኤል ሲማረኩ ጦቢት የተባለ ጻድቅ ሰው ዐብሮ ተማርኳል፡፡
ቅዱስ ሩፋኤል ይህን ጦቢትን የተራዳ መልአክም ነው፡፡ በመጽሐፈ ጦቢት 2÷14 እንደተጻፈው ሰውን በመርዳት በደግነቱ የታወቀው ጦቢት ከመንገድ ወድቆ የተገኘ በድን ቀብሮ፤ በዚያው ሌሊት ከቅጥሩ አጠገብ ፊቱን ተገልጦ ተኝቶ ሳለ አዕዋፍ ትኩስ ኩስ ዐይኑ ላይ ጥለውበት እንደ ብልዝ ያለ ወጥቶበት ዐይኑ ጠፋ፤ ሚስቱም ባለማስተዋል “በጐነትህ ምጽዋትህ ያዳነህ ወዴት ነው?” በማለት ስትናገረው ዐዝኖ ሞትን ተመኘ፡፡ ቅዱስ ሩፋኤልም አይኑን ሲፈውሰው፣ በላይዋ ላይ ያደረ ጋኔን ባሏን ይገድልባት ቤተሰቦቿን ያንቋሽሿት የነበረችውን የራጉኤል ልጅ ሳራን ያደረባትን ርኩስ መንፈስ አስወጥቶ የጦቢት ልጅ ጦብያ እንዲያገባት አድርጓል፡፡ የመላዕክት ተራዳኢነት በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ትልቅ ስፍራ አለው፡፡
ቅዱስ ሩፋኤልም ከዚህ በኋላ ወደ ጦቢት በመኼድ ረዥም ዘመን የታወረ ዐይኑን አብርቶለት ከሰብዐቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሩፋኤል እኔ ነኝ ብሏቸው ተሰውሯል፡፡ ጦቢት 12÷15፡፡ ፈታሔ ማኀፀን ወሰፋድል። መወለድ መንፈሳዊ። ወሐኪም ሰማያዊ ይባላል። የወላድ ማኀፀን እንዲፈታ በእግዚአብሔር ስለተሾመ አዋላጅ ብትኖርም ባትኖርም ቅዱስ ሩፋኤል በዚያ አይታጣም፡፡
በተለይ በባላገር ያሉ ሴቶች በምጥ ጊዜ ሁሉ መልክአ ሩፋኤል በአንገታቸው ያነግታሉ፣ ይጸልያሉ፣ የተጸለየበትንም ጸበል ይጠጣሉ፤ በፍጥነትም ይወልዳሉ። ቅዱስ ሩፋኤል ቊጥሩ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት ሲኾን፤ “ሩፋ” ማለት ሐኪም፤ ኤል ማለት እግዚአብሔር ማለት ሲኾን ሩፋኤል ማለት “እግዚአብሔር ሐኪሜ ነው” ማለት ነው፡፡ በመጽሐፈ ሄኖክ 6÷3 ላይም “በሰው ቁስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው” ተብሏል፡፡
ሊቁ ቅዱስ ባስልዮስም “በፊቱ የሚቆሙ የመላእክት ሰራዊትም ኹሉ ጩኸው ያመሰግኑታል፤ የመላእክት አለቆችም ለማይታይ ለባለዚህ ስም ዘንበል ብለው ይሰግዳሉ፤ ዙፋኑን የሚሸከሙ አርባዕቱ እንስሳ ጩኸው ያመሰግኑታል፤ ዕጣንን የተመሉ የወርቅ ማዕጠንት በእጆቻቸው ያለ ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ይኸውም የቅዱሳን ጸሎት ነው እስከ ዘላለሙ ሕያው በሆነው ፊት የሚቀበለው መሥዋዕት አድርገው ወደ ላይ ያሳርጋሉ” በማለት አስተምሯል፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል ነገደ መናብርት የሚባሉትን ራማ በሚባለው ሰማይ የሚኖሩትን ነገደ መላእክት የሚመራቸው ናቸው፡፡ ዓመታዊ በዓሉ ጳጉሜ 3 ሲሆን በየወሩ በ13ኛው ቀን ደግሞ መታሰቢያ በዓሉ ይከበራል፡፡ ገዳማውያንም ይህን ተራዳኢነቱን በመታመን ዘወትር በጸሎታቸው ይጠሩታል፡፡
