TIKVAH-MAGAZINE
رفتن به کانال در Telegram
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። #ኢትዮጵያ ያግኙን +251913134524
نمایش بیشتر2025 سال در اعداد

194 394
مشترکین
-5024 ساعت
-1767 روز
-81830 روز
آرشیو پست ها
ከአስከፊው የሱዳን ጦርነት ጀርባ የውጪ ሀገራት ተሳትፎ ምን ይመስላል?
ሱዳን ሁለቱ ጀነራሎች በሚመሯቸው ጦሮች የተነሳ የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ ከገባችና የበርካቶች ህይወት መቀጠፍ ከጀመረ 31 ወራት ተሻግሯል።
የሱዳንን ጦርነት ካባባሱ ነገሮች አንዱ የውጪ ሃገራት በጦርነቱ እጃቸውን ማስገባት ሲሆን የውጪ ኃይሎች ሁለቱንም ተፋላሚዎች በየጎራው መደገፍ የንጹሐንን ህይወት ስቃይ ውስጥ ከቷል።
እንደ ግብፅና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ያሉ ሃገራት በሱዳን ጦርነት በጉልህ ቢነሱም ከ10 በላይ የአፍሪካ፣ የመካከለኛውን ምስራቅና እስያ ሃገራት በጦርነቱ እጃቸውን እንዳስገቡ ይነገራል።
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ሚና
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቀጣናው ባሉ የልማትም ሆነ የግጭት ዜናዎች ስሟ የማይጠፋው የመሃመድ ቢንዛይዷ ሃገር የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በሱዳን ጉዳይ ስሟ መነሳት ከጀመረ ሰነባብቷል።
ኤምሬቶች ሱዳን በ2009 ከቻድ ጋር የድንበር ግጭት ውስጥ ስትገባ ያሸማገለች ሲሆን ከአልበሽር መነሳት በኋላ ለነበረው የሽግግር ምክር ቤትም ድጋፍ ስታደርግ ነበር።
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መጀመሪያ አካባቢ በግጭቱ ገለልተኛ ነበረች ቢባልም በኋላ ላይ ለፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ድጋፍ ማድረግ መጀመሯ ይነሳል።
በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ በተፈፀሙ ወንጀሎችም በተባባሪነት በጦሩ በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት የተከሰሰችው የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከደቡብ አሜሪካ ጭምር ተዋጊዎችን እያሰለጠነች የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን ትደግፋለች ተብላ ትከሰሳለች።
የግብፅ እና ሳዑዲ አረቢያ ሚና
ግብፅ በተደጋጋሚ ለሱዳን ጦር ድጋፍ እንደምታደርግ ሲነገር በተደጋጋሚም ከፍተኛ ባለስልጣናቷን ወደ ሱዳን እየላከችና የጦሩን መሪዎች በካይሮ እያስተናገደች ትገኛለች። ሌላኛዋ ሃገር ሳዑዲ አረቢያ ለጦሩ የፋይናንስና የሎጅስቲክስ ድጋፍ እንደምታደርግ ይታመናል
የፈጥኖ ደራሽ ኃይል መሪ ጀነራል ዳጋሎ ግብፅ ለጦሩ የጦር መሳሪያ ድጋፍ ታደርጋለች ብለው ሲከሱ ቆይተዋል።
ሀገራቱ በየዘርፋቸው ተፋላሚዎችን ከመደገፍ በተጨማሪ በሱዳን ባለው የወርቅ ንግድ እጅጉን አትራፊ እየሆኑ መጥተዋል።
ለራሳቸው ጦርነት ውስጥ ያሉትና የሰነበቱት እንደ ሩሲያና ኢራን ያሉ ሃገራትም በየፊናቸው የድሮንና ወታደራዊ ድጋፎችን እያደረጉ ይገኛሉ።
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ግብፅና ሩሲያ ኦማር አል በሽር ከስልጣን ሲወገዱ አራቱም ለሱዳን ጦር ድጋፍ ነበራቸው።
ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ውጊያ ውስጥ ብትሆንም በጦርነቱ ተሳታፊ እየሆነች ሲሆን አሜሪካ ሩሲያ የራሷን የፖለቲካ አላማ ለማሳካት ከሁለቱም ተፋላሚዎች ጋር ትሰራለች ስትል ትከሳታለች።
በቅርቡም የሩሲያው ዋግነር ለፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ የሚሳኤል ድጋፍ አድርጓል የሚሉ ሪፖርቶች ወጥተው ነበር።
ሁሉም በጦርነቱ ተሳታፊ የሆነ አካል የራሱ ጥቅሞች ያሉት ሲሆን የወርቅ ንግድ አለፍ ሲልም ከሰሃራ በታች ባለው አፍሪካና በአፍሪካ ቀንድ ተፅዕኗቸውን ለማሳደግ ተሳታፊ እንደሆኑ ይታመናል።
Source: CNN, THE CONVERSATION , FPRI
@TikvahethMagazine
❤ 79😢 25🤔 6💔 4👍 2👎 2👏 2
Photo unavailableShow in Telegram
ይዘት ፈጣሪው ኤ.አይ (Generative AI? ) ምንድን ነው ?
ባለፉት 10 ዓመታት የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ድንቅ የፈጠራ ውጤት ሆኖ የሚታይ ቢሆንም በዚህ ልክ ለመስፋፋቱ ምክንያት በራሱ ይዘት መፍጠር የሚችለው ኤ.አይ (Generative AI) ይበልጡኑ እ.ኢ.አ 2022 የቻት ጂፒቲ መተዋወቅ ጋር የተያያዘ ነው።
ለመሆኑ Generative AI ምንድን ነው ?
ከዚህ ቀደም ሰዎች ኢንተርኔት ላይ የሚፈልጉት ነገር ለማግኘት ኢንተርኔትን በማሰስ (Web Browsing) ነው ይህም ይህም በፊት ያሉ ውጤቶችንና መረጃዎችን የምናገኝበት መንገድ ነው።
Generative AI የምንለው ከዚህ ይለያል። ይህም ቀደም ያሉ ውጤቶችን ማምጣት ሳይሆን በሰዎች ጥያቄ ላይ መሰረት አድርጎ የተሰናሰለ አዲስ መልስ የሚሰጥ ነው።
Generative AI መሰረት ያደረገው ምን ላይ ነው ?
ሰዎች ለሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት መሰረት የሚሆነው ቀድሞ ማሽኑን ለማሰልጠን የምንጠቀምበት ዳታ (የመረጃዎች ጥርቅም) ነው። ለዚህም በርካታ መረጃዎች ያስፈልጋሉ።
እዚህ ላይ ማወቅ ያለብን የምናገኘው መልስ በዋነኝነት በሰለጠነበት የመረጃ ክምችት ላይ የተወሰነ በመሆኑ ሊሳሳትና ትክክለኛ መልስ ሊሰጠን እንደሚችል ነው።
Generative AI ምን መስራት ይችላል ?
