ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ)
Ir al canal en Telegram
በዚህ ቻናል ዲ/ዮርዳኖስ የሚያስተምራቸው ወቅታዊ እና የነገረ ቅዱሳን (ዝክረ ቅዱሳን ትምህርቶችን ከእርሱ በመቀበል እናስተላልፋለን):: "ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
Mostrar más2025 año en números

50 489
Suscriptores
+1024 horas
+37 días
+11030 días
Archivo de publicaciones
††† ኅዳር 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1."24ቱ" ቅዱሳን ካህናተ ሰማይ (ሱራፌል)
2.ቅዱስ አዝቂር ሰማዕት
3."48" ሰማዕታት (ማሕበሩ)
4.አባ ዮሴፍ ዘሃገረ ጻን
5.ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ጥዑመ ዜና
6.ቅዱስ ኪርያቅ ሰማዕት††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት (መምሕረ ትሩፋት)
2.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ
3.አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ ዘክብራን
4.ቅዱስ አጋቢጦስ (ጻድቅ ኤጲስቆጶስ)
5.ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ
6.ቅዱስ አባ ሙሴ ጸሊም (ኢትዮጵያዊ)
7.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
††† "በዙፋኑ ዙሪያም ሃያ አራት ዙፋኖች ነበሩ:: በዙፋኖቹም ላይ ነጭ ልብስ ለብሰው: በራሳቸውም የወርቅ አክሊል ደፍተው ሃያ አራት ሽማግሌዎች ተቀምጠው ነበር:: ከዙፋኑም መብረቅና ድምጽ: ነጐድጓድም ይወጣል:: በዙፋኑም ፊት ሰባት የእሳት መብራቶች ይበሩ ነበር:: እነርሱም ሰባቱ የእግዚአብሔር መናፍስት ናቸው::" †††
(ራዕይ ፬፥፬)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
https://t.me/zikirekdusn
††† ❇️እንኳን ለ24ቱ ቅዱሳን ካህናተ ሰማይ እና ቅዱስ አዝቂር ሰማዕት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††
†††✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††✝
††† ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ †††
††† እግዚአብሔር ቅዱሳን መላእክትን ሲፈጥራቸው በነገድ መቶ (100): በክፍለ ነገድ አሥር (10) አድርጓቸዋል:: አቀማመጣቸውንም በሦስት ሰማያትና በ10 ከተሞች (ዓለማት) አድርጓል::
††† መላእክት ያሉባቸው ከተሞች ከታች ወደ ላይ "ኤረር: ራማና ኢዮር" ይባላሉ:: አሥሩ ክፍለ ነገድ ደግሞ ከነ አለቆቻቸው ይህንን ይመስላሉ:-
1."አጋእዝት" (የቀድሞ አለቃቸው ሳጥናኤል: አሁን የተረፉት በቅዱስ ሚካኤል ሥር ናቸው)
2."ኪሩቤል" (አለቃቸው ኪሩብ)
3."ሱራፌል" (አለቃቸው ሱራፊ)
4."ኃይላት" (አለቃቸው ሚካኤል)
5."አርባብ" (አለቃቸው ገብርኤል)
6."መናብርት" (አለቃቸው ሩፋኤል)
7."ስልጣናት" (አለቃቸው ሱርያል)
8."መኳንንት" (አለቃቸው ሰዳካኤል)
9."ሊቃናት" (አለቃቸው ሰላታኤል)
10."መላእክት" (አለቃቸው አናንኤል) ናቸው::
††† ከእነዚህም:-
