TIKVAH-ETHIOPIA
رفتن به کانال در Telegram
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። መረጃ እና መልዕክት ፦ 0998999899 ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም 0979333111 @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ
نمایش بیشتر2025 سال در اعداد

1 572 719
مشترکین
-46024 ساعت
-1 9487 روز
-3 00530 روز
آرشیو پست ها
ድንበር የለሹ የሃኪሞች ቡድን(MSF) ስለ ጋምቤላ ግጭት ምን አለ ?
" በታህሳስ 15፣ 2018 ብቻ ከ100 በላይ በመሳሪያ የቆሰሉ ሰዎችን ተቀብያለሁ "- ድንበር የለሹ የሃኪሞች ቡድን
ድንበር የለሹ የሃኪሞች ቡድን በጋምቤላ ክልል ተባብሶ የቀጠለው ግጭት የበርካቶችን ህይወት እየቀማና ጉዳት እያደረሰ መሆኑን አሰታውቋል።
ቡድኑ በክልሉ ተባብሶ የቀጠለው ግጭት እንዳሳሰበው ገልፆ በትናንትናው እለት ታህሳስ 15፣ 2018 ብቻ ከ100 በላይ በመሳሪያ የቆሰሉ ሰዎችን መቀበሉን አስታውቋል።
ታህሳስ 8፣ 2018 የሃኪሞች ቡድኑ ኩሌ ስደተኞች ካምፕ ወደሚገኘው ፋሲሊቲው የተጎዱ ሰዎች እየጨመሩ መምጣታቸውን ተከትሎ ምላሽ ለመስጠት የሚሆን ስራ መጀመሩን ገልፆ በመጀመሪያው 48 ሰዓት ውስጥ 50 የቆሰሉ ሰዎቾ መምጣታቸውንና 19 ያህሉ አሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ እንደሆኑ ገልጿል።
ድንበር የለሹ የሃኪሞች ቡድን ባለፉት 7 ቀናት 150 የቆሰሉ ሰዎችን መቀበሉን ገልፆ የጤና ሚኒስትርን ድጋፍ ለመደገፍ የሚያገለግሉ የጅምላ ጉዳት ምላሽ ለመስጠት የሚውሉ መሳሪያዎችን ለጋምቤላ አጠቃላይ እና ለጋምቤላ የመጀመሪያ ሆስፒታሎች ማከፋፈሉን ገልጿል።
ቡድኑ የተፈጠረው ግጭት መደበኛ የሆነውን የጤና አገልግሎት ረብሿል ያለ ሲሆን ያለ አድሎ ድጋፍ ለሚሹ ሁሉ አገልግሎት መስጠቱን እንደሚቀጥልና የጤና ባለሙያዎች፣ ታካሚዎች እና የጤና ተቋማት እንዲከበሩ ጠይቋል።
#TilvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
❤ 273😢 77😭 20🙏 8🕊 7😡 2🤔 1
Photo unavailableShow in Telegram
#MPESAEthiopia
100% ነፃ ነው!
የM-PESAን መተግበሪያ በመጠቀም ወደ ሌላ የM-PESA አካውንት ገንዘብ ለመላክ የአገልግሎት ክፍያ የለውም።
መተግበሪያውን ለማውረድ ይህንን ይጫኑ
https://onelink.to/ewsb22
ለተጨማሪ መረጃ በቴሌግራም ያግኙን፥
https://t.me/MPesaETCustomerCare
#MPESAEthiopia
❤ 142😡 19😭 7👏 6🥰 4🙏 1🕊 1
#Tigray
በቅርቡ ወደ አዲስ አበባ አቅንተው የነበሩት የትግራይ ጊዚያዊ አሰተዳደር ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀ) ከፌደራል መንግስት በ7 ጉዳዮች አመርቂ ውይይትና መግባባት መድረሳቸው ተገለፀ።
ወደ ግጭት የሚያመሩ ፓለቲካዊ ሁኔታዎች ወደ ሰላማዊ የጠረጴዛ ውይይት ማምጣት ስምምነት ከተደረሰባቸው ጉዳዮች አንዱ ነው።
የጊዚያዊ አስተዳደሩ የፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት ታህሳስ 15/2018 ዓ.ም ውይይት ተደርጎባቸዋል ስምምነት ተደርሶባቸዋል ብሎ መግለጫ ያወጣባቸው ነጥቦች ምንና ምን ናቸው ?
