fa
Feedback
አዲስ ነገር መረጃ

አዲስ ነገር መረጃ

رفتن به کانال در Telegram

#አዲስ_ነገር_መረጃ #መረጃዎች_በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ Addis Ababa , Ethiopia Buy Ads : https://telega.io/?r=UbutLo2z #ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇 @Addisnegermereja_bot

نمایش بیشتر
2025 سال در اعدادsnowflakes fon
card fon
103 418
مشترکین
-5124 ساعت
-3077 روز
+12730 روز
آرشیو پست ها
Photo unavailableShow in Telegram
የመጀመሪያው የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሀሰን ዓሊ ከ27 ዓመታት ቆይታ በኋላ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ። አቶ ሀሰን አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ፤ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ አቀባበል አድርገውላቸዋል። የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ “አቶ ሀሰን ዓሊ ወደ ሦስት አሥርተ ዓመታት ከሚደርስ ጊዜ በኋላ ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲመለሱ የተቀበልኳቸው ከታላቅ ክብር ጋር ነው” ብለዋል። የቀድሞው የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሀሰን ዓሊ የክልሉ መንግሥት ዛሬ ለደረሰበት ደረጃ በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱ ግለሰቦች መካከል አንዱ እንደሆኑም ጠቅሰዋል። አቶ ሀሰን ዓሊ ከ1984 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 1987 ዓ.ም ድረስ የመጀመሪያው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ሆነው አገልግለዋል። @Addisinsider_ETH @Addisinsider_ETH
نمایش همه...
38🤪 18🤔 1🥱 1
የወርቁ አይተነውን የ 15 ሚሊየን ብር ድጋፍ አንቀበልም አግማስ የመንግስት አጋዥ ድርጅት ነው ሲሉም በመግለጫቸው ገልፀዋል :: ሙሉ መግለጫው 👇 አግማስ ኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ድርጅት ከኢፌድሪ ሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶት ባለስልጣን ፈቃድ ወስዶ መንቀሳቀስ ከጀመረ አራት አመታትን አስቆጥሯል። በነዚህ አመታት ውስጥ በርካታ በጎ ተግባራትን የፈጸመና የመንግስት አጋዥም ሆኖ የቆየ ድርጅት ነው። በተለይም ተፈናቃይ ወገኖች ጋር በተያያዘ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን በእለት ደራሽ ድጋፍና በቅርቡ ደግሞ በደቡብ ወሎ ሀርቡና ደጋን መጠለያ ካምፖች የዘላቂ መፍትሄ መርህን በመከተል በርካታ ወገኖችን እያደራጀ ወደ ስራ አስገብቷል። አግማስ ኢትዮጵያ እያንዳንዱን ስራዎቹን ሲሰራ በየአካባቢው ከሚገኙ የመንግስት መዋቅር ጋር የፕሮጀክት ስምምነት ( project Agreement) በመፈራረም ነው። ከክልልም ይሁን ከፌደራል መንግስት በሚቀመጡ አቅጣጫዎች መሰረት እየሰራ የቆየ ሲሆን በዚህም ድርጅታችን ከተለያዩ የዞን ሴክተር መስሪያ ቤቶች የእውቅናና የምስጋና ሰርቲፌኬቶችን ተቀብሏል። አግማስ ኢትዮጵያ ይህንን በጎ ተግባርና ወገኖችን በዘላቂነት ወደ ስራ የማስገባት እንቅስቃሴውን ለመደገፍ ያለመ የቀጥታ ስርጭት ( online) የድጋፍ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላለፉት ስድስት  ቀናት ያደረገ ሲሆን በዚህ ፕሮግራም ላይም አንዳንድ ከድርጅታችን መርህ ጋር አብረው የማይሄዱ አካሄዶችን አይተናል። ድርጅታችን ከፖለቲካ ከዘርና ሀይማኖት የጸዳና ገለልተኛ ሆኖ የሚሰራ በመሆኑ ምንም አይነት የፖለቲካም ይሁን ሌላ አላማ ካለው ግለሰብም ይሁን ድርጅት ድጋፍን የማይቀበል መሆኑንም ለማረጋገጥ እንወዳለን። በዚህም መሰረት እንድህ አይነት አመለካከት ያላቸው ጉዳዮን ከድርጅታችን ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌላቸው በማረጋገጥ የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብራችንንም በይፋ ማጠናቀቅና መዝጋታችንን እንገልጻለን። @Addis_News @Addis_News
نمایش همه...
🤣 72 26🤪 10🥱 3😢 2
3
Photo unavailableShow in Telegram
በአዲስአበባ ሰራተኞች አድማ መቱ የቢዩ ዴሊቨሪ ሰራተኞች በዛሬው እለት አድማ መምታታቸውን አንዳፍታ ሚዲያ አረጋግጧል። ሰራተኞቹ "ጥያቄያችን ሳይመለስ ወደ ስራ አንገባም" ብለዋል። በዛሬው እለት የቢዩ ዴሊቨሪ የምግብ ማዘዣ የስልክ አፕሊኬሽን ስራ ማቆሙን አንዳፍታ ሚዲያ አረጋግጧል። ስለ ሰራተኞቹ አድማ እና ጥያቄ ድርጅቱ እስካሁን ያለው ነገር የለም። @Yenetube @Fikerassefa
نمایش همه...
