ch
Feedback
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

前往频道在 Telegram

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች፣ ስንክሳር፣ መዝሙራትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም አስተያየት @Zimaredawitmessanger ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል። ስለሚሰጡን ገንቢ ሃሳብ እናመሰግናለን። YouTube Page - https://bit.ly/2O1Z3d8 Facebook Page - https://www.fb.com/l/6lp1kJRRR

显示更多
2025 年数字统计snowflakes fon
card fon
166 281
订阅者
-1724 小时
-227
-430
帖子存档
Repost from TgId: 2131344856
照片不可用在 Telegram 中显示
« ይሄው አዲስ ነገር » በ6ኛው ዙር የግራፊክስ ዲዛይን ሥልጠና 3 አሸናፊዎችን የቪዲዮ ኤዲቲንግ ኮርስ እንዲህ ልንሸልም ነው 1ኛ አሸናፊ 100% በነጻ 2ኛ አሸናፊ 50% በነጻ 3ኛ አሸናፊ 25% በነጻ ቤታቹ ሆናቹ ብቻ አሁን ነገሩ በአንድ ድንጋይ 4 ወፍ አልሆነም ወይ 🤭😁 የኮርስ ቀናት ቅዳሜ ምሽት 1:00 - 3:00 እሑድ ምሽት 1:00 - 3:00 3ኛ ቀን በብዙሃኑ ምርጫ ሆኖ ምሽት 2:00 - 4:00 ምን ያስፈልጋል ? ፟» » Laptop » » Internet or Wifi » » Enough Time በነዚህ ላይ የምትስማሙ ብቻ በ300 ብር ቅድመ ክፍያ ( 4500 ጠቅላላ ክፍያ) አሁኑኑ እዚህ ላይ ተመዝገቡና 2 ወራት በህይወታቹ ምን እንደሆኑ በሚገባ እናሳያችኋለን @Greenbirdtechnology ኮርሱ ታኅሳስ 5 ይጀምራል @greenbirdtechs @greenbirdtechs የለውጥዎ ክንፍ 🔑 🐥
显示全部...
57
ሕዳር 24\፳፬\
በዚችም ዕለት የናግራን አገር ቄስ የከበረ አዝቂር የሐሚር ንጉሥ ሰራብሄል በነገሠበት ወራት ከእርሱ ጋር ካሉ አርባ ስምንት ሰዎች ጋር በሰማዕትነት አረፈ ። ይህም ንጉሥ አዝቂርን ወደ ወህኒ አስገብተው እንዲዘጉበት ጠባቂዎቹንም ከሰው ወገን ማንም እንዳይገባ ብሎ አዘዘ ። ቅዱስ አዝቂርም በጸለየ ጊዜ የወህኒ ቤቱ ደጃፍ ተከፈተና ሃምሳ ሰዎች ወደርሱ ገቡ እርሱም በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቃቸው ። ንጉሥ ሰራብሄልም በሰማ ጊዜ ከወህኒ ቤት አውጥተው ወደሌላ አገር እንዲወስዱት አዘዘ በጉዞም ላይ ስሙ ኪርያቅ ከሚባል ሰው ጋር ተገናኘ ቀሲስ አዝቂርም ኪርያቅን ኪርያቅ ሆይ ላንተ የምሥራች ይገባል ለሰማዕትነት ይወስድሃልና አለው ። የንጉሥ ሎሌዎችም ሰምተው አሥረው ከእርሱ ጋር ወሰዱት ። ዳግመኛም ሁለት ሰዎች ተገናኙትና ስለ ክርስቶስ አጥምቀን አሉት ያን ጊዜም ቅዱስ አዝቂር ጸለየና ከበረሀ ቦታ ውኃ አፍልቆ ከኪርያቅ ጋር አጠመቃቸው ። ወደ ናግራን አገርም በአደረሱት ጊዜ በዕንጨት ላይ ሰቅለው ከበታቹ እሳትን አነደዱ ቅዱስ አዝቂርም ወደ ጌታችን ጸለየ በዚያንም ጊዜ ከማሠሪያው ተፈትቶ ከእሳት ውስጥ በደኅና ወጣ አይሁድም በደንጊያ እንውገረው ተባብለው በወገሩት ጊዜ ደንጊያዎች ተመልሰው ከአይሁድ የሚበዙትን ገደሉ ። ከተረፉትም ሰይፍን አንሥተው የቅዱስ አዝቂርን ራስ ቆረጡ ምስክርነቱንም ፈጽሞ የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጀ ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት ሰማዕት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን ። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
显示全部...
205🕊 14
ክበር ባለኝ ነገር ክበር ባለኝ ነገር/2/ የለም ከእኔ የምለው ሁሉ ከአንተ ነው/2/
አዝ
አንተ ታይበት እኔ ልደበቅ በአገልግሎቴ ብቻህን ድመቅ መዝሙሬ ከአንተ ስብከቴ ከአንተ ከእኔ አንዳች የለኝም የአንተን ለአንተ
አዝ
የዕውቀቴ ምንጭ ነህ አብርሆቴ የስኬቴ ቁልፍ ሞገሴ ቤቴ ራቁቴን መጣሁ ራቁቴን እሄዳለው ምን ተገኘና አንተን ተዋለው
አዝ
ምንም ሳይኖረኝ ካለኸኝ አንተ ባለፀጋ ነኝ ያልተራቆተ እንዳመንኩብህ በታች እያለሁ በላይም ሆኜ አመልክሀለው
አዝ
እንደታዘዝኩህ በልጅነቴ ለክብር አቁመኝ በአዋቂነቴ በትዳር በልጅ ስትባርከኝ እንደ ትላንቱም ዛሬም የአንተው ነኝ
አዝ
ሹመኛ ብሆን ገንዘብ ብቆጥር ኩራት አይግባ በልቤ ቅጥር የነቀልክልኝ የኃጢአቴን መርዝ በእኔ ላይ እዘዝ ባለኝ ላይ እዘዝ ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
显示全部...
