68 961
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-137 روز
-96730 روز
آرشیو پست ها
#ከገሃዱ ዓለም
#ለስኬት እንዳንበቃ
የሚያደርጉን ሰበቦች:-
---------------------------------------
፩.አደጋዎች ለመጋፈጥ አለመሞከር
፪.በፍጥነት ለመበልጸግ መፈለግ
፫.ቅድሚያ መሰጠት ያለባቸውን ጉዳዮች ለይቶ አለማወቅ
፬.አቋራጭ መንገዶችን ማሰስ
፭.አቋመ-ቢስነት
፮.የተፈጥሮ ህግጋትን አለመረዳት
፯.ለማቀድና ለመዘጋጀት አለመፈለግ
፰.ምክንያት ሰበብ መደርደር
፱.ካለፉት ስህተቶች አለመማር
፲.መልካም አጋጣሚዎችን አለማጤን
፲፩.ፍርሃት
፲፪.ተሰጥኦን መጠቀም አለመቻል
፲፫.የዲስፕሊን ጉድለት
፲፬.ለራስ የሚሰጥ ዝቅተኛ ግምት
፲፭.የዕውቀት እጥረት
፲፮.ጉጂ/ገዳይ አመለካከት
፲፯.የግብ አለመኖር
፲፰.ወኔ ማጣት
-----------------------------------------
✍✍DT(@dtvote12)
❤ 67👍 61🤔 2🤣 1
ጉዞው የፍጻሜውን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ አስታውስ!
“ለአንድ ጉዞ ግብና ፍጻሜ የመኖሩ ጉዳይ አስፈላጊ ነው፡፡ በመጨረሻው ላይ ግን የጉዞው ጉዳይ ነው አስፈላጊው ነገር” -
Ursula K. LeGuin
አንዳንድ ሰዎች ህልማቸውን እውን ለማድረግ የሚሄዱበት ጎዳና ለድካም፣ ለህመምና ለቆሰለ ስሜት አሳልፎ ሲሰጣቸው ይታያሉ። በእንደዚህ አይነት መልኩ ማንነቱን ለጉዳት ያጋለጠ ሰው ህልሙ ጋር ቢደርስ ትርጉሙ ምንድን ነው? ህልሙ ጋር ሲደርስ በስኬቱ ለመደሰት የሚያበቃ ጤንነቱም እንኳን አይኖረውም፡፡ ሰዎች ገንዘብ የማግኘትን ህልም ይዘው ያሰቡትን ገንዘብ ለማግኘት ጤንነታቸውን ሲያጡ ክስረቱ ሁለት ነው። አንዱ ክስረት ያገኙትን ገንዘብ ጤንነታቸውን ለመመለስ እንደገና ማጥፋታቸው ነው፡፡ ሁለተኛው ክስረት ደግሞ ገንዘብ የማግኘት ህልም ጋር የደረሰው ሰው ገንዘቡን እንደፈለገው ለማድረግ የሚያበቃ የስሜትም ሆነ የአካል ጤንነት ማጣቱ ነው፡፡
ለአንዳንድ ሰዎች ሕይወት ማለት አንድ የሚደረስበት ግብ ነው፡፡ ሕይወት ግን የሚደረስበት ግብ አይደለም፤ ሕይወት የየእለት ሂደት ነው፡፡ ምንም እንኳ ይህ ሂደት በመጨረሻው አንድ ደረጃ ላይ ቢያደርሰንም፣ የሕይወት ዋናው ክፍል ያለው ወደዚያ ጥግ ለመድረስ የምናደርገው ጉዞ ነው፡፡ አላማ ላይ በመድረስ ምክንያት ሰዎች ትዳርን፣ ልጆችን፣ ቤተሰብን ሲበትኑ ማየት አሳዛኝ ነው፡፡
አንድን በንግዱ ስኬታማ ለመሆን ብዙ የለፋ፣ የተጨቃጨቀና በብዙ የስሜት ውጣ ውረድ ያለፈን ሰው አስብ፡፡ ንግዱን ለማጧጧፍ ሲሯሯጥ ለትዳሩና ለልጆቹ ያለውን ጊዜ ሰርቆበት ከቤተሰቡ ጋር ብዙም ጤናማ ግንኙነት የለውም፡፡ ከወዳጆቹ ጋር በገንዘብ ምክንያት ተለያይቷል፣ የተለያዩ ከስሜት ቀውስ የተነሳ የሚመጡ በሽታዎች አግኝተውታል፣ ስሜቱ ተጎድቷል ...። በመጨረሻ ግን ንግዱ ተሳካለትና ገንዘብን አካበተ። ሰብሰብ ብሎ ሲያስበው ግን ጤንነቱን አጥቷል፣ ቤተሰቡ ፈራርሷል፣ ወዳጆቹ ተለይተውታል ... የክስረት ሁሉ ክስረት!
ይህንን አስታውስ፡- ትርፍና ኪሳራ ሁል ጊዜ ከገንዘብ ጋር የተያያዘ አይደለም፡፡ መፍትሄው ምን መሰለህ፣ ወደህልም የምትሄድበትን ጉዞ ህልሙን የማግኘትህን ያህል አስፈላጊ ነውና ተደሰትበት፡፡
🙏 መልካም ምሽት!!
Join: @Human_Intelligence
Join: @Human_Intelligence
🙏 28👍 26❤ 5👏 5🤔 2🥰 1
Abush_Zeleke_HAGER_ENA_SEW_ሀገር_እና_ሰው_Official_Lyric_Video128k.m4a4.25 MB
👏 74👍 21🙏 14❤ 8😢 2
Photo unavailableShow in Telegram
አንድ ሰው ሳይኮአናሊስስ ጆርጅ በርናርድ ሾውን እንዲህ ሲል ጠየቀው፦ "ከዚህ ሁሉ እድሜ በኋላ ያንተ የህይወት ፍልስፍና ምንድን ነው?"