*አጋእዝት: *ኪሩቤል *ሱራፌልና *ኃይላት መኖሪያቸው በኢዮር (በ3ኛው ሰማይ) ነው::
*አርባብ: *መናብርትና *ስልጣናት ቤታቸው ራማ (2ኛው ሰማይ) ነው::
*መኳንንት: *ሊቃናትና *መላእክት ደግሞ የሚኖሩት በኤረር (በ1ኛው) ሰማይ ነው::
መላእክት ተፈጥሯቸው እምኀበ አልቦ ኀበ ቦ ነው:: አይራቡም: አይጠሙም: አይዋለዱም: አይሞቱም:: ተፈጥሯቸውም ረቂቅ ነው:: ተግባራቸውም ዘወትር "ቅዱስ: ቅዱስ: ቅዱስ" እያሉ ፈጣሪያቸውን ማመስገን ነው:: ምግባቸውም ይሔው ነው::
ዕረፍት ብሎ ነገርን አያውቁም:: "አኮቴቶሙ ዕረፍቶሙ: ወዕረፍቶሙ አኮቴቶሙ" እንዲል:: በተጨማሪም መልአክ ማለት ተላላኪ (አገልጋይ) ነውና ከፈጣሪ ወደ ሰው ልጆች ለምሕረትም: ለመዓትም ይላካሉ::
ምሕረትን ያወርዳሉ:: ልመናን ያሳርጋሉ:: ቅጡ ሲባሉም ይቀጣሉ:: ስነ ፍጥረት (አራቱ ወቅቶች) እንዳይዛቡ ይጠብቃሉ::
*ዘወትርም ስለ ሰው ልጆች ያማልዳሉ:: (ዘካ. 1:12)
*ምሥጢርን ይገልጣሉ:: (ዳን. 9:21)
*ይረዳሉ:: (ኢያ. 5:13)
*እንዳንሰናከል ይጠብቃሉ:: (መዝ. 90:11)
*ያድናሉ:: (መዝ. 33:7)
*ስግደት ይገባቸዋል:: (መሳ. 13:20, ኢያ. 5:13, ራዕ. 22:8)
*በፍርድ ቀንም ኃጥአንን ከጻድቃን ይለያሉ:: (ማቴ. 25:31)
*በአጠቃላይ ለሰው ልጆች ሕይወትና ድኅነት ሲባል ከፈጣሪያቸው የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ሲጠብቁና ፈቃዱን ሲፈጽሙ ይኖራሉ::
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዚህች ዕለት የሃያ አራቱን ቅዱሳን ካህናተ ሰማይን መታሰቢያ ታደርጋለች:: እኒህ ቅዱሳን መላእክት በነገድ 10 ሲሆኑ መጠሪያቸው "ሱራፌል" : መኖሪያቸውም በኢዮር ነው:: ነገር ግን ሃያ አራቱ አለቆቻቸው ተመርጠው በመሪያቸው በቅዱስ ሱራፊ አለቅነት በጽርሐ አርያም ያገለግላሉ::
በቀናች ሃይማኖት ትምሕርት ሁሉም ቅዱሳን መላእክት ለእግዚአብሔር ቅርብ ቢሆኑም: በነጠላ የቅዱስ ሚካኤልን ያህል: በነገድ ደግሞ የኪሩቤል (አራቱ እንስሳ) እና የሱራፌልን (ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ) ያህል ቅርብ የለም::
††† ሃያ አራቱ ቅዱሳን ካህናት ሥራቸው:-
1.እንደ ሞገድ ከአንደበታቸው ምስጋና እየወጣ: ጧት ማታ ፈጣሪያቸውን ይቀድሱታል:: (ኢሳ. 6:1, ራዕይ 4:11, 5:11)
2.የሥላሴን መንበር ያለ ማቋረጥ ያጥናሉ:: (ራዕይ 5:8)
3.የሰው ልጆችን: በተለይም የቅዱሳንን ጸሎት በማዕጠንታቸው ያሳርጋሉ:: (ራዕይ 8:3)
4.የረከሱትን ይቀድሳሉ:: (ኢሳ. 6:6)
5.ዘወትርም ለሰው ልጆች ምሕረትን ሲለምኑ ይኖራሉ:: (ዘካ. 1:12)
ስለ እነዚህ ቅዱሳን ካህናት (ሱራፌል) ታላቁ ቅዱስ መጽሐፍ ብዙ ይላል:: ለምሳሌ:- ዐቢይ ነቢይ ወልዑለ ቃል ኢሳይያስ ፈጣሪው ተቀይሞት በነበረበትና ዖዝያን በሞተበት ወራት: ግሩማን ሆነው ሥላሴን "ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ" እያሉ ዙሪያውን ከበው ሲያመሰግኑ ሰምቷል::
ከእነርሱም አንዱ (ሱራፊ) መጥቶ በጉጠት እሳት ከንፈሩን ዳስሶ ከለምጹ አንጽቶታል:: (ኢሳ. 6:1) አቡቀለምሲስ የተባለ ቅዱስ ዮሐንስም በራዕዩ በግርማ: በአምሳለ አረጋዊ ተመልክቷቸዋል:: (ራዕይ 4:4)
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫን የመሰሉ ቅዱሳን ሊቃውንት ደግሞ በጣዕመ ምስጋናቸው ሲገልጿቸው:-
