fa
Feedback
ግጥም ብቻ 📘

ግጥም ብቻ 📘

رفتن به کانال در Telegram

✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን። ✔ @getem @serenity13@wegoch @Words19@seiloch @shiyach_bicha@zefenbicha @leul_mekonnen1

نمایش بیشتر
2025 سال در اعدادsnowflakes fon
card fon
65 755
مشترکین
-924 ساعت
-597 روز
-32030 روز
آرشیو پست ها
ድህነት አስናቀኝ መኖሬ መኖሪያው ጠፍቶበት እያንገዳገደኝ እያርበደበደኝ ልክ እንደጥርስ ህመም እየጠዘጠዘኝ ያኖረኝ ህመም እያመሳጠረኝ ለከንቱ ትዝታ እጅ ስጥ እያለ ለዝሙት አኖረኝ ውድቀቴን አፅፎ ህልሜን እያሳጣኝ ህልሜን አስነብቦ ልቤን እያስደማኝ ድህነት ያልኩትን የጥርሱ ህመሜን ዘላለም አስረሳኝ። By አለምሰገድ ወልዴ @getem @getem @getem
نمایش همه...
👍 28🔥 5
ብዬማ አልዋሽሽም እኔ'ኮ ያላንቺ ምንም ነኝ ብዬ ብዙ አልዘበዝብም ስሚኝ አንቺ ሆዬ ትተሽኝ ከሄድሽ ልቤ ድንኳን ጥሎ ደረቱን ይደቃል ከሰው ተነጥሎም ሀዘን ይቀመጣል ከመኖር ተጣልቶም ሞትን ይናፍቃል ። ብዬማ አልዋሽሽም ከተውሽኝ አልኖርም ያላንቺ ምስቀዉ ሳቄም ሳቅ አይሆንም ስልማ አልዋሽሽም ምን በወጣሽ ፍቅሬ ባምላክ ትዕዛዝ እንጂ ባንቺ አይደል መኖሬ ። #ኢዮብ_(ዮሚን) @getem @getem @getem
نمایش همه...
43👍 29🔥 1
ላይድን ቁስል፤ ጨዉ መነስነስ፤ ከድንጋይ ላይ፤ ዉሃ ማፍሰስ ፤ ለሟች ዘመድ ፤ ዳግም ማልቀስ፤ መኖር ካሉት፤ እንደዚህ ነው፤ ሳቅን ትቶ፤ መንሰቅሰቅ ነው። By ዔደን ታደሰ @topazionnn @getem @getem
نمایش همه...
66👍 28🔥 11
የመኖሬን ቅንጣት በጥርሶችሽ ንጣት ቀናውን እድሌን በአይኖችሽ ብሌን የነገዬን ድምቀት በውበትሽ ስምረት አየሁኝ ተስሎ ነገ አንቺን መስሎ።                   By @poetkidus @getem @getem @getem
نمایش همه...
48👍 29🔥 4😱 2🎉 1
📢 NOTICE: Register Now for Xpert Training Institute’s Master Trading Program! Are you ready to Master Trading with Experts? Xpert Training Institute, in collaboration with Jmad Capital Consultancy, presents a VIP & Mentorship Trading Program designed to equip you with essential and advanced Forex trading skills. 🔹 Programs Offered: ✅ VIP Class – Comprehensive training covering essential trading concepts. ✅ Mentorship Class (Online) – Advanced flexible learning with expert guidance from anywhere. ✅ Mentorship Class (Offline) – In-depth coaching with hands-on learning experience. 📅 Program Details: 📌 Duration: 6 Weeks 📌 Class Type: Online & Offline (Flexible Schedule) 📌 Batch Limit: Only 20 Students Per Batch 📍 Registration & Contact Information: 📞 Call Us: 📲 +251953888882 📲 +251116504000 📧 Email Us: Infinitygroupet@gmail.com 🌐 Register Now: Click Here to Register 🚀 Secure your spot today and start your journey to financial success! Join our Telegram channel https://t.me/xpert_et
نمایش همه...
