en
Feedback
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

Open in Telegram

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች፣ ስንክሳር፣ መዝሙራትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም አስተያየት @Zimaredawitmessanger ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል። ስለሚሰጡን ገንቢ ሃሳብ እናመሰግናለን። YouTube Page - https://bit.ly/2O1Z3d8 Facebook Page - https://www.fb.com/l/6lp1kJRRR

Show more
2025 year in numberssnowflakes fon
card fon
166 322
Subscribers
-1724 hours
-227 days
-430 days
Posts Archive
ነፍሴ የወደደችውን አገኘች ነፍሴ የወደደችውን አገኘች/2/ እኔም ለዘላለም በእርሱ እረካለሁ/2/ አዝ የጎደለኝ የለም በነፍስ በስጋዬ ይሄ ነው አልልም ያልሰጠኝ ጌታዬ ወደ ሰርጉ ጠራኝ ሁሉን አዘጋጅቶ እውነተኛ መብልን እራሱን ሰውቶ እውነተኛ መጠጥ እራሱን ሰውቶ አዝ መልካሙ እረኛዬ ከቶስ ሳይተወኝ በለመለመው መስክ አሰማራኝ ከማይደርቀው ምንጩ ውሃን ጠጥቻለሁ ከማር የጣፈጠ ቃሉን አግኝቻለሁ/2/ አዝ ጌታ ሆይ በደጅህ መጣል ይሻለኛል ከኃጥአን ድንኳን እጁጉን ይበልጣል ምንም ሳልናወጽ በቤትህ እኖራለሁ የነፍሴን ማረፊያ አንተን ስላገኘው/2/ አዝ ማንን እንደምይዝ አሁን ተረድቼ መጣሁ ወደ አምላኬ ዝናውን ሰምቼ የምፈልገውን ለነፍሴ አገኘሁ ከቤተመቅደሱ ጸሎት አኖራለሁ/2/ ሙሀዘ ስብሐት ልዑልሰገድ ጌታቸው 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show all...
ነፍሴ_የወደደችውን_አገኘሁ_Nefse_yewededchiwun_mezmur_by_Deacon_Zemari_Lulseged.mp34.99 MB
119🕊 8🔥 1😍 1
ገብርኤል ስለው ሰምቶ ገብርኤል /2/ ስለው ሰምቶ መጣ ወደኔ ፈጥኖ ሰንሰለቴን በጠሰው የአንበሶቹን አፍ ዘግቶ
አዝ
ገብርኤል ስጋዬ ሳይረግፍ በአናብስቱ ጥፍር     ››     ታድጎኛል ምልጃው የመልአኩ ክብር     ››     በረሀብ ለነደዱ አናብስት ሲጥሉኝ     ››     አንተ አለኸኝና ክንፎችህ ከለሉኝ
አዝ
ገብርኤል ከአፎቱ ሲመዘዝ የጠላቴ ሰይፍ     ››     አጽንቶ ይዞኛል ፍሬዬ ሳይረግፍ     ››     አደገድጋለሁ አለኝና ፍቅሩ     ››     በእሳት ክንፍ ታጥሯል የደጄ ድንበሩ
አዝ
ገብርኤል በሰይፍ ተመትርዋል የክፉዎች ክህደት     ››     ሐብሉ ተበጥሷል የአመጹ ሰንሰለት     ››     ከቅዱሱ ድንጋይ ሕይወት የሚያፈልቀው     ››     እንዳልለይ እረዳኝ ክብሬን ከፍ አደረገው
አዝ
ገብርኤል አለው ልዩ ስልጣን ከአምላክ የተሰጠው     ››     ይመጣል ወደ እኛ እሳቱን ሊያጠፋው     ››     እኛም እናምናለን ሰምተናል አይተናል     ››     የመላዕክት አለቃ ከአምላክ ያማልዳል ሊቀ መዘምራን ዲ/ን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show all...
