TIKVAH-ETHIOPIA
Открыть в Telegram
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። መረጃ እና መልዕክት ፦ 0998999899 ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም 0979333111 @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ
Больше2025 год в цифрах

1 572 505
Подписчики
-46024 часа
-1 9487 дней
-3 00530 день
Архив постов
" ደግመን ደጋግመን አሳውቀናል " - ጊዜያዊ አስተዳደሩ
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በላከው ደብዳቤ በክልሉ ተፈናቃዮች ስላሉበት ሁኔታ ደግሞ ደጋግሞ ማሳወቁን አመልክቷል።
" በክልላችን ያለውን ሰብአዊ ቀውስ እና የእርዳታ ፍላጎት በተመለከተ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሰብሳቢነት የሁሉም ክልሎች ፕረዚደንቶች እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽነሮች በተገኙበት በየጊዜው በሚካሄደውን የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ም/ቤት ላይ አሳሳቢነቱን እየገለጽን መምጣታችን እና ከፌደራል ለድጋፍና ክትትል ወደ ክልላችን በየጊዜው የሚመጡ ቡድኖች በአካል ተግኝተው እያዩት እና እየተረዱት የቆዩት ነው " ብሏል።
በተጨማሪ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ጨምሮ የክልል እና የፌደራል መንግስታዊ ተቋማትና ዩኒቨርስቲዎች፤ በክልሉ የሚገኙ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት (Humanitarian Agencies) በጋራ በመሆን የተጠናውን የ2024 Multi-Sectoral Meher Seasonal Assessment መሰረት በክልሉ 2.459 ሚልዮን ተረጂ ያለ መሆኑ በጥናት መረጋገጡን ገልጿል።
" በተለያዩ ወቅቶች በሚደረጉ ግንኙነቶች (በደብዳቤ፣ በሪፖርት፣ በስልክ፣ በ-Virtual Meetings፣ በአካል በመገኘትም ጭምር፣ በክልላችን ባሉት የ-Cluster and ECC አደረጃጀቶች) ያሉብንን ችግሮች እያስረዳን የመጣን መሆናችን ይታወቃል " ብሏል።
በክልሉ ያለውን ሁለንተናዊ ችግር አገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን አለም እንዲያውቀው እየተደረገ የመጣ ጉዳይ መሆኑ በሚገባ የሚታወቅ መሆኑ ሊሰመርበት የሚገባ ጉዳይ ነው ሲልም አክሏል።
አሁንም በመጠለያ ጣቢያዎች (IDP Camps) የሚገኙ ተፈናቃዮች የሚሰጣቸው የምግብ ድጋፍ በቂ አለመሆኑን ገልጿል።
" ከምግብ ውጪ ያለባቸው መሰረታዊ ፍላጎቶች ፦
- የጤና፣
- ውሃ WaSH፣
- የልብስ እና መሰረታዊ ቁሳቁስ፣
- የመጠሊያ፣
- የእህል ማስፈጫ ዋጋ፣
- የልጆቻቸው ትምህርት ወጪ ... ወዘተ ባለሟሟላታቸው ምክንያት ለነዚህ መሰረታዊ ፍላጎቶቻቸው ወጪ የሚሽፍኑት ከሚሰጣቸው ምግብ (15 ኪ/ግራም እህል፣ 1.5 ኪ/ግራም ጥራጥሬ እና 0.45 ሊትር የምግብ ዘይት በመሆኑ ምክንያት የሚሰጣቸው የምግብ ድጋፍ ይህንን ሁሉ ወጪያቸው ሸፍኖ በሂወት ለመኖር የሚያስችላቸው አለመሆኑ መታወቅ አለበት " ብሏል።
ይህንን ሰብአዊ ቀውስ በህፃዕ መጠለያ ጣቢያ ብቻ ሳይሆን በሌሎቹ 146 መጠለያ ጣቢያዎች ጭምር እያጋጠመ ያለ ችግር መሆኑን አስረድቷል።
" በየወሩ የምግብ እርዳታ እያቀረቡ ያሉት የJEOP/CRS Partners ከላይ የተጠቀሰው መጠን ያለው ምግብ ባለማቅረባቸው እየተፈጠረ ያለ ችግር ሳይሆን ተፈናቃዮች ከምግብ በተጨማሪ ሌሎች ወጪዎችን ለመሸፈን ተጨማሪ ድጋፎች ባለማግኘታቸው የተፈጠረ መሆኑ ሁላችን ግልጸኝነት ሊኖረን ይገባል " ብሏል