ምስሎችን መፍጠር፣ ሙዚቃ ማቀናበር፣ ቪዲዮ መስራት፣ ጹሑፍ መጽሐፍ፣ ኮድ መጻፍ እና መሰል ተግባራትን ማከናወን ይችላል።
#IsItAI
#Concepthub #InterNews #EU
via @concepthubeth
- Tikvah Magazine | @TikvahethMagazine
❤ 47👍 1👎 1
Photo unavailableShow in Telegram
በአፍሪካ በሚሸጡ የህፃናት ምግቦች ላይ ስኳር እየጨመረ የሚሸጠው የስዊዘርላንድ ድርጅት
"Nestle" የተሰኘው የስዊዘርላንድ የምግብ አምራች ወደ አፍሪካ በሚላኩ የህፃናት ምግብ ላይ ስኳር እየጨመረ እንደሚልክ የምርመራ ሪፖርት አመላክቷል።
ድርጅቱ ወደ ሃብታም ሃገሮች ሲልክ የተቀመጠውን የጤና መመዘኛ በአፍሪካ እየተገበረ እንዳልሆነ ነው ክስ የቀረበበት።
"Public Eye" የተሰኘው የስዊዘርላንድ የሰብዓዊ መብት ተቋም ወደ አፍሪካ የሚላኩ የህፃናት የምግብ ምርቶች ላይ ድርጅቱ በአውሮፓ ከሚሸጡት በተጨማሪነት ስኳር እየጨመረ እየሸጠ እንደሆነ አጋልጧል።
የሰብዓዊ መብት ተቋሙ በ20 የአፍሪካ ሀገራት የሚሸጡ 100 የህፃናት ምግቦችን ወስዶ በላብራቶሪ ምርመራ 90 በመቶዎቹ የተጨመረ ስኳር እንደተገኘባቸው አስታውቋል።
በምርመራው በአማካይ ከ6 -7.5 ግራም ስኳር የተጨመረባቸው ምርቶች ሲገኙ ትልቁ የተገኘው በኬንያ በተሸጠ ምርት ላይ ነው።
የዓለም ጤና ድርጅት በ2022 እ.ኤ.አ ህፃናትን በለጋነታቸው ለስኳር ምርቶች ማጋለጥ ለከፋ በሽታ እንደሚያጋልጥ መመሪያ ቢያወጣም ይህ ድርጅት ግን መመሪያውን ጥሶ ወደ አፍሪካ በሚላኩ የህፃናት ምግቦች ላይ ስኳር እየጨመረ መሸጡን ነው ሪፖርቱ ያስቀመጠው።
ድርጅቱ የሚያመርተው የህፃናት ምግብ በስዊዘርላንድ ሲሸጥ ምንም ስኳር የሌለው ሲሆን በሌሎች የአውሮፓ ሃገራት ሲሸጥም እስከ 6 ወር ላሉ ህፃናት በሚሸጠው ምግብ ላይ ምንም ስኳር የለውም።
19 የአፍሪካ የሲቪል ማኅበረሰብ ተቋማትም ድርጅቱ ወደ አፍሪካ ስኳር ያለባቸውን የህፃናት ምግብ መላክ እንዲያቆም በደብዳቤ ጠይቀዋል።
በደብዳቤው "ለስዊዝና ለአውሮፓ ህፃናት የተጨመረ ስኳር ተገቢ ካልሆነ ለአፍሪካ ህፃናትም ተገቢ አይደለም" ሲሉ ጠይቀዋል።
አምራቹ ድርጅት ግን የወጣው ሪፖርት የተሳሳተ ነው ሲል በሁሉም ሃገራት ተመሳሳይ ምርት እንደሚልክና አድሎ እንደማይፈፅም ገልጿል።
ድርጅቱ ስኳር ያለባቸውና የሌለባቸውን ምርቶች በአውሮፓም ሆነ በአፍሪካ በተመሳሳይ ዋጋ እንደሚያቀርብ ገልፆ 97% በሚሆነው ገበያው ስኳር የሌለባቸውን ምርቶች እያቀረበ መሆኑን ገልጿል።
የአለም ጤና ድርጅት ከ1990 ወዲህ ከአምስት አመት በታች የሆኑ ህፃናት ከመጠን በላይ ውፍረት በአፍሪካ በእጥፍ እንደጨመረና ስጋት እየሆነ መምጣቱን መግለፁ ይታወሳል።
መረጃው የአልጄዚራ ነው።
@TikvahethMagazine
🤔 61🤬 43❤ 40😢 18💔 9👍 8🔥 2
Photo unavailableShow in Telegram
አፍሪካ የራሷ የስትሮክ መመሪያ ለምን ያስፈልጋታል?
የስትሮክ በሽታ አዕምሮ በቂ የሆነ ደም ሳያገኝ ሲቀር የሚከሰት በሽታ ሲሆን በሽታው ከጊዜ ወደ ጊዜ በአፍሪካ እየተስፋፋ መጥቶ አሁን ላይ በአህጉሪቱ ለሞት እና ለአካል ጉዳት መንስኤ ከሆኑ በሽታዎች አንዱ ሆኗል።
በየዓመቱ በበሽታው ከ100,000 ሰዎች ውስጥ 316 #አዳዲስ ተጠቂዎች ሲመዘገቡ አሁን ላይ ከ100,000 ሰዎች ደግሞ 1460 ያህሉ በበሽታው በአፍሪካ ተይዘው ይገኛሉ።
ምንም እንኳን ስትሮክ በዚህ ልክ አሳሳቢ ቢሆንም በአኅጉር ደረጃ ስትሮክን ለመቆጣጠር የተቀመጠ ማዕቀፍ ለም። በአህጉሪቱም ብቸኛዋ በብሔራዊ ደረጃ የተቀመጠ መመሪያ ያላት ሀገር ደቡብ አፍሪካ ነች።
ባደጉት የሰሜን አሜሪካና አውሮፓ ሃገራት ስትሮክን የተመለከቱ መመሪያዎች ሲኖሩ እነዚህ መመሪያዎችንም በየጊዜው ማሻሻያዎች ይደረግባቸዋል። የአፍሪካ ሀገራትም በእነዚህ መመሪያዎች ላይ የተመሰረቱና የራሳቸው መመሪያ የሌላቸው ናቸው።
ታዲያ መመሪያው ለምን ያስፈልጋል?
ካደጉት ሀገራት የተወሰዱ መመሪያዎች አፍሪካ ካላት ኃብትና የጤና ሥርዓት አንፃር ተስማሚ እና ውጤታማ አይደሉም። አፍሪካ የራሷን የጤና ስርዓት ማዕከል ያደረገ መመሪያ እንደሚያስፈልጋት ይታመናል።
በአፍሪካ በርካታ ሆስፒታሎች የትኛው የስትሮክ ዓይነት እንደሆነ ለመለየት የሚያስችል መሳሪያ እንኳን የላቸውም።
በአፍሪካ በርካታ የህዝብ ቁጥር ያላት ናይጄሪያ በ2021 እ.ኤ.አ 209 "CT scanners" የነበራት ሲሆን ለንፅፅር በጀርመን በወቅቱ ከ3000 በላይ መሳሪያዎች ነበሩ።
በአፍሪካ በ100,000 ሰዎች 0.12 ኒውሮሎጂስቶች ( የነርቭና የአዕምሮ ሃኪሞች) እንዳሉ ሲገለጽ፥ እንደ ጂቡቲ፣ ኤርትራ፣ ጊኒ ቢሳው፣ ሌሴቶ፣ ላይቤሪያና ደቡብ ሱዳን ደግሞ በዘርፉ የተማረ አንድም ሰው የላቸውም።
በአንዳንድ የአፍሪካ ኃገራት ምጣኔው 1 ኒውሮሎጂስት ለ500,000 ሰው ይደርሳል። በአውሮፓ በንፅፅር ከተመለከትን ደግሞ በ100,000 ሰው 8.45 ይሆናል።
በአፍሪካ በርካቶች የስትሮክ ተጋላጭነትን በሚጨምሩ በሽታዎች ሲያዙ ለአብነትም 28.5% የሚሆነው ህዝብ ከፍተኛ በሆነ የደም ግፊት የተጠቃ ነው። ቁጥሩ ቀላል ያልሆነ ሰውም በስኳር በሽታ ተይዟል።
አፍሪካ ምን አይነት የስትሮክ መመሪያ ያስፈልጋታል?
