es
Feedback
አዲስ ነገር መረጃ

አዲስ ነገር መረጃ

Ir al canal en Telegram

#አዲስ_ነገር_መረጃ #መረጃዎች_በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ Addis Ababa , Ethiopia Buy Ads : https://telega.io/?r=UbutLo2z #ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇 @Addisnegermereja_bot

Mostrar más
2025 año en númerossnowflakes fon
card fon
103 408
Suscriptores
-5124 horas
-3077 días
+12730 días
Archivo de publicaciones
🤣 73 27👏 4😢 2
የፌደራሉ መንግስት ‛ በረሃብ ለተጠቁት ’ ሰዎች የሚደረጉ የድጋፍ ማሳባሰብ ዘመቻዎች “ ህገወጥ ናቸው ” ሲል ፈረጀ‼️ ህወሓትንም “ ሰብዓዊ እርዳታ በመስረቅ ” ወንጅሏል‼️ የፌደራሉ መንግስት “ በማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች በቡድንም ሆነ በተናጠል የሚደረጉ የድጋፍ ማሰባሰብ ዘመቻ የአሰራር ስርዓትን የጣሱ ህገ-ወጥ አካሄዶች ” ናቸው ሲል በይኗል። የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽነር ሽፈራው ተ/ማርያም(ዶ/ር) ‛ ትህነግ ’ እያሉ የጠሩት ህወሓት “ ሕዝብን በረሃብ በመቅጣት ለፖለቲካ መሣሪያነት የመጠቀም ተግባሩን ዳግም በትግራይ ሕዝብ ላይ እያሳየ ነው ” ሲሉ በብርቱ ወንጅለዋል። ‛ የትህነግ ቡድን ’ እያሉ የጠሩት ህወሓት “ የፌደራል መንግስት በትግራይ ክልል በመጠለያ ማዕከላትና በልማታዊ ሴፍቲኔት መርሃ ግብር የሚያቀርበውን ሰብዓዊ ድጋፍ ለተፈለገው ዓላማ እንዳይወል እያደረገ እንደሚገኝ ” የጠቀሱት ኮሚሽነሩ፣ የሰሞኑ የሕጻጽ መጠለያ ጣቢያ ማስረጃ መሆኑን ለኢዜአ ነግረውታል። ህወሓት ይህን ያደርግበታል ያሉትን ምክንያት አስረድተዋል። እሱም “ በትግራይ ክልል በመጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ ወገኖች የሚቀርብን ሰብዓዊ ድጋፍ በመንጠቅ ” ድራማዊ ፕሮፓጋንዳ ማስተጋባት መሆኑን አመልክተዋል። ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም የፌደራል መንግስት በግልጽ መረጃና ማስረጃ የሚልከው ሰብዓዊ ድጋፍ የት እንደገባ መጠየቅ አለበት ያሉት ሽፈራው “ በቡድኑ የሃሰት ፕሮፓጋንዳ መደናገር እንደሌለበትም ” አሳስበዋል። የፌደራሉ መንግስት አስተማማኝ ድጋፍ እያደረገ ነው ሲሉ የሚከራከሩት ኮሚሽነሩ ሙግታቸውንም በአሐዝ አስደግፈዋል። በዚህም በትግራይ ክልል ከባለፈው ጥር 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታኅሳስ ወር 2018 ዓ.ም ድረስ ሁለት ሚሊየን ኩንታል በገንዘብ ሲተምን 32 ቢሊዮን ብር የሚገመት ሰብዓዊ ድጋፍ መሰራጨቱን አስታውቀዋል። ይሁንና ህወሓት “ በትግራይ ክልል ሰብዓዊ ድጋፉ ተደራሽ እንዳይሆን በማስተጓጎል፣ ድጋፉን ከችግረኛ ዜጎች በመንጠቅ ዳግም የሕዝብ ጠላትነቱን እያረጋገጠ እንደሚገኝም ” ጠቅሰው ኮንነዋል። ህወሓትን በብርቱ የወነጀሉት የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽነር ሽፈራው፣  በተናጠልም ሆነ በቡድን የሚደረጉ የድጋፍ ማሰባሰብ ዘመቻዎችም “ የአሰራር ሥርዓትን የጣሱ ህገወጥ አካሄዶች ናቸው ” ሲሉ ተናግረዋል። “የተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮችን በመጠቀም ሰብዓዊ ድጋፍ በማሰባሰብ ላልተገባ ዓላማ እያዋሉ የሚገኙ አካላት ከድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባም ” አሳስበዋል። @Addis_News @Addis_News
Mostrar todo...
