Bank of Abyssinia
Open in Telegram
Bank of Abyssinia – The Choice for All Welcome to BoA’s official Telegram channel! Use @BOA_ATM_bot to access: ATM locators Card services & support Real-time updates
Show more2025 year in numbers

182 997
Subscribers
+4724 hours
+7487 days
+4 55830 days
Posts Archive
የባንካችን እችላለሁ መርሃ ግብር አካል የሆነው የሴት ስራ ፈጣሪዎች የንግድ ትዕይትና ባዛር ዛሬ በድምቀት ተከፈተ
ባንካችን አቢሲንያ የአለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ማለትም (ማርች 8ን)
ምክንያት በማድረግ ለአራተኛ ጊዜ ያዘጋጀው የእችላለሁ መርሃ ግብር ዘንድሮ በአይነቱ ለየት ብሎ ፣ በተለያዩ ማህበረሰቡን በሚያሳትፉ ተግባሮች ታጅቦ እንደቀጠለ ይገኛል፡፡
በዛሬው ዕለት በመስቀል አደባባይ በይፋ የተከፈተው የንግድ ትርኢት
እና ባዛር፣ ሴት የስራ ፈጣሪዎችን ለማበረታታት ይቻል ዘንድ፤ የንግድ ትስስር ለመፍጠር እንዲግዝ በተጨማሪም ሴት የስራ ፈጣሪዎች የተለያዩ ምርትና አገልግሎታቸውን ለማህበረሰብ ማቅረብ ይችሉ ዘንድ ታስቦ የተከወነ
ነው፡፡
መርሃ ግብሩን በይፋ መርቀው የከፈቱት የባንካችን ዋና -ኢንተርፕራይዝኦፊሰር የሆኑት ወ/ሮ መሠረት አስፋው እንዲሁም ወ/ሮ ትሁና ስንሻው በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት
ማጎልበት ዴስክ ሃላፊ ሲሆኑ በተጨማሪም የኢትዮጵያ ሴት ነጋዴዎች ማህበር ፕሬዝዳንትና ለስራ ፈጣሪ ሴቶች ተምሳሌት በመሆን የበኩሏን እየተወጣች የምትገኘው ወ/ሮ በረከት ወርቁ (በረከት ገበሬዋ)፣ የባንካችን
ከፍተኛ የስራ መሪዎች፣ በተለያየ ደረጃ የሚገኙ የስራ ሃላፊዎችና የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች ናቸው፡፡
እንደሚታወሰው ባንካችን አቢሲንያ ማኅበራዊ ሃላፊነቱን ከሚወጣባቸው ተግባራት አንዱ አካል በሆነው የእችላለሁ መርሃ ግብር ውድድር እስከ መጋቢት 22 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ከድምፅ ውድድር በተጨማሪ በቲክታክ የባንካችንን
አደይ እና ዘሃራ የቁጠባ ሂሳቦችን በተለየ መልኩ ማስተዋወቅን ጨምሮ የመርሃ ግብሩ አካል የሆነው ለሴት የስራ ፈጣሪዎች በአነስተኛ ወለድ ያለ ማስያዣ አስከ ብር 500 ሺህ ድረስ ብድር ተመቻችቷል፡፡
በዛሬው ዕለት በይፋ የተከፈተው የንግድ ትርኢትና ባዛር በመስቀል አደባባይ
እስከ መጋቢት 18 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ በመሆኑ በመጎብኘትና ግብይት በመፈፀም ስራ ፈጣሪዎችን እንድታበረታቱ እንጋብዛለን፡፡
👍 49
ባንካችን ዘንድሮን ጨምሮ ላለፉት ተከታታይ አራት ዓመታት አዳዲስ ሴቶችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ማዕቀፎችን በማካተት ማርች 8 እና ሙሉ የመጋቢት ወርን በልዩ ሁኔታ ሴቶች የሚበረታቱበት ለማድረግ አዳዲስ እና አሳታፊ ሥራዎችን በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡
ባዛሬው ዕለት ማለትም መጋቢት 16 ቀን 2017 ዓ.ም. ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የባንካችን ሴት የበላይ የሥራ አመራሮች በተገኙበት በኤግዚቢሽን ማዕከል፣ ሴት ሥራ ፈጣሪዎች ምርቶቻቸውንና አገልግሎቶቻቸውን የሚያስተዋውቁበት እንዲሁም የገበያ ትስስር የሚያስገኝላቸው የንግድ ትርዒትና ባዛር የማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሂዷል፡፡
እስከ መጋቢት 18 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ለሶሶት ቀናት በሚቆየው በዚህ
የንግድ ትርዒትና ባዛር በዋናነት በሴቶች ተሳትፎ የተዘጋጁ የእጅ ሥራ ውጤቶች፣አልባሳት፣ የውበት መጠበቂያዎች፣ ምግብና መጠጦች እና ሌሎችም ቁሳቁሶች ለሽያጭ እና ለዕይታ ክፍት ይሆናሉ፡፡ ይምጡና ይጎብኙ፣ ያሻዎትን ይሸምቱ፣ ይደሰቱበት!
