en
Feedback
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

Open in Telegram

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች፣ ስንክሳር፣ መዝሙራትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም አስተያየት @Zimaredawitmessanger ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል። ስለሚሰጡን ገንቢ ሃሳብ እናመሰግናለን። YouTube Page - https://bit.ly/2O1Z3d8 Facebook Page - https://www.fb.com/l/6lp1kJRRR

Show more
2025 year in numberssnowflakes fon
card fon
166 279
Subscribers
-2324 hours
+187 days
-1430 days
Posts Archive
ከዚህም በኋላ ሐዋርያ እንድርያስ ርግብን ጠርቶ ዕድሜሽ ስንት ነው አላት እርሷም ስምንት ዓመት ነው አለችው ። እርሱም ለደቀ መዝሙሬ ስለታዘዝሽ ወደ ዱር ሒጂ ለዓለም ሰዎች ከመገዛት ነጻ ሁኚ አላት ወዲያውኑ ሔደች ሕዝቡም ይህን ድንቅ ሥራ አይተው አምነው ሁሉም የክርስትና ጥምቀትን ተጠመቁ ። ከዚህም በኋላ ከእርሳቸው ዘንድ ወጥቶ አክራድ አክሲስ አክሳስያ ሴኒፎሮስም ወደ ተባሉ አገሮች ሒዶ አስተማረ ከሐዋርያ በርተሎሜዎስም ጋር ተገናኝቶ ጋዝሪኖስ ወደ ሚባል አገር በአንድነት ሔዱ የሀገር ሰዎች እግዚአብሔርን ወደ ማወቅ እስከተመለሱ ድረስ ረዳት ከተደረገላቸው ገጸ ከልብ ጋር ገብተው ወንጌልን ሰበኩ ድንቅ ተአምራትንም አደረጉ ። ከዚህም በኋላ ሐዋርያ እንድርያስ ወደ ሌሎች አገሮች ሒዶ አስተማረ በፍጻሜውም ወደ አንዲት አገር ገብቶ ቅዱስ ወንጌልን ሰበከ የዚያች አገርሰዎች ግን እጅግ የከፉ ስለሆኑ ትምህርቱን አልተቀበሉትም ። ከቅዱስ ሐዋርያ እንድርያስም ድንቅ ተአምራትን ስለአዩ ያመኑ አሉ ያላመኑ ግን ወደእነርሱ እንዲመጣና እንዲገድሉት በቅዱስ እንድርያስ ላይ ክፉ ምክርን መክረው በተንኩል ወደርሱ መልእክተኞችን ላኩ መልእክተኞችም ወደ ቅዱስ እንድርያስ ሲደርሱ ማራኪ የሆነ ትምህርቱን ሰሙ ፊቱንም ብርሃን ሁኖ አዩትና ክብር ይግባውና በጌታችን አመኑ ደቀ መዝሙሮችም ሆኑት ወደላኳቸውም አልተመለሱም ። ሁለተኛም በእሳት ሊአቃጥሉት ተማከሩና ተሰብስበው ወደርሱ ሔዱ እርሱ ግን የልባችሁን ክፋት ትታችሁ ትድኑ ዘንድ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እመኑ ይህ ካልሆነ ግን ለእኔ ያላችኋት ይቺ እሳት እናንተን ትበላለች አላቸው ። ቃሉንም ባልሰሙ ጊዜ ከሰማይ እሳት ወርዳ እንድታቃጥላቸው ክብር ይግባውና ጌታችንን ለመነው ወዲያውኑ እሳት ወርዳ አቃጠለቻቸው በዚያች አገር አውራጃዎች ሁሉ ዜናው ተሰማ እጅግም ፈርተው ብዙዎች ክብርይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ ። የጣዖታት አገልጋዮች ግን ይህን ሁሉ ድንቅ ተአምራት አይተው አላመኑም ቅዱስ ሐዋርያ እንድርያስን ሊገድሉት ፈለጉት እንጂ ። ከዚህም በኋላ ተሰብስበው መጡና ቅዱስ ሐዋርያ እንድርያስን ይዘው ወሰዱት ታላቅ ግርፋትንም ገርፈው በከተማው ሁሉ ራቁቱን አዙረው ከወህኒ ቤት ጨመሩት በማግሥቱ የሚሰቅሉትን ሰው ልማዳቸው እንዲሁ ነውና ሰው ሊገድሉ በሚሹ ጊዜ ወስደው በእንጨት ላይ ይሰቅሉታል እስከሚሞትም ድረስ በደንጊያዎች ይወግሩታል ። በዚያችም ሌሊት የተመሰገነ ሐዋርያ አባታችን እንድርያስ እንደ ፊተኞቹ እሳት ወርዳ እንድትበላቸው ክብር ይግባውና ጌታችንን ክርስቶስን ለመነው ክብርይግባውና ጌታችንም ተገለጠለትና ከዚህ ዓለም የምትለይበት ጊዜ ደርሷልና አትዘን አለው ሰላምታም ሰጥቶት ከእርሱ ተሠወረ የተመሰገነ የሐዋርያ እንድርያስም ልቡናው ፈጽማ ደስ አላት ። ንጋትም በሆነ ጊዜ ወስደው በዕንጨት ላይ ሰቀሉት እስከ ሞተ ድረስም በደንጊያዎች ወገሩት አማንያን ሰዎችም መጥተው ሥጋውን ወስደው ገንዘው ቀበሩት ከእርሱም ታላላቅ የሆኑ አስደናቂዎች ተአምራት ተገለጡ ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ በሐዋርያ እንድርያስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን ። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show all...