"ካህናተ ሰማይ ቅውማን በዐውዱ::
አክሊላቲሆሙ ያወርዱ::
ቅድመ መንበሩ እንዘ ይሰግዱ::
ይርዕዱ::
ከመ ኢይዝብጦሙ ሶበ ይበርቅ ነዱ::" ብለዋል:: (መጽሐፈ ሰዓታት)
ትርጉሙም "በፈጣሪ መንበር ዙሪያ የሚቆሙ የሰማይ ካህናት አክሊለ ክብራቸውን አውርደው በመንበሩ ፊት ይሰግዳሉ:: መብረቀ መለኮቱ በተገለጠ ጊዜም በፍርሃት ይንቀጠቀጣሉ::" ነው:: ግሩም ባሕርየ ሥላሴን ሊቋቋመው የሚችል ፍጡር የለምና::
ቅዱሳን ካህናተ ሰማይ በምስጋናቸው: በማዕጠንታቸውና በምልጃቸው ክቡራን ናቸውና ዘወትር ልናከብራቸው ይገባናል:: የረከሰ ማንነታችንን ይቀድሱ ዘንድ: በምልጃቸውም ዘንድ እንድንታሰብ: ጸሎታችንንም ያሳርጉልን ዘንድ እንለምናቸው::
††† ኅዳር 24 ቀን ዓመታዊ በዓላቸው ነው ማለት በየወሩ በ24 ወርኀዊ በዓላቸው መሆኑን ያሳያልና ዘወትር ልናስባቸው ይገባል::
በተለይ ያዘነን ልብ ደስ ያሰኛሉና እንደ ሊቃውንት እንዲህ ብለን እንጠራቸዋለን::
"ሰላም ለክሙ ካህናተ ሕጉ ወትዕዛዙ::
ለእግዚአብሔር ቃል ዘጶዴሬ ሥጋ አራዙ::
እምነቅዐ አፉክሙ ሐሴት ዘኢይነጽፍ ዉሒዙ::
ኪያየ ኅዙነ ወትኩዘ ልብ ናዝዙ::
ወበክንፍክሙ ብርሃናዊ ዐውድየ ሐውዙ::" (አርኬ ዘኅዳር 24)
††† ቅዱስ አዝቂር ካህን †††
††† ከዜና ካህናት ወደ ዜና ካህናት እንለፍ:: ቅዱስ አዝቂርን የመሰሉ ካህናት ምንም ሥጋ ለባሽ ቢሆኑም ሥልጣናቸውና ግብራቸው ሰማያዊ ነውና መላእክትን ይመስላሉ:: አንድም በስልጣናቸው ከመላእክት ይበልጣሉ::
"ካህናትየ ይቤሎሙ::
ወእምኩሉ ፈድፋደ አክበሮሙ::
ዘኢተገብረ ለመላእክት ተገብረ ለካህናት::"
ትርጉም "አገልጋዮቼ አላቸው::
ከሁሉ በላይ አከበራቸው::
ለመላእክት ያልተደረገ ለካህናት ተደረገ::" እንዳለ ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ:: (መጽሐፈ ቅዳሴ)
ቅዱስ አዝቂርም የናግራን (አሁን የመን) ክርስቲያን ሲሆን በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን በንጹሕ የክህነት አገልግሎቱ ሰውንም: ክርስቶስንም ደስ ያሰኘ አባት ነው:: አሕዛብን: አረማውያንን ሁሉ ድል ነስቶ መንጋውን ጠብቋል:: በቁጥርም አብዝቷል::
ገርፈው ቢያስሩት በቃሉ ስልጣን የብረት በሮችን ከፍቶ አሕዛብን ሲያጠምቅ ተገኝቷል:: ሊገድሉት ሲወስዱት በየመንገዱ ይሰብክ ነበር:: ገዳዮቹ በርሃ ላይ ውኃ ጥም እንዳይገድላቸውም በአንዲት ገበታ ላይ ዝናም አዝንሞ 700 ወታደሮች ከነ ፈረሶቻቸው አጥግቧል::
በመጨረሻም አይሁድ በድንጋይ ሲወግሩት ድንጋዮቹ እየተመለሱ አናት አናታቸውን ብሏቸዋል:: ያን ጊዜ በብስጭት አንገቱን ቆርጠውታል:: አብረውም ቅዱስ ኪርያቅ ወዳጁንና 48 ተከታዮቹን ሰይፈዋል::
††† አምላከ ቅዱሳን ካህናተ ሰማይ ከምስጋናቸው ሐሴትን: ከማዕጠንታቸው በጐ መዓዛን ያውርድልን:: በረከታቸውንም ያብዛልን::
Photo unavailableShow in Telegram
✝እንኳን አደረሳችኹ
""ከእግዚአብሔር ዘንድ ወሬ ሰምተናል መልእክተኛ ወደ አሕዛብ ተልኮ፦ተነሡ በላይዋም በሰልፍ እንነሣ ብሏል።እንሆ በአሕዛብ ዘንድ ታናሽ አድርጌሃለሁ አንተ እጅግ ተንቀሃል።""
(አብድዩ ፩:፩)
<<ኅዳር 23 የቅዱስ አብድዩ ዕረፍቱ ነው በረከቱ ይድረሰን።>>
Cornelius reached and called upon him. And because the Holy Spirit had instructed the Apostle, “Go with them,” he went with the servants.