1. የደመወዝና የበጀት ጉዳይ
በክልሉና በፌደራል መንግስት መካከል ከአቅም በላይ በሆነ የሰራተኛ ቅጥር ምክንያት ሳይለቀቀ የቆየው የመንግስት ሰራተኞች የደመወዝ ጭማሪ በጀት እንዲለቀቅ በመደበኛ ዓመታዊ በጀት ላይ የነበረው መሳሳብ እንዲፈታና ወደ ስራ እንዲገባ መግባባት ተደርሷል።
2. የሰገን ወንዝ የውሃ ፕሮጀክት ግንባታ የሚመለከት
ለመቐለ ከተማና አከባቢዋ በቂ የንፁህ የመጠጥ ውሃ በማቅረብ የነዋሪዎች ችግር ይፈታል ተብሎ የሚጠበቀው ፕሮጀክት በመሆኑ አስፈላጊ የግንባታ እቃዎች ተማልተውለት እንዲቀጥል ተወስኗል።
3. ያልተቋራረጠ የነዳጅ አቅርቦት
ለክልሉ ወርሃዊ የነዳጅ ፍጆታ የሚበቃ ነዳጅ ሳይቆራረጥ እንዲገባ ውይይት ተደርጎበታል መፍትሄ ተቀምጦለታል።
4. ተፈናቃዮች ስለ መመለስና ግዛታዊ አንድነት የማረጋገጥ ጉዳይ
ተፈናቃዮች የመመለስና ግዛታዊ አንድነት የማረጋገጥ ጉዳይ ቀጣይነት ባለው ውይይትና የፊት ለፊት ግንኙነት መፍትሄ እየተበጀለት እንዲሄድ መግባባት ተደርሶበታል።
5. በሰላማዊ ውይይት የፓለቲካ ችግሮች የመፍታት ጉዳይ
የግጭት መንገዶች ተዘግተው ለጠረጴዛ ውይይት ቅድሚያ እንዲሰጠው መግባባት ተደርሶበታል " ራሳችን የፈጠርነው ችግር ራሳችን መፍታት ይገባል " ተብሏል።
6. የአገራዊ የምክክር ሂደትና አፈፃፀሙ የሚመለከት
ከአገራዊ የምክክር ኮሚሽን ከፍተኛ አመራሮች ውይይት ተካሂደዋል። የትግራዩ የምክክር ሂደት በሌሎች ክልሎች ከሚካሄደው ውይይት በተለየ በጦርነቱ የደረሰ ጉዳት ታሳቢ ባደረገ መልኩ እንዲቀጥል ውይይት ተደርጎበታል መግባባት ተደርሶበታል።
7. አገራዊና ክልላዊ ምርጫ በሚመለከት
በቀጣዩ ወርሃ ግንቦት 2018 ዓ.ም የሚካሄደው ሰባተኛው አገራዊና ክልላዊ ምርጫ በትግራይ ለማካሄድ አስቻይ ሁኔታዎች መኖራቸውና አለመኖራቸው አስመልክቶ ጊዚያዊ አስተዳደሩ በያዝነው ሳምንት ይፋዊ መግለጫ እንዲሰጥ መግባባት ላይ ተደርሷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
@tikvahethiopia
❤ 1 310🕊 208😡 91👏 48😭 24🤔 18💔 16😱 12😢 11🙏 9🥰 4
" የፍቼ ሰላሌን ህዝብ ይቅርታ ጠይቃለሁ " - ነብይ ሄኖክ ግርማ
የፍቼ ከተማ ፖሊስ " ሰላሌን የጠንቋይ እና ሟርተኛ ሀገር " ብለው ሰድበዋል ያላቸውን የJPS INTERNATIONAL CHURCH መስራችን ነብይ ሄኖክ ግርማን በቁጥጥር ስር ለማዋል የፍርድ ቤት የእስር ማዘዣ ቢያወጣም እሳቸው #አሜሪካን ሀገር ሆነው ህዝቡን ይቅርታ ጠይቀዋል።