🤣 11 8
Photo unavailableShow in Telegram
የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎችና የሶሻል ሚዲያ ነጋዴዎች ግብር ሊከፍሉ ነው! ታህሳስ 16 ቀን 2018 ዓ.ም * ከዩቲዩብ (YouTube)፣ * ከቲክቶክ (TikTok) እና ከሌሎች የዲጂታል መድረኮች ገቢ የሚያገኙ ግለሰቦችም ሆኑ ተቋማት፣ ከሚያገኙት ገቢ ላይ ግብር እንዲከፍሉ የሚያስገድድ አሰራር እየተዘረጋ መሆኑ ተሰማ። ባለፈው ዓመት በተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ መሰረት፣ በኦንላይን ይዘቶችን በማምረት ገቢ የሚያገኙ አካላት በሙሉ፦ * በገቢዎች ቢሮ የመመዝገብ፣ * የግብር መለያ ቁጥር (TIN) የማውጣት ግዴታ ተጥሎባቸዋል። የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ እንዳስታወቀው፣ ክፍያዎችን የሚያመቻቹ የኦንላይን መድረኮች ለእያንዳንዱ ይዘት ፈጣሪ የከፈሉትን ዓመታዊ ጠቅላላ ገቢ ለቢሮው ሪፖርት የማድረግ ኃላፊነት ይኖርባቸዋል። ቢሮው ይህንን ስራ ከኢትዮ ቴሌኮም፣ ከንግድ ቢሮ እና ከፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ገልጿል። የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ሰውነት አየለ እንደገለጹት፣ እስካሁን ከዚህ ዘርፍ የሚገኘው ግብር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። በመሆኑም የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች ገቢያቸውን በፈቃደኝነት እንዲያሳውቁ ጥሪ የቀረበ ሲሆን፣ ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ቢሮው ወደ ማስገደድ ስራ እንደሚገባ አስጠንቅቀዋል። ቁጥጥሩ ይዘት ፈጣሪዎችን ብቻ ሳይሆን፣ የተለያዩ ምርቶችንና አገልግሎቶችን በማህበራዊ ሚዲያ (Facebook, Telegram ወዘተ) የሚያስተዋውቁና የሚሸጡ ነጋዴዎችንም የሚጨምር መሆኑ ታውቋል። Via SHEGER FM 102.1 RADIO @Addis_Reporter @Addis_Reporter
نمایش همه...
🤣 26 13👏 6😢 1
Photo unavailableShow in Telegram
“ዝቅተኛ የመነሻ ደመወዝ ወለል እንዲወሰን እየተሰራ ነው”_ኢሠማኮ “በኢትዮጵያ ቤተሰብን ሊያኖር የሚችል የግል ድርጅት ሠራተኞችን ዝቅተኛ የመነሻ ደመወዝ ወለል ለማስወሰን የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን” የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) አስታወቀ። የኮንፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዚዳንት ድሪብሳ ለገሰ፤ በኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት የግል ሠራተኞች የመነሻ ደመወዝ ወለል ሳይወሰን መቆየቱን ገልፀዋል። በአሁኑ ጊዜ ይህንን ችግር ለመፍታትና ቤተሰብን ሊያኖር የሚችል የመነሻ ደመወዝ ወለል የሚወስን ቦርድ ለማቋቋም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል። የቦርዱን ማቋቋሚያ ደንብ በተመለከተ ኮንፌዴሬሽኑ አስፈላጊውን ግብዓት መስጠቱን የጠቀሱት አቶ ድሪብሳ፤ ቦርዱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተቋቁሞ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንዲገባ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል። @Addisinsider_ETH @Addisinsider_ETH
نمایش همه...
