352 749
Suscriptores
-9324 horas
+37 días
+1 19630 días
Archivo de publicaciones
Photo unavailableShow in Telegram
#WerabeUniversity
በ2018 ዓ.ም በመደበኛ እና በተከታታይ መርሐግብር የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርት በወራቤ ዩኒቨርሲቲ ለመማር የማመልከቻ ቀናት እስከ ህዳር 04/2018 ዓ.ም ድረስ መራዘሙን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡
በቂ አመልካቾች ባመለከቱበት የትምህርት መስኮች የቅበላ መስፈርቱን ለምታሟሉ አመልካቾች ህዳር 05/2018 ዓ.ም በውስጥ ማስታወቂያ ይገለጻል ተብሏል፡፡
በቂ አመልካቾች ባመለከቱበት የትምህርት መስኮች የቅበላ መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ለ1ኛ ዓመት 1ኛ ሴሚስቴር የምዝገባ ቀናት ህዳር 09 እና 10/2018 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል፡፡
@tikvahuniversity
❤ 115👏 6😱 5👍 3🙏 1
Photo unavailableShow in Telegram
#ጥቆማ
ዲላ ዩኒቨርሲቲ 13ኛ ሀገር ዐቀፍ የትምህርት ምርምር ኮንፍረንሱን ታህሳስ 20 እና 21/2018 ዓ.ም ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ይገኛል።
ጉባኤው “Revitalizing Applied Education: Igniting Innovation, Empowering Future” በሚል ጭብጥ ላይ ይመክራል፡፡
ፍላጎት ያላቸው ተመራማሪዎች ለጉባኤው የሚሆኑ ሙሉ ፅሁፎችን፣ የጉባኤው አጠቃላይ ጭብጥ በሆነው 'Quality Education' እንዲሁም በምስሉ ላይ በተገለፁት አስር ንዑሳን ጭብጦች ላይ ማገባት እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡
ሙሉ ፅሁፎችን ማስገቢያ ጊዜ የሚያበቃው፦ ህዳር 16/2018 ዓ.ም
የተመረጡ ፅሁፎች ከህዳር 22/2018 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 01/2018 ዓ.ም የሚገለፁ ሲሆን፤ ጉባኤው ታህሳስ 20 እና 21/2018 ዓ.ም ይካሔዳል፡፡
ለበለጠ መረጃ፦
መላኩ አደላ (ዶ/ር) ➫ 0911639099
አዲሱ ሙሉ ➫ 0924703531
ሙሉ ፅሁፎችን መላኪያ አድራሻ ➫ 13thnerc@du.edu.et
@tikvahuniversity
❤ 52👎 9😢 2😱 1
የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጀር የሠሩት ወጣቶች 👏
ሰመረ ገ/ልዑል እና ሁለት ጓደኞቹ የኢንጂነሪንግ መምህራን ናቸው፡፡ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በሚያዘጋጀው የክህሎት ኢትዮጵያ ተሳትፈዋል፡፡
መምህራኖቹ በኢንስቲትዩቱ በመታገዝ ኤሌክትሪክ መኪኖችን ቻርጅ የሚያደርግና በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተመረተ ቴክኖሎጂ ፈጥረዋል፡፡
Ultra AC Wall Box EV Charger የተሰኘው ፈጠራው፤ AC Power የሚጠቀም ሲሆን 22 ኪዋ የሚደርስ output አለው፡፡
ፈጠራው በተለይ በኢትዮጵያ እያደገ በመሔድ ላይ ያለውን የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጀር ፍላጎት ለማሟላት እንደሚያስችል መምህራኑ ተናግረዋል፡፡
በብዛት ወደማምረት አለመግባታቸውን የገለፁት ፈጣሪዎቹ፤ እስካሁን ባለው ሒደት የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የማቴርያል እና የገንዘብ አቅርቦት እንዳደረገላቸው ገልፀዋል፡፡
@tikvahuniversity
👍 54❤ 49👏 18😱 5
Photo unavailableShow in Telegram
ሰቨን ስታር ጤና ሳይንስ እና ቢዝነስ ኮሌጅ
የበርካታ ዓመታት የማስተማር ልምድ ባላቸው የዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሐኪሞች የተመሰረተ ኮሌጅ!