👍 27❤ 6🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
ለግብይቶ ዛሬ ባለው የምንዛሪ ተመን ላይ የ2% ተጨማሪ ጉርሻ ያግኙ። #Banking #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
❤ 13👍 8👏 2🤩 2
Photo unavailableShow in Telegram
ባንካችን ማርች 8 አስመልክቶ ያዘጋጀው ባዛር ነገ በመስቀል አደባባይ ይከፈታል
ባንካችን አቢሲንያ በየዓመቱ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ማርች 8 አስመልክቶ ለ4ተኛ ጊዜ ባዘጋጀው የ”እችላለሁ!” መርሐ ግብር ካዘጋጃችው የተለያዩየተሰጥኦ ውድድሮች በተጨማሪ ማኅበራዊ ኃላፊነትን ከመወጣት አንጻር የሚሰሩ ስራዎችም አሉት፡፡
ከእነዚህም መካከል ሴት ደንበኞቻችንና ከባንካችን ብድር የወሰዱ ሴት የሥራ ፈጣሪዎች ሥራቸውን የሚያስተዋውቁበትናምርቶቻቸውን ለሽያጭ የሚያቀርቡበት የንግድ ትርዒትና ባዛር ነው፡፡
በዚህ ከነገ መጋቢት 16 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለ 3 ቀናት በመስቀል አደባባይ በሚካሄደው የንግድትርኢትና ባዛር ላይ ወደ 100 የሚደርሱ ሴት የሥራ ፈጣሪዎች ይሳተፋሉ፡፡ ይምጡና ይጎብኙት፣ ያሻዎትን ይሸምቱ፣ ይደሰቱበት!
👍 87😁 7❤ 6👏 4🤩 2
Photo unavailableShow in Telegram
ለግብይቶ ዛሬ ባለው የምንዛሪ ተመን ላይ የ2% ተጨማሪ ጉርሻ ያግኙ። #Banking #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
👍 23❤ 5🤩 2
ባንካችን አቢሲንያ የአእምሮ ዕድገት ውስንነት ለገጠማቸው ሕጻናት የትምህርት እና ሥልጠና ማዕከል በማቋቋም ከ2,000 በላይ ሕጻናትን እያገዘ ያለው ዲቦራ ፋውንዴሽን “መጋቢትን ከዲቦራ ጋር” በሚል ዛሬ ለ5ኛ ጊዜ የሚያከብረውን ዓለም አቀፍ የዳውን ሲንድረም ክብረ በዓል የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ አጋር ሆነ፡፡
በኢትዮጵያ ከአእምሮ ዕድገት ውስንነት ሕመም ጋር የሚኖሩ ከ600,000 በላይ ሕጻናት አሉ የሚል ግምት አለ፡፡ እነዚህን ሕፃናት እና ወላጆቻቸውን የማገዝ ዓላማን አንግበው የተቋቋሙ ሌሎች የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ያሉ ሲሆን፣ ከዚህ አኳያም የምስረታ ጊዜው ከአምስት ዓመት በላይ የሆነው ዲቦራ ፋውንዴሽን ያቀደው ግዙፍ ፕሮጀክት ወደ መሬት ሲወርድ ጎዶሎ የሚሞላ፣ አገራችን ያለባትን ትልቅ ክፍተት የሚደፍን እና በየቤቱ ተዘግቶባቸው ያሉ የብዙ ሕጻናትንና መኖር ስቃይ የሆነባቸውን እናቶች ችግር የሚያቀል ነው።
