es
Feedback
YeneTube

YeneTube

Ir al canal en Telegram

መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

Mostrar más
2025 año en númerossnowflakes fon
card fon
107 362
Suscriptores
-5724 horas
-4017 días
-2 12730 días
Archivo de publicaciones
የጠለፋ እና የእገታ ተግባር የፈፀሙ አምስት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ በምዕራብ ሸዋ እና  በሰሜን ሸዋ  ሁለት ዞኖች ውስጥ የጠለፋና የእገታ ተግባር የፈፀሙ አምስት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ።እንደ ምዕራብ ሸዋ ዞን የአደአ በርጋ ወረዳ አቃቢ ሕግ ፅህፈት መግለጫ 1ኛ ተከሳሽ ግርማ ሳሕሉ 2ኛ ተከሳሽ ፀጋ ሐይሉ 3ኛ ተከሳሽ  ቶሊ ደጉ የተባሉ ሶስት ተከሳሾች ጥቅምት 11 ቀን 2018ዓም ከቀኑ ዘጠኝ ሠዓት ላይ ለአንደኛው ተከሣሽ በግዳጅ የትዳር አጋሩ ለማድረግ የአስራ አራት ዓመቷን ታዳጊ ከወፍጮ ቤት ስትመለስ ጠብቀው የጠለፋ ተግባር ፈፅመው ለማምለጥ ሲሞክሩ ተጠላፊዋ ባሰማችው የድረሱልኝ ጩኸት ስልጠና ላይ የነበሩ የፀጥታ አካላት ሰምተው ተከታትለው በቁጥጥር ስር ዉለዋል። ሶስቱም ተከሳሾች በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኃላ በፖሊስ የምርመራ መዝገባቸው  በበቂ ማስረጃ ተጣርቶ ለአቃቤ ሕግ የተላከ ሲሆን አቃቤ ሕግም በወንጀል ሕግ ቁጥር 587 ንዑስ አንቀፅ 1 ሴትን በመጥለፍ ወንጀል ክስ መስርቷል፡፡ ክሱን ሲከታተል የቆየው የአደአ በርጋ ወረዳ ፍርድ ቤት ጥቅምት 24-2018ዓ.ም በዋለው ችሎት በሶስቱም ተከሣሾች ላይ በእያንዳዳቸው ላይ በሉለት አመት ከሶስት ወር እስራት እንደተወሰነባቸው የአቃቤ ሕግ ፅህፈት ቤት መግለጫው አመልክቷል። በተመሳሳይ በወረጃርሶ ወረዳ ሌንጮ ቦርሱ ቀበሌ የጦር መሣርያ በመታጠቅ የእገታ ተግባር ሲፈፅሙ የነበሩ ግለሰቦች በእስራት ተቀጠተዋል።እንደ ወረጃርሶ ወረዳ አቃቤ ሕግ ፅህፈት ቤት መግለጫ  ደሬሣ ተሾመ እና ጀማል ደምሴ የተባሉ ሑለት ተከሳሾች ለግዜው እጃቸው ካልተያዙ ሑለት ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን የጦር መሣርያ በመታጠቅ  መስከረም 25 ቀን 2018 ዓም ሁለት ግለሰቦችን አግተው አፍነው ለመውሠድ ሲሞክሩ በፀጥታ ስራ ላይ በተሠማሩ አካላት በቁጥጥር ስር ሊውሉ ችለዋል። ፖሊስም በሁለቱ ተከሣሾች ላይ አስፈላጊውን ማስረጃ በማሠባሰብ አጠናክሮ የምርመራ መዝገቡን ለአቃቤ ሕግ የላከ ሲሆን አቃቤ ሕግም ከፖሊስ የተላከውን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ በጦር መሣርያ በመታገዝ የእገታ ተግባር መፈፀምን ጠቅሶ ክስ የመሠረተ ሲሆን ክሱን ሲከታተል የቆየው የወረጃርሶ ወረዳ ፍርድ ቤት ሕዳር 24 ቀን 2018ዓም በዋለው ችሎት አንደኛ ተከሣሽ ደሬሣ ተሾመ ስምንት አመት ከአራት ወር  እስራት ሁለተኛ ተከሳሽ ጀማል ደምሴ በስድስት አመት ከስድስት ወራት እስራት እንዲቀጡ የወሠነ መሆኑን የአቃቤ ሕግ ፅህፈት ቤት መግለጫ አመላክቷል። Via :- ዳጉ_ጆርናል @Yenetube @Fikerassefa
Mostrar todo...
