ch
Feedback
TIKVAH-SPORT

TIKVAH-SPORT

前往频道在 Telegram

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ስፖርት ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የስፖርታዊ መረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። በዚህ ቻናል ሀገራዊ እና አለም አቀፋዊ የስፖርት መረጃዎች ይዳሰሱበታል። ለመረጃ እና ማስታወቂያ +251926797469

显示更多
2025 年数字统计snowflakes fon
card fon
272 646
订阅者
-5524 小时
+107
+1 35830
帖子存档
照片不可用在 Telegram 中显示
መቐለ 70 እንደርታ የመጀመሪያ ድሉን አሳክቷል ! በ ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር መቐለ 70 እንደርታ ከአርባምንጭ ከተማ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል። የመቐለ 70 እንደርታን የማሸነፊያ ግቦች ብርሀኑ አዳሙ 2x ከመረብ ማሳረፍ ችሏል። መቐለ 70 እንደርታ በውድድር አመቱ የመጀመሪያ የፕሪሚየር ሊግ ድሉን ማሳካት ችሏል። የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ? 1️⃣8️⃣ መቐለ 70 እንደርታ :- 8 ነጥብ 2️⃣0️⃣ አርባምንጭ ከተማ :- 5 ነጥብ @Tikvahethsport       @kidusyoftahe
显示全部...
49👏 8👎 5👍 4
照片不可用在 Telegram 中显示
“ ፈርናንዴዝን መተካት የማይቻል ነው “ ሩበን አሞሪም “ ነገርግን ሀሳብ አለኝ “ የማንችስተር ዩናይትዱ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ብሩኖ ፈርናንዴዝ እና ኮቢ ማይኖ ከኒውካስል ዩናይትድ ጨዋታ ውጪ መሆናቸውን ገልጸዋል። በተጨማሪም ሀሪ ማጓየር እና ማትያስ ዴሊት ከጨዋታው ውጪ መሆናቸውን አሰልጣኙ ተናግረዋል። አሰልጣኙ አክለውም ኮቢ ማይኖ ከብሩኖ ፈርናንዴዝ ቀድሞ ወደ ሜዳ ይመለሳል የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል። ፈርናንዴዝ ለምን ያህል ጊዜ ይቆያል ብዬ መጠየቅ አልፈልግም ያሉት ሩበን አሞሪም " ሀሳብ አለኝ እናያለን “ ሲሉ እቅድ እንዳላቸው ጠቁመዋል። “ ፈርናንዴዝን መተካት የማይቻል ነው “ ያሉት አሰልጣኙ ነገርግን ሌሎች ተጨዋቾች እድል ያገኛሉ ለተጨዋቾቹ ይህንኑ ብያቸዋለሁ በአንድ ተጨዋች ላይ መመርኮዝ አንችልም ብለዋል። የተወሰኑ ጉዳቶች አሉብን ነገርግን በዚህ ቡድን እተማመናለሁ በተጨዋቾቼ ሙሉ እምነት አለኝ “ ሩበን አሞሪም @Tikvahethsport       @kidusyoftahe
显示全部...
172😁 78😢 16👍 11🔥 4
照片不可用在 Telegram 中显示
60 ' ቡርኪናፋሶ 0 - 0 ኢኳቶሪያል ጊኒ @Tikvahethsport       @kidusyoftahe
显示全部...
24👎 1
照片不可用在 Telegram 中显示
እረፍት ቡርኪናፋሶ 0 - 0 ኢኳቶሪያል ጊኒ @Tikvahethsport       @kidusyoftahe
显示全部...
25
照片不可用在 Telegram 中显示
22 ' ቡርኪናፋሶ 0 - 0 ኢኳቶሪያል ጊኒ @Tikvahethsport       @kidusyoftahe
显示全部...
31
照片不可用在 Telegram 中显示
“ በሞሮኮ ሥራ ልንኮራ ይገባል “ ሀቴም ትራቤልሲ በተንታኝነት እያገለገለ የሚገኘው የቀድሞ ተጨዋች ሀቴም ትራቤልሲ በአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጇ ሞሮኮ ሥራ መደነቁቅ ተናግሯል። “ በሞሮኮ መኩራት እና ማመስገን አለብን “ ያለው ተጨዋቹ በዝናብ ምክንያት ውድድሩን ማዘጋጀት ቀላል አይደለም ብሏል። “ በከባድ ዝናብ ምክንያት ጨዋታዎች ማድረግ ቀላል ባይሆንም አንድም ጨዋታ በግርፍ ምክንያት ሲራዘም አላየንም “ ሲል ሀገሪቱ ያደረገችውን ዝግጅት አድንቋል። የቀድሞ የማንችስተር ሲቲ እና አያክስ የመስመር ተጨዋች ሀቴም ትራቤልሲ በአሁኑ ሰዓት በቤን ስፖርት ተንታኝነት እየሰራ ይገኛል። ሀቴም ትራቤልሲ 2004 ከሀገሩ ቱኒዚያ ጋር የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ እንደነበር ይታወሳል።
显示全部...