ክበር_ባለኝ_ነገር_ዘማሪት_ምርትነሽ_ጥላሁን_Lyrics.m4a6.54 MB
224🥰 11🔥 9😍 6🕊 4
ሕዳር ፳፫ /23/
‎ ‎በዚችም ዕለት ዳግመኛ የስሙ ትርጓሜ የእግዚአብሔር አገልጋይ የሆነ የነቢይአብድዩ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው ። ‎ ‎ይህም ቅዱስ ከጠፍ በረሀ አቅራቢያ ከአለች ሱሳም በምትባል አገር ካሉ ሰዎች ወገን ነው ለነቢይ ኤልያስም ደቀ መዝሙሩ ሁኖ ብዙ መከራን በእርሱ ላይየመጣውን ታግሦ ከመከራውም በትዕግሥቱ ዳነ ። ‎ ‎ይህም ኤልያስን የተለማመጠና ኤልያስም አዝኖለት አብሮት ወደ ንጉሥ አክዓብ የሔደለት ሦስተኛው የሃምሣ አለቃ ነው ። ከዚህም በኋላ ምድራዊ ንጉሥን ማገልገል ትቶ ነቢይን ሆነ የትንቢቱንም ወራት አድርሶ በሰላም አረፈ ። ‎ ‎ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በነቢዩ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን ። ‎ ‎ወስብሐት ለእግዚአብሔር ‎ምንጭ :- መጽሐፈ ስንክሳር ‎💚 @ortodoxmezmur 💚 ‎💛 @ortodoxmezmur 💛 ‎❤️ @ortodoxmezmur ❤️ ‎
显示全部...
198🕊 9
እንደኔ የማርከው እንደኔ የማርከው ማንን ነው እንደኔ ይቅር ያልከው ማንን ነው ሀጢያቱ በዝቶበት በደሉ በዝቶበት የማርከው እንደኔ ከቶ ማነው
አዝ
በሞገስ አስጊጠህ በዜማ ቃኘኸኝ ፊትህ ምታቆመኝ ጌታየ እኔ ማነኝ ለኔ ያበዛኸው አቤት ደግነትህ ምረኸኝ/2/ አያልቅም ምህረትህ አይተኸኝ በምህረት /2/ ዛሬም አለሁኝ በህይወት
አዝ
የምስጋና መስዋት ማቅረቢያ መሰዊያ ልቤ ንፁህ ባይሆን ፀጋየን አልቀማህ ተትቀበለኛለህ ምልተህ በጎደለ እኔን የወደደ እንዳንተ ማን አለ አይተኸኝ በምህረት /2/ ዛሬም አለሁኝ በህይወት
አዝ
በምኞት ተስቤ ለሀጢያት ተሽጬ በመስቀልህ ስራ ከሞት ጣር አምልጬ አንተ እንዳዳነከው ሰው መሆን ቢያቅትም እኔ ተስፋ ብቆርጥ ተስፋ አትቆርጥብኝም አይተኸኝ በምህረት /2/ ዛሬም አለሁኝ በህይወት
አዝ
የኖርኩበት ዘመን የቁጣ ልጅ ሆኜ ምዕራፉ ተዘጋ ባ'ንተ በአዳኜ ከኔ ምንም ሳይኖር አንተ ሁሉን ሆነህ ሰገነት ታየሁኝ ስለእኔ ተንቀህ አይተኸኝ በምህረት/2/ ዛሬም አለሁኝ በህይወት
አዝ
እኔን ማረኝ ከምል ከፊትህ ወድቄ በሌላው ፈራጅ ነኝ እራሴን አፅድቄ መመልከት ባልችልም የዓይኔን ምሰሶ የሚያኖረኝ ፍቅርህ ነው ይ'ን ሁሉ ታግሶ አይተኸኝ በምህረት /2/ ዛሬም አለሁኝ በህይወት ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
显示全部...
ጋሜል_ዘ_ኦርቶዶክስ_እንደኔ_የማርከው_ማንን_ነው.mp310.19 MB
179🕊 2🥰 1
በነደደ እሳት ውስጥ በነደደ እሳት ውስጥ  በተሳለ ስለት ደማቸው ፈሰሰ እንደ ውሃ ሙላት የአምላክ ባለሟሎች ሰማዕታት በሙሉ መከራ መስቀሉን ተሸክመው ዋሉ
አዝ
ሰማዕታት ገቡ ወደ ጠባቡ በር የአምላካቸውን ስም ተሸክመው በክብር በአላውያን ነገሥታት ሥጋቸው ታረደ ደማቸው ከመሬት እንደ ጎርፍ ወረደ
አዝ
በእውነት ወደቀ ሥጋቸው ከመሬት የሚቀብረው አጣ እሱም ተፈርዶበት ምግብም ሆኖ ዋለ ለአእዋፍ ለአራዊት እንዲሸጋገሩ ከሞት ወደ ሕይወት
አዝ
ሰማዕታት በሙሉ መከራን ድል ነሱ የሕይወትን አክሊል በእውነት ወረሱ ለተራበ አንበሳ ቢጣልም ሥጋቸው ሥጋቸው ነው እንጂ  አልሞተች ነፍሳቸው
አዝ
ወደ ፈጣሪያቸው በክብር ተጠሩ ከሞት ወደ ሕይወት በድል ተሻገሩ መከራ መስቀሉ ምልክት ሆኗቸው በመንግሥተ ሰማይ አረፈች ነፍሳቸው ዘማሪ ዲያቆን ፍሬዘር ደሳለኝ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
显示全部...