✞And when he reached to Cornelius, both discussed their 2 revelations. And Cornelius bowed down to the Arch-apostle. However, for humility, St. Peter said, “Do not bow for me.” Thereafter, he opened his mouth and thought the Holy Word to Cornelius and his family. And after he baptized them, by the laying on of his hands they received the gifts of the Holy Spirit.
✞And after that day, St. Cornelius shunning his wealth, property, rank and honor followed the Apostles. And holding only one stick he went to serve in the land of Egypt (some say to Caesarea of Palestine). And there, he attracted many to Christianity, struggled for years and departed on this day.
✞✞✞Saint Obadiah the Prophet✞✞✞
=>Obadiah means “Servant of God". And he is counted with the 12 Minor Prophets and was the disciple of St. Elijah the Great. The Saints Jonah and Elisha, who also were prophets, were his acquaintances.
✞St. Obadiah had served as the third captain of the apostate king’s (Ahab’s) army around 800 years before the birth of Christ. When the tyrant, Jezebel, slaughtered the prophets of Israel, he saved 50 in one cave and 50 in another. However, 900 were killed.
✞He had also fed the ones he rescued until that malicious time passed. And after Ahab and Jezebel died, he left his office and followed St. Elijah. And he lived prophesizing what God revealed to him and rebuking the people.
✞This Prophet is the one who wrote the shortest book of prophecy in the Old Testament, Obadiah (The Prophecy of Obadiah), which has only one chapter. The Saint passed away on this day and his kinfolk buried him.
✞✞✞May the God of the Prophets and the Apostles bring for us an era of blessing and peace. And may He grant us from their blessings.
✞✞✞ Annual feasts celebrated on the 23rd of Hedar
1. Saint Cornelius the Centurion (Apostle and Righteous)
2. Saint Obadiah the Prophet
✞✞✞ Monthly Feasts
1. St. David (a man after God’s own heart/will)
2. St. George Arch-Martyr
3. The Righteous St. Solomon (King of Israel)
4. Abba Timothy, the Anchorite
5. St. Daniel the Prophet
6. Abba Samuel
7. Abba Simon
8. Abba Gabriel
✞✞✞“The pride of thine heart hath deceived thee, thou that dwellest in the clefts of the rock, whose habitation is high; that saith in his heart, Who shall bring me down to the ground? Though thou exalt thyself as the eagle, and though thou set thy nest among the stars, thence will I bring thee down, saith the Lord.”✞✞✞
Obad. 1:3-4
✞✞✞ Salutations to God ✞✞✞
(Translated by Mhr. Esuendale Shemeles with the permission of Dn. Yordanos Abebe)
#Feasts of #Hedar_23
✞✞✞On this day we commemorate Saint Cornelius the Centurion and Saint Obadiah the Prophet✞✞✞
✞✞✞In the name of the Father, the Son and the Holy Spirit, one God. Amen!✞✞✞
✞✞✞Saint Cornelius✞✞✞
=>The life account of this Saint, which we will see on this day, is mostly taken from the Acts of the Apostles chapter 10. Since the conversion and baptism of this Saint is one of the main scenes in the history of the New Testament Church, it has been recorded in Holy Scripture extensively.