በመሆኑም ፓርትነሮች በተለይ ከፕሪቶሪያ ስምምነት ብኋላ ከተጠቃሚዎች ምልመላ እስከ እርዳታ ማሰራጨት እና እርዳታው ለተባለለት አላማ ስለመዋሉ ክትትል (Post Distribution Monitoring) እስከ ማድረግ ያለው ሂደት ያለ ምንም የመንግስት ጣልቃ ገብነት ራሳቸው ችለው እየሰሩ የቆዩ እንደሆነ ገልጿል።
አሁንም በክልሉ ላይ በተለይ በተፈናቃዮች፣ በከተማ ነዋሪዎች እና በየቦታው ያሉ ከ1.7 ሚልዮን በላይ ያለምንም ድጋፍ የተመለሱ ተመላሽ ተፈናቃዮች ያለው ከፍተኛ ችግር ከክልሉ እና በክልሉ ከሚገኙ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት አቅም በላይ መሆኑን አመልክቷል።
ያለው የነዳጅ እጥረትም ሰብእዊ ድጋፍ በወቅቱ እንዳይደርስ የበለጠ እያባባሰው መሆኑን አስረድቷል።
የፌደራል መንግስት፣ የክልል መንግስታትና መላው የኢትዮጵያ ህዝብ፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ያለውን አስከፊ የሰብአዊ ቀውስ ተረድተው ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።
የተፈናቃዮች መሰረታዊ ችግር የሚፈታው ግን ወደ ቤታቸው ሲመለሱ መሆኑን ገልጿል።
(ሙሉ ደብዳቤው ከላይ ተያይዟል)
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
@tikvahethiopia
❤ 673😡 60🤔 28😭 21🙏 19🕊 15💔 9🥰 5😢 5😱 2
" የሚላከው ሰብዓዊ ድጋፍ ለተፈለገው ዓላማ እንዳይወል እያደረገ ይገኛል፤ የሰሞኑ የህፃፅ መጠለያ ጣቢያ ማስረጃ ነው ! " - ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር)
የህወሓት ቡድን " ሕዝብን በርሃብ በመቅጣት ለፖለቲካ መሣሪያነት የመጠቀም ተግባሩን ዳግም በትግራይ ሕዝብ ላይ እያሳየ ነው " አሉ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽነር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር)።
የማህበራዊ ሚዲያ በመጠቀም ድጋፍ እያሰባሰቡ ያሉ አካላትም ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አስጠንቅቀዋል።
ኮሚሽነር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር) ምን አሉ ?
- ህወሓት የፌደራል መንግስት በትግራይ ክልል በመጠለያ ማዕከላትና በልማታዊ ሴፍቲኔት መርሃ ግብር የሚያቀርበውን ሰብዓዊ ድጋፍ ለተፈለገው ዓላማ እንዳይወል እያደረገ ይገኛል ብለዋል። የሰሞኑ የህፃፅ መጠለያ ጣቢያ ማስረጃ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
- ቡድኑ የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ትኩረት ለመሳብ ሲል በትግራይ ክልል በመጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ ወገኖች የሚቀርብን ሰብዓዊ ድጋፍ በመንጠቅ ድራማዊ ፕሮፓጋንዳ እያስተጋባ ነው ብለዋል።
- ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የፌደራል መንግስት በግልጽ መረጃና ማስረጃ የሚልከው ሰብዓዊ ድጋፍ የት እንደገባ መጠየቅ አለበት ፤ በቡድኑ የሃሰት ፕሮፓጋንዳ መደናገር እንደሌለበት ሲሉ ገልጸዋል።
- የፌደራል መንግስት በትግራይ ክልል አስተማማኝና ቀጣይነት ያለው ሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ እያደረገ ይገኛል ብለዋል።
- በትግራይ ክልል ከባለፈው ጥር 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታኅሳስ ወር 2018 ዓ.ም ድረስ ሁለት ሚሊየን ኩንታል በገንዘብ ሲተምን 32 ቢሊዮን ብር የሚገመት ሰብዓዊ ድጋፍ ተሰራጭቷል ሲሉ ገልጸዋል።
