ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
Open in Telegram
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች፣ ስንክሳር፣ መዝሙራትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም አስተያየት @Zimaredawitmessanger ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል። ስለሚሰጡን ገንቢ ሃሳብ እናመሰግናለን። YouTube Page - https://bit.ly/2O1Z3d8 Facebook Page - https://www.fb.com/l/6lp1kJRRR
Show more2025 year in numbers

166 319
Subscribers
-1724 hours
-227 days
-430 days
Posts Archive
ዛሬም አለሽ በልቤ
ዛሬም አለሽ በልቤ/3/
ድንግል ሆይ ወለታሽ አይጠፋም ከሀሰቤ
አዝእንደ ሀጥያቴ ብዛት እንዴ በደሌማ የጥልቁ ሰንሰለት ሲይንሰኝ ነው ጨለማ ግን ያንች ሆንኩኝና ሁሉንም አለፈኩኝ ያንን የሞት ባህር በምልጃሽ ቀዝፈኩኝ
አዝ አርፏል ልቤ በአንቺ በአዛኝቷ ማርያም ውስጤ እያፈሰሰ ፍቅርና ሠለም ህመሜም ቢያስረሳኝ የወዳሴሽ ቃና እመቤቴ እላለሁ ዛሬም እንደገና
አዝእናታችን ፅዮን ሰው ሁሉ ይልሻል ዳዊት በበገና ያመሰግንሻል የአሴቦን ነግሥታት ለክብርሽ ዘማሩ የማትፈርሽ መቅደስ የእግዚአብሔር ሀገሩ
አዝእጅግ ብዙ ነገር አድርገሽልኛል ይቅር ባይ ልጅሽ በፍቅር አይቶኛል እኔስ እኖራሉሁ ድንግል በአንች ጥላ ጨለማን አላይም ከእንግድህ በኃላ ዘማሪ ልዑልሰገድ ጌታቸው 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
file_18564.mp34.92 MB
❤ 176😍 11🕊 6🥰 5🔥 2
ኅዳር ፱ /9/በዚች ዕለት ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት አርባ አንደኛ የእስክንድርያ አገር ሊቃ ጳጳሳት ቅዱስ አባት ይስሐቅ አረፈ። ወላጆቹ ይህን ቅዱስ በወለዱት ጊዜ በታላቅ ደስታ ደስ ተሰኙበት። ያጠምቀው ዘንድ ወደ ኤጲስቆጶስ በአቀረቡት ጊዜ ሲያጠምቀው በሕፃኑ ራስ ላይ የብርሃን መስቀልን አየ። እንዲህም ብሎ ትንቢት ተናገረለት ይህ ሕፃን በእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ላይ ይሾማል እርሱ ለእግዚአብሔር የተመረጠ መሣሪያ ይሆናልና። የቤተ ክርስቲያንን ትምህርትና ጽሕፈትን አስተማሩት ወላጆቹንም ትቶ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔደ በአበምኔቱ በአባ ዘካርያስም ዘንድ መንኩሶ በገድል ተጠመደ። በአንዲትም ዕለት አንድ ጻድቅ ሰው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አየው በእርሱም ላይ ይስሐቅ በክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ላይ ይሾም ዘንድ አለው ብሎ ትንቢት ተናገረ። ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሐንስ ጸሐፊ የሚሆነውና የሚረዳው ብልህ ሰው ፈለገ ስለ አባ ይስሐቅም ነገሩት እሱንም አስመጣው ይጽፍለትም ዘንድ ደብዳቤ ሰጠው እርሱ ግን አባ ይስሐቅ እያወቀ ጽሕፈቱን አበላሽ ሊቀ ጳጳሳቱ እንዲተወውና ወደ አስቄጥስ ገዳም እንዲመለስ ነበር የዚህን ዓለም ክብር ይጠላልና። ሊቀ ጳጳሳቱም እንዲተወውና እንዲአሰናብተው አውቆ ማበላሸቱን በአወቀ ጊዜ በጥሩ ጽፈሃል እንድትሔድም እኔ አልተውህም አለው ከወራትም በኋላ አባ ይስሐቅ ወደ አስቄጥስ ገዳም ተመለሰ አባ ዮሐንስም የሚያርፍበት ቀን በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔርን በራእይ ከአንተ በኋላ ለዚች ሹመት የሚጠቅም ረዳትህ ይስሐቅ ነው አለው። አባ ዮሐንስ በአረፈ ጊዜ ይህን ቅዱስ አባት ይስሐቅን ይዘው በእስክንድርያ አገር ላይ ሊቀ ጳጳሳት አድርገው ሾሙት። