TIKVAH-MAGAZINE
رفتن به کانال در Telegram
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። #ኢትዮጵያ ያግኙን +251913134524
نمایش بیشتر2025 سال در اعداد

194 399
مشترکین
-5024 ساعت
-1767 روز
-81830 روز
آرشیو پست ها
"ከ10,900 በላይ ኢትዮጵያውያን በህገ ወጥ መንገድ ከሃገር ሊወጡ ሲሉ ተይዘዋል" - የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት
የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለውጪ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበው ሪፖርት መሰረት በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት (ከሐምሌ - መስከረም) ፦
- አጠቃላይ 545,491 ፓስፖርት ለዜጎች መሰጠቱን ገልጿል።
- ከአጠቃላይ ለ373,000 በላይ ዜጎች መደበኛ፣ ከ136 በላይ ለሚሆኑት አስቸኳይ ፣ ከ14,000 በላይ ኢ-ፓስፖርት እንዲሁም ከ20,000 በላይ ለሚሆኑት ደግሞ በቆንጽላ በኩል አገልግሎት ያገኙ ናቸው።
- ከ3400 በላይ የውጪ ዜጎች ወደ ሃገር ሊገቡ ሲሉ የተያዙ ሲሆን ከ10,900 በላይ ኢትዮጵያውያን በህገ ወጥ መንገድ ከሃገር ሊወጡ ሲሉ ተይዘዋል።
- ከሰጠው አገልግሎት 11 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 10.5 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታውቋል።
- ሃሰተኛ የጉዞ ሰነድ ያቀረቡ 860 ኢትዮጵያውያንና የውጪ ሃገር ዜጎች ተጠያቂ ተደርገዋል፤
- 96 የውጭ ሀገር ዜጎች የተጭበረበረ የጉዞ ሰነድ ሲጠቀሙ ተይዘዋል።
@TikvahethMagazine
❤ 44😢 11🤬 6💔 1
Photo unavailableShow in Telegram
በካሽ 100% ለሚከፍል 35% ቅናሽ
📍ሳር ቤት ቫቲካን እና በአዋሬ
🎯65/35 አከፍፈል (35%ቅናሽ)
👉2መኝታ 81 ካሬ = 6 ሚሊዮን ብር
👉2መኝታ 106 ካሬ=7.8 ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 139 ካሬ=10.3 ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 152 ካሬ= 11.8 ሚሊዮን ብር
🎯ቀስ ብሎ ለሚከፍል
👉2መኝታ 81ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%) = 1.78 ሚሊዮን ብር
👉2መኝታ 106ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%)=2.33ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 139ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%)= 3.06 ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 152ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%)=3.34 ሚሊዮን ብር
