es
Feedback
TIKVAH-SPORT

TIKVAH-SPORT

Ir al canal en Telegram

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ስፖርት ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የስፖርታዊ መረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። በዚህ ቻናል ሀገራዊ እና አለም አቀፋዊ የስፖርት መረጃዎች ይዳሰሱበታል። ለመረጃ እና ማስታወቂያ +251926797469

Mostrar más
2025 año en númerossnowflakes fon
card fon
272 645
Suscriptores
-5524 horas
+107 días
+1 35830 días
Archivo de publicaciones
Photo unavailableShow in Telegram
ኪሊያን ምባፔ ሞርኮ መግባቱ ተነግሯል ! ፈረንሳዊው የሪያል ማድሪድ የፊት መስመር ተሰላፊ ኪሊያን ምባፔ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ሞሮኮ መግባቱ ተገልጿል። ኪሊያን ምባፔ በነገው ዕለት የሞሮኮ እና ማሊን ጨዋታ ለመታደም በማሰብ ከቤተሰቡ ጋር ወደ ሞሮኮ ማቅናቱ ተነግሯል። ምባፔ በጨዋታው እንዲገኝ ከቅርብ ጓደኛው አሽራፍ ሀኪሚ እና ከሞሮኮ ግብዣ እንደቀረበለት መዘገቡ ይታወሳል። በተጨማሪም የፒኤስጂው ተጨዋች ኡስማን ዴምቤሌ በጨዋታው ሊገኝ እንደሚችል ተነግሯል። ኡሴማን ዴምቤሌ በነገው ዕለት ወደ ሞሮኮ ሊያቀና እንደሚችል የፈረንሳይ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። @Tikvahethsport       @kidusyoftahe
Mostrar todo...
452👍 61🔥 24👏 8💯 3🙏 1
Photo unavailableShow in Telegram
#EthPL በ ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ1 አጠናቀዋል። የፈረሰኞቹን ግብ ሀብታሙ ጉልላት ሲያስቆጥር ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ናትናኤል ዳንኤል ከመረብ አሳርፏል። የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ? 6️⃣ ቅዱስ ጊዮርጊስ :- 17 ነጥብ 1️⃣3️⃣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ :- 12 ነጥብ ቀጣይ መርሐግብር ? ሰኞ - መቐለ 70 እንደርታ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ እሮብ - ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ኢትዮጵያ መድን @Tikvahethsport       @kidusyoftahe
Mostrar todo...
74😁 11👍 9👎 3🤬 3
Photo unavailableShow in Telegram
ማድሪድ ከሳንቲያጎ በርናቦ ስንት ያገኛል ? ሪያል ማድሪድ በዘንድሮው የውድድር ዘመን ከሳንቲያጎ በርናቦ ስታዲየም ከፍተኛ ገቢ እንደሚጠብቅ ተገልጿል። ሎስ ብላንኮዎቹ ከስታዲየሙ ብቻ 400 ሚልዮን ዩሮ ገቢ ያገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል። ገቢው የሚገኘው ከሙዚቃ ድግስ ፣ ከጉብኝት ፣ ከተለያዩ ዝግጅቶች እና ሬስቶራንት መሆኑ ተዘግቧል ። ክለቡ ከስታዲየሙ የሚያገኘው ገቢ በ 31% ከፍ እንደሚል ሲገለፅ ሪከርድ ሆኖ ይመዘገባል ተብሎ ይጠበቃል።
Mostrar todo...