ጆርጅ መለሰ፡-
`` በሕይወቴ ውስጥ የእኔ ፍልስፍና በጣም ቀላል ነው። እነሱ ከሚፈቅዱት በላይ ወደ ሰዎች አልቀርብም፤ ሰዎችም ከሚገባቸው በላይ እንዲቀርቡኝ አልፈቅድም..!። ``👍 107❤ 24🔥 2🙏 2
``
ልጆችን ከማሳደግህ በፊት መጀመሪያ እራስህን ማሳደግ አለብህ። ይህ ካልሆነ ግን ከእንስሳዊ ፍላጎት የተነሳ ልጅ መውለድ ትፈልጋለህ፤ ብቸኝነት አልያም በራስህ ውስጥ ጉድለቶችህን ለመሙላት እንደማለት ነው። የአባትነት ተልዕኮህ ልጅ መውለድ ሳይሆን በቅድሚያ እራስህን መውለድ ነው ከፍ ወዳለ ነገር.. ``
-Thus spoke Zarathustra 📖👏 67👍 39❤ 8🤔 1
Repost from TgId: 1173613158
"ሳያሰቃዩ ቢገድሉን ጥሩ ነው"
* * *
እንደ ህዝብ በአንድ እንቅፋት ደጋግመን እንመታለን። አልፈነው የተሻገርነው የመሰለን ገደል አፈፍ ላይ እየደጋገመን እንገኛለን። ትላንት ያደናቀፈን ዛሬም ያደናቅፈናል። የቀደመውን የሚመስል ሰቆቃን እንኖራለን። ለቅሶ እንደጋግማለን።
ተቀፀል የደራሲ ፍቅረማርቆስ ደስታ ጓደኛ ነው። የአበባነት ዘመኑን የፖለቲካ እሳት የለበለው ወጣት ነው ፥ ተቀፀል።
ፍቅረ ማርቅስ ደስታ እና ተቀፀል በዘመነ ደርግ ለእስር ተዳረጉ። ያ ዘመን ወጣት ሁሉ ወደእስር ሲከፋ ደግሞ ወደ ሞት የሚነዳበት ዘመን ነበርና ተቀፀል እና ፍቅረ ማርቆስ ደስታ ታሰሩ። የታሰሩት በባህርዳር ከተማ ነው። የእስራቸው ሰበብ ደግሞ "ኢህአፓን ደግፋችኋል" የሚል ነበር።
ፍቅረ ማርቅስ "የሚሳም ተራራ" በሚለው መፅሐፉ 'ባዶ የሲሚኒቶ ወለል ላይ አስተኝተው እንደ ሲጋራ ሰውነታችንን ደፈጠጡት' ብሏል።
እነ ፍቅረ ማርቆስ ከገበሬዎች ፥ ከሙህራን ፥ ከተማሪዎች ፥ ከመምህራን ወዘተ ጋር ታጭቀው ለአመት ያህል ታሰሩ። በእስራቸው ዘመን ሞት ወግ ሲያጣ ተመልክተዋል። ገላ በግርፋት ብዛት ሲተለተል አይተዋል።
ፍቅረ ማርቆስ 'የሚሳም ተራራ' መፅሐፍ ላይ 'ተቀፀል ጓደኛዬ' በሚል ርዕስ ስለ ወዳጁ ፅፏል።
አንድ ቀን "ዛሬ እኛንም ይገድሉናል" አለ ተቀፀል።
"ኧረ" አለ ፍቅረማርቆስ ፍርሃት እያራደው።
ሁለቱ እስረኞች አጠገብ ለአጠገብ ፍርሃት እያራዳቸው ተቀምጠዋል። የሞታቸው ቀን እንደደረሰ ያመነው ተቀፀል "ሳንሰቃይ ብንሞት ጥሩ ነበር" አለ።
ምኞቹ በህይወት መቆየት አልነበረም። መንግስትን ተቃውመሃል ተብሎ ዘብጥያ የወረዳው ወጣቱ የፖለቲካ እስረኛ በህይወት መቆየትን አልተመኘም። ከአሳሪዎቹ ዘንድ ምህረት ማግኘት ቅንጦት መሆኑ ገብቶታል። ምኞቱ ስቃይ አልባ ሞት ነበር።
"ሳያሰቃዩ ቢገድሉን ጥሩ ነበር"
ዘመነ ደርግን የሚያሳዩ መፅሐፍት የሰዎችን አሟሟት ሲዘግቡ ከስቃይ ጋር ነው። ሰዎች ወፌ ላላ ይገረፋሉ ፥ ሰውነታቸው ተዘቅዝቆ ይሰቃያሉ ፥ መፈጠራቸውን እስኪጠሉ ይደረጋሉ። ከመሞት በፊት ብዙ ሰቆቃ አለ።
እንዳለ ጌታ ከበደ "ማዕቀብ" በሚለው መፅሐፉ በጋዜጣ ተጠቅልሎ እሳት ተለቆበት ስለተሞተ ሰው አስፍሯል።
ያ ዘመን እንዲህ ነው። ወግ ያለው ሞት ማግኘት ብርቅ ነው። ሮጠው ያልጨረሱ ወጣቶች ተሰቃይቶ ይገደላሉ።
የፍቅረ ማርቆስ ጓደኛ በህይወት መትረፍን አልተመኘም። ምኞቱ ሳይሰቃይ መሞት ነበር።
እንዲህ ነን። የተሻገረነው የመሰለን ገደል ዳግመኛ ይጠብቀናል። አባቶቻችንን የመታ እንቅፋት እኛን ይደግማል። ታላላቆቻችን የተሸከሙትን መስቀል እኛም እንሸከማለን።
ያልታደልን
@Tfanos
👍 83❤ 19👏 3🤔 1😢 1
📚ርዕስ: የልማድ አስደናቂ ሀይል
