ግጥም ብቻ 📘
Відкрити в Telegram
✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን። ✔ @getem @serenity13 ✔ @wegoch @Words19 ✔ @seiloch @shiyach_bicha ✔ @zefenbicha @leul_mekonnen1
Показати більше2025 рік у цифрах

65 749
Підписники
-924 години
-597 днів
-32030 день
Архів дописів
ላይድን ቁስል፤
ጨዉ መነስነስ፤
ከድንጋይ ላይ፤
ዉሃ ማፍሰስ ፤
ለሟች ዘመድ ፤
ዳግም ማልቀስ፤
መኖር ካሉት፤
እንደዚህ ነው፤
ሳቅን ትቶ፤
መንሰቅሰቅ ነው።
By ዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
❤ 66👍 28🔥 11
የመኖሬን ቅንጣት
በጥርሶችሽ ንጣት
ቀናውን እድሌን
በአይኖችሽ ብሌን
የነገዬን ድምቀት
በውበትሽ ስምረት
አየሁኝ ተስሎ
ነገ አንቺን መስሎ።
By @poetkidus
@getem
@getem
@getem
❤ 48👍 29🔥 4😱 2🎉 1
📢 NOTICE: Register Now for Xpert Training Institute’s Master Trading Program!
Are you ready to Master Trading with Experts? Xpert Training Institute, in collaboration with Jmad Capital Consultancy, presents a VIP & Mentorship Trading Program designed to equip you with essential and advanced Forex trading skills.
🔹 Programs Offered:
✅ VIP Class – Comprehensive training covering essential trading concepts.
✅ Mentorship Class (Online) – Advanced flexible learning with expert guidance from anywhere.
✅ Mentorship Class (Offline) – In-depth coaching with hands-on learning experience.
📅 Program Details:
📌 Duration: 6 Weeks
📌 Class Type: Online & Offline (Flexible Schedule)
📌 Batch Limit: Only 20 Students Per Batch
📍 Registration & Contact Information:
📞 Call Us:
📲 +251953888882
📲 +251116504000
📧 Email Us: Infinitygroupet@gmail.com
🌐 Register Now: Click Here to Register
🚀 Secure your spot today and start your journey to financial success!
Join our Telegram channel
https://t.me/xpert_et
👍 8🔥 2🤩 1
ቅጽርህ የእናት እቅፍ
ሸክምን የሚያራግፍ
አልተነፍስ ጸሎት አይወጣ ቃል ከአፌ
ይተናል ጭንቀቴ ስመለስ አርፌ
እመጣለሁ ደጅህ ሀሳብ አንጠልጥዬ
እገባለሁ ቅጽርህ አንገቴን ደፍቼ
መች ታዝንብኛለህ
መች ትወቅሰኛለህ በሽቅጬ ከርፍቼ
አይነድህ ድፍረቴ
አይቆጨኝ ስንፈቴ
አይበሽቅህ ስህተቴ
አይገደኝ ዝለቴ
በኦና ተግባሬ
ውድቀት አንከርፍፌ ስቆም ከነእድፌ
ምን አድርጌልህ ነው?
አክመህ ምትልከኝ በምህረት መርፌ
ከመቀመጥ በቀር
ኢምንት ታህል ድርጊት ፈጽሜ የማላውቅ
አንዲት ዘለላ እንባ
በጉንጬ ሳልሰድ እንዴት ደመቅኩ በሳቅ?
እንዴት ቻልኩ መፍገግ?
እንዴት ቻልኩ ማማር?
እሬት ህይወት ይዤ
አጣፍጥልኝ ሳልል ሳልጠይቅ የሀሴት ማር
ትዕቢት አይሉት ጥጋብ
ፍርሃት አይሉት ስጋት
ስም ያላገኘሁለት
አንዳች አሳሪ ኃይል ወርሮኝ እንደ ውጋት
አላልኩኝ እግዚኦታ አልቆምኩኝ ሰዓታት
ፈውስ አሰኝቶኝ አላደረስኩ ኪዳን
ስለረገጥኩ ብቻ
ስላረፍኩ በቤትህ ይገባኝ ነበር መዳን?