🔔 ለ2018 ዓ.ም ምዝገባ ጀምረናል!
በዲግሪ የጤና መርሐግብሮች
➫ ነርሲንግ ➫ ፐብሊክ ሄልዝ
➫ ፋርማሲ ➫ ሚድዋይፈሪ
➫ ሜዲካል ላብራቶሪ ሳይንስ
➫ ሜዲካል ራዲዮሎጂ ቴክኖሎጂ
በዲግሪ የቢዝነስ መርሐግብሮች (በቀን እና በማታ)
➫ አካውንቲንግና ፋይናንስ
➫ ማርኬቲንግ ማኔጅመንት
➫ ቢዝነስ ማኔጅመንት
➫ ሰው ሀብት አስተዳደር
በጤና በደረጃ-4 መርሐግብሮች
➫ በፋርማሲ ➫ በላብራቶሪ
➫ በነርሲንግ ➫ በሚድዋይፈሪ
➫ በሜዲካል ራዲዮግራፊ
በቢዝነስ በደረጃ-4 መርሐግብሮች
➫ በአካውንቲንግና ፋይናንስ
➫ በማርኬቲንግና ሴልስ ማኔጅመንት
በሪሚዲያል መርሐግብር
⏩ ፈጥነው ይመዝገቡ!
አድራሻ፡-
አዲስ አበባ፣ ፒያሳ አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን፣ ከባቡር ትኬት መቁረጫው ፊት ለፊት
☎️ 0982373737 / 0965686819
❤ 29🥰 1
Photo unavailableShow in Telegram
የጋዜጠኝነት ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን።
ስልጠናው
👉 መሠረታዊ የጋዜጠኝነት መርሆች፣ የሚዲያ አይነቶች እና የጋዜጠኝነት ዓይነቶች
👉 የዜና አሰራር እና የቃለመጠይቅ አደራረግ
👉 የመዝናኛ ፕሮግራም ጋዜጠኝነት፣ የፕሮግራም ዝግጅት፣ የማስታወቂያ አሰራር እና የዶክመንተሪ ዝግጅት
👉 የሞባይል ጋዜጠኝነት እና የ YouTube Journalism አካቷል፡፡
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute
TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
❤ 50👍 1
#ጥቆማ
#BoranaUniversity
ቦረና ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የሙያ መስኮች ብቃት ያላቸውን ባለሙያዎች አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።
➤ የሥራ መደብ፦ በተለያዩ የሙያ መስኮች
➤ ተፈላጊ ባለሙያዎች ብዛት፦ 48
➤ ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፦ ከመጀመሪያ ዲግሪ ጀምሮ
➤ የሥራ ልምድ፦ ዜሮ ዓመትና በላይ
➤ የሥራ ቦታ፦ ቦረና ዩኒቨርሲቲ
የማመልከቻ ጊዜው የሚያበቃው፦
ጥቅምት 28/2018 ዓ.ም
ቦረና ዩኒቨርሲቲ የሰው ሀብት አስተዳደርና ልማት ዳይሬክቶሬት ቢሮ በአካል በመገኘት ወይም አዲስ አበባ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ወኪል ቢሮ፣ አራት ኪሎ፣ የቀድሞው የጀርመን ባህል ኢንስቲትዩት ህንፃ ቢሮ ቁ. 15 የማመልከቻ ደብዳቤ፣ ሲቪ እና የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒውን ማስገባት ይጠበቅባችኋል፡፡
(የዩኒቨርሲቲው ማስታወቂያ ከላይ ተያይዟል፡፡)
@tikvahuniversity
❤ 147👍 16😱 4
#AddisAbabaUniversity
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያለፉት ሁለት ዓመታት የራስገዝነት ሪፎርም ትግበራውን ገምግሟል፡፡
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው ራስገዝ ዩኒቨርሲቲ ሆኖ በድጋሜ ከተቋቋመ በኋላ በተሠሩ የሪፎርም ሥራዎችና በመደበኛ ተግባራት አፈፃፀም እና በተመዘገቡ ውጤቶች ላይ ያተኮረ ውይይት አካሒዷል፡፡