#ቀሪውን 80% ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት
* 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ 15%-25% ቅናሽ አዘጋጅተናል
👉👉 መረከቢያ ጊዜ - 2 አመት ከ 6 ወር
ለበለጠ መረጃ
👇👇👇👇👇👇
+251980782850
❤ 13🕊 1
Photo unavailableShow in Telegram
በ2020 የተለያዩ ሰዎችን የቲዊተር አካውንት ጠልፎ የነበረው ግለሰብ 5.4 ሚሊየን ዶላር የሚያዋጣ ቢትኮይኑ ሊወረስ ነው።
ጆሴፍ ጀምስ የተባለው የ26 ዓመት ወጣት በወቅቱ እንደ ጆ ባይደን፣ ኢሎን መስክ፣ ባራክ ኦባማ፣ ቢል ጌትስና ዋረን ቡፌት ያሉ ዝነኞችን የቲዊተር አካውንት ከጠለፈ በኋላ ሰዎችን ሲያጭበረብር ነበር።
በጠለፋቸው አካውንቶችም ተከታዮች በርከት ያለ ቢትኮይን እንዲልኩና በምላሹ እጥፍ አድርጎ እንደሚመልስ ቃል በመግባት በርካቶችን አጭበርብሮ ነበር።
በ2021 በስፔን ከተያዘ በኋላ ስፔን ግለሰቡን ለአሜሪካ አሳልፋ የሰጠች ሲሆን በ2023 በአሜሪካ የአምስት አመት እስር ተፈርዶበት ነበር።
የብሪታኒያ መርማሪዎችም ከማጭበርበሩ ጋር የተገኙ 42 ቢትኮይንና ሌሎች የዲጂታል ሃብቶችን ለመያዝ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸዋል።
ቢትኮይኑና ግለሰቡ በማጭበርበሩ ያገኛቸው ሌሎች ዲጂታል ሃብቶች በፍርድ ቤት በሚመረጥ አካል በኩል እንዲሸጥ እና ግለሰቡ ሲፈታ ምንም አይነት ጥቅም ከማጭበርበሩ እንዳያገኝ ወስኗል።
ዘገባው የዘ ኢንዲፔንደንት ነው።
@TikvahethMagazine
❤ 77🤣 19👍 13👏 7
Photo unavailableShow in Telegram
በህንድ በወሊድ ሆስፒታል ላይ በተፈፀመ የሳይበር ጥቃት የበርካታ ሴቶቾ ቪዲዮ መለቀቁ ተሰማ።
በሆስፒታሉ የተገጠመው የሲሲቲቪ ካሜራ ቪዲዮዎች ከተጠለፉ በኋላም በቴሌግራም ላይ እየተሸጡ ነው ተብሏል።
ካሜራዎቹ የተገጠሙት የሃኪሞችን ደህንነት ለመጠበቅ ነበር ሲባል በመላው ሃገሪቱም ከ50,000 በላይ የሲሲቲቪ ቪዲዮዎች መጠለፋቸውንና መሸጣቸውን ፖሊስ አስታውቋል።
በህንድ የሲሲቲቪ ካሜራዎች በቂ የሳይበር ደህንነት ስልጠና ባልወሰዱ ሰዎች እንደሚገጠም የተጠቀሰ ሲሆን ይህም በቀላሉ ለጥቃት እንደሚያጋልጥ ተነስቷል።
ህንድ የሳይበር ደህንነቷን ለማጠናከር በርካታ ስራዎችን ብትሰራም የጥቃቱ መጠን መጨመር እንጂ መቀነስ አልታየበትም ተብሏል።
ጥቃቱ ተፈፀመ የተባለበት የጉጅራት አካባቢ ፖሊስ በህንድ በሆስፒታሎች ፣ በትምህርት ቤቶችና በሌሎችም ቦታዎች የሚገኙ የሲሲቲቪ ካሜራዎችን ኢላማ የሚያደርጉ የመረጃ መዝባሪዎች ኔትዎርክ እንዳለ ገልጿል።
የተሰረቁት ቪዲዮዎች ከ800-2000 የህንድ ገንዘብ(9$-22$) እየተሸጡ መሆኑ ሲገለፅ በሰብስክሪፕሽን ደግሞ የሲሲቲቪ ካሜራዎች የሚቀርፁትን በቀጥታ መከታተል ይችላሉ ተብሏል።
ፖሊስ ከዩቲዩብና ቴሌግራም ጋር በመነጋገር ቪዲዮዎቹ እንዲወርዱ ተደርጓል ያለ ሲሆን ከባለፈው የካቲት ወር ጀምሮም 8 ሰዎች መታሰራቸውን ገልጿል።
ዘገባው የቢቢሲ ነው።
@TikvahethMagazine
❤ 75🤔 36🤬 15😢 15🤯 4🤣 3
Photo unavailableShow in Telegram
#IsItAI ?