29👎 5👍 3🔥 2
Photo unavailableShow in Telegram
“የኢትዮጵያን ጠላቶች እንደ ፀጉር ቅማል አንድ በአንድ እናራግፋለን” - ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ “የኢትዮጵያን ጠላቶች እንደ ፀጉር ቅማል አንድ በአንድ እናራግፋለን” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት 20ኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ክብረ በዓል በዛሬው ዕለት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ ሲከበር ባደረጉት ንግግር ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በዚሁ ወቅት “የሀገርን መሻት እና የባዳን ክፋት መለየት ይጠበቅብናል” ያሉ ሲሆን “ባዳ በክፋት የእኛን መሻት ለማጨለም ሲነሳ፤ ኢትዮጵያውያን ለባዳ ፍላጎት መሳሪያ እንዳንሆን” ሲሉ አሳስበዋል። “እርስ በርስ መተሳሰር ሲገባን፣ ክፉ እሳቤ ያለውን የባዳን መሻት በውስጣችን እንዳናስገባ እና በታሪክ ተወቃሽ እንዳንሆን፤ ኢትዮጵያውያን ልብ ገዝተን ሰላማችንን እናጽና” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አክለውም “በንግግር እንመን። በተሰማራንበት የስራ መስክ ሁሉ በትጋት እንስራ፣ ሌብነትን እንጠየፍ። የሀገር ጥቅም እና የህዝቦቻችን ክብር እናስቀድም። ለዘመናዊነት፣ ለለውጥ ክፍት እንሁን። ሉዓላዊነታችንም በሁሉም መስክ እናሳካ” ብለዋል። “ኢትዮጵያ በብዙ ተስፋ የተሞላች ሀገር መሆኗን” ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አያይዘውም “ብዙ አስደናቂ ጅምሮች እና ውጤት እያሳየች፣ እየተመነደገች፣ እያንሰራራች ያለች ሀገር ናት” ሲሉ ገልፀዋል። “ይህ መልካም ጅምሮ በፈጣሪያችን የሚደገፍ ቢሆንም፣ በሰይጣን ትጋት ቀን ከሌት ለማደናቀፍ ሙከራዎች ይደረጋሉ” ሲሉ ገልፀው ሆኖም “ማንኛውም ፈተና፣ ማንኛውም ትንኮሳ፣ ማንኛውም የክፉ ሀሳብ ኢትዮጵያን ከብልጽግና ማቆም አይችልም” ሲሉ አፅንኦት ሰጥተዋል። Via AS @YeneTube @FikerAssefa
Mostrar todo...
😁 45 43👎 14🔥 2😭 2
Photo unavailableShow in Telegram
ናይጄሪያ እሁድ እለት የተካሄደውን የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተከትሎ በቤኒን ወታደራዊ ዘመቻ ማካሄዷን አረጋገጠች የሀገሪቱ ወታደራዊ ኃይሎች "ከቤኒን መንግሥት በቀረበላቸው ሁለት የተለያዩ ጥያቄዎች" መሰረት እና በኢኮዋስ ፕሮቶኮል ስር እርምጃ መውሰዳቸውን የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት አስታውቋል። ተዋጊ ጄቶች የቤኒንን የአየር ክልል አልፈው እንደገቡ እና የምድር ጦርም በየብስ መሠማራቱ ተገልጿል። ፕሬዝዳንት ቲኑቡ የናይጄሪያ የጦር ኃይሎች በፍጥነት ምላሽ በመስጠታቸው እና በሙያዊ ብቃታቸው አድናቆት ችረዋል።
"የናይጄሪያ የጦር ኃይሎች በመንግሥት ግብዣ የቤኒን ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓትን ለመከላከል እና ለመጠበቅ በጀግንነት ቆመዋል" ሲሉ ተናግረዋል።
እሁድ ምሽት የቤኒን ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ታሎን ሁኔታው "ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ውሏል" ብለዋል። @Yenetube @Fikerassefa
Mostrar todo...