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ራስገዝ መሆን ዋናው ግብ ተቋሙን የአካዳሚክ፣ የምርምር እና የአገልግሎት ልህቀት ማዕከል በማድረግ ለአገራዊ ፍላጎቶች ምላሽ የሚሰጥ ፍላግሺፕ የምርምር ዩኒቨርሲቲ መገንባት እንደሆነ በውይይት መድረኩ ተገልጿል፡፡
ባለፉት ሁለት ዓመታት በዩኒቨርሲቲው የተከናወኑ አበይት ተግባራት፦
➫ የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ (2024-2028) ተዘጋጅቷል፣
➫ አዲስ የሴኔት ህግ ፀድቋል፣
➫ በርካታ ፖሊሲዎች እና መመሪያዎች ወጥተዋል፣
➫ የአካዳሚክ ፕሮግራሞች ግምገማና መልሶ ማደራጀት ሥራ ተሰርቷል፣
➫ ዩኒቨርሲቲው በራሱ መስፈርት ተማሪዎችን መቀበል መጀመሩ፣
➫ አዲስ የዩኒቨርሲቲው መዋቅር ተጠንቶና በሥራ አመራር ፀድቆ ወደ ሥራ መግባቱ፣
➫ አዲስ በፀደቀው መዋቅር መሰረት የመካከለኛና መሰረታዊ አመራር ምደባ መከናወኑ፣
➫ ገቢ የማመንጫት አቅም እየተሻሻለ መምጣቱንና በ2017 በጀት ዓመት ከዩኒቨርሲቲው ጠቅላላ ወጪ 30 በመቶ ባመነጨው ገቢ መሸፈኑ ተነስቷል፡፡
በቀጣይ የሚከናወን የሰራተኞች መልሶ ድልድል ለመፈፀም በተዘጋጀ ማስፈፀሚያ ማዕቀፍ ላይ ሰፊ ውይይት ተካሒዷል፡፡
@tikvahuniversity
❤ 88👎 83👏 3😱 1😢 1
Photo unavailableShow in Telegram
የዳግማዊ ምኒልክ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የ2016 እና 2017 ዓ.ም ገቢ ነባር የድኅረ-ምረቃ ተማሪዎች የ2018 ዓ.ም አንደኛ ሴሚስተር ምዝገባ ከጥቅምት 27-30/2018 ዓ.ም እንደሚከናወን ኮሌጁ አሳውቋል፡፡
➫ የመደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ፦ ጥቅምት 27 እና 28/2018 ዓ.ም
➫ የእረፍት ቀናት ተማሪዎች ምዝገባ፦ ጥቅምት 29 እና 30/2018 ዓ.ም
የመመዝገቢያ እና የትምህርት ክፍያ በመክፈል የክፍያ ደረሰኝ ዋናውና አንድ ኮፒ እንዲሁም የምዝገባ ስሊፕ በመያዝ ሬጅስትራር ቢሮ በአካል በመገኘት እንድትመዘገቡ ኮሌጁ ገልጿል፡፡
@tikvahuniversity
❤ 25👍 3
Photo unavailableShow in Telegram
#ሎርካን_ሜዲካል_ኮሌጅ
የበርካታ ዓመታት ልምድ ባላቸው ሐኪሞችና ምሁራን ባለቤትነት የሚመራው ሎርካን ሜዲካል ኮሌጅ ምዝገባ ጀምሯል❗️
BSc Fields of Study:
→ Doctor of Medicine
→ Doctor of Dental Medicine
→ Bachelor of Dental Science
→ Nursing
TVET Programs:
→ Dental Therapy
→ Nursing
→ Medical Laboratory
→ Pharmacy
→ Radiography
የ CPD ማዕከል አገልግሎት
☎️ 0913398780 / 0911596059
አድራሻ፦
CMC አደባባይ ከፀሐይ ሪል እስቴት ጀርባ ከ ICMC ጠቅላላ ሆስፒታል አጠገብ
Addis Ababa, CMC square, Behind Tsehay Real Estate, next to ICMC General Hospital
Facebook: https://www.facebook.com/Lorcanmedicalcollege
❤ 24
Photo unavailableShow in Telegram