እንጃ!
ብቻ እመጣለሁ ሀሳብ አንጠልጥዬ
ደጅህ እገኛለሁ ማረኝ ቃልን ጥዬ
አርፋለሁ ካንዱ ጥግ አንገቴን ደፍቼ
መች ትቆጣኛለህ
ሰማዕቱ ጊዮርጊስ ከነእድፌ ተኝቼ
ቆይቼ
ቆይቼ
.
.
.
ቆይቼ ስነሳ
ተጋድሞ አየዋለሁ ሸክሜ እንደ ሬሳ
አልጸለየም ሳትል
አልለመነም ሳትል
አላነባም ሳትል
ይገርመኛል እኮ
ጊዮርጊስ አባቴ ጭንቀቴን ስትጥል
ይገርመኛል ቅጽርህ...
ልክ እንደ እናት እቅፍ
ደስታን 'ሚያሳቅፍ!
አባብሎ 'ሚያሳርፍ!
ሸክምን 'ሚያራግፍ!
.
.
.
እርፍ!
#ኤልዳን
@marda129
@getem
@getem
@getem
❤ 32👍 27🔥 6
የማይነቃ ውሸት
(ሳሙኤል አለሙ)
እንደ ተወዛዋዥ ግንባር
በየምሶሶው የለጠፍሽው
"አለ" የምትለው አድባር፤
ሰርክ...
መዳኑን ብቻ አስለምደሽው፤
ሰርክ...
መኖሩን ብቻ አሳይተሽው፤
ሰርክ...
ሲስቅ...ሲጫወት
ይረሳዋል!
እንደሚሞት ካልነገርሽው።
@Samuelalemuu
@getem
@getem
@getem
👍 11❤ 8🤩 3
እናፍቅሽ ይሆን
~ ~ ~ ~ ~ ~
ስቀሽ ስትለይኝ ስትሄጅ ካጠገቤ
ስትሰናበቺ ከሚወጅሽ ልቤ
ያመጣሽ ጎዳና ሲመልስሽ ወስዶ
መፋቀርን ክዶ ነግርኝ ሲሄድ መርዶ
እናፍቅሽ ይሆን ?
ታውቂው የለም እንዴ 🤔
ሀዘኔን ልረሳው መፍራቴን ልደብቅ
አጥብቄ መያዜን የቀሚስሽን ጨርቅ
ገና ሳትቀልጂ በመምጣትሽ
ብቻ እንደምፍለቀለቅ ።
ትውስ ይልሽ ይሆን ?
እናፍቅሽ ይሆን ?
እንደምሳሳልሽ ትሳሽልኝ ይሆን ?
እኔማ .....
እወድሽማለሁ አፈቅርሽማለሁ
አስብሽማለሁ ናፍቅሽማለሁ
አንቺስ አንቺ ሆዬ እናፍቅሽ ይሆን ?
እናፍቅሻለሁ ?
By ኢዮብ_አሠፋ(@yomin1_2)
@getem
@getem
@getem
❤ 44👍 36🔥 8👎 1
( ሚስትህ የኔ እኮ ናት )
አገሬው ቢተቸኝ በገዛ ድግሴ ሳለሁ ተባርሬ ፤
ስቀህ ብታየኝም አንተ ተደስተህ ሳልፍ ተማርሬ ፤
አዎን ያንተው መውደድ የራስህ ያረካት ፤
ሳታገባት በፊት ለኔ ሚስቴ እኮ ናት ፤
የምሬን ስነግርህ......