📝ደራሲ: ጄምስ ክሌር
👤ትርጉም: ድረስ ጋሻነህ
📜ዘውግ: self help
📖የገፅ ብዛት:264
📅ዓ.ም: 2013
@Human_Intelligence
የልማድ አስደናቂ ሀይል.pdf75.17 MB
👍 32❤ 6
Photo unavailableShow in Telegram
| #የልማድ ኃይል
#ATOMIC_HABITS
#አንተ_ማለት_ልማዶችህን_ነህ!!! _ በጠቅላላው ሲታይ የምትፈልገውን ሰው እንድትሆን ይረዱሃልና ልማዶች በጣም ጠቃሚ ነገሮች ናቸው። ልማዶች መሆን የምትፈልገውን ሰው ለመሆን የምታልፍባቸው መንገዶች ናቸው። ባጭሩ አንተ የምትሆነው ልማዶችህን ነው። #በየቀኑ በልማዳችን ላይ የምናሳያቸው ጥቃቅን_ለውጦች ሕይወታችንን ፍፁም የተለየ መዳረሻ ይሰጡታል፡፡ በጊዜ ሂደት ግን አሁን አንተ በሆንከው እና አንተ ትሆን በነበረው ማንነት መካከል ያለውን ልዩነት የሚፈጥሩት እነዚህ ጥቃቅን ልዩነቶች ናቸው፡፡ ስኬት የ በየቀኑ ልማዶች ድምር ውጤት ነው፡፡ ወሳኙ ነገር 'ልማዶችህ ወደ ስኬት የሚወስዱህ ናቸው ወይስ አይደሉም?' የሚለው ነው፡፡ ስለሆነም አብዝተህ መጨነቅ ያለብህ ዛሬ ላይ ስላመጣኸው ውጤት ሳይሆን የዛሬው ጉዞህ አቅጣጫ ላይ ነው፡፡ ልማዶች በሁለቱም በኩል የተሳሉ ሰይፎች ናቸው፡፡ መልካም ልማዶች ሊስሉህና ሊያሳድጉህ የሚችሉትን ያህል መጥፎ ልማዶች ደግሞ ቆራርጠው ሊጥሉህ የሚችሉበት እድል በዚያው መጠን ነው፡፡ #ልማድህን_መቀየር_ከባድ ሆኖብህ_ከሆነ ችግሩ ያንተ አይደለም | ችግሩ የስርዓትህ_ነው_መጥፎ ልማዶች_እየተደጋገሙ የሚከሰቱት ልትቀይራቸው_ስላልፈለግክ ሳይሆን_የተሳሳተ_የለውጥ ሥርዓት_ስ ላለህ ነው። #Atomic_habits_የልማድ ኃይል በሚል የተተረጎመው መጽሐፍ ደግሞ የተሳሳተ የለውጥ ስርአትህን በመቀየር እንዴት ስኬታማ መሆን እንደምትችል ያሳይሀል። #የፈላ ውሃ_ድንችን ሲያለሰልስ እንቁላልን ግን ያጠነክረዋል #እኛ_ድንች ወይም እንቁላል መሆንን መምረጥ አንችልም፤ ጠንካራ ወይም ለስላሳ ሊያደርጉን በሚችሉ ጨዋታዎች ውስጥ ለመጫወት መወሰን ግን እንችላለን። ለዚህም ደግሞ #Atomic_habits_የልማድ ኃይል መጽሐፍ ይረዳናል፡፡
@Human_Intelligence
👍 39❤ 6🔥 4😢 2
Photo unavailableShow in Telegram
ሰባኪው አዲስ ተጋቢ ሙሽሮችን ወደመድረክ ጠርቶ የጋብቻ ስስነርዓታቸውን እያስፈፀመ እያለ
"ይህንን ጋብቻ የሚቃወም ካለ ወደ መድረክ ይምጣ አለ!"
በዚህ ጊዜ አንድ የ3 ዓመት ህፃን ልጅ ያቀፈች እርጉዝ ሴት ከአዳራሹ መጨረሻ ወንበር ተነስታ ወደፊት ማዝገም ጀመረች።
ሙሽሪትም ያች ህፃን የያዘች እርጉዝ ሴት ወደፊት ስትመጣ ስታይ ሙሽራውን ወራዳ ልክስክስ በሚስትህ ላይ ነው ልታገባኝ የነበረው አለችና በጥፊ መታው በጎን ባለው በር ወጥታ ሮጠች።
ታዳሚውም አብዛኛው በተፈጠረው ክስተት ተገርሞ እያጉረመረመ በሚቀርበው በር እየወጣ ሄደ።
ያች ህፃን የያዘች ሴት ፊት ወንበር ላይ ስትደርስ ከአንዱ ወንበር ላይ ቁጭ አለች። ሰባኪውም ግራ ተጋብቶ "ምነው ችግር አለ እህቴ?" አላት።
ያች ሴትዮም "ምንም ችግር የለም ጌታዬ! ጆሮዬ የመስማት ችግር ስላለበት በደንብ እንዲሰማኝ ከፊት ልቀመጥ ብዬ ነው!" አለችው።
♥የመልዕክቱ አንኳር ጭብጥ፡-
የነገሮችን ፍፃሜ ሳናይና ሳንሰማ ቸኩለን በግምት አንደምድም ማስተዋል አለመቻላችን እና ቸኩሎ መወሰን ብዙ ያሳጣናል ።
መልካም ቀን ይሁንላችሁ!!!
