አዲስ ነገር መረጃ
Відкрити в Telegram
#አዲስ_ነገር_መረጃ #መረጃዎች_በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ Addis Ababa , Ethiopia Buy Ads : https://telega.io/?r=UbutLo2z #ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇 @Addisnegermereja_bot
Показати більше2025 рік у цифрах

103 231
Підписники
-9224 години
-3717 днів
+21730 день
Архів дописів
Фото недоступнеДивитись в Telegram
አዋሽ ወይን፣ አራዳ ቢራን ሊገዛ ተቃርቧል!
-አዋሽ ወይን ኮማሪን ለመጠቅለል ከስምምነት ሲደርስ፣ የሀይነከን እቅድ በምንዛሬ ለውጥ ምክንያት ተሰርዟል
የዓለም አቀፉ ግዙፍ የቢራ ኩባንያ ሀይነከን፣ የኮማሪ መጠጥ ኩባንያን ለመጠቅለል የነበረው እቅድ መክሸፉ ተሰማ።
ይህን ተከትሎ አንጋፋው አዋሽ ወይን አክሲዮን ማህበር፣ ይፋዊ የግዢ ስምምነት ውስጥ በመግባት የኮማሪን ብራንድ ለመረከብ መቃረቡ ተገልጿል።
ካፒታል ጋዜጣ ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ በሀገሪቱ አንጋፋውና ስኬታማው የመጠጥ አምራች አዋሽ ወይን፣ በአራዳ መጠጥ ምርቱ የሚታወቀውን ኮማሪ መጠጥ ኩባንያን ለመግዛት ከስምምነት ደርሷል።
በጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም ተጠናቆ የነበረው የሀይነከን እና ኮማሪ ስምምነት ሊፈርስ የቻለው በኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ለውጥ ምክንያት መሆኑ ተጠቁሟል። ምንጮች እንደገለጹት፣ በውጭ ምንዛሬ ተመን ላይ የተደረገው ማስተካከያና የብር የመግዛት አቅም በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ፣ የኩባንያውን ዋጋ የመወሰንና የክፍያ ስርአቱን ውስብስብ በማድረጉ ስምምነቱ እንዲቋረጥ ምክንያት ሆኗል ሲል ካፒታል ዘግቧል፡፡
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤ 13
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ከጥር 23 ጀምሮ ስስ የፕላስቲክ ከረጢቶችን መጠቀምና ማምረት በህግ ያስቀጣል
የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ለአንድ ጊዜ አገልግሎት የሚውሉ ስስ የፕላስቲክ ከረጢቶች ላይ የተጣለው እገዳ ከጥር 23 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ተፈጻሚ እንደሚሆንና እርምጃ መውሰድ እንደሚጀምር አስታወቀ።
ዋና ዋና ነጥቦች፦
📌 የእገዳው ገደብ፦ የ6 ወራት የሽግግር ጊዜው ጥር 23 ያበቃል። ከዚህ ቀን በኋላ ስስ ፕላስቲኮችን ማምረት፣ ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባትና መጠቀም በህግ ያስጠይቃል።
📌 አማራጭ አቅርቦቶች፦ የወረቀትና ሌሎች ለአካባቢ ተስማሚ የሆኑ ከረጢቶችን ለሚያመርቱ አካላት የማሽነሪ ከቀረጥ ነፃ መብትና የብድር አቅርቦት እንዲመቻች እየተሰራ ነው።
📌 የክትትል ስራ፦ ባለስልጣኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት በገበያ ውስጥ የሚታዩ ህገወጥ የፕላስቲክ ስርጭቶችን ለመቆጣጠር ዝግጅቱን አጠናቋል።
🚨 ማሳሰቢያ፦ ማንኛውም ነጋዴም ሆነ አምራች እስከ ጥር 23 ድረስ አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ ወደ አማራጭ ምርቶች እንዲሸጋገር ጥሪ ቀርቧል።
@seledadotio
@seledadotio
🤣 17❤ 10👍 5
የእርሻ ማሳ ውስጥ የገባ ዝሆን የ76 ዓመቱን አዛውንት ሕይወት ሲያጠፋ በአንድ ሰው ላይ ጉዳት አደረሰ
በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ሀረማያ ወረዳ እርሻ ማሳ ውስጥ የገባው ዝሆን የአንድ ሰው ሕይወት ሲያጠፋ በአንድ ሰው ላይ ጉዳት ማድረሱን ፖሊስ አስታውቅቋል።የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ፖሊስ ዋና መምሪያ የኮምንኬሽን ፅህፈት ቤት ኃላፍ ምክትል ኢንስፔክተር ካሲዬ አበበ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት በዞኑ ሐረማያ ወረዳ በሊና ቀበሌ ውስጥ ድርጊቱ ተፈፅሟል።