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ :- መጽሐፈ ስንክሳር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
❤ 186🕊 12
የሚያበረታታውን
የሚያበረታታውን ያንን መልዓክ አሰብኩት አቤቱ{፪}
ጉልበቴም ሲዝል ልቤም ሲፈራ ያንን መልዓክ ጌታ ሆይ አደራ
አዝያበረታህ መልዓክ ያበርታኝ የታየህ አገልጋይ ይታየኝ ሰልፉ ሲበረታ እንዳልፈራ ያንን ቅዱስ መልዓክ ጌታ ሆይ አደራ አለው በሞገስ ኖራለው በፀጋ የጨለመው ሌሊት መልሶ እየነጋ አባቴ መልዐኩን አዝዘኸው ስለኔ የመውጣት የመውረስ የምርኮ ነው ቅኔ
አዝታላቁ ሚካኤል ያንተ ወዳጅ ዘንዶውን የጣለ በፀናች እጅ ስለ ሙሴም ስጋ ሲከራከር አየው በመንፈሴ ሰይጣንን ሲያሳፍር እግሮቼ በድንጋይ ላይሰናከሉ አለህ ከአጠገቤ በመንገዴ ሁሉ ከደመናው በታች ይጓዛል እስራኤል ምክሩን ይፈፅማል ታዛዡ ሚካኤል
አዝወኅኒው ወለል አለ ተከፈተ ሕመሜም ታመመ ሞቴም ሞተ አምላክ ከኔ ጋራ ስለሆነ በውስጥም በውጪም ሰላም ሆነ ከእስረኞቹ መኃል አንዳች ነክቶት ጎኔን ልክ እንደ ጴጥሮስ ማምለጥ ሆኗል ለኔ አየሁት ጎጆዬን ቤቴ በእሳት ታጥሮ የጌታዬን ማዳን የእረፍቴን ቀጠሮ ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
6082726593_1 (11).mp34.62 MB
❤ 141🥰 9🕊 5🔥 3
ፈቃዴ ይህ ነው
ፈቃዴ ይህ ነው የሠውን ነገር ላልናገር/2/
የእኔ ተሽፍኖ ከቆምኩኝ በክብር
ፈቃዴ ይህ ነው የሰውን ነገር ላልናገር
አዝህይወቴ በሙሉ በኃጢአት ተመልታ አምላኬ ከማረኝ በፍቅሩ ዝምታ የሰው በደል ላላይ በእውነት ምያለው እኔን ከታገሰኝ ፍቅር ተምሪያለው /2/
አዝባይኔ ፊት ተጋርዶ ያለውን ምሰሶ እያየ ካለፈኝ በምህረት ታግሶ የሰው ጉድፍ ላላይ በእውነት ምያለው እኔን ከታገሰኝ ፍቅር ተምሪያለው/2/
አዝአንተ ቀራጩ ሰው ያለህ አቀርቅረህ በምህረት ተመለስክ ከኔ ይልቅ ድነህ ባንተ ላይ ስጠቁም የኔን ጸሎት ትቼ የመዳኑ ሰዓት አለፉ ቀኖቼ/2/
አዝተቆጥሮ የማያልቅ በደሌ ተከድኖ በሞትና በደም ሃጥያቴን ሸፍኖ ሰው አርጎኝ በሰው ፊት አቁሞኝ ጌታዬ በማንም አልፈርድም ሀጥያተኛ ብዬ ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ፈቃዴ_ይህ_ነው_Fekade_Yih_New_ሊቀ_መዘምራን_ቴዎድሮስ_ዮሴፍ.m4a5.91 MB
❤ 167🥰 18🕊 5
ሕዳር ፰ /8/ በዚችም ቀን የአረማዊ መኰንን ልጅ የነበረ አባ ቅፍሮንያ አረፈ። ከዕለታትም በአንዲቱ ስሙ መርቆሬዎስ የሚባል መነኰስ ከአባ ጳኵሚስ ገዳም ወደ ሀገሩ መጣ እርሱ ክርስቲያን እንደሚሆን በእርሱ ላይ ትንቢት ተናገረ። ከጥቂት ወራትም በኋላ ገዳማትን ሊያጠፋ ምርኮንም ሊማርክ ሠራዊቱን ሰብሰቦ ወደ ግብጽ አገር ዘመተ ወደ አባ ጳኵሚስም ገዳም በደረሰ ጊዜ አበ ምኔቱ ወደርሱ ወጥቶ እኔ ነኝ አለው ቅፍሮንያም ሰምቶ አበምኔቱን ለብቻው አግልሎ እንዲአጠምቀውና የምንኵስናንም ልብስ እንዲአለብሰው ለመነው አበ ምኔቱም እሺ በጎ አለው። ከዚህም በኋላ ሠራዊቱ ወደ ሀገራቸው በተመለሱ ጊዜ ብቻውን ቀረ በዚያንም ጊዜ የምንኵስናን ልብስ ለበሰ ተጋድሎውንም በመጾምና በመጸለይ ጀመረ። ሰይጣንም በእርሱ ላይ ቀንቶ ነገረ ሠሪ አስነሣበት በመኳንንቱም ዘንድ ወነጀለው እነርሱም አገራችንን ያጠፋ የመኰንን ልጅ ከዚህ አለ ብለው ገዳሙን ከበቡ እግዚአብሔርም ሠወረው በአጡትም ጊዜ ነገረ ሠሪውን ገደሉት። ይህም ቅዱስ በገድል ተጠምዶ ኖረ በየሰባት ቀንም ይጾማል ያለ መራራ አደንጓሬ አይመገብም። በዚያም ወራት የምድር አውሬ እንስሶቻቸውን እየገደለ በገዳሙ ላይ ጥፋትን አደረሰ አባ ቅፍሮንያም ወደርሱ መጥቶ እንደ በግ ይዞ አሠረው ዐሥር ዓመትም ቆይቶ ሞተ። ቅዱስ ቅፍሮንያም የእግዚአብሔር መልአክ እየመራው ወደ ኢየሩሳሌም ሔደ በአንዲትም ቀን ደረሰ በዚያም ታላቅ ምሥጢርን አየ ከከበሩ ቦታዎችም ተባርኮ ወደ መኖሪያው ተመልሶ በሰላም አረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ :- መጽሐፈ ስንክሳር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
❤ 194🕊 14😍 3
አወድሰኝ ኤፍሬም
አወድሰኝ ኤፍሬም ብላ ጠየቀችው ድንግል እናታችን
ባርክኒ ብሎ ወገቡን ታጠቀ ኤፍሬም አባታችን
የልጄ በረከት ይደርብህ ብላው ጀመረ ምስጋና
ወደ ብርሃን ድንኳን ወደ ተከበረው ደራሲው ገባና
አዝልቡ ያዘነ አዳምን ሊያድን ጌታ ወደደ ዳግሚት ሰማይ ማደሪያው ልትሆን እሱ ፈቀደ የሰማይ ምስጢር በማህጸንሽ ተከናወነ ከዘሩ ቀርተሽ በንጽሕናሽ የሰው ዘር ዳነ ሰዐሊ ለነ /2/ አእምሮውን ልቡን ሳይብን አሳድሪብን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን
አዝበሔዋን ምክንያት በለስዋን በልተን ገነት ቢዘጋ በአንቺ እናትነት ዳግም ተዛመድን ከአምላካችንጋ ትውልድ ሁሉ ስምሽን በክብር አመሰገነ የሲዖል ቀንበር በላያችን ላይ ስላልተጫነ ሰዐሊ ለነ/2/ አእምሮውን ልቡን ሳይብን አሳድሪብን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን
አዝየእዳ ደብዳቤ ተቀዳደደ የባርነቱ አዳም ሔዋንም ከእስራታቸው ወጡ ተፈቱ የሲዖል ጽልመት በልጅሽ ጠፍቶ ብርሃን ሆነ እረፍት አገኘን የምሕረት ዓመት ባንቺ ዘመነ ሰዐሊ ለነ /2/ አዕምሮውን ልቡን ሳይብን አሳድሪብን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን
አዝሙሴ በሲና ሳትቃጠይ ያየሽ ሐመልማል እግዚአብሔር መርጦሽ በማህጸንሽ ዙፋኑን ተክሏል የዲያብሎስን ጥበብ እንዲያፈርስ አምላክ ሰው ሆነ በልጅሽ መሞት መዳናችንም ተከናወነ ሰዐሊ ለነ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ጋሜል_ዘ_ኦርቶዶክስ_አወድሰኝ_ኤፍሬም.mp37.84 MB
❤ 168🕊 5🥰 4
Photo unavailableShow in Telegram
ኅዳር ፯ /7/
በዚች ቀን የእስክንድርያ አገር የሆነ ቅዱስ ጊዮርጊስ በሰማዕትነት አረፈ።
የዚህም ቅዱስ አባቱ ልጅም አልነበረውም የልዳዊው ቅዱስ ጊዮርጊስም ቤተ ክርስቲያኑ የከበረችበት የበዓልዋ መታሰቢያ ኅዳር ሰባት በደረሰ ጊዜ ልጅን ይሰጠው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እንዲማልድለት ቅዱስ ጊዮርጊስን ለመነው ጌታችንም ልመናውን ተቀብሎ ይህን ልጅ ሰጠው ስሙንም በታላቁ ሰማዕት ስም ጊዮርጊስ ብሎ ስም አወጣለት።
የዚህም ልጅ እናትና አባቱ አረፉ እርሱም ከእናቱ ወንድም ዘንድ ተቀመጠ ሃያ አምስት ዓመትም በሆነው ጊዜ በጎ ሥራ የሚሠራ ሆነ ድኆችን እጅግ ይረዳቸው ይወዳቸውም ነበረ የሚራራና የሚመጸውት ሆነ ወደ ቤተክርስቲያን መገሥገሥንም ይወዳል። ለመኰንን አርማንዮስም ሴት ልጅ አለችው ቦታዎችንም በመጐብኘት ደስ ይላት ዘንድ ከባልንጀሮቿ ጋር ወጣች ወደ ደብረ ቊስቋምም ስትደርስ ጣዕም ባለው ድምጽ በመዘመር ሲያመሰግኑ የተሰበሰቡ መነኰሳትን አገኘቻቸው ምስጋናቸውና መዝሙራቸውም ወደ ልቡዋ ገብቶ ተቀረጸ።