እኛንም የቅዱስ ሩፋኤል በረከትና ረድኤቱ አይለየን፤ ምልጃው ይጠብቀን፡፡ ገዳማቸውን በመደገፍና በዓታቸውን በማጽናት የበረከታቸው ተሳታፊ እንሁን፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957
❤ 41🤪 3
照片不可用在 Telegram 中显示
🚨ውፍረት መጨመር ይፈልጋሉ❓❓
+251964593642
✔ ከአንድ ወር እስከ 45 ቀን ዉስጥ
ክብደት መጨመር የሚረዳ
✔ የምግብ ፍላጎት መጨመር የሚያስችል
✔ የቆዳን ጥራት እና ልስላሴ ለመጨመር
የሚረዳ
✔ ምንም አይነት የጎንዮሽ ጉዳት የሌለዉ ፤
ለቀጭን ሰዎች የሚመከር
✔ ለሴቶችም የተስተካከለ አቋም
እንዲጎናፀፉ የሚያግዝ
✔ ለወንዶችም ለሴቶችም የሚሆን አለን ፤
🚴♂ያሉበት እናደርሳለን
------------------------------------
ለበለጠ መረጃ ☎️ +251964593642
+251906495051
+251907495051
Telegram: 📥 t.me/AM_CS
t.me/AM_CS1
t.me/AM_CS2
------------------------------------
❤ 6🤪 6💯 1
በረሃብ አለንጋ እየረገፉ ያሉ ወገኖች ከሕፃፅ የተሰማ ሰቆቃ‼️
በትግራይ ክልል ህፃፅ ከተማ የሚታየው ትዕይንት እጅግ አሳዛኝ ነው። የረሃብ ፅልመት በየቤቱ ገብቶ ህፃናትንና አረጋውያንን እየቀጠፈ ይገኛል። እናቶች ልጆቻቸውን የሚያበሉት አጥተው፣ ልጆችም የደረቀ ጡት እየመጠጡ ለሞት ሲፋጠጡ ማየት ሰብአዊነትን የሚፈትን ሆኗል።
ይህን ርሃብ ተከትሎ የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ምላሽ ለመስጠት ኮሚቴ ማቋቋሙን ምንጮቻችን ገልጸዋል።
@Addis_News
@Addis_News
😢 78❤ 19💔 3😨 1
04:30
视频不可用在 Telegram 中显示
ሰዎች viral የሆነው በ view የሚከፍለውን አፕፕ እኛም እንስራው
በመጀመሪያ ከታች ያለውን ትነኩትና አፑን download ታደርጉታላችሁ በመቀጠል create account የሚለውን ከነካችሁ ቡሃላ
1 በዚህ ሊንክ ግቡ ና Appun playstoreን or appstoreእን ምረጡ
https://app.buzzerfan.com/referral-invite/rsdf3de6aff03447bab57010ece7626afe
👉 Gmail
👉 የማረሱትን password
👉 ከዛ otp code ይላክላችሁአል ያንን paste ታደርጉታላችሁ
👉ከዛም ምትፈልጉትን sports ትመራጣላችሁ, ስም, username እና እድሜ ታስገባላችሁ
👉በመጨረሻም referral code ይጠይቃችሁአል ከስር ያለውን copy ታደርጉትና አስገብታችሁ
🕹️ Referral code ይህንን ተጠቀሙ
👉6AF-10 Ereferral code የሚል ሲመጣላችሁ bonus point ለማግኘት ይህን ኮድ አስገቡ 👉 6AF10E
ከዛ የመጀመርያችሁን 100 point ይሰጣችቹአል ✌️
ከዛም ከ tiktok ላይ ፅድት ያሉ የ sports edits ያለ watermark download እያደረጋችሁ post በ ማድረግና invite በማድረግ ሸቅሉ አሰራሩ ካልገባችሁ ከላይ ቪዲኦ ተያይዟል ተመልከቱና ስሩ👆💲💰💰
31.85 MB
❤ 5👍 2
照片不可用在 Telegram 中显示
አዋሽ ወይን፣ አራዳ ቢራን ሊገዛ ተቃርቧል!