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የኅብረተሰብ ጤና ትምህርት ቤት በኅብረተሰብ ጤና ትምህርት የማስተርስ ፕሮግራም (MPH) የ2018 ዓ.ም አመልካቾች የመግቢያ ፈተና ቅዳሜ ጥቅምት 29/2018 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን ኮሌጁ አሳውቋል።
የእረፍት ቀናት መርሐግብር አመልካቾች ፈተና ጠዋት 4:00 እና የመደበኛ መርሐግብር አመልካቾች ፈተና ከሰዓት 8:00 እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡
ፈተናው የሚሰጥበት ቦታ፦
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ዲጂታል ላይብራሪ
(ለፈተናው የተመረጡ አመልካቾች ዝርዝር በተቋሙ የማኅበራዊ ሚዲያ ይመልከቱ፡፡)
@tikvahuniversity
❤ 40👍 10🙏 2👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
#ETA
ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በቅድመ-ምረቃ እና በድኅረ-ምረቃ መርሐግብር ተመዝጋቢዎችን ሲቀበሉ የመግቢያ መስፈርቶችን ማሟላታቸውን ሊያረጋግጡ እንደሚገባ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አሳስቧል፡፡
በዚህም አመልካቾች፦
➫ የትምህርት ሚኒስቴር ለትምህርት ዓመቱ ያስቀመጠውን የከፍተኛ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪ መግቢያ የመቁረጫ ነጥብ አሟልተው መገኘት አለባቸው፡፡
➫ ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋም የተመረቁ ባለሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም ለመመዝገብ በሰለጠኑበት የሙያ መስክ በደረጃ 4 ወይም በቀድሞ 10+3 ወይም 12+2 ዲፕሎማ ያጠናቀቁ ሆነው በሙያው ደረጃ 4 የብቃት ማረጋገጫ ምዘና (COC level 4) ተፈትነው ያለፉበትን ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
➫ ለሁለተኛ ዲግሪ ተመዝጋቢዎች በባለሥልጣኑ ህጋዊነቱ የተረጋገጠ የመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ማስረጃ ማቅረብ እንዲሁም የድኅረ-ምረቃ የመግቢያ ፈተና የማለፊያ ውጤት ያላቸው ሊሆኑ ይገባል፡፡
➫ ከውጭ ሀገር የተገኘ የትምህርት ማስረጃ ለመግቢያ መስፈርት የሚያገለግለው በባለሥልጣኑ የአቻ ግምት ሲሰራለት ብቻ ይሆናል፡፡
ከላይ ከተጠቀሱት መመሪያዎች ውጪ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው የሚማሩ በሙሉ ኃላፊነቱ የተመዝጋቢዎቹ እና የተቋማቱ ብቻ መሆኑን ባለሥልጣን መስሪያቤቱ አሳስቧል፡፡
@tikvahuniversity
❤ 19
ከአልጀሪያ መንግሥት የተገኘ ስኮላርሺፕ ተጠቃሚ የሆኑ ሁለት የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የደረጃ 6 (የመጀመሪያ ዲግሪ) ሰልጣኞች ሽኝት ተደርጎላቸዋል።
የስኮላርሺፕ ዕድሉ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቅርብ ክትትል ተገኘ ሲሆን፤ ተማሪ ታምራት እና ተማሪ ትህትና የዕድሉ ተጠቃሚ የሆኑ የኢንስቲትዩ ሰልጣኞች መሆናቸው ተገልጿል፡፡
@tikvahuniversity
❤ 34🥰 7👏 7👍 5😢 3
Photo unavailableShow in Telegram
ፓዩኒየር ኮሌጅ (ጀርመን አደባባይ ካምፓስ)
⭐️ የእውቅና ፈቃድ ያለው!