175👍 32👎 12🔥 11
የሞሮኮ ስታዲየሞች እንዴት ዝናቡን ተቋቁመው ዝግጁ ሆኑ ? በሞሮኮ ከባድ ዝናባማ የአየር ሁኔታ ቢኖርም የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ያለ ምንም መቋረጥ መካሄዱን ቀጥሏል። ምንም እንኳን በሀገሪቱ ዝናብ እና ጎርፍ ቢስተዋልም እስካሁን አንድ ጨዋታ አለመቋረጡ ሞሮኮን አስመስግኗታል። ዝናብ ቢኖርም የመጫወቻ ሜዳዎቹ ውሃ ሳያስቸግራቸው ዝግጁ ሆነው የመቆየታቸው ሚስጥር ሞርኮ የወሰደችው እርምጃ መሆኑ ተገልጿል። ሀገሪቱ ለውድድሩ ያዘጋጀቻቸው ዘጠኝ ስታዲየሞች ዘመናዊ የፍሳሽ ማስወገጃ ስርዓት እንደሚጠቀሙ ተነግሯል። እንዲሁም ውድድሩ ከመጀመሩ ሳምንት በፊት የሜዳው ሳር ሙቀትን ከሚቋቋመው " Bermuda " እርጥበትን ወደሚቋቋመው " Ryegrass " ተቀይሮ ነበር።
Mostrar todo...
👏 515 133👍 18🔥 15👎 1🥰 1
Photo unavailableShow in Telegram
ድሬዳዋ ከተማ ኢትዮጵያ ቡናን አሸንፏል ! በ ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐግብር ድሬዳዋ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል። የድሬዳዋ ከተማን የማሸነፊያ ግቦች ጀሚል ያዕቆብ እና መሀመድ ኑር ናስር አስቆጥረዋል። ቡናማዎቹ በአቡበከር አዳሙ ግብ ጨዋታውን እየመሩ ነበር። ኢትዮጵያ ቡና በውድድር ዘመኑ አምስተኛ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታውን ተሸንፏል። የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ? 8️⃣ ድሬዳዋ ከተማ :- 16 ነጥብ 1️⃣4️⃣ ኢትዮጵያ ቡና :- 12 ነጥብ ቀጣይ መርሐግብር ? ማክሰኞ - ድሬዳዋ ከተማ ከ አርሲ ነገሌ እሮብ - መቻል ከ ኢትዮጵያ ቡና
Mostrar todo...
74😁 65👍 9👎 2😢 1
Photo unavailableShow in Telegram
#EthPL በ ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ሀዋሳ ከተማ ከሸገር ከተማ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ1 ማሸነፍ ችሏል። የሀዋሳ ከተማን ግብ ያሬድ ብሩክ እና ጌታነህ ከበደ ሲያስቆጥሩ ለሸገር ከተማ ያሬድ መኮንን ከመረብ አሳርፏል። ቀደም ብሎ በተደረገ መርሐ ግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሽረ ምድረ ገነትን በአቤል አዳሙ ግብ 1ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል። የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ? 3️⃣ ሀዋሳ ከተማ :- 20 ነጥብ 4️⃣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ :- 20 ነጥብ 1️⃣0️⃣ ሽረ ምድረ ገነት :- 14 ነጥብ 1️⃣4️⃣ ሸገር ከተማ :- 12 ነጥብ @Tikvahethsport       @kidusyoftahe
Mostrar todo...
65🙏 7🥰 2👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
“ ሞሮኮ የአፍሪካ ምርጥ ቡድን ነች “ ቶም ሴንትፊት " ያልተጠበቀ ለማድረግ እንሞክራለን " ቤልጄማዊው የማሊ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ቶም ሴንትፊት የነገ ተጋጣሚያቸውን ሞሮኮ " ጠንካራ " ሲሉ ገልጸዋል። አሰልጣኙ ሲናገሩም “ የሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ምርጡ እንዲሁም ከአለም ምርጥ ቡድኖች አንዱ ነው “ ብለዋል። ስለ ዝግጅታቸው የተጠየቁት አሰልጣኙ “ ሞሮኮ ከኮሞሮስ ያደረገችውን ጨዋታ በተለይ የተከላካይ ክፍላቸውን በጥልቀት መርምረን ተንትነናል “ ሲሉ ጠቁመዋል። “ በጣም የምተማመንባቸው አስደናቂ ተጨዋቾች ስላሉን አስጨንቀናቸዋል ፤ ነገርግን እውነት ለመናገር ሞሮኮ የማሸነፍ ቅድመ ግምት የሚሰጣት ቡድን ነች " ቶም ሴንትፊት የሞርኮን ከፍተኛ የእግርኳስ እድገት ያነሱት አሰልጣኙ “ ይሄ በአንድ ለሊት የሚመጣ ነገር አይደለም “ ሲሉ ገልጸዋል። “ ሞርኮ በበርካታ ደጋፊ ፊት ትጫወታለች ፤ ከእኛ የበለጠ ጫናም ይኖርባቸዋል ፤ ያልተጠበቀ ነገር ለማድረግ እንሞክራለን “ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል።
Mostrar todo...