አብልጬ ምወዳት ከራሴ ከሁሉ ፤
ሚስትህ ሚስቴ ደሆነች ባያውቅልኝ ሁሉ ፤
የሰው ሚስት ተመኘ ይለኛል ሰው ሁሉ ።
ግዴለም ይበሉኝ እነሱ ያሻቸውን ፤
ቆርጠው ይቀጥሉ ያለ የሌለውን ፤
አንተ ግን አደራ እንዳትዘብተኝ ፤
ደርሰህ በነሱ ፊት እንዳትቦጭቀኝ ፤
ወዳጅን መቀማት ፤
በለሆሳስ ማጥቃት ፤
ሳይቆፍሩ መቅበር ፤
ያውም ባንድ ጀንበር ፤
ሙሾም ሳይወረድ ፤
ምነው ሳይረገድ ።
ሰሚ ባይሰማልኝ ባላቆም ጠበቃ፤
ይኸን ሁሉ ነገር አርገህ ስታበቃ ፤
ሚስቴን ቀማኝ ብለህ ብትሄድ አቤቱታ ፤
ለወናፍ አፍ ሁሉ ብታቀርብ ስሞታ ፤
የምሬን ነው ምልህ ዳኛውም አይፈርድም ፤
እኔ አልከሰስም እኔ አልወቀስም ፤
ከቻልክ የሚስቴ ባል ምላስህን ሰብስብ ።
#ኢዮብ_አሰፋ
@yomin1_2
@getem
@getem
@getem
😁 40👍 33❤ 17😢 10👎 1🤩 1
አንቺና ጨረቃ
=========
መብረቅ ብልጭ ብሎ
ምስልሽን ሲፈጥር፤
ፀሀይ ስትስቅ ነው
አንቺን የምትመስል፣
ኩልል ያለ ውሃ
ሲያይሽ ይጠራል፣
ከዋክብትን አይተሽ
ስንቴ አሽኮርምመሻል።
ጨረቃ ደግሞ አይታ፣
ካንቺ ካልተዋስኩኝ ብርሃንሽን ብላ፣
እንደዘብ ጠባቂ
አንቺን ተከትላ፣
ከአጼ ቤት ጎጆ
ገባች ሰተት ብላ።
አውቀሽ ነው ቢባልም
አሁን አምኛለሁ፣
አንቺን ለመፈለግ፤
አይደለም ጨረቃ እኔም ደክሜያለሁ።
ሰአሊ እንዳይስልሽ
ቀለምሽ አይገባም፣
ገጣሚ እንዳይገጥምሽ
ያለው ቃል አይበቃም።
ሆኖብኝ ነው እንጂ
እንደ አጼ ቤት ልጆች፣
መች እዋስ ነበረ
ዋንጫና ቁልፊቶች።
አውቃለሁኝ አዎ
በዚ ውስጥ አትቆዪም፣
በፍቅርሽ ተይዤ፤
በልቤ ብልቃጥ ውስጥ
አንቺን ባስቀምጥም፣
ሰበርሽው እሱንም፣
አንቺና ጨረቃ
ጭራሽ አትያዙም፣
ድንገት ብትያዙ፤
የያዛችሁን ነገር ከመስበር አትቀሩም፣
አንቺና ጨረቃ
መስበርን አተዉም፣
አንቺም ጨረቃም
ወደኋላ አትሉም።
@abela_black
@getem
@getem
@getem
👍 44🔥 6❤ 2
ፍቅር ነው አውቃለሁ
።።።።።።።።።።።።።።
መራር ፅዋ በመንገዴ፣
አንቺ ነሽ ወይ የኔ ገዴ።
እንደእንቅፋት እየመታሽ፣
ህይወቴ ውስጥ ገብተሽ ወጣሽ።
ዝብርቅርቋ አንቺ አለሜ
አለሽ ስልሽ የሌለሽው፣
ቢታየኝም ባይታየኝ
ፍቅርሽ እኮ አለ እላለው።
መች መሰለሽ፣
እንደ እሳት፣