የእርሻ ማሳ ውስጥ የገባው ዝሆን አቶ መሐመድ አሕመድ ቱሌ የተባሉትን የስምንት ልጆች አባት በኩንቢው ጠልፎ የጣላቸው ከእርሻ ማሳቸው ውስጥ ዝሆኑን ለማውጣት ባደረጉት ጥረት እንደሆነ ገልፀዋል። በኩቢው አዛውንቱን ጠቅልሎ ከጣላቸው በኃላ በእግሩ ሲረጋግጣቸው የተመለከተው የሀያ አመት ወጣት አዛውንቱን ከዝሆኑ ጥቃት ለመታደግ ጥረት ሲያደርግ ዝሆኑ ጉዳት አድርሶበት እንደ ሄደ ገልፀዋል።
የአካባቢ ሰዎች ዝሆኑ ስፍራውን ለቆ ከሄደ በኋላ ሲደርሱ የአዛውንቱ ሕይወት ያለፈ ሲሆን ጉዳት የደረሰበትን ወጣት ደግሞ በሕይወት ያለ በመሆኑ ወዲያው ወደ ሀረማያ ሆስፒታል በማድረስ የሕክምና እርዳታ አግኝቶ በጤንነት ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
ዝሆኖች አንዳንዴ ከባብሌ ፖርክ በመውጣት በሰብል ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ሲሆን ይህንኑ ለመከላከል በሚደረግ ሙከራም በሰው ላይ ጉዳት እንደሚያደርሱ ምክትል ኢኒስፔክተር ካሲዪ አበበ ጨምረው ገልፀዋል።dagu
@seledadotio
@seledadotio
❤ 30😢 20
Фото недоступнеДивитись в Telegram
"ባንኮች ከጡረታ መዋጮ የአገልግሎት ክፍያ በሚል መቁረጥ አይችሉም" - የግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር
አንዳንድ ባንኮች የጡረታ ክፍያ ለተጠቃሚዎች ሲክፍሉ የአገልግሎት ክፍያ በሚል እንደሚቆርጡ ተነግሯል።
የአገልግሎት ክፍያውን እየቆረጡ ያሉት ብሄራዊ ባንክ መመሪያ አውጥቷል በሚል እንደሆነ ተጠቅሷል።
በ2014 የወጣው የጡረታ አዋጅ ግን ከጡረታ መዋጮ ገንዘብ ላይ ቀንሶ ለአገልግሎት ክፍያ፣ ለገንዘብ ማስተላለፊያ እያሉ መጠቀም እንደማይቻል ይደነግጋል ተብሏል።
ብሄራዊ ባንክ አወጣው የተባለው መመሪያ ከአዋጁ በላይ ሊሆን ስለማይችል ግን ተግባሩ ሊቆም ይገባል ሲሉ የአስተዳደሩ የህግ ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ግርማ ሢሣይ አሳስበዋል።
ዘገባው የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ነው።
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤ 22👍 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ 179 አመራሮችና ባለሙያዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ባለፉት 5 ወራት ውስጥ ስራቸውን በአግባቡ ባልተወጡና በስነ-ምግባር ጉድለት በተገኙ 179 ሰራተኞች ላይ የዲስፕሊን እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።
ዋና ዋና ነጥቦች፦
• የእርምጃው ምክንያት፦ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር፣ ከሌብነትና ብልሹ አሰራር ጋር የተያያዙ ጥፋቶች እንዲሁም የስነ-ምግባር ግድፈቶች።
• የተቀጡ አካላት፦ 20 አመራሮች እና 159 ፈፃሚ ባለሙያዎች።
• የክትትል ዘዴዎች፦ በሰርቪላንስ ካሜራ፣ በምስለ ተገልጋይ እና በዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ የተገኙ ግድፈቶች ናቸው።
• የቀጣይ ትኩረት፦ በኢ-ፋይሊንግ፣ በኢ-ፔመንት እና በቲን ቁጥር አሰጣጥ ዙሪያ አገልግሎቱን በማዘመን የግብር ከፋዩን እንግልት መቀነስ።
ቢሮው በቀጣይም ጥብቅ ክትትል በማድረግ ገቢን በፍትሃዊነት የመሰብሰብ ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።
❤ 17👍 8🤣 4
Фото недоступнеДивитись в Telegram
በወልዲያ ከተማ የኤች አይቪ ኤድስ ቫይረስ ሥርጭት ባልተለመደ ሁኔታ እየጨመረ እንደሚገኝ ተጠቆመ
በወልዲያ ከተማ የኤች አይቪ ኤድስ ቫይረስ ስርጭት እየጨመረ በመምጣቱ ትኩረት የሚሻ ጉዳይ መሆኑን የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ጤና መምሪያ አስታውቋል።