166👍 24🔥 8
Repost from TgId: 1571225671
Photo unavailableShow in Telegram
🎅Even Santa Wears Matchday Energy.🎄 Good Holiday☃️. Good football.⚽️ Better jerseys.🎄 That’s a Wanaw Christmas. 🎁 Merry Christmas!🎄 🔗Social Media🔗 Instagram|Facebook |TikTok |X|Youtube
⭐️| #WanawSportwear |Moving Forward»»» 🇪🇹
Mostrar todo...
25🤬 1🎉 1
Photo unavailableShow in Telegram
“ እኛ ማንንም አንፈራም ለሁሉም ዝግጁ ነን “ ሆሳም ሀሰን የፈርዖኖቹ ዋና አሰልጣኝ ሆሳም ሀሰን ቡድናቸው የትኛውንም ቡድን ለመግጠም ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል። “ በውድድሩ የትኛውንም ቡድን ለመፋለም ዝግጁ ነን “ ሲሉ በጥሩ ቁመና ላይ መሆናቸውን የገለፁት አሰልጣኙ “ ማንንም ቢሆን አንፈራም “ ብለዋል። በፍፃሜው የትኛውን ቡድን ቢገጥሙ እንደሚመርጡ የተጠየቁት አሰልጣኙ “ ለየትኛውም ጨዋታ ዝግጁ ነን “ብለዋል። “ ሁሉንም ብሔራዊ ቡድን እናከብራለን ፤ ደቡብ አፍሪካ ከጠንካራ ቡድኖች አንዱ ነው ነገርግን እኛ የምንጫወተው ሶስት ነጥብ ለመውሰድ ነው።"ሆሳም ሀሰን ግብፅ ነገ ከምሽቱ 12:00 ከደቡብ አፍሪካ ጋር የምድብ ሁለተኛ ጨዋታዋን ታደርጋለች።
Mostrar todo...
132😁 66👍 16👎 11🔥 3👏 3
Photo unavailableShow in Telegram
“ የዘንድሮው አፍሪካ ዋንጫ ከምንግዜውም በላይ ለማሸነፍ ከባዱ ነው “ ወሊድ ረክራኪ የሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ወሊድ ረክራኪ የዘንድሮው አፍሪካ ዋንጫ ከየትኛውም ጊዜ በላይ ጠንካራ ፉክክር እንደሚኖረው ገልጸዋል። “ የዘንድሮው አፍሪካ ዋንጫ ከምንግዜውም በላይ ለማሸነፍ ከባዱ ይሆናል “ ያሉት ወሊድ ረክራኪ “ እኛ ያለን የተሻለ ጥቅም ደጋፊው ነው “ ብለዋል። “ ሁሉም ቡድኖች በጥሩ ዝግጁነት ቀርበዋል ያለው ሁኔታ ለሁሉም የሚስማማ ነው እያንዳንዱ ቡድን ዋንጫውን ማሸነፍ ይፈልጋል “ ወሊድ ረክራኪ አክለውም “ ደጋፊዎች የበለጠ ጥረት ማድረግ አለባቸው “ ሲሉ የጠየቁት አሰልጣኙ “ ስታዲየም ውስጥ ሊሰማን ይገባል “ ብለዋል።
Mostrar todo...