"ሰዎች ሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) የሚነግራቸውን ሁሉ በጭፍን ማመን የለባቸውም
የኤአይ ሞዴሎች ለስህተት የተጋለጡ ናቸው። ሰዎች ከሌሎች መሳሪያዎች ጋር ሊጠቀሟቸው ይገባል።
ሰዎች እነዚህን መሳሪያዎች ጥሩ በሆኑት ጉዳይ ላይ ብቻ መጠቀምን መማር እንዲሁም የሚናገሩትን ሁሉ በጭፍን አለማመን አለባቸው" - ሳንዳር ፒቻይ (የጉግል እናት ኩባንያ አልፋቤት ኃላፊ)
ምንጭ: ቢቢሲ
#Concepthub #InterNews #EU
Via @Concepthubeth
@TikvahethMagazine
❤ 62🤷♂ 5👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
የ10 አመት ታዳጊ በነብር ተበልቶ ሞቶ መገኘቱን ፖሊስ ገለፀ።
በድሬደዋ ከተማ ዙሪያ አዋሌ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ገንደ ሳሊ ተብሎ በሚጠራው መንደር ህዳር 8 ቀን 2018 ዓ/ም ከንጋቱ 12 ሰአት ገደማ የ10 አመት ታዳጊ በነብር ተበልቶ መሞቱን ፖሊስ አስታውቋል።
የቢየ አዋሌ ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ ኢ/ር አብዱሰላም መሀመድ ሞች ገመዳ አብደላ የተባለው የ10 አመት ታዳጊ ህዳር 7 ቀን ከምሽቱ 12 ሰአት ገደማ ከቤት እንደወጣ ባለመመለሱ ቤተሰቦቹ ምሽቱን ሲያፈላልጉት ማደራቸውን ጠቁመዋል።
ፍለጋውን የቀጠሉት ቤተሰቦች፥ በንጋታው ጠዋት 12 ሰአዓት ላይ ልጁ በነብር እየተበላ ቢያገኙትም ህይወቱን ማትረፍ አለመቻላቸውን አና ታዳጊው ሞቶ ማግኘታቸውን ኢ/ር አብዱሰላም ገልፀዋል።
በአካባቢው ነብር መኖሩን እና ከአሁን በፊትም በተደጋጋሚ ግዜ ጥቃት ማደረሱን ፖሊስ አስታውሶ የአከባቢው ማህበረሰብ በተለይ ልጆችን ብቻቸውን ከመልቀቅ በመቆጠብ ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ መልዕክቱን አስተላልፏል።
@TikvahethMagazine
😢 157❤ 48💔 22👍 4🕊 3
Photo unavailableShow in Telegram
በናይጄሪያ ታጣቂዎች አስተማሪ ገድለው 25 ተማሪዎችን አግተው መውሰዳቸው ተዘገበ።
በስሜን ምዕራብ ናይጄሪያ በሚገኝ የሴቶች የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ ታጣቂዎች ጥቃት ፈፅመው አስተማሪውን ከገደሉ በኋላ 25 ተማሪዎችን ይዘው ተሰውረዋል።
ታጣቂዎቹ የተኩስ ልውውጥ በሚያደርጉበት ወቅት ተማሪዎቹን ሊከላከል የሞከረ ግለሰብ መገደሉ ሲነገር ለጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ አካል የለም።
ሰሜናዊ ናይጄሪያ በተደጋጋሚ ጥቃት የሚፈፀምባት ስትሆን ሽፍታዎች ሰዎችን አግተው በገንዘብ የሚደራደሩበትም አካባቢ ነው።
የአካባቢው ፖሊስ ታጣቂዎች ወደ ትምህርት ቤቱ ከመግባታቸው በፊት ከኦፊሰሮች ጋር የተኩስ ልውውጥ እንዳደረጉና ታጣቂዎቹ በደንብ ስለታጠቁ ከጸጥታ ኃይሎች የተሻሉ እንደነበር ገልጿል።
ዘገባው የ DW ነው።
@TikvahethMagazine
😢 48❤ 23🕊 2🤬 1🙏 1
Photo unavailableShow in Telegram
የ10 አመት ታዳጊ በነብር ተበልቶ ሞቶ መገኘቱን ፖሊስ ገለፀ።
በድሬደዋ ከተማ ዙሪያ አዋሌ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ገንደ ሳሊ ተብሎ በሚጠራው መንደር ህዳር 8 ቀን 2018 ዓ/ም ከንጋቱ 12 ሰአት ገደማ የ10 አመት ታዳጊ በነብር ተበልቶ መሞቱን ፖሊስ አስታውቋል።