አፍሪካ የራሷን ኃብት ባገናዘበ መልኩ የስትሮክ መመሪያ ሊኖራት እና በዘርፉ የሰለጠኑ የጤና ባለሙያዎዎች ያስፈልጓታል።
በታንዛኒያ ተሞክሮ ውጤታማ የሆነው የቴሌሜዲስን መተግበርም በአማራጭነት ይቀመጣል። ይህም በገጠር የጤና ማዕከላትና በስትሮክ ማዕከላት መካከል ትስስር እንዲኖር ያግዛል።
መመሪያዎቹ በየጊዜው የሚደረግን የደም ግፊት ምርመራን የሚያበረታቱና መከላከልን መሰረት ያደረጉ ሊሆኑ ይገባል።
ለህብረተሰቡ በቂ ግንዛቤ መስጠትና ስትሮክን ለመከታተል የሚያስችሉ ቀላል የጤና መተግበሪያዎች መሰራትም ሌላኛው መንገድ ነው።
መመሪያዎቹ በተጨማሪ በገጠርና በከተማው መካከል ያለውን ክፍተት በማጥበብ ደረጃ ሚናቸው የጎላ ሊሆን ይገባል።
የጋራ የሆነ የስትሮክ መመሪያ በአፍሪካ ለማምጣት የጋራ አመራር የሚጠይቅ ሲሆን በዘርፉ ያሉ የጤና ባለሙያዎችም ለዚህ ግንባር ቀደም መሪ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
ይህ ጹሑፍ ፅሁፉ ከTHE CONVERSATION ድህረገጽ ላይ የተወሰደ ነው።
@TikvahethMagazine
❤ 54👍 3👎 2
Photo unavailableShow in Telegram
🌟 ታማኝነት
🌟 ጥራት
🌟 ማሕበረሰብን መገንባት የሚታወቀው የናተው አያት አሁን ደሞ
✨ በካሳንቺስ
✨በልደታ
✨በሴሚሲ ሚካኤል
✨በቤልየር
✨በመሪ
✨በአያት
⚡️በ ካሬ 89,815 ብር
⚡️አፓርትመንት እና የ ንግድ ሱቆችን በ477,000 ብር ቅድመ ክፍያ ምንም አይነት የዋጋ ጭማሪ ሣይደረግቦት የራስዎ ያርጉ!
💥 ለበለጠ መረጃ 2519-77-63-06-93 በቀጥታ @ayat121921 በቴሌግራም በዋትሳፕ ይደውሉ
❤ 11👍 1
የትምህርት አዋኪ ጉዳዮችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው ረቂቅ ደንብ በውስጡ ምን ይዟል?
በመላ ሃገሪቱ ባሉ ከቅድመ አንደኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ባሉ የመንግስትና መንግስታዊ ባልሆኑ ትምህርት ቤቶችና አካባቢው ተፈፃሚ ይሆናል የተባለው ይህ ረቂቅ ደንብ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰብሳቢነት የሚመራ ግብረ-ኃይል ጭምር እንዲቋቋም የሚያስችል አሰራር ዘርግቷል።
በዚህ ረቂቅ ደንብ ትምህርት ቤቶችና አካባቢው ተብለው የተለዩት ከትምህርት ቤቱ እስከ 500 ሜትር ባለው ርቀት ውሰሰጥ ያሉ አከባቢዎች ናቸው።
ደንቡን ለማውጣት በትምህርት ተቋማትና አካባቢ የትምህርት አዋኪ ተግባራት በመስፋፋታቸው፤ ከጊዜ ወደ ጊዜ የተማሪዎች ለአደንዛዥ ዕፆችና አደገኛ መድኃኒቶች ተጋላጭነታቸው እየሰፋ መሄዱ በምክንያትነት ተቀምጧል።
በዚህ ደንብ መሰረት በትምህርት ቤቶችና አካባቢው የተከለከሉ ተግባራት ምን ምን ናቸው ?
- ፊልም ማጫዎቻ ቤቶች፣ ፕሌይ ስቴሽን ቤቶች፣ "ዲ.ኤስ.ቲቪ" ቤቶች፤ ከረንቡላ፣ ፑል፣
ጆተኒ፣ ቢንጎ እና የስፖርት ቁማር መጫወቻ ቤቶች፤
- የአልኮል መሸጫ እና ማከፋፈያ ቤቶች፤ የሰውነት መታሻ ቤቶችና የእንግዳ ማረፊያ ቤቶች፤
- የሲጋራ መሸጫ ሱቆች፣ ሺሻ ቤቶች፣ ጫት መሸጫና መቃሚያ ቤቶች፤ የናርኮቲክ እና ሳይኮትሮፒክ ዝሪያ ያላቸው ህገወጥ መድሃኒቶችና ሱስ የሚያስዙ ዕፆች [ይዞ መገኘት]፤
- በመማር ማስተማሩ ላይ ተፅዕኖ የሚያደርጉ ድምፅ፣ ጫጫታ፣ መጥፎ ጠረን የሚያወጡ፣ የትራፊክ ፍሰት፣ ገበያ፣ ፋብሪካ፣ ወፍጮ ቤቶች፣ ብረታ-ብረት ብየዳ ቤቶች፣ እንጨት መሰንጠቂያ ቤቶች፣ ጋራዥ ቤቶች፣ አውቶብስ ፌርማታዎች እና የጣውላ ውጤት ማምረቻ ድርጅቶችን ያጠቃልላል።
እነዚህ ተግባራት “ትምህርት ቤትና አካባቢ” ተብለው በተለዩ ማለትም የትምህርት ቤት ግቢውን እና በሁሉም አቅጣጫ ከአጥሩ እስከ 500 ሜትር ርቀት ባለው ቦታ ላይ መፈጸም ይከለክላል።
ይህንን ተግባር ማን በበላይነት ይመራዋል ?