ሲያደምቀኝ ወይ ሲያሞቀኝ ፣
ሌላ ጊዜ ስታስከፊኝ፣
ንዴት ሆኖ በግለት መልክ ሲያተኩሰኝ።
ፍቅሬ ሙሉ
ከልብሽ ውስጥ የጎደለለው፣
እንዳልተውሽ፣
ተዋት የሚል ዝግ ሀሳቤን
አይምሮዬ እየተወው፣
እራኩሽ ስል፣
ሸፋፋ እግሬ
እየዞረ ካንቺ ስር ነው፣
ልቤን ካንቺ
ፍቅርሽ ካልኩት እንዳስጥለው፣
ሳሰላስል
ካንድ ሀሳብ ጋር ተገናኘሁ፣
ሀሳቡ፣
አምላክ ወዶን
ፍቅርን በሞት ከገለፀው፣
ለምን ታዲያ፣
በሞት ማግስት በፍርድ ወንበር
ወደሲኦል የምንወርደ፣
ገባኝ፣ ለካ ፍቅር ትርጓሜው
መያዝም ነው መልቀቅም ነው።
ፍቅር ይዤ ባትመረጪኝም
ምርጫሽ ይሁን ፈቅጃለሁ፣
ፍቅር ነው አውቃለው
ለወደድሽው ትቼሻለሁ፣
ፍቅር ነው አውቃለሁ
እረስቼሻለሁ ይቅር ብዬሻለሁ፣
ፍቅር ነው አውቃለሁ።
@abela_black
@getem
@getem
@getem
👍 51❤ 15🔥 1🤩 1
አንዲት ውብ አበባ የተኮተኮተች:
መዐዛዋ ጥዑም ናርዶስ የሸተተች
አላፊ አግዳሚ መቀንጠስ ሚመኛት
ዛሬ ጠወለገች ምነው ምን አገኛት?
ጠፋ ያማረለት ጥቂት ዘመን በርካች
ከጥውልግ ጥግ አምላጭ
መልኩን አሰማምሮ ካባውን ደርቦ
እርቃን ነብሱን ገላጭ
ባይሆን መጨረሻው የሰው ልጅ ዳር ድንበር
የተኮተኮተች ያቺ ፅጌሬዳ ዛሬም ትኖር ነበር::
ብኩን ያልተረዳ አንብቦ ያልገባው
ማወቅ መረዳቱ እምነቱ ያልረባው
ሰላላ ሰው ሲያይ ደረቱን ይደቃል
የዛፍ ፍሬው መድረቅ መች አሳስቦት ያውቃል
አለም ትንሽ አለም ገፊ አለም ታካች
ምርቁዝ ቁስል ፈዋሽ ደሞ ራሷ ፈንካች
የተፈነከተ ልቡ ያባበጠ ሰንካላ ቁስለኛ
ፍሬዋን ቀጣፊ ደሞ ደሞ አድፋፊ
መሆኑ ቀማኛ
ታድያ ምን ይገርማል ውሉ አይደለ የአለም
የማለዳ ደስታ የማለዳ ውበት ጀምበር ስትጠልቅ የለም
በሳቅ በውዳሴ እሰይ እሰይ ብሎ
ቀይ ምንጣፍ አንጥፎ ውብ ቃላት ደልድሎ
ለሀገር ያሽቃብጣል ላይ ታች ይሯሯጣል
ፍሬውን ገና ሲያይ ከነ ስሩ ይቆርጣል
እናማ.....ትናንትና ያበበ ዛሬ ከደረቀ
ከለጋው ቅርንጫፍ ፍሬው ከለቀቀ
የለመለመው መስክ ድንገት ከከሰመ
ተቃናልኝ ያሉት ደግሞ ከጠመመ
ታድያ ምን ይገርማል ውሉ አይደል የአለም
የማለዳ ተስፋ የማለዳ ትጋት አመሻሽ ላይ የለም::
By kidist
@getem
@getem
@getem
👍 37❤ 15🔥 2
