Addis Ababa Education Bureau
Ir al canal en Telegram
ይህ ቻናል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቴሌግራም ቻናል ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የተከናወኑ እንዲሁም ሀገራዊ ፣ አህጉራዊ እና አለማቀፋዊ የትምህርት መረጃዎች ተደራሽ የሚደረጉበት ነው፡፡
Mostrar más2025 año en números

150 232
Suscriptores
Sin datos24 horas
+677 días
+34630 días
Archivo de publicaciones
ማስታወቂያ! Beeksisa!
(16/12/2017 ዓ.ም)
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 209👍 64👎 52🔥 14🥰 13😁 12👏 10
የሚዲያ ይዘት ማበልጸግና ስርጭት ዳይሬክቶሬት በኤፍ ኤም 94.7 አማካይነት ቢሮው የሚያከናውናቸውን ተግባራት ለህብረተሰቡ በአግባቡ ተደራሽ ማድረግ እንዲችል ሁሉም ስራ ክፍሎች ከዳይሬክቶሬቱ ጋር በቅንጅት መስራት የሚገባቸው መሆኑን የቢሮው አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ ገልጸው ስራ ክፍሉም ወቅታዊ መረጃዎች ለሕብረተሰቡ ተደራሽ ከማድረግ አንጻር ትኩረት አድርጎ መንቀሳቀስ እንደሚጠበቅበት አመላክተዋል።
በውይይቱ ማጠቃለያ የሪፎርም አገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፈንታሁን እያዩ በቢሮ የሚገኙ ስራ ክፍሎች በየአስራ አምስት ቀኑ ለአጠቃላይ ካውንስል አባላት ሪፖርት እንዲያቀርቡ የተዘጋጀ የግንኙነት መርሀግብር አቅርበዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 67👍 7
የቢሮው አጠቃላይ ካውንስል አባላት የሚዲያ ይዘት ማበልጸግና ስርጭት ዳይሬክቶሬትን የ15 ቀን እቅድ አፈጻጸም ገመገሙ።
(16/12/2017 ዓ.ም) በመርሀ ግብሩ የቢሮው የሚዲያ ይዘት ማበልጸግና ስርጭት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ የውብዳር አያሌው ስራ ክፍሉ በ2018ዓ.ም አንደኛ ሩብ አመት በነሐሴ ወር 15 ቀናት በቁልፍ አመላካች ተግባራት እና በሪፎርም ስራዎች የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት አቅርበው ውይይት ተካሂዷል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቢሮ ኃላፊ አማካሪ ወይዘሮ አበበች ነጋሽ የቢሮው አጠቃላይ ካውንስል አባላት የስራ ክፍሎችን የ15 ቀን እቅድ አፈጻጸም እየገመገሙ ቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ላይ መሆናቸውን አስታውሰው የሚዲያ ይዘት ማበልጸግና ስርጭት ዳይሬክቶሬት በነሐሴ ወር 15 ቀን ውስጥ በቁልፍ አመላካች ተግባራት እና በሪፎርም ስራዎች ያከናወናቸውን ተግባራት መሰረት አድርጎ ባቀረበው ሪፖርት መነሻ ከአጠቃላይ ካውንስል አባላቱ የተሰጡ አስተያየቶችን መሰረት በማድረግ በቀጣይ የተሻለ ስራ መስራት እንደሚጠበቅበት አስገንዝበዋል።
❤ 61👍 7🤗 1
ሀገር አቀፍ የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
(15/12/2017 ዓ.ም) በምክክር መድረኩ ላይ የ2017 ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም በመገምገምና በ2018 ዓ.ም እቅድ ላይ በመምከር የሀገራችንን የትምህርት ስራዎች በላቀ ትጋት ለማስቀጠል በጋራ መስራት በሚገቡን ጉዳዮች ላይ ከመግባባት ላይ የምንደርሰበት ይሆናል።
በሀዋሳ ከተማ በመካሄድ ላይ በሚገኘው በዚህ በመርሃ ግብሩ ላይ የትምህርት ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ፣ የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ ፣ የሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ም/ርዕሰ መስተዳድርና የትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በየነ በራሶ ፣ የከተማ አስተዳደርና የክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊዎችና ምክትል ቢሮ ሀላፊዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡
በምክክር መድረኩ ትምህርትን ለዜጎች በፍትሃዊነት ለማዳረስ የሚደረገውን ጥረት አጠናክሮ በማስቀጠል ረገድ ያሉ ጅምር ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ ፣ በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ የተጀመሩ ስራዎች መጎልበት እንዳለባቸው ፣ የአምስት አመት የልማት መርሃ ግብር እንዲሁም የስድስተኛው የትምህርት ልማት መርሃ ግብር የሚጠናቀቅበት ወቅት በመሆኑ በ2018 ዓ.ም እቅድን ስኬታማ ለማድረግ በትኩረት መስራት እንዳለበት እንዲሁም የተገኙ ስኬቶችን ይበልጥ ለማዳበር ፣ ያጋጠሙ ችግሮችና ተግዳሮቶችን በልምድ ልውውጥና በሌሎች ስልቶችን በመንደፍ ለመፍታት እንዲያግዝ ታስቦ የተዘጋጀ ነው።
ክቡር ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 94😁 14👍 6👎 1👏 1
Barattoonni Mana Barumsa Bultii Addaa Dubaraa Iteegee Mananiifi Barattoota dhiira Bultii Addaa Galaanitti barachuuf magaalaa Shaggar irraa Qormaata seensaa fudhattan bu’aa qorumsa keessanii toora qunnamsiiftuu(Link) armaan gadii tuquun ilaallachuu dandeessu.
http://bs.ministry.et
(15/12/2017 A.L.I) Mootummaan xiyyeeffannoo Damee Barnootaaf kenne bu’uureffachuun Manneen Barnootaa Bultii Addaa Lama (2) Bulchiinsa Magaalaa Finfinnee keessatti hundeeffamanii giddugala qaroominaa ta’anii tajaajilaa kan jiran yoo ta’u, Bara Barnootaa 2018ttis kutaa 7ffaafi kutaa 9ffaa Manneen Barnootaa lamaanitti magaalaa Shaggar irraa simannee barsiisuuf beeksisa bahe irratti hundaa’uun qormaata seensaa barattoonni fudhattan bu’aa keessan karaa Marsariitiin(online) toora kanaan akka ilaaltan isin beeksifna.
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 89👍 32👏 13👎 2
Photo unavailableShow in Telegram
በእቴጌ መነን የሴትና በገላን የወንድ ተማሪዎች አዳሪ ትምህርት ቤቶች ላይ ለመማር ከሸገር ሲቲ የመግቢያ ፈተና የወሰዳችሁ ተማሪዎች ውጤታችሁን ከዚህ በታች በተቀመጠው ሊንክ ላይ መመልከት ትችላላችሁ።
(15/12/2017 ዓ.ም) መንግስት ለትምህርት ዘርፍ በሰጠው ትኩረት መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሁለት አዳሪ ትምህርት ቤቶች ተቋቁመው የልህቀት ማዕከል በመሆን እያገለገሉ የሚገኙ ሲሆን በ2018 የትምህርት ዘመን የ7ኛ እና የ9ኛ ክፍል ተማሪዎችን በእቴጌ መነን የሴትና በገላን የወንድ ተማሪዎች አዳሪ ትምህርት ቤቶች ላይ ከሸገር ሲቲ ተቀብለን ለማስተማር በወጣው ማስታወቂያ መሰረት የመግቢያ ፈተና የወሰዳችሁ ተማሪዎች ውጤታችሁን በOnline አድራሻ
http://bs.ministry.et
ላይ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
❤ 55🥰 8👍 3🤔 1
Photo unavailableShow in Telegram
የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ምዝገባ ማስታወቂያ!