በዚህ ደንብ መሠረት በትምህርት ቤቶችና አካባቢ የትምህርት አዋኪ ነገሮችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በፌደራል ደረጃ “ተከላካይ ግብረ-ኃይል” እንደሚቋቋም ይገልጻል።
ይህ ግብረ-ኃይል ም/ጠ/ሚኒስትሩ በሰብሳቢነት የትምህርት ሚኒስትሩ በም/ሰብሳቢነት የሚመራ ሲሆን ሌሎች ተጨማሪ 6 ሚኒስትሮችን በአባልነት ያካተተ ነው።
በተጨማሪም የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር፤ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ሰብሳቢ፤ የመምህራን ማህበር ፕሬዚዳንት፤ የሲቪክ ማህበራት ፕሬዝዳንት፤ የተማሪዎች ወላጆች ህብረት ፕሬዝዳንትን በአባልነት ያካተተ ነው።
ተከላካይ ግብረ-ኃይሉ ይሄንኑ ተግባር ወደ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የማውረድ ኃላፊነት ተሰጥቶታል።
በትምህርት ቤትና አካባቢ የተከለከሉትን ተግባራት ፈፅሞ የተገኘ ምን ይቀጣል ?
ህጉን ለተላለፉ፥ በቅጣት ደረጃ ከ10,000 ብር - 150,000 ብር የገንዘብ ቅጣት በረቂቅ ደንቡ ተቀምጧል። ለምሳሌ፦
- የጫት መሸጫና መቃሚያ የከፈተ 50,000 ብር እና ቦታውን መዝጋት፤
- ማንኛውንም ዓይነት ቁማር ቤት የከፈተ 150,000 ብር እና ቁማር ቤቱን መዝጋት፤
- የሰውነት መታሻ/Massage House ቤት የከፈተ 150,000 ብር እና ማሳጅ ቤቱን መዝጋት የሚሉት ይጠቀሳሉ።
ቀድሞ በተከፈቱት ላይ ደንቡ ተግባራዊ ይሆናል ?
ይህ ደንብ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት ትክክለኛውን ርቀት ሳይጠብቁ በትምህርት ቤትና አካባቢ የተከፈቱ የትምህርት አዋኪ ጉዳዮች ላይ ደንቡ ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን የማስተካከያ ጊዜን እና የማካካሻ ጉዳይን በተመለከተ በዝርዝር መመሪያ የሚወሰን
ይሆናል ሲል አስቀምጧል።
በተጨማሪም በረቂቅ ደንቡ ማንኛውም የንግድ ፈቃድ ሰጭ አካል ፈቃዱን ለንግድ ፈቀድ ጠያቂው ከመስጠቱ በፊት የነጋዴውን የስራ ቦታ ከትምህርት ቤት ያለውን ርቀት በምልከታ ማረጋገጥ አለበት ይላል።
በደንቡ ላይ ምክረ ሃሳብ ለመስጠት https://forms.gle/HisAZoyTpmo1ZFCA6 መጠቀም ይቻላል።
#TikvahEthiopia
@TikvahethMagazine
❤ 109👏 38🤔 6👍 5👎 3
44 ሚሊየን በላይ ኢትዮጵያውያን የንጹህ የመጠጥ ውኃ አቅርቦት እንደሌላቸው ተገለጸ።
"World Population Review" በ2025 ኢትዮጵያ ዝቅተኛ የመጠጥ ውሃ ጥራት ካላቸው ሃገራት መካከል አንዷ ነች ብሏል። በዚህም ለኢትዮጵያ 19.2/100 ውጤት ተሰጥቷታል።
ንፁህ ያልሆነን ውሃ ከሚጠጡ 100,000 ሰዎች ውስጥ ምን ያህሉ ዕድሜውን ከውሃው ጋር በተያያዘ እንደሚያጣ መሰረት በማድረግ መለኪያው የተሰራ ሲሆን እንደ ጀርመን፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ጣልያንና ግሪክ ያሉ ሃገራት 100 ተሰጥቷቸው፥ ዜጎቻቸው ንፁህ ውሃ የሚጠጡባቸው ሀገራት ተብለዋል።
በዝርዝሩ ዝቅተኛው ነጥብ የተሰጣቸው 10 ሃገራት ሙሉ ለሙሉ ከአኅጉራችን አፍሪካ ናቸው።
ኢትዮጵያ አሁንም 44 ሚሊየን በላይ ዜጎቿ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት እንደሌላቸው በዝርዝሩ ሲመላከት ይህም 42.7% ህዝቧን መሆኑ ተገልጿል።
በተጨማሪ የንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ባለመኖሩ ሰዎች ከመጠጥ ውሃ ጋር በተያያዘ ለሚፈጠሩ በሽታዎች የሚጋለጡባትም ነች ተብሏል።
44 ሚሊየን ዜጎቿ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት አያገኙባትም የተባለችው ኢትዮጵያ ከናይጄሪያ 60.1 ሚሊየን ህዝብ በመቀጠልም ብዙ ሰዎች ንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት የማያገኙባት አፍሪካዊ ሀገር ነች።
@TikvahethMagazine
😢 93❤ 41👍 7🙏 3🤔 1🤝 1
44 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን የንጹህ የመጠጥ ውኃ አቅርቦት እንደሌላቸው ተገለጸ።
"World Population Review" በ2025 ኢትዮጵያ ዝቅተኛ የመጠጥ ውሃ ጥራት ካላቸው ሃገራት መካከል አንዷ ነች ብሏል። በዚህም ለኢትዮጵያ 19.2/100 ውጤት ተሰጥቷታል።
ንፁህ ያልሆነን ውሃ ከሚጠጡ 100,000 ሰዎች ውስጥ ምን ያህሉ ዕድሜውን ከውሃው ጋር በተያያዘ እንደሚያጣ መሰረት በማድረግ መለኪያው የተሰራ ሲሆን እንደ ጀርመን፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ጣልያንና ግሪክ ያሉ ሃገራት 100 ተሰጥቷቸው፥ ዜጎቻቸው ንፁህ ውሃ የሚጠጡባቸው ሀገራት ተብለዋል።
በዝርዝሩ ዝቅተኛው ነጥብ የተሰጣቸው 10 ሃገራት ሙሉ ለሙሉ ከአኅጉራችን አፍሪካ ናቸው።
ኢትዮጵያ አሁንም 44 ሚሊየን ዜጎቿ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት እንደሌላቸው በዝርዝሩ ሲመላከት ይህም 42.7% ህዝቧን መሆኑ ተገልጿል።
በተጨማሪ የንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ባለመኖሩ ሰዎች ከመጠጥ ውሃ ጋር በተያያዘ ለሚፈጠሩ በሽታዎች የሚጋለጡባትም ነች ተብሏል።
44 ሚሊየን ዜጎቿ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት አያገኙባትም የተባለችው ኢትዮጵያ ከናይጄሪያ 60.1 ሚሊየን ህዝብ በመቀጠልም ብዙ ሰዎች ንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት የማያገኙባት አፍሪካዊ ሀገር ነች።
@TikvahethMagazine
Photo unavailableShow in Telegram
#Update
⚫ ሜታ በአውስትራሊያ የሚገኙ ከ16 ዓመት በታች ያሉ ህፃናት አካውንትን መዝጋት ሊጀምር ነው።
በአውስትራሊያ የሚገኙ ከ13-15 ዓመት ያሉ ህፃናት በመልዕክት፣ በኢሜይል እና በመተግበሪያዎቹ በኩል የኢንስታግራም፣ የፌስቡክ እና ትሬድስ አካውንታቸው ከመጪው ታህሳስ 4 ጀምሮ መዘጋት እንደሚጀምር አሳውቋል።
አውስትራሊያ ከ16 ዓመት በታች ያሉ ህፃናትን ከማህበራዊ ሚዲያ የሚያግደውን ህግ ከታህሳስ 10 ጀምራ መተግበር የምትጀምር ሲሆን ሜታ ህጉ ከመተግበሩ በፊት የህፃናቱን አካውንት መዝጋት እንደሚጀምር ገልጿል።
በአውስትራሊያ ከ13-15 ዕድሜ ክልል ውስጥ 150,000 የፌስቡክ እና 350,000 የኢንስታግራም ተጠቃሚዎች አሉ ሲባል ሜታ ከታህሳስ 4 በኋላም ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናት በሜታ ስር ያሉ የማህበራዊ ሚዲያዎችን አካውንት መክፈት እንደማይችሉም ገልጿል።
ሜታ የማኅበራዊ ሚዲያዎቹን የሚጠቀሙ ህፃናት ዕድሜያችን ደርሷል ብለው ካሰቡ መታወቂያ ማቅረብ አለባቸው ብሏል።