-አዋሽ ወይን ኮማሪን ለመጠቅለል ከስምምነት ሲደርስ፣ የሀይነከን እቅድ በምንዛሬ ለውጥ ምክንያት ተሰርዟል
የዓለም አቀፉ ግዙፍ የቢራ ኩባንያ ሀይነከን፣ የኮማሪ መጠጥ ኩባንያን ለመጠቅለል የነበረው እቅድ መክሸፉ ተሰማ።
ይህን ተከትሎ አንጋፋው አዋሽ ወይን አክሲዮን ማህበር፣ ይፋዊ የግዢ ስምምነት ውስጥ በመግባት የኮማሪን ብራንድ ለመረከብ መቃረቡ ተገልጿል።
ካፒታል ጋዜጣ ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ በሀገሪቱ አንጋፋውና ስኬታማው የመጠጥ አምራች አዋሽ ወይን፣ በአራዳ መጠጥ ምርቱ የሚታወቀውን ኮማሪ መጠጥ ኩባንያን ለመግዛት ከስምምነት ደርሷል።
በጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም ተጠናቆ የነበረው የሀይነከን እና ኮማሪ ስምምነት ሊፈርስ የቻለው በኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ለውጥ ምክንያት መሆኑ ተጠቁሟል። ምንጮች እንደገለጹት፣ በውጭ ምንዛሬ ተመን ላይ የተደረገው ማስተካከያና የብር የመግዛት አቅም በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ፣ የኩባንያውን ዋጋ የመወሰንና የክፍያ ስርአቱን ውስብስብ በማድረጉ ስምምነቱ እንዲቋረጥ ምክንያት ሆኗል ሲል ካፒታል ዘግቧል፡፡
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤ 13
照片不可用在 Telegram 中显示
ከጥር 23 ጀምሮ ስስ የፕላስቲክ ከረጢቶችን መጠቀምና ማምረት በህግ ያስቀጣል
የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ለአንድ ጊዜ አገልግሎት የሚውሉ ስስ የፕላስቲክ ከረጢቶች ላይ የተጣለው እገዳ ከጥር 23 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ተፈጻሚ እንደሚሆንና እርምጃ መውሰድ እንደሚጀምር አስታወቀ።
ዋና ዋና ነጥቦች፦
📌 የእገዳው ገደብ፦ የ6 ወራት የሽግግር ጊዜው ጥር 23 ያበቃል። ከዚህ ቀን በኋላ ስስ ፕላስቲኮችን ማምረት፣ ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባትና መጠቀም በህግ ያስጠይቃል።
📌 አማራጭ አቅርቦቶች፦ የወረቀትና ሌሎች ለአካባቢ ተስማሚ የሆኑ ከረጢቶችን ለሚያመርቱ አካላት የማሽነሪ ከቀረጥ ነፃ መብትና የብድር አቅርቦት እንዲመቻች እየተሰራ ነው።
📌 የክትትል ስራ፦ ባለስልጣኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት በገበያ ውስጥ የሚታዩ ህገወጥ የፕላስቲክ ስርጭቶችን ለመቆጣጠር ዝግጅቱን አጠናቋል።
🚨 ማሳሰቢያ፦ ማንኛውም ነጋዴም ሆነ አምራች እስከ ጥር 23 ድረስ አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ ወደ አማራጭ ምርቶች እንዲሸጋገር ጥሪ ቀርቧል።
@seledadotio
@seledadotio
🤣 17❤ 10👍 5
የእርሻ ማሳ ውስጥ የገባ ዝሆን የ76 ዓመቱን አዛውንት ሕይወት ሲያጠፋ በአንድ ሰው ላይ ጉዳት አደረሰ
በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ሀረማያ ወረዳ እርሻ ማሳ ውስጥ የገባው ዝሆን የአንድ ሰው ሕይወት ሲያጠፋ በአንድ ሰው ላይ ጉዳት ማድረሱን ፖሊስ አስታውቅቋል።የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ፖሊስ ዋና መምሪያ የኮምንኬሽን ፅህፈት ቤት ኃላፍ ምክትል ኢንስፔክተር ካሲዬ አበበ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት በዞኑ ሐረማያ ወረዳ በሊና ቀበሌ ውስጥ ድርጊቱ ተፈፅሟል።