አሜሪካን ሀገር ለአገልግሎት እንደሄዱ የገለጹት ነብይ ሄኖክ ግርማ " በሶሻል ሚዲያ ተቆርጦ የተሰራጨው ንግግር የፍቼ ሰላሌን ህዝብ እንደምጠላ አይነት ትርጉም ይዞ ነው ለዚህ ንግግሬ ይቅርታ ጠይቃለሁ " ብለዋል።
" ለአካባቢው ህዝብ ለመላው ኢትዮጵያውያን ሁሉ ፍቅር እና አክብሮት ኖሮኝ ነው የማገለግለው ፤ በማገለግልበት ቤተክርስቲያን የተለየ የአንድ ጎሳ ግሩፕ የለም፤ ቤተክርስቲያናችን የተለያየ ብሄር የተለያየ ጎሳ እግዚአብሔር አምኖ የሚያመልክበት ቦታ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
" በንግግሬ ያሳዘንኳችሁ ፣ ያስከፋዋችሁ የዛ አካባቢ ተወላጆች በጣም ይቅርታ እጠይቃለሁ ፤ ይቅርታዬን እንድትቀበሉም በጌታ ፍቅር እጠይቃችኋለሁ " ሲሉ አክለዋል።
" የዛ አካባቢ አመራሮች፣ የመንግሥት ቢሮ አመራሮች ይቅርታዬን ተቀበሉኝ። በአካል እዛው ከተማ መጥቼ ይቅርታ የምጠይቅበት ህዝቡንም የማገለግልበት እድልን እግዚአብሔር ያመቻችልኛል " ብለዋል።
በአጭር ቀን ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱም ገልጸዋል።
የፍቼ ከተማ ፖሊስ ነብይ ሄኖክ ግርማን ህዝብ በመሳደብ ፣ ብጥብጥ በመፍጠር በማሰብ ወንጀል ከሷቸዋል።
የእስር ማዘዣም አውጥቶባቸው የነበረ ቢሆንም እሳቸው በሰዓቱ ወደ አሜሪካ ሀገር ጉዞ ላይ ነበሩ።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
@tikvahethiopia
❤ 728😡 714🤔 61🕊 25🙏 23👏 21😭 20🥰 10😱 4
ዋሪት ፈርኒቸር !
ክቡራን ደንበኞቻችን! መጪው በዓል የሰላም፤የፍቅር እና የስኬት እንዲሆንላችሁ ከወዲሁ ከልብ እየተመኘን፡ ምቾታቸውን እና ጥራታቸውን የጠበቁ ምርቶቻችንን በሁሉም የማሳያ ቅርንጫፎቻችን ከበዓ ቅናሽ ጋር እስከ ጥር 15 ቀን 2018 ዓ.ም. አዘጋጅተን እንጠብቅዎታልን!!
Visit us today @
📍 22 - ዋሪት ህንፃ
📍 ጉርድ ሾላ - ሴንቸሪ ሞል
📍 ለቡ - ቫርኔሮ ፊት ለፊት
📍 አዳማ - ሶረቲ ሞል
📍 ቡልቡላ- ልዑል ህንፃ ፊት ለፊት
📍 ወሎ ሰፈር- Ethiolife life real estate
📍 ጦር ሀይሎች- ኩዊንስ ፊት ለፊት
ዋሪት ፈርኒቸር
ትክክለኛ ምርጫ!
