ETHIO-MEREJA®
رفتن به کانال در Telegram
News & Media Company® USA : Washington Addisababa, Ethiopia🇪🇹 . Buy ads: https://telega.io/c/ethio_mereja . ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!! 👉 @ethio_merejabot ✔
نمایش بیشتر2025 سال در اعداد

110 266
مشترکین
-4624 ساعت
-2877 روز
-1 28930 روز
آرشیو پست ها
Photo unavailableShow in Telegram
#ቴምርፕሮፐርቲስ
⩩ 100% ለሚከፍሉ ከ30% እስከ 35% የሚደርስ ታላቅ እውነተኛ ቅናሽ አዘጋጅተናል።
⩩ እንዲሁም 40% ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ የ20% ቅናሽ አዘጋጅተናል።
📍 ሊሴ ገ/ማርያም
👉 66 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 7,590,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (759,000)
👉 71 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 8,165,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (816,500)
👉 132 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 14,520,000
ቅድመ ክፍያ 10% (1,452,000)
👉 146 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 16,060,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (1,606,000)
📍ሐይሌ ጋርመንት
ባለ 3 መኝታ
👉 139ካሬ ሙሉ ክፍያ = 14,590,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (1,459,000)
📍 አያት (ፈረስ ቤት)
👉 88 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 8,360,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (836,000)
👉 108 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 10,260,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (1,026,000)
👉 137 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 15,070,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (1,50,000)
⩩ ቀሪውን 90%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት።
ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን!
+251964439488
+251907232222
Telegram: https://t.me/OusmanTemer
WhatsApp: https://wa.me/251964439488
❤ 18
"አሁን መልሶ ግንባታ እንጀምራለን"- ዶናልድ ትራምፕ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በእስራኤል ምክር ቤት ንግግር ካደረጉ በኋላ ወደ ግብፅ አቅንተዋል።
በግብፅ፣ ሻርም ኤል-ሻይክ ከ20 በላይ የሚሆኑ የአገራት መሪዎች ተሰባስበው በቀጣዩ የጋዛ የሰላም ዕቅድ ላይ ተወያይተዋል።
ግብፅ፣ ኳታር፣ ቱርክ እና አሜሪካ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ጠባቂዎች ሆነው ፊርማቸውን አኑረዋል።
"አዲስ ውብ ቀን መጥቶልናል። አሁን ጊዜው መልሶ የመገንባት ነው" ብለዋል ትራምፕ።"ለመካከለኛው ምሥራቅ ታሪካዊ ቀን ነው" ሲሉም አክለዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በእስራኤል ምክር ቤት ንግግር ካደረጉ በኋላ ወደ ግብፅ አቅንተዋል።
በግብፅ፣ ሻርም ኤል-ሻይክ ከ20 በላይ የሚሆኑ የአገራት መሪዎች ተሰባስበው በቀጣዩ የጋዛ የሰላም ዕቅድ ላይ ተወያይተዋል።
ግብፅ፣ ኳታር፣ ቱርክ እና አሜሪካ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ጠባቂዎች ሆነው ፊርማቸውን አኑረዋል።
"አዲስ ውብ ቀን መጥቶልናል። አሁን ጊዜው መልሶ የመገንባት ነው" ብለዋል ትራምፕ።
"ለመካከለኛው ምሥራቅ ታሪካዊ ቀን ነው" ሲሉም አክለዋል።
ትራምፕ የሰላም ዕቅዱ ሁለተኛ ክፍል ተጀምሯል ብለዋል።
ትራምፕ በግብፁ ውይይት ላይ "ሁሉም ሰው ደስተኛ ነው። እዚህ ለመድረስ 3,000 ዓመታት መውሰዱን ታምናላችሁ? ብለዋል።
የግብፅ ፕሬዝዳንት አብደልፋታሕ አል-ሲሲ በአገራቸው ትልቁ የሆነውን 'ኦርደር ኦፍ ዘ ናይል' ሽልማት ለትራምፕ ሰጥተዋል።
አል-ሲሲ "አስከፊው ጊዜ ያከተመበት ታሪካዊ እርምጃ ነው" ሲሉ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ገልጸዋል።
❤ 50
Photo unavailableShow in Telegram
የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ድህነት መጠን በ2025 ዓ.ም. ወደ 43 በመቶ ከፍ ሊል እንደሚችል ገለጸ
የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ያለውን ድህነት በተመለከተ አዲስ ባወጣው ግምገማ፣ በአውሮፓውያን አቆጣጠር 2016 ዓ.ም 33 በመቶ የነበረው የድህነት መጠን፣ በተያዘው 2025 ዓ.ም ወደ 43 በመቶ ከፍ ሊል እንደሚችል አስታወቀ። ይህም የዓመታት ለውጥን ወደ ኋላ የሚቀለብስ ነው ብሏል።
የዓለም ባንክ እንደገለጸው፣ ኢትዮጵያ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ድህነትን በመቀነስ ረገድ ጉልህ እድገት ካሳየች በኋላ፣ ባለፉት ጥቂት አመታት የተከሰቱ ውስጣዊና ውጫዊ ተግዳሮቶች የኑሮ ደረጃ ላይ ተጽዕኖ አድርገዋል። እነዚህ ተግዳሮቶች የኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ የትግራይ ግጭት፣ ከፍተኛ ድርቅ፣ የጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) ዕድገት መቀዛቀዝ እና የዋጋ ግሽበት ናቸው ብሏል።
በዚህም ምክንያት፣ የድህነት መጠኑ እ.ኤ.አ. በ2016 ከነበረው 33 በመቶ በ2021 ወደ 39 በመቶ ከፍ ማለቱ ገልጿል። በቀጣይ ዓመታትም የበለጠ ይጨምራል ተብሎ እንደሚጠበቅ የዓለም ባንክ አስታውቋል።
የዋጋ ግሽበት በከተማ ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያደረሰ ሲሆን፣ አብዛኛው የገጠር ቤተሰቦችም ቢሆኑ ውስን በሆነ የገበያ ተሳትፎ ምክንያት ከምግብ ዋጋ ጭማሪ ተጠቃሚ አለመሆናቸውም ተገልጿል።
😁 49❤ 43😭 21👎 4🥰 2👍 1😱 1
Photo unavailableShow in Telegram
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በOBN HORN OF AFRICA TV ሊመጣ ነው
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን ለማስተላለፍ የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ (OBN) የሚያስችለውን የምስል መብት በጨረታ ማሸነፉ በነገው ዕለት ይፋ ይሆናል ።
ታዲያ በነገው ዕለትም ይፋዊ የስምምነት ፊርማ ከሊጉ አወዳዳሪ ጋር የሚፈራረሙ ሲሆን ከ ቅዳሜ ጥቅምት 8 ጀምሮ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን በቀጥታ እንደሚያደርስ ተገልጿል።
የቀጥታ ሰርጭቱ በOBN HORN OF AFRICA በአማርኛ ቋንቋ የሚተላለፍ ሲሆን እንደ አማራጭ በኦሮምኛ ቋንቋም ሊሰራጭ ስለመቻሉ ጣቢያችን ያገኘው መረጃ ያመላክታል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ያለፉትን አምስት አመታት DSTV ሲያሰትላልፍ እንድነበር ይታውሳል። የ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ጥቅምት 08/2018 እንደሚጀምር ይታወቃል።
❤ 49😁 31🤔 3
Photo unavailableShow in Telegram
#ቴምርፕሮፐርቲስ
⩩ 100% ለሚከፍሉ ከ30% እስከ 35% የሚደርስ ታላቅ እውነተኛ ቅናሽ አዘጋጅተናል።
⩩ እንዲሁም 40% ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ የ20% ቅናሽ አዘጋጅተናል።
📍 ሊሴ ገ/ማርያም
👉 66 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 7,590,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (759,000)
👉 71 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 8,165,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (816,500)
👉 132 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 14,520,000
ቅድመ ክፍያ 10% (1,452,000)
👉 146 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 16,060,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (1,606,000)
📍ሐይሌ ጋርመንት
ባለ 3 መኝታ
👉 139ካሬ ሙሉ ክፍያ = 14,590,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (1,459,000)
📍 አያት (ፈረስ ቤት)
👉 88 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 8,360,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (836,000)
👉 108 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 10,260,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (1,026,000)
👉 137 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 15,070,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (1,50,000)
⩩ ቀሪውን 90%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት።
ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን!