የእርሻ ማሳ ውስጥ የገባው ዝሆን አቶ መሐመድ አሕመድ ቱሌ የተባሉትን የስምንት ልጆች አባት በኩንቢው ጠልፎ የጣላቸው ከእርሻ ማሳቸው ውስጥ ዝሆኑን ለማውጣት ባደረጉት ጥረት እንደሆነ ገልፀዋል። በኩቢው አዛውንቱን ጠቅልሎ ከጣላቸው በኃላ በእግሩ ሲረጋግጣቸው የተመለከተው የሀያ አመት ወጣት አዛውንቱን ከዝሆኑ ጥቃት ለመታደግ ጥረት ሲያደርግ ዝሆኑ ጉዳት አድርሶበት እንደ ሄደ ገልፀዋል።
የአካባቢ ሰዎች ዝሆኑ ስፍራውን ለቆ ከሄደ በኋላ ሲደርሱ የአዛውንቱ ሕይወት ያለፈ ሲሆን ጉዳት የደረሰበትን ወጣት ደግሞ በሕይወት ያለ በመሆኑ ወዲያው ወደ ሀረማያ ሆስፒታል በማድረስ የሕክምና እርዳታ አግኝቶ በጤንነት ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
ዝሆኖች አንዳንዴ ከባብሌ ፖርክ በመውጣት በሰብል ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ሲሆን ይህንኑ ለመከላከል በሚደረግ ሙከራም በሰው ላይ ጉዳት እንደሚያደርሱ ምክትል ኢኒስፔክተር ካሲዪ አበበ ጨምረው ገልፀዋል።dagu
@seledadotio
@seledadotio
❤ 30😢 20
照片不可用在 Telegram 中显示
"ባንኮች ከጡረታ መዋጮ የአገልግሎት ክፍያ በሚል መቁረጥ አይችሉም" - የግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር
አንዳንድ ባንኮች የጡረታ ክፍያ ለተጠቃሚዎች ሲክፍሉ የአገልግሎት ክፍያ በሚል እንደሚቆርጡ ተነግሯል።
የአገልግሎት ክፍያውን እየቆረጡ ያሉት ብሄራዊ ባንክ መመሪያ አውጥቷል በሚል እንደሆነ ተጠቅሷል።
በ2014 የወጣው የጡረታ አዋጅ ግን ከጡረታ መዋጮ ገንዘብ ላይ ቀንሶ ለአገልግሎት ክፍያ፣ ለገንዘብ ማስተላለፊያ እያሉ መጠቀም እንደማይቻል ይደነግጋል ተብሏል።
ብሄራዊ ባንክ አወጣው የተባለው መመሪያ ከአዋጁ በላይ ሊሆን ስለማይችል ግን ተግባሩ ሊቆም ይገባል ሲሉ የአስተዳደሩ የህግ ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ግርማ ሢሣይ አሳስበዋል።
ዘገባው የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ነው።
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤ 22👍 2
照片不可用在 Telegram 中显示
በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ 179 አመራሮችና ባለሙያዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ባለፉት 5 ወራት ውስጥ ስራቸውን በአግባቡ ባልተወጡና በስነ-ምግባር ጉድለት በተገኙ 179 ሰራተኞች ላይ የዲስፕሊን እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።
ዋና ዋና ነጥቦች፦
• የእርምጃው ምክንያት፦ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር፣ ከሌብነትና ብልሹ አሰራር ጋር የተያያዙ ጥፋቶች እንዲሁም የስነ-ምግባር ግድፈቶች።
• የተቀጡ አካላት፦ 20 አመራሮች እና 159 ፈፃሚ ባለሙያዎች።