🔔 ምዝገባ ላይ ነን!
በዲግሪ ፕሮግራም
➢ በሜዲስን
➢ በዴንታል ሜዲስን
➢ በፋርማሲ
➢ በሜዲካል ላብራቶሪ ሳይንስ
በሪሚዲያል ፕሮግራም
➢ በተፈጥሮ ሳይንስ ፕሮግራሞች
በCPD እና ሌሎች አጫጭር ስልጠናዎች
አድራሻ፦
ከጀርመን አደባባይ ወደ ለቡ መብራት በሚወስደው መንገድ በግራ በኩል 550 ሜትር እንደተጓዙ ያገኙናል
ለበለጠ መረጃ፦ 0902443344 / 0902442244 / 0903222233
❤ 11
Photo unavailableShow in Telegram
መስራት ማህበር ለኢትዮጵያውያን ሥራ ፈጣሪዎች ተግባራዊ ድጋፍ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ ነው፡፡
✅ በንግድ፣ በፋይናንስ፣ በማርኬቲንግ፣ በኢንቨስትመንት፣ በገበያ ማፈላለግ እና በህግ ጉዳዮች ዙርያ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች የተዘጋጁ ፅሁፎችን ማጋራት
✅ የንግድ ሥራችሁን ለማስተዳደር የምትጠቀሙበት መመሪያዎችና ሃሳቦችን ማጋራት
✅ በናንተ የሥራ ፈጠራ መንገድ ቀድመው ካለፉና ብዙ ልምድ ማካፈል ከሚችሉ ጋር ሃሳብ የምትለዋወጡበት መድረክ
✅ በሥራችሁ ወደፊት ለመራመድ የሚያግዟችሁን የተለያዩ ሃሳቦች ማጋራት እንዲሁም ጠቃሚ ግንኙነቶችን የምትፈጥሩባቸው ኹነቶችን መጠቆም
የንግድ ሥራችሁን አሳድጉ 👇
https://mahber.mesirat.org/wp-login.php?loggedout=true&wp_lang=en_US
❤ 41
Photo unavailableShow in Telegram
#JigjigaUniversity
ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የ2018 ዓ.ም የድኅረ-ምረቃ ትምህርት አመልካቾች የምዝገባ ጊዜን እስከ ጥቅምት 26/2018 ዓ.ም አራዝሟል።
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
➫ የNGAT ማለፊያ ውጤት
➫ የመጀመሪያ ዲግሪ ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው
➫ አራት የቅርብ ጊዜ ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ
@tikvahuniversity
❤ 95👎 13👍 3😢 2
Photo unavailableShow in Telegram
#FellowshipOpportunity
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የህጻናት ትምህርት ክፍል አመልካቾችን በማወዳደር ለ2018 ዓ.ም Pediatric Pulmonary & Critical Care Fellowship ፕሮግራም አንድ ብቁ አመልካች መቀበል ይፈልጋል።
የቅበላ መስፈርቶች
➫ የNGAT ፈተና ውጤት ያለፈ/ያለፈች፣
➫ ከታወቀ የህክምና ትምህርት ቤት በህክምና ዲግሪ የተመረቀ/የተመረቀችና በህጻናት ህክምና ስፔሻሊቲ ያለው/ያላት፣
➫ በመንግሥት ተቋም የሁለት ዓመት የሥራ ልምድ ያለው/ያላት፣
➫ ከመንግሥት ተቋም የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ የሚያቀርብ/የምታቀርብ፣
➫ የህጻናት ህክምና ለመስጠት ፈቃድ ያለው/ያላት፣
➫ ጥሩ አዕምሯዊና አካላዊ ጤና ያላት/ያለው፣
የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው፦
ህዳር 06/2018 ዓ.ም
አመልካቾች ሊያሟሏቸው የሚገቡ፦
➫ የማመልከቻ ደብዳቤ
➫ የቅርብ ጊዜ CV
➫ የድጋፍ ደብዳቤ (ቢያንስ 2)
➫ የድኅረ ምረቃ ፈተና ውጤት
➫ የትምህርት ማስረጃዎች
➫ የፍላጎት መግለጫ ከ500 ቃላት ያልበለጠ
ማመልከቻዎን በኮሌጁ የህጻናት ትምህርት ክፍል በአካል ማስገባት ይችላሉ ወይም በኢሜይል አድራሻ pedinfo@sphmmc.edu.et መላክ ይችላሉ።