44🤪 19😢 2
Photo unavailableShow in Telegram
1
Photo unavailableShow in Telegram
የኢትዮ ቴሌኮምን  የመገናኛ ድምፅ ማስተላለፍያ ሽቦችን የሰረቁ አራት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ በምዕራብ ሐረርጌ ዞን  ጭሮ ከተማ አስተዳደር ጨፌ አራራ ቀበሌ ውስጥ የኢትዮ ቴሌኮም ንብረት የሆነውን የመገናኛ ድምፅ ማስተላለፍያ ሽቦ የሰረቁ አራት ግለሠቦች በእስራት ተቀጥተዋል። እንደ ምዕራብ ሐረርጌ ዞን አቃቢ ሕግ ፅህፈት ቤት መግለጫ ለግዜው ስማቸው ያልተገለፀ አራት ግለሠቦች የኢትዮ ቴሌኮም ንብረት የሆነውን ኦፕቲካል ፋይበር የመገናኛ ማስተላለፍያ  ድምፅ  ሽቦ የሰረቁ ሲሆን በቁጥጥር ስር የዋሉት የሰረቁትን ሽቦ ጭነው ወደ አዲስ አበባ ከተማ ለማሸጋገር ሲሞክሩ እንደሆነ ታውቋል። አራቱ ተከሣሽ ግለሠቦች ግምታዊ ዋጋው አንድ መቶ አስራ ስድስት ሺህ ሰባት መቶ ብር የሚያወጣውን ሽቦ  ሰርቀው ከሸሸጉ በሗላ ከቦታ ቦታ ለማዘዋወር  ሲሞክሩ በቁጥጥር ስር ውለው በፖሊስ በኩል አስፈላጊው የምርመራ መዝገብ ተጣርቶ ለአቃቢ ሕግ ተልኳል። አቃቢ ሕግም ከፖሊስ የቀረበውን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ  የቴሌኮምና የኤሌትሪክ አገልግሎትን ለመጠበቅ እና ለማስተዳደር የወጣውን መመርያ ቁጥር 464/ 1997 ንኡስ  አንቀፅ አራት  መሠረት በማድረግ  ክስ መስርቷል። ክሱን ሲከታተል የቆየው የምዕራብ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ታሕሣስ 13 ቀን 2018 ዓም በዋለው ችሎት 1ኛ፣2ኛ፣3ኛ ተከሣሾች እያንዳዳቸው  በአራት አመት ከሶስት ወር እስራት እና በሶስት ሺሕ ብር የገዘብ መቀጮ እንዲቀጡ የወሰነ ሲሆን አራተኛው ተከሣሽ በሁለት አመት ከሶስት ወር እስራት እና በተመሣሣይ ሶስት ሺህ ብር መቀጮ እንዲቀጣ የተወሠነበት መሆኑን መግለጫው አመልክቷል። Dagu @Addis_News @Addis_News
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
🚨ውፍረት መጨመር ይፈልጋሉ❓❓          +251964593642 ✔ ከአንድ ወር እስከ 45 ቀን ዉስጥ       ክብደት መጨመር የሚረዳ ✔ የምግብ ፍላጎት መጨመር የሚያስችል ✔  የቆዳን ጥራት እና ልስላሴ ለመጨመር        የሚረዳ ✔ ምንም አይነት የጎንዮሽ ጉዳት የሌለዉ ፤       ለቀጭን ሰዎች የሚመከር ✔ ለሴቶችም የተስተካከለ አቋም       እንዲጎናፀፉ የሚያግዝ ✔ ለወንዶችም ለሴቶችም የሚሆን አለን ፤       🚴‍♂ያሉበት እናደርሳለን ------------------------------------ ለበለጠ መረጃ ☎️ +251964593642                              +251906495051                              +251907495051 Telegram:   📥  t.me/AM_CS                             t.me/AM_CS1                             t.me/AM_CS2 ------------------------------------
Mostrar todo...