አውስትራሊያ ያወጣችውን ህግ የሚጥሱ የማህበራዊ ሚዲያዎችን 50 ሚሊየን የአውስትራሊያ ዶላር እንደምትቀጣም ማስታወቋ ይታወሳል።
መረጃው የቢቢሲ ነው።
@TikvahethMagazine
❤ 45👍 10👏 5👎 1😢 1
Photo unavailableShow in Telegram
አዋሽ ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ አ.ማ. ፈቃድ አገኘ።
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ለአዋሽ ካፒታል አ.ማ. የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪነት ፈቃድ ሰጥቷል። ፈቃዱም ድርጅቱ በባንክ ቡድን ውስጥ በሆነ የኢንቨስትመንት ባንክ ዘርፍ እንዲሠራ ያስችለዋል ተብሏል።
በሀገሪቱ ውስጥ ያሉት የተፈቀደላቸው የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ጠቅላላ ቁጥር ወደ አስራ ሦስት (13) እንዲሁም የኢንቨስትመንት ባንኮችን ጠቅላላ ቁጥር ወደ አራት (4) ከፍ አድርጎታል።
@TikvahethMagazine
👍 18❤ 11🕊 3
Photo unavailableShow in Telegram
‼️ ይፍጠኑ
‼️ በመሀል ሳር ቤት ቫቲካን ኢምባሲ አካባቢ ‼️
# ቴምር ሪልስቴት ከ8 በላይ ሳይቶችን ጥንቅቅ አድርገን አስረክበን አሁን ደግሞ ሳርቤት ቫቲካን ኢምባሲ አካባቢ ለሽያጭ ያወጣናቸው አፓርትመንቶች
➤ 100% ለሚከፍሉ 35% ቅናሽ
👉 ባለ 2 መኝታ = 81ካሬ = 6ሚሊዮን
👉 ባለ 2 መኝታ = 106ካሬ = 7.9ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 139ካሬ = 10.3ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 152ካሬ = 11.3ሚሊዮን
➤ በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ)
👉 81ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 9.3ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (1.8ሚሊዮን)
👉 106ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 12.1ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (2.4ሚሊዮን)
👉 139ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 15.9ሚሊዮን
ቅድመ ክፍያ = 20% (3.1ሚሊዮን)
⩩ ቀሪውን 80%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት።
⩩ 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፤ ከከፈሉት ላይ ከ15 -25% ቅናሽ አዘጋጅተናል።
ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን
☎️+251980782850
❤ 21
Photo unavailableShow in Telegram
በአሜሪካ የተፈቀደው የኤች አይ ቪ መከላከያ በ2 የአፍሪካ ሀገራት በጥቅም ላይ ሊውል ነው።
የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ቢሮ "Gilead sciences" በተሰኘው የመድኃኒት አምራች የበለፀገውና እራሷ አሜሪካ ከአምስት ወራት በፊት ፈቃድ የሰጠችው "lanacapavir" የተሰኘውን የኤች አይ ቪ መከላከያ ክትባት እስዋቲኒ እና ዛምቢያ መውሰዳቸውን ገልጿል።
ሁለቱ ሀገራት በዓመት ሁለት ጊዜ በመውሰድ ከኤች አይ ቪ ይከላከላል የተባለውን ክትባት 500 ዶዝ መውሰዳቸውን ነው አሜሪካ ያስታወቀችው።
ኤች አይ ቪን ጨምሮ እንደ ቲቢና ወባ ያሉ በሽታዎችን ለመዋጋት ድጋፍ የሚያደርገው ግሎባል ፈንድ ከአሜሪካ ውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤትና ከአምራቹ ጋር በመሆን በ2028 ክትባቱን በብዛት በአፍሪካ በሚገኙና በርካታ ተጠቂዎች ባሉባቸው ሀገራት ቢያንስ 2 ሚሊየን ዶዞችን ለማዳረስ እየሰራ ስለመሆኑም ተገልጿል።
ለሁለቱ ሀገራት የሚሰጡት 500 ዶዞች ያለ ምንም ትርፍ የወጣባቸውን ወጪ ብቻ በመሸፈን የሚሰጡ መሆኑ ሲገለፅ፥ አምራቹ ሀገራት ፈቃድ ከሰጡ የመከላከያ መድኃኒቱን ለመላክ የሚያስችል አቅርቦት እንዳለ ገልጿል።
በአሜሪካና በአለም ጤና ድርጅት ፈቃድ የተሰጠው መድኃኒቱ በአፍሪካ በደቡብ አፍሪካና ዛምቢያ ፈቃድ ሲሰጠው አምራቹ ድርጅት በኬንያ፣ ሩዋንዳና ኡጋንዳ እንደዚሁም ሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ፈቃድ እንዲሰጠው ጠይቋል።
አክሎም መድኃኒቱን ለማዳረስ ቅድሚያ የሚሰጣቸው 70% የሚሆኑ የዓለም የኤድስ ተጠቂዎች ያሉባቸውን 18 ሀገራት እንደሆነም ገልጿል።
ዘገባው ከNPR የተወሰደ ነው።
@TikvahethMagazine
❤ 118👏 19🤬 10👎 6👍 5🤔 2
በሊቱዌኒያ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ከውጪ በመጡ ተማሪዎች ላይ ድንገተኛ ፍተሻ ተጀመረ
በሊቱዌኒያ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ሳይነገራቸው ዶርማቸውና መማሪያ ክፍሎች ድረስ ተገብቶ ፍተሻዎች በመደረጉ ቅሬታ ፈጥሯል።
ፍተሻው በሀገሪቱ የስደተኞች ጉዳይ መ/ቤት የተደረገ ሲሆን ዩኒቨርሲቲ መግባትን ወደ አውሮፓ ህብረት ሀገራት የሥራ መግቢያ በር ምክንያት አድርገው የሚጠቀሙ የውጪ ሃገር ተማሪዎችን ለመያዝ ያለመ ነው ተብሏል።
ለፍተሻ የገቡ ሰዎች ከአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት ውጪ የመጡ ሰዎችን የመኖሪያ ፈቃድ ቪዲዮ እየቀረጹ ሲጠይቁ ነበር ሲባል የመማር ማስተማሩን ያወከና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ራስ ገዝነት የሚጥስ ነው ተብሏል።
የስደተኞች መስሪያ ቤቱ አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች በር ለመክፈት ፈቃደኛ እንዳልነበሩና ፈታሾች ለቀው እንዲወጡ እንደነገሯቸው ገልፆ እነዚህ ተቋማት ከእኛ ምን እንደሚደብቁና ለምን እንደሚፈሩ መጠየቅ አለብን ብሏል።
ቢሮው ተማሪዎቹ እውን ለትምህርት ነው ያሉት ወይስ ወይስ ወደ ሌሎች የአውሮፓ ሀገራት ስራ ለመፈለግ ነው የሚለው መታወቅ አለበት ብሏል።
አክሎም፥ ምንም እንኳን የውጪ ሃገር ተማሪዎች በክፍል ውስጥ መገኘት ግዴታቸው ቢሆንም በአንዳንድ ፍተሻዎች ጭራሽ አንዳቸውም አልተገኙም ነው ያለው።
ሊቱዌኒያ በአሁኑ ጊዜ ከ10,000 በላይ ጊዜያዊ የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ተማሪዎችን እያስተናገደች ትገኛለች።
ዘገባው የሊቱዌኒያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ነው።
@TikvahethMagazine
❤ 60💔 7👍 1🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
የኤ.አይ (AI) ክህሎትና እውቀት መቼ ያስፈልገናል ? . . . አሁን ያስፈልገናል!