ጊዮርጊስንም መነኰሳቱ ስለሚዘምሩት ያስረዳት ዘንድ ጠየቀችው እርሱም ወደማይጠፋ ዕረፍትና ተድላ እንደሚያደርሳቸው ነገራት ወደ አባቷም በተመለሰች ጊዜ በፊቱ ቁማ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነች አባቷም ሊሸነግላት ጀመረ ልጄ ሆይ ይህን አታድርጊ አላት ነገሩን ባልተቀበለች ጊዜ ራሷን በሰይፍ አስቆረጠ በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለች ከዚህም በኋላ ልጅህን ያሳታት ጊዮርጊስ ነው ብለው ለመኰንኑ ነገሩት እርሱም ቅዱስ ጊዮርጊስን ይዞ ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃየው ጭካኔውንም አይቶ ወደ ሀገረ እንጽና ሰደደው በዚያም የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበለ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ :- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
❤ 291🕊 15🥰 8
Repost from TgId: 2131344856
Photo unavailableShow in Telegram
« የመጨረሻው ቀን »
« ከ30 በላይ ፕሮጀክቶች »
የተካተቱበት
- የማትቆጩበት
- የማትጠብቁት
ልዩ የግራፊክስ ዲዛይን ሥልጠና
ምዝገባ ዛሬ ይጠናቀቃል 🤗
• Laptop
• Internet
• በቂ ጊዜ
አላችሁ ?
ይሄው አሁን ተመዝገቡ ባለሙያ ሁኑ
@Greenbirdtechnology
√ በ300 ብር ቅድመ ክፍያ ብቻ
√ ጠቅላላ ክፍያ ደግሞ 4500
√ ቤታቹ ሆናቹ ብቻ
@greenbirdtechs
@greenbirdtechs
የለውጥዎ ክንፍ 🔑 🐥
❤ 73
ገሊላ እትዊ
እመቤቴ እሰከ መቼ
በባዕድ ሀገር ትኖርያለሽ /2/
ገሊላ ግቢ/4/ ሀገርሽ ገሊላ ግቢ/2/
ገሊላ እትዊ/4/ ሀገረኪ ገሊላ እትዊ/2/
አዝእመቤቴ ማርያም ገሊላ እትዊ ስደቱ ይበቃሻል ገሊላ እትዊ ሄሮድስ ሞቷልብሎ ገሊላ እትዊ ገብርኤል ነግሮሻል ገሊላ እትዊ በእሳት ሰርገላ ገሊላ እትዊ ዑራኤል ይመራሻል ገሊላ እትዊ ሀገረኪ ገሊላ እትዊ/2/
አዝየዝናቡን ጌታ ገሊላ እትዊ እናቱ ሁነሽ ሳለ ገሊላ እትዊ ሰይጣን በሰው አድሮ ገሊላ እትዊ እያስከለከለ ገሊላ እትዊ ውሃ ጥም ጸንቶብሽ ገሊላ እትዊ አፍሽ ደርቆ ዋለ ገሊላ እትዊ ይበቃል እናቴ ገሊላ እትዊ እረሀብ ጥማትሽ ገሊላ እትዊ ሂጅ ወደ ገሊላ ገሊላ እትዊ ወደ ዘመዶችሽ ገሊላ እትዊ ሀገረኪ ገሊላ እትዊ/2/
አዝየሰማዕታት አክሊል ገሊላ እትዊ የፃድቃን እናት ገሊላ እትዊ ባርከሽ ሰጠሻቸው ገሊላ እትዊ መከራን ስድት ገሊላ እትዊ እኛም ይታደለን ገሊላ እትዊ የአንቺው በረከት ገሊላ እትዊ ሀገረኪ ገሊላ እትዊ/2/
አዝገጽሽ ብሩህ መልካም ገሊላ እትዊ ልክ እንደ ፀሐይ ገሊላ እትዊ እግዝእትነ ማርያም ገሊላ እትዊ እሙ ለአዶናይ ገሊላ እትዊ አይገባም ለአንቺ ገሊላ እትዊ መከራ ስቃይ ገሊላ እትዊ ሀገረኪ ገሊላ እትዊ /2/ ገሊላ ግቢ /4/ አገርሽ ገሊላ ግቢ/2/ ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ገሊላ እትዊ.mp32.42 MB
❤ 163🕊 11🔥 3
Photo unavailableShow in Telegram
ይህቺ ቀን ለእኛ ለክርስቲያኖች ሁሉ እጅግ የደስታ ቀን ነውና ሐሴትን እናድርግ፤ የሰማይና የምድር ጌታ ለእኛ ሲል ካደረገው ስደቱ ኅዳር 6 ተመልሷልና:: ስደቷን አስበን ካዘንን: መመለሷን አስበን ደስ ልንሰኝ ይገባልና:: ‹‹አብርሒ አብርሒ ናዝሬት ሃገሩ፤ ንጉሥኪ በጽሐ ዘምስለ ማርያም መጾሩ›› ልንልም ይገባል፡፡
👉 @ortodoxmezmur