132🕊 9🔥 4
ታህሳስ ፬ /4/
በዚች ቀን የሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ ወንድም የተመሰገነ ቅዱስ ሐዋርያ እንድርያስ በምስክርነት አረፈ ። ለዚህም ቅዱስ ይሰብክ ዘንድ ዕጣው በልዳ ሀገር ወጣ ከእርሷም ብዙዎች በቅዱስ ጴጥሮስ ትምህርት አምነው ነበር አንደበቱ የሚጥም በሥራው ሁሉና በአምልኮቱ የተወደደ ያማረ ደቀ መዝሙሩ ፊልሞና አብሮት ነበር ሐዋርያ እንድርያስም ከፍ ካለ ቦታ ላይ ወጥቶ ጣዕም ባለው አንደበቱ ከቅዱሳት መጻሕፍት እንዲአነብ አዘዘው ። የጣዖታት ካህናትም የሐዋርያ እንድርያስን መምጣት በሰሙ ጊዜ አማልክቶቻቸውን ይረግሙ እንደሆነ ሊጣሏቸው ሽተው የጦር መሳሪያቸውን ይዘው መጡ ። በዚያንም ጊዜ ፊልሞና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከወርቅና ከብር የሰው እጅ ሥራ የሆኑ የአሕዛብ አማልክቶቻቸው አፍ አላቸው አይናገሩም፣ ዐይን አላቸው አያዩም፣ ጆሮ አላቸው አይሰሙም፣ አፍንጫ አላቸው አያሸቱም፣ እጅ አላቸው አይዳስሱም፣ እግር አላቸው አይሔዱም፣ በጉሮሮአቸውም አይናገሩም፣ የሚሠሩአቸውና የሚኣምኑባቸው ሁሉ እንደእነርሱ ይሁኑ እያለ ሲያነብ ሰሙት ስለ ቃሉ ጣዕምና ስለ ንባቡ ማማር ልባቸው ከክህደት ማሠሪያ ተፈታ ወደ ቤተ ክርስቲያንም ገብተው ከሐዋርያ እንድርያስ እግር በታች ሰገዱ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስም አመኑ እርሱም የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት አስተምሮ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው ከእሳቸውም ጋር ጣዖትን ከሚያመልኩ ውስጥ ብዙዎች አምነው ተጠመቁ ። በዚያ ወራትም እንዲህ ሆነ በልዳ አገር አቅራቢያ ስሙ ዮሐንስ የሚባል አንድ ቄስ ነበረ ለእርሱም አንድ ልጅ አለው እርሱም ከባልንጀራው ጋር ሲጫወት በድንገት ገደለው የሟች አባትም ልጄን የገደለ ልጅህን አሳልፈህ ስጠኝ ሲል ቀሲስ ዮሐንስን ያዘው ቀሲስ ዮሐንስም የሀገር ሰዎችን ሔጄ ሐዋርያ እንድርያስን እስከማመጣው ዋስ ሁኑኝ እርሱ የሞተውን ያነሣልኛልና ብሎ ለመናቸው እነርሱም በተዋሱት ጊዜ ቀሲስ ዮሐንስ ወደ ሐዋርያ እንድርያስ ሒዶ ችግሩን ሁሉ ነገረው ። ሐዋርያ እንድርያስም ቀሲስ ዮሐንስን እንዲህ አለው ከእኔ ዘንድ የሚጠመቁ ብዙ ሕዝቦች ስላሉ ከአንተ ጋር እሔድ ዘንድ አይቻለኝም ግን ደቀ መዝሙሬ ፊልሞና አብሮህ ይሒድ እርሱ የሞተውን ያስነሣልሃል አለው ። ሐዋርያ እንድርያስም ከቄሱ ጋር ሒዶ የሞተውን ያስነሣለት ዘንድ ፊልሞናን አዘዘው ወደ ከተማውም ሲቀርቡ ቄሱንና ፊልሞናን ሰዎች በከተማው ውስጥ ሁከት ሁኗልና አገረ ገዥው እንዳይገድላችሁ ወደ ከተማ አትግቡ አሏቸው ። ፊልሞናም እንዲህ አለ እኔ የመምህሬን ትእዛዝ መተላለፍ አልችልም የሞተውን ለማንሣት እሔዳለሁ እንጂ መኰንኑ ቢገድለኝም መምህሬ እንድርያስ መጥቶ እኔንም አስቀድሞ የሞተውንም ያስነሣናል ። ሲገባም መኰንኑን ኒቆሮስን ተገናኘውና ፊልሞና እንዲህ አለው ሀገርን ለምን ታጠፋለህ የሾሙህ ከክፉ ነገር ሁሉ ሀገርን ልትጠብቅ አይደለምን መኰንኑም ይህ ሰው ነፍሰ ገዳይ ይመስላል አለ ወታደሮችንም ይዛችሁ ሰቅላችሁ ግረፉት አላቸው ወታደሮችም ይገርፉት ዘንድ ይዘው ሰቀሉት ። ፊልሞናም ኒቆሮስ የተባለውን መኰንን እንዲህ አለው የበደልኩት በደል ሳይኖርለምን ሰቅለህ ትገርፈኛለህ እኔ ታናሽ ብላቴና ስሆን ደቀ መዝሙሩን እኔን ሰቅለው ሲገርፉኝ ይመለከት ዘንድ ለመምህሬ እንድርያስ ማን በነገረው አለ ። ወደ ወታደሮችም ፊቱን መልሶ እንዲህ አላቸው ከውስጣችሁ የሚራራና የሚያዝንልኝ የለምን በመሰቀልና በመገረፍ እንዳለሁ ሒዶ ለመምህሬ እንድርያስ ስለ እኔ ይነግረው ዘንድ አለ ከቃሉ ጣዕም የተነሣ ወታደሮች ተሰብስበው መጥተው አለቀሱ ። በዚያንም ጊዜ አዕዋፍ ሁሉ መጥተው እኛን ላከን ብለው ተናገሩት ድምቢጥ ቀርባ እኔ በአካሌ ቀላል ነኝና እኔን ላከኝ አለችው አንቺስ አመንዝራ ነሽ ከወገንሽ በመንገድ አንዱን ያገኘሽ እንደሆነ ከርሱ ጋር ትጫወቺአለሽ ፈጥነሽ አትመለሽም አላት ከዚህም በኋላ ቁራ ቀርቦ እኔን ላከኝ አለው ፊልሞናም እንዲህ አለው አንተም በቀድሞ ዘመን በተላክህ ጊዜ ለአባታችን ኖኅ የመልእክቱን መልስ አልመለስክም አለው ። ፊልሞና ግን ርግብን ጠርቶ እንዲህ አላት እግዚአብሔር የዋሂት ብሎ ስም ያወጣልሽ ከኣዕዋፍ ሁሉ የተመረጥሽ ወገን አንቺ ለአባታችን ኖኅ በመርከብ ውስጥ ሳለ መልካም ዜና አድረሰሽለታልና አባታችን ጻድቅ ኖኅም ባርኮሻልና አሁንም ወደ ልዳ ከተማ ወደ መምህሬ እንድርያስ ሔደሽ ንገሪው ሰቅለው እየገረፉኝ ነውና ወደ እኔ ወደ ደቀ መዝሙሩ ፊልሞና ይመጣ ዘንድ ። በዚያን ጊዜ ርግብ ሒዳ ለሐዋርያ እንድርያስ ነግራ የመልእክቱን መልስ ይዛ ተመለሰች የተባረከች ርግብም ለፊልሞና መምህርህ እንድርያስ እኔ እመጣለሁና አይዞህ በርታ ብሎሃል አለችው ። በዚያንም ጊዜ ርግብ በሰው ቋንቋ ለፊልሞና ስትነግረው ኒቆሮስ መኰንን ሰማት እጅግም አደነቀ ፈጥኖ ተነሥቶም ራሱ በእጁ ፊልሞናን ፈትቶ ከተሰቀለበት አወረደው ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም አመነ ። ሰይጣን ግን ቀና በመኰንኑ ሚስት ልቡና አድሮ አሳበዳትና ልጅዋን ገደለች አገልጋዮቹም ሒደው የሆነውን ሁሉ ለመኰንኑ ነገሩት ፊልሞናም አትፍራ አይዞህ አለው ። ከዚህም በኋላ ርግብን ጠርቶ ወደ መኰንኑ ቤት ሒጂ እንዳይሸበሩ በጸጥታ እንዲቆዩ ንገሪያቸው አላት ርግቢቱም ሒዳ ፊልሞና እንዳዘዛት ለሕዝቡ ነገረቻቸው ሕዝቡም ርግቢቱ በሰው ቃል ስትናገር በሰሙ ጊዜ እጅግ አድንቀው ፊልሞና ወዳለበት ተሰበሰቡ ። በዚያንም ጊዜ ሐዋርያ እንድርያስ ደረሰ አስቀድሞ የሞተውን ያስነሣው ዘንድ ደቀ መዝሙሩ ፊልሞናን አዘዘው እርሱም ክብር ይግባውና ወደ ጌታችን በመጸለይ ከሞት አስነሣው ሁለተኛም ወደ መኰንኑ ቤት ሔዱ ሐዋርያ እንድርያስም የመኰንኑን ልጅ እናቱ የገደለችውን አስነሣው የመኰንኑንም ሚስት አዳናት ከእርሷ የወጣውንም ያንን ጋኔን ይዞ በሰው ሁሉ ፊት ምድርን ከፍቶ ወደ ጥልቅ አዘቅት አሰጠመው ።
Show all...
84🕊 7
በጎል በጎል በጎል በጎል ሰብአ ሰገል በበረት ሰብአ ሰገል/2/ በጎል ሰብአ ሰገል ሰገዱ ሎቱ/4/ ፀሐይ ፀሐይ ፀሐይ ሠረቀ /4/ ፀሐይ ሠረቀ ልደቱ ተዐውቀ/4/ አንቺ ቤተልሔም ምንኛ ታደልሽ ኤፍራታ ምንኛ ታደልሽ /2/ የመለኮት ክብር ከላይ ወርዶብሽ የዓለም መድኀኒት ተወለደብሽ/2/ ድንግል ማርያም ንጽሕት ቅድስት /4/ የጌታዬ እናት ምስጋና ይገባሻል ከሴቶች ሁሉ አንችን መርጦሻል/2/ እልል እልል ደስ ይበለን /2/ ወልድ ተወልዶ ነፃ ወጣን ከመላእክት ጋር ቆመን ዘመርን/4/ የአእላፋት ዝማሬ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show all...
በጎል_በጎል_2018_የአእላፋት_ዝማሬ_መዝሙር_በጃን_ያሬድ_ኅብረ_ዝማሬ_የተዘመረ.mp32.70 MB
125🕊 9😍 6🥰 3
Photo unavailableShow in Telegram
1 ቀን ብቻ ቀረው ስጦታችንን ተቀበሉ ብለን ነው የምናስገድዳችሁ 😁 √ በዚህ ዋጋ √ በዚህ ጥራት √ ይህን ሁሉ ባንድ ላይ ሌላ ምንም አንልም •  Laptop •  Internet •  በቂ ጊዜ አላችሁ ? አሁኑኑ ተመዝገቡ @Greenbirdtechnology √ በ300 ብር ቅድመ ክፍያ ብቻ √ ጠቅላላ ክፍያ ደግሞ 4500 √  ቤታቹ ሆናቹ ብቻ ብቁ ግራፊክስ ዲዛይነር ሁኑ ደግሞም Video Editing Course ተሸለሙ √ 1ኛ አሸናፊ 100% በነጻ √ 2ኛ አሸናፊ 50% በነጻ √ 3ኛ አሸናፊ 25% በነጻ የኮርስ ቀናት • ቅዳሜ ምሽት 1:00 - 3:00 • እሑድ ምሽት 1:00 - 3:00 • 3ኛ ቀን በብዙሃኑ ምርጫ ሆኖ ምሽት 2:00 - 4:00 @greenbirdtechs @greenbirdtechs የለውጥዎ ክንፍ 🔑 🐥
Show all...