- ህወሓት የሚላከው ሰብዓዊ ድጋፉ ተደራሽ እንዳይሆን በማስተጓጎል፤ ድጋፉን ከችግረኛ ዜጎች በመንጠቅ ዳግም የሕዝብ ጠላትነቱን እያረጋገጠ ይገኛል ብለዋል።
- ኮሚሽኑ የድጋፍ ጥሪ ባላቀረበበት ሁኔታ በማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች በቡድንም ሆነ በተናጠል የሚደረጉ የድጋፍ ማሰባሰብ ዘመቻ የአሰራር ስርዓትን የጣሱ ህገ-ወጥ አካሄዶች ናቸው ሲሉ ተናግረዋል።
- የተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮችን በመጠቀም ሰብዓዊ ድጋፍ በማሰባሰብ ላልተገባ ዓላማ እያዋሉ የሚገኙ አካላት ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ይገባል ሲሉ አስጠንቅቀዋል። #ENA
@tikvahethiopia
😡 619❤ 584🤔 51💔 22😢 21🕊 17👏 11😭 9🙏 7🥰 5
" ያለ ስጋት የቀረንን እድሜ እንድንኖር የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አፋጣኝ ምላሽ ይስጠን "-ቅሬታ አቅራቢዎች
የኩላሊት ንቅለ ተከላ ያደረጉ ታካሚዎች የሚወስዱት መድኃኒት አቅርቦት ከወር በላይ ለሚሆን ጊዜ በመጥፋቱ አብዛኛው ህሙማን ወደ ከፋ ችግር ውስጥ እየገባ በመሆኑ አፋጣኝ ምላሽ ይሰጠን ሲሉ የጠየቁ ታማሚዎች ቅሬታቸውን ለጤና ሚኒስቴር ማስገባታቸው ታውቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው ቅሬታ አቅራቢዎች ለጤና ሚኒስቴር ያስገቡት ደብዳቤ "ያለ ስጋት የቀረንን እድሜ እንድንኖር የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አፋጣኝ ምላሽ ይስጠን" የሚል ተማጽኖን የያዘ ነው።
ቅሬታ አቅራቢዎቹ " እኛ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ያደረግን ስንሆን በተደጋጋሚ የኩላሊት መድሀኒት አቅርቦት እና የላብራቶሪ ምርመራ መጥፋት እየተከሰተ ለብዙ ችግር እየተዳረግን እንገኛለን " ብለዋል።
ለጤና ሚኒስቴር የገባው የተማጽኖ ደብዳቤ በአዲስ አበባ እና ከአዲስ አበባ ውጪ የሚገኙ ጉዳዩ የሚመከታቸውን የኩላሊት ንቅለ ተከላ ያከናወኑ ዜጎችን በመወከል 35 ሰዎች ፊርማቸውን አኑረውበታል።
ደብዳቤው " የንቅለ ተከላ መድሀኒትን በብቸኝነት የሚያቀርበው የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል መሆኑ እየታወቀ: በድንገት መድሀኒት አልቋል ማለት ከየት እንድናገኝ ታስቦ እንደሆነ አሳዛኝ ነው " በማለት የመድኃኒቱን ሰአት ማዛነፍ እና ማቋረጥ በህይወት የመኖር እና ያለመኖር ጉዳይ ነው ይላል።
በተጨማሪም " መድሀኒታችንን አይደለም ለአንድ ቀን መዝለል ሰዓት እንክዋን ሲዛነፍ በህይወት የመኖር እና ያለመኖር ከዚያ ከተረፈም ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ እና ስነልቦናዊ ቀውስ ወደሚያስከትለው ዳያሊሲስ የሚመልስ ነው " ሲሉ አክለዋል።
የመድኃኒት አቅርቦቱ በመቋረጡ ለምኖ ላሳከመ ቤተሰብ ዱብዳ እና አስደንጋጭ ነው ሲሉም የችግሩን ግዝፈት አስረድተዋል።
ቅሬታውን ወደ ጤና ሚኒስቴር ያደረሱት ለጳውሎስ ሆስፒታል ንቅለ ተከላ ከፍል እንዲሁም ለአስተዳደር ክፍል ጉዳዩን ቢያሳውቁም ጊዜያዊ እንጂ ዘላቂ መፍትሄ ማግኘት ባለመቻላቸው ነው።
" ከዚህ ቀደም መድሀኒቶቹ ሲጠፉ በጣም ከቆየ 15 ቀን ድረስ ጠፍቶ ቢቆይ ነው " ያሉ ሲሆን አሁን የመድኃኒት አቅርቦቱ ከወር በላይ በመቋረጡ ህሙማን እጃችን ላይ ያለውን መድኃኒት ለሌላው ታማሚ እያዋስን ቆይተናል ነው ያሉት።
ከመድኃኒት አቅርቦት ችግሩ ሌላም የታክሮሊሞስ ምርመራ በኬሚካል እጥረት ምክኒያት መቆሙ ጠቅሰዋል።
ቅሬታ አቅራቢዎቹ ለጤና ሚኒስቴር ጉዳዩን በሚመለከት ባስገቡት ደብዳቤ ያቀረቡት የመፍትሄ ሃሳብ ምንድነው ?