+251964439488
+251907232222
Telegram: https://t.me/OusmanTemer
WhatsApp: https://wa.me/251964439488
❤ 18👎 2🤔 1
አሳዛኝ ዜና!
በጨፋ_ሮቢት ከተማ በደረሰ አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ የ11ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ 23 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት ደረሰ
በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ጨፋ ሮቢት ከተማ ጃራ ድልድይ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በደረሰ አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ 23 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።
አደጋው የደረሰው ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ በመጓዝ ላይ የነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኢት 73290 የሆነ አውቶብስ እና ከደሴ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኢት 41157 ተሳቢ መኪና ጃራ ድልድይ አካባቢ በመጋጨታቸው ነው ተብሏል።
የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ፖሊስ መምሪያ ኀላፊ ዑመር መሐመድ በአደጋው እስካሁን የ11 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ገልፀው 23 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል።
በተጨማሪም በርካታ ሰዎች ቀላል ጉዳት እንዳጋጠማቸው ጠቅሰው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በአሁኑ ሰዓት በጨፋ ሮቢት ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላቸው መኾኑን ገልጸዋል።
የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችልም የገለፁት ኀላፊው አያይዘውም አሽከርካሪዎች በሚጓዙበት ወቅት በጥንቃቄ ሊያሽከረክሩ እንደሚገባ ማሳሰባቸውን አሚኮ ዘግቧል።
በኢትዮጵያ የተለያዩ አከባቢዎች የሚደርሱ የትራፊክ አደጋዎች መባባሳቸውን ዘገባዎች ያመለክታሉ፡፡ አደጋዎቹ የበርካታ ሰዎችን ህይወት የቀጠፉ ሲሆን አያሌ የአካል ጉዳት እና የንብረት ውድመት አስከትለዋል፡፡
😭 74❤ 50👍 4
Photo unavailableShow in Telegram
በትግራይ ክልል ዛሬ ቅዳሜ ጥቅምት 1፤ 2018 ምሽት፤ ለሁለት ጊዜያት የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የአሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ መስሪያ ቤት ገለጸ።
ከምሽቱ 1፡01 ላይ የደረሰው ርዕደ መሬት በሬክተር ስኬል 5.3 መለካቱን የገለጸው መስሪያ ቤቱ፤ ከ17 ደቂቃ በኋላ የተከሰተው በሬክተር ስኬል 5.3 መድረሱን አስታውቋል።
ከእነዚህ ክስተቶች አራት ሰዓት አስቀድሞ፤ በሬክተር ስኬል 4.2 የተላከ ሌላ የመሬት መንቀጥቀጥ ከመቐለ ከተማ በሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ 47 ኪሎ ሜትር ርቀት ባለ ቦታ ላይ መድረሱን መስሪያ ቤቱ መዝግቧል። ዛሬ ምሽት ከደረሱት ርዕደ መሬቶች የመጀመሪያው የተመዘገበው ከመቐለ ከተማ 58 ኪሎ ሜትር ርቀት ባለ ቦታ ላይ መሆኑንም ከተቋሙ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ሁለተኛው የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተው ከውቅሮ ከተማ 32 ኪሎ ሜትር በሚርቅ ቦታ ላይ እንደሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከሰቱ ርዕደ መሬቶችን የሚመዘግበው “ቮልካኖ ዲስከቨሪ” በድረ ገጹ ላይ አስፍሯል። ርዕደ መሬቱ ያስከተለው ንዝረት በሻጉባይ፣ በውቅሮ፣ ዶሎ፣ በዕዳጋ ሐሙስ እና በአዲግራት ከተሞች እንደተሰማ ድረ ገጹ ጠቁሟል።
የዛሬው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት፤ ክስተቱ ከተፈጠረበት 92 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው የአረርቲ ከተማ ጭምር እንደደረሰ “ቮልካኖ ዲስከቨሪ” ገልጿል። በትግራይ ክልል ርዕደ መሬት ሲያጋጥም ካለፈው የካቲት ወር በኋላ የአሁኑ የመጀመሪያው ነው።
ባለፈው ዓመት የካቲት ወር መጨረሻ ገደማ ከአዲግራት ከተማ 46 ኪሎ ሜትር በስተምስራቅ ርቀት ላይ በሚገኝ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ እንደነበር ይታወሳል። እኩለ ለሊት አቅራቢያ የተከሰተው ይኸው ርዕደ መሬት በሬክተር ስኬል 5.2 የተለካ ነበር።
Via ኢትዮጵያ ኢንሳይደር
T.me/ethio_mereja
❤ 57👍 7😢 3🤔 2👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
በሰሜን ወሎ ተካሔዶ በነበረው ውጊያ፤ በፋኖ ኀይሎች ተይዘው የነበሩትን የመንግሥት የፀጥታ አባላት መረከቡን ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ አስታወቀ!