6
Photo unavailableShow in Telegram
የመጀመሪያው የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሀሰን ዓሊ ከ27 ዓመታት ቆይታ በኋላ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ። አቶ ሀሰን አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ፤ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ አቀባበል አድርገውላቸዋል። የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ “አቶ ሀሰን ዓሊ ወደ ሦስት አሥርተ ዓመታት ከሚደርስ ጊዜ በኋላ ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲመለሱ የተቀበልኳቸው ከታላቅ ክብር ጋር ነው” ብለዋል። የቀድሞው የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሀሰን ዓሊ የክልሉ መንግሥት ዛሬ ለደረሰበት ደረጃ በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱ ግለሰቦች መካከል አንዱ እንደሆኑም ጠቅሰዋል። አቶ ሀሰን ዓሊ ከ1984 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 1987 ዓ.ም ድረስ የመጀመሪያው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ሆነው አገልግለዋል። @Addisinsider_ETH @Addisinsider_ETH
Mostrar todo...
38🤪 18🤔 1🥱 1
የወርቁ አይተነውን የ 15 ሚሊየን ብር ድጋፍ አንቀበልም አግማስ የመንግስት አጋዥ ድርጅት ነው ሲሉም በመግለጫቸው ገልፀዋል :: ሙሉ መግለጫው 👇 አግማስ ኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ድርጅት ከኢፌድሪ ሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶት ባለስልጣን ፈቃድ ወስዶ መንቀሳቀስ ከጀመረ አራት አመታትን አስቆጥሯል። በነዚህ አመታት ውስጥ በርካታ በጎ ተግባራትን የፈጸመና የመንግስት አጋዥም ሆኖ የቆየ ድርጅት ነው። በተለይም ተፈናቃይ ወገኖች ጋር በተያያዘ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን በእለት ደራሽ ድጋፍና በቅርቡ ደግሞ በደቡብ ወሎ ሀርቡና ደጋን መጠለያ ካምፖች የዘላቂ መፍትሄ መርህን በመከተል በርካታ ወገኖችን እያደራጀ ወደ ስራ አስገብቷል። አግማስ ኢትዮጵያ እያንዳንዱን ስራዎቹን ሲሰራ በየአካባቢው ከሚገኙ የመንግስት መዋቅር ጋር የፕሮጀክት ስምምነት ( project Agreement) በመፈራረም ነው። ከክልልም ይሁን ከፌደራል መንግስት በሚቀመጡ አቅጣጫዎች መሰረት እየሰራ የቆየ ሲሆን በዚህም ድርጅታችን ከተለያዩ የዞን ሴክተር መስሪያ ቤቶች የእውቅናና የምስጋና ሰርቲፌኬቶችን ተቀብሏል። አግማስ ኢትዮጵያ ይህንን በጎ ተግባርና ወገኖችን በዘላቂነት ወደ ስራ የማስገባት እንቅስቃሴውን ለመደገፍ ያለመ የቀጥታ ስርጭት ( online) የድጋፍ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላለፉት ስድስት  ቀናት ያደረገ ሲሆን በዚህ ፕሮግራም ላይም አንዳንድ ከድርጅታችን መርህ ጋር አብረው የማይሄዱ አካሄዶችን አይተናል። ድርጅታችን ከፖለቲካ ከዘርና ሀይማኖት የጸዳና ገለልተኛ ሆኖ የሚሰራ በመሆኑ ምንም አይነት የፖለቲካም ይሁን ሌላ አላማ ካለው ግለሰብም ይሁን ድርጅት ድጋፍን የማይቀበል መሆኑንም ለማረጋገጥ እንወዳለን። በዚህም መሰረት እንድህ አይነት አመለካከት ያላቸው ጉዳዮን ከድርጅታችን ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌላቸው በማረጋገጥ የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብራችንንም በይፋ ማጠናቀቅና መዝጋታችንን እንገልጻለን። @Addis_News @Addis_News
Mostrar todo...