ኤ.አይን መሰረት ያደረጉ ሀሰተኛ መረጃዎች ሥርጭት በሀገራችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከፍተኛ ሁኔታ በመሰራጨት ላይ ይገኛል፡፡
ከዚህ ቀደም በጹሐፍ ወይም ፎቶ በማቀናበር ይለቀቁ የነበሩ ሀሰተኛ መረጃዎች አሁን ላይ በቀላሉ ጹሑፍም ሆነ ተለጣፊ ምስል( Picture ) ወይም ተንቀሳቃሽ ምስል( Video ) የታገዘ ለማድረግ ቀላል ሁኔታዎች ስለተመቻቹ ሥርጭቱንና መጠኑን ጨምሮታል፡፡
በኤ.አይ የሚፈጠሩ ይዘቶች ለዕይታ ታሳቢ እና አጓጊ ሆነው ስለሚፈጠሩም በቀላሉ ሰዎች ጋር የመድረስ እና የማሳመን አቅማቸው ከፍተኛ ነው፡፡
እንዳንዶቹን ይዘቶች መለየት እስከሚከብድ ድረስ ለፍጹም ምስስል የቀረቡ ሆነው ይቀርባሉ፡፡ የኤ.አይ (AI) ክህሎትና እውቀት አሁን ያስፈልገናል ስንል ይህንን ለመለየት አቅም መፍጠር ግድ ስለሚል ጭምር ነው።
በአንጻሩ፥ ኤ.አይን ለሥራችን እንዲሁም ለመልካም ነገር ለመጠቀም ትክክለኛውን አጠቃቀም መረዳት ያስፈልጋል። ለዚህም አስፈላጊውን ክህሎትና እውቀት ማዳበር ያስፈልጋል።
#IsItAI
#Concepthub #InterNews #EU
Via @Concepthubeth
@TikvahethMagazine
❤ 27👏 14👍 3👎 1
Photo unavailableShow in Telegram
"በ2025 የመጀመሪያ አጋማሽ በሞያሌ በኩል ከወጡ ስደተኞች መካከል 74 በመቶ የሚሆኑት መነሻቸው ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ነው" - አይ.ኦ.ኤም
ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት በምስራቅ - ደቡባዊ (Eastern Southern Africa Route) አፍሪካ የስደተኞች መስመር ላይ በርካቶች አሁንም ህይወታቸውን ለአደጋ ሰጥተው እየሄዱ መሆኑን ባወጣው ሪፖርት ገልጿል።
የምስራቅ - ደቡባዊ መንገድ ኢትዮጵያን፣ ኬንያን እና ሶማሊያን ከታንዛኒያ፣ ማላዊ፣ ሞዛምቢክ ፣ ዛምቢያና ዚምባቡዌ የሚያገናኝ መስመር ሲሆን በዚህ መንገድ የሚሄዱ ስደተኞች የመጨረሻ መዳረሻቸውም ደቡብ አፍሪካ ነው።
ከጥር - ሰኔ 2025 ባለው ጊዜ ከኢትዮጵያ በሞያሌ በኩል የወጡ የ4900 የስደተኞች እንቅስቃሴ የታየ ሲሆን ይህም ከ2024 አንፃር በ35 በመቶ ቅናሽ ያሳየ ነው ተብሏል።
ከኢትዮጵያ በሞያሌ በኩል ከሚወጡ ስደተኞች መካከል 17% ያህሉ ህፃናት እንደሆኑ በሪፖርቱ ሲገለፅ በጾታ ስብጥርም 74 በመቶ የሚሆኑት ወንዶች፤ 9 በመቶ ሴቶች ናቸው።
በሪፖርቱ እንደተጠቀሰው 85 በመቶዎቹ ዕድሜያቸው ከ30 ዓመት በታች ሲሆን በዚህ መንገድ የሚደረጉ የስደት ጉዞዎች መነሻ ምክንያታቸው 94 በመቶ ኢኮኖሚያዊ ነው ተብሏል።
74 በመቶ የሚሆኑት ስደተኞች መነሻቸው ማዕከላዊ ኢትዮጵያ እንደሆነ ሪፖርቱ ይጠቅሳል። 6 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ መነሻቸው አዲስ አበባ ነው ይላል።
የኬንያዋ ዋና ከተማ ናይሮቢ ለእነዚህ ጉዞዎች እንደ ዋነኛ መሸጋገሪያ ከመሆኗ በላይ የስደተኞች መዳረሻ እየሆነች መምጣቷ በሪፖርቱ ተመላክቷል።
ድርጅቱ ይህ የስደት መስመር በአለም ላይ ፈታኙ የስደተኞች መንገድ መሆኑን ገልፆ የተቀናጀ ምላሽ ያስፈልጋል ብሏል።
@TikvahethMagazine
❤ 30👎 2🕊 2
Photo unavailableShow in Telegram
በመዲናዋ በጾታዊ ጥቃት ወደ ህክምና ከሚሄዱት እስከ 80 በመቶ የሚሆኑት ከ18 ዓመት በታች ናቸው ተባለ።
በአዲስ አበባ በጾታዊ ጥቃት የህክምና አገልግሎት ለማግኘት ከሚሄዱት መካከል ከ70 እስከ 80 በመቶ የሚሆኑት ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ያሉ ልጆች ናቸው ተብሏል።
አራዳ ኤፍ.ኤም በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ሴቶች ህጻናት ጉዳይ ዳይሬክተር ሄለን አዱኛን አናግሮ በሰራው ዘገባ በልጆች ላይ የሚደርሰው ጾታዊ ጥቃት እጅግ ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሷል።
ቢሮው ጥቃት ደርሶባቸው ህክምና ለማግኘት ከሚመጡት ተገልጋዮች ውስጥ 90 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች 10 በመቶዎቹ ወንዶች መሆናቸውንም ዳሬክተሯ ለጣቢያው ተናግረዋል።
አክለውም፥ 60 በመቶ የሚሆኑት ጥቃት አድራሾች የተጠቂዎቹ የቅርብ ቤተሰብ ወይም በቅርብ ያሉ ሰዎች መሆናቸውን ጠቅሰው፥ 40 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ የማያውቋቸው ሰዎች እንደሆኑ ነው የገለጹት።
ዘገባው ጥቃት ከደረሰባቸው መካከል በኤች አይ ቪ እና ሌሎች የአባላዛር በሽታዎች የተያዙ ተጠቂዎች ቁጥር አነስተኛ ቢሆንም በበሽታዎቹ መያዛቸው የታወቁ እንዳሉ ጠቅሷል።
ምንጭ: አራዳ ኤፍ.ኤም 95.1
@TikvahethMagazine