በሰሜን ወሎ ዞን ዋና ከተማ ወልዲያ ዙሪያ ተካሔዶ በነበረው ውጊያ በፋኖ ኀይሎች ተይዘው የነበሩትን የመንግሥት የፀጥታ አባላት መረከቡን ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ አስታውቋል።
በመስከረም ወር አጋማሽ በዞኑ የተካሔደው “ድንገተኛ ውጊያ ከፍተኛ ጉዳትን ያስከተለ” እንደነበር ዓለም አቀፉ ድጋፍ ሰጪ ተቋም ገልጿል። ባለፉት 6 ቀናት ሁለት ቡድኖችን በወልዲያና በላሊበላ ከተማዎች በማስፈር የሰብአዊ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን ጉዳዩ ን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ላይ አስፍሯል።
በአንድ ሳምንት ውስጥ ለወልዲያ ሆስፒታል እንዲሁም በሙጃ እና ኩልመስክ አካባቢ ለሚገኙ የጤና ተቋማት የሕክምና መሳሪያዎችን ማበርከቱን አስታውቋል።ከመሳሪያዎቹ ውስጥ የቀዶ ጥገና ሕክምና ለመስጠት የሚያገለግሉ እንደሚገኝበት ተመላክቷል። በዚህም በውጊያው ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰባቸው ውስጥ 250 ለሚሆኑት የቀዶ ጥገና ሕክምና መስጠት እንደቻለ ተገልጿል።
ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ካደረገው የሕክምና ድጋፍ በተጨማሪ በፋኖ ኃይሎች ተይዘው የሚገኙ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎችን መጎብኘቱን ትላንት ባወጣው መግለጫ ላይ አመልክቷል። ኮሚቴው አክሎም ወታደሮቹን ከፋኖ ኃይሎች ተረክቦ ወልዲያ ከሚገኙ አባላቶቻቸው ጋር እንዲቀላቀሉ መደረጋቸውን አመልክቷል።
በላሊበላ ከተማ የሚገኘውን የድጋፍ ሰጪ ቡድን የሚመሩት ማርቲን ታልማን “በቅርብ ቀናት ውስጥ በሰሜን ወሎ በርካታ ሰዎች በውጊያው ተገድለዋል እንዲሁም ቆስለዋል” ሲሉ ተናግረዋል። ሆኖም የጤና ተቋማት “በተገደበ አቅም” የቆሰሉ ወታደሮችንና ሲቪሎችን እያከሙ መሆናቸውንም ቡድን መሪው አስታውቀዋል።
T.me/ethio_mereja
❤ 85👏 15🤔 5🥰 3
Photo unavailableShow in Telegram
የመንግሥት የዩኒቨርሲቲ ምደባ ሊቆም ነው፤ ሚኒስትሩ 'ጥራት የሌላቸውን በቢሊዮን አንደጉም' አሉ!!