✞Though it is known that before him, the Ethiopian Eunuch - Bakos had believed and was baptized (Acts 8:26), St. Cornelius is considered to be the first among the gentiles to have believed and to have been incorporated to the flock of the Apostles. If asked how that came to be, it was as follows.
✞The Roman Empire by its Caesars used to dominate the world in the 1st century A.D. And in its different provinces there were appointees to the smallest rank that would collect tax for the Emperor and subjugate the people for him.
✞And one of them was this centurion, Cornelius, who was appointed in Caesarea of Palestine (Keisarya/Qaysaria) as a captain of the army. And the name his legion was “Italiqe” (Cohors Italica).
✞Cornelius did not know God and was a worshipper of the stars like the heathens (Greeks). Though that it may be, he despised evil, did much kindness, frequented almsgiving and lived searching (trying to find the True God).
✞And at that time, our Savior Jesus Christ had competed His ministry and the Apostles, our fathers, like a swift mule were hastily on the move to teach the Gospel, to evangelize. And as Cornelius was an appointee, the news of the Apostles came to him promptly.
✞Thus, he was amazed after hearing that the Saints healed the sick in the name of Christ, raised the dead, and performed many miracles by the Power of the Holy Spirit. And recognizing that the star he worshipped, Zuḥal (Saturn/Cronus), was a futile creation, he stopped his idolatry.
✞Even though he was a centurion, he started to daily pray and fast during the day and at night. And his prayer was, “O True God reveal [Yourself to me].” Since fasting and prayer without almsgiving do not do much, he made his home the abode of the hungry and the house of the destitute.
✞And such delightful fasting, prayer and charity reached heaven without any hinderance, before God. Though he was a gentile (unbaptized), the Lord sent him His holy angel.
✞One day, when he prayed as usual, at 3:00 PM (at Nones) the angel appeared to him wearing a luminous vestment. And he said, “O Cornelius! Your prayer and alms have reached before God. And God has remembered you.”
✞He then added, “Now that you be saved as there is a person named Peter in the house of Simon the tanner in Joppa, send for him. And he shall tell you how you shall be saved.” Then, after telling him the good tiding, the angel disappeared. And amazed by the revelation, he summoned his servants and sent them to Joppa.
✞And on the same day, St. Peter the Arch-apostle went to the housetop of Simon the tanner to pray. And while he was praying, he went into a trance and saw a great vision, a certain drape. He saw a great sheet knit at the four corners that had in it the image of animals, wild beasts, creeping things, and fowls of the air.
✞And while a hand pointed towards a wild boar, a voice said, “O Peter! Rise. Slaughter this and eat.” However, Peter replied, “I have never eaten anything that is unclean.”
✞Thus, a response came that said, “What God hath cleansed, that call not thou unclean.” And he saw this vision 3 times. Then that great drape ascended.
✞The meaning of the revelation for the time being showed that there was none which was unclean from what God had created. And for its fulfillment that sheet/drape was a symbol of the Gospel and the Mother of Light the Virgin Mary as well.✞The boar was a symbol of St. Cornelius and the revelation was saying, “Do not despise rather baptize him.” And while St. Peter pondered about the matter, the servants of St.