❤ 476🕊 20🥰 13😍 6
Photo unavailableShow in Telegram
ኅዳር ፮ /6/
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ኅዳር ስድስት በዚች ቀን ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከአረጋዊ ዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ከስደት በሚመለሱ ጊዜ ወደ ደብረ ቊስቋም ገባ በመንገድ ጉዞ ካገኛቸውም ድካም አረፉ ።
ዳግመኛም በኋላ ዘመን በዚህ በደብረ ቊስቋም ቅዱሳን ሐዋርያቶቹን ሰበሰባቸው ታቦትንና ቤተ ክርስቲያንንም አክብሮ የቊርባን መሥዋዕትንም ሠርቶ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለወገኖቹ ሰጣቸው ። ለዚህም የእስክንድርያ አገርሊቃነ ጳጳሳት ቅዱሳን አባቶቻችን ቄርሎስና ቴዎፍሎስ ምስክሮችን ሆኑ ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን አምላክን የወለደች የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በረከቷ ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
❤ 173🕊 11😍 1
የፀሀይ መውጫ
የፀሀይ መውጫ ምስራቅ ነሽ/2/
ድንግል የእኛ እናት በብርሃን የተከበብሽ
ማርያም የእኛ እናት በብርሃን የተከበብሽ
አዝታምረኛ ነው ክርስቶስ ሁሉን በጥበብ ያረገው ብርሀን ተክሎ በላይሽ በማህፀንሽ ያደረው አይመረመር ጥበቡ እፁብ እፁብ ብለናል ያስደነቀንን አምላክ በዝማሬ ከበናል
አዝጨለማው ተሰዶ ሄደ ፀሃይ ከሆድሽ ሲወጣ አለፈ የጭንቁ ዘመን ምድር በብርሃን ተውጣ ከድቅድቁ ወተናል በወለድሽልን ፀሃይ አያልፍም ብርሃኑ ኤልሻዳይ ነው አዶናይ
አዝአንቺ የምስራቅ ደጃፍ ሕዝቅኤል በረዕይ ያየሽ የመዳናችን ምዕራፍ የፅድቃችን ምክንያት ነሽ ህይወት ፈሰሰ መቅደስሽ እየቀዳን ጠጣነው ልጅሽ ሲዳስሰን ነው በልምላሜ ያደግነው
አዝየማይጠፋ ፋኖስ ነው በመቅረዛችን ያበራ ከአንቺ የተወለደው በጎቹን በፅድቅ የመራ የአንፀባራቂው አለት አምዱ ተተክሎልናል የሌሊቱንም ግርማ ያለፍርሃት አልፈናል
አዝአንቺ የምስራቅ ደጃፍ ሕዝቅኤል በራዕይ ያየሽ የመዳናችን ምዕራፍ የፅድቃችን ምክንያት ነሽ ህይወት ፈሰሰ መቅደስሽ እየቀዳን ጠጣነው ልጅሽ ሲዳስሰን ነው በልምላሜ ያደግነው ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
- oLEWFNPrB6g.m4a5.36 MB
❤ 138🥰 8🕊 5
ኅዳር 6
በዚች ቀን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ እንዲሁም ከዮሴፍ እና ሰሎሜ ጋር 3 ዓመት ከ 6 ወር በስደት ከተንገላታች በኋላ ወደ ሀገራቸው የተመለሱበት ቀን ነው።
ታድያ ጌታችን በእመቤታችን ጀርባ ላይ ሆኖ በእነዛ የምህረት ጣቶቹን ወደ ኢትዮጵያ ይጠቁም ነበር እመቤታችንም ልጄ ሆይ ለምንድነው ጣትህን ምታመለክተው ስትለው "ያቺ የተባረከች ሀገር ናት" እኔን የሚያመልኩ አንቺን የሚማልዱ በፍቅርሽ የነደዱ ቅዱሳን መነኮሳት የሚፈልቁባት አገር ናት!! ያንቺ ዘመዶች ሰቅለው ይገሉኛል በዚች አገር ያሉ ግን ሳያዩ ያምኑኛል አስራት በኩራት ትሁንሽ ብሎ ሰጣት። በቅዱስ እግራቸውም ጣና ሀይቅን ዋልድባንና ሌሎችንም ዞረው እንደባረኩም ድርሳነ ኡራኤልና ተዓምረ ማርያም ላይ በስፋት ተጽፏል።
እመቤታችንን ከሐና መሀፀን ፈጥሮ ከፍጥረት ዓለም ለይቶ ከሁሉ አልቆ የእናት አማላጅ ትሁናችሁ ብሎ የሰጠን ልዑል እግዚአብሔር ይመስገን የእመቤታችን ቁስቋም ማርያም ምልጃዋና በረከቷ አይለየን!! ሀገራችንን ሰላም ታድርግልን !!