ለተጨማሪ መረጃ: ☎️ 0911210706/07
https://t.me/warytfurniture
tiktok:/warytzefurniture
❤ 165🙏 3🕊 3
Photo unavailableShow in Telegram
የትኛው ይሁንሎት? መኪናው? ፍሪጁ፥ TV፥ የልብስ ማጠብያው? በዲጅታል ባንኪንግ ወይም ቅርንጫፍ በመምጣት የአቢሲንያ ባንክ አገልግሎቶችን ያግኙ። ሽልማቱ የእርስዎ ሊሆን ይችላል።
#StartRenewGrow #BOARewards #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
Photo unavailableShow in Telegram
" ልክፈላችሁ ሂዱልኝ ! "
" 3,000 ዶላር እሰጣችኋለሁ (ከ465,000 ብር በላይ) ፤ ነጻ በረራ ሁሉ አዘጋጃለሁ ብቻ እናተ በፍቃዳችሁ ምድሬን ለቃችሁ ውጡልኝ " ስትል አሜሪካ በሀገሯ ለሚገኙ ሰነድ አልባ ስደተኞች መልዕክት አስተላልፋለች።
በ2026 መጨረሻ ላይ ከአሜሪካ በገዛ ፈቃዳቸው ለመውጣት ለሚፈልጉና በፈረንጆች እስከ ታህሳስ 31 ለሚመዘገቡ ስደተኞች ሀገሪቱ ነፃ በረራ እንዲሁም የ3000 ዶላር ክፍያም ይሰጣቸዋል።
በገዛ ፈቃዱ አልወጣም ያለ ስደተኛ ግን ፦
- እስራት፣
- በግዳጅ መባረር
- ዳግም ወደ አሜሪካ ምድር መግባት እንዳይችል እገዳ እንደሚጣልበት ሀገሪቱ አሳውቃለች።
Via @tikvahethmagazine
❤ 1 290😭 657🤔 144😱 90💔 76👏 66😡 63🙏 56🕊 50😢 25🥰 24
" ግለሰብን እንደዛ ማላት ይችላል ሃገርን ግን እንደዛ ማለት አይችልም። ... ከፍርድ ቤት የእስር ማዘዣ ወጥቷል " - ኢንስፔክተር ታምሩ ባይሳ
የሰሜን ሸዋ ዞን ሰላሌን ተሳድቧል ያላቸውን የሃይማኖት መምህር ሄኖክ ግርማን በቁጥጥር ስር ለማዋል እንቅስቃሴ መጀመሩን ገልጿል።
የሰሜን ሸዋ ዞን አቃቤ ህግ ነብይ ሄኖክ ግርማ የ "JPS INTERNATIONAL CHURCH" መስራች ህዝብን በመሳደብ ብጥብጥ በመፍጠር በማሰብ ወንጀል ከሷቸዋል።
ከሰሞኑ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሃይማኖት አስተማሪው አንዲት ሴት ከየት እንደመጣች ከጠየቁ በኋላ ሴትየዋ ከሰላሌ መሆኗን ስትናገር ነብይ ሄኖክ " ሃገሩ የጠንቋይ ነው " ብለው ሲናገሩ የሚያሳይ ቪዲዮ ተሰራጭቶ የብዙዎች መነጋገሪያ ሆኗል።
ቪዲዮው በማህበራዊ ሚዲያዎች ከተለያዩ አካላት ግብረመልስ ያገኘ ሲሆን ነብይ ሄኖክ ግርማም የወጣው ቪዲዮ ያለ አግባብ ተወስዶ ቅሬታን ፈጥሯል በማለት #ይቅርታ ጠይቀዋል።
የፊቼ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኢንስፔክተር ታምሩ ባይሳ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ በሰጡት ቃል፥ " ነብይ ሄኖክ ሰላሌን ' የጠንቋይና የሟርተኛ ሃገር ' " ብሏል ያሉ ሲሆን " ግለሰብን እንደዛ ማለት ይችላል፤ ሃገርን ግን ማለት አይቻልም " ሲሉ ተናግረዋል።
ኢንስፔክተሩ በቪዲዮው ላይ የታየችው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሏን ገልፀው ነብይ ሄኖክን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከፍርድ ቤት የእስር ማዘዣ ወጥቷል ብለዋል።
" ነብይ ሄኖክ አዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ አካባቢ ነዋሪ መሆኑን ሰምተናል " ያሉት ኢንስፔክተር ታምሩ የተያዘችው ግለሰብ ስለሁኔታው ማመኗን ገልፀዋል።