130👍 38😁 4👎 2
Photo unavailableShow in Telegram
ኪሊያን ምባፔ ሞሮኮ ይገኛል ? ፈረንሳዊው የሪያል ማድሪድ ኮከብ ኪሊያን ምባፔ የሞሮኮን ሁለተኛ የምድብ ጨዋታ ሊታደም እንደሚችል ተዘግቧል። ሞሮኮ ከ ማሊ ጋር በነገው ዕለት የምታደረገውን የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ እንዲታደም ግብዣ እንደቀረበለት ታውቋል። ኪሊያን ምባፔ የሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን አምበል አሽራፍ ሀኪሚ የቅርብ ጓደኛ መሆኑ የሚታወቅ ነው። ሞሮኮ ከማሊ ጋር የምታደርገው የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ ነገ ከምሽቱ 5:00 ሰዓት ይደረጋል። @Tikvahethsport       @kidusyoftahe
Mostrar todo...
302👍 58👎 1🥰 1
ሁለት አይን ካላቸው እኔ በአንድ አይን የተሻለ ማድረግ እችላለሁ “ በ 2023 የውድድር ዘመን በቅድመ ውድድር ዝግጅት ላይ ጆርጂ ሚኑንጉ በአይን ኢንፌክሽን የግራ አይኑን እይታ ለማጣት ተገዶ ነበር። በቀዶ ጥገና ህክምና ተደርጎለት የተሳካ የነበረ ቢሆንም እይታውን ግን ዳግም ለማግኘት ተችግሯል። የህክምና ባለሙያዎች ዳግም የሚወደውን እግር ኳስን መጫወት እንደማይችል ነግረውትም ነበር። “ የህይወቴ ከባዱ እና ፈታኙ ጊዜ ነበር “ ሲል ወቅቱን ያስታውሳል በአይኑ ምክንያት የፕሮፌሽናል ኮንትራት ለማግኘት ተቸግሮ እንደነበረ ይናገራል። ይህን ከባድ ጊዜያት ያሳለፈው ጆርጂ ሚኑንጉ የመጀመሪያ የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታውን በትላንትናው ዕለት ለቡርኪናፋሶ ተሰልፎ መጫወት ቻለ። ተጫዋቹ ቡድኑን ከሽንፈት የታደገች ግብም በጭማሪ ደቂቃ ላይ 90+5 ላይ ማስቆጠር ቻለ። “ ሀገሬ እንድታሸንፍ የተቻለኝን ማድረጌ ትልቅ ደስታን ፈጥሮልኛል “ ሲል ከትላንቱ ድል በኃላ አስተያየቱን ሰጥቷል። አሁን ላይ ይህን ከባድ ጊዜያት አልፎ 22ኛ እድሜው ላይ የሚገኘው ጆርጂ ሚኑንጉ ከአለም የክለቦች ዋንጫ እስከ አፍሪካ ዋንጫው ተሰልፎ እየተጫወተ ይገኛል። “ ይህ እኔን ከህልሜ አያስቆመኝም “ የሚለው ጆርጂ “ ሁለት አይን ካለቸው ተጫዋቾች እኔ በአንድ አይን የተሻለ ማድረግ እችላለሁ “ ሲል ተደምጧል። ጆርጂ በዚህ ሁሉ ከባድ ጊዜያት ግን አብረውት የነበሩትን ያመሰግናል በተለይም ለክለቡ ሲያትል ሳውንደርስ ያለው ምስጋና የላቀ ነው። @tikvahethsport @kidusyoftahe
Mostrar todo...