የመምሪያው የኤች አይ ቪ ዘርፈ ብዙ ምላሽ አሥተባባሪ አቶ ሰኢድ ይማም ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት በከተማዋ የኤች አይቪ ኤድስ ቫይረስ ሥርጭት እየጨመረ ይገኛል ።በአመራር በኩል ለጉዳዮ በቂ ትኩረት አለመስጠት፣ስለ በሽታው ለማህበረሰቡ ይሰጡ የነበሩ የግንዛቤ ስራዎች መቀዛቀዝና በወሲብ ስራ የተሰማሩ ሴቶች ከሌላ ቦታ ወደ ከተማዋ መምጣታቸው የበሽታው ስርጭት ከፍተኛ እንዲሆን ካደረጉ ምክንያቶች ውስጥ ይጠቀሳሉ ብለዋል።
ከሐምሌ እስከ ኅዳር 2018 ዓ.ም ድረስ ባሉት አምስት ወራት ውስጥ 13 ሺህ 5መቶ15 ሰዎች ተመርምረው 1መቶ 12 ሰዎች የኤች አይ ቪ ኤድስ ቫይረስ በደማቸው ተገኝቶባቸዋል።በበጀት ዓመቱ 6 ሺህ 1መቶ71 አዋቂ እና 96 ሕጻናት በጥቅሉ 6 ሺህ 2መቶ 67 ሰዎች መድኃኒት የሚወስዱ መኖራቸውን አቶ ሰኢድ ጨምረው ለጣቢያችን ገልፀዋል።
የጤና መምሪያው ለጉዳዮ መፍትሄ ለማምጣት የኤች አይ ቪ ኤድስ ቫይረስ ሥርጭት መከላከል እና ቁጥጥር ላይ ያተኮረ ምክክር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር አካሂዷል። ሥርጭቱን ለመቆጣጠር በወሲብ ንግድ ሰራተኞች፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና ኮሌጆች ላይ ትኩረት በማድረግ የአቻ ለአቻ ውይይት እየተካሄደ እንደሚገኝ ተገልጿል።
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤ 12🤣 11😢 7
አየር መንገዱ በረራዎችን ያቋረጠበት የአየር ፀባይ ለዉጥ በደሴ እና አካባቢው የደረሱ ሰብሎችን አወደመ፡፡
በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ደሴ ከተማና አካባቢዋ በድንገት በተቀየረ የአየር ሁኔታ ምክንያት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎቹን ለማቋረጥ መገደዱን ማስታወቁ ይታወቃል።
አየር መንገዱ ለበረራ አመቺ ያልሆነ የአየር ፀባይ በመከሰቱ የታህሳስ 12 አና 13 ቀን በረራዎቹን መሰረዙን ትናንት ባወጣው መግለጫ ገልጿል።
አየር መንገዱ ከሚቲዎሮሎጂ በሚያገኘው መረጃ መሠረት ሁኔታውን እየተከታተለ የአየር ሁኔታው ሲስተካከል በረራዎቹ ወደ መደበኛ አገልግሎታቸው እንደሚመለሱ አመልክቶ በአገልግሎቱ መቋረጥ ለተፈጠረው መጉላላት ይቅርታ ጠይቋል።
በተመሳሳይ በደሴ ዙሪያ ወረዳ በተለይም በደረባ እና በአደይ ቀበሌዎች ታህሳስ 11 ቀን ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ በረዶ ቀላቅሎ በጣለው ከባድ ዝናብ በደረሱ ሰብሎች ላይ ከፍተኛ ውድመት ማድረሱን የወረዳው ግብርና ልማት ጽህፈት በት አስታዉቋል።
የወረዳው ግብርና ልማት ጽሕፈት ቤት ምክትል ሃላፊ አቶ ሁሴን የሱፍ በረዶው ለመሰብሰብ ደርሰው በነበሩ ሰብሎች ላይ በድንገት በመጣሉ ከፍተኛ ብክነት ማስከተሉን ጠቅሰዋል።
ምክትል ኃላፊው አክለውም ሰሞኑን የሚታየው ዝናብ በደረሱ ሰብሎች ላይ ጉዳት እያደረሰ በመሆኑ፣ አርሶ አደሩ ከሰላም ስራዎች በተጨማሪ የደረሱ ሰብሎችን በተደራጀ ሁኔታ በመሰብሰብ የሚደርሰውን ተጨማሪ ውድመት እንዲከላከል ጥሪ አቅርበዋል።
@Addisinsider_ETH
@Addisinsider_ETH
❤ 17😢 11🤪 2👍 1
ከ6 ሺህ በላይ አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ያደረገ መልሶ ግንባታ ሥራ ተጠናቀቀ
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሸረ ሪጅን ከ6 ሺህ በላይ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ የሚያደረግ የመልሶ ግንባታ እና አቅም ማሳደግ ሥራ ማከናወኑን ተናገረ፡፡
ባለፉት አራት ወራት ውስጥ የ73.4 ኪ.ሜ የመካከላኛ መስመር መልሶ ግንባታ መከናወኑን የሪጅን የኔትወርክ ኢንፍራስትራክቸር ማኔጅመንት ኃላፊ አቶ ተወልደ በርሀ አስታወቁ፡፡
የመልሶ ግንባታው በአዲ ፃሓፊት 8 ነጥብ 5፣ ዛና 20.4 ኪሜ፣ በማይ ቕነጣል 10 ኪሜ፣ በዓዲ አውዓላ 13.3፣ በይሓ 15.6፣ በአክሱም ሽረ መስመር 8 ኪሜ፣ በነቅዓ 8.07 መልሶ ግንባታ የተደረገባቸው ከተሞች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
በሪጅኑ የኔትወርክ ኢንፍራስትራክቸር ማኔጅመንት ኃላፊ አቶ ተወልደ በርሀ እንዳሉት በመልሶ ግንባታው 1190 በላይ ምሰሶ ተተክሏል ብለዋል፡፡