" በቲክቶክ እና በማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጨው ቪዲዮ በማስረጃነት ተይዟል በህግ አካሄድ ሰንሰለትን በመከተል በቁጥጥር ስር ለማዋል እየተሰራ ነው " ሲሉ አክለዋል።
@tikvahethiopia
👏 1 720❤ 793😡 143🤔 64😭 46🙏 31💔 27🕊 15😢 7😱 4🥰 3
Repost from N/a

" ተጠርጣሪው በተለምዶአዊው ንግግር ሊገለፁ የማይችሉ አስፀያፊ ቃላትን በመጠቀም በትውልዱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሲያሳድር ነበር " - ፖሊስ
የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ከህብረተሰቡ ባህል፣ ሞራልና እሴት ተቃራኒ የሆኑ መልዕክቶችን በማህበራዊ ሚዲያ ሲያሰራጭ የነበረን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ።
ከህብረተሰቡ ባህል፣ ሞራልና እሴት ተቃራኒ የሆኑ መልዕክቶችን በማህበራዊ ሚዲያ ሲያሰራጩ ከነበሩ ግለሰቦች አንዱ የሆነው ነዋሪነቱ በን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 6 የሚገኝ ናትናኤል ባደግ ገብሬ የተባለን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል።
ግለሰቡ የማህበራዊ ሚዲያን (YouTube እና TikTok) ን በመጠቀም በንግግር ልቅ ፆታዊ ግንኙነትን የሚያበረታታና የሚያስፋፋ አፀያፊ መልዕክቶችን ሲያሰራጭ በመቆየቱ በቁጥጥር ስር እንዳዋለው አስረድቷል።
ተጠርጣሪው በተለምዶአዊው ንግግር ሊገለፁ የማይችሉ አስፀያፊ ቃላትን በመጠቀም በትውልዱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሲያሳድር እንደነበር እና መሰል ይዘቶችን በተደጋጋሚ ጊዜ በመስራት በማህበራዊ ሚዲያ (YouTube እና TikTok) በመጠቀም ሲያሰራጭ እንደነበር ፖሊስ አብራርቷል፡፡
ፖሊስ በቁጥጥር ስር በዋለው ናትናኤል ባደግ ወይም " የማህበራዊ ሚዲያ አንቂ ወይም ይዘት ፈጣሪ ነኝ " በሚለው ግለሰብ ላይ ምርመራ ጀምሯል።
በአንዳንድ ኃላፊነት በማይሰማቸው ግለሰቦች በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከህብረተሰቡ ሞራል ባህልና እሴት ባፈነገጠ ሁኔታ አሉታዊ መረጃዎች እየተሰራጩ መሆኑን ያስታወቀው ፖሊስ በማህበረሰቡ በተለይም ታዳጊ በሆኑ ህፃናት ሥነ-ልቦናና ሞራል ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ መሆኑን ገልጿል። በቀጣይም ተመሳሳይ ድርጊት ውስጥ በሚገቡ ግለሰቦች ላይ ተገቢውን ህጋዊ ርምጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል።
ከዚህ ቀደም ፖሊስ በቲክቶክና ሌሎች የማህበራዊ ሚዲያዎች ከህብረተሰቡ ባህል፣ ሞራልና እሴት ተቃራኒ የሆኑ መልዕክቶችን አሰራጭተዋል ፣ በአለባበስም አሳይተዋል ያላቸውን ወጣቶች በቁጥጥር ስር ውሎ ለቋቸዋል።
#TilvahEthiopiaFamilyAA
#AddisAbabaPolice
@tikvahethiopia
Photo unavailableShow in Telegram
እድለኞቹ ከተሞች እነሆ! 💰
በመላው ሀገሪቱ በሽ እድለኞች ያፈራው ፕሮግራማችን እነዚህን ቦታዎች ነክቶ አልፏል!
ስለተሳትፎአችሁ እጅግ እናመሰግናለን!