††† እንኳን ለቅዱሳን ቆርኔሌዎስ ሐዋርያዊ እና አብድዩ ነቢይ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† ቅዱስ ቆርኔሌዎስ †††
††† ዛሬ የምንመለከተው የዚህ ቅዱስ ዜና ሕይወት በአብዛኛው የተወሰደው ከሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 10 ላይ ነው:: በቤተ ክርስቲያን የሐዲስ ኪዳን ታሪክ ወሳኝ ከሚባሉ ክዋኔዎች የዚህ ቅዱስ አምኖ መጠመቅ ነውና በታላቁ ቅዱስ መጽሐፍ ላይ በስፋት ተመዝግቧል::
ምንም እንኩዋ ከእርሱ አስቀድሞ ኢትዮዽያዊው ባኮስ እንዳመነና እንደ ተጠመቀ ቢታወቅም (ሐዋ. 8:26) ቅዱስ ቆርኔሌዎስ ከአሕዛብ ወገን አምኖ ሐዋርያትን የተቀላቀለ የመጀመሪያው ሰው ነው:: ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
የሮም መንግሥት በቄሣሮች ሥር በ1ኛው መቶ ክ/ዘመን ዓለምን እንደ ሰም አቅልጦ: እንደ ገል ቀጥቅጦ ይገዛ ነበር:: በየ አሕጉሩም እስከ መንደርተኛ ሹሞች ድረስ ተሹመው ግብርን ለቄሣር ይሰበስቡ: ሕዝቡን ለቄሣር ያስገዙ ነበር::
ከእነዚህ መካከልም አንዱ የሆነው ቆርኔሌዎስ በቂሣርያ ዘፍልስጥኤም (ሌላ ቂሣርያ ስላለች ነው) የመቶ አለቃ (ሃቤ ምዕት): የሠራዊት መሪ (ሊቀ ሐራ) ሆኖ ተሹሞ ነበር:: የሠራዊቱን ስምም "ኢጣሊቄ" ይሉታል::
ቆርኔሌዎስ እግዚአብሔርን አያውቅም:: እንደ አረሚ (ግሪካውያን) የከዋክብት አምላኪ ነበር እንጂ:: ያም ሆኖ ክፋትን የሚጠላ: ደግነትን የሚያበዛ: ምጽዋትን የሚያዘወትርና በሐቲት (በምርምር) የሚኖር ሰው ነበር::
ታዲያ በዚያ ሰሞን ክርስቶስ ኢየሱስ መድኃኒታችን የማዳን ሥራውን ፈጽሞ: አበው ሐዋርያት ለትምሕርተ ወንጌል እንደ ሠጋር በቅሎ ይፋጠኑ ነበር:: ሹም (አለቃ) ነውና ቆርኔሌዎስ የሐዋርያት ዜና ፈጥኖ ነበር የደረሰው::
ቅዱሳኑ በስመ ክርስቶስ ድውያንን እንደሚፈውሱ: ሙታንን እንደሚያነሱ: በኃይለ መንፈስ ቅዱስም ብዙ ምልክቶችን (ተአምራትን) እንደሚያደርጉ ሰምቶ ተገረመ:: እርሱ የሚያመልከው ዙሐል (የኮከብ ስም ነው) አቅመ ቢስ ፍጡር መሆኑን ተረዳና እርግፍ አድርጐ ተወው::
ምንም የሠራዊት አለቃ ሹም ቢሆንም ዘወትር በመዓልትና በሌሊት ይጾምና ይጸልይ ገባ:: ጸሎቱም "የእውነት አምላክ ተገለጥ" ነበር:: ጾምና ጸሎት ያለ ምጽዋት ቁም ነገር አይሠሩምና ቤቱን ቤተ-ርሑባን: ቤተ-ነዳያን አደረገው::
ይሕ ተወዳጅ ጾም: ጸሎትና ምጽዋት ደግሞ ያለ ከልካይ ወደ ሰማያት: ቅድመ እግዚአብሔር ደረሰ:: ምንም አሕዛባዊ (ኢ-ጥሙቅ) ቢሆንም ጌታ ግን ቅዱስ መልአኩን ላከለት::
አንድ ቀን እንዳስለመደ ሲጸልይ ዘጠኝ ሰዓት (በሠርክ) አካባቢ መልአኩ ብሩህ ልብስ ተጐናጽፎ ተገለጠለት:: "ቆርኔሌዎስ ሆይ! ጸሎትህና ምጽዋትህ ወደ እግዚአብሔር ደረሰልህ:: እግዚአብሔርም አሰበህ" አለው::
"አሁንም ትድን ዘንድ በሰፋዪ ስምዖን ቤት: በሃገረ ኢዮዼ: ዼጥሮስ የሚሉት ስምዖን አለና እርሱን ጥራው:: እርሱ የምትድንበትን ይነግርሃል" ብሎት: የምሥራቹንም ነግሮት ተሰወረው:: ወዲያውም ከራዕዩ የተነሳ እያደነቀ ብላቴኖቹን ጠርቶ ወደ ኢዮዼ ላካቸው::