20👍 6🤪 2
Photo unavailableShow in Telegram
በደቡብ አፍሪካ መጠጥ ቤት ውስጥ በተፈጸመ ጅምላ ጥቃት 11 ሰዎች ተያዙ እሁድ እለት በደቡብ አፍሪካ በሚገኝ መጠጥ ቤት ውስጥ 9 ሰዎች በሞቱበት የጅምላ ጥቃት 11 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።በጆሃንስበርግ አቅራቢያ በሚገኘው ቤከከርዳል  በደንበኞች ላይ የተኩስ ልውውጥ የፈጸሙትን ማንነታቸው ያልታወቁ 12 ታጣቂዎችን ፖሊስ ማደን ጀምሯል።ረቡዕ የግዛቲቱ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ሜጀር ጄኔራል ፍሬድ ኬካና እንደተናገሩት ከተያዙት ተጠርጣሪዎች መካከል ዘጠኙ የሌሴቶ ዜጎች ሲሆኑ አንደኛው የሞዛምቢክ ዜጋ ነዉ። ደቡብ አፍሪካዊ የማዕድን ሰራተኛ ነው ተብሎ የሚገመተው ሌላ ተጠርጣሪም በቁጥጥር ስር ውሏል።በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ያለው የግድያ ወንጀ፤ል በአለም ላይ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚቀመጥ ሲሆን ብዙውን ጊዜ የግጭት፣ የዘረፋ እና የቡድን ጥቃት ውጤቶች ናቸው።ጥቃቱ ከህገ-ወጥ ማዕድን ማውጫ ጦርነቶች ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል::በጥቃቱ ወቅት ሰዎች ከመጠጥ ቤቱ ሲሸሹ ታጣቂዎች መተኮሳቸውን ቀጥለዋል፣ በአቅራቢያው አንድ ተሳፋሪ ሲጎዳ አንድ የታክሲ ሹፌር ተገድሏል። በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በርካታ ፍቃድ የሌላቸው ኤኬ-47 ሽጉጥ በተጠርጣሪዎቹ እጅ ተገኝተዋል።በደቡብ አፍሪካ 3 ሚሊዮን ያህል በህጋዊ መንገድ የተያዙ ሽጉጦች እና ቢያንስ ተመሳሳይ ቁጥር ያላቸው ያልተፈቀዱ የጦር መሳሪያዎች እንዳሉ ከደቡብ አፍሪካ የወጣዉ አሀዛዊ መረጃ ያሳያል፡፡ ምንም እንኳን እ.ኤ.አ 2025 በጅምላ የተኩስ ልውውጥ እየቀነሰ ቢመጣም ከ2020 ጀምሮ አራት እና ከዚያ በላይ ሰዎች የተገደሉበት ወይም የተጎዱባቸው አጋጣሚዎች በከፍተኛ ሁኔታ ጨምረዋል ሲሉ የገን ፍሪ ደቡብ አፍሪካ የዘመቻ ቡድን ተመራማሪ ክሌር ቴይለር ተናግረዋል። በስምዖን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
12
Photo unavailableShow in Telegram
የቡና ዋጋ ቅናሽ‼️ በተያዘው የፈረንጆቹ 2025 አመት መጨረሻ ወራት ላይ የቡና ዋጋ ቅናሽ ያሳየ ሲሆን ለዋጋው ማሽቆልቆል የምርት መጨመር እንዲሁም በመጥፎ የአየር ጠባይ ምክንያት በብዛት የሚሸጡ ሀገራት በመብዛታቸው መሆኑን እንደምክንያት ተጠቅሷል፡፡ ከሳምንት በፊት የወጣው የUSDA ሪፖርት እንደሚያመለክተው የ2025/26 የዓለም የቡና ምርት ከላፈው ዓመት ምርት የ3.5 ሚሊዮን ኬሻ ብልጫ በማድረግ 178.8 ሚሊዩን ኬሻ ደርሷል፡፡ በተመሳሳይ ሪፖርት እንደተቀመጠው የፍጆታ መጠንም በተመሳሳይ ዓመት 173.9 ሚሊዮን ኬሻ እንደደረሰ ያሳል፡፡ በተያዘው 2025 መገባጃ የቡና ዋጋ ቅናሽ አሳይቷል። @Addis_Reporter @Addis_Reporter
نمایش همه...
12
Photo unavailableShow in Telegram
በኢትዮጵያ ወጥ የሆነ የመሬት ፖሊሲ አለመኖር በዜጎች የመብት ጥያቄ ላይ ተግዳሮት መፍጠሩ ተገለጸ በኢትዮጵያ 80 በመቶ የሚሆነው የህዝብ ክፍል ኑሮው ከመሬት ጋር የተቆራኘ ቢሆንም፤ በአገራችን እስካሁን ድረስ ራሱን የቻለ የመሬት ፖሊሲና አጠቃላይ የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ አለመኖሩ በምርታማነትና በዜጎች የካሳ መብት ላይ ተግዳሮት እየፈጠረ መሆኑ ተመላክቷል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህሩ ዶክተር መለሰ ዳምጤ ለጣቢያችን እንደገለጹት፤ በአገራችን የመሬት አስተዳደር ስርዓቱን የሚመራ ግልጽ ፖሊሲና የተቀናጀ ዕቅድ ባለመኖሩ ዘርፉ ለተለያዩ ችግሮች ተጋልጦ ይገኛል። ምንም እንኳን አንዳንድ ክልሎች የራሳቸውን መመሪያ ለማውጣት ቢሞክሩም፤ አፈጻጸሙ ግን አሁንም ድረስ ወጥ ያልሆነ አሰራር የተጋረጠበት መሆኑን አመልክተዋል። በተለይም በልማት ምክንያት ከመሬታቸው የሚፈናቀሉ ዜጎች የሚከፈላቸው የካሳ መጠን ሌላኛው አነጋጋሪ ጉዳይ ሆኖ ቀጥሏል ብለዋል። እንደ ዶክተር መለሰ ማብራሪያ፤ በኢትዮጵያ መሬት የመንግስት በመሆኑ፣ ካሳ የሚከፈለው በመሬቱ ላይ ለለማው ንብረት እንጂ ለመሬቱ አይደለም። ይህም ከቦታው መገኛ አኳያ ሊገኝ የሚችለውን የገበያ ዋጋና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ያላገናዘበ በመሆኑ በዜጎች ላይ ከፍተኛ ኪሳራ እያደረሰ እንደሚገኝ ተገልጿል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የካሳ ግመታው በገለልተኛ አካል ሳይሆን በመንግስት አስፈጻሚ ኮሚቴዎች ብቻ መከናወኑ፤ ለግልጽነትና ለተጠያቂነት ክፍተት መፍጠሩን የሕግ ባለሙያው ጠቁመዋል። ይህም በዜጎች ላይ የሚስተዋሉ የሕግ ጥሰቶችንና ሕገ-መንግስታዊ የመብት ጥያቄዎችን እያባባሰ ይገኛል ተብሏል። @Addis_Reporter @Addis_Reporter
نمایش همه...