22👀 2
Photo unavailableShow in Telegram
ባሉበት ፎቶ አንስተው በመላክ ያገለገለ እቃዎትን ይሽጡ - መግዛትም ይቻላል ✅ ልብ ይበሉ ሁላችንም ቤት አንድ የማንፈልገውና የማንጠቀምበት ያገለገለ እቃ አለ በተቃራኒው ደግሞ ያንን እቃ የሚፈልጉ ግን የት እንደሚገኝ የማያውቁ ሰዎች አሉ። አላማችን እርሶ የማይጠቀሙበትን ያገለገለ እቃ በቀላሉ ካሉበት ሆነው ፖስት በማስደረግ እንዲሸጡ ማስቻል ሲሆን ያገለገለ እቃ መግዛት ሲፈልጉ ደግሞ በቀጥታ ከእቃው ባለቤት በጥሩ ዋጋ እንዲገዙ ማስቻል ነው። ስለሆነም እርሶም ቤት አገልግሎት ሳይሰጥ ቦታ ይዞ የተቀመጠ ያገለገለ እቃ ካሎት ፎቶ አንስተው ይላኩልን ወይም በሌሎች ሰወች ፖስት የተደረጉ ያገለገሉ እቃዎችን ፎቶ ፣ አድራሻ ፣ ዋጋ እና የእቃውን ባለቤት ስልክ ቁጥር በ ET Creatives በቀላሉ ያገኛሉ ✅ JOIN 👉 https://t.me/ET_Creatives_Family ET Creatives
Mostrar todo...
18👍 4
Photo unavailableShow in Telegram
ለውጭ ገበያ ከቀረበው የኤሌክትሪክ ሀይል ከ46 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ‼️ ባለፉት አራት ወራት ለውጭ ገበያ ከቀረበው የኤሌክትሪክ ሀይል ከ46 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ሞገስ መኮንን እንደገለጹት ተቋሙ በሀገር ውስጥ ላሉ ከፍተኛ ኃይል የሚጠቀሙ ኢንዱስትሪዎች፣ ለኢትዮ-ጅቡቲ የምድር ባቡር እና በማይኒንግ ዘርፍ ተሰማርተው ክፍያን በዶላር ለሚፈፅሙ አካላት እያቀረበ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ለውጭ ኤሌክትሪክ ሃይል ፈላጊ ሀገራት የሚያቀርብ ሲሆን በዋነኝነት ኬንያ፣ ጂቡቲ እና ታንዛንያ እንደሚገኙበት ተናግረዋል። እንደ ኢዜአ ዘገባ በ2018 በጀት አመት ባለፉት አራት ወራት ለኬንያ፣ ጁቡቲ እና ታንዛንያ በሽያጭ ከቀረበ የኤሌክትሪክ ኃይል 46 ነጥብ 8 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ መገኘቱን ገልጸዋል፡፡ @Yenetube @Fikerassefa
Mostrar todo...
27😭 11👀 2👎 1🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
ይሸጣል ብሎ መለጠፍ ድሮ ቀረ ያገለገለ እቃዎትን ባሉበት ፎቶ በማንሳት ይሽጡ - መግዛትም ይቻላል ✅ ልብ ይበሉ ሁላችንም ቤት አንድ የማንፈልገውና የማንጠቀምበት ያገለገለ እቃ አለ በተቃራኒው ደግሞ ያንን እቃ የሚፈልጉ ግን የት እንደሚገኝ የማያውቁ ሰዎች አሉ። አላማችን እርሶ የማይጠቀሙበትን ያገለገለ እቃ በቀላሉ ካሉበት ሆነው ፖስት በማስደረግ እንዲሸጡ ማስቻል ሲሆን ያገለገለ እቃ መግዛት ሲፈልጉ ደግሞ በቀጥታ ከእቃው ባለቤት በጥሩ ዋጋ እንዲገዙ ማገዝ ነው። ስለሆነም እርሶም ቤት አገልግሎት ሳይሰጥ ቦታ ይዞ የተቀመጠ ያገለገለ እቃ ካሎት ፎቶ አንስተው ይላኩልን ወይም በሌሎች ሰወች ፖስት የተደረጉ ያገለገሉ እቃዎችን ፎቶ ፣ አድራሻ ፣ ዋጋ እና የእቃውን ባለቤት ስልክ ቁጥር በ ET Creatives በቀላሉ ያገኛሉ ✅ JOIN 👉 https://t.me/ET_Creatives_Family ET Creatives
Mostrar todo...