የቢየ አዋሌ ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ ኢ/ር አብዱሰላም መሀመድ ሞች ገመዳ አብደላ የተባለው የ10 አመት ታዳጊ ህዳር 7 ቀን ከምሽቱ 12 ሰአት ገደማ ከቤት እንደወጣ ባለመመለሱ ቤተሰቦቹ ምሽቱን ሲያፈላልጉት ማደራቸውን ጠቁመዋል።
ፍለጋውን የቀጠሉት ቤተሰቦች፥ በንጋታው ጠዋት 12 ሰአዓት ላይ ልጁ በነብር እየተበላ ቢያገኙትም ህይወቱን ማትረፍ አለመቻላቸውን አና ታዳጊው ሞቶ ማግኘታቸውን ኢ/ር አብዱሰላም ገልፀዋል።
በአካባቢው ነብር መኖሩን እና ከአሁን በፊትም በተደጋጋሚ ግዜ ጥቃት ማደረሱን ፖሊስ አስታውሶ የአከባቢው ማህበረሰብ በተለይ ልጆችን ብቻቸውን ከመልቀቅ በመቆጠብ ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ መልዕክቱን አስተላልፏል።
@TikvahethMagazine
Photo unavailableShow in Telegram
በካሽ 100% ለሚከፍል 35% ቅናሽ
📍ሳር ቤት ቫቲካን እና በአዋሬ
🎯65/35 አከፍፈል (35%ቅናሽ)
👉2መኝታ 81 ካሬ = 6 ሚሊዮን ብር
👉2መኝታ 106 ካሬ=7.8 ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 139 ካሬ=10.3 ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 152 ካሬ= 11.8 ሚሊዮን ብር
🎯ቀስ ብሎ ለሚከፍል
👉2መኝታ 81ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%) = 1.78 ሚሊዮን ብር
👉2መኝታ 106ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%)=2.33ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 139ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%)= 3.06 ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 152ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%)=3.34 ሚሊዮን ብር
#ቀሪውን 80% ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት
* 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ 15%-25% ቅናሽ አዘጋጅተናል
👉👉 መረከቢያ ጊዜ - 2 አመት ከ 6 ወር
ለበለጠ መረጃ
👇👇👇👇👇👇
+251980782850
❤ 12
Photo unavailableShow in Telegram
ተመራጯ የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ልጇንና የልጇን ባል በሚኒስትርነት ሹመዋል።
አወዛጋቢ በነበረውና የአፍሪካ ህብረት ሳይቀር ጥያቄ ያነሳበትን ምርጫ እንዳሸነፉ የታወጀላቸው ሳሚያ ሱሉሁ ዘመዶቻቸውን በከፍተኛ የስልጣን ቦታዎች ላይ መድበዋል።
ፕሬዚዳንቷ ሴት ልጃቸውን የትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታ አድርገው ሲሾሙ የልጃቸውን ባል የጤና ሚኒስቴር አድርገው ሾመዋል።
ሁለቱም ተሿሚዎች የፓርላማ አባል መሆናቸው ተገልጿል።
98% ድምፅ በማግኘት ምርጫውን አሸነፉ የተባሉት ሳሚያ ሱሉሁ 27 ሚኒስትሮችንና 29 ሚኒስትር ዴኤታዎችን የያዘውን አዲስ ካቢኔም ይፋ አድርገዋል።
ዘገባው የTRT ነው።
@TikvahethMagazine