ለበለጠ መረጃ፦
ዶ/ር አባተ የሺድንበር 0911993975 ወይም abate.yeshidinber@sphmmc.edu.et
@tikvahuniversity
❤ 125👎 9👍 6👏 4🥰 1
የመቱ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ በድንገት ህይወቱ ላለፈው ተማሪ ታረቀኝ ታፈሰ ዎሬሳ የሻማ ማብራት ስነ-ስርዓት አካሒዷል።
ወጣት ታረቀኝ ታፈሰ በመቱ ዩኒቨርሲቲ የ2ኛ ዓመት የኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል ተማሪ ነበር።
በተማሪው ድንገተኛ ህልፈተ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን የገለፀው ዩኒቨርሲቲው፤ ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጆቹ እንዲሁም ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ መጽናናትን ተመኝቷል። ነፍስ ይማር! 😭
@tikvahuniversity
😢 152❤ 45🥰 4😱 4👍 2👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
Mesirat Mahber is a dedicated space for Ethiopian entrepreneurs who need more than just motivation:
Expert-built resources: In-depth PDFs on business development, finance, legal, investment, and marketing — all tailored to the local context
Practical toolkits to help you manage and scale your business
A supportive community of people
Events and resources designed to help you move forward strategically
Access these resources and grow your business
Join Now 👉 https://mahber.mesirat.org/wp-login.php?redirect_to=https%3A%2F%2Fmahber.mesirat.org%2F&bp-auth=1&action=bpnoaccess
❤ 35
Photo unavailableShow in Telegram
#SamaraUniversity
በ2018 ዓ.ም በሠመራ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ በሁለተኛ ዲግሪ በመደበኛ እና በኤክስቴንሽን መርሐግብር እንዲሁም በመጀመሪያ ዲግሪ በኤክስቴንሽን መርሐግብር ለመማር ያመለከታችሁ ምዝገባ ከጥቅምት 25-27/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
ቅዳሜ ጥቅምት 29/2018 ዓ.ም ትምህርት ይጀምራል ተብሏል።
(ተጨማሪ መረጃ ከምስሉ ላይ የመልከቱ።)
@tikvahuniversity
❤ 60👍 3😱 1
Photo unavailableShow in Telegram
#HawassaUniversity
በ2018 ዓ.ም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም ለመማር ተወዳድራችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች ምዝገባ ጥቅምት 24 እና 25/2018 ዓ.ም መሆኑን ኮሌጁ አሳውቋል፡፡
ለምዝገባ ሲሔዱ Official Transcript, የቅበላ ደብዳቤ፣ የGAT ውጤት፣ የAcceptance ደብዳቤ፣ ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ እና በምክትል ፕሬዝዳንት የተፈረመ የስፖንሰርሽፕ ደብዳቤ መያዝ ይኖርባችኋል፡፡
@tikvahuniversity
❤ 37👍 3