14👍 4😁 1
ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ዳግም ወደ እርስ በርስ መወነጃጀል እና የጦርነት ቅስቀሳ ክስ ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ፣ የኤርትራ ነዋሪዎች ከፍተኛ ስጋት ውስጥ መውደቃቸውን ኤኤፍፒ (AFP) ዘገበ። በአስመራ ነዋሪ የሆነውና ከዚህ ቀደም በነበሩት የድንበር ግጭቶች እንዲሁም በትግራይ ጦርነት የተሳተፈው "ተወልደ" (ለደህንነቱ ሲባል ስሙ የተቀየረ)፣ ሌላ ጦርነት እንዳይነሳ እየጸለየ መሆኑን ተናግሯል። "ጦርነት ከተጀመረ ብዙ ልጆች አባት አልባ ይሆናሉ፤ እናቶች ባሎቻቸውን፣ ወላጆችም ልጆቻቸውን ያጣሉ" ሲል ስጋቱን ገልጿል። የጋለ ውጥረትና የጦርነት ዝግጅት ክስ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ባለፉት ዓመታት በትግራይ ኃይሎች ላይ በጋራ ሲዋጉ የቆዩ ቢሆንም፣ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ ግንኙነታቸው መሻከሩ ይታወሳል። ኤርትራ፣ "ኢትዮጵያ የአሰብን ወደብ ለመውሰድ እያቀደች ነው" የሚል ክስ ስታቀርብ፤ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ቲሞቲዎስ በበኩላቸው "የኤርትራ ትንኮሳ እና ጠብ አጫሪነት የኢትዮጵያን ትዕግስት እየፈተነ ነው" ሲሉ በቅርቡ መናገራቸው ይታወሳል። ኢትዮጵያ ኤርትራን "ለግጭት በንቃት እየተዘጋጀች ነው" ስትልም ከሳለች። የወጣቶች ሽሽትና የግዳጅ ክትባት በትግራይ ጦርነት ተሳትፎ የነበረውና "መሀሪ" የተባለ ኤርትራዊ የቀድሞ ወታደር፣ "ወጣቶች ሊመጣ ያለውን ጦርነት በመፍራት ወደ ኢትዮጵያ እና ሱዳን በብዛት እየሸሹ ነው" ብሏል። በስደት የምትኖረው "ሉዋን" የተባለች ኤርትራዊትም ቤተሰቦቿ በፍርሃት ውስጥ መሆናቸውን ጠቁማለች። እንደ እሷ ገለጻ፣ እናቶች ለስብሰባ እየተጠሩ "ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በእናንተ ላይ ጦርነት ሊከፍት ስለሆነ ልጆቻችሁን አዘጋጁ" እየተባሉ ነው። አንዳንዶቹ እናቶች በትግራይ ጦርነት የጠፉ ልጆቻቸው የት እንደገቡ እንኳን ሳያውቁ፣ ቀሪ ልጆቻቸውን ለጦርነት እንዲልኩ እየተጠየቁ መሆኑን ተናግራለች። የኤርትራ መንግስት ቃል አቀባይ የማነ ገብረመስቀል ለጉዳዩ ምላሽ እንዲሰጡ ቢጠየቁም ፈቃደኛ አልሆኑም። ነዋሪዎች ግን አሁን ያለውን ሁኔታ "ተአምር ብቻ ነው የሚያቆመው" ሲሉ ተስፋ መቁረጣቸውን ዘገባው አመልክቷል። @Yenetube @Fikerassefa
Mostrar todo...