👍 122👏 15❤ 4🤔 3
የመጨረሰን ጣዕም የማያውቅ ለራሱ ክብር አይኖረውም
✍በሚስጥረ አደራው
💎ነገርን ጀምሮ መጨረስ የሚሰጠው ስሜት ልዩ ነው። ብዙ ጊዜ ግልጽ የሆነ የጥፋተኝነት ስሜት የሚሰማን ለሌሎች የገባነውን ቃል ማክበር ሲሳነን ነው። የጥፋተኝነት ስሜት ብቻም ሳይሆን እራስን ወቀሳ ውስጥም እንገባለን። ሆኖም ግን ይህ ስሜት ማንነታችን ላይ የሚያደርሰው ጥፋት አናሳ ነው። ትልቁ ጥፋት የሚመነጨው ለራሳችን የገባነውን ቃል ማክበር ሲሳነን ነው። ለራሳችን የገባነንውን ቃል ማክበር ሲያቅተን፤ አፍ አውጥተን እራሳችንን መውቀስ ባንችል እንኳን ለራሳችን ያለንን እምነትና አመለካከት በእጅጉ ይጎዳዋል። አብዛኛውን ጊዜ ይህ የገዛ ቃል ኪዳንን ካለማክበር የሚመጣው የጥፋተኝነት ስሜት የሚያደርስብን ጥፋት በገሃድ የሚታይ አይደለም። ልክ እንደ ትንሽ የኮርኒስ ቀዳዳ በቀን በቀን የሚያስገባው ዝናብ እምብዛም አይረብሽም። ከብዙ ጊዜ በኋላ ግን ቀዳዳው ይሰፋና አይምሮዋችን ሳይወድ በግዱ የችግሩን መኖር እንዲቀበል ያስገድደዋል።
💡ናትናዬል ብራንደን የተባለው ሳይኮሎጂስት “በራስ መተማመን ማለት እኛ ስለእራሳችን የገነባነው ስም ነው” ይላል። የገነባነው ስም ሲል፤ በስራችን፤ በውሳኔዎቻችን እና በአመለካከቶቻችን ለረጅም ጊዜ ያስመሰገብነውን ውጤት ነው። መልካም ስም የሚገነባው ሰው እንደተጠበቀው መጠን ሆኖ ሲገኝ ነው። ለምሳሌ አንድ ሰው ሁሌ እመጣለሁ እያለ ቢቀርብን፤ ከግዜ በኋላ ለዚህ ሰው “ቃለ-አባይ” የሚል ስም መስጠታችን አይቀርም። በተደጋጋሚ እመጣለሁ እያለ ከቀረ፤ ከጊዜ በኋላ እኛም ቀጠሮው ቦታ መገኘት እናቆማለን። ምክንያቱም፤ በድግግሞሽ ማንነቱን ስላስተዋወቀን።
“Self-Esteem is the reputation we acquire with ourselves”- Nathaniel Branden
🔱እኛም ላይ የሚፈጸመው ከዚህ የተለየ አይደለም። ነገሮችን አደርጋለሁ እያልን ባላደረግን ቁጥር፤ እራሳችን እየቀጠርን በቀረን ቁጥር ከጊዜ በኋላ እኛ ለእራችን የምንገባው ቃል ዋጋ ያጣል። እምነት ማለት ይደረግልኛል ብሎ መጽናት ማለት ነው። በራስ መተማመን ለእኔ እንደሚገባኝ፤ እኛ እራስችን ላይ ያለን እምነት ነው። ምን ያህል ለእራሳችን ቃል እንገዛለን? ማንም ሰው በቃሉ የሚቆምን 'ሰው ይውዳልም ያከብራልም። ለቃሉ የሚታመን ሰው የተከበረና የተመሰገነ ነው። እኛም ለእራሳችን የምንገባውን ትንሽም ሆነ ትልቅ ቃል ባከበርን ቁጥር፤ ለእራሳችን ያለን ፍቅርም ሆነ ክብር እየጨመረ ይመጣል።
💎አብዛኛውን ጊዜ ከሌሎች ጋር የምንጋጨው በቃላቸው አልተገኙም፤ በጠበቅናቸው ቦታ አልቆሙም ብለን ነው። እኛ በእራሳችን መደሰት ሲያቅተን፤ ምናልባት ያጠፍነው ቃል ይኖር ይሆን ብለን አስበን እናውቃለን? የሰው ልጅ ባህሪ ይደንቃል፤ እራሳችንን ከማስደሰት ይልቅ ሌሎችን ለማስደሰት የምንጥረውን ያህል፤ ሌሎች ላይ ከምናሳርፈው ወቀሳ በላይ እራሳችን ላይ የምናሳርፈው ወቀሳ ይበልጣል።
💡 ያላስተዋነው አንድ ነገር ቢኖር፤ ሌሎች በቃላቸው አልተገኙም ብለን ይህን ያህል ከተከፋን፤ እኛ ለገዛ እራሳችን ቃለ-አባይ ስንሆን ምን ያህል ቅያሜ ውስጥ እንገባለን? ብዙ ሰዎች ከሌሎች ሰዎች በላይ እራሳቸው ላይ የመጨከን አቅም አላቸው። የእርባና ቢስነት ስሜት የዚህ የጭካኔ አንዱ ውጤት ነው። እስከመቼ ነው የምታለለው ብሎ አንድ ቀን ውስጣችን ተስፋ ይቆርጥብናል። ነገ እደርስልሃለሁ ብለን ብንሞግተው እንኳን፤ ከዚህ በፊት መቶ ጊዜ የገባነው ቃል ነበርና አይሰማንም። ሌሎችን በከንቱ የቃላት ድርደራ አስረን ማቆየት እንደማይቻል ሁሉ፤ እኛም እራሳችንን በቃል ብቻ ያለድርጊት ልናከርመው አይቻለንም። ሰው በእራሱ እምነት ሲያጣ ከራሱ ይሸሻል…