17
Photo unavailableShow in Telegram
አብዛኛዎቹ ሩሲያውያን የዩክሬን ጦርነት በ2026 ያበቃል ብለው እንደሚጠብቁ አንድ ጥናት አረጋገጠ አብዛኛዎቹን ሩሲያውያን በዩክሬን ያለው ጦርነት በ2026 ያበቃል ብለው እንደሚጠብቁ የመንግስት የምርምር ማዕከል ያስታወቀ ሲሆን የሩስያ ሀይሎች በጦር ሜዳ ላይ የሚያደርጉት ግስጋሴ ቢቀጥልም በኪየቭ እና በሞስኮ መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስ ጥረቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል። ከሩሲያ ህዝብ የተሰበሰበዉ አስተያየት እንዳመላከተዉ በወጪው አመት ሩሲያውያን ጦርነቱ እንደሚያበቃ ብሩህ ተስፋ እንዳላቸዉ ተመላክቷል፡፡ ጥናቱን የሰራዉ ቪቲሲኦኤም የተሰኘዉ ማዕከል ምክትል ኃላፊ ሚካሂል ማሞኖቭ በዓመት መጨረሻ ላይ ሆነዉ እንደተናገሩ በጥናቱ ከተካሄደባቸው 1,600 ሰዎች መካከል 70 በመቶው ለሩሲያ 2026 “የተሳካ” ዓመት እንደሆነ አድርገው ይመለከታሉ ብለዋል።ለብሩህ ተስፋ ዋናው ምክንያት በፕሬዚዳንት ፑቲን ከተገለጹት ብሄራዊ ጥቅሞች ጋር በተገናኘ ልዩ ወታደራዊ ዘመቻውን ማጠናቀቅ እና የተገለጹትን ዓላማዎች ማሳካት ይቻላል የሚል ተስፋ አድርገዋል፡፡ ማሞኖቭ እንዳሉት የሩስያ ጦር በዩክሬን እያካሄደ ያለውን ጥቃት፣ ዋሽንግተን የዩክሬንን ጦርነት ለመደገፍ ፈቃደኛ አለመሆኗ እና የአውሮፓ ህብረት በዩክሬን ውስጥ የዩናይትድ ስቴትስ ሚናን ሙሉ በሙሉ ለመተካት አለመቻሉ በገንዘብ እና በወታደራዊ ድጋፍ እጥረት ጦርነቱን ለማቆም የመጨረሻው ስምምነት ከሚጠበቀው ቁልፍ ምክንያቶች በስተጀርባ ይገኛል ሲሉ ጠቁመዋል ።በግጭቱ ማጠቃለያ ላይ የሩሲያ ወታደራዊ ዘማቾችን ወደ ህብረተሰብ መመለስ እና በሩሲያ ቁጥጥር ስር ያሉ የዩክሬን ክልሎችን እንዲሁም የሩሲያ የድንበር አካባቢዎችን እንደገና መገንባት ዋና ዋና ጉዳዮች ይሆናሉ ሲሉ ማሞኖቭ አክለዋል። @Yenetube @Fikerassefa
نمایش همه...
19👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
የጥንቃቄ መልዕክት!! የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የክቡር ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዲዎን ጢሞቲዎስን ስም እና ሀሰተኛ ፊርማ በመጠቀም የሥራ እና የነጻ ትምህርት ዕድል ማረጋገጫ እና ውክልና እንደሰጡ በማስመሰል በማኀበራዊ ሚዲያ ሐሰተኛ መረጃዎች እየተሰራጩ እንደሚገኙ ለመረዳት ችለናል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ክቡር ሚኒስትሩ የሥራ እና የነጻ ትምህርት ዕድልን በተመለከተ ለማናቸውም አካል ውክልና እንዳልተሰጠ ታውቆ ኀብረተሰቡ ከእንዲህ አይነቶቹ ሕገወጥ የማጭበርበር እና የማታለል ወንጀሎች ራሱን እንዲጠብቅ እያሳሰበ :በሚኒስቴሩም ሆነ በክቡር ሚኒስትሩ ስም የሚያጭበረብሩ ሕገ ወጦችን ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን የሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ለማድረግ እየሠራ መሆኑን ማስገንዘብ ይወዳል። @ethio_mereja_news @ethio_mereja_news
نمایش همه...