🤣 72 26🤪 10🥱 3😢 2
3
Photo unavailableShow in Telegram
በአዲስአበባ ሰራተኞች አድማ መቱ የቢዩ ዴሊቨሪ ሰራተኞች በዛሬው እለት አድማ መምታታቸውን አንዳፍታ ሚዲያ አረጋግጧል። ሰራተኞቹ "ጥያቄያችን ሳይመለስ ወደ ስራ አንገባም" ብለዋል። በዛሬው እለት የቢዩ ዴሊቨሪ የምግብ ማዘዣ የስልክ አፕሊኬሽን ስራ ማቆሙን አንዳፍታ ሚዲያ አረጋግጧል። ስለ ሰራተኞቹ አድማ እና ጥያቄ ድርጅቱ እስካሁን ያለው ነገር የለም። @Yenetube @Fikerassefa
Mostrar todo...
🤣 11 8
Photo unavailableShow in Telegram
የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎችና የሶሻል ሚዲያ ነጋዴዎች ግብር ሊከፍሉ ነው! ታህሳስ 16 ቀን 2018 ዓ.ም * ከዩቲዩብ (YouTube)፣ * ከቲክቶክ (TikTok) እና ከሌሎች የዲጂታል መድረኮች ገቢ የሚያገኙ ግለሰቦችም ሆኑ ተቋማት፣ ከሚያገኙት ገቢ ላይ ግብር እንዲከፍሉ የሚያስገድድ አሰራር እየተዘረጋ መሆኑ ተሰማ። ባለፈው ዓመት በተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ መሰረት፣ በኦንላይን ይዘቶችን በማምረት ገቢ የሚያገኙ አካላት በሙሉ፦ * በገቢዎች ቢሮ የመመዝገብ፣ * የግብር መለያ ቁጥር (TIN) የማውጣት ግዴታ ተጥሎባቸዋል። የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ እንዳስታወቀው፣ ክፍያዎችን የሚያመቻቹ የኦንላይን መድረኮች ለእያንዳንዱ ይዘት ፈጣሪ የከፈሉትን ዓመታዊ ጠቅላላ ገቢ ለቢሮው ሪፖርት የማድረግ ኃላፊነት ይኖርባቸዋል። ቢሮው ይህንን ስራ ከኢትዮ ቴሌኮም፣ ከንግድ ቢሮ እና ከፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ገልጿል። የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ሰውነት አየለ እንደገለጹት፣ እስካሁን ከዚህ ዘርፍ የሚገኘው ግብር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። በመሆኑም የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች ገቢያቸውን በፈቃደኝነት እንዲያሳውቁ ጥሪ የቀረበ ሲሆን፣ ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ቢሮው ወደ ማስገደድ ስራ እንደሚገባ አስጠንቅቀዋል። ቁጥጥሩ ይዘት ፈጣሪዎችን ብቻ ሳይሆን፣ የተለያዩ ምርቶችንና አገልግሎቶችን በማህበራዊ ሚዲያ (Facebook, Telegram ወዘተ) የሚያስተዋውቁና የሚሸጡ ነጋዴዎችንም የሚጨምር መሆኑ ታውቋል። Via SHEGER FM 102.1 RADIO @Addis_Reporter @Addis_Reporter
Mostrar todo...
🤣 26 13👏 6😢 1
Photo unavailableShow in Telegram
“ዝቅተኛ የመነሻ ደመወዝ ወለል እንዲወሰን እየተሰራ ነው”_ኢሠማኮ “በኢትዮጵያ ቤተሰብን ሊያኖር የሚችል የግል ድርጅት ሠራተኞችን ዝቅተኛ የመነሻ ደመወዝ ወለል ለማስወሰን የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን” የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) አስታወቀ። የኮንፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዚዳንት ድሪብሳ ለገሰ፤ በኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት የግል ሠራተኞች የመነሻ ደመወዝ ወለል ሳይወሰን መቆየቱን ገልፀዋል። በአሁኑ ጊዜ ይህንን ችግር ለመፍታትና ቤተሰብን ሊያኖር የሚችል የመነሻ ደመወዝ ወለል የሚወስን ቦርድ ለማቋቋም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል። የቦርዱን ማቋቋሚያ ደንብ በተመለከተ ኮንፌዴሬሽኑ አስፈላጊውን ግብዓት መስጠቱን የጠቀሱት አቶ ድሪብሳ፤ ቦርዱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተቋቁሞ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንዲገባ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል። @Addisinsider_ETH @Addisinsider_ETH
Mostrar todo...