በተያያዘ ዜና ተጨማሪ ከአክሱም እስከ ሽረ፣ ከአድዋ አስከ አክሱም እና ሌሎች 7/ሳይቶች/ የመልሶ ግንባታ የምሰሶ ተከላ ስራ ሥራ መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡
ኃላፊው በመልሶ ግንባታው ከ2 ሺህ 900 በላይ ከስሚንቶ የተሠራ ምሰሦ መተከሉን እና ቀሪ ስራው ለመጠናቀቅ የሽዎ/የኤሌክትሪክ ገመድ/ አቅርቦት እጥረት በመኖሩ ምክንያት እስከአሁን ሊጠናቀቅ እንዳልቻለ ተናግረዋል፡፡
በተሰራ የማካከለኛ መስመር መልሶ ግንባታ በክረምት ግዜ አብዛኛዎች የገጠር ከተሞች ከነበረ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ መቆራረጥ የተሻለ ልግሎት ማግኘት እንድችሉ ተደርገዋል፡፡
የነበሩ የእንጨት ምሰሶዎች ለረጅም አመታት የቆዩ ከመሆናቸው አንፃር በሰው እና እንስሳ ከፍተኛ የአካል ጉዳት እና ሞት ያደርሱት የነበረ ማስቀረት ተችሏል፡፡
@Addis_News
@Addis_News
❤ 9
01:08
Відео недоступнеДивитись в Telegram
👉 ከ8 በላይ ሳይቶችን ገንብቶ ያስረከበው
ቴምር ፕሮፐርቲ
አሁንም በድጋሜ አዳዲስ ሳይቶችን
ለሽያጭ አቅርቧል ።
📍 ሳር ቤት
#በ35%ቅናሽ! (በ100% ክፍያ)
👉 ባለ 2 መኝታ = 81ካሬ = 5.7ሚ
👉 ባለ 2 መኝታ = 106ካሬ = 7.9ሚ
👉 ባለ 3 መኝታ = 139ካሬ = 10.3ሚ
👉 ባለ 3 መኝታ = 153ካሬ = 11.4ሚ
#በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ)
👉 81ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 9.3ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (1.8ሚሊዮን)
👉 106ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 12.1ሚ
ቅድመ ክፍያ = 20% (2.4ሚሊዮን)
👉 139ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 15.9ሚ
ቅድመ ክፍያ = 20% (3.1ሚሊዮን)
📍 አዋሬ
#በ35%ቅናሽ! (በ100% ክፍያ)
👉 ባለ 1 መኝታ = 78ካሬ = 5.5ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 117ካሬ = 8.3ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 137ካሬ = 9.7ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 145ካሬ = 10.3ሚሊዮን
#በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ)
👉 78ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 8.5ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (1.7ሚሊዮን)
👉 135ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 14.8ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (2.9ሚሊዮን)
👉 157ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 17.2ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (3.4ሚሊዮን)
⩩ ቀሪውን 80%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት።
⩩ 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፤ ከከፈሉት ላይ ከ15 -25% ቅናሽ አዘጋጅተናል።
ለበለጠ መረጃ ;- 0940464607
0994003949
25.16 MB
❤ 11
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የሩሲያ ጀነራል በሞስኮ መገደላቸው ተነገረ፡፡
በመኪና ውስጥ በተጠመደ ቦምብ ጀነራሉ ህይወታቸውን ማጣታቸውን የአር ቲ ዘገባ ያሳያል፡፡
የሩሲያ የምርመራ ኮሚቴ ከፍተኛው ጀነራል ህይዎታቸውን ማጣታቸውን ከማረጋገጡም ባሻገር ምርመራውን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
በደቡባዊ የከተማዋ ክፍል በርካታ ተሸከርካሪዎች ወድመዋል፤አሽከርካሪም ተጎድቷል፡፡
ሌተናንት ጀነራል ፋኒል ሳርቫሮቭ የኦፕሬሽናል ስልጠና መሪ እንደነበሩም ተነግሯል፡፡