በዚያች ዕለትም የሐዋርያት አለቃ ቅዱስ ዼጥሮስ በቤተ ስምዖን ሰፋዪ ሳለ ይጸልይ ዘንድ ወደ ደርቡ (ፎቅ) ወጣ:: በዚያም በጸሎት ላይ ሳለ ተደሞ መጣበት:: ግሩም ራዕይንም ተመለከተ:: "ሞጣሕት ስፍሕት" ይላታል:: ከሰማይ በ4 ማዐዝን የተያዘች መጋረጃ: በውስጧ የእንስሳት: የአራዊት: የአዕዋፍ ስዕል ተስሎባት ስትወርድ ተመለከተ::
አንዲት እጅም ወደ እሪያው (አሳማ) እያመለከተች "ተንስእ ኦ ዼጥሮስ ኅርድ ዘንተ ወብላእ . . . - ዼጥሮስ ሆይ! ተነስ: ይህንንም አርደህ ብላ" ስትለው:: እርሱ ግን "ግሙራ ኢቦአ ርኩስ ውስተ አፉየ-የረከሰ ነገር ከአፌ ገብቶ አያውቅም" ብሎ መለሰ::
መልሶም "ዘእግዚአብሔር አንጽሐ አንተ ኢታስተራኩስ- እግዚአብሔር ያነጻውን አንተ አታርክሰው" ሲለው:: ይሕም ራዕይ 3 ጊዜ ሲደጋገም ተመለከተ:: ወዲያውም ያቺ መጋረጃም ወደ ላይ ተመለሰች::
የራዕዩ ምሥጢር ለጊዜው እግዚአብሔር ከፈጠረው "ርኩስ" የሚባል እንደ ሌለ ያጠይቃል:: ለፍጻሜው ግን ያቺ ሞጣሕት የወንጌል (የክርስትና) አንድም የእመ ብርሃን ድንግል ማርያም ምሳሌ ናት::
እሪያው ደግሞ የቅዱስ ቆርኔሌዎስ ምሳሌ ነውና "አትጸየፈው: አጥምቀው" ሲለው ነበር:: ቅዱስ ዼጥሮስ ስለዚህ ነገር ሲያሰላስል የቅዱስ ቆርኔሌዎስ ብላቴኖች ደርሰው ጠሩት:: መንፈስ ቅዱስ "አብረሃቸው ሒድ" ብሎታልና አብሯቸው ሔደ::
ወደ ቆርኔሌዎስ ዘንድ ደርሶም 2ቱ ራዕያቸውን ተጨዋወቱ:: ቆርኔሌዎስም በግንባሩ ተደፍቶ ለሊቀ ሐዋርያት ሰገደለት:: ቅዱስ ዼጥሮስ ግን ስለ ትሕትና "አትስገድልኝ" አለው:: ከዚያም አፉን ከፍቶ ለእርሱና ለቤተሰቡ ከቅዱስ ቃሉ መገባቸው:: አጥምቆም እጁን ሲጭንባቸው ከቅዱስ መንፈሱ ተካፈሉ::
ከዚህች ዕለት በሁዋላም ቅዱስ ቆርኔሌዎስ ሃብቱን: ንብረቱን: ሹመቱንና ክብሩን ንቆ ሐዋርያትን ተከተላቸው:: ለስብከተ ወንጌል አገልግሎትም አንዲት በትር ብቻ ይዞ ወደ ምድረ ግብጽ ወረደ:: በዚያም ብዙዎችን ወደ ክርስትና ስቦ: ለዓመታት ተጋድሎ በዚህች ቀን ዐርፏል::
††† ቅዱስ አብድዩ ነቢይ †††
††† "አብድዩ" ማለት "የእግዚአብሔር አገልጋይ" ማለት ነው:: ቁጥሩ ከ12ቱ ደቂቀ ነቢያት ሲሆን የቅዱስ ኤልያስ ታላቁም ደቀ መዝሙር ነው:: ቅዱሳን ነቢያት ዮናስና ኤልሳዕም ባልንጀሮቹ ነበሩ::
ቅዱስ አብድዩ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በ800 ዓመት አካባቢ የከሃዲው ንጉሥ የጦር መሪ ሆኖ በሃምሳ አለቃነት አገልግሏል:: ግፈኛዋ ኤልዛቤል ነቢያተ እሥራኤልን ስታስፈጅ 50ውን በአንድ ዋሻ 50ውን ደግሞ በሌላ ዋሻ አድርጐ አትርፏቸዋል:: 900ው ግን ተጨፍጭፈዋል::
ያተረፋቸውንም ክፉ ዘመን እስኪያልፍ ድረስ መግቧቸዋል:: አክአብና ኤልዛቤል ከሞቱ በሁዋላም ቅዱስ ኤልያስን ተከትሎ ሹመቱን ትቷል:: እግዚአብሔር ገልጾለትም ትንቢት ሲናገር: ሕዝቡንም ሲገሥጽ ኑሯል::
በብሉይ ኪዳን ካሉ የትንቢት መጻሕፍትም በጣም አጭሩን የጻፈው ይሕ ነቢይ ነው:: ትንቢተ አብድዩ ባለ አንድ ምዕራፍ ብቻ ናትና:: ቅዱሱ በዚህች ቀን ዐርፎ ወገኖቹ ቀብረውታል::