ባንካችን አቢሲንያ ከመንግሥት፣ ከግብረ ሠናይ ድርጅቶችና ሌሎች ተቋማት ለተጠየቁ የድጋፍ ጥያቄዎችና ሀገራችን እና ሕዝቧ የገጠሟቸውን ችግሮች በተቻለ ለመቅረፍ ያለስስት እጆቹን መበዘርጋት ማኅበራዊ ኃላፊነቱን በሚገባ ሲወጣ ቆይቷል፡፡
ባንካችን አቢሲንያ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማኅበር፣ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር፣ ሜሪ ጆይ፣ ፓርኪንሰንስ ፔሸንት ሳፖርት ኦርጋናይዜሽን የንግድና አሠሪዎች ምክር ቤት የክብር አባል በመሆን በተጨማሪ ማኅበራዊ ኃላፊቱን እየተወጣ ይገኛል፡፡
እንዲሁም ባንካችን ዲቦራ ፋውንዴሽንንም ከምስረታ ጀምሮ አጋርነት በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች አጋርነቱን ሲያሳይ ቆይቷል፡፡
ብዙ ቤተሰቦች ከአእምሮ ዕድገት ውስንነት ያለባቸውን ሕፃናት ከማሳደግ ጋር ተያይዞ ከባድ ፈተና ይገጥማቸዋል፡፡ ዲቦራ ፋውንዴሽን እነዚህን ወገኖች ለማገዝ ታስቦ የተቋቋመ እንደመሆኑ ከዚህ ጋር ተያይዞ እየሠራቸው ያሉትን የትምህርት፣ ጤና እና ማኅበረሰብ አቀፍ የሆኑ ሥራዎችን አጠናክሮ እንዲቀጥል በማበረታታት የሀገር የወገን አለኝታነቱን በቀጣይም አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።
👍 61❤ 6🔥 3🤩 2
ባንካችን አቢሲንያ ከቶሞካቡና ጋር በጥምረት የጀመረውን ልዩ ካፌ ለአገልግሎት ክፍት አደረገ
ባንካችን አቢሲንያ ደንበኞች እየተዝናኑ የባንክ አገልግሎት ማግኘት ይችሉ ዘንድ ቅርንጫፎችን ከካፌ ጋር በማቀናጀት ሁለተኛውንልዩ ካፌ (Branch with Café) በባንካችን ኤርፖርት ቅርንጫፍ ለአገልግሎት ክፍት አድርጓል፡፡
በዛሬው ይፋዊ የምርቃት ሥነ-ሥርዓት አገልግሎት የጀመረው ይህ ልዩ ካፌ የወቅቱን የባንክ ቴክኖሎጂዎች በማስተዋወቅ የሚታወቀው ባንካችን አቢሲንያ እና በቡና አቅርቦቱ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ከሚታወቀው ቶሞካ ቡና ጋር በጥምረት የከፈተው ነው፡፡
አገልግሎቱ በአሁኑዘመን ሰዎች በቀላሉ ከቴክኖሎጂ የሚያገኙትን ደስታ ከባንክ አገልግሎት ጋር በማጣመር እየተዝናኑ ጎን ለጎን በቴክኖሎጂ የታገዘ የባንክ አገልግሎት የሚያገኙበትን ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር ነው፡፡
ዓላማው ቀለል ያለአገልግሎትን መስጠት፣ የደንበኞቻችንን ልምድ ማሻሻል እና የባንክ ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ከፍ ማድረግ ሲሆን በተጨማሪም ደንበኞች ለመገልገል ሲመጡ፦
✔️ በተመቸ ከባቢ ውስጥ የካፌ አገልግሎት እየተጠቀሙ እንደ ሞባይል ባንኪንግ ፣ፖስ ፣አይ ቲ ኤም እና ኤቲ.ኤም ማሽን በመሳሰሉ ራስ አገዝ የባንክ ቴክኖሎጂዎች በቀላሉ አገልግሎት ያገኛሉ፣