😢 69❤ 22💔 11🤬 10🙏 2
Photo unavailableShow in Telegram
በምያንማር በማጭበርበር ካምፖች በተሰራ ኦፕሬሽን ወደ 350 ሰዎች ተያዙ።
የምያንማር ጦር በታይላንድ ድንበር አቅራቢያ በሚገኝ አካባቢ ኬኬ ፓርክ በተባለ የማጭበርበሪያ ማዕከል ዘልቆ ገብቷል። ጦሩ በዚሁ የማጭበርበሪያ ካምፕ የነበሩ 350 ሰዎችን መያዙን ገልጿል።
የምያንማር ጦር የታጠቁ ቡድኖች የማጭበርበሪያ ካምፖቹን እንደሚጠብቁ ገልፆ አካባቢውን መቆጣጠሩን ገልጿል። የተያዙት አጠቃላይ 346 ሰዎች የውጪ ሃገር ዜጎች መሆናቸው ሲገለፅ ለኦንላይን ቁማርና የማጭበርበር አገልገሎት ሲውሉ የነበሩ ከ10 ሺህ በላይ ሞባይሎችም ተይዘዋል።
ከ2019 ወዲህ በታይላንድ፣ በምያንማር፣ ላኦስና ካምቦዲያ የጋራ ድንበሮች የኦንላይን የማጭበርበር ድርጊቶች የተስፋፉ ሲሆን ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የበርካታ ሃገር ዜጎች ተታለው በእነዚህ ካምፖች ተገደው ይሰራሉ።
በ2021 በምያንማር የመፈንቅለ መንግስት ከተፈፀመ በኋላ ሃገሪቷ በተለያዩ ደካማ ወታደራዊ ታጣቂዎች እየየተመራች ሲሆን ይህም ለማጭበርበሪያ ካምፖቹ ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል።
ባለፈው ጥቅምት በዚሁ ኬኬ ፓርክ በተደረገ ዘመቻ ከ2000 በላይ ሰዎች ሲታሰሩ አሜሪካም ከወር በፊት ከአጭበርባሪዎቹ ጋር ግንኙነት አላቸው ባላቻቸው 20 ድርጅቶች ላይ ማዕቀብ መጣሏ ይታወሳል።
በተመሳሳይ ቻይና በተለያዩ አጋጣሚዎች የተያዙ በምያንማርና ካምቦዲያ የሚገኙ የማጭበርበሪያ ካምፖችን የሚመሩ ሰዎችን በሞት ፍርድ እየቀጣች ሲሆን አሁንም በርካታ ኦፕሬሽኖችን እያከናወነች ነው።
ዘገባው የአልጄዚራ ነው።
@TikvahethMagazine
❤ 36👍 16👏 6
Photo unavailableShow in Telegram
📌 በ መሀል ሜክሲኮ 12,000 ካሬ ላይ ያረፈ ኮምፓዉንድ ህልሞን እውን ያርጉ ዘመናዊነት ምርጫ ነው…… በማይታመን ዋጋ ይዘንሎት ቀርበናል
👉0946690908
📌 ባለአንድ መኝታ
👉 78 ካሬ
ሙሉ ክፍያ 6,699,780
ቅድመ ክፍያ 5% = 334,989ብር
📌 ባለሁለት መኝታ
👉 125.53 ካሬ
ሙሉ ክፍያ 10,732,815
ቅድመ ክፍያ 5%= 536,640 ብር
📌 ባለ ሦስት መኝታ158.8ካሬ ሙሉ ክፍያ 13,577,400
ቅድመ ክፍያ 5%= 678,870 ብር
ሱቆች ከ12 ካሬ ጀምሮ
📌 ኮምፓውንዱ ያካተተው
👉የ ልጆች መጫወቻ
👉የ መዋኛ ገንዳ
👉አራት ቤዝመንት መኪና ማቆሚያ
📌 የካሬ ዋጋ በ ካሬ 85,500 ብር
👉 ቅድመ ክፍያ 5%
👉የቀረውን በግንባታ ሂደት በ3 አመት
ለ በለጠ መረጃ
0946690908
❤ 18👍 2
የተማሪዎች የሥነ ምግባር ረቂቅ መመሪያ በውስጡ ምን ምን አካቷል?
⚫ "Crazy day፣ olds day፣ Valentine day " እና ሌሎችም አላስፈላጊ የሆኑ ባህልን የማይገልፁ ድርጊቶችን ማክበር ይከለክላል።
መመሪያው በመንግስት፣ መንግስታዊ ባልሆኑ፣ የግል፣ በኃይማኖት ተቋማት የሚተዳደሩ ትምህርት ቤቶችና ከኢትዮጵያ ውጪ ባሉ ኮሚዩኒቲ ትምህርት ቤት በሚማሩ ተማሪዎች ላይ ተፈፃሚ ይሆናል።
በመመሪያው የተማሪዎች መብትና ግዴታዎች ሲቀመጡ በተማሪዎች ግዴታ ስር ፀጉርን በአግባቡ መሰራት/ማሳጠር፣ ከተፈጥሯዊ ጸጉራቸው ውጪ እንዳይጠቀሙ ተቀምጧል።
የሴቶቾ የትምህርት ቤት የደንብ ልብስ ቀሚስ ቁመት ከባት በታች መሆን ያለበት ሲሆን ከአካባቢው ባህል ጋር የማይቃረን ልብስ መልበስ የሚለውም ተካቷል።
በመመሪያው ከተከለከሉ ተግባራት መካከል ሲጋራ ማጨስ፣ አልኮል መጠጣት፣ ጫት መቃም፣ ዕፆችን መጠቀም/ማዘዋወር እንደዚሁም ሞባይልና የሙዚቃ ማዳመጫዎችን ወደ ትምህርት ቤት ይዞ መምጣት ይገኙበታል።
በትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ኃይማኖታዊ አምልኮ ስርዓትና የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችን ማከናወንም በመመሪያው ተከልክሏል።
በመመሪያው ሀገራዊ እሴት ያልሆኑ መጤ ነገሮችን በሰውነት ላይ መነቀስ ሲከለከል፤ ሴት ተማሪዎች የጥፍር፣ የፀጉርና የከንፈር ቀለም ከመቀባትና ከመኳኳል እንደዚሁም አላስፈላጊ ጌጥ ከማድረግ ይከለክላል።
በተጨማሪም በረቂቁ በትምህርት ቤት ውስጥ አላስፈላጊ የሆኑ የኢትዮጵያዊነት ባህልን የማይገልፁ ያላቸውን ድርጊቶች (Crazy Day, Gentle Day, Olds Day, Baby Day, Fruit Day, Tomato
Day, Valentine Day, April the full, Color Day, Pyjama Day…etc) መፈጸም፤ እና ሌሎችም አላስፈላጊ የሆኑ ባህልን የማይገልፁ ድርጊቶችን ማክበር እንደማይቻል ተገልጿል።
የተከለከሉ ተግባራትን በሚፈፅመት ላይ የተለያያ የእርምት እርምጃዎች ሲቀመጡ ቀላል እርምጃ ሊያስወስዱ በሚችሉ ጥፋቶች ስር ከፀጉር ጋር የተያያዙ እና ሌሎች ቀላል ጥፋቶች ተካተዋል።