(15/12/2017 ዓ.ም) የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ምዝገባ ባለፉት ቀናት በኦንላይን ሲካሄድ መቆየቱ ይታወቃል ። ነገር ግን በተቀመጠው ጊዜ ገደብ ውስጥ የ8ኛ ክፍል ውጤት ያልደረሰላቸው በርካታ አካባቢዎች በመኖራቸው እንዲሁም በሌሎች ምክንያቶች ያልተመዘገቡ ተማሪዎች በመኖራቸው ምዝገባውን ለተወሰነ ጊዜ ማራዘም ማስፈለጉን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡
በመሆኑም እስካሁን ያልተመዘገባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ እስከ ነሃሴ 25/2017 ዓ.ም ድረስ የተራዘመ መሆኑን አውቃችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።
ማሳሰቢያ፦
ምዝገባው እስከ ነሃሴ 25/2017 ዓ.ም ድረስ የሚከናውን ሲሆን: -
የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በ2015 የትምህርት ዘመን ያልወሰዳችሁ ተማሪዎች የክፍል ውጤታችሁንና ካርዳችሁን፤
8ኛ ክፍል በተመለከተ የምታስገቡት ውጤት የሚኒስትሪ ውጤታችሁን ሲሆን የሚኒስትሪ ካርድ ያልወሰዳችሁ ኦላይን
ያለውን ውጤታችሁን ስካን አድርጋችሁ ማያያዝ ይጠበቅባችዋል፡፡
ከዚህ ቀደም የተመዘገባችሁ እና በትክክል ያላስገባችሁ ተማሪዎች በድጋሚ አስተካክለችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን የተገለጸ ሲሆን ለመመዝገብ https://sbs.moe.gov.et/apply
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 76👍 11👏 5🥰 3🖕 2
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት ግብአት ፍላጎት አቅርቦትና ስርጭት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ ምስራቅ ብርሀነመስቀል በበኩላቸው በከተማ አስተዳደሩ በቅድመ አንደኛ፣አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ 840,585 ተማሪዎች በቀን ሁለት ጊዜ የምገባ አገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆናቸውን ግልጸው የምገባ አገልግሎቱ በ560 ማህበራት ለተደራጁ 12,943 መጋቢ እናቶች የስራ እድል መፍጠሩን በመጥቀስ ቢሮው በየትምህርት ቤቱ በመገኘት የምገባ አገልግሎቱን አተገባበር በድጋፍና ክትትል በማረጋገጥ ላይ መሆኑንም አስረድተዋል።
በመርሀግብሩ የቢሮው የትምህርት ቤት ምገባ አገልግሎት ቡድን መሪ አቶ ናትናኤል ገብረዋድ በየትምህርት ቤቱ ያለውን የምገባ አገልግሎት መሰረት አድርጎ የተካሄደ የድጋፍና ክትትል ሪፖርት አቅርበው ውይይት ተካሂዷል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 72👍 29👏 6🍾 6🔥 4
ከተማ አስተዳደሩ በከፍተኛ በጀት ተግባራዊ ያደረገው የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም ውጤታማ እንዲሆን በየትምህርት ተቋማቱ የሚገኙ የምገባ ተቆጣጣሪ ባለሙያዎች ተገቢውን ክትትል ማድረግ እንደሚገባቸው ተጠቆመ።
(14/12/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በየትምህርት ተቋማቱ ከሚገኙ የምገባ ተቆጣጣሪ ባለሙያዎች ጋር በትምህርት ቤት ምገባ አገልግሎት እና ከአገልግሎቱ ጋር በተገናኘ በተካሄደ ድጋፍና ክትትል ግብረመልስ ዙሪያ ውይይት አካሂዷል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ እና የዘርፉ አስተባባሪ አቶ ሳምሶን መለሰ በመርሀግብሩ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት መንግስት በከፍተኛ በጀት ተግባራዊ ያደረገው የተማሪዎች ምገባ አገልግሎት የተማሪዎች ውጤት እና ስነምግባር እንዲሻሻል ከማድረጉ ባሻገር ለወላጆች እፎይታ መፍጠር ያስቻለ ፕሮግራም መሆኑን ገልጸዋል።
ምክትል ቢሮ ኃላፊው አያይዘውም በየትምህርት ቤቱ ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም በአግባቡ ተግባራዊ እንዲሆን አገልግሎቱን የሚከታተሉ የምገባ ተቆጣጣሪ ባለሙያዎች እንዲመደቡ መደረጉን ገልጸው ባለሙያዎቹ በ2017ዓ.ም የነበሩ አፈጻጸሞችን መሰረት በማድረግ በ2018ዓ.ም የተሻለ ስራ ለመስራት ከወዲሁ በቂ ቅድመ ዝግጅት ማድረግ የሚገባቸው መሆኑን አስገንዝበዋል።
❤ 51👍 13
ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ለሚማሩ አይነስውር ተማሪዎች የተዘጋጀ የብሬል መጽሐፍ ግምገማ በመካሄድ ላይ መሆኑ ተገለጸ።
(14/12/2017 ዓ.ም) የብሬል መጽሐፍ ግምገማው በከተማ አስተዳደሩ ከሚገኙ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በተውጣጡ አይነስውር መምህራን እና በቢሮ የሁለቱ ስርአተ ትምህርት ባለሙያዎች አማካይነት በመካሄድ ላይ መሆኑን ከልዩፍላጎትና ጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የልዩፍላጎትና ጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ተወካይ አቶ ጌታቸው በላይነህ ከተማ አስተዳደሩ የልዩፍላጎት ተማሪዎችን በትምህርት ስርአቱ ተጠቃሚ ለማድረግ ተጨባጭ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ መሆኑን ጠቁመው ትምህርታቸውን ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል በመከታተል ላይ ለሚገኙ አይነስውራን ተማሪዎች ተዘጋጅቶ በመገምገም ላይ የሚገኘው የብሬል መጽሐፍ የዚሁ ተግባር ማሳያ መሆኑን አመላክተዋል።
አቶ ጌታቸው አያይዘውም የብሬል መጽሐፍ ግምገማው ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ አራት ቀናት እንደሚካሄድ ጠቁመው ግምገማው ከተጠናቀቀ በኋላ የሚሰጡ የማስተካከያ ሀሳቦች ተካተው ለህትመት የሚላክ መሆኑን አስገንዝበዋል።
የቢሮው የልዩፍላጎትና አካቶ ትምህርት ባለሙያ አቶ ጸጋዬ ሁንዴ በበኩላቸው የብሬል መጽሐፎቹ በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ አይነስውር ተማሪዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ዳይሬክቶሬቱ ከቢሮው ስርአተ ትምህርት ባለሙያዎች እና የብሬል ክህሎት ካላቸው አይነስውር መምህራን ጋር በጋራ ማዘጋጀቱን ገልጸው ግምገማው ሲጠናቀቅ መጽሐፍቶቹን በማሳተም በ2018 ዓ.ም የትምህርት አመት ለተማሪዎች ተደራሽ እንደሚደረጉ አስታውቀዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 59👍 4👌 3👏 1
የትምህርት ግብአት አቅርቦትና ስርጭት ዳይሬክቶሬት የ2018 ዓ.ም የትምህርት ግብአት ስርጭት ያለበትን ደረጃ ገመገመ።
(14/12/2017 ዓ.ም) ግምገማው ከክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት የትምህርት ግብአት ቡድን መሪዎች ጋር የተካሄደ ሲሆን በመርሀግብሩ የደንብ ልብስ ፣መጽሐፍ፣ እንዲሁም የደብተር እና ሌሎች የመማሪያ ቁሳቁሶች ስርጭት ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ሪፖርት ቀርቦ ተገምግሟል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት ግብአት አቅርቦትና ስርጭት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ ምስራቅ ብርሀነመስቀል ቢሮው የ2018 ዓ.ም የትምህርት አመት ከመጀመሩ በፊት የትምህርት ግብአት አቅርቦቱን ወደትምህርት ተቋማት ተደራሽ ለማድረግ የ90 ቀን የንቅናቄ እቅድ አዘጋጅቶ ወደ ተግባር መግባቱን ገልጸው በአሁኑ ወቅት በየትምህርት ቤቱ ተማሪዎች ምዝገባ ካካሄዱ በኋላ ግብአቶቹን በመውሰድ ላይ እንደሚገኙ በዛሬው ግምገማ መረጋገጡን አመላክተዋል።
ዳይሬክተሩዋ አያይዘውም የትምህርት ግብአት አቅርቦቱን በእቅዱ በተቀመጠው መሰረት ቀሪ ስራዎችን በማጠናቀቅ አዲሱ የትምህርት አመት ከመጀመሩ በፊት ለተማሪዎች ተደራሽ እንዲሆን በትኩረት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 74👍 14👌 3
የከተማ ግብርና በሽመልስ ሀብቴ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
(13/12/2017 ዓ.ም) በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ሽመልስ ሀብቴ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመከናወን ላይ የሚገኝ የከተማ ግብርና መርሀ ግብር።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 76👍 29👎 14
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅህፈት ቤት ለትምህርት አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ስልጠና ሰጠ።