31🔥 1
ዮም_ሰማያዊ_2018_የአእላፋት_ዝማሬ_መዝሙር_በጃን_ያሬድ_ኅብረ_ዝማሬ_የተዘመረ.m4a3.05 MB
123🕊 6🔥 2😍 2
Photo unavailableShow in Telegram
ከቃል በላይ ያስረከብናቸው ከ8 በላይ ሳይቶች ማሳያ ናቸው #ቴምርሪልስቴት #temerproperties #temerrealestate 📞+251912954919 ‼️ሳር ቤት ቫቲካን 🎯65/35 አከፍፈል 👉2መኝታ 81ካሬ ሙሉ ክፍያ 6ሚሊዮን 👉2መኝታ 106ካሬ ሙሉ ክፍያ 7.9ሚሊዮን 👉3መኝታ 139ካሬሙሉ ክፍያ 10.3ሚሊዮን 🎯ቀስ ብሎ ለሚከፍል 👉2መኝታ 81ካሬ 20%ቅድመ ክፍያ 1.86ሚሊዮን ሙሉ ክፍያ 9.3ሚሊዮን 👉2መኝታ 106ካሬ 20% ቅድመ ክፍያ 2.4ሚሊዮን ሙሉ ክፍያ 12.1ሚሊዮን 👉3መኝታ 139ካሬ 20%ቅድመ ክፍያ 3.1ሚሊዮን ሙሉ ክፍያ 15.9ሚሊዮን ‼️አዋሬ 🎯65/35 አከፍፈል 👉 ባለ 1 መኝታ = 78ካሬ = 5.5ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 117ካሬ = 8.3ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 137ካሬ = 9.7ሚሊዮን 🎯ቀስ ብሎ ለሚከፍል 👉 1መኝታ 78ካሬ 20%ቅድመ ክፍያ 1.7ሚሊዮን ሙሉ ክፍያ = 8.5ሚሊዮን                  👉3 መኝታ 117ካሬ 20%ቅድመ ክፍያ  2.6ሚሊዮን ሙሉ ክፍያ 12.9ሚሊዮን 👉 157ካሬ = 20% ቅድመ ክፍያ 3.4ሚሊዮን ሙሉ ክፍያ = 17.2ሚሊዮን  ❗️ልብይበሉ ቀሪውን 80% በ 15ዙር  ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ  ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት ይሆናል 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ 15%_25% ቅናሽ አዘጋጅተናል ለበለጠ መረጃ 👇👇👇👇👇👇 +251912954919
Show all...
43🕊 1
​​ታኅሣሥ 3 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ታኅሣሥ ሦስት በዚህች ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ነው፣ የሊቀ መላእክት ቅዱስ ፋኑኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው፣ የጻድቁ አቡነ ዜና ማርቆስ ዕረፍታቸው ነው። በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም ታኅሣሥ ሦስት በዚህች ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሦስት ዓመት ሲሆናት ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ነው ። እርሷ ለእግዚአብሔር የስእለት ልጅ ነበረችና። እናቷ ቅድስት ሐና ልጅ የሌላት ስለሆነች በቤተ እግዚአብሔር ውስጥ ከሴቶች ተለይታ ርቃ ትኖር ነበር ሽማግሌ ከሆነ ከኢያቄም ከባሏ ጋርም እጅግ የምታዝን ሆነች ። እግዚአብሔርም ኀዘናቸውን ሰማ ቅድስት ሐናም እንዲህ ብላ ለእግዚአብሔር ተሳለች የሰጠህኝን ፍሬ ለእግዚአብሔር አገልጋይ አደርገዋለሁ ። ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያምንም በወለደቻት ጊዜ ሦስት ዓመት በቤቷ ውስጥ አሳደገቻት ከዚህም በኋላ ከደናግል ጋር ትኖር ዘንድ ወደ ቤተ መቅደስ ወሰደቻት በቤተ መቅደስም ምግቧን ከመላእክት እጅ እየተቀበለች ዐሥራ ሁለት ዓመት ኖረች ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ዓለም መጥቶ ከእርሷ ሥጋን እስከ ነሣ ድረስ። ከሴቶች ሁሉ የተመረጠች ይቺ ናት በቤተ መቅደስም በመኖር ዐሥራ ሁለት ዓመት ሲፈጸምላት እርሷ ለእግዚአብሔር የተሰጠች የስዕለት ልጅ ናትና ለሚጠብቃት ይሰጧት ዘንድ ካህናት እርስበርሳቸው ተማከሩ በሴቶች ላይ የሚደርስ በርሷ ላይም ይደርስባታል ብለው ስለፈሩ በቤተ መቅደስ ውስጥ ይተዋት ዘንድ ለእርሱ ትክክል መስሎ አልታያቸውም ስለዚህም ሊጠብቃት ለሚገባው በእርሷ ላይ እጮኛ ሊአኖሩ ወደዱ። ከዚህም አስቀድሞ ሊቀ ካህናት ዘካርያስ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ልጄ ማርያም ሆይ አንቺ እንዳደግሽና ለአካለ መጠን እንደደረስሽ ዕወቂ ልትታጪ ትወጃለሽን እግዚአብሔርን የሚፈራ መልካም የሆነ የተባረከ ጐልማሳ እንፈልግልሽን ወይም በሕይወትሽ ዘመን ሁሉ በቤተ መቅደስ ተቀምጠሽ እግዚአብሔርን ልታገለግዪው የምትሺ ከሆነ በሴቶች ላይ የሚደርሰው በሚደርስብሽ ወራት ወደ ቤተ መቅደስ ደጅ ከመግባት ትጠበቂ ዘንድ በኦሪቱ የተጸፈውን የርግማን ሥርዓት በአንቺ ላይ እንሠራለን አላት ። ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያምም እነሆ እኔ የእግዚአብሔር አገልጋዩ በፊታችሁ ነኝ አባትና እናት የሉኝም ስሙ ቡሩክ ምስጉን ከሆነ ከእግዚአብሔር በታች በእናትና አባት ፈንታ እናንት ናችሁና የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እንደምታውቁ አድርጉ ብላ መለሰች። ካህናቱና ማኅበሩም ሁሉ ዘካርያስን ወደ ቤተ መቅደስ ገብተህ ስለዚች ብላቴና ማርያም ወደ እግዚአብሔር ጸልይ አሉት ዘካርያስም ገብቶ ሲጸልይ በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠለትና እንዲህ አለው። ዘካርያስ ሆይ ወጥተህ ከዳዊት ወገን ሚስቶቻቸው የሞቱባቸውን ሁሉ ወንዶች ሰብስብ የየአንዳንዱንም በትር ከስሙ ጋር ውሰድ ወደ ቤተ መቅደስም በምሽት አግብተህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይበት በነጋ ጊዜም በትሮቻቸውን አውጣ እግዚአብሔርም በበትሩ ላይ ምልክት ለገለጠልህ ለዚያ ሰው ማርያምን ተቀብሎ ሊጠብቃት ይገባዋል። ካህኑ ዘካርያስም ወጥቶ አንድነት ለተሰበሰቡት ሕዝብ የእግዚአብሔር መልአክ የነገረውን ነገራቸው በዚያንም ጊዜ ከዳዊት ወገን ጐልማሳም ቢሆን ሽማግሌም ቢሆን ሚስቱ የሞተችበት ሁሉ በኢየሩሳሌም ወደአለ ቤተ መቅደስ ይሒድ እያሉ ዓዋጅን ዙረው የሚናገሩ በእስራኤል አገር ሁሉ ላከ ። ከዳዊት ወገን የሆነ ጠራቢው ዮሴፍም በሰማ ጊዜ በትሩን ይዞ ከናዝሬት ወደ ኢየሩሳሌም ሔደ ካህኑ ዘካርያስም የሁሉንም በትሮች ተቀብሎ ስማቸውን በላያቸው ጻፈ ቁጥራቸውም አንድ ሽህ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ አምስት ሆነ ዘካርያስም በትሮችን ወደ ቤተ መቅደስ አስገብቶ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ እንዲሁም ሰዎች ሁሉ ከቤተ መቅደስ ውጭ ቁመው ይጸልዩ ነበር ዘካርያስም ጸሎቱን በፈፀመ ጊዜ ለየአንዳንዱ በትራቸውን አውጥቶ ሰጠ ጠራቢው ዮሴፍም በትሩን ሊቀበል በቀረበ ጊዜ ከእርሷ ነጭ ርግብ የመሰለች ተገለጠች እየበረረችም ሒዳ በጠራቢው ዮሴፍ ራስ ላይ ተቀመጠች ካህናቱና ሕዝቡ ሁሉ አይተው እጅግ አደነቁ ምስጉን የሆነ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት። ዘካርያስም ዮሴፍን ዮሴፍ ሆይ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ እንደ ተናገረ ድንግል ማርያምን ወደ ቤትህ ወስደህ ጠብቃት አለው ዮሴፍም ቅድስት ድንግል ማርያምን ከካህናት እጅ ተቀበላት በእርሱም ዘንድ ኖረች ። ከዚህም በኋላ የመላእክት አለቃ ገብርኤል ስለ እግዚአብሔር ልጅ ከእርሷ ሰው ሁኖ ስለመወለዱ በዮሴፍ ቤት አበሠራት። ለሁሉም ኦርቶዶክሳዊ ሼር አድርጉ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show all...
388🕊 25🔥 9😍 8
ሰአሉ ለነ ቅዱሳን ሰአሉ ለነ ቅዱሳን መላእክት /2/ ሰአሉ ለነ ጻድቃን ሰማዕታት ኀበ አምላከ ምሕረት ሰአሉ ለነ ለምኑልን ቅዱሳን መላእክት /2/ ለምኑልን ጻድቃን ሰማዕታት ወደ አምላከ ምሕረት ለምኑልን
አዝ
እንተ የመረጥከውን ማን ይከስሳል ያጸደቅከውን ማን ይወቅሳል ለሚገባው ክብርን መስጠት ታዝዟልና በመጻሕፍት ያከበርካቸው ባርያዎችህን እናከብራለን ቅዱሳንህን/2/
እዝ
ሁሉ መዳንን እንዲይዙ የሚላኩ የሚያግዙ ሠርክ በፊትህ እየቆሙ ጥዑም ቅዳሴን እያሰሙ በምስጋናቸው የሚያከብሩህን እናከብራለን መላእክትህን/2/
አዝ
ጤዛ ልሰው ዳዋ ለብሰው ዋእይ ቁሩንም ታግሰው በየፍርክታው በየዱሩ ሌጦ ለብሰው እየዞሩ በጽናታቸው የሚያከብሩህን እናከብራለን ጻድቃንህን/2/
እዝ
እንደሚታረዱ በጎች ሆነው አንገታቸውን ለሰይፍ ሰጥተው ስለስምህ እየተጠሉ ከእንበሳ ጋር እየታገሉ በተጋድሏዋቸው የሚያከብሩህን እናከብራለን ሰማዕታትህን/2/
አዝ
ከሕያው ቃልህ እየጠቀሱ መናፍቃንን ድል የነሱ በገዛ ደምህ የዋጀኀትን ቤተ ክርስቲያንን የጠበቋትን በሕይወታቸው ያስደሰቱህን እናከብራለን ሐዋርያትህን/2/ የአእላፋት ዝማሬ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show all...
ሰአሉ_ለነ_ቅዱሳን_መላእክት_ዘማሪት_አዳነች_አስፋው_2018_የአእላፋት_ዝማሬ_መዝሙር_በጃን_ያሬ.m4a6.39 MB
164🥰 10🔥 4
Photo unavailableShow in Telegram
« አንዳቸውንም እንኳን ሳትሠሩ ማለፍ አትችሉም » 2 ቀናት ብ ቻ ቀሩት በቆይታቹ ሁሉንም መሥራት ሁሉንም ጽንሰ ሀሳብ ማወቅ ሁሌም አብረው ናቸው ። ያላችሁበትን ሁኔታና የጊዜ ጥበት እንረዳለን ግን ደግሞ እሱ ፕሮጀክት እንዳትሠሩ እንደማያደርጋቹ ጠንቅቀን እናውቃለን ። የምናስተምራቹ ቀለል አድርገን ነዋ🤗 ስንቀርባቹ የፈለጋቹትን እንድታውቁ ነው ባለመሥራታቹ ስንጣላ ደግሞ እንዲሁ 😅 •  Laptop •  Internet •  በቂ ጊዜ አላችሁ ? ይሄው በሉ አሁኑኑ ተመዝገቡ @Greenbirdtechnology √ በ300 ብር ቅድመ ክፍያ ብቻ √ ጠቅላላ ክፍያ ደግሞ 4500 √  ቤታቹ ሆናቹ ብቻ ብቁ ግራፊክስ ዲዛይነር ሁኑ ደግሞም Video Editing Course ተሸለሙ 1ኛ አሸናፊ 100% በነጻ 2ኛ አሸናፊ 50% በነጻ 3ኛ አሸናፊ 25% በነጻ የኮርስ ቀናት ቅዳሜ ምሽት 1:00 - 3:00 እሑድ ምሽት 1:00 - 3:00 3ኛ ቀን በብዙሃኑ ምርጫ ሆኖ ምሽት 2:00 - 4:00 @greenbirdtechs @greenbirdtechs የለውጥዎ ክንፍ 🔑 🐥
Show all...