ኀዳር 6 ቀን ወደ ግብጽ አገር ተሰዳ ስትመለስ ቁስቋም በምትባል አገር ገብታ ያረፈችበት በዓል ነው፡፡ ከገነት የተሰደደውን አዳም ወደ ገነት ለመመለስ ሲል ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ከአረጋዊው ዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ወደ ግብጽ ተሰደደ፡፡
ጌታችን ከ3 ዓመት ከ6 ወር የግብጽ ስደት በኋላ ወደ እስራኤል እንደሚመለስ አስቀድሞ ነቢየ ልዑል ሆሴዕ በትንቢት መነጽርነት ተመልክቶ “ልጄንም ከግብጽ ጠራሁት ” ብሎ ተናግሯል ሆሴ 11÷1
ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር - እነሆ የተወደደው ማኅሌተ ጽጌ ተፈጸመ!
«ተመየጢ ተመየጢ ሱላማጢስ ... ሱላማጢስ ሆይ ተመለሽ ተመለሽ » መኃ ፯፥፩ የተዋህዶ ልጆች እንኳን እመቤታችን ከስደት ተመልሳ ቁስቋም የገባችበት በዓል ቀን በሰላም አደረሳችሁ!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
❤ 409🕊 22🔥 1
Repost from TgId: 2131344856
Photo unavailableShow in Telegram
ውድ ኦርቶዶክሳዊያን እንኳን
ለበዓለ ደብረ ቁስቋም አደረሳችሁ
« አንቺ የሰላም መፍሰሻ
አንቺ የደስታ መገኛ ሆይ፥
ተመለሽ ሰላምን እናይብሽ
ዘንድ ተመለሽ 🙏 »
ወይናችን እንዲያፈራ፤
አበባም በምድራችን ላይ
እንዲታይ በመርከቧ ውስጥ
ያለን እኛ ልጆችሽ ምድርን
እንድንወርሳት ሱላማጢስ
ሆይ ተመለሽ
የበዓል ስጦታችን እነሆ
√ Make Your Profile
√ Make Your Story
√ Share for your beloved
ጥራት ያለው ምስል👇
https://t.me/greenbirdtechs/263
Here is a Green Bird Tech's
design #gift for you
ምዝገባችንም ሊጠናቀቅ
1 ቀን ብቻ ቀርቶታል
ቀድማችሁ ተመዝገቡ
@greenbirdtechs
@greenbirdtechs
የለውጥዎ ክንፍ 🔑 🐥
❤ 136
በማይነገር ስጦታ
በማይነገር ስጦታ በማይከፈል ውለታ
ለዘላለም አዳንከኝ/2/
እግዚአብሔር ተመስገንልኝ/2/
አዝስኖር በሞት ጥላ ነፍሴ ከክብር ጎላ ኪዳንህን አስበህ መጣህ ወደ ልጅህ ቃል የለኝም የሚችል የሚገልጥ ያንተን ሃይል አወራለው ለትውልዱ እንደዳነ ሞተህ አንዱ
አዝካቀረቀርኩበት ከሃጢያት ሸለፈት ገዛኸኝ በዋጋ አስፈሪው ሌት ነጋ አሁን ባንተ ነፃ ነኝ ፍፁም ሸክሜ ቀሎልኝ ማዳንህን አውጃለው ቀና አርገኸኝ ቀን ሰላየው
አዝቀረ መባዘኔ ሰላለህ መድህኔ አፈረ ጠላቴ ባንተ መድሃኒቴ ምን እላለው ምን አለኝ ፍቅርህ ከቃል ገዝፎብኝ በሁኔታ ማትለካ አንተ ብቻ ምታስለካ ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
6082726593_1 (9).mp34.80 MB
❤ 214🥰 8🕊 6😍 3
Photo unavailableShow in Telegram