14🤣 3👏 2
Photo unavailableShow in Telegram
አብዛኛዎቹ ሩሲያውያን የዩክሬን ጦርነት በ2026 ያበቃል ብለው እንደሚጠብቁ አንድ ጥናት አረጋገጠ አብዛኛዎቹን ሩሲያውያን በዩክሬን ያለው ጦርነት በ2026 ያበቃል ብለው እንደሚጠብቁ የመንግስት የምርምር ማዕከል ያስታወቀ ሲሆን የሩስያ ሀይሎች በጦር ሜዳ ላይ የሚያደርጉት ግስጋሴ ቢቀጥልም በኪየቭ እና በሞስኮ መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስ ጥረቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል። ከሩሲያ ህዝብ የተሰበሰበዉ አስተያየት እንዳመላከተዉ በወጪው አመት ሩሲያውያን ጦርነቱ እንደሚያበቃ ብሩህ ተስፋ እንዳላቸዉ ተመላክቷል፡፡ ጥናቱን የሰራዉ ቪቲሲኦኤም የተሰኘዉ ማዕከል ምክትል ኃላፊ ሚካሂል ማሞኖቭ በዓመት መጨረሻ ላይ ሆነዉ እንደተናገሩ በጥናቱ ከተካሄደባቸው 1,600 ሰዎች መካከል 70 በመቶው ለሩሲያ 2026 “የተሳካ” ዓመት እንደሆነ አድርገው ይመለከታሉ ብለዋል።ለብሩህ ተስፋ ዋናው ምክንያት በፕሬዚዳንት ፑቲን ከተገለጹት ብሄራዊ ጥቅሞች ጋር በተገናኘ ልዩ ወታደራዊ ዘመቻውን ማጠናቀቅ እና የተገለጹትን ዓላማዎች ማሳካት ይቻላል የሚል ተስፋ አድርገዋል፡፡ ማሞኖቭ እንዳሉት የሩስያ ጦር በዩክሬን እያካሄደ ያለውን ጥቃት፣ ዋሽንግተን የዩክሬንን ጦርነት ለመደገፍ ፈቃደኛ አለመሆኗ እና የአውሮፓ ህብረት በዩክሬን ውስጥ የዩናይትድ ስቴትስ ሚናን ሙሉ በሙሉ ለመተካት አለመቻሉ በገንዘብ እና በወታደራዊ ድጋፍ እጥረት ጦርነቱን ለማቆም የመጨረሻው ስምምነት ከሚጠበቀው ቁልፍ ምክንያቶች በስተጀርባ ይገኛል ሲሉ ጠቁመዋል ።በግጭቱ ማጠቃለያ ላይ የሩሲያ ወታደራዊ ዘማቾችን ወደ ህብረተሰብ መመለስ እና በሩሲያ ቁጥጥር ስር ያሉ የዩክሬን ክልሎችን እንዲሁም የሩሲያ የድንበር አካባቢዎችን እንደገና መገንባት ዋና ዋና ጉዳዮች ይሆናሉ ሲሉ ማሞኖቭ አክለዋል። ዳጉ_ጆርናል @Addis_News @Addis_News
نمایش همه...
00:42
Video unavailableShow in Telegram
13.58 MB
86🤣 6
01:08
Video unavailableShow in Telegram
👉 ከ8 በላይ ሳይቶችን ገንብቶ ያስረከበው ቴምር ፕሮፐርቲ አሁንም በድጋሜ አዳዲስ ሳይቶችን ለሽያጭ አቅርቧል ። 📍 ሳር ቤት #በ35%ቅናሽ! (በ100% ክፍያ) 👉 ባለ 2 መኝታ = 81ካሬ = 5.7ሚ 👉 ባለ 2 መኝታ = 106ካሬ = 7.9ሚ 👉 ባለ 3 መኝታ = 139ካሬ = 10.3ሚ 👉 ባለ 3 መኝታ = 153ካሬ = 11.4ሚ #በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ) 👉 81ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 9.3ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (1.8ሚሊዮን) 👉 106ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 12.1ሚ                  ቅድመ ክፍያ = 20% (2.4ሚሊዮን) 👉 139ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 15.9ሚ                  ቅድመ ክፍያ = 20% (3.1ሚሊዮን) 📍 አዋሬ #በ35%ቅናሽ! (በ100% ክፍያ) 👉 ባለ 1 መኝታ = 78ካሬ = 5.5ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 117ካሬ = 8.3ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 137ካሬ = 9.7ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 145ካሬ = 10.3ሚሊዮን #በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ) 👉 78ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 8.5ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (1.7ሚሊዮን) 👉 135ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 14.8ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (2.9ሚሊዮን) 👉 157ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 17.2ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (3.4ሚሊዮን) ⩩ ቀሪውን 80%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት። ⩩ 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፤ ከከፈሉት ላይ ከ15 -25% ቅናሽ አዘጋጅተናል። ለበለጠ መረጃ ;- 0940464607 0994003949
نمایش همه...