የትምህርት ሚኒስትር ፤ በተማሪዎች መመረጥ ያልቻሉ ዩኒቨርሲቲዎችን መንግሥት ለሌሎች አገልግሎቶች ሊያውል ይችላል ሲል ማስጠንቀቂያ ሰጠ።
ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር) በቅርብ ዓመታት ውስጥ ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምደባ እንደሚያቆም ገልጸዋል። በምትኩም ተማሪዎች በራሳቸው በመረጡት ዩኒቨርሲቲ መማር እንደሚጀምሩ አስታውቀዋል።
ሚኒስትሩ ይህ ውሳኔ ምክንያታዊ መሆኑን ሲያስረዱ፣ በተማሪዎች ለማይመረጡ ዩኒቨርሲቲዎች መንግሥት በቢሊየን የሚቆጠር በጀት መመደቡ ተገቢ አይሆንም ብለዋል።
በተጨማሪም፣ "እንደከዚህ ቀደሙ አንዴ ዩኒቨርሲቲ ተከፍቷልና በዚሁ ይቀጥላል የሚባል አሰራርም እንደማይኖር" አስረድተዋል።
ይህ የተገለጸው የትምህርት ሚኒስቴር ከመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የቁልፍ ተግባራት የፊርማ ስነሥርዓት በዛሬው ዕለት ባካሄደበት ወቅት መሆኑን ኢፕድ ዘግቧል።
"በተማሪዎች መመረጥ ያልቻሉ ዩኒቨርሲቲዎችን መንግሥት ለሌሎች አገልግሎቶች ሊያውል እንደሚችል ጥርጥር አይግባችሁ" ያሉት ሚኒስትሩ ዩኒቨርሲቲዎች ተመራጭ ሆነው ለመቀጠል፣ የመማር ማስተማር ሥርዓታቸው ጥራት ያለው እንዲሆን መስራት እንደሚጠበቅባቸው ማሳሰቢያ ተሰጥቷቸዋል።#CapitalNews
❤ 54👍 44😁 15🤔 3🤯 1
Photo unavailableShow in Telegram
እስራኤል የጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነትን አፀደቀች
የእስራኤል የደህንነት ካቢኔ የመጀመሪያውን ዙር የጋዛ ተኩስ አቁም ስምምነትን በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኒታንያሁ ጽ/ቤት እንዳስታወቀው÷ በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቀረበው የተኩስ አቁም ስምምነት ቀሪ የእስራኤል ታጋቾችን የሚያስለቅቅና ዘላቂ ሰላምን የሚያመጣ እንደሆነ ታምኖበታል፡፡ በስምምነቱ መሰረት እስራኤል 53 በመቶ ከሚሆነው የጋዛ ክፍል ጦሯን የምታስወጣ ሲሆን፥ ሀማስ በበኩሉ 20 የእስራኤል ታጋቾችን በ72 ሰዓታት ውስጥ የሚለቅ ይሆናል፡፡
በተመሳሳይ እስራኤል 250 እስረኞችንና በጋዛው ዘመቻ በቁጥጥር ስር ያዋለቻቸውን ከ1 ሺህ 700 በላይ ሰዎች እንደምትለቅ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
የሀማስ ከፍተኛ ባለስልጣን ኻሊል አል ሀያ በበኩላቸው÷ ዶናልድ ትራምፕ ያቀረቡት የተኩስ አቁም ስምምነት እቅድ ዘላቂ ሰላምን የሚያመጣ ነው ብለዋል፡፡ ታጣቂ ቡድኑ ለትራምፕ የተኩስ አቁም እቅድ ፈጣን አዎንታዊ ምላሽ መስጠቱን ገልጸው፥ ስምምነቱ ያለምንም ችግር ተግባራዊ እንዲደረግ ከዋሽንግተን መተማመኛ አግኝተናል ነው ያሉት፡፡
ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ ሀማስ በጋዛ ከሚንቀሳቀሱ ሌሎች ኃይሎች ጋር በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡የእስራኤል እና ሃማስ የተኩስ አቁም ስምምነትን ተከትሎ የተባበሩት መንግስታት ምግብ፣መድሀኒት እና ነዳጅ ወደ ጋዛ ለማጓጓዝ ዝግጁ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡
❤ 60👏 21👍 6😱 2👎 1
Photo unavailableShow in Telegram
የሥጋና የአትክልት ምርቶችን ከነገ ጀምሮ ወደ አፍሪካ አገሮች መላክ ሊጀመር ነው
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነት መሠረት ወደ ውጭ የሚላኩ የሥጋ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን ከነገ መስከረም 29 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የማጓጓዝ አገልግሎት ሊጀመር መሆኑ ተገለጸ፡፡
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ማክሰኞ መስከረም 27 ቀን 2018 ዓ.ም. የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነት ግብይት ማስጀመሪያ ፕሮግራምን አስመልክቶ፣ መግለጫ ሲሰጥ እንደተናገረው ነገ ሐሙስ መስከረም 29 ቀን 2018 ዓ.ም. በአፍሪካ ነፃ ንግድ ስምምነት መሠረት ለሦስት የአፍሪካ አገሮች ለመጀመሪያ ጊዜ የሥጋ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ፣ እንዲሁም የጥራጥሬ ምርቶች ለመላክ መዘጋጀታቸው አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድም ምርቶቹን ለማጓጓዝ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን መግለጫውን የሰጡት የንግድ ትስስርና ወጪ ንግድ ፕሮሞሽን ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ ወ/ሮ ያስሚን ውሀብረቢ አስታውቀዋል፡፡ሚኒስቴሩ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በስምምነቱ መሠረት ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች ጋር የሚደረግ የንግድ ልውውጥን አስመልክቶ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን፣ ለማስጀመሪያ ሥራው ብቻ ሳይሆን የወጪ ንግድ ከሚከናወንባቸው መካከል አንዱ የአውሮፕላን የጭነት ትራንስፖርት ስለሆነ፣ በቀጣይም አብሮ ለመሥራት የሚያስችል ዝግት መደረጉን ገልጸዋል።