32
Photo unavailableShow in Telegram
ታህሳስ 2 /፪/
በዚች ቀን ናቡከደነዖር ከአባታቸው ጋር ለማረካቸው ሦስት ለሆኑ ለይሁዳ ንጉሥ ለኢዮአቄም ልጆች እግዚአብሔር ኃይልን አደረገላቸው። እሊህም አናንያ አዛርያ ሚሳኤል ናቸው በቤቱም ውስጥ አሳድጎ በባቢሎን ሀገሮች ውስጥ ሾማቸው። ከዚህም በኋላ ናቡከደነፆር የወርቅ ምስል በሠራ ጊዜ መኳንንቱንና በግዛቱ ውስጥ ያሉትን ሁሉ ለዚያ ምስል እንዲሰግዱ አዘዘ እሊህ ቅዱሳን ግን መሰገድን እምቢ አሉ በወነጀሏቸውም ጊዜ ከቀድሞው ሰባት እጅ ወደ አነደዱት የእሳት ማንደጃ ውስጥ ይጨምሯአቸው ዘንድ ንጉሥ አዘዘ። በእሳቱ መካከልም ረጅም ጸሎትን ጸለዩ የእግዚአብሔር መልአክም ወርዶ እንደ ቀዘቀዘ ነፋስ አደረገው። ንጉሥ ናቡከደነፆርም ይህን ድንቅ ተአምር በአየ ጊዜ አደነቀ ለእግዚአብሔርም በመገዛት ሰገደ እነርሱንም ከእሳት ማንደጃ ውስጥ አወጣቸው እጅግም አከበራቸው። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በእሊህ ቅዱሳን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show all...
245🕊 16🥰 1
ግሩም ድንቅ ነህ ግሩም ድንቅ ነህ አምላኬ ግሩም ድንቅ ነህ ግሩም ድንቅ ነህ ጌታዬ ግሩም ድንቅ ነህ ሰው የጣለውን ከምድር ከፍ ታደርጋለህ የተረሳውን አምላኬ ታስታውሳለህ
አዝ
ከቤተ ሳይዳ ያነሳል ባልጋ ያለውን መጠመቅ ሽቶ እረዳት ወገን ያጣውን ካጢያተኛው ቤት ይገባል እራት ሊበላ በቀል አያውቅም ጌታዬ ከፍቅር ሌላ እንዳምላካችን ማንም የለም /2/ እንደ እግዚአብሄር ማንም የለም /2/ እንደ ፈጣሪ ማንም የለም /2/ እንዳማኑኤል ማንም የለም /2/
አዝ
የበደለውን አይንቅም ያነሳል በእጁ ፍፁም ይራራል በእውነት ጌታ ለልጁ ከሳምራዊው ጋር ይውላል እንደ ጉዋደኛ ሁሉን በፍቅር የሚያስብ ታማኝ እረኛ እንዳምላካችን ማንም የለም /2/ እንደ እግዚአብሄር ማንም የለም /2/ እንደ ፈጣሪ ማንም የለም /2/ እንደ አማኑኤል ማንም የለም /2/
አዝ
ሰው የናቀውን አንስቶ ሾሞ ያከብራል ዘይት አፍሶ ባርያውን በእጁ ይቀባል አክሊል ይደፋል አንስቶ ላጎነበሰው ክብርና ጋሻ መከታ ዝናር ሊሆነው እንደ አምላካችን ማንም የለም /2/ እንደ እግዚአብሄር ማንም የለም /2/ እንደ ፈጣሪ ማንም የለም /2/ እንደ አማኑኤል ማንም የለም /2/
አዝ
ያዘነውን ሰው ያፅናናል ፍቅር እየዘራ ያነሳለታል የጭንቁን ግዙፍ ተራራ ደግሞ አይኖርም በቤቱ የእስር ቀንበር እርሱን ተማምኖ የቆመ ከመቅደሱ ስር እንደ አምላካችን ማንም የለም /2/ እንደ እግዚአብሄር ማንም የለም /2/ እንደ ፈጣሪ ማንም የለም /2/ እንደ አማኑኤል ማንም የለም /2/ የአእላፋት ዝማሬ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show all...
ግሩም_ድንቅ_ነህ_ዘማሪ_ዳግማዊ_ደርቤ_2018_የአእላፍት_ዝማሬ_መዝሙር_በጃን_ያሬድ_ኅብረ_ዝማሬ.m4a5.86 MB
218🥰 8🕊 5🔥 2
ታህሣሥ 1 /፩/
በዚችም ቀን የእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት ዮሐንስ አረፈ እርሱም ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሠላሳኛ ነው። ይህም የከበረ ቀሲስ የሆነ የገምኑዲ አገር ሰው ነው በዘመኑም የቅዱሳን ሰማዕታት የሰርጊስና የባኮስ ቤተ ክርስቲያናቸው ተሠራች ዳግመኛም የአቡቂርና የዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን በምስር መሰብሰቢያ ቅጽር አጠገብ ተሠራች ያነፃቸውም ስሙ እንድርያስ የሚባል እግዚአብሔርን የሚፈራ ያዕቆባዊ አንድ የግብጽ ሰው ነው። እርሱም ለመርዋን ልጅ ለገዢው ለንጉሥ አብደል ጸሐፊው ነው። ይህም አባ ዮሐንስ የወንጌላዊ ቅዱስ ማርቆስን ቤተ ክርስቲያን በእስክንድርያ አገር በታወቀ ቃምስ በሚባል ቦታ የሠራ ነው። በዚህ በንጉሥ አብደል ዘመንም ሦስት ዓመት ያህል ጽኑ ረኃብ ሆነ ይህም አባት ለድኆች ለጦም አዳሪዎችና ለችግረኞች የሚያስብ ሆነ በየሳምንቱም አራት ጊዜ ወርቅና ብር እንጀራም ይሰጣቸዋል አብዝቶ የሚራራ መመጽወትን የሚወድ በጎ ሥራዎችን የሚሠራ ነውና። በዘመኑም ንጉሥ ይዜድ ሙቶ በርሱ ፈንታ መርዋን ነገሠ ይህም አባት በማርቆስ ወንበር ዘጠኝ ዓመት ኖረ በሰላምም አረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘለዓለሙ አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show all...