• የክትትል ዘዴዎች፦ በሰርቪላንስ ካሜራ፣ በምስለ ተገልጋይ እና በዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ የተገኙ ግድፈቶች ናቸው።
• የቀጣይ ትኩረት፦ በኢ-ፋይሊንግ፣ በኢ-ፔመንት እና በቲን ቁጥር አሰጣጥ ዙሪያ አገልግሎቱን በማዘመን የግብር ከፋዩን እንግልት መቀነስ።
ቢሮው በቀጣይም ጥብቅ ክትትል በማድረግ ገቢን በፍትሃዊነት የመሰብሰብ ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።
❤ 17👍 8🤣 4
照片不可用在 Telegram 中显示
በወልዲያ ከተማ የኤች አይቪ ኤድስ ቫይረስ ሥርጭት ባልተለመደ ሁኔታ እየጨመረ እንደሚገኝ ተጠቆመ
በወልዲያ ከተማ የኤች አይቪ ኤድስ ቫይረስ ስርጭት እየጨመረ በመምጣቱ ትኩረት የሚሻ ጉዳይ መሆኑን የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ጤና መምሪያ አስታውቋል።
የመምሪያው የኤች አይ ቪ ዘርፈ ብዙ ምላሽ አሥተባባሪ አቶ ሰኢድ ይማም ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት በከተማዋ የኤች አይቪ ኤድስ ቫይረስ ሥርጭት እየጨመረ ይገኛል ።በአመራር በኩል ለጉዳዮ በቂ ትኩረት አለመስጠት፣ስለ በሽታው ለማህበረሰቡ ይሰጡ የነበሩ የግንዛቤ ስራዎች መቀዛቀዝና በወሲብ ስራ የተሰማሩ ሴቶች ከሌላ ቦታ ወደ ከተማዋ መምጣታቸው የበሽታው ስርጭት ከፍተኛ እንዲሆን ካደረጉ ምክንያቶች ውስጥ ይጠቀሳሉ ብለዋል።
ከሐምሌ እስከ ኅዳር 2018 ዓ.ም ድረስ ባሉት አምስት ወራት ውስጥ 13 ሺህ 5መቶ15 ሰዎች ተመርምረው 1መቶ 12 ሰዎች የኤች አይ ቪ ኤድስ ቫይረስ በደማቸው ተገኝቶባቸዋል።በበጀት ዓመቱ 6 ሺህ 1መቶ71 አዋቂ እና 96 ሕጻናት በጥቅሉ 6 ሺህ 2መቶ 67 ሰዎች መድኃኒት የሚወስዱ መኖራቸውን አቶ ሰኢድ ጨምረው ለጣቢያችን ገልፀዋል።
የጤና መምሪያው ለጉዳዮ መፍትሄ ለማምጣት የኤች አይ ቪ ኤድስ ቫይረስ ሥርጭት መከላከል እና ቁጥጥር ላይ ያተኮረ ምክክር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር አካሂዷል። ሥርጭቱን ለመቆጣጠር በወሲብ ንግድ ሰራተኞች፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና ኮሌጆች ላይ ትኩረት በማድረግ የአቻ ለአቻ ውይይት እየተካሄደ እንደሚገኝ ተገልጿል።
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤ 12🤣 11😢 7
አየር መንገዱ በረራዎችን ያቋረጠበት የአየር ፀባይ ለዉጥ በደሴ እና አካባቢው የደረሱ ሰብሎችን አወደመ፡፡
በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ደሴ ከተማና አካባቢዋ በድንገት በተቀየረ የአየር ሁኔታ ምክንያት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎቹን ለማቋረጥ መገደዱን ማስታወቁ ይታወቃል።
አየር መንገዱ ለበረራ አመቺ ያልሆነ የአየር ፀባይ በመከሰቱ የታህሳስ 12 አና 13 ቀን በረራዎቹን መሰረዙን ትናንት ባወጣው መግለጫ ገልጿል።
አየር መንገዱ ከሚቲዎሮሎጂ በሚያገኘው መረጃ መሠረት ሁኔታውን እየተከታተለ የአየር ሁኔታው ሲስተካከል በረራዎቹ ወደ መደበኛ አገልግሎታቸው እንደሚመለሱ አመልክቶ በአገልግሎቱ መቋረጥ ለተፈጠረው መጉላላት ይቅርታ ጠይቋል።