45😭 7
የትግራይ ክልል የንግዱ ማኅበረሰብ በክልሉ ባለው ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጫና ምክንያት የገቢ ግብር አፈጻጸም እንዲታገድ የፌዴራል መንግሥትን ጠየቀ የትግራይ ክልል የንግዱ ማኅበረሰብ የገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1395/2017 በክልሉ ያለውን ወቅታዊ የኢኮኖሚ እውነታ የማያንጸባርቅ ነው በማለት ወዲያውኑ እንዲታገድ ጠይቋል። የትግራይ ንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት እንዲሁም የትግራይ የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ሐሙስ ዕለት በመቀሌ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ አዋጁ ከጦርነት በኋላ በክልሉ ያሉ ነጋዴዎች እና ድርጅቶች ከሚገጥሟቸው የኢኮኖሚ ሁኔታዎች ጋር የሚጣጣም አይደለም ብለዋል። የትግራይ ንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት የቦርድ አባል የሆኑት አቶ ቶማስ ዋሲሁን እና ምክትል ፕሬዚዳንቱ ጸጋይ ሃድጉ፣ ማሻሻያው የንግድ ድርጅቶች በጦርነቱ ወቅት ያጋጠማቸውን ከፍተኛ ኪሳራ፣ የብድር ወለድ መጠን በእጅጉ መጨመርን እና ከፌዴራል በኩል እነዚህን ችግሮች ለመፍታት የሚረዱ ተጨባጭ እርምጃዎች አለመኖራቸውን ከግምት ውስጥ ሳይገባ መጽደቁንና ወደ ተግባር መግባቱን ተናግረዋል። @Yenetube @Fikerassefa
Mostrar todo...
13👍 1😁 1
00:14
Video unavailableShow in Telegram
🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉 እስከ 30% በተሻለ ዋጋ የተሻለ ጉዞ በYango ይጓዙ
Mostrar todo...
IMG_0425.MOV1.10 MB
😁 2 1👎 1
ለም ሆቴል አካባቢ ተደራራቢ አውቶቡስ የቀላል ባቡር የኤሌክትሪክ ገመድ በመበጠሱ አገልግሎት አቆመ! በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት መስመር ላይ የሚገኘው ከሃያት ወደ ጦር ኃይሎች የሚወስደው መስመር አገልግሎት መገናኛ አካባቢ ለም ሆቴል መሻገሪያ ላይ በተፈጠረ ብልሽት ምክንያት መቋረጡ ታውቋል። ብልሹቱ የተከሰተው ለም ሆቴል አቅራቢያ በቅርቡ ለመተላለፊያነት በተሰራ መንገድ ላይ ሲሆን፣ በተለይም ተደራራቢ የአንበሳ አውቶቡስ መንገዱን ሲያቋርጥ የቀላል ባቡሩን ማስተላለፊያ የኤሌክትሪክ ገመድ በመበጠሱ አደጋው እንደደረሰ ተገልጿል። በዚህ አደጋ ምክንያት የባቡር አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ በመቋረጡ፣ በወቅቱ በመስመሩ ላይ የነበረው ባቡርም ተሳፋሪዎችን ለማውረድ መገደዱን ካፒታል ተመልክቷል። መረጃዎች እንደሚያሳዩት ይህን መሰል የባቡር መሠረተ ልማት ብልሽት (የኤሌክትሪክ ገመድ መበጠስ) ከዚህ በፊት አጋጥሞ አያውቅም። የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት የኤሌክትሪክ ገመዱን በአስቸኳይ ለመጠገን ጥረት እያደረገ ነው። የሃያት-ጦር ኃይሎች መስመር ተጠቃሚዎችም አገልግሎቱ ወደ መደበኛ ሥራው እስኪመለስ ድረስ የትራንስፖርት አማራጮችን እንዲጠቀሙ ተጠይቀዋል። ባለሥልጣናት በአሁኑ ወቅት የደረሰውን ጉዳት መጠን በመገምገም ላይ ሲሆኑ፣ አገልግሎቱ በፍጥነት ወደ መደበኛ ሥራው እንዲመለስ የሚያስችላቸውን ጥረት እያደረጉ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። Via Capital @YeneTube @FikerAssefa
Mostrar todo...
37👀 5😭 3😁 2👍 1
Repost from YeneTube
Photo unavailableShow in Telegram
ባሉበት ፎቶ አንስተው በመላክ ያገለገለ እቃዎትን ይሽጡ - መግዛትም ይቻላል ✅ ልብ ይበሉ ሁላችንም ቤት አንድ የማንፈልገውና የማንጠቀምበት ያገለገለ እቃ አለ በተቃራኒው ደግሞ ያንን እቃ የሚፈልጉ ግን የት እንደሚገኝ የማያውቁ ሰዎች አሉ። አላማችን እርሶ የማይጠቀሙበትን ያገለገለ እቃ በቀላሉ ካሉበት ሆነው ፖስት በማስደረግ እንዲሸጡ ማስቻል ሲሆን ያገለገለ እቃ መግዛት ሲፈልጉ ደግሞ በቀጥታ ከእቃው ባለቤት በጥሩ ዋጋ እንዲገዙ ማስቻል ነው። ስለሆነም እርሶም ቤት አገልግሎት ሳይሰጥ ቦታ ይዞ የተቀመጠ ያገለገለ እቃ ካሎት ፎቶ አንስተው ይላኩልን ወይም በሌሎች ሰወች ፖስት የተደረጉ ያገለገሉ እቃዎችን ፎቶ ፣ አድራሻ ፣ ዋጋ እና የእቃውን ባለቤት ስልክ ቁጥር በ ET Creatives በቀላሉ ያገኛሉ ✅ JOIN 👉 https://t.me/ET_Creatives_Family ET Creatives
Mostrar todo...