147👏 28👍 10🙏 2
照片不可用在 Telegram 中显示
2 ' ቡርኪናፋሶ 0 - 0 ኢኳቶሪያል ጊኒ @Tikvahethsport       @kidusyoftahe
显示全部...
👍 13 11👏 2
照片不可用在 Telegram 中显示
የላሊጋ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ? የስፔን ላሊጋ የ 2025/26 የውድድር ዘመን የወርሀ ጥቅምት የወሩ ምርጥ ተጨዋች አምስት እጩዎች ይፋ ተደርገዋል። በዚህም መሰረት :- - ኪሊያን ምባፔ ( ሪያል ማድሪድ ) - ላሚን ያማል ( ባርሴሎና ) - ኮኬ ( አትሌቲኮ ማድሪድ ) - ቫሌራ ( ኤልቼ ) - ራዱ ( ሴልታቪጎ ) በእጩነት መቅረብ የቻሉ ተጨዋቾች ናቸው። @tikvahethsport     @kidusyoftahe
显示全部...
44👍 41
照片不可用在 Telegram 中显示
የላሊጋ የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ማን ይሆናል ? የስፔን ላሊጋ የ 2025/26 የውድድር ዘመን የወርሀ ኅዳር የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ሶስት እጩዎች ይፋ ተደርገዋል። በዚህም መሰረት :- - የባርሴሎናው አሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ - የሴልታቪጎ አሰልጣኝ ክላውድዮ ጊራልዴዝ እና - የሲቪያው አሰልጣኝ ማኖሎ ጎንዛሌዝ በእጩነት ቀርበዋል። @tikvahethsport     @kidusyoftahe
显示全部...
51👍 3
የጨዋታ አሰላለፍ ! 9:30 ቡርኪናፋሶ ከ ኢኳቶሪያል ጊኒ
显示全部...
36
照片不可用在 Telegram 中显示
ነገሌ አርሲ ወሳኝ ድል አሳክቷል ! በ ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ መርሐ ግብር ነገሌ አርሲ ከወልዋሎ ዓ.ዩ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1ለ0 አሸንፏል። የነገሌ አርሲን የማሸነፊያ ግብ አሸብር ውሮ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል። ነገሌ አርሲ ካለፉት ስድስት ጨዋታዎች አራቱን በአሸናፊነት ሲወጣ በአንዱ ተሸንፎ በቀሪው አቻ ተለያይቷል። የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ? 7️⃣ ነገሌ አርሲ :- 16 ነጥብ 1️⃣8️⃣ ወልዋሎ ዓ.ዩ  :- 8 ነጥብ ቀጣይ መርሐግብር ሰኞ - ወልዋሎ ዓ.ዩ ከ ባሕርዳር ከተማ ማክሰኞ - ድሬዳዋ ከተማ ከ ነገሌ አርሲ @Tikvahethsport       @kidusyoftahe
显示全部...
78🔥 4👍 3👎 1
照片不可用在 Telegram 中显示
“ አስቶን ቪላ በሙሉ በራስ መተማመን ላይ ነው “ ማሬስካ የሰማያዊዎቹ አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ቀጣዩ የአስቶን ቪላ ጨዋታ “ ለእኛ በጣም ከባድ ጨዋታ ይሆናል “ ሲሉ ገልፀውታል። “ በምርጥ ብቃታችን ላይ መሆን አለብን “ ያሉት ማሬስካ “ ምክንያቱም አስቶን ቪላ አስደናቂ አቋም እያሳየ ነው “ብለዋል። “ እነሱ የራሳቸው አጨዋወት አላቸው ከኳስ ጋር እና ከኳስ ውጪ በደንብ የተደራጁ ናቸው “ ሲሉ ኢንዞ ማሬስካ ተናግረዋል። “ በአሁኑ ሰዓት አስቶን ቪላ በሙሉ በራስ መተማመን ላይ ነው ፤ ነገርግን እኛ በሜዳችን ነው የምንጫወተው ሶስት ነጥቡን ለመውሰድ ጥረት እናደርጋለን። “ ማሬስካ
显示全部...