💡ለእኔ የደስታ ትልቁ ንጥረ ነገር ሰላም ነው፤ የአይምሮ ሰላም! የአይምሮ ሰላም ደግሞ የመንፈስና የስጋ፤ የፍላጎትና የድርጊት፤ የእውነታና የፍርድ ሚዛንን የመጠበቅ ሃላፊነት አለበት። ለውስጣችን ሰላም ማጣት ብዙ ምክንያቶች ሊደረደሩ ቢችሉም፤ ያለጥርጥር ቃልን ካለማክበር የሚመነጩት ምክንያቶች አብዛኛዎቹ ናቸው። አንዳንዴ የሆነ ነገር ለማድረግ አስባችሁ በደስታ ጫፍ ከደረሳችሁ በኋላ፤ ጥቂት ጊዜ እንዳለፈ የደስታው ስሜት በርዶ የአለመቻል ስሜት ወሮዋችሁ አያውቅም? እኔ እንደሚመስለኝ እንዲህ የሚሰማን፤ ውስጣችን ከዚህ በፊት ያጠፈነውን ቃል ሲያስታውስ ነው።
🔱በውህደት ሃሳብ ውስጥ የሚመላለስ ሰው፤ እራሱን ሌሎች ውስጥ በቀላሉ ያያል። በሌሎች ስሜቶች ውስጥ የገዛ እራሱን ስሜት ስለሚያስተውል፤ ለሌሎች በሚያዝነበት መጠን ለእራሱም ያዝናል። ይህንን ያልኩበት ምክንያት፤ ለሌሎች ሰዎች የገባነውን ቃል ባለማከበራችን የሚደርሰው መጥፎ ስሜት፤ የእራሳችንን ቃል ስናጥፍ ከሚፈጠረው ስሜት ጋር ተመሳሳይ ስለሆነ ነው። እንደውም ባይበልጥ። ስለዚህ ለእራስ የገቡትን ቃል ማጠፍ እንደ ቀላል ነገር የምንወስደው አይደለም። ጥፋቱ ከምናስበው በላይ ነው።
💎ከላይ እንዳሰፈርኩት ስለእራሳችን የሚኖረን እምነት፤ ፍቅርና ክብር፤ በቃል አክባሪነታችን መጠን ይወሰናል። ጀምረን የምንጨርሳቸው ማንኛቸውም ተግባሮች የእምንት ጡቦች ናቸው። ከጊዜ ብዛት በነዚህ ጡቦች የሚገነባው ግንብ እኛን ከእራስችንም ሆነ ከሌሎች ሰዎች ጥርጣሬ ይከላከለናል። የመጨረስን ጣዕም ካላወቅን እውነትም ለራሳችን ክብርና እምነት አይኖረንም። የሚገርመው ነገር፤ ይህንን ስሜት ለማምጣት ትልቅ ነገር ጀምረን መጨረስ አይጠበቅብን.…ማንኛቸውም ጅማሬዎች ፍጻሚያቸው ወደዚህ ስሜት ያደርሰናል።
⚜ ዋናው ነገር ለእራሳችን የምንገባቸውን ማንኛቸውንም ቃል ኪዳኖች በቁም ነገር መውሰዳችን እንዲሁም ሁሉንም ጅማሬዎች ከፍጻሜ እንዲደርሱ መጣራችን ነው። ሁላችንም ቃሉን የማያከብር ሰው አናከብርም…የገዛ እራሳችንን ጨምሮ። ቃል ተቀብሎ የማይደረግለት ደግሞ እንደተካደ ይሰማዋል …የገዛ እራሳችንን ጨምሮ።
Join: @Human_Intelligence
Join: @Human_Intelligence
👍 58❤ 5👏 2🤔 2
❥••••በ ትንሽ ድንጋይ እስክትመታ አትጠብቅ!!
•
๏ የኮንስትራክሽን ተቆጣጣሪው ከ 6ኛ ፎቅ ላይ ሆኖ መሬት ላይ የሚስራውን ሰራተኛ ይጠራዋል፣ ስራተኛው ሊስማው አልቻለም፡፡
•
ስራተኛው የአሰሪውን ጥሪ ሊስማው ስላልቻለ ተቆጣጣሪው መላ ዘየደ፡፡ እናም የሰራትኛውን ሃሳብ ልማግገኘት ሲል ተቆጣጣሪው ከላይ ብር ጣለለት ብሩም ከሰራተኛው እግር ስር አረፈ፣ ሰራተኛው ብሩን አንስቶ ወደ ኪሱ አሰገብቶ ስራውን ቀጠለ……
•
በድጋሜ የሰራተኛውን ሃሳብ ለማግኘት ተቆጣጣሪው መጀመሪያ ከጣለው ብር በላይ ሌላ ብር ጨምሮ ጣለለት፣ የቀን ሰራተኛውም ልከ እንደ መጀመሪያው ብሩን አንስቶ ወደ ኪሱ አስገብቶ ስራውን ቀጠለ፡፡
•
በመጨረሻ ሌላ መላ ዘየደ ብር በመጣል የሰራተኛውን ሀሳብ ማግኘት ስላልቻለ የሰራተኛውን ሃሳብ ለማግኘት አነስ ያለ ድንጋይ አነሳና ወደ ሰራተኛው ወረወረው፣ ድንጋዩም የሰራተኛውን ጭንቅላት አገኝው በዚህ ሰዓት ነበር ሰራተኛው ወደ ላይ የተመለከተው እና ከተቆጣጣሪው ጋር መነጋግር የጀመረው፡፡
---------------------------
:
:
ይሄ ታሪክ ከእኛ ህይወት ጋር ይመሳሰላል ፈጣሪ ከኛ ጋር መገናኘት ይፈልጋል ነገር ግን እኛ በጣም በ አለማዊ ስራ ራሳችንን ጠምደናል ከዛ ፈጣሪ ትንሽ ስጦታ ይሰጠናል እኛም ስራችንን እንቀጥላለን ከየት እንዳገኘነው ቀጥ ብለን ለማየት ጊዜ የለንም፡፡
በድጋሜ ፈጣሪ ከመጀመሪያው የተሸለ ስጦታን ይሰጠናል አሁንም ልክ እንደ መጀመሪያው ስጦታውን ወስደን ምስጋናም ለፈጣሪ ሳናቀርብ እድልኞች ነን ብቻ ብለን ስራችንን እንቀጥላልን ከየት እና ከማን እንዳገኘነው ቀና ብለን ለማየት አንሞክርም፡፡
እናም በትንሽ ድንጋይ ስንመታ፣ ማለት ትንሽ ችግር ቢጤ ስታገኘን ወደ ላይ ማየት እና መጮህ ከዚያም ከፈጣሪ ጋር መነጋገር እንጀምራለን፡፡ ስለዚህ ምንግዜም በህይወታችን ስጦታን ስናገኝ በፍጥነት ፈጣሪን ማመስገን አለብን በጭራሽ በትንሽ ድንጋይ እስክንመታ መጠበቅ የለብንም ሁሌም ቢሆን ከፈጣሪ ጋር እንገናኝ ...