2

በሀዲድ ገበያ የደረሰው የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ውሏል ዛሬ ህዳር 26 ቀን 2018 ዓ.ም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 9:45 ሰአት ላይ ሀዲድ ገበያ  እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በንግድን መኖሪያ ቤቶች ላይ  ተከስቶ የነበረዉ የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ውሏል። የእሳት አደጋው የተከሰበት ቦታ ለአደጋ መቆጣጠር ስራ ምቹ ያልሆነ ፣ ቤቶቹ የተገነቡበት ግብዓቶች ፈጣን ተቀጣጣይ ከሆኑ ከቆርቆሮና ከእንጨት የተገነቡ በመሆኑ እሳቱ ተስፋፍቶ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ በፍጥነት  መቆጣጠር ተችሏል። የእሳት  አደጋው መንስኤ በፖሊስ እየተጣራ ሲሆን  አደጋው በሠው ላይ ያስከተለው ጉዳት የለም ። አሁን ያለንበት ሞቃታማና ነፈሻማ የአየር ንብረት ለእሳት መከሰትና መባባስ አስተዋጾኦ የሚያደርግ በመሆኑ ህብረተሰቡ እሳትና የኤሌክትሪክ ኃይል ምንጮችን ሲጠቀም ከወትሮው የተለየ ጥንቃቄ እንዲያደርግ የእሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ማሳሰቡን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል። @Yenetube @Fikerassefa
Mostrar todo...
34😭 6😁 1
Photo unavailableShow in Telegram
የቀድሞው የሠላም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደአ ጥፋተኛ በተባሉበት ክስ የ7 ዓመት ከ2 ወር እስር ተፈረደባቸው። አቶ ታዬ ዛሬ አርብ ኅዳር 26/2018 ዓ.ም. የቅጣት ውሳኔ የተላለፈባቸው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሕገ መንግሥት እና በሕገ መንግሥት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ችሎት ጥፋተኛ በተባሉበት ሕገወጥ የጦር መሣሪያ ይዞ በመገኘት ነው። የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣን እና የክልል ምክር ቤት አባል የነበሩት አቶ ታዬ ሕገ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ይዞ በመገኘት እንዲሁም ፍቃድ ሳይኖራቸው በቤታቸው ውስጥ አንድ ታጣፊ ክላሽንኮቭ ጠመንጃ ከ60 ጥይቶች ጋር ተገኝቷል በሚል ክስ ቀርቦባቸው ነበር። @YeneTube @FikerAssefa
Mostrar todo...
👎 57 21😭 3🔥 2
Photo unavailableShow in Telegram
ሰኔ ላይ የሚጀመረው የ2026 ፊፋ ዓለም ዋንጫ ዕጣ ማውጣት ስነስርአት ዛሬ በአሜሪካ ይካሄዳል እጣ ማውጣት ፕሮግራሙ ዛሬ 11 ሰአት የሚካሄድ ይሆናል። 48 ብሔራዊ ቡድኖች እጣ ውስጥ የሚገቡ ሲሆን ፕሮግራሙ የሚካሄደው በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው በኬኔዲ የኪነ ጥበባት ማዕከል ነው።
Mostrar todo...