🔥 150 114👍 31😁 17
照片不可用在 Telegram 中显示
የዩጋንዳን ግብ ያስቆጠረው ኦሜዲ ማን ነው ? ትላንት ምሽት ዩጋንዳ በቱኒዚያ 3ለ1 በተሸነፈችበት ጨዋታ ብቸኛዋን የዩጋንዳ ግብ ዴኒስ ኦሜዲ አስቆጥሯል። ዴኒስ ኦሜዲ የትርፍ ጊዜ እግርኳስ ተጨዋች እንደነበር ሲገለፅ ትምህርቱን ተከታትሎም በነርሲንግ ዲፕሎማውን አግኝቷል። በኋላም ተጨዋቹ የህይወት መንገዱ ተቀይሮ የእስር ቤት ጥበቃ ሰራተኛ በመሆን እያገለገለ እንደነበር ተገልጿል። የ 31ዓመቱ ዴኒስ ኦሜዲ ከስድስት አመታት በኋላ ግን ሀገሩን በአፍሪካ ዋንጫ ውድድር መወከል ችሏል። ተጨዋቹ በመጀመሪያ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎውም ለሀገሩ ዩጋንዳ ጎል ማስቆጠር ችሏል። @tikvahethsport     @kidusyoftahe
显示全部...
392😁 111👏 87👍 11
照片不可用在 Telegram 中显示
“ ሞሮኳውያን ደማቅ አቀባበል አድርገውልናል “ ሪያድ ማህሬዝ የአልጄሪያ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋች ሪያል ማህሬዝ ቡድናቸው ከሞሮኮ ጥሩ አቀባበል እንደተደረገለት ገልጿል። “ ሞሮኳውያን ጥሩ አቀባበል አድርገውልናል ያለው ማህሬዝ “ በጎረቤት ሀገር በመሆናችን በጣም ደስተኞች ነን “ ብሏል። ከአልጄሪያዊ አባት እና ሞሮኳዊ እናት እንደተገኘ የገለፀው ማህሬዝ " ይሄ ውድድሩን ለእኔ የተለየ ያደርገዋል “ ሲል ተናግሯል። " ከአልጄሪያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ታሪክ መፃፍ ለመጀመር ዛሬ ትክክለኛው ቀን ነው “ ማህሬዝ @tikvahethsport     @kidusyoftahe
显示全部...
245😁 12👍 10🔥 4
照片不可用在 Telegram 中显示
“ የአንጎላ ደጋፊ ነኝ “ ካማቪንጋ ፈረንሳዊው የሪያል ማድሪድ አማካይ ካማቪንጋ በአፍሪካ ዋንጫው የአንጎላ ብሔራዊ ቡድን ደጋፊ መሆኑን ተናግሯል። “ በአፍሪካ ዋንጫው ከአንጎላ ጎን ነኝ “ ያለው ካማቪንጋ “ ያለፈውን ውድድር ተከታትያለሁ ጥሩ ተጫውተን ነበር ሲል ገልጿል። አክሎም “ አንጎላ በዚህ አመት ጥሩ እድል አላት “ ሲል ያለውን እምነት ተናግሯል። ኤድዋርዶ ካማቪንጋ ከዲሞክራቲክ ኮንጓዊያን ቤተሰቦቹ አንጎላ የስደተኞች ማቆያ ጣቢያ ውስጥ ነበር የተወለደው። ተጨዋቹ ከቤተሰቡ ጋር ወደ ፈረንሳይ በማምራት በፈረንሳይ ያደገ ሲሆን እግርኳስን በፈረንሳይ ጀምሯል። @tikvahethsport     @kidusyoftahe
显示全部...
227👍 34😁 8🔥 3😢 1
照片不可用在 Telegram 中显示
የሱዳን ተጨዋቾች በውድድሩ ላይሳተፉ ይችላሉ ! የሱዳን ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ለረጅም ጊዜ ያልተከፈላቸው የአበል እና ጉርሻ ክፍያ እንዲሰጣቸው መጠየቃቸው ተገልጿል። ተጨዋቾቹ ያቀረቡት የፋይናንስ ጥያቄ ከመክፈቻ ጨዋታው በፊት ምላሽ ካላገኘ በአፍሪካ ዋንጫው እንደማይካፈሉ ማስፈራራታቸው ተነግሯል። ከዚህ በፊት በነበረ ውድድር ተመሳሳይ ጥያቄ ተነስቶ አንድ የሀገሪቱ እግርኳስ ፌዴሬሽን ሀላፊ ጣልቃ በመግባት ተማፅነው እንዲጫወቱ አድርገው ነበር። ሀላፊው በወቅቱ የተጨዋቾቹ የገንዘብ ጥያቄ ከአፍሪካ ዋንጫ ውድድር በፊት ምላሽ እንደሚያገኝ ቃል ገብተው እንደነበር ተገልጿል። አሁን ላይ ውድድሩ ቢጀምርም ለተጨዋቾቹ ቃል የተገባው ባለመፈፀሙ በቡድኑ ተቃውሞው በድጋሜ መቀስቀሱ ተሰምቷል። በምድብ አራት የተደለደለው የሱዳን ብሔራዊ ቡድን የመክፈቻ ጨዋታውን ዛሬ ምሽት ከአልጄሪያ ጋር ያደርጋል። @tikvahethsport     @kidusyoftahe
显示全部...