🤣 286❤ 26👏 11🤔 9👍 2😢 2💔 2
Photo unavailableShow in Telegram
#እንድታውቁት: ከኪራይ በሚገኝ ገቢ ላይ ተፈጻሚ የሚሆን ምጣኔን በተመለከተ
የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር 1395/2017 ላይ በግለሰቦች ኪራይ ገቢ ላይ ተፈፃሚ የሚሆኑ የግብር መጣኔዎች ተቀምጧል፡፡
🔗 በግለሰቦች ኪራይ ገቢ ላይ ተፈፃሚ የሚሆኑት መጣኔዎች ከላይ በምስሉ ተያይዟል።
ምንጭ: የገቢዎች ሚኒስቴር
@TikvahethMagazine
👎 113❤ 36👍 7😢 3🤣 1
Photo unavailableShow in Telegram
#እንድታውቁት: ከኪራይ በሚገኝ ገቢ ላይ ተፈጻሚ የሚሆን ምጣኔን በተመለከተ
የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር 1395/2017 ላይ በግለሰቦች ኪራይ ገቢ ላይ ተፈፃሚ የሚሆኑ የግብር መጣኔዎች ተቀምጧል፡፡
🔗 በግለሰቦች ኪራይ ገቢ ላይ ተፈፃሚ የሚሆኑት መጣኔዎች ከላይ በምስሉ ተያይዟል።
ምንጭ: የገቢዎች ሚኒስቴር
👎 1
⚫ በአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር የቀበሌ መታወቂያ በፋይዳ መተካቱን በይፋ ተገለጸ።
⚫በከተማው ባሉ ሁሉም ቀበሌዎች ከዛሬ ጀምሮ መደበኛ መታወቂያ ተሰርዟል።
የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር የቀበሌ መታወቂያ እንዳይሰጥና እንዲሰረዝ እንዲሁም በከተማው ማንኛውም አገልግሎት የሚሰጠው በብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ብቻ መሆኑን አስታውቋል።
ከዛሬ ጀምሮ ሁሉም ሰው በብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ብቻ እንዲጠቀምና በከተማው በሁሉም ቀበሌያት መደበኛ መታወቂያ እንዳይሰጥና እንዲሰረዝ ነው አስተዳደር ምክር ቤቱ የወሰነው።
ከተማ አስተዳደሩ በከተማው የሚከናወኑ ህገ-ወጥ ተግባራትና ወንጀሎች ለመከላከል በማሰብ ለማንኛውም ዓይነት አገልግሎቶች ህብረተሰቡ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ብቻ እንዲጠቀም አሳስቧል።
በከተማው ባሉ ሁሉም ቀበሌዎች ከዛሬ ጀምሮ መደበኛ መታወቂያ እንደማይሰጥና እንደተሰረዘ ነው የተገለጸው።
ነዋሪዎች እንዲሁም በከተማው የሚንቀሳቀሱ ማንኛውም ግለሰብ ከዚህ በኃላ ምንም ዓይነት የቀበሌ መታወቂያ መጠቀም እንደማይቻልም አጽንኦት ሰጥቶ ገልጿል።
በመሆኑም የመደበኛ መታወቂያ የሰጠ እንዲሁም በመታወቂያው የተጠቀመ ግለሰብ በህግ እንደሚጠየቅም ነው ያሳሰበው።
መረጃው የከተማ አስተዳደሩ ኮሚኒኬሽን ነው።
@TikvahethMagazine
👏 91❤ 50👎 34🤔 13🙏 5
Photo unavailableShow in Telegram
"83 በመቶ የአስተዳደር በደል አቤቱታዎች በመንግስት ተቋማት ላይ የቀረቡ ናቸው" - የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም
የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም በሩብ አመቱ ከቀረቡለት አቤቱታዎች መካከል 83 በመቶ የሚሆኑት በመንግስት ተቋማት ላይ የቀረቡ መሆናቸውን አስታውቋል።
ከቀረቡት አቤቱታዎች 114 አቤቱታዎች ከአገልግሎት አለማግኘት ጋር ተያይዞ የቀረቡት ቅሬታዎች ቡዙውን ድርሻ የሚይዝ ነው ተብሏል።