👍 8🔥 2🤩 1
ቅጽርህ የእናት እቅፍ ሸክምን የሚያራግፍ አልተነፍስ ጸሎት አይወጣ ቃል ከአፌ ይተናል ጭንቀቴ ስመለስ አርፌ እመጣለሁ ደጅህ ሀሳብ አንጠልጥዬ እገባለሁ ቅጽርህ አንገቴን ደፍቼ መች ታዝንብኛለህ መች ትወቅሰኛለህ በሽቅጬ ከርፍቼ አይነድህ ድፍረቴ አይቆጨኝ ስንፈቴ አይበሽቅህ ስህተቴ አይገደኝ ዝለቴ በኦና ተግባሬ ውድቀት አንከርፍፌ ስቆም ከነእድፌ ምን አድርጌልህ ነው? አክመህ ምትልከኝ በምህረት መርፌ ከመቀመጥ በቀር ኢምንት ታህል ድርጊት ፈጽሜ የማላውቅ አንዲት ዘለላ እንባ በጉንጬ ሳልሰድ እንዴት ደመቅኩ በሳቅ? እንዴት ቻልኩ መፍገግ? እንዴት ቻልኩ ማማር? እሬት ህይወት ይዤ አጣፍጥልኝ ሳልል ሳልጠይቅ የሀሴት ማር ትዕቢት አይሉት ጥጋብ ፍርሃት አይሉት ስጋት ስም ያላገኘሁለት አንዳች አሳሪ ኃይል ወርሮኝ እንደ ውጋት አላልኩኝ እግዚኦታ አልቆምኩኝ ሰዓታት ፈውስ አሰኝቶኝ አላደረስኩ ኪዳን ስለረገጥኩ ብቻ ስላረፍኩ በቤትህ ይገባኝ ነበር መዳን? እንጃ! ብቻ እመጣለሁ ሀሳብ አንጠልጥዬ ደጅህ እገኛለሁ ማረኝ ቃልን ጥዬ አርፋለሁ ካንዱ ጥግ አንገቴን ደፍቼ መች ትቆጣኛለህ ሰማዕቱ ጊዮርጊስ ከነእድፌ ተኝቼ ቆይቼ ቆይቼ . . . ቆይቼ ስነሳ ተጋድሞ አየዋለሁ ሸክሜ እንደ ሬሳ አልጸለየም ሳትል አልለመነም ሳትል አላነባም ሳትል ይገርመኛል እኮ ጊዮርጊስ አባቴ ጭንቀቴን ስትጥል ይገርመኛል ቅጽርህ... ልክ እንደ እናት እቅፍ ደስታን 'ሚያሳቅፍ! አባብሎ 'ሚያሳርፍ! ሸክምን 'ሚያራግፍ! . . . እርፍ! #ኤልዳን @marda129 @getem @getem @getem
نمایش همه...
32👍 27🔥 6
የማይነቃ ውሸት (ሳሙኤል አለሙ) እንደ ተወዛዋዥ ግንባር በየምሶሶው የለጠፍሽው "አለ" የምትለው አድባር፤ ሰርክ... መዳኑን ብቻ አስለምደሽው፤ ሰርክ... መኖሩን ብቻ አሳይተሽው፤ ሰርክ... ሲስቅ...ሲጫወት ይረሳዋል! እንደሚሞት ካልነገርሽው። @Samuelalemuu @getem @getem @getem
نمایش همه...
👍 11 8🤩 3
#ጥርጣሬ እጄ በካቴና፣ ታስሮ ተሸብቦ በድን ሰውነቴ፣ በፖሊስ ታጅቦ እስር ቤት ስነዳ ያዩኝ ሰዎች ሁሉ፣ “ያው ሌባ! ሌባ!” አሉ። የኔን ንፅህና፣ እኔው እያወኩት 'ብዙኃን ይመውኡ!' ምስክር እራሴን እኔ ውስጥ አጣሁት። «እንዴት ይህ ሁሉ ሰው ይዋሻል ባንድ ቃል? ብሰርቅ ነው 'ጂ እንግዲህ ማን ያውቃል?» By Nureddin Issa @getem @getem @paappii
نمایش همه...