#ሼር አድርጉ
Join: @Human_Intelligence
Join: @Human_Intelligence
👍 102❤ 35👏 3🙏 1
የስቴቨን ኮቬይ የጊዜ አጠቃቀም ማትሪክስ አራቱ ኳድራንቶች
እያንዳንዱ ኳድራንት የተለየ ባህሪ አለው እና ለእርስዎ ተግባራት እና ሃላፊነቶች ቅድሚያ እንዲሰጡ ለማገዝ የተነደፈ ነው። እነዚህ አራት ማዕዘናት እንደሚከተለው ናቸው።
ኳድራንት 1 - አስቸኳይ እና አስፈላጊ
ኳድራንት 2 - አስቸኳይ ያልሆነ ነገር ግን አስፈላጊ የሆነ
ኳድራንት 3 - አስቸኳይ ግን አስፈላጊ ያልሆነ
ኳድራንት 4 - አስቸኳይ እና አስፈላጊ ያልሆነ
ኳድራንት 1 - አስቸኳይ እና አስፈላጊ
ከወሳኝ ውጤቶች ጋር የተያያዙ ኃላፊነቶችን ወይም ተግባሮችን ያካተተ ሲሆን አስቸኳይ ትኩረት ይጠይቃል። በዚህ ባለ አራት ማእዘን ውስጥ ያሉት ጉዳዮች በአስቸኳይ እና አስፈላጊነታቸው ምክንያት አስጨናቂዎች ሊሆኑ ይችላሉ ፣ ስለዚህ እነዚህን ተግባራት ማወቅ እና በዚህ መሠረት መመደብ አስፈላጊውን ጊዜ እና ጥረት በእነሱ ላይ እንዲያተኩሩ ያስችልዎታል። በ Q1 ውስጥ የተካተቱ ጉዳዮች የሚከተሉት ባሕርያት አሏቸው:-
የሚመጡ የጊዜ ገደቦች
ከግዜ-ተኮር ግቦች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት
አስቸኳይ አደጋን በማቃለል ውስጥ የሚከወን
ኳድራንት 2 - አስቸኳይ አይደለም ነገር ግን አስፈላጊ ነው
Q2 የተግሣጽ እና የቁርጠኝነት ስሜትን ለማዳበር በእንቅስቃሴዎች ላይ ማተኮር ፣ እንዲሁም እርስዎ ሊቆጣጠሯቸው በሚችሏቸው ነገሮች ላይ መለየት እና መስራት ያካትታል። አንዳንድ የ Q2 ንጥሎች የሚከተሉት ባሕርያት ሊኖራቸው ይችላል
ዕቅድ ወይም ተጨማሪ እርምጃዎችን ይጠይቁ
ከአጠቃላይ ግቦች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት
አራተኛ 3 - አስቸኳይ ግን አስፈላጊ አይደለም
በ Q3 ውስጥ ያሉ እንቅስቃሴዎች አስቸኳይ ናቸው እና በቅጽበት ውስጥ አንዳንድ አስፈላጊነትን ይይዛሉ። እነዚህ ከሥራ ፍሰትዎ ሊቀንሱ ወይም ሊወገዱ የሚችሉ ባህርያት ወይም ነገሮች(items) ናቸው። ከሚከተሉት ባሕርያት መካከል አንዳንዶቹን ሊኖራቸው ይችላል-
በ Q1 እና Q2 ውስጥ ያሉት ዝርዝሮች ላይ የሚኖር ደካማ ዕቅድ የሚከተሉትን ውጤቶች ያስከትላል:-
* ምርታማነትን ማቋረጥ
* መዘናጋት
አራተኛ 4 - አስቸኳይ እና አስፈላጊ አይደለም
በ Q4 ውስጥ ያሉ ተግባራት ሙሉ በሙሉ ሊወገዱ ወይም ሊቀነሱ ይችላሉ። የትኞቹ ሥራዎች ወይም ጉዳዮች ዝቅተኛ ቅድሚያ(minimum priority) የሚሰጧቸው እንደሆኑ ማወቅ እና በዚህ አራት ማእዘን(ኳድራንት) ውስጥ የትኞቹ ዝርዝሮች እንደሆኑ መለየት አስፈላጊ ነው። እነዚህ ዝርዝሮች በተለምዶ የሚከተሉት ባሕርያት አሏቸው:-
አነስተኛውን የጭንቀት መጠን ያስከትሉ
ከአጠቃላይ ወይም ጊዜ-ተኮር ግቦች ጋር በቀጥታ የተዛመደ አይደለም።
The four quadrants of the Covey Time Management Matrix
Each quadrant has a different property and is designed to help you prioritize your tasks and responsibilities. These quadrants are as follows:
Quadrant 1: Urgent and important
Quadrant 2: Not urgent but important
Quadrant 3: Urgent but not important
Quadrant 4: Not urgent and not important
Quadrant 1: Urgent and important
Q1 involves responsibilities or tasks related to critical results and require urgent attention. The items in this quadrant may also be stressors due to their urgency and importance, so being aware of these tasks and categorizing them accordingly can ensure you focus the necessary time and effort on them. Items that fall into Q1 have the following qualities:
Impending deadlines
Direct relation to time-sensitive goals
Involve alleviating immediate risk
This quadrant is located top left in the matrix.
Quadrant 2: Not urgent but important
Q2 involves focusing on activities to develop a sense of discipline and commitment, as well as identifying and working on things you can control. Some Q2 items may have the following qualities:
Require planning or additional steps
Direct relation to overall goals
This quadrant is located top right in the matrix.