6082726593_1 (23).mp35.32 MB
193😍 11🕊 8🔥 1
ጥቅምት ፲፱ /19/
‎ ‎አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ጥቅምት ዐሥራ ዘጠኝ በዚች ቀን በከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ዘመን ቅዱስ በርቶሎሜዎስና ሚስቱ በሰማዕትነት አረፉ ። ‎ ‎እሊህ ቅዱሳንም የግብጽ ምዕራብ ከሆነ ፍዩም ከሚባል አገር ናቸው ክርስቲያኖችም እንደሆኑ በመኰንኑ ዘንድ ወነጀሏቸው መኰንኑም ልኮ አስቀረባቸውና ስለ ሃይማኖት ጠየቃቸው እነርሱም ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፊቱ ታመኑ ። ‎ ‎መኰንኑም ጥልቅ ጒድጓድ እንዲቆፍሩላቸው በዚያም እንዲጨምሩአቸውና በሕይወታቸው እንዲደፍኑባቸው አዘዘ ። መኰንኑም እንዳዘዘ አደረጉባቸው በዚህም ምስክርነታቸውን ፈጽመው የሰማዕትነት አክሊልን በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ ። ‎ ‎ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕታቱ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን ። ‎ ‎ወስብሐት ለእግዚአብሔር ‎ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር ‎💚 @ortodoxmezmur 💚 ‎💛 @ortodoxmezmur 💛 ‎❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show all...
218🥰 9🕊 8
ሞቼ ሰለማልቀር ሞቼ ስለማልቀር ትንሣኤ ስላለኝ በሰማይ ቤታችን ስለምንገናኝ ወዳጅ ዘመዶቼ አታልቅሱ በቃኝ/2/
አዝ
አገኛለሁና ገና አዲሱን ኑሮ አምላክን አስቡት ይብቃችሁ እሮሮ/2/ ይልቅ ጸልዩላት ለነፍሴ እረፍት በቀኝ እንዲያቅማት የጻድቃን አባት/2/
አዝ
ዓለም ኪራይ ቤት ናት ዘላቂ አይደለች ለሥጋ ነው እንጂ ለነፍስ አትመችም/2/ ግን በእርሷ ስንኖር ትዕዛዙን ከፈጸምን ለተዘጋጀው ቤት ወራሾች እኛው ነን/2/ ዲ/ን አቤል ተስፋዬ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show all...
፵.ሞቼ ስለማልቀር (አቤል ተስፋዬ).mp37.25 MB
112🥰 8🕊 5
ጥያቄ❓ከመመለስዎ በፊት የእለቱን ስንክሳር ይመልከቱ። ለምትሳተፉ ለሁላችሁ ቃለ ሕይወት ያሰማልን። በዚች ቀን የከበረ ቅዱስ ሮማኖስ በሰማዕትነት አረፈ ። Anonymous voting
  • ‎ሀ. እውነት ‎
  • ለ. ሐሰት
0 votes
84🕊 10
በአምሳሉ ለሠራኝ በአምሣሉ ለሠራኝ ለቅድስት ሥላሴ በዓርአያው ለሠራኝ ለቅድስት ሥላሴ እገዛለታለሁ በሥጋ በነፍሴ/2/
አዝ
ከድንኳኔ ገብቶ በቸርነት ያየኝ ከሐገር ከወገን ከዘመድ የለየኝ ሥሙን ሊያሸክመኝ ሥሜን የቀየረው ዘሬን እንደ አሸዋ ያበዛው እርሱ ነው ቅድስት ሥላሴ
አዝ
ሥሙን እንድቀድስ ክብሩን እንድወርስ እፍ ብሎብኛል የሕይወት እስትንፋስ ከፍጥረቱ ሁሉ አልቆኛል ሠርቶ መንግስቱን እንድወርስ ሕያውነት ሠጥቶ ቅድስት ሥላሴ
አዝ
ገና ሳልፈጠር ጀምሮ የሚያውቀኝ በበረከት አጥሮ ነገን የሚያይልኝ በእርሱ ነው መቆሜ በእርሱ ነው መኖሬ ትናንትን አልፌ መድረሴ ለዛሬ ቅድስት ሥላሴ
አዝ
በከሐሊነቱ የአመጣኝ ከምድር ከፍጥረት ለይቶ የሰራኝ ለክብር የሚመሰገን ነው በአንድነት ሦስትነት እግዚአብሔር እርሱ ነው አምላከ አማልዕክት ቅድስት ሥላሴ           ዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show all...