👍 41 18🔥 6🎉 2
( ነዳይ ... ) ============ ውዴ .... እግዜርን ፍለጋ በዱር በተራራ ምድሩን አታስሽው በምናኔ ጉዞ ዋሻ ለመገስገስ እግርሽን አታንሽው መውረድ ከጀመረ የማይቆም እምባሽን ይቅር አታፍስሽው ጽድቅ ያማረሽ እንደው ነዳይ ልቤ ፊትሽ ደጅሽ ወድቋል አንሽው !!! By @kiyorna @getem @getem @getem
نمایش همه...
👍 33 20🔥 1
እናፍቅሽ ይሆን ~ ~ ~ ~ ~ ~ ስቀሽ ስትለይኝ ስትሄጅ ካጠገቤ ስትሰናበቺ ከሚወጅሽ ልቤ ያመጣሽ ጎዳና ሲመልስሽ ወስዶ መፋቀርን ክዶ ነግርኝ ሲሄድ መርዶ እናፍቅሽ ይሆን ? ታውቂው የለም እንዴ 🤔 ሀዘኔን ልረሳው መፍራቴን ልደብቅ አጥብቄ መያዜን የቀሚስሽን ጨርቅ ገና ሳትቀልጂ በመምጣትሽ ብቻ እንደምፍለቀለቅ ። ትውስ ይልሽ ይሆን ? እናፍቅሽ ይሆን ? እንደምሳሳልሽ ትሳሽልኝ ይሆን ? እኔማ ..... እወድሽማለሁ አፈቅርሽማለሁ አስብሽማለሁ ናፍቅሽማለሁ አንቺስ አንቺ ሆዬ እናፍቅሽ ይሆን ? እናፍቅሻለሁ ? By ኢዮብ_አሠፋ(@yomin1_2) @getem @getem @getem
نمایش همه...
44👍 36🔥 8👎 1
     ( ሚስትህ የኔ እኮ ናት ) አገሬው ቢተቸኝ በገዛ ድግሴ ሳለሁ ተባርሬ ፤ ስቀህ ብታየኝም አንተ ተደስተህ ሳልፍ ተማርሬ ፤ አዎን ያንተው መውደድ የራስህ ያረካት ፤ ሳታገባት በፊት ለኔ ሚስቴ እኮ ናት ፤       የምሬን ስነግርህ...... አብልጬ ምወዳት ከራሴ ከሁሉ ፤ ሚስትህ ሚስቴ ደሆነች ባያውቅልኝ ሁሉ ፤ የሰው ሚስት ተመኘ ይለኛል ሰው ሁሉ ። ግዴለም ይበሉኝ እነሱ ያሻቸውን ፤ ቆርጠው ይቀጥሉ ያለ የሌለውን ፤ አንተ ግን አደራ እንዳትዘብተኝ ፤ ደርሰህ በነሱ ፊት እንዳትቦጭቀኝ ፤ ወዳጅን መቀማት ፤ በለሆሳስ ማጥቃት ፤ ሳይቆፍሩ መቅበር ፤ ያውም ባንድ ጀንበር ፤ ሙሾም ሳይወረድ ፤ ምነው ሳይረገድ ። ሰሚ ባይሰማልኝ ባላቆም ጠበቃ፤ ይኸን ሁሉ ነገር አርገህ ስታበቃ ፤ ሚስቴን ቀማኝ ብለህ ብትሄድ አቤቱታ ፤ ለወናፍ አፍ ሁሉ ብታቀርብ ስሞታ ፤ የምሬን ነው ምልህ ዳኛውም አይፈርድም ፤ እኔ አልከሰስም እኔ አልወቀስም ፤ ከቻልክ የሚስቴ ባል ምላስህን ሰብስብ ። #ኢዮብ_አሰፋ @yomin1_2 @getem @getem @getem
نمایش همه...