20👍 6🤪 2
Photo unavailableShow in Telegram
በደቡብ አፍሪካ መጠጥ ቤት ውስጥ በተፈጸመ ጅምላ ጥቃት 11 ሰዎች ተያዙ እሁድ እለት በደቡብ አፍሪካ በሚገኝ መጠጥ ቤት ውስጥ 9 ሰዎች በሞቱበት የጅምላ ጥቃት 11 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።በጆሃንስበርግ አቅራቢያ በሚገኘው ቤከከርዳል  በደንበኞች ላይ የተኩስ ልውውጥ የፈጸሙትን ማንነታቸው ያልታወቁ 12 ታጣቂዎችን ፖሊስ ማደን ጀምሯል።ረቡዕ የግዛቲቱ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ሜጀር ጄኔራል ፍሬድ ኬካና እንደተናገሩት ከተያዙት ተጠርጣሪዎች መካከል ዘጠኙ የሌሴቶ ዜጎች ሲሆኑ አንደኛው የሞዛምቢክ ዜጋ ነዉ። ደቡብ አፍሪካዊ የማዕድን ሰራተኛ ነው ተብሎ የሚገመተው ሌላ ተጠርጣሪም በቁጥጥር ስር ውሏል።በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ያለው የግድያ ወንጀ፤ል በአለም ላይ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚቀመጥ ሲሆን ብዙውን ጊዜ የግጭት፣ የዘረፋ እና የቡድን ጥቃት ውጤቶች ናቸው።ጥቃቱ ከህገ-ወጥ ማዕድን ማውጫ ጦርነቶች ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል::በጥቃቱ ወቅት ሰዎች ከመጠጥ ቤቱ ሲሸሹ ታጣቂዎች መተኮሳቸውን ቀጥለዋል፣ በአቅራቢያው አንድ ተሳፋሪ ሲጎዳ አንድ የታክሲ ሹፌር ተገድሏል። በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በርካታ ፍቃድ የሌላቸው ኤኬ-47 ሽጉጥ በተጠርጣሪዎቹ እጅ ተገኝተዋል።በደቡብ አፍሪካ 3 ሚሊዮን ያህል በህጋዊ መንገድ የተያዙ ሽጉጦች እና ቢያንስ ተመሳሳይ ቁጥር ያላቸው ያልተፈቀዱ የጦር መሳሪያዎች እንዳሉ ከደቡብ አፍሪካ የወጣዉ አሀዛዊ መረጃ ያሳያል፡፡ ምንም እንኳን እ.ኤ.አ 2025 በጅምላ የተኩስ ልውውጥ እየቀነሰ ቢመጣም ከ2020 ጀምሮ አራት እና ከዚያ በላይ ሰዎች የተገደሉበት ወይም የተጎዱባቸው አጋጣሚዎች በከፍተኛ ሁኔታ ጨምረዋል ሲሉ የገን ፍሪ ደቡብ አፍሪካ የዘመቻ ቡድን ተመራማሪ ክሌር ቴይለር ተናግረዋል። በስምዖን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Mostrar todo...
12
Photo unavailableShow in Telegram
የቡና ዋጋ ቅናሽ‼️ በተያዘው የፈረንጆቹ 2025 አመት መጨረሻ ወራት ላይ የቡና ዋጋ ቅናሽ ያሳየ ሲሆን ለዋጋው ማሽቆልቆል የምርት መጨመር እንዲሁም በመጥፎ የአየር ጠባይ ምክንያት በብዛት የሚሸጡ ሀገራት በመብዛታቸው መሆኑን እንደምክንያት ተጠቅሷል፡፡ ከሳምንት በፊት የወጣው የUSDA ሪፖርት እንደሚያመለክተው የ2025/26 የዓለም የቡና ምርት ከላፈው ዓመት ምርት የ3.5 ሚሊዮን ኬሻ ብልጫ በማድረግ 178.8 ሚሊዩን ኬሻ ደርሷል፡፡ በተመሳሳይ ሪፖርት እንደተቀመጠው የፍጆታ መጠንም በተመሳሳይ ዓመት 173.9 ሚሊዮን ኬሻ እንደደረሰ ያሳል፡፡ በተያዘው 2025 መገባጃ የቡና ዋጋ ቅናሽ አሳይቷል። @Addis_Reporter @Addis_Reporter
Mostrar todo...
