es
Feedback
"ኡማ ቲቪ " Tv

"ኡማ ቲቪ " Tv

Ir al canal en Telegram

ለበለጠ ወቅታዊ መረጃወችን ለማገኘት የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇 https://t.me/+UAKV32q7U2HKzEMf

Mostrar más
2025 año en númerossnowflakes fon
card fon
46 279
Suscriptores
Sin datos24 horas
-877 días
-54930 días
Archivo de publicaciones
Photo unavailableShow in Telegram
ለቤት ሰራተኞች በሙሉ የሳውዲ አረቢያ የሰው ኃይል እና ማህበራዊ ልማት ሚኒስቴር በሀገሪቱ በሚገኙ የቤት ሠራተኞች የደመወዝ አከፋፈል ላይ መሠረታዊ ለውጥ ማድረጉን አስታወቀ። በአዲሱ መመሪያ መሠረት፣ ከፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ጀምሮ ማንኛውም አሠሪ ለቤት ሠራተኞች የሚከፍለውን ደመወዝ በጥሬ ገንዘብ (Cash) መስጠት የሚከለከል ሲሆን፣ ክፍያው በይፋዊ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መስመሮች ብቻ እንዲከናወን ተደንግጓል። ይህ ውሳኔ በተለይ በኢትዮጵያ እና በሳውዲ አረቢያ መንግሥት መካከል እ.ኤ.አ በ2023 የተፈረመውን የሁለትዮሽ የሥራ ስምሪት ስምምነት ተከትሎ ወደ ሀገሪቱ ለገቡ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን ትልቅ የምስራች ሆኗል። አዲሱ አሠራር የሠራተኞችን የደመወዝ መብት ከማስከበር ባለፈ፣ ክፍያዎች በወቅቱ መፈጸማቸውን የሚያረጋግጥና በአሠሪና ሠራተኛ መካከል የሚፈጠሩ የክፍያ አለመግባባቶችን በዘላቂነት የሚፈታ መሆኑ ተገልጿል። እንደ ሚኒስቴሩ ገለጻ፣ የደመወዝ ክፍያው የሚፈጸመው በ"ሙሳነድ" (Musaned) የዲጂታል መድረክ አማካኝነት በታወቁ ባንኮች ወይም የዲጂታል የገንዘብ ማስተላለፊያ መተግበሪያዎች (Digital Wallets) በኩል ይሆናል። ሠራተኞች ደመወዛቸውን በጥሬ ገንዘብ መጠቀም በሚፈልጉበት ጊዜ በስማቸው በሚወጣ የ"ማዳ" (Mada) የባንክ ካርድ አማካኝነት በማንኛውም የገንዘብ ማውጫ ማሽን (ATM) መጠቀም ይችላሉ። ይህም ሠራተኞች ያጠራቀሙትን ገንዘብ ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ወደ ሀገራቸው ለቤተሰቦቻቸው እንዲልኩና የሥራ ውላቸው ሲጠናቀቅ የሚገባቸውን ጥቅማጥቅም በቀላሉ እንዲያገኙ ይረዳቸዋል። ይህ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት እኤአ ከሐምሌ 2024 ጀምሮ ደረጃ በደረጃ ተግባራዊ ሲደረግ የቆየ ሲሆን፣ ከጥር 2026 ጀምሮ ግን ለማንኛውም አሠሪና ሠራተኛ አስገዳጅ ይሆናል። ውሳኔው የሳውዲ አረቢያን የቤት ሠራተኛ ዘርፍ ዘመናዊ ለማድረግና የሠራተኞችን ሰብአዊና ቁሳዊ መብቶች ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለመጠበቅ የሚደረገው ጥረት አካል መሆኑ ታውቋል። የሳውዲ አረቢያ የሰው ሃይል እና ማህበራዊ ልማት ሚኒስተር
Mostrar todo...
47👍 12🥰 1😭 1
ማስታወቂያ/Promotion ማሰራት የምትፈልጉ  አናግሩኝ @Faysul
Mostrar todo...
3👍 1
00:27
Video unavailableShow in Telegram
🕌🕌🕌 ተወኩል ይሉሀል!❤🤲 " በአላህ ላይ ያለህ እምነትና ተወኩልህ ላቅ ሲል ካዝናም ሰንዱቅና ሳጥን ተራ ነገሮች ናቸው።" ይህ መስጂድ ታይላንድ ውስጥ የሚገኝ ነው። እንደምታዩት ጫማ ሳይሆን ሞባይላቸውን እንደዚህ ጥለውት ለእርሱ ወደሱ ሰጥተው ነው ወደ ሰላት የሚገቡት ምን ያማረ ተወኩል።🙌🤲❤
Mostrar todo...