አንደኛ የመድሀኒት ግዢ ሲፈፀም የታማሚዎችን ቁጥር ባገናዘበ መልኩ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ተሞከሮ በመውሰድ የአንድ አመት ግዢ ቢፈፀም።
ሁለተኛ እንደ ብዙ የአፍሪካ ሀገራት ህሙማን ቢያንስ ለ2 ወር ከተቻለ ደግሞ የ3 ወር መድሀኒት እጃችን ላይ ቢገባ።
ሶስተኛ የከፍለ ሀገር ታማሚዎች ለትራንስፖርት እና ለመኝታ እንዲሁም የምግብን ወጪ ከመድሀኒት ወጪ ጋር ተዳምሮ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጫና እያደረገ ስለሆነ ረዘም ላለ ጊዜ የመድሀኒት አቅርቦት ቢያገኙ።
አራተኛ የታክ ሌቭል መመርመሪያ ኬሚካል ልክ እንደመድሀኒቱ የአንድ አመት ጊዜን ባገናዘበ መንገድ ቢገባ" የሚሉት ይገኙበታል።
እነዚህን እና ሌሎችንም ተጨማሪ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያግዙ ነጥቦችን በዝርዝር በመጥቀስ ለጤና ሚኒስቴር ደብዳቤ ያስገቡት ታካሚዎቹ ጉዳያቸው"ትኩረት ተሰጥቶት ያለ ስጋት የቀረንን እድሜ እንድንኖር የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጠን ስንል በትህትና እንጠይቃለን" ሲሉ ተማጽኖአቸውን አቅርበዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቅሬታ አቅራቢዎቹ በተቀበለው ቃል ደብዳቤያቸው ታህሳስ ሁለት 2018 ዓም ካስገቡ በኋላ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ጋር በመገናኘት ተወያይተዋል።
ዶ/ር መቅደስ ችግራቸውን በመስማት ጉዳያቸውን ወደ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት እንደመሩላቸው ገልጸዋል።
ቅሬታ አቅራቢዎቹ በተመሩት መሰረት ወደ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ቢመላለሱም ችግራቸው እስካሁን እንዳልተፈታ ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሚመለከታቸው አካላት በማነጋገር ተጨማሪ መረጃ የሚያደርስ ይሆናል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
@tikvahethiopia
" ጧሪ ቀባሪ ልጃችንን ነዉ የነጠቁን " - የሟች ወላጅ
አቶ ባና ቦና ይባላሉ ነዋሪነታቸው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ቡንቲ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ እንደሆነ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
አቶ ባና ቦና ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ልጃቸው አብነት ባና ቦና ከጓደኛዉ ጋር ሆነዉ ሞተር ሳይክል ለማስጠገን ወደ አርባምንጭ ከተማ እንደሄዱ ገልጸዋል።