††† አምላከ ነቢያት ወሐዋርያት የበረከትና የሰላም ዘመንን ያምጣልን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::
††† ኅዳር 23 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ቆርኔሌዎስ (ሐዋርያዊ ጻድቅ)
2.ቅዱስ አብድዩ ነቢይ
††† ወርኀዊ በዓላት
1.ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት
2.ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት
3.ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ሰሎሞን (ንጉሠ እሥራኤል)
4.አባ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ
5.ቅዱስ ዳንኤል ነቢይ
6.አባ ሳሙኤል
7.አባ ስምዖን
8.አባ ገብርኤል
††† "በተሰነጠቀ ዓለት ውስጥ የምትኖር: ማደሪያህንም ከፍ ከፍ ያደረግህ: በልብህም:- 'ወደ ምድር የሚያወርደኝ ማን ነው?' የምትል አንተ ሆይ! የልብህ ትዕቢት አታልሎሃል:: እንደ ንስር መጥቀህ ብትወጣ: ቤትህም በከዋክብት መካከል ቢሆን: 'ከዚያ አወርድሃለሁ' ይላል እግዚአብሔር::" †††
(አብድዩ 1:3)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
https://t.me/zikirekdusn
❖ትንሽ በሰነበቱ የሚል ምኞት ነበረኝ እንጂ፥ መሔዳቸውማ ወዴት ይቀራል!
•ለመጀመሪያ ጊዜ፥ ስለደገኛው ሊቅ የኔታ ይባቤ የሰማሁት ከጎጃም የመጡ የአቋቋም ተማሪ ነበር። (ገና ሕጻን እያለሁ) ስለማንነታቸው ሲነግሩኝ የተሰማኝን መገረም አልረሳውም። (እንዲህም ያለ የጉባዔ መምህ አለ?)
•እኔማ ሊቅነታቸው አይገርመኝም። (ሀገር ያውቀዋልና)
•በመንፈሳዊ ትጋትና ጥብአት ግን፥ ከመሰሎቻቸው ሁሉ እርሳቸው የመጨረሻው ይመስሉኛል፡፡ (ሊቅነት፥ መንፈሳዊነትና ጥብአትን አስተባብሮ የያዘ ማን ቀረ እንግዲህ?)
•ክቡር አባታችን በእግዚአብሔር ፊት ያስቡን፤ ይልቁኑ ሀገራችንንን ያስቧት፡፡ (ከአረመኔዎች እንዲታደጋት)
Repost from ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ)
Mostrar todo...Photo unavailableShow in Telegram
መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"💠
/(ማቴ ፫:፫/)
❇️ዝክረ ቅዱሳን ተማሩ ላልደረሳቸው አጋሩ!!!
✝እንኳን አደረሰን!!
✝ለ ፳፻፲፯ የቤት ሥራ የሚሆኑ ፭ መልእክቶች
፩.ለጸሎት ተነሱ
፪.ክርስትናን መኖርን እንጀምር
፫.የእውነት ንስሐ ያስፈልገናል
፬.ካቆሸሸን ማኅበራዊ ሚዲያ ጥቂት እንራቅ
፭.ትልቁ መከራ እንዳያገኘን
ነቢያት ወሐዋርያት፥ ጻድቃን ወሰማዕት፥ ደናግል ወመነኮሳት፥ አዕሩግ ወሕጻናት፥ ገዳማውያን ወሊቃውንት፥ ሰአሉ ለነ ኩልክሙ ቅድመ መንበሩ ለጸባኦት።✝
✝ ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት።
" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
🔗https://t.me/zikirekdusn
▶️https://www.youtube.com/@ZikereKedusan