2.45 MB
99💯 9👍 8
Photo unavailableShow in Telegram
😥💔 ኢና ሊላሒ ወዒና ኢለይሂ ራጂዑን ኤርትራዊው ኢማም በአሜሪካን እስር ቤት ውስጥ ለህልፈት ተዳረጉ፣ሼህ ፉዓድ ሰዒድ አ/ቃድር ICE በተባሉት የአሜሪካን ኢማይግሬሽን ፖሊሶች ተይዘው ለ 215 ቀናት በእስርና ቀጠሮ ላይ የነበሩት ኢማምMoshannon Valley በተሰኘ ፔንሲልቫኒያ ውስጥ በሚገኝ የማቆያ ማዕከል ውስጥ ነበር የታሰሩት። የመጨረሻ ውሳኔያቸውን ከኢሚግሬሽን ዳኛው ለመስማት በቀጠሮ ላይ የነበሩት ሸህ ባለፈው እሁድ ዲሴምበር 14 , 2025 ወደ አኺራ መሔዳቸው ታውቋል። ሸህ ፉዓድ የተወለዱት ሳዑዲ ዓረቢያ ሪያድ ውስጥ በ1979 ሲሆን በዜግነት ኤርትራዊ ናቸው።አሟሟታቸው በጤንነት ዕክል በዕስር ላይ ሳሉ ሲሆን የ ICE እስር ቤትን የዕስረኞች አያያዝ አጠያያቂ አድርጎታል። አላህ ጀናቱል ፊርደውስ ይስጣቸው ይማራቸው🤲🤲🤲
Mostrar todo...
😭 76 32😢 7
Photo unavailableShow in Telegram
በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ታዳጊዎችን ከማኅበራዊ ሚዲያ ልታቅብ እንደምትችል ስዊዘርላንድ አስታወቀች የስዊዘርላንድ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ኤልዛቤት ባውም ሽናይደር፤ ልጆችን ከማኅበራዊ ሚዲያ አደጋዎች ለመጠበቅ ሲባል ከማኅበራዊ ትስስር መድረኮች ሊታገዱ እንደሚችሉ ተናግረዋል። አውስትራሊያ በታኅሣሥ ወር መጀመርያ ከ16 ዓመት በታች ለሆኑ ታዳጊዎች ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ እገዳ መጣሏን ተከትሎ ስዊዘርላንድ ተመሳሳይ ርምጃዎችን መውሰድ እንደሚገባት ሚኒስትሯ ገልጸዋል። እንደ ሬውተርስ ዘገባ ከሆነ፤ በአውስትራሊያ እና በአውሮፓ ኅብረት የተጀመረው እንቅስቃሴ በስዊዘርላንድ መቀጠል አለበት ያሉት ኤሊዛቤት፤ ለማኅበራዊ ሚዲያ ክልከላ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል። ባለሥልጣናት መከልከል ያለባቸውን እንደ የሕፃናት የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምን መከልከል፣ ጎጂ ይዘቶችን መግታት እና የወጣቶችን ተጋላጭነት የሚጎዱ አልጎሪዝሞችን ማስተካከል ያሉ አማራጮችን ዝርዝር ማካተት አለባቸው ብለዋል። በተጨማሪም በመጪው የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት በሪፖርት የተደገፈ ዝርዝር ውይይቶች ይጀመራሉ ተብሏል። የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ራሳቸው ልጆችና ወጣቶች ለሚጠቀሙት ነገር ኃላፊነቱን መውሰድ አለባቸው ብለዋል። የስዊዘርላንድ በያዝነው ወር መጀመሪያ በፓርላማ ልጆች 15 ዓመት እስኪሞላቸው በትምህርት ቤት የሞባይል ስልኮችን እንዳይጠቀሙ ለመከልከል ድምጽ ሰጥቷል። በተመሳሳይ ማሌዥያም ከ16 ዓመት በታች ያሉ ታዳጊዎችን በመጪው አዲስ አመት ክልከላውን ተግባራዊ እንደምታደርግ ተዘግቧል።
Mostrar todo...
29👍 4
ደስ የሚል ዜና! በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን ገደባኖ ወለኔ ወረዳ መሀል ጉታዘር ቀበሌ የሀጅ ሙሀመድ መስጅድና ኢስላማዊ ማዕከል ግንባታ የመሠረት ድንጋይ የማስቀመጥና የሰደቃ ፕሮግራም ተካሄደ።
Mostrar todo...