25.16 MB
ግብፅ በአሰብና ጅቡቲ ወደቦችን ለመገንባት ስምምነት ላይ መድረሷ ተገለፀ፡፡ ዘናሽናል ጋዜጣ ዛሬ እንደዘገበው ግብፅ የአፍሪካ ቀንድ አካል ከሆኑት ኤርትራና ጅቡቲ ጋር ወደቦችን ለመገንባት ስምምነት ፈፅማለች፡፡ እንደዘገባው ይህ ስምምነት ግብፅ በአባይ ወንዝ ጉዳይ በገባችበት ውዝግብ በኢትዮጵያ ላይ እያካሄደች ያለው ጫና አንዱ አካል ነው፡፡ ቅርበት ያላቸው ምንጮቹን በዋቢነት የጠቀሰው ዘገባው ግብፅ እንብዛም የሚዲያ ሽፋን ባልተሰጠውና ባልተወራለት መንገድ ከሁለቱ አገራት ጋር የፈፀመችው የስምምነት ፊርማ የኤርትራውን አሰብ ወደብንና የጅቡቲውን ዶራሌ ወደብ ‹‹አቅም ማሳደግ›› የሚል መሆኑን አስረድቷል፡ ፡ ሁለቱም ወደቦች በቀይ ባህር ደቡባዊ ክፍል ባብ አልመንደብ ሰርጥ አቅራቢያ የሚገኙ መሆናቸውን የጠቀሰው ዘገባው ጅቡቲና ኤርትራ የኢትዮጵያ ጎረቤቶች ከመሆናቸውም በላይ ኢትዮጵያ ሸቀጦችን የምታስገባው በዶራሌ ወደብ መሆኑን አውስቷል፡፡ ዘገባው ሲቀጥልም ‹‹ግብፅ በቀይ ባህር ላይ ከ2 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ ጠረፍ ያላትና ቀይባህርንና ሜዲትራኒያንን የሚያገናኘውን ስዊዝ ካናል የተቆጣጠረች አገር ናት›› ካለ በኋላ በተደጋጋሚ እንደኢትዮጵያ ያሉ የባህር በር የሌላቸው አገራት ወደቀይ ባህር ለመዳረስ የሚያደርጉትን ጥረት ስትቃወም መቆየቷን አስረድቷል፡፡ ዘናሽናል በዘገባው ይህ ብዙ ያልተወራለት ስምምነት ከኤርትራ ጋር የተፈፀመው ከአንድ ወር በፊት ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በካይሮ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት መሆኑን አስታውቆ፣ ግብፅና ጅቡቲ ግን በከፍተኛ ባለስልጣናት መካከል መፈራረማቸውን አስረድቷል፡፡ እነዚህ ስምምነቶች ከሁለቱም አገራት ጋር ጠንካራ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ግንኙነት የመሰረተችው ግብፅ በወደቦቹ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንድታደርግ የሚያስችላት እንደሚሆንም ገልጿል፡፡ የዘገባው ምንጭ ሲናገሩ ‹‹ይህ ስምምነት በሁለቱ ወደቦች ላይ እያደረግነው ያለውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ህጋዊ መሰረት እንዲኖረው ያስችለናል›› ማለታውንም ከጋዜጣው ላይ ተመልክተናል፡፡ @Addis_News @Addis_News
نمایش همه...
17😢 10🤪 7🔥 4
Photo unavailableShow in Telegram
​በዲጂታል የክፍያ ተቋማት ላይ ተጥሎ የነበረው የባንክ እገዳ በከፊል ተነሳ‼️ - ከፍተኛ የንግድ ድርጅቶች ኃላፊዎች አሁንም በቁጥጥር ሥር ናቸው የፌዴራል ባለሥልጣናት በዲጂታል ፋይናንስ ዘርፍ ላይ በወሰዱት እርምጃ ታግደው የነበሩ የባንክ ሂሳቦችን በከፊል አንስተዋል። ​የፍትህ ሚኒስቴር ታኅሣሥ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ባስተላለፈው ትዕዛዝ፣ የያጉት ፔይ (YagoutPay) ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተሾመ ዓለማየሁን ጨምሮ የ50 ግለሰቦች የባንክ ሂሳቦች እንዲንቀሳቀሱ አዟል። እነዚህ የባንክ ሂሳቦች ከሦስት ሳምንታት በፊት፣ ህዳር 23 ቀን፣ በዘርፉ የታየ የፋይናንስ ብልሹ አሰራርን ለመመርመር በሚል ታግደው የቆዩ ናቸው። ​በተጨማሪም፣ ለዘጠኝ ቀናት የባንክ ሂሳቦቻቸው ተገድበው የነበሩ 10 የዲጂታል ክፍያ (Gateway) ኩባንያዎች እገዳው ተነስቶላቸዋል። የሚኒስቴሩ የሀብት ማስመለስ መምሪያ ዋና ዳይሬክተር ፀጋ ዋቅጅራ ውሳኔውን ለሁሉም ባንኮች በይፋዊ ደብዳቤ አሳውቀዋል። ​እገዳው የተነሳላቸው የክፍያ ተቋማት ​አሪፍ ፔይ (ArifPay Financial Technologies): ​አዲስ ፔይ (AddisPay Financial Technologies): ​ፈናን ፔይ (FenanPay Solutions): ​ላኪ ፔይ (LakiPay Financial Technologies): ​ስታር ፔይ (StarPay Financial Services): ​ያጉት ፔይ (YagoutPay) ​ሳንቲም ፔይ (SantimPay Financial Technologies): ​ካቻ (Kacha Financial Technology): እና ​ሲናን ፔይ (Sinan Pay Solutions) ናቸው:: ​ምንም እንኳን የኩባንያዎቹ የባንክ ሂሳቦች ቢለቀቁም፣ የምርመራው ሂደት ግን ተጠናክሮ ቀጥሏል። የሳንቲም ፔይ፣ የቻፓ ፔይ (Chapa Pay) እና የአሪፍ ፔይ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አሁንም በፌዴራል ፖሊስ ቁጥጥር ሥር የሚገኙ ሲሆን፣ “ከፍተኛ የፋይናንስ ሕገ-ወጥነት” ተጠርጥረው ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው። ​ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንደጠቆሙት፣ የምርመራው ዋነኛ ትኩረት የግብር ስወራ እና ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር (Money Laundering) ላይ ነው። የፌዴራል ባለሥልጣናት በፍጥነት እያደገ የመጣውን የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ጥብቅ ቁጥጥር ለማድረግና ሕጋዊ መስመር ለማስያዝ ቅድሚያ ሰጥተው መስራት እንደሚፈልጉ ይናገራሉ። @Addis_News @Addis_News
نمایش همه...