12
Photo unavailableShow in Telegram
በኢትዮጵያ ወጥ የሆነ የመሬት ፖሊሲ አለመኖር በዜጎች የመብት ጥያቄ ላይ ተግዳሮት መፍጠሩ ተገለጸ በኢትዮጵያ 80 በመቶ የሚሆነው የህዝብ ክፍል ኑሮው ከመሬት ጋር የተቆራኘ ቢሆንም፤ በአገራችን እስካሁን ድረስ ራሱን የቻለ የመሬት ፖሊሲና አጠቃላይ የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ አለመኖሩ በምርታማነትና በዜጎች የካሳ መብት ላይ ተግዳሮት እየፈጠረ መሆኑ ተመላክቷል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህሩ ዶክተር መለሰ ዳምጤ ለጣቢያችን እንደገለጹት፤ በአገራችን የመሬት አስተዳደር ስርዓቱን የሚመራ ግልጽ ፖሊሲና የተቀናጀ ዕቅድ ባለመኖሩ ዘርፉ ለተለያዩ ችግሮች ተጋልጦ ይገኛል። ምንም እንኳን አንዳንድ ክልሎች የራሳቸውን መመሪያ ለማውጣት ቢሞክሩም፤ አፈጻጸሙ ግን አሁንም ድረስ ወጥ ያልሆነ አሰራር የተጋረጠበት መሆኑን አመልክተዋል። በተለይም በልማት ምክንያት ከመሬታቸው የሚፈናቀሉ ዜጎች የሚከፈላቸው የካሳ መጠን ሌላኛው አነጋጋሪ ጉዳይ ሆኖ ቀጥሏል ብለዋል። እንደ ዶክተር መለሰ ማብራሪያ፤ በኢትዮጵያ መሬት የመንግስት በመሆኑ፣ ካሳ የሚከፈለው በመሬቱ ላይ ለለማው ንብረት እንጂ ለመሬቱ አይደለም። ይህም ከቦታው መገኛ አኳያ ሊገኝ የሚችለውን የገበያ ዋጋና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ያላገናዘበ በመሆኑ በዜጎች ላይ ከፍተኛ ኪሳራ እያደረሰ እንደሚገኝ ተገልጿል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የካሳ ግመታው በገለልተኛ አካል ሳይሆን በመንግስት አስፈጻሚ ኮሚቴዎች ብቻ መከናወኑ፤ ለግልጽነትና ለተጠያቂነት ክፍተት መፍጠሩን የሕግ ባለሙያው ጠቁመዋል። ይህም በዜጎች ላይ የሚስተዋሉ የሕግ ጥሰቶችንና ሕገ-መንግስታዊ የመብት ጥያቄዎችን እያባባሰ ይገኛል ተብሏል። @Addis_Reporter @Addis_Reporter
Mostrar todo...