16
Photo unavailableShow in Telegram
የኤርትራ መንግሥት ያለፍርድ ለ18 ዓመታት አስሯቸው የነበሩ 13 ሰዎችን ለቀቀ! የኤርትራ መንግሥት በወታደራዊ እስር ቤት ያለ ፍርድ ለ18 ዓመታት ያህል አስሯቸው የነበሩ 13 ሰዎችን መልቀቁን ቤተሰቦቻቸው ለቢቢሲ ትግርኛ ተናገሩ።አስራ ሦስቱ ግለሰቦች ታስረው የነበረው በአስቸጋሪ አነወኗር ማይ ስርዋ ተብሎ በሚጠራ ጥብቅ ቁጥጥር በሚደረግበት ወታደራዊ እስር ቤት ነው። ከእስር የተለቀቁት ሰዎች ነጋዴዎች፣ የፖሊስ አባላት እንዲሁም በተለያየ የሙያ ዘርፎች ላይ ተሰማርተው የነበሩ ባለሙያዎች ሲሆኑ፣ ያለ ምንም ማብራሪያ ሐሙስ ኅዳር 25/2018 ዓ.ም. ተለቀው ከቤተሰባቸው ጋር ተቀላቅለዋል።በማይ ስርዋ ወታደራዊ እስር ቤት ታስረው የነበሩ እና ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ አንድ ግለሰብ ለቢቢሲ ትግርኛ እንደተናገሩት ጥቅምት 2000 ዓ.ም. ላይ በወቅቱ የአገር ውስጥ ደኅንነት ኃላፊ ከነበሩት ከኮሎኔል ስምኦን ገብረድንግል መገደል ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ገልፀዋል።አክለውም የተያዙት ከሁለት ነጋዴዎች ጋር በተያያዘ መሆኑን አብራርተዋል። መጀመሪያ ላይ 30 የሚሆኑ ሰዎች በቁጥጥር ሥር ውለው የነበረ ሲሆን፣ የተወሰኑት ከዓመታት እስር በኋላ ተለቅቀው 20ዎቹ ብቻ በአስቸጋሪው እስር ቤት ውስጥ ቆይተዋል።ከተለቀቁት መካከል የቀድሞው የኦሊምፒክ ብስክሌተኛ እና ነጋዴ ዘርአግብር ገብረሕይወት፣ በንግድ ሥራቸው ታዋቂ የሆኑት ተስፋለም መንግሥተአብ እና በኩረ መብርሃቱ እንዲሁም ኢንጂነር ዳዊት ኃብተማሪያም እና ማቲዮስ ኃብተማሪያም የተባሉ ሁለት ወንድማማቾች ይገኙበታል። Via BBC @YeneTube @FikerAssefa
Mostrar todo...
30😭 4
Photo unavailableShow in Telegram
ባሉበት ፎቶ አንስተው በመላክ ያገለገለ እቃዎትን ይሽጡ - መግዛትም ይቻላል ✅ ልብ ይበሉ ሁላችንም ቤት አንድ የማንፈልገውና የማንጠቀምበት ያገለገለ እቃ አለ በተቃራኒው ደግሞ ያንን እቃ የሚፈልጉ ግን የት እንደሚገኝ የማያውቁ ሰዎች አሉ። አላማችን እርሶ የማይጠቀሙበትን ያገለገለ እቃ በቀላሉ ካሉበት ሆነው ፖስት በማስደረግ እንዲሸጡ ማስቻል ሲሆን ያገለገለ እቃ መግዛት ሲፈልጉ ደግሞ በቀጥታ ከእቃው ባለቤት በጥሩ ዋጋ እንዲገዙ ማስቻል ነው። ስለሆነም እርሶም ቤት አገልግሎት ሳይሰጥ ቦታ ይዞ የተቀመጠ ያገለገለ እቃ ካሎት ፎቶ አንስተው ይላኩልን ወይም በሌሎች ሰወች ፖስት የተደረጉ ያገለገሉ እቃዎችን ፎቶ ፣ አድራሻ ፣ ዋጋ እና የእቃውን ባለቤት ስልክ ቁጥር በ ET Creatives በቀላሉ ያገኛሉ ✅ JOIN 👉 https://t.me/ET_Creatives_Family ET Creatives
Mostrar todo...