የትምህርት ቤት ፕላዝማና ኮምፒውተር ለሌላ አላማ መጠቀም፣ በአጥር መዝልና መሽሎክ፣ ከላይ የተጠቀሱ አላስፈላጊ ባህሎችን ማክበር፣ አሉታዊ ምልክቶችን መነቀስ፣ ድብድብ እንደዚሁም ኃይማኖታዊ ስርዓት መፈፀምና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ማድረግ በከባድ ጥፋት ውስጥ ተካተዋል።
የቅጣት እርከኑ እንደ ተማሪዎች የትምህርት ደረጃና ጥፋቱ ሲለያይ ለከባድ የስነ ምግባር ግድፈት በመደበኛ ህግ መሰረት የህግ ተጠያቂነት ይኖራል።
መመሪያው የዲሲፕሊን ክስ አመሰራረት፣ የዲስፕሊን ኮሚቴ ስብጥር እንደዚሁም ተግባርና ኃላፊነትን በዝርዝር አስቀምጧል።
በተጨማሪ መመሪያው በየደረጃው ያሉ የባለድርሻ አካላትን ተግባርያ ኃላፊነትም ዘርዝሮ ሲያስቀምጥ ማንኛውም ትምህርት ቤት ያለ መሸኛ ተማሪዎችን ተቀብሎ መመዝገብንም ከልክሏል።
ትምህርት ሚኒስቴር በመመሪያው ላይ ምክረ ሃሳብ ያላቸው ሰዎች በ https://forms.gle/R72ai6EiMnzZtGsC6 እንዲያቀርቡ ጠይቋል።
@TikvahethMagazine
❤ 265👍 64🤣 35👏 24👎 16🤔 3🕊 2
Photo unavailableShow in Telegram
“ህገወጥ አዘዋዋሪዎች ሕፃናትን ለጾታዊ ብዝበዛ እና ለሕገወጥ ዝውውር ለመመልመል የማኅበራዊ ሚዲያን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠቀሙ ነው” - ሪፖርት
የኢትዮጵያ መንግስት ህገ-ወጥ የሰዎችን ዝውውር ለማስቀረት ያደረጋቸው ጥረቶች መልካም ቢሆኑም የተቀመጠውን ዝቅተኛ መመዘኛ ሙሉ ለሙሉ ማሳካት እንዳልቻለ የአሜሪካ መንግስት ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል።
በህገወጥ የሰዎች ዝውውርር ተሳታፊ የነበሩ ባለሥልጣናትን ጨምሮ አዘዋዋሪዎችን የመለየት ሥራ እንዲሁም በሀገሪቱ የመጀመሪያ የሆነውን የህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባዎች ማረፊያ በድሬዳዋ መስራቱንም በጥሩ ጎኑ ተነስቷል።
በተጨማሪም በቅርብ ጊዜ መንግስት የህገወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከታተል የፋይናንስ ዝውውሮችን መከታተል የሚያስችለውን አሰራር (SOPs) መዘርጋቱ በሪፖርቱ በጠንካራ ጎኑ ተነስቷል።
ሆኖም ህገወጥ የሰዎችን ዝውውር በሚመለከተው ሪፖርት ኢትዮጵያ ዝቅተኛውን መመዘኛ አላሟላችም በሚል በሁለተኛ ምድብ (Tier2) ላይ አስቀምጧታል።
በሪፖርቱ መንግስት በሀገር ውስጥ ያለውን ህገወጥ የሰዎች ዝውውር እንደዚሁም ህፃናትን ለወሲብ ማዘዋወርን በተመለከተ በቂ ሥራዎችን አልሰራም ሲል ይጠቅሳል።
በተጨማሪን “ህገወጥ አዘዋዋሪዎች ሕፃናትን ለጾታዊ ብዝበዛ እና ለሕገወጥ ዝውውር ለመመልመል የማኅበራዊ ሚዲያን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠቀሙ ነው” ሲል ይገልጻል።
መንግስት የሰዎች ዝውውርን በተመለከተ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን የመረጃ አሰባሰብ በማዕከል ደረጃ አለመኖሩን እና በጉዳዩ ተሳታፊ የሆኑ በጸጥታ አካላትና በባለሥልጣናት ዘንድ ያለው ሙስና ፈተና ሆኗል ተብሏል።
ሪፖርቱ ህፃናትን ከህግ አግባብ ውጪ በመመልመል ለውትድርና መጠቀምን ማቆም እንደዚሁም በሌሎች ታጣቂዎች ውስጥና በመንግስት ውስጥ ያሉ የታጠቁ ህፃናት ትጥቃቸውን እንዲፈቱ ምክረ ሃሳብም አቅርቧል።
ህፃናትን ለውትድርና የመለመሉና በሰዎች ዝውውር የሚሳተፉ ባለስልጣናትም ጨምሮ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ተመርምረው ለህግ እንዲቀርቡም አሜሪካ ጠይቃለች።
በሌላም በኩል ሰራተኛ በሚመለምሉ ኤጀንሲዎች ላይ ጠንካራ ክትትል ማድረግ ይገባል ሲል የጠቀሰው ሪፖርቱ መንግስት 809 የስራ ኤጀንሲዎችን እንደሚቆጣጠርና በ121 ኤጀንሲዎች ላይ እርምጃ ስለመወሰዱም መግለጹን ያነሳል።
መንግስት በፈረንጆቹ 2022-23 የሰዎችን ዝውውር ለመዋጋት 1.58 ቢሊየን ብር በጀት ይዞ ነበር ያለው ሪፖርቱ በዚህ ዓመት ምን ያህል በጀት እንደያዘ አልታወቀም።
አዘዋዋሪዎች ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም ይሰራሉ ሲል ሪፖርቱ ጠቅሷል። በተለይም የዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎችን ኢላማ በማድረግ ወደ ደቡብ ምስራቅ እስያ የማጭበርበር ስራዎች እንደሚመለምሉም ገልጿል።
በሀገሪቱ ያሉ ግጭቶችም የሰዎች ዝውውር እንዲጨምር ያደረጉ መሆኑን ያነሳችው አሜሪካ በትግራይ፣ አማራና ኦሮሚያ የሚገኙ ታጣቂዎች ህፃናትን ለውትደርና ተጠቅመዋል ብላለች።
ህገወጥ የሰዎች ዝውውር በ3 መስመሮች በስፋት እንደሚከናወን ሪፖርቱ ናነሳል እነዚህም የጂቡቲ/ሶማሊያ፣ የኬንያና የሱዳን እንደሆኑ ያነሳል።
@TikvahethMagazine
❤ 37😢 6🤯 1