ጋሜል_ዘ_ኦርቶዶክስ_በአምሣሉ_ለሠራኝ_ለቅድስት_ሥላሴ.mp35.08 MB
171🕊 5🥰 2😍 2
Photo unavailableShow in Telegram
ጥቅምት ፲፰ /18/
‎ ‎በዚህች ቀን ክርስቲያኖችን በአሳደደ በመኰንን አስቅልጵያኖስ ዘመን የከበረ መነኰስ ሮማኖስ በሰማዕትነት አረፈ። ይህም ቅዱስ የክርስቲያን ወገኖችን መኰንኑ እንዳሳደዳቸው በሰማ ጊዜ ከቀሳውስትና ከዲያቆናት ጋር የክርስቲያን ወገኖችን ሁሉ በአንድነት ሰበሰባቸው ስለ ክርስቶስ ሃይማኖትም መክሮ አጸናቸው። ‎ ‎አስቅልጵያኖስም ይህን ሰምቶ እንዲአመጡት አዘዘ በፊቱም በቆመ ጊዜ አስቅልጵያኖስ በወገን የከበርክ ሮማኖስ አንተ ነህን አለው ቅዱሱም የወገን ክብር ምን ይጠቅመኛል ክብሬ ግን ክርስቶስ ነው ብሎ መለሰለት። መኰንኑም ሰምቶ እንዲሰቅሉትና ጉንጮቹን ይሰነጣጥቁ ዘንድ አዘዘ ጉንጮቹንም ሲሰነጣጥቁት ምንም አልተናገረምና መኰንኑ ትዕግሥቱን አደነቀ። ‎ ‎በዚያንም ጊዜ ሮማኖስ መኰንኑን እንዲህ አለው እነሆ ስንፍናህን እዘልፍ ዘንድ ፈጣሪዬ አፌን ከፈተ በዚያንም ጊዜ የሕፃኑን ራስ በሰይፍ እንዲቆርጡ የቅዱስ ሮማኖስንም ምላሱን ከግንዱ እንዲቆርጡ መኰንኑ አዘዘ። ያን ጊዜ መኰንኑን ይዘልፍ ዘንድ ለአባ ሮማኖስ ረቂቅ አንደበት ተሰጠው ሲዘልፈውም መኰንኑ ሰምቶ ምላሱ እንዳልተቆረጠ ተጠራጠረ። ወታደሩንም ጠርቶ ምላሱን ያልቆረጥክ ለምንድን ነው አለው ወታደሩም የምላሱን ቁራጭ ያመጡ ዘንድ እዘዝ አለው አምጥተውለትም አይቶ መኰንኑም ወደ ወህኒ ቤት አስገብተው በዚያ አንቀው እንዲገድሉት አዘዘ። እንዲህም ምስክርነቱን ፈጽሞ የምስክርነት አክሊልን በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ። ‎ ‎የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን አሜን ! ‎ወስብሐት ለእግዚአብሔር ‎ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር ‎💚 @ortodoxmezmur 💚 ‎💛 @ortodoxmezmur 💛 ‎❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show all...