የግድያው ሁኔታ ምንድን ነው የሚለውን የደህንነት ኃይሎች አሁንም በማጣራት ላይ ናቸው ተብሏል፡፡
የዩክሬን የኢንተለጀንስ አገልግሎት በጉዳዪ ላይ እጁ ሊኖርበት ይችላል የሚል ጥርጣሬም ሞስኮ አላት፡፡
ሳርቫሮቭ በመከላከያው ውስጥ ለከፍተኛ ባለሙያዎች ስልጠናን በማዘጋጀት እንዲሁም የተለያዩ ኃላፊነቶችን በመውሰድ የሚታወቁ ነበሩ፡፡
@Addisinsider_ETH
@Addisinsider_ETH
❤ 19😢 10👏 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ወርቅ በአለም አቀፍ ገበያ ላይ ከፍተኛ ዋጋ ታየበት
ዛሬ በአለም አቀፍ ገበያ የወርቅ ዋጋ ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍተኛ ዋጋ እየተሸጠ ነው ።
ሮይተርስ እንደዘገበው፣ ለዋጋው መጨመር ዋነኛው ምክንያት የአሜሪካ የፌደራል መጠባበቂያ የወለድ ምጣኔን ይቀንሳል የሚለው ጠንካራ ግምት ነው።
የአንድ ወቄት ወርቅ ዋጋ 4,383.76 ዶላር በመድረስ አዲስ ታሪክ አስመዝግቧል።
ባለፈው ሳምንት የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ በአሜሪካ የሥራ ገበያ ላይ የታየው ድክመት እና የዋጋ ግሽበት መቀነስ ማዕከላዊ ባንኩ የገንዘብ ፖሊሲውን ለማላላት ምቹ ሁኔታ ፈጥሮለታል።
በጂኦፖለቲካዊ ውጥረቶች፣ በንግድ ግጭቶች እና በሚቀጥለው የፈረንጆቹ ዓመት የወለድ ምጣኔ ይቀንሳል በሚል ግምት ሳቢያ የወርቅ ዋጋ በዚህ የፈረንጆቹ ዓመት በ67 በመቶ ጨምሯል።
ቀደም ብሎ በጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ የወርቅ ዋጋ ከፍተኛ ቅናሽ አሳይቶ የነበረ ሲሆን፣ በወቅቱ የአንድ ወቄት ወርቅ ዋጋ ወደ 4,130.40 ዶላር ዝቅ ብሎ ነበር።
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤ 15👍 2🔥 2🤣 2
በኮንትራክሽን ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ሰራተኞች ለተለያዩ ጉዳቶች ተጋላጭ መሆናቸው በጥናት ተመላከተ
በአዲስ አበባ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ሰራተኞች ለተለያዩ ጉዳቶች ተጋላጭ መሆናቸው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥናት አመላከተ።
ዩኒቨርስቲው ባጠናው ጥናት 5 መቶ 62 የአምራች ፣ የአገልግሎት ሰጪና ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪዎች ተካተውበታል።
በዚህም 1 መቶ 2 ኢንዲስትሪዎች ውስጥ 76 ነጥብ 8 በመቶ ከአምራች ዘርፍ፣ ከኮንስትራክሽን ዘርፍ ሁሉም፣ ከአገልግሎት ዘርፍ ደግሞ 25 ነጥብ 9 በመቶ እየሰሩ ያሉበት የስራ ሁኔታ፣ ሠራተኞችን በከፍተኛ ደረጃ ለአደጋ አጋላጭ ነው ተብሏል።
በእያንዳንዱ የጤና ችግር ላይ ከ1 ሺህ 5 መቶ እስከ 2 ሺህ በተደረገ ጥናት፣ 34 ነጥብ 3 በመቶ አምራች ኢንዱስትሪዎች ፣ 25 ነጥብ 2 በመቶ በአገልግሎት ዘርፍ ፣ 23 ነጥብ 1 በመቶ ደግሞ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ሰራተኞች የመተንፈሻ አካላት በሽታ ምልክቶች እንደተገኘባቸው ተጠቅሷል።
በተጨማሪም 58 በመቶ የአምራች ኢንዲስትሪዎች ፣ 69 ነጥብ 9 በመቶ የአገልግሎት ፣ 65 ነጥብ 5 በመቶ የኮንስትራክሽን ሰራተኞች የአንገት ፣ የጀርባ የጡንቻ መገጣጠሚያ የጤና ችግር እንዳጋጠማቸው ተገልጿል።
እያንዳንዱ የኢንዱስትሪ የስራ ቦታ ደህንነትና የጤና ፖሊሲ ሊኖረው ይገባል የተባለ ሲሆን ጥናቱን መሰረት በማድረግ በጉዳዩ ላይ ደረጃውን የጠበቀ ስልጠና መስጠት የሚያስችል መመሪያ መዘጋጀቱም ተገልጿል።
በዓለም የስራ ድርጅት ሪፖርት መሰረት በአለም አቀፍ ደረጃ በስራ ምክንያት በየአመቱ ከ2 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ሰራተኞች ሲሞቱ፣ ከ270 ሚሊየን በላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት ፣ ከ160 ሚሊየን ቀላል የአካል ጉዳት ይዳረጋሉ።
ዘገባው የሪፖርተር ነው
@Addis_News
@Addis_News
❤ 12
Фото недоступнеДивитись в Telegram
♨️ እንኳን ደስ አላችሁ ለመላው ስራ ፈላጊ ኢትዮጲያዊያን!