#SafaricomEthiopia
#furtheraheadtogether
#besh
❤ 109😡 32🙏 11🤔 8🥰 6💔 2
" ተጠርጣሪው በተለምዶአዊው ንግግር ሊገለፁ የማይችሉ አስፀያፊ ቃላትን በመጠቀም በትውልዱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሲያሳድር ነበር " - ፖሊስ
የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ከህብረተሰቡ ባህል፣ ሞራልና እሴት ተቃራኒ የሆኑ መልዕክቶችን በማህበራዊ ሚዲያ ሲያሰራጭ የነበረን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ።
ከህብረተሰቡ ባህል፣ ሞራልና እሴት ተቃራኒ የሆኑ መልዕክቶችን በማህበራዊ ሚዲያ ሲያሰራጩ ከነበሩ ግለሰቦች አንዱ የሆነው ነዋሪነቱ በን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 6 የሚገኝ ናትናኤል ባደግ ገብሬ የተባለን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል።
ግለሰቡ የማህበራዊ ሚዲያን (YouTube እና TikTok) ን በመጠቀም በንግግር ልቅ ፆታዊ ግንኙነትን የሚያበረታታና የሚያስፋፋ አፀያፊ መልዕክቶችን ሲያሰራጭ በመቆየቱ በቁጥጥር ስር እንዳዋለው አስረድቷል።
ተጠርጣሪው በተለምዶአዊው ንግግር ሊገለፁ የማይችሉ አስፀያፊ ቃላትን በመጠቀም በትውልዱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሲያሳድር እንደነበር እና መሰል ይዘቶችን በተደጋጋሚ ጊዜ በመስራት በማህበራዊ ሚዲያ (YouTube እና TikTok) በመጠቀም ሲያሰራጭ እንደነበር ፖሊስ አብራርቷል፡፡
ፖሊስ በቁጥጥር ስር በዋለው ናትናኤል ባደግ ወይም " የማህበራዊ ሚዲያ አንቂ ወይም ይዘት ፈጣሪ ነኝ " በሚለው ግለሰብ ላይ ምርመራ ጀምሯል።
በአንዳንድ ኃላፊነት በማይሰማቸው ግለሰቦች በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከህብረተሰቡ ሞራል ባህልና እሴት ባፈነገጠ ሁኔታ አሉታዊ መረጃዎች እየተሰራጩ መሆኑን ያስታወቀው ፖሊስ በማህበረሰቡ በተለይም ታዳጊ በሆኑ ህፃናት ሥነ-ልቦናና ሞራል ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ መሆኑን ገልጿል። በቀጣይም ተመሳሳይ ድርጊት ውስጥ በሚገቡ ግለሰቦች ላይ ተገቢውን ህጋዊ ርምጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል።
ከዚህ ቀደም ፖሊስ በቲክቶክና ሌሎች የማህበራዊ ሚዲያዎች ከህብረተሰቡ ባህል፣ ሞራልና እሴት ተቃራኒ የሆኑ መልዕክቶችን አሰራጭተዋል ፣ በአለባበስም አሳይተዋል ያላቸውን ወጣቶች በቁጥጥር ስር ውሎ ለቋቸዋል።
#TilvahEthiopiaFamilyAA
#AddisAbabaPolice
@tikvahethiopia
❤ 1
"በኢታንግ ልዩ ወረዳ ዛሬ ንጋት 11 ሰዓት በጀመረው ተኩስ ከ30 በላይ ሰዎች ተገድለዋል። የሞቱት ህፃናትም በርካታ ናቸው። የአጎቴ ልጆች የት እንዳሉ አይታቅም። ቤታቸው ተቃጥሏል" - ነዋሪዎችና ቤተሰብ
➡️ "ሥራ እየሰራን ነው፤ ስንጨርስ እንነግራችኋለን"- የጋምቤላ ክልል ፕሬዝዳንት ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ
በጋምቤላ ክልል ኢታንግ ልዩ ወረዳ ተርፋም ቀበሌ ዛሬ ረቡዕ ታህሳስ 15 ቀን 2018 ዓ/ም ከንጋቱ 11 ሰዓት ጀምሮ በተከፈተ ተኩስ "ከ30 በላይ ሰዎች መገደላቸውን" ነዋሪዎችና የዓይን እማኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።