13
Photo unavailableShow in Telegram
የኤርትራ መንግሥት ያለፍርድ ለ18 ዓመታት አስሯቸው የነበሩ 13 ሰዎችን ለቀቀ! የኤርትራ መንግሥት በወታደራዊ እስር ቤት ያለ ፍርድ ለ18 ዓመታት ያህል አስሯቸው የነበሩ 13 ሰዎችን መልቀቁን ቤተሰቦቻቸው ለቢቢሲ ትግርኛ ተናገሩ።አስራ ሦስቱ ግለሰቦች ታስረው የነበረው በአስቸጋሪ አነወኗር ማይ ስርዋ ተብሎ በሚጠራ ጥብቅ ቁጥጥር በሚደረግበት ወታደራዊ እስር ቤት ነው። ከእስር የተለቀቁት ሰዎች ነጋዴዎች፣ የፖሊስ አባላት እንዲሁም በተለያየ የሙያ ዘርፎች ላይ ተሰማርተው የነበሩ ባለሙያዎች ሲሆኑ፣ ያለ ምንም ማብራሪያ ሐሙስ ኅዳር 25/2018 ዓ.ም. ተለቀው ከቤተሰባቸው ጋር ተቀላቅለዋል።በማይ ስርዋ ወታደራዊ እስር ቤት ታስረው የነበሩ እና ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ አንድ ግለሰብ ለቢቢሲ ትግርኛ እንደተናገሩት ጥቅምት 2000 ዓ.ም. ላይ በወቅቱ የአገር ውስጥ ደኅንነት ኃላፊ ከነበሩት ከኮሎኔል ስምኦን ገብረድንግል መገደል ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ገልፀዋል።አክለውም የተያዙት ከሁለት ነጋዴዎች ጋር በተያያዘ መሆኑን አብራርተዋል። መጀመሪያ ላይ 30 የሚሆኑ ሰዎች በቁጥጥር ሥር ውለው የነበረ ሲሆን፣ የተወሰኑት ከዓመታት እስር በኋላ ተለቅቀው 20ዎቹ ብቻ በአስቸጋሪው እስር ቤት ውስጥ ቆይተዋል።ከተለቀቁት መካከል የቀድሞው የኦሊምፒክ ብስክሌተኛ እና ነጋዴ ዘርአግብር ገብረሕይወት፣ በንግድ ሥራቸው ታዋቂ የሆኑት ተስፋለም መንግሥተአብ እና በኩረ መብርሃቱ እንዲሁም ኢንጂነር ዳዊት ኃብተማሪያም እና ማቲዮስ ኃብተማሪያም የተባሉ ሁለት ወንድማማቾች ይገኙበታል። Via BBC @YeneTube @FikerAssefa
Mostrar todo...
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለሰባተኛው ሃገራዊ ምርጫ የእጩዎች የድጋፍ ፊርማ ግዴታ የሚያነሳዉን ማሻሻያ አፀደቀ፣ ሁለት አለም አቀፍ የብድር ስምምነቶችም ጸድቀዋል! የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለሰባተኛው አገራዊ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች የእጩ ተወዳዳሪዎች የድጋፍ ፊርማ የማሰባሰብ ግዴታን በአንድ ድምፅ የሚያስቀር ማሻሻያ አፀደቀ። በስድስተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሦስተኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ በህዳር 25 ቀን 2018 ዓ.ም. በአዋጅ ቁጥር 1397/2018 የጸደቀው ይህ አዋጅ ፣ ቀደም ሲል የጸደቀውን አዋጅ ቁጥር 1162/2014 አንቀጽ 32(2) እና አዲስ የተጨመረውን ንዑስ አንቀጽ 8 ከሥራ ውጪ ያደርጋል። የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ፣ የድጋፍ ፊርማው ግዴታ ከዚህ ቀደም ለስድስተኛው ሃገራዊ ምርጫ በአዋጅ ቁጥር 1235/2014 መሠረት በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ገደቦች ምክንያት መነሳቱን አውስተዋል። ፓርቲዎች በኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አማካኝነት፣ ጊዜው ውስን መሆኑና ቀጣይነት ያለው የምርጫ ዝግጅት የፊርማ አሰባሰቡን አዳጋች እንዳደረገው በተደጋጋሚ ቅሬታቸውን ሲገልጹ መቆየታቸውን አስረድተዋል። አፈ-ጉባዔው አክለውም “የድጋፍ ፊርማ ሕጉን አሁን ማስፈጸም ፓርቲዎች በምርጫው ተወዳድረው የመሳተፍ ብቃታቸው ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ስለሚፈጥር ይህንን ማስቀረት የግድ አስፈላጊ ነው”ብለዋል። @YeneTube @FikerAssefa
Mostrar todo...
18😁 3🔥 1