_በነደደ እሳት ውስጥ.mp34.39 MB
161🕊 3🥰 1
ሕዳር ፳፪ /22/
‎ በዚች ቀን ቅዱሳን ቆዝሞስና ድምያኖስ ወንድሞቻቸውም አንቲቆስ ዮንዲኖስ አብራንዮስ በሰማዕትነት አረፉ ። እሊህም ድዮማ ከምትባል ከተማ ስለ እግዚአብሔር ልጅ የታነፀች ግምብ ከአለችበት አረምያ ከምትባል አገር ናቸው ‎ ‎እናታቸውም ቴዎዳዳ እግዚአብሔርን የምትፈራና የምትራራ መጻተኞችንና ዶኆችን የምትወዳቸው የምትረዳቸው ናት አባታቸውም ከሞተ በኋላ ልጆቿን እያስተማረች አሳደገቻቸው ። እሊህም ሁለቱ ቆዝሞስና ድምያኖስ የሕክምና ጥበብን ተምረው በሽተኞችን ያለ ዋጋ የሚፈውሱአቸው ይልቁንም ድኆችን አብዝተው የሚረዷቸው ሆኑ ። ‎ ‎ወንድሞቻቸው ሦስቱ ግን ወደ ገዳም ሒደው መነኰሱ በጾምና በጸሎትም ተጠመዱ ። ከአባ አጋግዮስ አደራ በአስጠበቀው በንጉሠ ቊዝ ልጅ ምክንያት ዲዮቅልጥያኖስ ክዶ የረከሱ ጣዖታትን በአመለከ ጊዜ በምእመናን ላይ መከራ ሆነ ገንዘብ ወዳጅ አጋግዮስ ብዙ ወርቅን ተቀብሎ የንጉሠ ቊዝን ልጅ ወደ አባቱ ልኮታልና ከዚህም በኋላ የንጉሠ ቊዝን ልጅ ዲዮቅልጥያኖስ ዳግመኛ ከጦር ሜዳ አግኝቶ ማረከው እርሱንም የንጉሡን ልጅ ሠውሮ አባ አጋግዮስን ጠራው ያንንም አደራ የሰጠውን የንጉሠ ቊዝን ልጅ እንዲአመጣ አዘዘው ‎ ‎አጋግዩስም ሙቶ ተቀብሮአል ብሎ በሐሰት ተናገረ በዚያንም ጊዜ በመሠዊያው ፊት አማለው እሳትም ከሰማይ ወርዳ እንደምታቃጥለው ጠበቀ የእሳትም መውረድዋ በዘገየ ጊዜ ወርቅን በእሳት አቅልጦ አጠጣውና አቃጠለው ስለዚህም ከወርቅና ከብር የተሠሩ ጣዖታትን አመለከ ። ‎ ‎ቆዝሞስና ድምያኖስ በሀገሩ ሁሉ ስለ ክርስቶስ እነርሱ እንደሚያስተምሩ ዲዮቅልጥያኖስ በሰማ ጊዜ ወደርሱ እንዲአቀርቧቸው አዘዘ በደርሱም ጊዜ ለአገረ ገዢው ለሉልዮስ እንዲአሠቃያቸው ሰጠው ። እርሱም በብዙ ሥቃዮች ማሠቃየትን ጀመረ በእሳት የሚያቃጥልበት ጊዜ አለ በግርፋት የሚገርፍበትም ጊዜ አለ ሦስት ወንድሞችም እንዳሏቸው ሰምቶ እነርሱንም ወደርሱ ‎ ‎አስመጣቸውና አምስቱንም በመኰራኲር ውስጥ እንዲአሠቃዩአቸው አዘዘ ። ከዚህም በኋላ ከእሳት ውስጥ ጨመሩዋቸው በውስጡም ሦስት ቀኖችና ሌሊቶች ኖሩ ያለ ጥፋትም በጤንነት ወጡ ዳግመኛም ከብረት አልጋ ላይ አስተኝተው ከበታቻቸው እሳትን አነደዱ እግዚአብሔርም ያለ ጥፋት ጠበቃቸው ። ‎ ‎መኰንኑም እነርሱን ማሠቃየት በሰለቸ ጊዜ ወደ ንጉሥ መለሳቸው ንጉሡም ዳግመኛ ታላቅ ሥቃይን አሠቃያቸው ቴዎዳዳ እናታቸውም የምታስታግሣቸው ንጉሡንና የረከሱ ጣዖቶቹን የምትረግም ሆነች ። ‎ ‎በዚያንም ጊዜ አንገቷን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ የሰማዕትንት አክሊልንም ተቀበለች ሥጋዋ ግን በምድር ላይ ወድቆ ነበር ቆዝሞስም እንዲህ ብሎ ጮኸ የዚች አገር ሰዎች ሆይ ይችን አሮጊት መበለት ሥጋዋን አፈር አልብሶ ይሠውራት ዘንድ ከውስጣችሁ ርኅራኄ በልቡ ያደረበት የለምን የህርማኖስ ልጅ ቅዱስ ፊቅጦርም በሰማ ጊዜ ተደፋፍሮ ሥጋዋን ገንዞ ቀበራት ። ‎ ‎ንጉሡም እነርሱን ማሠቃየት በሰለቸ ጊዜ ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ ። ከመከራውም ዘመን በኋላ ቤተ ክርስቲያን ተሠርታላቸው ሥጋቸውን በውስጧ አኖሩ ከእርሳቸውም ድንቆች የሆኑ ብዙዎች ተአምራት ተገለጡ ። ‎ ‎ወስብሐት ለእግዚአብሔር ‎ምንጭ :- መጽሐፈ ስንክሳር ‎💚 @ortodoxmezmur 💚 ‎💛 @ortodoxmezmur 💛 ‎❤️ @ortodoxmezmur ❤️ ‎
显示全部...
161🕊 11🥰 3
የልቤ ዜማ የልቤ ዜማ ነሽና ሰላም ነው ያንቺ ምስጋና ሞገሴ ነው ስምሽ ለኔ ስላለሽ ማርያም ከጎኔ
አዝ
በመገፍት ብኖር እምነቴን አፀናለሁ በጣቶችሽ  ተይዤ አዲሱ ቀን አያለሁ/2/ ስማፀን ደጅሽ መጥቼ ተመለሰኩ ተረጋግቼ እንደምን አንቺን እረሳለሁ በምልጃሽ ተፈውሻለሁ
አዝ
የጠላቶቼን አራስ የሚቀጠቅጠው የአብራክሽን ፍሬ ተስፍዬን አበራው /2/ የድኅነት ምክንያት አርጎሻል ለአዳም ዘር ትምክህት ሆነሻል የልቤ ብርሃን ፍና አዛኝት ባንቺ ልፅናና
አዝ
የአፌን እንጉርጉሮ ምስጋናዬ ወርሶታል እግሬ ከእረግረግ ወጥቶ በሰገነት ተተክሏል ዠ/2/ ሐዜኔን የምሻገረው ስምሽን እየጠራሁ ነው አገኘው ደስታ ሰላም ጠርቼ ብዬ ማርያም  ዘማሪ ዲያቆን እንዳለ ደረጀ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
显示全部...
6082726593_1 (16).mp35.09 MB
186🥰 6🕊 4😍 4
የጽዮን ደጆች የጽዮን ደጆች ቅኔ ተሞሉ ለድንግል ክብር እልል እያሉ እንደ ነጭ እንቁ የሚያበራ አርፈናል ስሟን ስንጠራ/2/ ኃይልን ለሚያደርገው ለተወዳጅ ስምሽ  የዜማ እቃችንን አነሳን ልጆችሽ  ማህተመ ቡራኬሽ በልባችን አለ  አፋችን ማርያም ሲል ጭንቃችን ቀለለ
አዝ
የምስጋና ጥበብ የቅኔ ሃብት ፀጋ ከደጃፍሽ መጥተን ገዛን ያለ ዋጋ ጥልቁን ወጥተነዋል በትከሻሽ ሆነን ፅዮንን በእልልታ በዜማ ሸፍነን
አዝ
ጠቢባን ምክራቸው ታየ ተሰውሮ ምስጢር ተገለጠ በህፃናት አእምሮ ቤተልሔም ሰማች የብስራቱን ዜማ ፍቅር ተለቀመ ከእግዚአብሔር ከተማ
አዝ
ከአሸናፊው ልጅሽ ከክርስቶስ ጋራ እንደ ዘበት ወጣን የሞትን ተራራ ፍሬሽን ቀምሰነው ልቦናችን ረጋ ሰላም ነው ከእንግዲህ አንኖርም ስንሰጋ
አዝ
ጠቢባን ምክራቸው ታየ ተሰውሮ ምስጢር ተገለጠ በህፃናት አእምሮ ቤተልሔም ሰማች የብስራቱን ዜማ ፍቅር ተለቀመ ከእግዚአብሔር ከተማ ዘማሪት ቅድስት ምትኩ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
显示全部...