17
Photo unavailableShow in Telegram
አብዛኛዎቹ ሩሲያውያን የዩክሬን ጦርነት በ2026 ያበቃል ብለው እንደሚጠብቁ አንድ ጥናት አረጋገጠ አብዛኛዎቹን ሩሲያውያን በዩክሬን ያለው ጦርነት በ2026 ያበቃል ብለው እንደሚጠብቁ የመንግስት የምርምር ማዕከል ያስታወቀ ሲሆን የሩስያ ሀይሎች በጦር ሜዳ ላይ የሚያደርጉት ግስጋሴ ቢቀጥልም በኪየቭ እና በሞስኮ መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስ ጥረቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል። ከሩሲያ ህዝብ የተሰበሰበዉ አስተያየት እንዳመላከተዉ በወጪው አመት ሩሲያውያን ጦርነቱ እንደሚያበቃ ብሩህ ተስፋ እንዳላቸዉ ተመላክቷል፡፡ ጥናቱን የሰራዉ ቪቲሲኦኤም የተሰኘዉ ማዕከል ምክትል ኃላፊ ሚካሂል ማሞኖቭ በዓመት መጨረሻ ላይ ሆነዉ እንደተናገሩ በጥናቱ ከተካሄደባቸው 1,600 ሰዎች መካከል 70 በመቶው ለሩሲያ 2026 “የተሳካ” ዓመት እንደሆነ አድርገው ይመለከታሉ ብለዋል።ለብሩህ ተስፋ ዋናው ምክንያት በፕሬዚዳንት ፑቲን ከተገለጹት ብሄራዊ ጥቅሞች ጋር በተገናኘ ልዩ ወታደራዊ ዘመቻውን ማጠናቀቅ እና የተገለጹትን ዓላማዎች ማሳካት ይቻላል የሚል ተስፋ አድርገዋል፡፡ ማሞኖቭ እንዳሉት የሩስያ ጦር በዩክሬን እያካሄደ ያለውን ጥቃት፣ ዋሽንግተን የዩክሬንን ጦርነት ለመደገፍ ፈቃደኛ አለመሆኗ እና የአውሮፓ ህብረት በዩክሬን ውስጥ የዩናይትድ ስቴትስ ሚናን ሙሉ በሙሉ ለመተካት አለመቻሉ በገንዘብ እና በወታደራዊ ድጋፍ እጥረት ጦርነቱን ለማቆም የመጨረሻው ስምምነት ከሚጠበቀው ቁልፍ ምክንያቶች በስተጀርባ ይገኛል ሲሉ ጠቁመዋል ።በግጭቱ ማጠቃለያ ላይ የሩሲያ ወታደራዊ ዘማቾችን ወደ ህብረተሰብ መመለስ እና በሩሲያ ቁጥጥር ስር ያሉ የዩክሬን ክልሎችን እንዲሁም የሩሲያ የድንበር አካባቢዎችን እንደገና መገንባት ዋና ዋና ጉዳዮች ይሆናሉ ሲሉ ማሞኖቭ አክለዋል። @Yenetube @Fikerassefa
Mostrar todo...
19👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
የጥንቃቄ መልዕክት!! የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የክቡር ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዲዎን ጢሞቲዎስን ስም እና ሀሰተኛ ፊርማ በመጠቀም የሥራ እና የነጻ ትምህርት ዕድል ማረጋገጫ እና ውክልና እንደሰጡ በማስመሰል በማኀበራዊ ሚዲያ ሐሰተኛ መረጃዎች እየተሰራጩ እንደሚገኙ ለመረዳት ችለናል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ክቡር ሚኒስትሩ የሥራ እና የነጻ ትምህርት ዕድልን በተመለከተ ለማናቸውም አካል ውክልና እንዳልተሰጠ ታውቆ ኀብረተሰቡ ከእንዲህ አይነቶቹ ሕገወጥ የማጭበርበር እና የማታለል ወንጀሎች ራሱን እንዲጠብቅ እያሳሰበ :በሚኒስቴሩም ሆነ በክቡር ሚኒስትሩ ስም የሚያጭበረብሩ ሕገ ወጦችን ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን የሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ለማድረግ እየሠራ መሆኑን ማስገንዘብ ይወዳል። @ethio_mereja_news @ethio_mereja_news
Mostrar todo...