በ2018 የመጀመሪያ ሩብ አመትም በ61 መዝገቦች ላይ የመፍትሄ ሃሳብ ተሰጥቷል ያለው ተቋሙ በ2017 ሳይፈፀሙ ቀርተው ወደ 2018 ከተዘዋወሩ 63 መዝገቦች ጋር ተዳምሮ በ124 መዝገቦች ላይ የአፈፃፀም ክትትል ተደርጓል።
ከነዚህም በ61 መዝገቦች ላይ የተሰጠው የመፍትሄ ሃሳብ ሲፈፀም በ3ቱ ላለመፈፀም በቂ ምክንያት ስለቀረበ ክትትል መቆሙንና በተቀሩት 56 መዝገቦች ላይ ክትትል እየተደረገ መሆኑን አስታውቋል።
ተቋሙ፥ በአዲሱ ረቂቅ አዋጅም መረጃ የሚሰጥበት ቀን ከ30 ወደ 21 ቀን እንዲቀንስ፣ መረጃ በዲጃታል መንገድ መስጠት እንዲጀመር እንዲሁም መረጃን የሚያጓትቱ እርምጃ እንዲወሰድባቸውና የመረጃ አሰጣጥ ዘርፍን የሚመራ ዕንባ ጠባቂ እንዲሾም ሃሳብ መቅረቡን አስታውቋል።
Read More https://telegra.ph/EIO-11-1
@TikvahethMagazine
Photo unavailableShow in Telegram
ኢጋድ ኢትዮጵያን ጨምሮ በሶስት ሃገራት የድርቅ ስጋት እንዳለ አስታወቀ።
የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት ኢጋድ የአየር ሁኔታ ማዕከል እስከ መጪው ጥር ድረስ የአፍሪካ ቀንድ ከተለመደው የዝናብ መጠን በታች እንደሚያገኝ ተንብይዋል።
ይህም በኢትዮጵያ ፣ ኬንያና ሶማሊያ ያለውን ድርቅ እንደሚያባብስና የሚሊየኖችን ህይወት ስጋት ውስጥ እንደሚከት አስታውቋል።
ማዕከሉ የዝናብ እጥረቱ የምግብ ችግር ሊያመጣ እንደሚችል ጠቅሶ መንግስታት እና የሰብዓዊ ተቋማት ለሚመጣው ነገር ከወዲሁ ዝግጅታቸውን ያጠናክሩ ብሏል።
ዘገባው ከሂራን ኦንላይን የተገኘ ነው።
@TikvahethMagazine
❤ 22🤔 9😢 4🤣 4👍 3
Photo unavailableShow in Telegram
ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በሲጋራ ኢንዱስትሪ ካልተሰማሩባቸው ሁለት የአፍሪካ ሃገራት አንዷ ኢትዮጵያ ነች ተባለ።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ የሲጋራ ኢንዱስትሪን ተፅዕኖ ከተቋቋሙ ሃገራት መካከል አንዷ መሆኗም ሪፖርት አመላክቷል።
የአፍሪካ የትምባሆ ቁጥጥር ጥምረት (ATCA) የኢትዮጵያ መንግስት ማኅበረሰቡን ከሲጋራ ጉዳት ለመጠበቅ የወሰደውን ህጋዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃዎች አድንቋል።
ኢትዮጵያ የኢንደስትሪ አጋርነትን በመቀነስ፣ የመንግስት ባለስልጣናት ከኢንዱስትሪው ጋር እንዳይገናኙ በማድረግና በመንግስት ተቋማት የሚኖርን የጥቅም ግጭት ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ በማስቀረት ተሳክቶላታል ተብሏል።
በሪፖርቱ ኢትዮጵያ የሲጋራ አምራቾች በትላልቅ ብሔራዊ ፕሮጀክቶችና የከተማ ልማት ፕሮጀክቶች ላይ እንዳይሳተፉ ማድረጓ በትልቅ ስኬትነት ተነስቷል።
ኢትዮጵያ የመንግስት አካላት ከሲጋራ አምራቾች ጋር አጋርነት እንዳይፈጥሩ ከ6 አመት በፊት አዋጅ ያወጣች ሲሆን የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣንም ከኢንዱስትሪው ጋር የሚኖርን አጋርነት በመከታተል ጉልህ ሚና ተወጥቷል።
በተጨማሪ ሪፖርቱ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከኡጋንዳ በተጨማሪ የመንግስት ከፍተኛ ኃላፊዎች የሲጋራ ኢንዱስትሪውን ያልተቀላቀሉበት ወይም ከሲጋራ ኢንዱስትሪ የመጣ ሰው ከፍተኛ ስልጣን ላይ ያልተቀመጠበት ሀገር ናት ተብሏል።