Yetsiyon-Dejoch-የጽዮን-ደጆች.m4a8.49 MB
204🕊 6🔥 5🥰 2
ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን /2/ ውስተ አፍላገ ባቢሎን ኅየ ነበርነ ወበከይነ እንዚራቲነ ሰቀልነ ውስተ ኲሓቲሃ ባሰብናት ጊዜ ጽዮንን /2/ በባቢሎን ወንዞች አጠገብ ተቀምጠን አለቀስን መሰንቆአችንን ሰቀልን በዛፎቿ ላይ
አዝ
ፅኑ መከራን ተቀበልን ተጨነቅን በፈተና የደዌ ሞት በላያችን እንደዝናብ ወርዷልና አሕዛብም ዘበቱብን እንዲህ ብለው በየተራ ዘምሩለት ለአምላካችሁ ቢያድናችሁ ከመከራ እግዚአብሔር ጽዮንን በመንግስቱ መርጧታል እና ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወዷታል እና ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አንቺን ብንረሳ ቀኛችን ትርሳን
አዝ
የማረኩን በጦራቸው በኃይላቸው የተመኩ በጽዮን ደጅ ያለፍርሃት የጽዮንን ክብሯን ነኩ ይህን ያየ ከላይ ሆኖ በደመና ተሸፍኖ ባቢሎንን አሻገረ የማረኩንን በትኖ እግዚአብሔር ጽዮንን በመንግስቱ መርጧታል እና ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወዷታል እና ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አንቺን ብንረሳ ቀኛችን ትርሳን
አዝ
ስጋችንን ሊገንዘን የሞት ጥላ ቢያጠላም እናልፋለን ሁሉን ባንቺ የአምላክ እናት ድንግል ማርያም ቅድስት ሆይ ከባረክሽን እንድናለን ከደዌያችን ለስጋና ለነብሳችን መድኃኒት ነሽ እናታችን እግዚአብሔር ጽዮንን በመንግስቱ መርጧታልና ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወዷታልና ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አንቺን ብንረሳ ቀኛችን ትርሳን መጋቤ ምሥጢር ሰሎሞን ተስፋዬ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
显示全部...
ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን(1).mp37.49 MB
270🥰 12🕊 7😍 5
​​እንኳን ለጽዮን "ማርያም ማሕደረ አምላክ" እና ለቅዱሳኑ "ጐርጐርዮስ ወዮሐንስ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ "ጽዮን ማርያም" "ጽዮን" ማለት "ጸወን - አምባ - መጠጊያ" ማለት ነው:: አንድም በምሥጢሩ "ማሕደረ አምላክ" ማለት ነው:: ጽዮን የሚለው ስም በቁሙ ለቅዱስ ዳዊት ተራራና ለኪዳኑ ጽላት ሲያገለግል በትንቢታዊ ምሥጢሩ ግን ለድንግል ማርያም: ለቤተ ክርስቲያንና ለዘለዓለማዊት ርስት ያገለግላል:: እግዚአብሔር ከዘመነ አበው በሁዋላ በጊዜው ለእሥራኤላውያን ክብር: ሞገስ: አምባ የምትሆናቸውን ታቦተ ጽዮንን በቅዱስ ሙሴ አማካኝነት ሰጥቷቸዋል:: (ዘጸ. 31:18) ከዚያም ለ500 ዓመታት ከእነሱ ጋር በመሆኗ በፈጣሪና በእነሱ መካከል ድልድይ ሆና ኖራለች:: ከዚያም ባለቤቱ ሲፈቅድ በዘመነ ሳባ: በቀዳማዊ ምኒልክ (እብነ መለክ-እብነ ሐኪም) አማካኝነት ወደ ኢትዮዽያ መጥታለች:: እነሆ በሃገራችን የ3ሺ ዓመት ቆይታዋን ልትደፍን የቀራት ጥቂት ዓመታት ብቻ ናቸው:: ጌታ እንደ ፈቀደ ቅዱስ መስቀሉንና ታቦተ ጽዮንን ይዘን ይሔው በቸርነቱ እንኖራለን:: ያም ሆኖ ታቦተ ጽዮንን መስረቅ የሚፈልጉ ብዙ ቀሳጢዎች እንዳሉ እናውቃለን:: ግን አንጨነቅም:: ምክንያቱም የመጣችውም: የምትጠበቀውም በፈቃደ እግዚአብሔር ነውና እንጸልያለን እንጂ አንጨነቅም:: በተለያየ ወሬም ራሳችንን አናማጥንም:: ባለቤቱ እንድትሔድ ከፈቀደ ደግሞ ማንም ጉልበተኛ አያስቀራትም:: ታቦተ ጽዮን ብዙ ጊዜ "ጽላተ ኪዳን: ታቦተ ሕጉ" እየተባለች ትጠራለች:: "ጽሌ" ማለት "ሰሌዳ" እንደ ማለት ሲሆን "ጽላት" ደግሞ በብዙ ቁጥር ነው:: "ኪዳን" ደግሞ በፈጣሪና በሰው ልጆች መካከል ያለ "ውል - ስምምነት" ነው:: "ታቦት" ማለት "ማሕደር-ማደሪያ" እንደ ማለት ነው:: ሕጉ የተጻፈባቸውን ሰላድው "ጽላት" ስንላቸው የጽላቱ ማደሪያ ደግሞ "ታቦት" ይባላል:: ጽላት (ታቦትን) ያመጣ ፈጣሪ ነው:: በሐዲስ ኪዳንም ምሥጢርና ሐተታ ቢኖረውም 2 ቦታ ላይ ስለ ታቦት ተጠቅሶ እናገኛለን:: (2ቆሮ. 6:16, ራዕይ. 11:19) #በመጨረሻም_ኅዳር_21 ቀን ጽዮን ማርያምን የምናከብርባቸውን ምክንያቶች እንመለከታለን:: በዚህች