14🤣 3👏 2
Photo unavailableShow in Telegram
አብዛኛዎቹ ሩሲያውያን የዩክሬን ጦርነት በ2026 ያበቃል ብለው እንደሚጠብቁ አንድ ጥናት አረጋገጠ አብዛኛዎቹን ሩሲያውያን በዩክሬን ያለው ጦርነት በ2026 ያበቃል ብለው እንደሚጠብቁ የመንግስት የምርምር ማዕከል ያስታወቀ ሲሆን የሩስያ ሀይሎች በጦር ሜዳ ላይ የሚያደርጉት ግስጋሴ ቢቀጥልም በኪየቭ እና በሞስኮ መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስ ጥረቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል። ከሩሲያ ህዝብ የተሰበሰበዉ አስተያየት እንዳመላከተዉ በወጪው አመት ሩሲያውያን ጦርነቱ እንደሚያበቃ ብሩህ ተስፋ እንዳላቸዉ ተመላክቷል፡፡ ጥናቱን የሰራዉ ቪቲሲኦኤም የተሰኘዉ ማዕከል ምክትል ኃላፊ ሚካሂል ማሞኖቭ በዓመት መጨረሻ ላይ ሆነዉ እንደተናገሩ በጥናቱ ከተካሄደባቸው 1,600 ሰዎች መካከል 70 በመቶው ለሩሲያ 2026 “የተሳካ” ዓመት እንደሆነ አድርገው ይመለከታሉ ብለዋል።ለብሩህ ተስፋ ዋናው ምክንያት በፕሬዚዳንት ፑቲን ከተገለጹት ብሄራዊ ጥቅሞች ጋር በተገናኘ ልዩ ወታደራዊ ዘመቻውን ማጠናቀቅ እና የተገለጹትን ዓላማዎች ማሳካት ይቻላል የሚል ተስፋ አድርገዋል፡፡ ማሞኖቭ እንዳሉት የሩስያ ጦር በዩክሬን እያካሄደ ያለውን ጥቃት፣ ዋሽንግተን የዩክሬንን ጦርነት ለመደገፍ ፈቃደኛ አለመሆኗ እና የአውሮፓ ህብረት በዩክሬን ውስጥ የዩናይትድ ስቴትስ ሚናን ሙሉ በሙሉ ለመተካት አለመቻሉ በገንዘብ እና በወታደራዊ ድጋፍ እጥረት ጦርነቱን ለማቆም የመጨረሻው ስምምነት ከሚጠበቀው ቁልፍ ምክንያቶች በስተጀርባ ይገኛል ሲሉ ጠቁመዋል ።በግጭቱ ማጠቃለያ ላይ የሩሲያ ወታደራዊ ዘማቾችን ወደ ህብረተሰብ መመለስ እና በሩሲያ ቁጥጥር ስር ያሉ የዩክሬን ክልሎችን እንዲሁም የሩሲያ የድንበር አካባቢዎችን እንደገና መገንባት ዋና ዋና ጉዳዮች ይሆናሉ ሲሉ ማሞኖቭ አክለዋል። ዳጉ_ጆርናል @Addis_News @Addis_News
Mostrar todo...
00:42
Video unavailableShow in Telegram
13.58 MB
86🤣 6
01:08
Video unavailableShow in Telegram
👉 ከ8 በላይ ሳይቶችን ገንብቶ ያስረከበው ቴምር ፕሮፐርቲ አሁንም በድጋሜ አዳዲስ ሳይቶችን ለሽያጭ አቅርቧል ። 📍 ሳር ቤት #በ35%ቅናሽ! (በ100% ክፍያ) 👉 ባለ 2 መኝታ = 81ካሬ = 5.7ሚ 👉 ባለ 2 መኝታ = 106ካሬ = 7.9ሚ 👉 ባለ 3 መኝታ = 139ካሬ = 10.3ሚ 👉 ባለ 3 መኝታ = 153ካሬ = 11.4ሚ #በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ) 👉 81ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 9.3ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (1.8ሚሊዮን) 👉 106ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 12.1ሚ                  ቅድመ ክፍያ = 20% (2.4ሚሊዮን) 👉 139ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 15.9ሚ                  ቅድመ ክፍያ = 20% (3.1ሚሊዮን) 📍 አዋሬ #በ35%ቅናሽ! (በ100% ክፍያ) 👉 ባለ 1 መኝታ = 78ካሬ = 5.5ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 117ካሬ = 8.3ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 137ካሬ = 9.7ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 145ካሬ = 10.3ሚሊዮን #በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ) 👉 78ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 8.5ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (1.7ሚሊዮን) 👉 135ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 14.8ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (2.9ሚሊዮን) 👉 157ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 17.2ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (3.4ሚሊዮን) ⩩ ቀሪውን 80%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት። ⩩ 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፤ ከከፈሉት ላይ ከ15 -25% ቅናሽ አዘጋጅተናል። ለበለጠ መረጃ ;- 0940464607 0994003949
Mostrar todo...
25.16 MB