ሞተር ሳይክላቸውን አስጠግነዉ ሲመለሱ ግን በጋርዱላ ዞን ደራሼ ወረዳ ገበል በኖ ቀበሌ ' ሆልቴ ' ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ሲደርሱ የፖሊስ አባልን ጨምሮ የተወሰኑ ሰዎች አንድ ሚኒባስ አስቁመዉ ተሳፋሪዎችን እያወርዱ ያገኟቸዋል።
እነሱንም ሞተር እንዲያቆሙ ሲጠይቁ ከቆሙ በኋላ ገንዘብና ስልኮቻቸዉን ከዘረፉ በኋላ ጥቃት ፈፅመዉባቸዉ ልጃቸዉ መገደሉን አቶ ባና ቦና ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።
ሟች አብነት ባና ገና የ19 ዓመት ወጣት ሲሆን ታናናሹቹ እንዲማሩ ትምህርቱን አቋርጦ በእርጅና ዉስጥ ያሉ አባትና እናቱን በማገዝና በመጦር ላይ የነበረ ወጣት እንደሆነ ወላጅ አባቱ ተናግረዋል።
" ልጄ መገደሉን የሰማሁት ስንፈልገዉ አድረን ጥቃቱ በተፈፀመ ማግስት በአከባቢው በሚገኝ አንድ የበቆሎ ማሳ ዉስጥ በዘግናኝ ሁኔታ ተገድሎ ተገኝቶ ሆስፒታል ከተወሰደ በኋላ ተደዉሎልን ነዉ " ብለዋል።
ወላጅ አባት " ጧሪ ቀባሪ ልጃችንን ነዉ የነጠቁን " ሲሉ በታላቅ ሀዘን ዉስጥ ሆነዉ ተናግረዋል።
" ልጃችን በምን ጥፋቱ ገና በለጋ ዕድሜው እንደተገደለ የምናዉቀዉ ነገር የለም " የሚሉት አባት ስለተፈጠረዉ ሁኔታ ከሞት አፋፍ የተረፈዉ ጓደኛዉና አብሮ አደጉ ካሳሁን መንገድ ላይ ከወደቀበት ሹፌሮች አንስተዉ አርባምንጭ ሆስፒታል ካደረሱት በኋላ ለቤተሰቡ መደወሉን ሰምተን የጋርዱላ ዞን ፖሊስን ደጋግመን ጠይቀናል ብለዋል።
" የዞኑ ፖሊስ ተጎድቶ አርባምንጭ ከገባዉ ልጅ ውጪ የተጎዳም ሆነ የሞተ ሰዉ አለመኖሩን ሲገልፁ ቆይተዉ በማግስቱ አስክሬኑ ጋርዱላ ሆስፒታል መሆኑን በመግለፅ ወደ ጉማይዴ ወሰን አከባቢ በሚትገኝ ሀይቤና ቀበሌ በፖሊስ አጅበዉ በማምጣት ከማስረከብ በስተቀር 'ስለ ገዳዮቹም ሆነ አሟሟቱ የዞኑ ፖሊስ በግልፅ የነገረን ነገር የለም' " ብለዋል።
ከጥቃቱ የተረፈዉ ካሳሁን ምን አለ?
" በዕለቱ አርባምንጭ ሞተር አሰርተን በሰላም ወደ ቤታችን እየተመለስን ነበር።
ጋርዱላ ዞን ደራሼ ወረዳ ገበልበኖ ኦልቴ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ስንደርስ አንድ አነስተኛ ሚኒባስ ቆሞ ተሳፋሪዎች ሲወርዱ እኛንም ሞተር እንድናስቆም ጠየቁን።
የደንብ ልብስ የለበሰ ፖሊስ በቦታዉ ስለነበር ምንም ጥርጣሬ ዉስጥ ሳንገባ በቆምንበት ነበር የያዝነዉን።
ገንዘብና የእጅ ስልካችንን በግድ ከወሰዱብን በኋላ 'ሄደዉ ለጉማይዴዎች ያቃጥራሉ፤ማንነታችንን ስላዩ እንግደላቸዉ' መባባል ሲጀምሩ እኔም በፊናዬ ጓደኛዬም በፊናው በእግር መሸሽ ጀመርን ለመጨረሻ ጊዜ ማስታዉሰዉ አብነትን ከጥቃት ፈፃሚዎቹ አንዱ በያዘዉ ስለት ማጅራቴን ሲወጋኝ ነዉ።
በደመነፍስ ስሮጥ ከወደቅኩበት ስነሳ በቆሎ ማሳ ዉስጥ ነበርኩ፤ እንደምንም አቅሜን አሟጥጬ ወደ መንገድ ወጣሁና አንድ መኪና አስቁሜ ወደቅኩኝ እግዚአብሔር ይስጣቸው አንስተዉ አርባምንጭ ሆስፒታል ወሰዱኝ፤ትንሽ ስሻለኝ ለቤተሰብ ደዉዬ የደረሰብኝን ነገርኳቸው።
የጓደኛዬን ሞት የሰማሁት በማግስቱ ቤተሰብ መጥቶ በጀልባ ወደ ቤት ከወሰዱኝ በኋላ ነዉ " ብሏል።
ኮሬ ዞን በጉዳዩ ዙሪያ ምን ይላል ?