-----------------------------------
✅ Make Money Online In Ethiopia 🇪🇹 ✅
በቀን 3000 ብር የሚከፍል ዌብሳይት
15,000- በላይ ክፍት ቦታዎች በ0 አመት እና በልምድ
🔺የትምህርት አይነት: በተለያዩ ዲፓርትመንቶች
🔺የስራ ልምድ: በ 0 ዓመትና በልምድ
🔺 የቅጥር ሁኔታ: በቋሚ ቅጥር
🔺 ብዛት: 15,000+ በላይ
🔺ደሞዝ: በቀን 3000 ብር
🛑 ፈጥነው ታች ባለው ሊንክ ስራውን ይጀምሩ
⁉️ ማሳሰቢያ:- VPN ወይም Psiphon መጠቀም ይኖርባችሗል
👇👇👇👇Apply Now👇👇👇👇👇
👇👇👇👇
https://reportervacancy.com/make-money-onlinejobs-for-beginners-2025/
--------Follow Our Website--------
👇👇👇👇👇👇
https://reportervacancy.com
----------Join Our Telegram-------
👇👇👇👇👇
https://t.me/reporter_vacancy
❤ 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ኢሎን ማስክ ገንዘብ መቆጠብ አያስፈልግም፣ AI ድህነትን ታሪክ ያደርገዋል አሉ
ታዋቂው ቢሊየነር ኢሎን ማስክ የሰው ሰራሽ አስተውሎት እና የሮቦቲክስ ቴክኖሎጂ እድገት ወደፊት ድህነትን ሙሉ በሙሉ እንደሚያጠፋና ሰዎች ለወደፊት ህይወታቸው የሚያደርጉትን የገንዘብ ቁጠባ አስፈላጊነት እንደሚያስቀረው ገለጹ።
ማስክ በቅርቡ በኤክስ (X) ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት፣ ወደፊት "ሁለንተናዊ ከፍተኛ ገቢ" የሚባል ስርዓት እንደሚመጣ ተንብየዋል። ይህም ማለት በቴክኖሎጂ አማካኝነት የሚመነጨው ሀብትና ምርት ለሰው ልጆች ሁሉ በበቂ ሁኔታ ስለሚተርፍ፣ ባህላዊው የስራ ባህል አስፈላጊነቱ ቀርቶ ስራ በሰዎች ፍላጎት ላይ ብቻ የተመሰረተ ምርጫ ይሆናል ብለዋል።
ይህ አስተያየት የተሰጠው ታዋቂው የኢንቨስትመንት ባለሙያ ሬይ ዳሊዮ ለወጣት አሜሪካውያን አዲስ የቁጠባ አካውንት መከፈት አለበት በሚል ላቀረቡት ሃሳብ ምላሽ ነው።
ማስክ የሬይ ዳሊዮ ሃሳብ በጎ ቢሆንም፣ ቴክኖሎጂው ግን ህብረተሰቡ ስለ ገቢ፣ ስለ ስራ እና ስለ ፋይናንስ ዋስትና ያለውን አመለካከት መሰረታዊ በሆነ መልኩ እንደሚቀይረው አፅንኦት ሰጥተዋል።
በተጨማሪም ማስክ ማሽኖች አብዛኛውን ስራ በሚረከቡበት በዚያ ዘመን፣ የሰው ልጅ የህይወት ትርጉሙን እንዴት ሊያገኝ እንደሚችል ትልቅ ጥያቄ መሆኑን ጠቁመዋል።
ቴክኖሎጂው መሰረታዊ ፍላጎቶችን ከማሟላት ባለፈ ለሁሉም ሰው የተትረፈረፈ ህይወት እንደሚያመጣ ቢገልጹም፣ ተቺዎች ግን ይህ ቴክኖሎጂ የሚያመጣው ሀብት ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ለሁሉም ስለመድረሱ ጥርጣሬያቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።
@seledadotio
@seledadotio
❤ 30🥱 3
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የኢትዮጵያዊቷ የቲክቶክ ንግስት ድል በአፍሪካ መድረክ!