መንግስት በብሔራዊ የትምባሆ ኢንተርፕራይዝ የነበረውን ድርሻ ለጃፓን ቶባኮ ኢንተርናሽናል በመሸጥ ከኢንዱስትሪው ሙሉ ለሙሉ መውጣቱንም ሪፖርቱ አስታውሷል።
በሌሎች ሀገራት የሲጋራ አምራቾች ተጽዕኗቸውን ለማሳደግ የማኅበራዊ ኃላፊነት ላይ የሚሳተፉ ሲሆን በኢትዮጵያ ግን ይኸው ተሳትፏቸው እጅግ ዝቅተኛ መሆኑ ተገልጿል።
የመረጃው ምንጭ ሪፖርተር ጋዜጣ ነው።
@TikvahethMagazine
❤ 100🤣 26👏 16👍 5👎 4🤔 4
Photo unavailableShow in Telegram
🌟 ታማኝነት
🌟 ጥራት
🌟 ማሕበረሰብን መገንባት የሚታወቀው የናተው አያት አሁን ደሞ
✨ በካሳንቺስ
✨በልደታ
✨በሴሚሲ ሚካኤል
✨በቤልየር
✨በመሪ
✨በአያት
⚡️በ ካሬ 89,815 ብር
⚡️አፓርትመንት እና የ ንግድ ሱቆችን በ477,000 ብር ቅድመ ክፍያ ምንም አይነት የዋጋ ጭማሪ ሣይደረግቦት የራስዎ ያርጉ!
💥 ለበለጠ መረጃ 2519-77-63-06-93 በቀጥታ @ayat121921 በቴሌግራም በዋትሳፕ ይደውሉ
❤ 12👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
በአለም አቀፍ ደረጃ የኢንተርኔት ነፃነት ለ15ኛ ተከታታይ አመት ሲቀንስ ኢትዮጵያ የኢንተርኔት ሳንሱር መሰረተ ልማት እየሰሩ ካሉ ሃገራት አንዷ ነች ተብሏል።
ኢንተርኔት ባለንበት ዘመን ዋነኛ ከሚባሉ ነገሮች ውስጥ የሚመደብ ቢሆንም ከጊዜ ወደ ጊዜ ቁጥጥር እየበዛበት መጥቷል።
በ2025 ይፋ በተደረገው ሪፖርትም ለ15ኛ ተከታታይ አመት የኢንተርኔት ነፃነት መቀነስ አሳይቷል።
ከዚህ በፊት "ነፃ" ከሚባሉት 18 ሃገራት በዘጠኙ ነፃነቱ መቀነሱ ሲነገር ጂኦርጂያ፤ ጀርመንና አሜሪካ ከፍተኛ ማሽቆልቆል ታይቶባቸዋል።
ሰዎች የኢንተርኔት ነፃነታቸው እየተገደበ በመምጣቱ ለቪ ፒ ኤን ያላቸው ፍላጎትም እየናረ ስለመሆኑ ሪፖርቱ አመልክቷል።
ከሰኔ 2024 እስከ ግንቦት 2025 በነበረው ወቅት ከፍተኛ የኢንተርኔት ነፃነት መቀነስ የታየው በጎረቤታችን ኬንያ ሲሆን በወቅቱ በነበረው ተቃውሞ ኬንያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢንተርኔት አገልግሎት ያቋረጠችበትም ነበር።
አውሮፓዊቷ ሃገር ጀርመን ከባለፈው የካቲት ጀምሮ ፖለቲከኞች ላይ "memes" የሚሰሩ ሰዎች በወንጀል እየተጠየቁ መሆኑ ሲገለፅ አሜሪካ ቪዛ ለመስጠት የሰዎችን የኢንተርኔት ተግባር ከማየቷ በተጨማሪ ያላቸውንም ቪዛ እየሻረች ነው።
በሪፖርቱ እንደተገለፀው አይስላንድና ኢስቶኒያ በኢንተርኔት ነፃነት መሪዎቹ ሲሆኑ ቻይናና ምያንማር ደግሞ ነፃነት በመንፈግ መሪዎቹ ናቸው።
እንደ ቻይና፣ ምያንማርያ ሩሲያ ያሉ ሃገራት የኢንተርኔት ሳንሱርን ለማጠናከር አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ለራሳቸው እየሰሩ ሲሆን እንደ ቻይና ያሉ ሃገራት ደግሞ ከራሳቸው አልፎ እንደ ፓኪስታን ላሉ ሃገራት ቴክኖሎጂውን እየሰሩ ነው።
በሪፖርቱ ኢትዮጵያን ጨምሮ ካዛኪስታን ፣ ምያንማር፣ ካምቦዲያ እና ቤላሩስ የሳንሱር ስርዓት መሰረት ልማት በመገንባት እንደተጠመዱ ተመላክቷል።
72 ሃገራትን የዳሰሰውን ሪፖርት ከ "An Uncertain Future for the Global Internet | Freedom House" https://freedomhouse.org/report/freedom-net/2025/uncertain-future-global-internet ማግኘት ትችላላችሁ።
@TikvahethMagazine
❤ 83🤣 18👍 9👎 2🤬 2🤔 1
Photo unavailableShow in Telegram
#IsItAI?