190🕊 11
ወትቤሎ ወትቤሎ ይኩነኒ/2/ በከመ ትቤለኒ ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ ይኩነኒ/2/ የአእላፋት ዝማሬ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show all...
ወትቤሎ_ይኵነኒ_2018_የአእላፍት_ዝማሬ_መዝሙር_በጃን_ያሬድ_ኅብረ_ዝማሬ_የተዘመረ.m4a1.67 MB
76🥰 8🕊 4
በምን ደስ ላሰኝህ ጌታዬ ሆይ በምን ደስ ላሰኝህ ጌታዬ ሆይ በምን ደስ ላሰኝህ አምላኬ ሆይ አለምና መላው ያንተው አይደለም ወይ የፈጠርከው ሁሉ ያንተው አይደለም ወይ
አዝ
ኪሩቤል ሱራፌል ቅዱስ ሥሉስ ያሉህ        መላዕክት በራማ የሚያመሰኑህ ድንቅ መካር ኃያል ኤልሻዳይ ነህና ትንቢያ ነኝ ምን ልስጥህ ምንስ አለኝና/2/
አዝ
ቅዱሱን  መስዋዕት ልዑል ስለሚወድ ምን ይዤ ልምጣና በአምላኬ ፊት ልስገድ ወደ ላይ በሰማይ ወደ ታች በጥልቀት አምላኬ  የት አለ የማትገኝበት ጌታ ሆይ የት አለ የማትገኝበት
አዝ
በኪዳን በፀሎት ቅዳሴ ሰዓታት አንተ የሰጠኸኝ የመንፈስ ቅዱስ ሀብት መልሰን ወደ አንተ ብንሰጥ ምን አለ ተወው ጉዳችንን ስስታችን ይኸው(2)
አዝ
ሀብትና ንብረቴስ ጉልበቴስ ምንድነው ጤናዬ የሰጠኝ ከአንተ በቀር ማነው በሰጠኸኝ እድሜ በሕይወት ዘመኔ ከገላዬስ ቢሆን የትኛው ነው የኔ ከአካላቴስ ቢሆን የትኛው ነው የኔ የአእላፋት ዝማሬ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show all...
በምን_ደስ_ላሰኝህ_ዘማሪ_ዳግማዊ_ደርቤ_2018_የአእላፋት_ዝማሬ_መዝሙር.m4a4.34 MB
255🕊 13🥰 9🔥 4
ሕዳር 30/፴/
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ኅዳር ሠላሳ በዚች ቀን የቊስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት አካክዮስ አረፈ ። ይህም ቅዱስ ቸር የሆነ ምሁር ነው አምላክ ያጻፋቸውንም መጻሕፍት ቃላቸውን አሳምሮ የሚተረጉም አዋቂ ነው በቁስጥንጥንያ ቤተ ክርስቲያንም ቅስና ተሹሞ ነበር ። በኬልቄዶንም ስብሰባ በሆነ ጊዜ ይህ አባት በጉባኤው ውስጥ በሆነው ሁሉ ደስ አላለውም ስለ እውቀቱም እንዲመጣ በፈለጉት ጊዜ እርሱ አሞኛል ብሎ ስለራሱ ምክንያት ሰጠ ። የቁስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት እንጣልዮስም በአረፈ ጊዜ በቁስጥንጥንያ አገር ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት ። በተሾመ ጊዜም ከብቻው እግዚአብሔር በቀር ማንም ሊአስወግደው የማይችል የጥልና የመለያየት የማይድን በሽታ በፍቅር አንድ አደረገ :: ዜናውም በሮማውያን ኤጲስቆጶሳት ዘንድ በተሰማ ጊዜ አባ አካክዮስን ከቁስጥንጥንያ መንበር አሳደዱት በቀናች ሃይማኖት እንደ ፀና በደሴት ውስጥ አረፈ ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን ። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show all...