ዩቲ ናስ (Yuti Nass) በዩጋንዳ ካምፓላ በተካሄደው Iconic African Awards ላይ በሁለት ታላላቅ ዘርፎች አሸናፊ በመሆን የሀገራችንን ስም በአህጉር አቀፍ ደረጃ አስጠርታለች።
በድል የተረከበቻቸው ዘርፎች፡-
1. Iconic Influencer of the Year: በአፍሪካ ደረጃ የዓመቱ ተጽዕኖ ፈጣሪ።
2. Iconic TikToker of the Year (East Africa): በምስራቅ አፍሪካ የዓመቱ ምርጥ ቲክቶከር።
ዩቲ ሽልማቷን ስትቀበል እንደገለጸችው፣ ይህ ስኬት የኢትዮጵያውያን ሁሉ ኩራት ነው። ቀደም ሲል በህዝብ ድምፅ ቀዳሚ የነበረችው ዩቲ፣ አሁን ሽልማቷን በይፋ በመረከብ ድሏን አድምቃለች።
ከሀገር ውስጥ የቲክቶክ ሽልማት እስከ አህጉራዊው መድረክ ስኬቷን የቀጠለችው ዩቲ ናስ፣ ለሀገራችን የጥበብ ዘርፍ ሌላው ትልቅ ትርፍ ሆናለች።
@Addisinsider_ETH
@Addisinsider_ETH
❤ 47🤪 6
Фото недоступнеДивитись в Telegram
በአፍሪካ ዋንጫ መክፈቻ አሰተናጋጇ ሞሮኮ ኮሞሮስን 2 ለ0 አሸነፈች
ትናንት ምሽት አራት ሰዓት በተካሄደው ጨዋታ ብራሂም ዲያዝ እና ኤል ካቢ ለአትላስ አንበሶቹ ጎሉን አስቆጥረዋል።
የኮሞሮስ ቡድን ግብ ጠባቂ ያኒክ ፓንዶር ፍፁም ቅጣት በማዳን እና ግብ የሚሆኑ ኳሶችን በማዳን ጥሩ ጥረት አድርጓል።
@Addis_News
@Addis_News
🔥 9❤ 6
00:37
Відео недоступнеДивитись в Telegram
🌟🌟ታላቅ የበዓል ቅናሽ በካሬ 78,000 ብር
✅እንዲሁም ሙሉ ክፍያ ለሚከፊል በካሬ 54,800
🔷 በ10 % ቅድመ ክፍያ
🔷 50 % የባንክ ብድር የተመቻቸለት
📍Location እንግሊዝ ኢንባሲ አጠገብ ውብ እይታ (Top View) ያላቸው ቤቶች በሽያጭ ላይ እንገኛለን
👉ከባለ 2 መኝታ- ባለ4 መኝታ
✅ ህንፃው ላይ ያሉ ተጨማሪ አገልግሎትች
👉5 ሰፋፊ ሊፍት /elevator
👉የቆሻሻ መጣያ/garbage chute
👉አውቶማቲክ ጀኔረተር/ automatic generator
👉ሰገነት/terrace
👉የመኪና ማቆምያ/car parking
👉 ጂም , እስፖ
👉 የዋና ገንዳ
👉 የልጆች መጫወታ
✨ባለ 2 መኝታ
138 ካሬ
157.3 ካሬ
163.6 ካሬ
✨ባለ 3 መኝታ
152.4 ካሬ
158.1 ካሬ
187.6 ካሬ
211.5 ካሬ
✨ባለ 4 መኝታ
240.7 ካሬ
258.4 ካሬ
📞 ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
0973559591
0919489575
Telegram -@Homef17
7.49 MB
❤ 3
እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን በነገዱ ውስጥ በመላእክት ሁሉ ላይ በብዙ ክብር ሾመው፡፡
ቅዱስ ሚካኤል በዚህ ሁሉ ልዕልና ላይ ትሕትናን ደርቦ የያዘ በጸሎቱ ተማጽኖ በተራዳኢነት አምኖ ለሚለምነው ሁሉ ፈጥኖ በመድረስ ከአጋንንት ሠራዊተ ተንኰል የሚያድን ነው፡፡ ሚካኤል የሥሙ ትርጓሜ በዕብራይስጥ “ማንነው እንደ እግዚአብሔር?” ማለት ነው፡፡
በክርስትና በአይሁድ፣ እንዲሁም በመላዕክት አማላጅነት በሚያምኑ ሃይማኖቶች የመላዕክት ሁሉ አለቃ ተብሎ ይጠራል፡፡ ይህም የከበረ መልአክ ክብር ይገባውና በጌታችን ፊት ስለ ሰው ልጆችና ስለ ፍጥረትም ሁሉ ይለምናል፤ ይማልዳልም፡፡ የቅዱስ ሚካኤል ተአምራቱ ብዙዎች ናቸው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ለቅዱስ ሚካኤል የተሰጠውን ክብርና ባለሟልነት እንዲሁም የሠራቸውን ሥራዎች በስፋት እንመለከታለን፡፡