ቀን:- 1. ታቦተ ጽዮን (ጽላተ ኪዳን) ለሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ መሰጠቷን እናስባለን:: ይሕ ሲሆንም ቅዱስ ሙሴ 40 መዓልት: 40 ሌሊት ጾሞ እንደ ተቀበለ ሳንዘነጋ ማለት ነው:: (ዘጸ. 31:18, ዘዳ. 9:19) 2. በዘመነ ኤሊ ሊቀ ካህናት ታቦተ ጽዮን በታሪኩዋ ለመጀመሪያ ጊዜ በአሕዛብ (ኢሎፍላውያን) እጅ ተማርካለች:: ግን ደግሞ ዳጐንን ቀጥቅጣዋለች:: (1ሳሙ. 5:1) 3. በዘመነ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በአሚናዳብ ሠረገላ ሁና: ከአቢዳራ ቤት ስትመጣ ቅዱሱ ንጉሥ በታላቅ ሐሴት በፊቷ ዘመረ: አገለገለ:: ምድራዊ ክብሩን እስኪረሳ ድረስ ለታቦተ አምላክ ተቀኘላት:: በዚህም ሜልኮል ንቃው ማሕጸኗ ተዘግቷል:: (1ዜና. 15:25) ሊቃውንትም "ድንግል እመቤታችን ማርያም በትንቢት መነጽር ተመልክቷል" ብለውናል:: "ሰላም ለኪ ማርያም እምነ:: ዘሰመይናኪ ጸወነ:: ሶበ እምርሑቅ ርእየ ዘጽላሎትኪ ስነ:: ለቢሶ ዳዊት ልብሰ ክብር ዘየኀይድ ዓይነ:: ቅድመ ታቦተ ሕግ ኀለየ ወዓዲ ዘፈነ::" እንዲል:: (አርኬ ዘኅዳር 21) 4. በዘመነ ንጉሥ ሰሎሞን (መፍቀሬ ጥበብ) ግሩም የሆነ ቤተ መቅደስ ተሰርቶላት ስትገባ ታላቅ ሐሴት ተደርጉዋል:: እግዚአብሔርም በደመና ወርዶ ንጉሡን አነጋግሯል:: (2ዜና. 5:1, 1ነገ. 8:1) 5. በዚያው ዘመንም በፈጣሪ ፈቃድ ንጉሥ ምኒልክ ቀዳማዊ (ዕብነ ሐኪም) ታቦተ ጽዮንን ይዞ ወደ ኢትዮዽያ ገብቷል:: 6. በዘመነ አፄ ባዜን (በ4 ዓ/ም አካባቢ) አማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያም ወደ አክሱም ጽዮን በስደት መጥታ ገብታለች:: በዚህ ጊዜም 2ቱ ጽዮኖች ሲገናኙ ታላቅ ብርሃን አክሱምን ውጧታል:: 7. በ4ኛው መቶ ክ/ዘመንም ነገሥት ጻድቃን አብርሐ ወአጽብሐ 12 መቅደሶች ያሏትን ግሩም ቤተ ክርስቲያን ለእመ ብርሃን ሠርተው በዚሁ ቀን በጌታችን ተቀድሷል:: 8. በተጨማሪም በየጊዜው: ማለትም በዮዲት ጉዲትና በግራኝ አማካኝነት ስትፈርስ ወደ ዝዋይ ትሰደድ ነበር:: ተመልሳ ስትታነጽም ቅዳሴ ቤቷ የሚከበረው ኅዳር 21 ቀን ነው:: በእነዚህና በሌሎች ምክንያቶች ይህ በዓል ልዩ ነው:: " አማናዊት ጽዮን እመ ብርሃን ድንግል ማርያምን እንዲህ እንላታለን " "ቅድስት" የሚለው ቃል ለሁሉም ቅዱሳት እናቶች ቢሰጥም ቅሉ ለድንግል ማርያም ሲሰጥ ግን ትርጉሙ ይለያል:: እርሷ "ቅድስተ ቅዱሳን: ንጽሕተ ንጹሐን: ቡርክት እምቡሩካን: ኅሪት እምኅሩያን" ናትና:: ከሰው ልጆችም ሁሉ ትበልጣለች:: ይቅርና የሰው ልጅን ንጹሐን መላእክትንም በንጽሕናና በቅድስና ትበልጣቸዋለች:: እርሷ እመ ብርሃን: የአምላክ እናቱ: የሰውነታችን መመኪያ ናትና:: #እመቤታችንን "ቅድስት" ስንል "ጽንዕት: ንጽሕት: ክብርት: ልዩ" ማለታችን ነው:: 1. "ንጽሕት" ትባላለች:: ሌሎች ቅዱሳን ቢነጹ ከገቢር: ከነቢብ ኃጢአት ነው እንጂ ከኃልዮ ኃጢአት አይደለም:: እርሷ ግን ከነቢብ: ከገቢር: ከኃልዮ ንጽሕት ናት:: "ለመኑ ተውኅቦ ተደንግሎ ኅሊና: ለመላእክትሂ ኢተክህሎሙ-ኃጢአትን ከማሰብ መጠበቅ ከሰው ልጆች ለማን ተሰጠው: ይህስ ለመላእክትም አልተቻላቸውም" እንዲል:: (ተአምረ ማርያም) 2. "ጽንዕት" እንላታለን:: ሴቶች ቢጸኑ ለጊዜው ነው እንጂ በሁዋላ በጊዜው ተፈትሆ አለባቸው:: እመቤታችን ግን ቅድመ ጸኒስ: ጊዜ ጸኒስ: ድኅረ ጸኒስ: ቅድመ ወሊድ: ጊዜ ወሊድ: ድኅረ ወሊድ ድንግል ናትና:: ¤ "ጽንዕት በድንግልና አልባቲ ሙስና" እንዳላት:: (ቅዱስ ያሬድ) ¤ ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስም "ወትረ ድንግል ማርያም-ማርያም ዘለዓለማዊት ድንግል ናት" እንዳለ:: (መጽሐፈ ቅዳሴ) 3. ድንግልን "ክብርት" እንላታለን:: ሌሎች ሴቶች ቢከብሩ ጻድቃን ሰማዕታትን: ነቢያት ሐዋርያትን ወልደው ነው:: እመቤታችንን ግን የምናከብራት "ወላዲተ አምላክ-የአምላክ እናቱ" ብለን ነውና:: 4. እመቤታችንን "ልዩ" እንላታለን:: ከእርሷ በቀር እናት ሁና ድንግል: እመቤት ሁና አገልጋይ የሆነች: በድንግልና ወልዳ ወተትን (ሐሊበ ድንግልናዌን) ያስገኘች ሌላ ሴት የለችምና:: #ሼር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
显示全部...