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጉዳዩን አስመልክቶ ያነጋገራቸው የኮሬ ዞን ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኮማንደር ሲዳሞ ማዳሞ በጋርዱላ ዞን ደራሼ ዙሪያ ወረዳ ሁለት የኮሬ ዞን ሳርማሌ ወረዳ ቡንቲ ቀበሌ ወጣቶች ላይ ጥቃት ተፈፅሞ ወጣት አብነት መገደሉንና ሌላኛው ጓደኛዉ መትረፉን ገልፀዋል።
የጋርዱላ ዞን ፖሊስ ጥቃት አድራሾችን አጣርቶ ለፍርድ እንዲያቀርብ የጋራ መድረክ ፈጥረዉ መነጋገራቸውን ገልፀዋል።
የጋርዱላ ዞን በጉዳዩ ዙሪያ ምን አለ ?
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስለጉዳዩ መረጃ ለማግኘት ወደ ጋርዱላ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ታዬ ታምሩ የእጅ ስልክ ደዉሎ ቢያነጋግራቸዉም አጠቃላይ የፀጥታ ጉዳዮችን አስመልክቶ መረጃ መስጠት የሚችሉት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ብቻ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የዞኑን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ግንኙነት ኪታሞን ቢያነጋግሯቸውም ለጊዜው በጉዳዩ ዙሪያ ምላሽ መስጠት እንደማይችሉ ገልፀዋል።
ቀናትን ጠብቆ ድጋሚ ብንደዉልላቸዉም ስልክ ባለማንሳታቸው ምላሻቸው በዚህ ዘገባ አልተካተተም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia
ድንበር የለሹ የሃኪሞች ቡድን(MSF) ስለ ጋምቤላ ግጭት ምን አለ ?
" በታህሳስ 15፣ 2018 ብቻ ከ100 በላይ በመሳሪያ የቆሰሉ ሰዎችን ተቀብያለሁ "- ድንበር የለሹ የሃኪሞች ቡድን
ድንበር የለሹ የሃኪሞች ቡድን በጋምቤላ ክልል ተባብሶ የቀጠለው ግጭት የበርካቶችን ህይወት እየቀማና ጉዳት እያደረሰ መሆኑን አሰታውቋል።
ቡድኑ በክልሉ ተባብሶ የቀጠለው ግጭት እንዳሳሰበው ገልፆ በትናንትናው እለት ታህሳስ 15፣ 2018 ብቻ ከ100 በላይ በመሳሪያ የቆሰሉ ሰዎችን መቀበሉን አስታውቋል።
ታህሳስ 8፣ 2018 የሃኪሞች ቡድኑ ኩሌ ስደተኞች ካምፕ ወደሚገኘው ፋሲሊቲው የተጎዱ ሰዎች እየጨመሩ መምጣታቸውን ተከትሎ ምላሽ ለመስጠት የሚሆን ስራ መጀመሩን ገልፆ በመጀመሪያው 48 ሰዓት ውስጥ 50 የቆሰሉ ሰዎቾ መምጣታቸውንና 19 ያህሉ አሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ እንደሆኑ ገልጿል።
ድንበር የለሹ የሃኪሞች ቡድን ባለፉት 7 ቀናት 150 የቆሰሉ ሰዎችን መቀበሉን ገልፆ የጤና ሚኒስትርን ድጋፍ ለመደገፍ የሚያገለግሉ የጅምላ ጉዳት ምላሽ ለመስጠት የሚውሉ መሳሪያዎችን ለጋምቤላ አጠቃላይ እና ለጋምቤላ የመጀመሪያ ሆስፒታሎች ማከፋፈሉን ገልጿል።
ቡድኑ የተፈጠረው ግጭት መደበኛ የሆነውን የጤና አገልግሎት ረብሿል ያለ ሲሆን ያለ አድሎ ድጋፍ ለሚሹ ሁሉ አገልግሎት መስጠቱን እንደሚቀጥልና የጤና ባለሙያዎች፣ ታካሚዎች እና የጤና ተቋማት እንዲከበሩ ጠይቋል።
#TilvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
❤ 273😢 77😭 20🙏 8🕊 7😡 2🤔 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
#MPESAEthiopia
100% ነፃ ነው!