14😢 2
ፕሬዝደንት ጣሂብ ኤርዶጋን እስራኤል “ቃሏን አላከበረችም” ሲሉ ወቀሱ የቱርኩ ፕሬዝደንት ረሲብ ጣሂብ ኤርዶጋን “እስራኤል የገባችውን ቃል አላከበረችም፤ ሰብዓዊ እርዳታ ወደጋዛ እንዳይደርስ ሆን ብላ እንቅፋት እየፈጠረች ነው” ሲሉ እስራኤልን ወቅሰዋል። ፕሬዚዳንት ኤርዶጋን ይህን ያሉት ትናንት ረቡዕ እርሳቸው የሚመሩት የፍትሕና ዕድገት ፓርቲ የግዛት አስተዳዳሪዎች ስብሰባ በአንካረ በተካሄደበት ወቅት ሲሆን፤ “እስራኤል የገባችውን ቃል እያከበረች አይደለም፤ የተፈበረኩ ማስተባበያዎችን በማቅረብ ሰብዓዊ እርዳታ ወደጋዛ እንዳይገባ ሆን ብላ ችግር እየፈጠረች፤ የሰብዓዊ እርዳታ ሂደቱንም በተደጋጋሚ እያስተጓጎለች ነው” ሲሉ እስራኤልን ወንጅለዋል። “በእነዚህ አስደሳች ሦስት ወራት ለፍልስጤም የምናደርገውን ድጋፍ አጠናክረን እንቀጥላለን፤ እንደቱርክ የገባነውን ቃል አናጥፍም፤ ዝም አንልም፤ አንረሳትም፤ መቼም ቢሆን ጋዛን ብቻዋን አንተዋትም” ሲሉም አክለዋል። “ከካውካስ እስከ ባልካን፣ ከአፍሪካ እስከ እስያ፣ ማንም ቢሆን በችግር ላይ ሆኖ እርዳታ በሚፈልግበት ጊዜ እኛ ቀድመን እዚያ እንገኛለን። ይህ ትናንት የነበረ፤ ዛሬም ያለ ነገም የማይቀየር የእኛ አቋም ነው” ያሉት ፕሬዚዳንት ኤርዶጋን ቱርክ ለፍልስጤም የምታደርገው ድጋፍ ሀገሪቱ በዓለም አቀፉ ደረጃ የምታራምደው የሰብዓዊ እርዳታ ፖሊሲዋ አንድ አካል መሆኑንም አመልክተዋል። ቱርክ ሰላምን የምትደግፍ ብትሆንም ኢ-ፍትሐዊነትን ግን እንደማትቀበልም ፕሬዚዳንት ኤርዶጋን አጽንኦት ሰጥተውበታል። “ጥንት እንደምናደርገው ሁሉ ዛሬም ለሰላም ያለንን ፍላጎት ሁሉም ሊያውቀው ይገባል። ይህ ማለት ግን ከኢ-ፍትሐዊነት ጋር እናብራለን፤ ጭቆናንም እንታገሳለን ማለት አይደለም፤ ይህን ፈጽመን አናደርገውም” ሲሉም አቋማቸውን አስረግጠዋል። Addis maleda @Addis_News @Addis_News
نمایش همه...
18🤣 6😨 1
Photo unavailableShow in Telegram
Ethio-Telecom Jobs 2025 ✅ ---—----------------------------      ♨️ እንኳን ደስ አላችሁ ለመላው ለስራ ፈላጊ ኢትዮጲያዊያን! ✅ ከ 600- በላይ ክፍት ቦታዎች በ0 አመት  እና በልምድ ✅ Number of Positions: 600+     ✅positions 0 EXP and with Exp 🔺የትምህርት ደረጃ: በሁሉም የትምህርት ደረጃ 🔺የትምህርት አይነት: በተለያዩ ዲፓርትመንቶች 🔺ቦታ: በተለያዩ የኢትዮጲያ ከተማዎች 🔺የስራ ልምድ: በ 0 ዓመትና በልምድ 🔺 የቅጥር ሁኔታ: በቋሚ ቅጥር 🔺 ብዛት: 600+ በላይ 🔺ደሞዝ:  ማራኪ 🟥 ፈጥነው ታች ባለው ሊንክ ይመዝገቡ ⁉️ማሳሰቢያ:- VPN ወይም Psiphon መጠቀም ይኖርባችሗል 👇👇👇👇👇Apply Now👇👇👇👇👇👇                         👇👇👇👇          https://reportervacancy.com/ethiotelecom-job-vacancy-2025-apply-now/ --------Follow Our Website--------                      👇👇👇👇👇👇          https://reportervacancy.com --------Join Our Telegram---------                      👇👇👇👇👇     https://t.me/reporter_Vacancy
نمایش همه...