ኅዳር ፭/5/በዚች ቀን ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ላይ ተሰቅሎ ሳለ ጐኑን የወጋ የቅዱስ ለንጊኖስ ራሱ የታየችበት ነው:: ይህም ቅዱስ በጌታችን ካመነ በኋላ በቀጰዶቅያ አገር ወንጌልን የሚሰብክ ሆነ ከሀድያን አይሁድም በላዩ ተነሡበት በመኳንንት ዘንድ በሐሰት ወንጅለው በቀጰዶቅያ አገር ራሱን አስቆረጡት ራሱንም ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዱዋት። በኢየሩሳሌም የሚኖሩም አይሁድ በአዩዋት ጊዜ እጅግ ደስ አላቸው ከዚህም በኋላ ከኢየሩሳሌም ከተማ ውጭ በአንድ ኮረብታ ላይ ቀበሩዋት። በቅዱሱ ስብከት ያመነች አንዲት ሴት በቀጰዶቅያ አገር ነበረች ራሱን ከቆረጡበት ጊዜ ጀምራ በተቆረጠበት ቦታ በመቆም ስለርሱ ታለቅስ ነበር የዚያች ሴት ዐይኖቿ ታወሩ። ከዚህም በኋላ ምናልባት ዐይኖቿ ቢገለጡላት በማሰብ ከከበሩ ቦታዎችና ክብር ይግባውና ከጌታችን መቃብር ለመባረክና ለመለመን ተነሥታ ልጅዋን ይዛ ወደ ኢየሩሳሌም ሔደች። ኢየሩሳሌምም በደረሰች ጊዜ በዚያ ልጅዋ ሞተ ኀዘንም ተጨመረባት ስለዚህም የመረረ ልቅሶን አለቀሰች ከኀዘኗም ብዛት የተነሣ ተኛች። ከዚህም በኋላ ቅዱስ ለንጊኖስን ከሞተው ልጅዋ ጋር በሕልሟ አየችው። ዕገሌ ከሚባልም ቦታ ሒደሽ ራሴን ከዚያ ውሰጂ አላት። ከእንቅልፍዋም በነቃች ጊዜ ስለዚያ ቦታ ጠየቀች ሰዎችም ወደርሱ አደረሱዋት። ያንንም ቦታ በቆፈረች ጊዜ መዓዛው እጅግ ጣፋጭ የሆነ የሽቱ መዓዛ ወጣ። ራሱ ወደአለችበትም ስትደርስ ታላቅ ብርሃን ተገለጠላትና ዐይኖቿም በዚያን ጊዜ ተገለጡላት እግዚአብሔርንም አመሰገነችው። ከዚህም በኋላ ከልጅዋ ሥጋ ጋር የቅዱስ ለንጊኖስን ራስ ወደ አገርዋ ወሰደቻት በታላቅ ክብርም ባማረ ቦታ አኖረቻት። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ :- መጽሐፈ ስንክሳር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
❤ 264🕊 19
እግዚአብሔርን አየሁ
እግዚአብሔርን አየሁ ወዮልኝ ፈራሁኝ
ከረጅም ተራራ ከፍ ካለው ዙፋን
የልብሱ ዘርፍ ሞልቶ መቅደሱን ሸፍኖ
እግዚአብሔርን አየሁ/ከሰማያት ሆኖ/2/
አዝባሕረ ሲመላለስ ብልጭልጭታ ሲሆን እደነቅ ነበረ በአምላክ ስነጥበብ እሳት የለበሱ ሱራፌልን ባይም ከእግዚአብሔር ግርማ/አይወዳደርም/2/
አዝየንጋቱ ጮራ የአጥቢያ ኮከብ የእግዚአብሔርን ብርሃን ቅንጣት አያህሉም የሞት ደጆች ሲያዩት ይከፋፈታሉ የሲዖል አለቆች /ፈጥነው ይወድቃሉ/2/
አዝቤቱንም ጢስ ሞላው ምድር ተናወጠ የእግዚአብሔር ክብር ሞገስ ተገለጠ ጠፍቻለው አልኩኝ ክብሩን በማየቴ ከንፈሬ ዕረክሶ /ስብ ነው አንደበቴ/2/
አዝፍህሙን አመጣና መልዐኩ በጉጠት ለምጻሙን እርኩሱን አፌን ዳሰሰበት ከንፈርህን ነካው ይህ እሳት ኢሳያስ ኃጥያትህ ተሽሯል /በድል ተመላለስ/2/
አዝመልዐኩ በጉጠት የያዘው በፍርሃት ስጋና ደም ሆነው ምሳሌው በእውነት ነጻ እንድትወጣ በደልህ እነዲሰረዝ ቀርበን እንቀበል ለአምላክ /እንታዘዝ/2/
አዝእሳታዊው መልዐክ እሳት እንዳይፈጀው እጅግ ተጠንቅቆ በጉጠት የያዘው እንደምን ይገርማል የሠው ልጅ ሲጎርሰው ካህን የዳሰሰው /እሳቱን እኮ ነው/2/ ሊቀ መዘምራን ይልማ ኅይሉ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