Quadrant 3: Urgent but not important
Activities in Q3 are urgent and assume some form of importance in the moment. These are likely items that can be reduced or removed from your workflow. They likely have some of the following qualities:
Result of poor planning of items in Q1 and Q2
Interrupting productivity
Distraction
This quadrant is located bottom left in the matrix.
Quadrant 4: Not urgent and not important
Tasks in Q4 are more likely able to be removed completely or reduced. It is important to identify which items belong in this quadrant so you know which tasks to classify as lowest priority. These items typically have the following qualities:
Cause the least amount of stress
Not directly related to overall or time-sensitive goals
By Maximilian A. (Engineer)
👍 40❤ 4👏 2🙏 2
ግብ እንዴት ልቅረጽ❔
_____
ለቢዝነሳችንም ሆነ ለግል ሕይወታችን የት እና እንዴት መድረስ እንደምንፈልግ ግልጽ የሆነ ግብ መያዝ ከመባከን ያድነናል። ይሁን እንጂ ሰዎችም ሆኑ ቢዝነሶች ብዙ ጊዜ ግባቸውን ግልጽ በሆነ መንገድ ለማስቀመጥ ይቸገራሉ፤ አንዳንዴ እንደውም ጭራሽ ምንም ግብ ሳይቀርጹ ይቀራሉ።
የትኛውም ዓይነት ግብ ሲቀረጽ፤ በሚከተለው መልኩ ቢሆን ለመቅረጽም፣ ለመከታተልም፣ እንዲሁም ለመተግበር ያመቻል። ይህ የግብ አቀራረጽ ዘዴ በእንግሊዝኛው ምህጻረ ቃል "SMART" ተብሎ የሚጠራ ሲሆን 5 መስፈርቶች አሉት።
የትኛውም የምናስቀምጠው ግብ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ መሆን ይኖርበታል።
1⃣ የማያሻማ (Specific)
የማያሻማ ግብ ማለት ግልጽ እና "ምን ማለት ይሆን?" የማያሰኝ መሆን አለበት።
ለምሳሌ:-
"በዚህ ዓመት ስኬታማ መሆን" የሚለው ፈጽሞ ለአንድ ቢዝነስ ግብ ሊሆን አይችልም። ስኬታማ ሲል ምን ማለት እንደሆነ፣ በዝርዝር እና ቁልጭ ባለ መንገድ መገለጽ መቻል አለበት።
2⃣ የሚለካ (Measurable)
የሚለካ ግብ ማለት ተሳክቷል አልተሳካም የሚለው በቀላሉ መመዘን የሚችል ማለት ነው።
ለምሳሌ:-
"ትርፋማ መሆን" የሚለው ግብ የሚለካ አይደለም። "የአንድ ሺህ ብር ትርፍ ማግኘት" የሚል ብናደርገው፣ ምን ያህል ተሳክቷል የሚለው በቀላሉ መመዘን ስለሚችል የሚለካ ግብ ሆነ ማለት ይቻላል።
3⃣ ሊደረስበት የሚችል (Achievable)
ግባችን ባለንበት ነባራዊ ሁኔታ ለመሳካት የማይቻል መሆን የለበትም። ሊደረስበት የሚችል የሚለው የሚያመለክተው ካለንበት ወቅታዊ ይዞታ አንጻር የመሳካት ዕድል ያለው መሆኑን ነው።
ለምሳሌ:-
በወር የ20 ሺህ ብር የገንዘብ ዝውውር ያለው ቢዝነስ፤ "በዓመቱ መጨረሻ የአንድ ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘት" ቢል ካለበት ሁኔታ ጋር የማይጣጣም እና ሊደረስበት የማይችል ሆኖ ይገኛል። ይልቅ ነገሮችን አገናዝቦ የበለጠ ሥራን በሚያበረታታ መልኩ ከፍ ያለ ግን ከእውነታው በጣም ያልራቀ ግብ ማስቀመጥ ይኖርበታል።
4⃣ ከእውነት ያልራቀ (Realistic)
ይህ "ሊደረስበት የሚችል" ከሚለው ጋር ተቀራራቢ የሆን መለኪያ ነው። "ሊደረስበት የሚችል" የሚለው የራስን አቅም ማገናዘብን የሚመለከት ሲሆን፣ "ከእውነት ያልራቀ" የሚለው ደግሞ የምንኖርበትን አገር እና አካባቢያዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ ማስገባትን የተመለከተ ነው።
ለምሳሌ:-
አሁን ባለው የአገራችን ሁኔታ፣ የቱንም ያህል የገንዘብ እና የሰው ኃይል አቅም ቢኖረን በኦንላይን የገንዘብ ዝውውር የመላው ዓለም ሰዎች የሚገበያዩበት የግብይት ቢዝነስ ኢትዮጵያ ውስጥ መጀመር አይቻልም። እንዲህ ያለ ግብ አንድ ሰው ቢቀርጽ፣ ከእውነት የራቀ ሆኖ ይገኛል።
5⃣ በጊዜ የተገደበ (Time-bound)
የጊዜ ወሰን ያልተበጀለት ግብ፣ ግብ ሳይሆን ሕልም ነው። "የእኔ ቢዝነስ ወደፊት አንድ ቀን አንድ ሚሊየን ብር ትርፍ ይኖረዋል" ማለት ጥሩ ሃሳብ ሊሆን ይችላል፤ ሆኖም ግብ አይደለም። ይህ የሚሆነው መቼ ነው? የሚለው ወሳኝ ጥያቄ መመለስ ይኖርበታል።
ለምሳሌ:-
"አንድ ሚሊዮን ብር ትርፍ ማግኘት" የሚለው #ሕልም "የሚቀጥለው ሰኔ መጨረሻ አንድ ሚሊዮን ብር ትርፍ ማግኘት" የሚለው ቢጨመርበት በጊዜ የተገደበ ግብ ይሆናል።
✅ ማሳሰብያ
አምስቱን የትክክለኛ ግብ መገለጫዎች ስናስብ መርሳት የሌለብን ነገር፣ አንድ ግብ እውነትም ግብ እንዲባል ከአምስቱ አንዱን ወይም ሁለቱን ቢያሳካ በትክክል ግብ ሊባል አለመቻሉን ነው። ግባችን እውነትም ግብ እንዲባል አምስቱንም የትክክለኛ ግብ መለያዎች ማሟላት ይኖርበታል።
የስብዕና ልህቀት
Join: @Human_intelligence
Join: @Human_intelligence
👍 42❤ 9
አንተ በሕይወትህ ላይ እርምጃ ካልወሰድክ ሕይወት በአንተ ላይ እርምጃ ትወስዳለች!!