143👎 50😁 27👍 6😢 4🥰 1
照片不可用在 Telegram 中显示
ተጠባቂ የዛሬ መርሐ ግብሮች ! 7:00 ወልዋሎ አዲግራት ዩ. ከ ነገሌ አርሲ 9:00 አርባምንጭ ከተማ ከ መቐለ 70 እንደርታ 9:30 ቡርኪና ፋሶ ከ ኢኳቶሪያል ጊኒ 10:00 ባህርዳር ከተማ ከ ፋሲል ከነማ 12:00 ሀድያ ሆሳዕና ከ ወላይታ ድቻ 12:00 አልጄርያ ከ ሱዳን 2:30 አይቮሪኮስት ከ ሞዛምቢክ 5:00 ካሜሮን ከ ጋቦን @tikvahethsport @kidusyoftahe
显示全部...
104👍 22👎 3👏 2
“ ብዙ ግብ ማስቆጠር እንችል ነበር “ አርቴታ “ አርሰናል ግድለኛ ነበር “ ኦሊቨር ግላስነር የመድፈኞቹ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በተከታታይ አመታት ግማሽ ፍፃሜ መድረሳቸውን እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል። በጨዋታው “ ብዙ የግብ እድሎችን ፈጥረናል “ ያሉት አርቴታ “ ተጨማሪ ግቦች ማስቆጠር እንችል ነበር “ ብለዋል። “ ግማሽ ፍፃሜ በመድረሳችን በጣም ደስተኛ ነኝ “ ሲሉ አሰልጣኙ ጨምረው ተናግረዋል። ለነበረው የስታዲየም ድባቡ ደጋፊን ያመሰገኑት አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ “ ሁላችሁም መልካም በዓል ይሁንላችሁ መልካም አዲስ አመት “ ሲል መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል። የክሪስታል ፓላሱ አሰልጣኝ ኦሊቨር ግላስነር በበኩላቸው ግብ ጠባቂው ዋልተር ቤኒቴዝ “ ጨዋታው ላይ እንድንቆይ አድርጎናል “ ሲሉ አወድሰውታል። አክለውም “ በመለያ ምቱ ወቅት ግን አርሰናል አእድለኛ ነበር “ ሲሉ ገልጸዋል።
显示全部...
368😁 102👍 23👎 6🥰 3👏 2
照片不可用在 Telegram 中显示
“ ለፍፃሜ መድረስ እንፈልጋለን “ የመድፈኞቹ ተከላካይ ዊሊያም ሳሊባ ቡድናቸው ለግማሽ ፍፃሜ በመድረሱ መደሰታቸውን ከጨዋታ በኋላ ተናግሯል። ቡድኑ ካለፈው አመት መማር አለበት ሲል ያሳሰበው ሳሊባ “ ምክንያቱም በግማሽ ፍፃሜው ሁለቱንም ተሸንፈን ነበር ብሏል። “ ስለዚህ በዚህ አመቱ ሁለቱንም ጨዋታዎች ማሸነፍ እንፈልጋለን ለፍፃሜ መድረስ እንፈልጋለን “ ሲል ሳሊባ ተናግሯል። አርሰናልን ለድል ያበቃች መለያ ምት ያዳነው ግብ ጠባቂው ኬፓ በበኩሉ “ በመጨረሻ ደቂቃ ግብ እያስተናገድን ነው ማሻሻል አለብን “ በማለት አስተያየቱን ሰጥቷል።
显示全部...
👍 304 112😁 52👎 15🔥 4
照片不可用在 Telegram 中显示
መድፈኞቹ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቀሉ ! የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ከክሪስታል ፓላስ ጋር ያደረገውን የካራባኦ ካፕ ጨዋታ በመለያ ምት 8ለ7 በሆነ ውጤት አሸንፏል። ሁለቱ ቡድኖች መደበኛውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል። የመድፈኞቹን ግብ ላክሮይክስ በራሱ መረብ ላይ ሲያስቆጥር ማርክ ጉሂ ክሪስታል ፓላስን አቻ አድርጓል። አርሰናል ማሸነፉን ተከትሎ ለካራባኦ ካፕ ግማሽ ፍፃሜ ማለፉን አረጋግጧል። በግማሽ ፍፃሜው አርሰናል በለንደን ደርቢ ከቼልሲ ጋር የሚገናኝ ይሆናል። ሌላኛው የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ በማንችስተር ሲቲ ኒውካስል ዩናይትድ መካከል ይደረጋል። የግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች ከሀያ ቀናት በኋላ ይደረጋል። @tikvahethsport     @kidusyoftahe
显示全部...
398😁 41🔥 26👎 24👍 22