205🕊 13🔥 2
ትናትና ካንተ ጋር ትላንትና ካንተ ጋር ዛሬ ደግሞ ከሌላ/1/ ሰልችቶኛል አባቴ ሆይ ሁሌ መሄድ ወደሁዋላ ሁሌ መጓዝ ወደሁዋላ/2/ ሰዶምን አልተውኩም ወደሁዋላ አየዋት ደግሜ ምንኛ ከንቱ ነኝ ሳልለወጥ ባለሁበት ቁሜ ይነዳል ከተማው ይቃጠላል በቁጣው እሳት እጄን ይዘህ አውጣኝ ዞአል ሳልደርስ ጌታዬ እንዳልሞት ጨው አልጫ ቢሆን በምን ይጣፍጣል አጣፍጠኝ በቃልህ ከደጅህ እንዳልወጣ
አዝ
ዴማስን ሆኛለሁ ተሰሎንቄ አስራ ያስቀረችኝ ስሸሽህ አግኝታ ከባህሩ ከጥልቁ የጣለችኝ ወፎች ለቅመውታል ቅዱስ ቃልህ በውስጤ የታለ አዘገየኝ እንጂ ያጠላቴ እየሸነገለ መልሰኝ ልመለስ በሎቅሶ በዕንባ አሳንባሪው ይትፋኝ ወደ ቤትህ ልግባ
አዝ
አለቀ ገንዘቤ የሰጠኸኝ አፍሰህ በችሮታህ እራሴን አገኘሁት አመሻሽላይ በተናቀ ቦታ ጨልሟል ዞሪያዬ ምይዘውን ነገር አጥቻለሁ የድሮዋ አደለሁም የኔ ጌታ ዛሬ ደክሜአለሁ መንገድ ለጠፋው ሰው ክንድህ ወዴት አለ ምንድነው ምሬትህ እራሱን ለጣለ
አዝ
ማለዳ ስነቃ ዘምሬልህ ሲመሽግን ሌላ ነኝ ቃልህ ያልለወጠኝ ያልቀየረኝ ጌታዬ እኔ ማነኝ አይወስንም ልቤ ያመነታል ይሸሻል አጥብቆ ዘላለም ላይደላኝ እስከመቼ ካንተ ተደብቆ እንድወስን እርዳኝ ይበርታ ጉልበቴ ጠላት ጭኑን ይስፋ እቀፈኝ አባቴ ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show all...
6082726593_1 (22).mp36.47 MB
161🕊 4😍 2
​​እልል በሉ እልል በሉ በአንድነት ዘምሩ አመስግኑ ለክብሩም ዘምሩለት እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም በሉ አዝ በኃጢያት ባርነት ስንኖር ተገዝተን ከቤቱ ስንርቅ ትእዛዙን አፍርሰን አይቶ ዝም ያላለን ጠላቶቹ ሳለን ውለታው ብዙ ነው ክብር ለእርሱ ይሁን/2/ አዝ ራሱን አዋርዶ እኛን አከበረን ሥጋውና ደሙን ብሉ ጠጡ አለን መልካም እረኛ ነው የሚያሳጣን የለም ምስጋና ይድረሰው ለመድኃኔዓለም/2/ አዝ ሕይወቱን የሰዋ እንደ አምላክ ማን አለ ለሰው ልጆች ብሎ በመስቀል የዋለ ፍቅሩም አይለካም አያልቅም ቢወራ ከሰማያት ወርዶ ሆነ ከእኛ ጋራ /2/ አዝ ሥራውን እናድንቅ እንዲህ ለወደደን ከማያልቀው ፍቅሩ በረከት ላደለን ለማይነገረው ለአምላክ ስጦታ ውዳሴን እናቅርብ እንዘምር በእልልታ /2/ በዘማሪ ፍቃዱ አማረ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show all...