በተመሳሳይ በደሴ ዙሪያ ወረዳ በተለይም በደረባ እና በአደይ ቀበሌዎች ታህሳስ 11 ቀን ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ በረዶ ቀላቅሎ በጣለው ከባድ ዝናብ በደረሱ ሰብሎች ላይ ከፍተኛ ውድመት ማድረሱን የወረዳው ግብርና ልማት ጽህፈት በት አስታዉቋል።
የወረዳው ግብርና ልማት ጽሕፈት ቤት ምክትል ሃላፊ አቶ ሁሴን የሱፍ በረዶው ለመሰብሰብ ደርሰው በነበሩ ሰብሎች ላይ በድንገት በመጣሉ ከፍተኛ ብክነት ማስከተሉን ጠቅሰዋል።
ምክትል ኃላፊው አክለውም ሰሞኑን የሚታየው ዝናብ በደረሱ ሰብሎች ላይ ጉዳት እያደረሰ በመሆኑ፣ አርሶ አደሩ ከሰላም ስራዎች በተጨማሪ የደረሱ ሰብሎችን በተደራጀ ሁኔታ በመሰብሰብ የሚደርሰውን ተጨማሪ ውድመት እንዲከላከል ጥሪ አቅርበዋል።
@Addisinsider_ETH
@Addisinsider_ETH
❤ 17😢 11🤪 2👍 1
ከ6 ሺህ በላይ አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ያደረገ መልሶ ግንባታ ሥራ ተጠናቀቀ
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሸረ ሪጅን ከ6 ሺህ በላይ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ የሚያደረግ የመልሶ ግንባታ እና አቅም ማሳደግ ሥራ ማከናወኑን ተናገረ፡፡
ባለፉት አራት ወራት ውስጥ የ73.4 ኪ.ሜ የመካከላኛ መስመር መልሶ ግንባታ መከናወኑን የሪጅን የኔትወርክ ኢንፍራስትራክቸር ማኔጅመንት ኃላፊ አቶ ተወልደ በርሀ አስታወቁ፡፡
የመልሶ ግንባታው በአዲ ፃሓፊት 8 ነጥብ 5፣ ዛና 20.4 ኪሜ፣ በማይ ቕነጣል 10 ኪሜ፣ በዓዲ አውዓላ 13.3፣ በይሓ 15.6፣ በአክሱም ሽረ መስመር 8 ኪሜ፣ በነቅዓ 8.07 መልሶ ግንባታ የተደረገባቸው ከተሞች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
በሪጅኑ የኔትወርክ ኢንፍራስትራክቸር ማኔጅመንት ኃላፊ አቶ ተወልደ በርሀ እንዳሉት በመልሶ ግንባታው 1190 በላይ ምሰሶ ተተክሏል ብለዋል፡፡
በተያያዘ ዜና ተጨማሪ ከአክሱም እስከ ሽረ፣ ከአድዋ አስከ አክሱም እና ሌሎች 7/ሳይቶች/ የመልሶ ግንባታ የምሰሶ ተከላ ስራ ሥራ መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡
ኃላፊው በመልሶ ግንባታው ከ2 ሺህ 900 በላይ ከስሚንቶ የተሠራ ምሰሦ መተከሉን እና ቀሪ ስራው ለመጠናቀቅ የሽዎ/የኤሌክትሪክ ገመድ/ አቅርቦት እጥረት በመኖሩ ምክንያት እስከአሁን ሊጠናቀቅ እንዳልቻለ ተናግረዋል፡፡
በተሰራ የማካከለኛ መስመር መልሶ ግንባታ በክረምት ግዜ አብዛኛዎች የገጠር ከተሞች ከነበረ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ መቆራረጥ የተሻለ ልግሎት ማግኘት እንድችሉ ተደርገዋል፡፡
የነበሩ የእንጨት ምሰሶዎች ለረጅም አመታት የቆዩ ከመሆናቸው አንፃር በሰው እና እንስሳ ከፍተኛ የአካል ጉዳት እና ሞት ያደርሱት የነበረ ማስቀረት ተችሏል፡፡
@Addis_News
@Addis_News
❤ 9
01:08
视频不可用在 Telegram 中显示
👉 ከ8 በላይ ሳይቶችን ገንብቶ ያስረከበው
ቴምር ፕሮፐርቲ
አሁንም በድጋሜ አዳዲስ ሳይቶችን
ለሽያጭ አቅርቧል ።
📍 ሳር ቤት
#በ35%ቅናሽ! (በ100% ክፍያ)
👉 ባለ 2 መኝታ = 81ካሬ = 5.7ሚ
👉 ባለ 2 መኝታ = 106ካሬ = 7.9ሚ
👉 ባለ 3 መኝታ = 139ካሬ = 10.3ሚ