✔️ በካፌው ውስጥ ምንም አይነት የጥሬ ገንዘብ ግብይት የማይኖር ሲሆን ሁሉም ግብይቶች ቴክኖሎጂን ማዕከል ባደረገ መልኩ በስፍራው ባሉ ታብሌቶች ፣ኤ.ቲ.ኤም፣ ኪዉ.አር እና በሞባይል ባንክ ያከናውናሉ፣
✔️ በባንካችን ዘመናዊ የክፍያ አማራጮች (ዴቢት እና ክሬዲት ካርዶች) አገልግሎቱን የሚጠቀሙ የባንካችን ደንበኞችም የልዩ ቅናሽ ተጠቃሚይሆናሉ፡፡
በምርቃቱ ሥነ-ሥርዓት ላይም ባንካችን ጥሩ ጣዕም ባለው ቡናውና በአገልግሎቱ ከሚታወቀው ቶሞካቡና ጋር በአጋርነት በመስራቱ ደስተኛ መሆኑንን ገልጾ ይህ ፕሮጀክት የተሳካ እንዲሆን ላደረጉ የባንኩ የሥራ ክፍል ኃላፊዎችና ሠራተኞች እና ለቶሞካ ቡና ባለቤትና ሠራተኞች ምስጋናውን አቅርቧል፡፡
👍 47❤ 7
00:48
Video unavailableShow in Telegram
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንዳንድ አጭበርባሪዎች ከፋይናንስ ተቋም ነው የምደውለው በማለት ለመስመር ብድር እንዲመዘገቡ በተለያዩ የማማለያ ቃላት በማግባባት የኤ.ቲ.ኤም ካርድ ቁጥርዎን ሚስጥራዊ መረጃና የአንድጊዜ የይለፍ ቃልዎን (ኦ.ቲ.ፒ) እየጠየቁ እንደሚገኙ ተደርሶበታል ፡፡ በመሆኑም አነኚህን ሚስጥራዊ መረጃዎችን ለማንም እንዳያጋሩና በጥንቃቄ እንዲይዙ እያሳሰብን ለመስመር ብድርምመመዝገብ ከፈለጉ፣ ህጋዊ መስመሩን ተከትለው ማከናወን እንደሚችሉ እንገልጽልዎታለን፡፡
በተጨማሪም እንዲህ አይነት መረጃዎችን ሲጠየቁ፣ መረጃውን ሳይናግሩ ወደ ባንካችን ነፃ የስልክ መስመር 8397 ይደውሉ፡፡
_security amharic (2).mp425.77 MB
👍 56👌 3😁 2🤩 2
Photo unavailableShow in Telegram
ለግብይቶ ዛሬ ባለው የምንዛሪ ተመን ላይ የ2% ተጨማሪ ጉርሻ ያግኙ። #Banking #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
👍 20❤ 3🤩 3🤔 2
Photo unavailableShow in Telegram
ሓጃችሁ መብሩር፣ ሰዕያችሁ መሽኩር እንዲሆን ከልብ የሚመኘው አቢሲንያ አሚን እንኳን ለ1446ኛው (ዓመተ ሂጅራ) የሐጅ እና ዑምራ ጉዞ በሠላም አደረሳችሁ እያለ፤ የሸሪዓ መርህን መሠረት አድርጐ በተዘጋጀው የሐጅና ዑምራ የሙዳራባህ ሂሳብ በመጠቀም፤ አንድም የሐጅና ዑምራ ንያዎን እንዲያሳኩ፣ ሁለትም ከሐላል ኢንቨስትመንት ከሚገኘው ትርፍ ተካፋይ በመሆን ከኛ ጋር በስኬት እንዲጓዙ በአክብሮት ይጋብዝዎታል፡፡
ሐጀን መብሩር፣ ወሰዕየን መሽኩር!
አቢሲንያ አሚን
ዕሴትዎን ያከበረ!
👍 53🔥 7🤩 4
Photo unavailableShow in Telegram
ለግብይቶ ዛሬ ባለው የምንዛሪ ተመን ላይ የ2% ተጨማሪ ጉርሻ ያግኙ። #Banking #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
👍 26❤ 2🔥 2🤩 2
አንድምሽት በባቡል ኸይር ልዩ የኢፍጣር መርሐ ግብር ተከናወነ!