1
የአባቴን ንብረት ይወርሳል በሚል ቅናት የእህቱን ልጅ ገድሎ ጫት እርሻ ውስጥ የቀበረው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ደደር ወረዳ ነዎሪነታቸው የሆኑት አቶ አህመድ ሙነር   የሰባ ሶስት አመት አዛዉንት ሲሆኑ በትዳር ህይወታቸውም  አንድ ወንድ እና ሴት ልጅ አፍረተዋል።የህግ ባለቤታቸው  በህመም ምክንያት በሞት ሲያጡ  ልጆቻቸውን ብቻቸውን ማሳደጋቸው  የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ፖሊስ ዋና መምርያ የኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ካሲዬ አበበ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።አቶ አህመድ  ሙነር ልጆቻቸውን በዚህ መልክ እያሳደጉ እያለ ሴት ልጃቸው ከጋብቻ ውጭ ታረግዝና ዘመዶች ጋር በድብቅ ወልዳ ታርሳ እንደመጣችም ተነግሯል። የተወለደው ልጅ አያት ተቀብለው  የአባት መጠሪያ ስምን በራሳቸው አድርገው  ፈንዲሼ አህመድ እዚያው ቤተሰብ ማደግ ጀምሯል። ከዓመታት በኋላ ግን የአቶ አህመድ ሴት ልጅ ለጋብቻ ትታጭ እና በሰርግ ድግስ  ትዳር መስርታ ከአባቷ ቤት ትወጣለች። ወንድሟ ኤልያስ ግን በተለይ አባት ያላቸውን ንብረት እና ሀብት የሚካፈሉት እህቱ እና ልጇ መሆኑን ሲረዳ የአስራ አምስት ዓመቱን ወንድሙን የእህቱን ልጅ አምርሮ ጠላው።ታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም  አባቱን እና  ወንድሙን ስራ ፍለጋ ወደ ከተማ እንደሚሄድ ነግሯቸው ከቤት ወጥቶ ይሄዳል። ከሳምንታት በኋላ ግን ስራ በመጥፋቱ ወደ አያቱ ቤት እየተመለሰ ያለው ፈንድሼ አህመድን ኤልያስ አህመድ ጠብቆ በስለታም ሳንጃ የተለያዪ የሰውነት ክፍሎችን በመውጋት ህይወቱ እንዲያልፍ አድርጎ አስክሬኑን ደብቆ ካዋለው በኋላ በነጋታው የአያቱ የጫት እርሻ ውስጥ በድብቅ ቀብሮ ሰላማዊ ሰው ሆኖ ይቀመጣል።ከበርካታ ወራት ቡኃላ የፈንዲሻ ለስራ ፍለጋ ከቤት ወጥቶ መቅረት ያሳሰባቸው አባት በተለያየ ጊዚያት ሲያፈላልጉ እሱን የሚያዉቁ ሰዎች  ስራ በመጥፋቱ ተመልሶ ወደ ቤቱ እንደተመለሰ ቢገልጹም አድራሻው ሊገኝ አልቻለም ።ይሁን እንጂ በኤልያስ እና በፈንዲሼ መካከል ያለው የመጠላላት ስሜት እንዲሁም ስለመጥፋቱ ሲነሳ የሚሰጠው ተቃራኒ መልስ አያት በልጃቸው ላይ ጥርጣሬ እንዲያሳድሩ አድርጓል። በዚህም አባት ልጃቸው ኤልያስን በአካባቢው ባለው የሀገር ሽማግሌዎች የአውጫጭኝ ስርዓት ላይ እንዲቀርብ ሲጠየቅ ፈቃደኛ ያለመሆን አዝማምያ ሲያሳይ ጉዳዩን ፖሊስ ጋር እንዲደርስ ተደረገ። የደደር ወረዳ ፖሊስም በቀረበው መረጃ መሰረት ኤልያስ መሀመድን በቁጥጥር ስር አድርጎ ሲመረምር  ኤልያስ ከአባቴ ያልተወለደው ልጅ ከእናቱ ጋር ሆኖ የአባቴን ንብረት ይወርሳል በሚል ቅናት ስራ እፈልጋለሁ ካለበት ቦታ ከሳምንት በኋላ ሲመለስ ጠብቄ ገድዬ የጫት እርሻው ስጥ ቀብርያለሁኝ በማለት የእምነት ቃሉን ይሰጣል።በተጨማሪም ለወራት በጫት እርሻ ውስጥ የተቀበረው የ15 ዓመቱ ኤልያስ አህመድ አስክሬን ከተቀበረበት ተቆፍሮ በመውጣት ለምርመራ ወደ ሆስፒታል ተልኮ ከተመረመረ በኋላ በክብር እንዲያርፍ ተደርጓል ሲሉ ምክትል ኢንስፔክተር ካስዬ አበበ ገልፀዋል።ፖሊስም የምርመራ መዝገቡን በአስክሬን ምርመራና በእምነት ቃሉ እንዲሁም የወንጀል ድርጊቱን ሲመራ በነበሩ ማስረጃዎች ተጠናክሮ ለአቃቢ ህግ ልኳል፡፡ አቃቢ ህግም ከፖሊስ የቀረበውን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ በከባድ የሰው መግደል ወንጀል ክስ መስርቷል።  ክሱን ሲከታተል የቆየው የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ታህሳስ 9 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ኤሊያስ አህመድ በእድሜ ልክ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል። Dagu @Addis_News @Addis_News
نمایش همه...
15👍 5😢 5