😁 40👍 33 17😢 10👎 1🤩 1
አንቺና ጨረቃ ========= መብረቅ ብልጭ ብሎ ምስልሽን ሲፈጥር፤ ፀሀይ ስትስቅ ነው አንቺን የምትመስል፣ ኩልል ያለ ውሃ ሲያይሽ ይጠራል፣ ከዋክብትን አይተሽ ስንቴ አሽኮርምመሻል። ጨረቃ ደግሞ አይታ፣ ካንቺ ካልተዋስኩኝ ብርሃንሽን ብላ፣ እንደዘብ ጠባቂ አንቺን ተከትላ፣ ከአጼ ቤት ጎጆ ገባች ሰተት ብላ። አውቀሽ ነው ቢባልም አሁን አምኛለሁ፣ አንቺን ለመፈለግ፤ አይደለም ጨረቃ እኔም ደክሜያለሁ። ሰአሊ እንዳይስልሽ ቀለምሽ አይገባም፣ ገጣሚ እንዳይገጥምሽ ያለው ቃል አይበቃም። ሆኖብኝ ነው እንጂ እንደ አጼ ቤት ልጆች፣ መች እዋስ ነበረ ዋንጫና ቁልፊቶች። አውቃለሁኝ አዎ በዚ ውስጥ አትቆዪም፣ በፍቅርሽ ተይዤ፤ በልቤ ብልቃጥ ውስጥ አንቺን ባስቀምጥም፣ ሰበርሽው እሱንም፣ አንቺና ጨረቃ ጭራሽ አትያዙም፣ ድንገት ብትያዙ፤ የያዛችሁን ነገር ከመስበር አትቀሩም፣ አንቺና ጨረቃ መስበርን አተዉም፣ አንቺም ጨረቃም ወደኋላ አትሉም። @abela_black @getem @getem @getem
نمایش همه...
👍 44🔥 6 2
ኩሬ ብሆንም ፥ ባህር ይሉኛል ለዐይን ባልሞላም ፥ ውብ አርገውኛል ከንቱ ሆኜ ሳል ፥ "አንቱ" ነው 'ምባል ዝምታዬ እንኳ ፥ ለጉድ ተነቧል ኧረ ይሄ ነገር ፥ ግራ ያጋባል ... እንዴት ሁሉም ሰው ፥ በሌለኝ አቅም ይተማመናል ? እንግዲህ እንጃ ፥ ባንቺ ልብ አልፈው ፥ ቢያዩኝ ይሆናል። By Habtamu Hadera @getem @getem @paappii
نمایش همه...
40👍 10🔥 1
አለም እንደ ልቧ ያሻትን አክብራ ያሻትን ማሽቀንጠር፤ ህይወት ቅራቅንቦ ዝም ብሎ ኖሮ ዝም ብሎ መቀበር። 01|07|2017 By ኢዮብ(ዮ_ሚን) @getem @getem @getem
نمایش همه...
👍 55 19🔥 7🎉 1
ፍቅር ነው አውቃለሁ ።።።።።።።።።።።።።። መራር ፅዋ በመንገዴ፣ አንቺ ነሽ ወይ የኔ ገዴ። እንደእንቅፋት እየመታሽ፣ ህይወቴ ውስጥ ገብተሽ ወጣሽ። ዝብርቅርቋ አንቺ አለሜ አለሽ ስልሽ የሌለሽው፣ ቢታየኝም ባይታየኝ ፍቅርሽ እኮ አለ እላለው። መች መሰለሽ፣ እንደ እሳት፣ ሲያደምቀኝ ወይ ሲያሞቀኝ ፣ ሌላ ጊዜ ስታስከፊኝ፣ ንዴት ሆኖ በግለት መልክ ሲያተኩሰኝ። ፍቅሬ ሙሉ ከልብሽ ውስጥ የጎደለለው፣ እንዳልተውሽ፣ ተዋት የሚል ዝግ ሀሳቤን አይምሮዬ እየተወው፣ እራኩሽ ስል፣ ሸፋፋ እግሬ እየዞረ ካንቺ ስር ነው፣ ልቤን ካንቺ ፍቅርሽ ካልኩት እንዳስጥለው፣ ሳሰላስል ካንድ ሀሳብ ጋር ተገናኘሁ፣ ሀሳቡ፣ አምላክ ወዶን ፍቅርን በሞት ከገለፀው፣ ለምን ታዲያ፣ በሞት ማግስት በፍርድ ወንበር ወደሲኦል የምንወርደ፣ ገባኝ፣ ለካ ፍቅር ትርጓሜው መያዝም ነው መልቀቅም ነው። ፍቅር ይዤ ባትመረጪኝም ምርጫሽ ይሁን ፈቅጃለሁ፣ ፍቅር ነው አውቃለው ለወደድሽው ትቼሻለሁ፣ ፍቅር ነው አውቃለሁ እረስቼሻለሁ ይቅር ብዬሻለሁ፣ ፍቅር ነው አውቃለሁ። @abela_black @getem @getem @getem
نمایش همه...