👍 15
ከ 18,000 በላይ ሰማዕታት =========== ጭራቋ እስራኤል በጋዛ ላይ ባካሄደችው የሁለት ዓመቱ የጅምላ ጭፍጨፋና የዘር ማፅደት ጦርነት ላይ ከ18,000 በላይ ሟቾችን (ሰማዕታት) በእጁ እንደቀበረ …ቀባሪ ዩሱፍ ሀታም ይናገራል።
Mostrar todo...
😭 29 8
Photo unavailableShow in Telegram
በቅርበት የማቃት አንዲት ታታሪ እህቴ በአዲስ ስራ መታለች የዚህ ቻናሌ ቤተሰቦቼ ደሞ የሚሰሩ እጆችን ስለምትተባበሩ ይችን እህታችንን ቤተሰብ ሁኖት በአይነታቸው ልዩ እና ጣፋጭ ሆነው የሚዘጋጁትን ቴራሚሱ ዴዘርቶች  በተለያዩ ጣእም(ፍሌቨሮች) አስቀድመው በማዘዝ ልዩነቱን ያጣጥሙ ቀኖን ያሳምሩ!!! ከታች ባሉት ስልኮች በመደወል አስቀድመው ይዘዙ 0967006882 0967008862 0965694688 በቴሌግራም https://t.me/sistersdesserts በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@sisters.dessert0?_r=1&_t=ZM-92QyV3hg4tM
Mostrar todo...
16
ዘምዘም ባንክ ለምስራቅ ሐረርጌ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፋይናንስ በማድረግ ዘመናዊ ተሽከርካሪ ገዝቶ አስረከበ!! ምክር ቤቱ የተለያዩ እስላማዊ አገልግሎቶችን በተቀላጠፈ ሁኔታ መስጠት ያስችለዉ ዘንድ እንዲሁም የመስክ ምልከታዎችን በቀላሉ ለማካሄድ የተሽከርካሪው ግዢ አስፈላጊ እንደነበር ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል። ዘምዘም ባንክ መሰል ማህበራዊ እንቅስቃሴዎችን በፋይናንስ መደገፉን በመቀጠል ህዝባዊ አለኝታነቱን ያረጋግጣል!! ዘምዘም ባንክ የማይነጥፍ የእድገት ምንጭ!
Mostrar todo...
37
Photo unavailableShow in Telegram
😡 32 11
Photo unavailableShow in Telegram
እንኳን ደስ አልዎ!! አዲሱ ኢ ፓስፖርት በሁሉም የሃገራችን  ክልሎች አገልግሎቱን ጀመረ! ካሉበት ሆነው አስፈላጊ ሰነዶችን በኦንለይን(በቴሌግራም) በመላክ ብቻ  ቀጠሮ አሲዘው፤ በቀጠሮ ቀን ወዳመለከቱበት ቅርንጫፍ ሄደው አሻራ በመስጠት በመደበኛ እና በአስቸኳይ (2 ቀን ወይም 5 ቀን) ፓስፖርቶን በእጅዎ ያድርጉ። አስፈላጊ ሰነዶች   አዲስ ፓስፖርት 1. የታደሰ የቀበሌ /የመስራ ቤት መታወቂያ 2. የተረጋገጠ የልደት ሰርተፊኬት ከ 41 አመት በታች ለሆኑ ፓስፖርት እድሳት 1. የቀድሞ ፓስፖርት የመረጃ ገጽ 2. ፓስፖርት መጠን (3*4) ቅርብ ግዜ የተነሱት ፎቶ   ለተበላሸ/ለጠፋ ፓስፖርት 1. የታደሰ የቀበሌ /የመስራ ቤት መታወቂያ 2. ለፖሊስ ያመለከቱበት መረጃ (ከጠፋ)   ለህጻናት (ከ 18 አመት በታች) 1. የአመልካች አባት ወይም እናት ወይም ሞግዚት የታደሰ መታወቂያ 2. የልጅ የልደት ካርድ 3. ልጅ ከ 5 አመት በላይ ከሆነ ፋይዳ መታወቂያ   ፓስፖርት ለመቀበል 1. የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ 2.ፋይዳ መታወቂያ 3. ኦንለይን ያመለከቱበት ፕሪንት አውት 4. ክፊያ የፈጸሙበት ደረሰኝ (CBE birr, CBE mobile banking, Tele birr) እጅግ ተመጣጣኝ ዋጋ!!! ይደውሉ፤ያማክሩን!!! ለበለጠ መረጃ; 0940958895 ይደውሉ። Join telegram group https://t.me/Urgentpassport157
Mostrar todo...
8👍 2