449🕊 29😍 3
ትምክህተ ዘመድነ ትምክተ ዘመድነ/2/ ማርያም ዕምነ ማርያም ትምክህተ ዘመድነ
አዝ
የድነታችን አርማ የነፃነታችን የህይወት መሰረት ነሽ ድንግል እናታችን አንቺን ለኛ ዘርን ባያስቀር እንደጥንቱ እንደ ሰዶም ምድር ሁላችን በጠፋን ነበር
አዝ
የአብርሀም ድንኮን ነሽ አምላክ ያደረብሽ የጌድዮንም ፀምር ለይቶ ያከበረሽ የኛ ቤዛ በጉ የተያዘብሽ የዋህ ርግብ  ከ አበውስር የተገኘሽ እፀሳቤቅ የህይወት ሀረገ ነሽ
አዝ
አምላክ ከሰማይ ሆኖ ይችን አለም ሲቃኝ ንፅህይት ቅድስት ሁነሽ ማርያም አንቺን ቢያገኝ ትህትናሽን ሂወትሽንም ወዶ ቃል ሰው ሆነ ከሰማያት ወርዶ አከበረሽ በፋፁም ተዋህዶ
አዝ
የመዳናችን ምክንያት የሰው ልጆች ሰላም ከሀጢያት ከመርገም የዳነብሽ አለም አምስት ሺ አምስት መቶ ዘመን በሲኦል ውስጥ ተግዘን የኖርን ድንግል ባንቺ ነፃነት አገኘን 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
显示全部...
የመዝሙር_ግጥሞች_ትምክህተ_ዘመድነ_16k.m4a6.63 KB
154🕊 10🔥 1
ሕዳር 21/03/2018 ዓ.ም የሕዳር ጽዮን ማርያም ✝ በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ። ዲያቆን፦ 2ቆሮ 7÷12-ፍ.ም ንፍቅ ዲያቆን፦ 1ጴጥ 2÷5-11 ንፍቅ ካህን፦ ግብረ ሐዋርያት፦ 7÷44-59
ምስባክ ፦ መዝ 131÷13-15
እስመ ሐረያ እግዚአብሔር ለጽዮን ወአብደራ ከመትኩኖ ማህደሮ ዛቲ ይእቲ ምዕራፍየ ለዓለም
ትርጉም
እግዚአብሔር ጽዮንን መርጧታልና ማደርያውም ትሆነው ዘንድ ወዷታልና እንዲህም ብሎ ይህች የዘለዓለም ማረፊያዬ ናት ወንጌል ፦ ማቴ 21÷42-ፍ.ም ቅዳሴ ፦ ዘእግዝእትነ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
显示全部...
ነይ ነይ ማርያም ዝማሬ ዳዊት6.85 KB
119🥰 4🔥 3
‎ኅዳር ፳ /20/ ‎ ‎በዚች ቀን ቅዱስ አባት አንያኖስ አረፈ እርሱም ለወንጌላዊ ማርቆስ ሁለተኛ የሆነ የእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት ነው። ‎ ‎የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ አረማውያን ናቸው እርሱም ጫማ ሰፊ ነበር ቅዱስ ወንጌላዊ ማርቆስም ወደ እስክንድርያ አገር መጀመሪያ በገባ ጊዜ እግሩን ተደናቅፎ ጫማው ተቆረጠ እንዲሰፋለትም ወደ ጫማ ሰፊ አንያኖስ ዘንድ ሔደና ጫማውን ሰጠው መስፋትም በጀመረ ጊዜ መስፊያው ጣቱን ወጋው በዮናኒም ቋንቋ አታኦስ አለ ትርጓሜውም አንድ እግዚአብሔር ማለት ነው ። ቅዱስ ማርቆስም የእግዚአብሔርን ስም ሲጠራ በሰማ ጊዜ ደስ ብሎት የክብርባለቤት ክርስቶስን አመሰገነው ። ‎ ‎ከዚህም በኋላ አፈር አንሥቶ በምራቁ ጭቃ አድርጎ በአንያኖስ ጣት ላይአደረገውና በዚያን ጊዜ አዳነው አንያኖስም ከዚህ ድንቅ ምልክት የተነሣ አደነቀ ቅዱስ ማርቆስንም ወደ ቤቱ ወሰደው ስለ ሥራው ስለ አምልኮቱም የመጣውም ከወዴት ቦታ እንደሆነ ጠየቀው ። ‎ ‎ቅዱስ ማርቆስም ከብሉያትና ከሐዲሳት መጻሕፍት የአንድ እግዚአብሔርን ህልውና ስለ ዓለሙ ሁሉ ድኅነት የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን፣ መከራ መስቀልንም ተቀብሎ ስለመሞቱ፣ ስለ ትንሣኤውና፣ ስለዕርገቱ፣ ዳግመኛም ለፍርድ ስለ መምጣቱ ይነግረው ጀመረ ። ‎ ‎የአንያኖስም ልቡ ብሩህ ሆኖለት በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ ከቤተሰቡ ሁሉ ጋር ተጠመቀ ። የመንፈስ ቅዱስም ጸጋ በላያቸው ወረደ አዘውትሮ በመጠመድ የሐዋርያ ቅዱስ ማርቆስን ትምህርት የሚሰማ ሆነ የቤተ ክርስቲያንንም ትምህርት ሕጓንና ሥርዓቷንም ተማረ ። ‎ ‎ቅዱስ ማርቆስም ወደ ሌሎች አገሮች ሒዶ ለማስተማር በፈለገ ጊዜ እጆቹን በአንያኖስ ላይ ጭኖ በግብጽ አገር ለወገኖቹ ወንጌልን ይሰብክ ዘንድ ሊቀ ጵጵስና ሾመው እርሱም ብዙዎችን አስተምሮ አጠመቃቸው በቀናች ሃይማኖትም አጸናቸው ቤቱንም ቤተ ክርስቲያን አደረጋት እርሷም በስተምዕራብ ከእስክንድርያ ከተማ ውጭ ያለች ዛሬ የሰማዕት ቅዱስ ሰርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሁና የታወቀች ናት ። ‎ ‎ይህ የተመሰገነ አባት አንያኖስም በወንጌላዊ ማርቆስ ወንበር ዐሥራ ሁለት ዓመት ኖረ እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ ። ‎ ‎ወስብሐት ለእግዚአብሔር ‎ምንጭ :- መጽሐፈ ስንክሳር ‎💚 @ortodoxmezmur 💚 ‎💛 @ortodoxmezmur 💛 ‎❤️ @ortodoxmezmur ❤️ ‎
显示全部...