👍 51 15🔥 1🤩 1
نمایش همه...
Zare ende adis.m4a1.69 MB
19👍 8🔥 1
Zare ende adis.m4a1.69 MB
ለየ - ቅል (በላይ በቀለ ወያ) . . የየግል ብሶት ፣ የየግል ችግር የየግል ሩጫ ፣ የየግል ውድድር የየግል ሀይማኖት ፣ የየግል ብሔር የየግል አላህ ፣ የየግል እግዜር የየግል ሀገር ፣ የየግል ስልጣን የየግል መልአክ ፣ የየግል ሰይጣን ይዘን እየወጣን... በየ ግል ቆስለን ፣ የጋራ ፈውስ አጣን!!! @getem @getem @paappii
نمایش همه...
👍 105 31😢 10🔥 8
አንዲት ውብ አበባ የተኮተኮተች: መዐዛዋ ጥዑም ናርዶስ የሸተተች አላፊ አግዳሚ መቀንጠስ ሚመኛት ዛሬ ጠወለገች ምነው ምን አገኛት? ጠፋ ያማረለት ጥቂት ዘመን በርካች ከጥውልግ ጥግ አምላጭ መልኩን አሰማምሮ ካባውን ደርቦ እርቃን ነብሱን ገላጭ ባይሆን መጨረሻው የሰው ልጅ ዳር ድንበር የተኮተኮተች ያቺ ፅጌሬዳ ዛሬም ትኖር ነበር:: ብኩን ያልተረዳ አንብቦ ያልገባው ማወቅ መረዳቱ እምነቱ ያልረባው ሰላላ ሰው ሲያይ ደረቱን ይደቃል የዛፍ ፍሬው መድረቅ መች አሳስቦት ያውቃል አለም ትንሽ አለም ገፊ አለም ታካች ምርቁዝ ቁስል ፈዋሽ ደሞ ራሷ ፈንካች የተፈነከተ ልቡ ያባበጠ ሰንካላ ቁስለኛ ፍሬዋን ቀጣፊ ደሞ ደሞ አድፋፊ መሆኑ ቀማኛ ታድያ ምን ይገርማል ውሉ አይደለ የአለም የማለዳ ደስታ የማለዳ ውበት ጀምበር ስትጠልቅ የለም በሳቅ በውዳሴ እሰይ እሰይ ብሎ ቀይ ምንጣፍ አንጥፎ ውብ ቃላት ደልድሎ ለሀገር ያሽቃብጣል ላይ ታች ይሯሯጣል ፍሬውን ገና ሲያይ ከነ ስሩ ይቆርጣል እናማ.....ትናንትና ያበበ ዛሬ ከደረቀ ከለጋው ቅርንጫፍ ፍሬው ከለቀቀ የለመለመው መስክ ድንገት ከከሰመ ተቃናልኝ ያሉት ደግሞ ከጠመመ ታድያ ምን ይገርማል ውሉ አይደል የአለም የማለዳ ተስፋ የማለዳ ትጋት አመሻሽ ላይ የለም:: By kidist @getem @getem @getem
نمایش همه...
👍 37 15🔥 2
#አወቅቴ (Déjà_vu) . . ለመጥለቅ ጨረሩን፥ ሲሰበስብና፥ ማልዶ ሲዘረጋ ወጋገን ያምታታል ብርሃን ያምታታል...አድማስ ከተጠጋ የገባው ይንገረኝ... እየመሸብን ነው? ወይስ እየነጋ? By Rediet Aseffa @getem @getem @paappii
نمایش همه...
34👍 18🔥 5