የM-PESAን መተግበሪያ በመጠቀም ወደ ሌላ የM-PESA አካውንት ገንዘብ ለመላክ የአገልግሎት ክፍያ የለውም።
መተግበሪያውን ለማውረድ ይህንን ይጫኑ
https://onelink.to/ewsb22
ለተጨማሪ መረጃ በቴሌግራም ያግኙን፥
https://t.me/MPesaETCustomerCare
#MPESAEthiopia
❤ 142😡 19😭 7👏 6🥰 4🙏 1🕊 1
#Tigray
በቅርቡ ወደ አዲስ አበባ አቅንተው የነበሩት የትግራይ ጊዚያዊ አሰተዳደር ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀ) ከፌደራል መንግስት በ7 ጉዳዮች አመርቂ ውይይትና መግባባት መድረሳቸው ተገለፀ።
ወደ ግጭት የሚያመሩ ፓለቲካዊ ሁኔታዎች ወደ ሰላማዊ የጠረጴዛ ውይይት ማምጣት ስምምነት ከተደረሰባቸው ጉዳዮች አንዱ ነው።
የጊዚያዊ አስተዳደሩ የፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት ታህሳስ 15/2018 ዓ.ም ውይይት ተደርጎባቸዋል ስምምነት ተደርሶባቸዋል ብሎ መግለጫ ያወጣባቸው ነጥቦች ምንና ምን ናቸው ?
1. የደመወዝና የበጀት ጉዳይ
በክልሉና በፌደራል መንግስት መካከል ከአቅም በላይ በሆነ የሰራተኛ ቅጥር ምክንያት ሳይለቀቀ የቆየው የመንግስት ሰራተኞች የደመወዝ ጭማሪ በጀት እንዲለቀቅ በመደበኛ ዓመታዊ በጀት ላይ የነበረው መሳሳብ እንዲፈታና ወደ ስራ እንዲገባ መግባባት ተደርሷል።
2. የሰገን ወንዝ የውሃ ፕሮጀክት ግንባታ የሚመለከት
ለመቐለ ከተማና አከባቢዋ በቂ የንፁህ የመጠጥ ውሃ በማቅረብ የነዋሪዎች ችግር ይፈታል ተብሎ የሚጠበቀው ፕሮጀክት በመሆኑ አስፈላጊ የግንባታ እቃዎች ተማልተውለት እንዲቀጥል ተወስኗል።
3. ያልተቋራረጠ የነዳጅ አቅርቦት
ለክልሉ ወርሃዊ የነዳጅ ፍጆታ የሚበቃ ነዳጅ ሳይቆራረጥ እንዲገባ ውይይት ተደርጎበታል መፍትሄ ተቀምጦለታል።
4. ተፈናቃዮች ስለ መመለስና ግዛታዊ አንድነት የማረጋገጥ ጉዳይ
ተፈናቃዮች የመመለስና ግዛታዊ አንድነት የማረጋገጥ ጉዳይ ቀጣይነት ባለው ውይይትና የፊት ለፊት ግንኙነት መፍትሄ እየተበጀለት እንዲሄድ መግባባት ተደርሶበታል።
5. በሰላማዊ ውይይት የፓለቲካ ችግሮች የመፍታት ጉዳይ
የግጭት መንገዶች ተዘግተው ለጠረጴዛ ውይይት ቅድሚያ እንዲሰጠው መግባባት ተደርሶበታል " ራሳችን የፈጠርነው ችግር ራሳችን መፍታት ይገባል " ተብሏል።
6. የአገራዊ የምክክር ሂደትና አፈፃፀሙ የሚመለከት
ከአገራዊ የምክክር ኮሚሽን ከፍተኛ አመራሮች ውይይት ተካሂደዋል። የትግራዩ የምክክር ሂደት በሌሎች ክልሎች ከሚካሄደው ውይይት በተለየ በጦርነቱ የደረሰ ጉዳት ታሳቢ ባደረገ መልኩ እንዲቀጥል ውይይት ተደርጎበታል መግባባት ተደርሶበታል።
7. አገራዊና ክልላዊ ምርጫ በሚመለከት
በቀጣዩ ወርሃ ግንቦት 2018 ዓ.ም የሚካሄደው ሰባተኛው አገራዊና ክልላዊ ምርጫ በትግራይ ለማካሄድ አስቻይ ሁኔታዎች መኖራቸውና አለመኖራቸው አስመልክቶ ጊዚያዊ አስተዳደሩ በያዝነው ሳምንት ይፋዊ መግለጫ እንዲሰጥ መግባባት ላይ ተደርሷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