176🥰 14🕊 4
ኦ ክርስቶስ ኦ ክርስስ ኦ አምላክ ብሩህ ነህ/2/ ልቦናዬን አብራው በጥዑም ቃልህ/2/
አዝ
የታቦር ደመና  ክርስቶስ የሲና ልምላሜ ክርስቶስ ምነው ሙሴን በሆንኩ  ክርስቶስ እንዳይህ ቀድሜ   ክርስቶስ የዮርዳኖስ ውሃ      ክርስቶስ በላዬ ሲፈላ           ክርስቶስ የሐንስን በሆንኩ እንዳይህ በተድላ
አዝ
ነበልባል ሐመልማል   ክርስቶስ ተዋህዶ ሲና   ክርስቶስ ሙሴ ከሩቅ ሆኖ  ክርስቶስ ተመልክቷልና      ክርስቶስ በቀረበ ጌዜም     ክርስቶስ ነገሩን ሲረዳ        ክርስቶስ ለእሥራኤል ሾምከው ሁሉ እንዳይጎዳ
አዝ
ሙሴ በበትሩ     ክርስቶስ ኤርትራን ሲመታ   ክርስቶስ ተሻገሩ እሥራኤል  ክርስቶስ በብዙ ደስታ    ክርስቶስ ያልተደሰቱማ   ክርስቶስ የፈርኦን ሠራዊት  ክርስቶስ እየተሰጠሙ ቀሩ ወደ ኀላ
አዝ
ትንቢቱ ጸደቀ   ክርስቶስ የኢሳይያስ      ክርስቶስ ድንግልም ወለደች  ክርስቶስ በመንፈስ ቅዱስ  ክርስቶስ ምነው ባደረገኝ   ክርስቶስ እንደ ሰሎሜ      ክርስቶስ ጌታዬ ሲወለድ ለማመስገን ቆሜ
አዝ
ሐዋርያት ሁሉ        ክርስቶስ ዞረው ያስተማሩት  ክርስቶስ ወንጌልህ ብርሃን ነው  ክርስቶስ የዓለም መድሃኒት  ክርስቶስ ዮሐንስ እንዳለው   ክርስቶስ ጥምቀት ለንሰሐ   ክርስቶስ እጠመቀዋለሁ የጎንህን ውሃ
አዝ
ሚካኤል በቀኝህ  ክርስቶስ ገብርኤል በግራ  ክርስቶስ ቅውማን የሆኑት  ክርስቶስ ሁሉም በየተራ     ክርስቶስ ሱራፌል ኪሩቤል  ክርስቶስ ዐይናቸው የበዛ    ክርስቶስ ያመሰግኑሃል አንተን የዓለም ቤዛ ዘማሪ  ታዴዎስ ግርማ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
显示全部...
- - - - - - - - 7xLaXWMEezA.m4a5.25 MB
175🥰 6🕊 5😍 2
ኅዳር ፲፱ /19/
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ኅዳር ዐሥራ ዘጠኝ በዚች ቀን ሩጻፋ በሚባል አገር የሰማዕት ሰርጊስ ቤተ ክርስቲያን የከበረችበት ነው። ይህም ቅዱስ ሰርጊስ በሩጻፋ አገር በሰማዕትነት በአረፈ ጊዜ ምእመናን ሥጋውን ወስደው ገንዘው በእነርሱ ዘንድ አኖሩት በፊቱም መብራቶችን አኖሩ የመከራውም ዘመን እስቲያልፍ በእነርሱ ዘንድ ተሠውሮ ኖረ። ከዚህም በኋላ ያማረች ቤተ ክርስቲያንን አነፁለት ዐሥራ አምስት ኤጲስቆጶሳትንም ሰብስበው አከበሩዋት በዚች ቀን ሥጋውንም በውስጧ አኖሩ ከእርሱም ድንቅ ተአምር ተገለጠ በእምነት ከእርሱ ለሚወስዱ ሁሉ በሽተኞችን የሚፈውሳቸው ሽታው እጅግ ጣፋጭ የሆነ የሽቱ ቅባት ከሥጋው የሚፈስ ሁኗልና። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
显示全部...
149🕊 6🥰 5
ነጋ ላመሰግንህ ነው ነጋ ላመሰግንህ ነው/3/ ጌታ አንደበቴን ፍታው
አዝ
የንዋም ፀሎት አድርጌ እተኛለሁ አምላኬ አንተን አምኜ ነው ለሽፋሽፍቴ እንቅልፍን ጌታ አንተርሰኝ ክንድህን
አዝ
ስጋዬን ትታ ነብሴ ትዞራለች ሌሊቱን ሙሉ ትቃዣለች የያእቆብ ሌሊት አርግላት ስሜቷ ከእሳት ሳይጥላት
አዝ
ድቅድቅ ጨለማው ገፎ ሄደ በምስራቅ ፀሀይ ጎህ ቀደደ ተኝቶ ሠላም መነሳት ባንተ ፈቃድ ነው የኔ አባት
አዝ
ሌሊቱን ሙሉ ተኝቼ አነባለሁ በእንባዬ አልጋዬን አርሻለሁ ልተው ልነሳ ከሀጥያት በጽድቅ ልቁም ባንተ ፊት
አዝ
በየ ቋንቋቸው አእዋፍ አዜሙ ልብ ይመስጣል በአንክሮ ሲሰሙ አያስታጉሉም በየእለቱ የሠው ሲደክም አንደበቱ ዘማሪ ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
显示全部...
ነጋ_ላመሰግንህ_ነው_አዲስ_መዝሙር_ቀሲስ_እንግዳወርቅ_በቀለ_Kesis_Engdawork_Bekele.m4a5.31 MB
147
በስራዬ በስራዬ የት ይሆን መግቢያዬ/2/ ጨነቀኝ ጠበበኝ ኧረ ወዲያልኝ ጨነቀኝ ጠበበኝ ነፍሴ ወዲያልኝ
አዝ
ተሸክሜ የኃጥያት ክምር/2/ ይመሻል ይነጋል በከንቱ ስዞር/2/ ገሰገሰ ቀኑ ጨለመብኝ/2/ ዋ ለነብሴ ምንም ስንቅ አልያዝኩኝ/2/
አዝ
በድያለሁ ወዳንተ ጮሃለሁ ይቅር በለኝ እማፀንሃለሁ ችላ አትበለኝ ከፊትህ ቆሜያለሁ/2/
አዝ
አለፈብኝ በከንቱ ጊዜዬ/2/ እየጓጓሁ ለዚች ለሥጋዬ/2/ በንስሐ ሳላጥበው እድፌን/2/ ልትደርስ ነው ያች ፈተና ቀን/2/ በኩረ ዘማርያን ኪነጥበብ ወ/ቂርቆስ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
显示全部...