199🕊 9🥰 6
Photo unavailableShow in Telegram
ኅዳር ፳፱ /29/
በዚችም ዕለት የተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ  (የሰማዕታት መጨረሻ) የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው። የቅዱሱ ሃገረ ሙላዱ ግብጽ ናት። ዘመኑም 3ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው። ወላጆቹ ካህን ቴዎድሮስና ቡርክት ሶፍያ ልጅ አጥተው ሐምሌ 5 ቀን ወደ ፈጣሪ ቢማጸኑ በራዕይ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ተገልጠው ብሥራትን ለሶፍያ ነገሯት:: በወለደችው ጊዜም በራዕዩ መሠረት "ጴጥሮስ" አለችው። ሰባት ዓመት በሆነው ጊዜም ለቤተ እግዚአብሔር ሰጥተው በሊቀ ጳጳሳቱ ቅዱስ ቴዎናስ እጅ አደገና በወጣትነቱ ሊቅ: ጥዑመ ቃልና በጐ ሰው ሆነ። ዲቁናና ቅስናን ተሹሞ ሲያገለግል ቅዱስ ቴዎናስ በማረፉ ቅዱስ ጴጥሮስን የግብጽ 17ኛ ፓትርያርክ አድርገው ሾሙት። ዘመኑ ደግሞ እጅግ ጭንቅ ነበር᎓᎓ ክርስቲያኖች በተገኙበት ስለሚገደሉ: አብያተ ክርስቲያናትም ስለ ተቃጠሉ የቅዱሱ መከራ የበዛ ነበር:: ለ14 ዓመታት በፍጹም ትጋት ከመንጋው ጋር ተጨነቀ᎓᎓ አርዮስን (ተማሪው ነበር) አውግዞ ለየው። ከጌታ ጋርም ብዙ ጊዜ ተነጋገረ። ብዙ ተአምራትንም ሠራ። በዚህ ሁሉ ጊዜ አንድም ቀን በመንበረ ጵጵስናው ላይ አልተቀመጠም:: በኋላ ግን ጨካኙ ንጉሥ እንዲገደል አዘዘ። ሕዝቡ "ከእሱ በፊት እኛን ግደሉን" በማለታቸው ሁከት እንዳይነሳ ቅዱስ ጴጥሮስ ተደብቆ ሔደና በፈቃዱ ለወታደሮች ተሰጠ። በዚያች ሌሊትም የእርሱ ደም የግፍ ማብቂያ እንዲሆን እያለቀሰ ጮኸ። ከሰማይም "አሜን! ይሁን!" የሚል ቃል መጣ። ያን ጊዜ የእርሱ አንገት ተሰየፈ። ዘመነ ሰማዕታትም አለፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show all...
269🕊 20🥰 7
መድኃኔዓለም መድኃኔዓለም የለም የሚሳነው አማኑኤል የለም የሚሳነው እርሱ ቃል ሲናገር ተራራው ሜዳ ነው መድኃኔዓለም የለም የሚሳነው
አዝ
አላስብም አልፈዋለሁ ብዬ ጉንጭ አልፎ ትራሴን እያጠበ እንባዬን እየተፈጸመ ኃይሉ በድካሜ ማእበሉን አለፍኩኝ ቀለለልኝ ሸክሜ
አዝ
የቤቴ እራስ ነው የእቅዴ መሪ በክፉም በደጉም ነፍሴን አስተማሪ ፈጥሮ የማይረሳኝ ቤዛዬ ደረሰ ቤቴን ደስታ ሞላው እንባዬ ታበሰ
አዝ
ትናንት ባዶ ነበር የለኝ የሚሰፈር አንዳች አልነበረኝ የሚታይ የሚቆጠር ከርሱ የተነሳ ዛሬ ግን ሙሉ ነኝ ክብር ለእርሱ ይሁን አለ የማይተወኝ
አዝ
እየከለከለ ለእኔ ማይጠቅመኝን በጊዜ እየሰጠ ደግሞ የሚረባኝን ሁሉ በእርሱ ሆኗል አልሆነም ያለ እርሱ ውዳሴ ምስጋና ይድረስ ለንጉሱ የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show all...
መድኃኔዓለም_የለም_የሚሳነው_ዘማሪት_ሲስተር_ሕይወት_ተፈራ_2018_የአእላፍት_ዝማሬ_መዝሙር.m4a3.87 MB
148🥰 14🕊 5
Repost from TgId: 2131344856
Photo unavailableShow in Telegram
አንዳንድ አጋጣሚዎች በሕይወታችን ትልቁን ለውጥ ሊፈጥሩ ወይም የሆነ ነገርን ሳናስብ ድንገት እንድንወደው ሊያደርጉን ይችላሉ ። Green Bird Tech የሚሰጣቸው ኮርሶችም ምናልባት እንዲሁ ሳይሆኑ አይቀሩም 🤗 ምንም መነሻ ዕውቀት ይዛችሁ ኑ አንልም ፣ ይልቅ ከምንም ተነስታቹ የትም ድረሱ ነው ሀሳባችን ። የማያግባባን አንድ ነገር ብቻ ነው አ ለ መ ሥ ራ ት አያግባባንም ብቻ ሳይሆን አያዛልቀንም ጭምር 🤫 ማወቅ ለሚፈልግና ለሚተጋ ግን የምንነፍገው አንዳች ነገር የለንም። √ የውሳኔ ሰው ሁኑ ዛሬውኑ ተመዝገቡ ይህንን ሁሉ ባንድ ጊዜ አስተምረን እስከቤታቹ እንሸኛቹሃለን 😄 •  Laptop •  Internet •  በቂ ጊዜ አላችሁ ? ይሄው @Greenbirdtechnology ላይ አሁኑኑ ተመዝገቡ @greenbirdtechs @greenbirdtechs የለውጥዎ ክንፍ 🔑 🐥
Show all...
57🔥 4🕊 4
Photo unavailableShow in Telegram
✨ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ➛ ለሰንበት ትምህርት ቤታችን ልብሰ ስብሐት ማሰፊያ የሚውል መንፈሳዊ ዕጣ በ100 ብር ብቻ በመቁረጥ ሰንበት ትምህርት ቤቱን እናግዝ። ➟ ዳሽን ባንክ፦ 5542906694011 ከላይ ባለው ባንክ ቁጥር 100 ብር ብቻ በመላክ ሰንበት ትምህርት ቤቱን እናግዝ። ትኬት ለመግዛት እነዚህን ስልኮች ይጠቀሙ +251909837170 +251962913061 ጽርሐ ጽዮን ሰንበት ትምህርት ቤት 2018 ዓ.ም
Show all...
82
Photo unavailableShow in Telegram
✨ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ➛ ለሰንበት ትምህርት ቤታችን ልብሰ ስብሐት ማሰፊያ የሚውል መንፈሳዊ ዕጣ በ100 ብር ብቻ በመቁረጥ ሰንበት ትምህርት ቤቱን እናግዝ። ➟ ዳሽን ባንክ፦ 5542906694011 ከላይ ባለው ባንክ ቁጥር 100 ብር ብቻ በመላክ ሰንበት ትምህርት ቤቱን እናግዝ። ትኬት ለመግዛት እነዚህን ስልኮች ይጠቀሙ +251909837170 +251962913061 ጽርሐ ጽዮን ሰንበት ትምህርት ቤት 2018 ዓ.ም
Show all...