@tikvahethiopia
❤ 1 310🕊 208😡 91👏 48😭 24🤔 18💔 16😱 12😢 11🙏 9🥰 4
" የፍቼ ሰላሌን ህዝብ ይቅርታ ጠይቃለሁ " - ነብይ ሄኖክ ግርማ
የፍቼ ከተማ ፖሊስ " ሰላሌን የጠንቋይ እና ሟርተኛ ሀገር " ብለው ሰድበዋል ያላቸውን የJPS INTERNATIONAL CHURCH መስራችን ነብይ ሄኖክ ግርማን በቁጥጥር ስር ለማዋል የፍርድ ቤት የእስር ማዘዣ ቢያወጣም እሳቸው #አሜሪካን ሀገር ሆነው ህዝቡን ይቅርታ ጠይቀዋል።
አሜሪካን ሀገር ለአገልግሎት እንደሄዱ የገለጹት ነብይ ሄኖክ ግርማ " በሶሻል ሚዲያ ተቆርጦ የተሰራጨው ንግግር የፍቼ ሰላሌን ህዝብ እንደምጠላ አይነት ትርጉም ይዞ ነው ለዚህ ንግግሬ ይቅርታ ጠይቃለሁ " ብለዋል።
" ለአካባቢው ህዝብ ለመላው ኢትዮጵያውያን ሁሉ ፍቅር እና አክብሮት ኖሮኝ ነው የማገለግለው ፤ በማገለግልበት ቤተክርስቲያን የተለየ የአንድ ጎሳ ግሩፕ የለም፤ ቤተክርስቲያናችን የተለያየ ብሄር የተለያየ ጎሳ እግዚአብሔር አምኖ የሚያመልክበት ቦታ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
" በንግግሬ ያሳዘንኳችሁ ፣ ያስከፋዋችሁ የዛ አካባቢ ተወላጆች በጣም ይቅርታ እጠይቃለሁ ፤ ይቅርታዬን እንድትቀበሉም በጌታ ፍቅር እጠይቃችኋለሁ " ሲሉ አክለዋል።
" የዛ አካባቢ አመራሮች፣ የመንግሥት ቢሮ አመራሮች ይቅርታዬን ተቀበሉኝ። በአካል እዛው ከተማ መጥቼ ይቅርታ የምጠይቅበት ህዝቡንም የማገለግልበት እድልን እግዚአብሔር ያመቻችልኛል " ብለዋል።
በአጭር ቀን ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱም ገልጸዋል።
የፍቼ ከተማ ፖሊስ ነብይ ሄኖክ ግርማን ህዝብ በመሳደብ ፣ ብጥብጥ በመፍጠር በማሰብ ወንጀል ከሷቸዋል።
የእስር ማዘዣም አውጥቶባቸው የነበረ ቢሆንም እሳቸው በሰዓቱ ወደ አሜሪካ ሀገር ጉዞ ላይ ነበሩ።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
@tikvahethiopia
❤ 728😡 714🤔 61🕊 25🙏 23👏 21😭 20🥰 10😱 4
ዋሪት ፈርኒቸር !
ክቡራን ደንበኞቻችን! መጪው በዓል የሰላም፤የፍቅር እና የስኬት እንዲሆንላችሁ ከወዲሁ ከልብ እየተመኘን፡ ምቾታቸውን እና ጥራታቸውን የጠበቁ ምርቶቻችንን በሁሉም የማሳያ ቅርንጫፎቻችን ከበዓ ቅናሽ ጋር እስከ ጥር 15 ቀን 2018 ዓ.ም. አዘጋጅተን እንጠብቅዎታልን!!
Visit us today @
📍 22 - ዋሪት ህንፃ
📍 ጉርድ ሾላ - ሴንቸሪ ሞል
📍 ለቡ - ቫርኔሮ ፊት ለፊት
📍 አዳማ - ሶረቲ ሞል
📍 ቡልቡላ- ልዑል ህንፃ ፊት ለፊት
📍 ወሎ ሰፈር- Ethiolife life real estate
📍 ጦር ሀይሎች- ኩዊንስ ፊት ለፊት
ዋሪት ፈርኒቸር
ትክክለኛ ምርጫ!
ለተጨማሪ መረጃ: ☎️ 0911210706/07
https://t.me/warytfurniture
tiktok:/warytzefurniture
❤ 167🙏 3🕊 3