በኢያሱ 5÷13 እንዲህ ይላል፡፡ “እንዲህም ሆነ ኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ ዓይኑን አንሥቶ ተመለከተ፡፡ እነሆም የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ ነበር፡፡ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህን አለው፡፡ እርሱም አይደለሁም እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁን መጥቻለሁ አለ፡፡ ኢያሱም ወደ ምድር በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደ፡፡ ጌታዬ ለባሪያው የሚነግረው ምንድን ነው አለው፡፡ የእግዚአብሔርም ሠራዊት አለቃም ኢያሱን አንተ የቆምህበት ሥፍራ የተቀደሰ ነውና ጫማህን በፊቱ አውልቅ አለው፡፡ ኢያሱም እንዲሁ አደረገ” ይላል፡፡ ኢያሱ ከኢያሪኮ ጀምሮ ታላላቅ አሕዛብን አጥፍቶ እግዚአብሔር ለአብርሃም፣ ለይስሐቅ፣ ለያዕቆብ የማለላቸውን የተስፋይቱን ምድር ለልጆቻቸው ያወረሳቸው በዚህ የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ ይዞ በተገለጸለት የእስራኤል መሪ በቅዱስ ሚካኤል እገዛ ነው፡፡ መልአኩ በሰው አምሳል ስለተገለጸለት አላወቀውም ነበር፡፡
ከቃሉ እንደምንረዳው ከራሱ ወገን ወይም ከጠላቶቹ ወገን የሆነ አንድ ወታደር መስሎት ነበር፡፡ ያነጋገረውም ያለ ፍርሃት ያለ ጭንቀት ያለድንጋጤ ወታደሮቹን እንደሚያነጋግር ዘና ብሎ ነው፡፡ ሆኖም “ከወገኖችህ ወይም ከጠላቶችህ አይደለሁም እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁን መጥቻለሁ” ሲለው ኢያሱ በፊቱ የቆመው ከሙሴ ሳይለይ እስራኤልን የሚጠብቅ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል መሆኑን ሲረዳ ለመልአኩ ክብር መስጠት ስለሚገባ የአክብሮት ስግደት ሰገደለት፤ “ጌታዬ ለባሪያው የሚነግረው ምንድነው” በማለት በትህትና ጠየቀ፡፡ ጌታዬ ማለቱ የእግዚአብሔርን ክብር ለፍጡር መስጠቱ አይደለም፣ መላእክት የጸጋ ጌቶች ስለሚባሉ እንጂ፡፡ ኢያሱ መልአኩን ጌታዬ ብሎ ከጠራው እኛም ጌታዬ፤ ቅዱስ ሚካኤል ለኔ ለባሪያህ ጸልይልኝ መጥተህ አድነኝ በማለት የአክብሮት የጸጋ ስግደት በመስገድ ብንለምነው፣ ብንታዘዘው ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት አልወጣንም፡፡
መላእክትን ማክበርና መታዘዝ እንደሚገባ እግዚአብሔርም ነግሮናል፡፡ በዘጸ.23÷20-22 “በመንገድህ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ሥፍራ ያገባህ ዘንድ እነሆ እኔ መልአክህን በፊትህ እሰዳለሁ፤ በፊቱ ተጠንቀቁ፤ ቃሉንም አድምጡ፤ ስሜም በእርሱ ስለሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት፤ አንተ ግን ቃሉን ብትሰማ፣ ያልሁህንም ሁሉ ብታደርግ፣ ጠላቶችህን እጣላቸዋለሁ፣ የሚያስጨንቁህንም አስጨንቃቸዋለሁ፣ መልአኬ በፊትህ ይሄዳል” በማለት ለሙሴ ተናግሯል፡፡ ይህ ቃል ለሙሴና ለሕዝቡ ብቻ ተነግሮ ያበቃ ሳይሆን ዛሬም ያለ ወደፊትም የሚቀጥል ነው፡፡
ገዳማውያንም ይህን ቃል ታምነው ሌሊትና ቀን ሚካኤል ሆይ አማልደን ይሉታል፡፡ ከጸሎታቸው በረከት እንድንካፈል ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957
❤ 36
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ባንኮች የሰራተኞቻቸውን የትምህርት ማስረጃ ትክክለኝነት እንዲያጣሩ ብሄራዊ ባንክ መመሪያ ሰጠ
በተለያዩ የሰራ መስኮች ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች መኖራቸውን የሚያሳይ ፍንጭ መገኘቱን ተከትሎ፣ ብሎም የዲግሪ ወረቀት ሽያጭ እንደነበረ ከተደረሰበት በኋላ፣ ብሔራዊ ባንክ የሀገሪቱ ባንኮች ውስጥ ያሉ ሰራተኞች የትምሕርት ማስረጃ ላይ ማጣራት እንዲደረግ አዟል።
ምንጭ : ዋዜማ
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍 24❤ 14👏 6🤣 4