እልል_በሉ_እልል_በሉ_በአንድነት_ዘምሩ_አመስግ.mp35.11 MB
175🔥 4🕊 2
Photo unavailableShow in Telegram
‎ጥቅምት ፲፯ /17/
‎ በዚችም ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሠላሳ አንደኛ የሆነ የእስክንድርያ አገርሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት ዲዮስቆሮስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው። ‎ ‎ይህም አባት በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ሊቀ ጵጵስና በተሾመ ጊዜ መልእክትን ጽፎ ወደ አንጾኪያ ሊቀ ጳጰሳት ቅዱስ ሳዊሮስ ላካት ። እርሱም ስለ ምስጢረ ሥላሴ እና ስለ ምስጢረ ስጋዌ ጽፎ ላከለት። ‎ ‎መልእክቱም ወደ ቅዱስ አባት ሳዊሮስ በደረሰች ጊዜ አነበባትና ፈጽሞ ደስ ተሰኘባት ለአንጾኪያም ሕዝብ አስተማረባት ሁሉም ደስ አለቸው። ‎ ‎ከዚህም በኋላ አባ ሳዊሮስ ለአባ ዲዮስቆሮስ የመልእክቱን መልስ እንዲህ ብሎ ጻፈ ። በኒቅያ ከተማ ተሰብስበው ሃይማኖታቸው የቀና 318ቱ ቅዱሳን አባቶቻችን በቀናች ሃይማኖት አጽንተው የሠሩዋትን ቤተ ክርስቲያኑን እንድትጠብቅ ለዚች ለከበረች አገልግሎት የመረጠህ እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ ። ዳግመኛም በዚሁ እንዲጸና ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ እንዳይል አስገነዘበው ደግሞም በቀናች ሃይማኖት እንዲጸኑ ሕዝቡን ሁል ጊዜ አስተምራቸው አለው ። ‎ ‎የአባ ሳዊሮስም መልእክት ወደ አባ ዲዮስቆሮስ በደረሰች ጊዜ ደስ ተሰኘባት በሁሉ ቦታም እንዲአስተምሩባት አዘዘ ይህም አባት ሕዝቡን ሁል ጊዜ የሚያስተምራቸው ሆነ ። ሁል ጊዜም ቅዱሳት መጻሕፍትን በማንበብ ያስተምራቸዋል ኤጲስቆጶሳቱንና ካህናቱንም መንጋዎቻቸውን ስለ መጠበቅ ያዛቸዋል መልካም አገልግሎቱንም አድርሶ እግዚአብሔርንም ደስ አሰኝቶ አረፈ። ‎ ‎ወስብሐት ለእግዚአብሔር ‎ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር ‎💚 @ortodoxmezmur 💚 ‎💛 @ortodoxmezmur 💛 ‎❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show all...
213🕊 14🥰 1
ፀጋን የተመላሽ ፀጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ/2/ የጌታዬ እናት ማርያም ላመስግንሽ ደስ ይበልሽ ደስ ይበልሽ
አዝ
እናቱ ስለሆንሽ    ደስ ይበልሽ የአማኑኤል         ደስ ይበልሽ ምስጋናን አገኘሽ  ደስ ይበልሽ ከቅዱስ ገብርኤል ደስ ይበልሽ እናትና ድንግል      ደስ ይበልሽ ሁለቱን ሆናለች      ደስ ይበልሽ ነውር የሌለባት     ደስ ይበልሽ የእግዚአብሔር ሀገርነች ደስ ይበልሽ
አዝ
የሄዋን መድሐኒት  ደስ ይበልሽ የአምላክ እናት      ደስ ይበልሽ እፀ ሕይወት ማርያም ደስ ይበልሽ ስብህት ወቡርክት  ደስ ይበልሽ የገነት ፈሳሽ ሆይ    ደስ ይበልሽ ንፁ የሰርግ ቤት     ደስ ይበልሽ በውስጧ ያለባት    ደስ ይበልሽ የኪዳኑ ፅላት         ደስ ይበልሽ
አዝ
ለምልማ የተገኘች   ደስ ይበልሽ የአሮን በትር           ደስ ይበልሽ መልካሟ እርግብ ማርያም ደስ ይበልሽ የአምላክ ማሕደር    ደስ ይበልሽ ቸርና ሰው ወዳጅ    ደስ ይበልሽ ነውና ልጅሽ           ደስ ይበልሽ በይቅርታው ብዛት.  ደስ ይበልሽ ማሪን በምልጃሽ     ደስ ይበልሽ ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show all...
ጸጋን የተመላሽ ሆይ (1).mp31.44 MB
176🕊 7🔥 2🥰 2