እግዚአብሔርን_አየሁ_Egziabheren_Ayehu_ሊቀ_መዘምራን_ይልማ_ኅይሉ_LikeMezemeranYilmaHailu.mp310.14 MB
❤ 160🕊 13😍 2
ኅዳር ፬ /4/በዚችም ቀን የደማስቆ ኤጲስቆጶስ ቅዱስ ቶማስ በግብጽና በሶርያ እስላሞች በነገሡ ጊዜ በሰማዕትነት አረፈ ። ይህንንም ቅዱስ ቶማስ ከመምህራኖቻቸው ውስጥ አንድ እስላም በተከራከረው ጊዜ ቅዱስ ቶማስ በረታበት ኢየሱስ ክርስቶስ ሰማይና ምድርን በውስጣቸው ያለውንም ሁሉ የፈጠረ አምላክ እንደሆነ በማስረዳት አይሎ ረታው:: ያም እስላም በአፈረ ጊዜ ወደ መኰንናቸው ሒዶ ይህ ክርስቲያናዊ ቶማስ ሃይማኖታችንን ረገመ ብሎ ወነጀለው ። መኰንኑም ወደርሱ አስቀርቦ በውኑ ሃይማኖታችንን ትረግማለህን አለው ቅዱሱም መርገምስ ከአፌ አልወጣም ክርስቶስ እውነተኛ አምላክ እንደሆነ ከእርሱም ሕግ በኋላ ሌላ ሕግ እንደማይመጣ አጽንቼ አስረዳሁት እንጂ ብሎ መለሰለት ። መኰንኑም የእኛስ ሕግ ከእግዚአብሔር ነውን ወይስ አይደለም አለው ቅዱሱም ከእግዚአብሔር አይደለም አለው ። በዚያንም ጊዜ መኰንኑ ተቆጣ ራሱንም በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘና ቅድስት ራሱን ቆረጡት ። በመንግሥተ ሰማያትም የምስክርነት አክሊልን ተቀበለ ። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ :- መጽሐፈ ስንክሳር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
❤ 211🕊 10
አቤቱ ላንተ
አቤቱ ላንተ ለስምህ አለኝ ምስጋና/2/
እንዳንተ ያለ ከአማልክት ማነው ገናና
እንዳንተ ያለ እግዚአብሄር ማንስ አለና
አዝአቤቱ ማዳንህ በእኛ ላይ ተገልጧል ግዙፉ ተራራ በፊታችን ቀልጧል በግንብ የተሰሩ ብረት የለበሱ የአህዛብ ከተሞች በመዝሙር ፈረሱ
አዝስምንቱን ነፋሳት አንተ ስታዛቸው ውቅያኖስ ባህሩም ይዘላል ፊታቸው ቤልፌጉር አልቻለም አንተን መገዳደር የጥበብ ሀገሯ ታላቅ ነህ እግዚአብሄር
አዝበብዙ መጽናናት ህይወቴን መለስካት በቃልህ ወይን ጠጅ ነፍሴን አረካሃት ለዝናም አይደለም ወይም ለሞቅታ የምዘምርልህ ለአምልኮ ነው ጌታ
አዝበጥብርያዶስ ባህር ድግስህ ናፍቆኛል ከፈርኦን እንጀራ ፍቅርህ ለይቶኛል የቦኤዝን እርሻ አልቃርምም እኔ ዋናውን አጭዳለሁ ጌታ ነው መድኅኔ ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
6082726593_1 (6).mp34.94 MB
❤ 183🕊 11🥰 3
ሕዳር ፫ /3/ በዚችም ቀን አባ አትናቴዎስና እኅቱ ኢራኢ አረፉ ። እሊህንም ቅዱሳን ከሀዲ ንጉሥ መክስምያኖስ ጽኑዕ የሆነ ሥቃይን አሠቃያቸው ። በማሠቃየትም በደከመ ጊዜ ዕራቁታቸውን ከጉድጓድ ጨመራቸው በላያቸውም የጒድጓዱን አፍ ዘጋ በውስጧም ነፍሳቸውን አሳለፉ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበሉ በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን ። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
❤ 216🕊 10