👉 ባለ 3 መኝታ = 153ካሬ = 11.4ሚ
#በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ)
👉 81ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 9.3ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (1.8ሚሊዮን)
👉 106ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 12.1ሚ
ቅድመ ክፍያ = 20% (2.4ሚሊዮን)
👉 139ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 15.9ሚ
ቅድመ ክፍያ = 20% (3.1ሚሊዮን)
📍 አዋሬ
#በ35%ቅናሽ! (በ100% ክፍያ)
👉 ባለ 1 መኝታ = 78ካሬ = 5.5ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 117ካሬ = 8.3ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 137ካሬ = 9.7ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 145ካሬ = 10.3ሚሊዮን
#በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ)
👉 78ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 8.5ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (1.7ሚሊዮን)
👉 135ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 14.8ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (2.9ሚሊዮን)
👉 157ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 17.2ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (3.4ሚሊዮን)
⩩ ቀሪውን 80%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት።
⩩ 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፤ ከከፈሉት ላይ ከ15 -25% ቅናሽ አዘጋጅተናል።
ለበለጠ መረጃ ;- 0940464607
0994003949
25.16 MB
❤ 11
照片不可用在 Telegram 中显示
የሩሲያ ጀነራል በሞስኮ መገደላቸው ተነገረ፡፡
በመኪና ውስጥ በተጠመደ ቦምብ ጀነራሉ ህይወታቸውን ማጣታቸውን የአር ቲ ዘገባ ያሳያል፡፡
የሩሲያ የምርመራ ኮሚቴ ከፍተኛው ጀነራል ህይዎታቸውን ማጣታቸውን ከማረጋገጡም ባሻገር ምርመራውን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
በደቡባዊ የከተማዋ ክፍል በርካታ ተሸከርካሪዎች ወድመዋል፤አሽከርካሪም ተጎድቷል፡፡
ሌተናንት ጀነራል ፋኒል ሳርቫሮቭ የኦፕሬሽናል ስልጠና መሪ እንደነበሩም ተነግሯል፡፡
የግድያው ሁኔታ ምንድን ነው የሚለውን የደህንነት ኃይሎች አሁንም በማጣራት ላይ ናቸው ተብሏል፡፡
የዩክሬን የኢንተለጀንስ አገልግሎት በጉዳዪ ላይ እጁ ሊኖርበት ይችላል የሚል ጥርጣሬም ሞስኮ አላት፡፡
ሳርቫሮቭ በመከላከያው ውስጥ ለከፍተኛ ባለሙያዎች ስልጠናን በማዘጋጀት እንዲሁም የተለያዩ ኃላፊነቶችን በመውሰድ የሚታወቁ ነበሩ፡፡
@Addisinsider_ETH
@Addisinsider_ETH
❤ 19😢 10👏 2