የሸሪዓውን መርሆች መሠረት አድርጎ የተሟላ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት የሚሰጠው አቢሲንያ አሚን ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት በተለያዩ ከተሞች በመገኘት ለተቸገሩ ወገኖቻችን የረመዳን የኢፍጣር መርሐ ግብሩን እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን በትላንትናው ዕለት መጋቢት 10/2017 ምሽት "አንድ ምሽት በባቡል ኸይር" በሚል መሪ ሐሳብ በባቡል ኸይር የበጎ አድራጎት ድርጅት በመገኘት የኢፍጣር መርሐ ግብር አከናውኗል።
በመርሐ ግብሩ አቶ አብዱልቃድር ሪድዋን ዋና ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ኦፊሰር፣ የአቢሲንያ አሚን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የአቢሲንያ አሚን ብራንድ አምባሳደር ሙሐመድ ፈረጅና፤ ሌሎች የባንኩ ሠራተኞች ተገኝተዋል።
የኢፍጣር መርሐ ግብሩን በባቡል ኸይር የበጎ አድራጎት ድርጅት ያደረገው አቢሲንያ አሚን፤ በበርካታ ማኅበረሰብ አቀፍ የበጎ አድራጎት ሥራዎች ላይ በሚያደርገው ተሳትፎና በሚያኖረው አሻራዎቹ የሚታወቅ ሲሆን፤ የትላንትናው የኢፍጣር መርሐ ግብርም የዚሁ አካል መሆኑ በመድረኩ ተወስቷል።
በተለያዩ የአገራችን አካባቢዎች ከተሰማሩ የተራድኦ ተቋማት ጋር በመቀናጀት በንጹህ የመጠጥ ውሃ ቁፋሮ፣ ለአካል ጉዳተኞች የዊልቼር ድጋፍ በማድረግና በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ አደጋዎች ተጎጂና ተጋላጭ ለሆኑ ወገኖቻችን ምግብና መሰል አስፈላጊ ግብዓቶችን ድጋፍ ከማድረጉ ባሻገር፤ በስኩል አዋርድ ፕሮግራሙ በትምህርት ውጤታቸው የላቀ ደረጃ ያስመዘገቡ ተማሪዎችን እና መምህራንን በመሸለምና በማበረታታት በትምህርት ልማትና ጥራት ላይም እየሠራ ይገኛል።
በወለድ ነፃ የፋይናንስ ሥርዓት ሰፊ ተደራሽነትና የከበረ ሥም ያለው አቢሲንያ አሚን፤ በሥራ ፈጠራ አቅማቸው ችግሮችን ወደ ዕድል መቀየር ለሚችሉ በርካታ ኢንተርፕሩነሮች በየደረጃው እስከ ብር አንድ ሚሊየን ድረስ የሚያሸልመውን "አሚን አዋርድ የሥራ ፈጠራ ውድድር" በሁለት ዙር በማዘጋጀት፤ ከተለያዩ የሃገራችን አካባቢዎች የተሳተፉ ባለሙያዎችን በቅርበት ሲያግዝና አቅማቸውን መጠቀም እንዲችሉ ሲያነቃቃ ቆይቷል።
በትላንትናው ምሽት መርሐ ግብር አቢሲንያ አሚንን በልዩነት ያመሰገኑት የባቡል ኸይር መሥራችና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሃናን ማህሙድ፤ የአቢሲንያ አሚን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ካደረጋችሁልን ድጋፍ ባሻገር ዛሬን ከኛ ጋር ውላችሁ ለወገኖቻችሁ ላሳያችሁት አብሮነት ክብር አለን ያሉ ሲሆን፤ ባቡል ኸይር የበጎ አድራጎት ድርጅት የምገባ ተግባሩን ከአምስት ዓመት በፊት ሲጀምር የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ቀዳሚው የፋይናንስ ተቋም አቢሲንያ አሚን እንደነበረ በማውሳት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡
👍 53🔥 4❤ 3👌 3😁 2🤩 2
Photo unavailableShow in Telegram
ለግብይቶ ዛሬ ባለው የምንዛሪ ተመን ላይ የ2% ተጨማሪ ጉርሻ ያግኙ። #Banking #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
👍 30❤ 7🤩 3
Photo unavailableShow in Telegram
ባንኮክ ላይ ፏ ብትን ይሉ ይሆናል!
ሊያውም ከሚወዱት ተጨማሪ አንድ ሰው ጋር! አሁኑኑ አፖሎን በማውረድ እና በማጋራት ወይም ዲፖዚት በማድረግ የእጣ ቁጥራችሁን ያዙ!
የመርሃ ግብሩን ዝርዝር መረጃ ከዚህ ያግኙ፡፡
https://t.me/BoAEth/1525
አፖሎን በማውረድ ተሳታፊ ይሁኑ፡
ለአንድሮይድ ስልኮች: https://play.google.com/store/apps/details...
ለአፕል ስልኮች: https://apps.apple.com/eg/app/apollo-digital/id1601224628
ለህዋዌ ስልኮች ፡https://appgallery.huawei.com/app/C108966741
#መጣሁልሽ #አምሮኛል_መጣሁልሽ #ApolloWinBig #DepositAndWin #JoinApolloGetRewarded
👍 51❤ 6😁 6
Photo unavailableShow in Telegram
ለግብይቶ ዛሬ ባለው የምንዛሪ ተመን ላይ የ2% ተጨማሪ ጉርሻ ያግኙ። #Banking #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
👍 26❤ 5👏 2🤩 2
Photo unavailableShow in Telegram
ለግብይቶ ዛሬ ባለው የምንዛሪ ተመን ላይ የ2% ተጨማሪ ጉርሻ ያግኙ። #Banking #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
👍 41❤ 8😱 4🤩 2