በክልሉ የተለያዩ ወረዳዎች ባለፉት ሳምንታት በጸጥታ ችግር የንጹሐን ህይወት መቀጠፉን፣ ተጎጅዎች የህክምና አገልግሎት እንዳላገኙ ነዋሪዎች፣ የተጎጂ ቤተሰቦች፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን መግለጻቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ዛሬ ደግሞ በኢታንግ ልዩ ወረዳ "በርካቶች ተገድለዋል" ተብሏል።
የአካባቢው ነዋሪዎችና አንድ የዓይን እማኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ "በኢታንግ ልዩ ወረዳ ዛሬ ንጋት 11 ሰዓት በጀመረው ተኩስ ከ30 በላይ ሰዎች ተገድለዋል። የሞቱት ህፃናትም በርካታ ናቸው" ብለዋል።
በወረዳው ተርፋም ቀበሌ የተኩል ልውውጥ ሲደረግ መዋሉን በመግለጽ፣ "ሁኔታው ከበድ እያለብን ነው" የሚሉት ነዋሪዎቹ፣ በርካታ ሰዎች በጥይት ተመትነው እንደቆሰሉ፣ ንጋት ላይ ሰዎች በተኙበት ቤት የማቃጠል ድርጊት እንደተፈጸመ አስረድተዋል።
ከቦታው ሆነው የተኩሱን ሁኔታ በቅርብ ርቀት ሲከታተሉ የነበሩ አንድ የዓይን እማኝ የክልሉ ነዋሪ፣ "የአንድ፣ የሁለት ዓመት ህፃናት" ጨምር ህይወታቸው ማለፉን ገልጸዋል። "የኔም የአጎቴ ልጆች የት እንዳሉ አይታቅም። ቤታቸው ተቃጥሏል። ልጆች፣ አረጋውያን፣ ወጣቶችም ተገድለዋል" ሲሉ ገልጸው፣ መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጥ በአንክሮ አሳስበዋል።
"ቤቶች ተቃጥለዋል፤ በቃጠሎና በጥይት ህይወታቸው ያረፈው በርካታ ናቸው። በቦንብ የተመቱ ነዋሪዎችም አሉ" የሚሉት የዓይን እማኝ፣ "ከደቡብ ሱዳን የገቡ ሰዎች በተኩሱ ሲሳተፉ ተስተውለዋል" ሲሉ አክለዋል።
የጸጥታ ችግሩ በተመለከተ ምን ምላሽ እንዳላቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጠየቃቸው የክልሉ ፕሬዚዳንት ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ፣ " የጸጥታ አካላት ጋር ደውሉ ስብሰባ ላይ ነኝ" ያሉ ሲሆን፣ የጸጥታ ኃላፊው ስልክ እንዳላነሱ ስንነግራቸውም፣ "ሥራ እየሰራን ነው፤ ስንጨርስ እንነግራችኋለን " የሚል አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።
የክልሉ ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ለጊዜው ስልክ ያላነሱ ሲሆን፣ የክልሉ መንግስት በበኩሉ፣ የጋምቤላ ከተማን ጨምሮ "የጸጥታ ችግር በሚስተዋልባቸው የክልሉ አካባቢዎች" "ከጸጥታ አካላት ውጭ የሰውና የተሽከርካሪ" የሰዓት እላፊ ገደብ መጣሉን አስታውቋል።
በክልሉ የተለያዩ ወረዳዎች "በአኘዋክና ኑዌር ብሔረሰቦች መካከል" በተለያዩ ጊዚያቶች "ግጭት" ሲነሳ እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን፣ ከአመት በፊት ቆሞ እንደነበር አሁን ደግሞ ማገርሸቱን፣ ችግሩን ለማስቆምም እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሽኔ አስቲን ከሳምንት በፊት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጻቸው ይታወሳል።
የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ በበኩሉ፣ ችግሩን ለማስቆም እየተሰራ መሆኑን፣ 18 ተጠርጣሪዎች እንደተያዙ ከሳምንት በፊት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጹ የሚታወስ ሲሆን፣ ነዋሪዎቹ ደግሞ ዛሬ በኢታንግ ልዩ ወረዳ የተኩስ ልውውጥ እንደተደረገ ገልጸው፣ "በደቡብ ሱዳን የሚኖሩ የአኙዋክና ኑዌር ብሔረሰቦች" እንዳሉ፣ በዛሬ ተኩስም "ከደቡብ ሱዳን የመጡ ታጣቂዎች" እንተሳተፉ እየተናገሩ ናቸው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
❤ 490😭 265🕊 44😱 18😡 15💔 14🤔 13🙏 9😢 8