በጣም ወሳኝ የሆኑ ግቦችን በግልጽ የማስቀመጥና እነርሱን በየእለቱ የመከለስ ያህል ለስኬት መሠረት የሚሆን ነገር የለም፡፡ ግብ በማስቀመጥና እነርሱን በቋሚነት ውሳኔ ለመስጠት የምታሳልፍበትን ጊዜ ሁሉ ከግምት ውስጥ ማስገባት ታላቅ ሕይወትን ለመምራት ወሳኝ ግብዕት ነው፡፡ ሰዎች እድሜ ዘመናቸውን ስኬታማ ለመሆን ሲያልሙ እና ሲለፉ ይኖራሉ። ሆኖም ግን በወር ውስጥ ለአስር ደቂቃ እንኳን ግባቸውን በጽሁፍ ላይ አስፍረው፣ በማሰብና በማሰላሰል አያሳልፉም፡፡እውነት ነው፤ ብዙ ሰዎች የሕይወታቸውን አቅጣጫ ከመተለም ይልቅ የእረፍት ጊዜያቸውን እንዴትና የት እንደሚያሳልፉ በማሰብ ነው ጊዜያቸውን የሚያጠፉት።
እንዲሁ በዘፈቀደ መኖር ቀላል ነው፡፡ አንተ በሕይወት ላይ እርምጃ ካልወሰድክ ሕይወት በአንተ ላይ እርምጃ ትወስዳለች። ዘወትር ማለዳ ለአምስት ደቂቃ ግቦችህን በመወጠንና በመከለስ ብታሳልፍ ተጽእኖህን በሕይወት ላይ ታሳርፋለህ እንዲሁም ሕይወትህን የምትመራው ለሚደርስብህ ነገር የአጸፋ ምላሽ በመስጠት ሳይሆን አንተው አስቀድመህ በተለምከው መንገድ በመጓዝ ነው፡፡ ግቦችን በማስቀመጥ የተሻሉ አማራጮችን የሚያስገኝልህ ማዕቀፍ ይኖርሃል፡፡ እቅድ ስትነድፍ ከፊት ለፊትህ ስለሚጠብቅህ ነገር እውቀትና ግንዛቤ ይኖራል። የምትፈጽመው ስህተት ይቀንሳል፡፡ በአጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ ነገር ትፈጽማለህ፡፡
«የሚለካ፣ የሚመዘን ነገር ይሻሻላል።» የሚል አባባል አለ። ግብ ማስቀመጥ የምትለካውን ነገር ይሰጥሃል። ግብህ የሰውነት ክብደትህን በ12% መቀነስ ቢሆን የምታስመዘግበውን መሻሻል የምትመዝንበት መለኪያ ይኖርሃል፡፡ ስትለካ ለመሻሻል መሠረት ይኖርሃል። ግቦችህን በግልጽ ስታውቅ የተሻሉ ምርጫዎች ይኖሩሃል። የተሻለ ምርጫ ሲኖርህ የተሻለ ውጤት ታገኛለህ፡፡
ግብን አስቀድመህ በማዘጋጀት በግቡ ውስጥ የሚካተቱትን ነገሮች በዝርዝር በወረቀት ላይ አሰፍራቸው።ግብህን ማቀድና በወረቀት ላይ ማስፈር፣ ህይወትህን በአስገራሚ ነገሮች ይሞላዋል።ይህንን ማርቀቅ በጀመርክበት ቅጽበት፣ የተፈጥሮ ሀይል በወረቀት ላይ የረቀቅውን ወደ እውነት ለመቀየር የራሱን ሚና ይጫወታል። እያንዳንዶቻችን በቀን በአማካይ 50,000 ሀሳቦችን እናስባለን፡፡ በእራፊ ወረቀት ላይ የራስህን ምኞቶችና ግብ በዝርዝር መክተቡ፣ ለጥልቁ አዕምሮህ እነዚህ ከቀሩት 49,999 የበለጠ አስፈላጊ እንደሆኑ የቀይ
ባንዲራ ምልክት ማሳየት እንደማለት ነው፡፡ ያንጊዜም አዕምሮህ ልክ አቅጣጫውን በራዳር እንደተዘጋጀለት ሚሳኤል ለመወንጨፍ፣አሰሳውን ይጀምራል፡፡ ይሄም በራሱ እጅግ አስደናቂ ሳይንሳዊ ሂደት ነው።
ግቦች በውሎህ ላይ የህይወት እስትንፋስን ይተነፍሳሉ፡፡ በአንድ ነጭ ወረቀት ላይ ግቦችህን ማስቀመጥ በራሱ ሕይወትህን ፍጹም ወደሚለውጥ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋግርሃል። ግቦችህን ማስቀመጥ ተራ ለመሆን አለመፍቀድህን መግለጫ ነው። ግቦችህን ማስቀመጥ ጀግንነት ነው፤ ምክንያቱም በውስጥህ ያለውን እምቅ አቅም ለማውጣት ትችላለህና፡፡
✍️ሮቢን ሻርማ
#ሼር በማድረግ ሌሎችን እናስተምር
Join: @Human_Intelligence
Join: @Human_Intelligence
👍 41❤ 4