(13/12/2017 ዓ.ም) የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅህፈት ቤት ለትምህርት አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ስልጠና የሰጠ ሲሆን በስልጠናው ላይ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅህፈት ቤት የመምህራን እና ትምህርት አመራር ልማት ቡድን መሪ አቶ ተሾመ ዘውዴ ስልጠናው ክፍተትን መሰረት አድርጎ መሰጠቱን ገልጸው በስልጠናው ላይ የትምህርት ቤት አመራሮች ፣ የትምህርት ፅህፈት ቤት ኋላፊዎች ፣ በድን መሪዎች ፣ ሱፐርቫይዘሮች ፣ ባለሙያዎች ፣ የወተምህ እና መምህራን ማህበር አመራሮች ፣ የትምህርት ቤቶች የፋይናስ እና የሰው ሀይል ቡድን መሪዎች መሳተፋቸዉን ተናግረዋል፡፡
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ከበደ ድሪባ ስልጠናው በ2017 ዓ.ም "የአገልጋይነት ስራ አመራር" ሂደት ያለበትን ሁኔታ በመለየት በ2018 ዓ.ም የተሻለ የአገልጋይነት ስራ አመራር ለመፍጠርና ተቋማትን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማምጣት ታስቦ የተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል።
አክለዉም የትምህርት አመራሮች በስልጠናው ያገኙትን እውቀት ወደ መሬት አውርደው ከራሳቸው ህይወት ጋር በማገናዘብ ተግባራዊ ሊሆን ከሚችል የማስተማር ስነ ዘዴ ጋር አገናኝተው መስጠት እንዲችሉ አቅማቸውን የሚገነቡበት መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
ስልጠናው "የአገልጋይነት ስራ አመራር" በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር በሆኑት በዶክተር ዮሀንስ ረጋሳ ተሰጥቷል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 63🏆 1
የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በመሰጠት ላይ ይገኛል።
(12/12/2017 ዓ.ም) በክፍለ ከተማው የትምህርት ለትውልድ ለበጎ ፍቃደ የሆኑ መምህራን በተለያዩ የትምህርት ዓይነቶች ከ500 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት እየሰጡ ይገኛሉ።
የፉሪ የመጀመሪያ ጀረጃ ት/ቤት ምክትል ርዕሰ መምህር አቶ ተስፉ የማጠናከሪያ ትምህርቱ ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ለሚገኙ ተማሪዎች የሚሰጥ መሆኑንና ዋና ዓላማውም ተማሪዎች በቀጣይ የትምህርት ዘመን የሚማሩትን ትምህርት ቀድመው በመረዳትና የትምህርቱን ይዘት በአግባቡ በመገንዘብ የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ የሚያስችል መሆኑን መናገራቸዉን ከክፍለ ከተማው ያገኘነው መረጃ ያሳያለ።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 82👍 15
የሰኞ ማለዳ የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡
(12/12/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሰኞ ማለዳ ከስራ ሰዓት መግቢያ በፊት የሚያዘጋጀው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር የተካሄደ ሲሆን በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስነምግባርና ጸረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አስራት ሽፈራው በትምህርት ቢሮ የዜጎች ቻርተርና በተቋሙ ራይይ ተልኮና ዕሴት ላይ መሰረት ያደረገ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በመድረኩ ማጠቃለያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አማካሪ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ የቢሮዉን የዜጎች ቻርተር ፤ ራዕይ ተልእኮ እና ዕሴት በአግባቡ ተገንዝቦ ውጤታማ ስራ ለመስራት እንዲቻል ሰነዱ መቅረቡ ትልቅ እገዛ ያደርጋል ያሉ ሲሆን አያይዘዉም ሰራተኞች የተገነዘቡትን ወደ ተግባር እንዲቀይሩ አደራ ብለዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤ 62👍 12👎 4😁 2🥰 1