በተለይ በኤ.አይ የተፈጠሩ ሀሰተኛ ምስሎችና መረጃዎች ሰዎችን የመሸወድና የመጉዳት መጠናቸው በየቀኑ እየጨመረ ይገኛል።
በዚህ ወቅት ምን ቢያደርጉ ይመከራል ?
1. ምንጩ ከየት እንደሆነ ደግሞ መጠየቅ፣ መረጃውን ከመነሻው ለማወቅ መሞከር፤
2. የተለጠፈበት ገጽ ትክክለኛ መሆኑን መመርመር፤ ከዚህ በፊት ተደጋጋሚ ሀሰተኛ መረጃዎችን ከሚያሰራጩ ገጾች ራስን መቆጠብ፤
3. የተመለከተቱት መረጃ ንዴት፣ ቁጣ ወይም ለየት ያለ ስሜት ከፈጠረቦት ቆም ብለው ስለመረጃው ትክክለኝነት ጠለቅ ብለው ይጠይቁ!
4. መረጃዎችን ለሌሎች ከማጋራቶት በፊት ከሁለት ሦስት ምንጮች ዜናውን ማረጋገጥ ይጠበቅቦታል።
በኤ.አይ የተፈጠረም ሊሆን ይችላል! ሁሉም እውነት አይደለም! ቆም ብለን እንጠይቅ!
#Concepthub #InterNews #EU
👍 30❤ 24
Photo unavailableShow in Telegram
እንጀራ በሸቀጣ ሸቀጦች ሱቅ መሸጥ መከልከሉ ተገለጸ።
የአዲስ አበባ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣንን የተለያዩ ሸቀጣሸቀጦች በሚሸጡባቸው ሱቆች ውስጥ እንጀራ መሸጥ መከልከሉን አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዘግቧል።
የባለስልጣኑ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ እንጋ እርቀታ የተለያዩ መርዛማ ነገሮች ሳሙና እና ለጤና ጠንቅ የሆኑ ሸቀጦች በሚሸጡባቸው ሱቆች በቀጥታ ለምግብነት የሚውሉትን እንጀራ እና ዳቦን መሸጥ ልክ ባለመሆኑ ለመከልከል መገደዳቸውን ተናግረዋል ሲል ነው ዘገባው የጠቀሰው።
እንጀራ እና ዳቦ መሸጥ ያለባቸው በምግብ ቤቶች፣ በዳቦ ቤተች እና በባልትና ወይም ለዚሁ መሻጫነት በተፈቀደ ቦታ ብቻ መሆኑንም በማንሳትም ያልተፈቀደላቸው ነጋዴዎችም ሲሸጡ ከተገኙ አስፈላጊው የእርምት እርምጃ እንደሚወሰድባቸው አስገንዝበዋል ሲል ገልጿል።
@TikvahethMagazine
👍 113🤣 45❤ 36👎 9🤔 5👏 2🤯 2