638👏 123👍 14🥰 7🔥 5
Photo unavailableShow in Telegram
የአፍሪካ ዋንጫን ምን ያህል ሰው ታደመ ? የሞሮኮ አፍሪካ ዋንጫ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታዎች ሲጠናቀቁ በርካታ ተመልካቾች ውድድሩን ተከታትለውታል። የመክፈቻው ጨዋታ ብዙ ተመልካቾች (6️⃣0️⃣,1️⃣8️⃣0️⃣ ) የታደሙት ሲሆን በቀዳሚነት ይጠቀሳል። በመቀጠል :- 👉ግብፅ ከ ዚምባቡዌ :- 2️⃣8️⃣,1️⃣9️⃣9️⃣ 👉ካሜሩን ከ ጋቦን :- 3️⃣5️⃣,2️⃣0️⃣0️⃣ 👉 ሴኔጋል ከ ቦትስዋና :- 1️⃣8️⃣,5️⃣9️⃣1️⃣ 👉አልጄሪያ ከ ሱዳን :- 1️⃣6️⃣,1️⃣1️⃣5️⃣ 👉 ዲሞክራቲክ ኮንጎ ከ ቤኒን :- 1️⃣3️⃣,0️⃣7️⃣3️⃣ ተመልካቾች ከታደሟቸው በርካታ መርሐ ግብሮች መካከል ይገኙበታል። የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታዎቹን በድምሩ 2️⃣3️⃣3️⃣,6️⃣3️⃣4️⃣ ተመልካቾች በስታዲየም ተገኝተው ታድመዋል። @tikvahethsport @kidusyoftahe
Mostrar todo...
203👍 39👏 9👎 7😱 1
Photo unavailableShow in Telegram
NUR TECHNOLOGIES አዳዲስ እና ዱባይ ዩዝድ የሆኑ ላፕቶፓች ☑️HP ☑️Lenovo ☑️Dell ☑️Microsoft Surface ☑️MacBook ☑️Gaming Laptops ☑️Iphone & Samsung Phones ☑️Tablets በተመጣጣኝ ዋጋ ከሙሉ ዋስትና ጋር እናቀርባለን። ለበለጠ መረጃ ከስር የሚገኘውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ Join Our Telegram Channel for more Information 📱📱📱📱📱📱📱📱📱📱 https://t.me/NurTechnologies 📞0911646359 አድራሻ - ቦሌ መድኃኒለም ሰላም ሲቲ ሞል ፊት ለፊት ለአሚር ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
Mostrar todo...
26
Photo unavailableShow in Telegram
ካሜሮን ድል አድርጋለች ! የካሜሮን ብሔራዊ ቡድን ከጋቦን አቻው ጋር ያደረገውን የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል። የካሜሮንን የማሸነፊያ ግብ ኤታ ኢዮንግ ከመረብ አሳርፏል። በጨዋታው ካሜሮናዊው ተጨዋች ብሪያን ምቤሞ ለግብ የሆነ ኳስ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል። የሁለቱን ብሔራዊ ቡድኖች ተጠባቂ ጨዋታ 35,200 ተመልካቾች ስታዲየም ተገኝተው ተከታትለውታል። በምድቡ ሁለተኛ ጨዋታ - ካሜሮን ከኮትዲቯር እንዲሁም - ጋቦን ከሞዛምቢክ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።
Mostrar todo...
178👏 16👍 15😱 9😁 3
Photo unavailableShow in Telegram
78 ' ካሜሮን 1 - 0 ጋቦን ⚽ ኢዮንግ @Tikvahethsport       @kidusyoftahe
Mostrar todo...
19
Photo unavailableShow in Telegram
52' ካሜሮን 1 - 0 ጋቦን ⚽ ኢዮንግ @Tikvahethsport       @kidusyoftahe
Mostrar todo...
23
Photo unavailableShow in Telegram
እረፍት ካሜሮን 1 - 0 ጋቦን ⚽ ኢዮንግ @Tikvahethsport       @kidusyoftahe
Mostrar todo...
15👍 3
Photo unavailableShow in Telegram
35 ' ካሜሮን 1 - 0 ጋቦን ⚽ ኢዮንግ @Tikvahethsport       @kidusyoftahe
Mostrar todo...
12👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
15 ' ካሜሮን 1 - 0 ጋቦን ⚽ ኢዮንግ @Tikvahethsport       @kidusyoftahe
Mostrar todo...
👍 13 7👏 1