ዝማሬ_ዳዊት_በስራዬ_የት_ይሆን_መግቢያዬ_16k.m4a9.30 KB
star reaction 50 169🥰 18🕊 10🔥 2
‎ሕዳር ፲፰ /18/
‎ ‎በዚችም ዕለት ከሮሜ አገር ቅዱስ ኤላውትሮስና እናቱ እንትያ በሰማዕትነት አረፉ ። ይህም ቅዱስ እግዚአብሔርን ከሚፈራ አንቂጦስ ከሚባል ኤጲስቆጶስ ዘንድ አደገ ዐሥራ ሰባት ዓመትም በሆነው ጊዜ ዲቁና ተሾመ ደግሞ በዐሥራ ስምንት ዐመቱ ቅስና ተሾመ ከዚህም በኋላ በሃያ ዓመቱ አላሪቆስ ለሚባል አገርጵጵስና ተሾመ ። ‎ ‎በዚያንም ወራት ንጉሥ እንድርያኖስ ወደ ሮሜ አገር መጣ ስለ ኤላውትሮስም ሰምቶ ወደርሱ ያመጣው ዘንድ ፊልቅስን አዘዘው ፊልቅስም በሔደ ጊዜ ቅዱሱን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የእግዚአብሔርን ቃል ሲያስተምር አገኘው ። ፊልቅስም ትምርቱን በሰማ ጊዜ አመነና በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቀ ። ‎ ‎ኤላውትሮስንም ወደ ንጉሥ እንድርያኖስ በአደረሱት ጊዜ ለአማልክት ሠዋ አንተ ነጻነት ያለህ ስትሆን ለተሰቀለ ሰው ለምን ትገዛለህ አለው ። ኤላውትሮስም ነጻነትማ ሰማይና ምድርን በፈጠረ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ነው ንጉሡም መንኰራኩር ካለው የእሳት ማንደጃ ውስጥ ጨምረው እንዲአቃጥሉት አዘዘ በጨመሩትም ጊዜ እሳቱ ጠፋ መንኩራኩሩም ተቆራረጠ ። ንጉሡም አይቶ አደነቀ የሚያደርገውንም አጥቶ ከወህኒ ቤት ጨመረው ርግብም ከገነት መብልን አምጥታለት በልቶ ጠገበ ። ቆሊሪቆስ የሚባለውም መኰንን አይቶ በቅዱስ ኤላውትሮስ አምላክ አምኖ በሰማዕትነት ሞተ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበለ ። ‎ ‎ከዚህም በኋላ ፈረሶችን አምጥተው በሠረገላ ላይ እንዲጠምዷቸው ቅዱስ ኤላውትሮስንም ከሠረገላው በታች አሥረው ሕዋሳቱ እስኪሰነጣጠቅ ፈረሶችን እንዲአስሮጡአቸው እንድርያኖስ አዘዘ ። በዚያንም ጊዜ የእግዚአብሔርመልአክ ወረደ ከማሠሪያውም ፈትቶ ወደ ከፍተኛ ተራራ ወሰደው በዚያም እግዚአብሔርን እያመሰገነ ከአራዊት ጋር ተቀመጠ ። ‎ ‎እንድርያኖስም አራዊትን ያድኑ ዘንድ ወታደሮቹን በአዘዘ ጊዜ በዚያ ተራራ ውስጥ ቅዱስ ኤላውትሮስን አግኝተው ከዚያ ወደ ንጉሥ እንድርያኖስ ወሰዱት ። ንጉሡም ለአንበሳ እንዲሰጥ አዘዘ አንበሶችም የፊቱን ላብ ጠረጉለትና እግሮቹን ሳሙ ከዚህም በኋላ ተመልሰው ከአረማውያን መቶ ሃምሳ ሰው ገደሉ እንድርያኖስም አይቶ ቁጣን ተመላ ሁለት ወታደሮችን ከእንትያ እናቱ ጋርበጦር እንዲወጉት አዘዘ እርሷንም ብዙ ከአሠቃይዋት በኋላ የልጅዋን አንገት እንዳቀፈች ከእርሱ ጋር ወጓት ነፍሳቸውንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጡ ። ‎ ‎ወስብሐት ለእግዚአብሔር ‎ምንጭ :- መጽሐፈ ስንክሳር ‎💚 @ortodoxmezmur 💚 ‎💛 @ortodoxmezmur 💛 ‎❤️ @ortodoxmezmur ❤️ ‎ ‎
显示全部...
180🕊 16😍 7
የማደርገውን አላውቅም የማደርገውን አላውቅም ይቅር በለኝ አባቴ የማደርገውን አላውቅም ይቅር በለኝ አባቴ ቸንክሬሃለው በበደሌ ቸንክሬሃለው በኃጢያቴ/2/
አዝ
ድምጼን ከፍ አድርጌ እያልኩኝ ተዋቸው የነገድ ቋንቋ ዘገን እፈልጋለሁ አልታረቅ አለኝ ቃልና ተግባሬ ኃይልህን ክዳለሁ ኃይልህን መስክሬ/2/
አዝ
ለኃጥያት ልሞት ነው የሞትክልኝ ለኔ ጨለማዬን የሻርክ ጌታ ብርሃኔ እጠበኝ ቆሸሽኩኝ ሆንኩኝ እንደ እሪያ ዘመን ጨምርልኝ ይቅርታህን ማያ/2/
አዝ
ህመም የሚነቅል መድኃኒት አግኝቼ የተሰሎንቄን ድምጽ ማባበል ሠምቼ ወደፊት ስትጠራኝ ሄድኩኝ ወደኋላ ማረፍ አቅቶኛል በምሕረትህ ጥላ/2/
አዝ
ለኔ ያሠብካትን ሃሳብህን ትቼ ማዕረጌን ጥያለሁ ከእቅፍህ ወጥቼ በመስቀልህ ስራ ካወረስከኝ ስፍራ እንድኖር አግዘኝ ሁሌ ካንተ ጋራ/2/
አዝ
ፍቅርን ስታጎርሰኝ እጅህን ነክሼ ለጽድቅ አነጻኸኝ በበደል ፈርሼ ህያው ነኝ ለኃጢአት ዳግም የሰቀልኩህ መራራዬን አጣፍጥ ጌታ ተማጸንኩህ
አዝ
ወዴት ነህ ስትለኝ በማፍርበት ቦታ እንዳልገኝ እርዳኝ ትችላለህ ጌታ ትልቁ ትንሹ ማንም ወደኔ ሲያይ አንተ ተንጸባረቅ በማንነቴ ላይ/2/ ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
显示全部...
የማደርገውን_አላውቅም_ሊቀ_መዘምራን_ቴዎድሮስ_ዮሴፍ.m4a10.39 MB
130🕊 7🥰 5