👎 45❤ 38🤔 4😭 2
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ግብይት ተጀመረ
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ግብይት ሥርዓት በዛሬው ዕለት ተጀምሯል፡፡
በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ በም/ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) እና የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ተገኝተዋል፡፡
ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ግብይት የኢትዮጵያን ወጪ ንግድ ከማሳለጥ ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡
ከዚህ ባለፈም ለኢትዮጵያን ንግድ ዘርፍ መስፈንጠር ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት አስገንዝበዋል፡፡
ግብይቱ መጀመሩን አስመልክቶ ሥጋ፣ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም ቡና፣ የጥራጥሬ ምርቶችና የቅባት እህሎች በኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና በየብስ ትራንስፖርት አማካይነት ወደ ኬንያ፣ ሶማሊያ እና ደቡብ አፍሪካ ተልከዋል፡፡
❤ 58😢 3🥰 1
Photo unavailableShow in Telegram
#ቴምርፕሮፐርቲስ
⩩ 100% ለሚከፍሉ ከ30% እስከ 35% የሚደርስ ታላቅ እውነተኛ ቅናሽ አዘጋጅተናል።
⩩ እንዲሁም 40% ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ የ20% ቅናሽ አዘጋጅተናል።
📍 ሊሴ ገ/ማርያም
👉 66 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 7,590,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (759,000)
👉 71 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 8,165,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (816,500)
👉 132 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 14,520,000
ቅድመ ክፍያ 10% (1,452,000)
👉 146 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 16,060,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (1,606,000)
📍ሐይሌ ጋርመንት
ባለ 3 መኝታ
👉 139ካሬ ሙሉ ክፍያ = 14,590,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (1,459,000)
📍 አያት (ፈረስ ቤት)
👉 88 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 8,360,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (836,000)
👉 108 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 10,260,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (1,026,000)
👉 137 ካሬ ሙሉ ክፍያ = 15,070,000
ቅድመ ክፍያ = 10% (1,50,000)
⩩ ቀሪውን 90%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት።
ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን!
+251964439488
+251907232222
Telegram: https://t.me/OusmanTemer
WhatsApp: https://wa.me/251964439488
❤ 24😁 1
Photo unavailableShow in Telegram
ክርስቲያኖ ሮናልዶ የመጀመሪያው የእግር ኳስ ቢሊየነር ሆነ
ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ የመጀመሪያው የእግር ኳስ ቢሊየነር ሆኗል፡፡
የአምስት ጊዜ የባሎንዶር አሸናፊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ የተጣራ የሀብት መጠን 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር መድረሱን የብሉምበርግ ዘገባ አመላክቷል፡፡
ተጨዋቹ ከሳዑዲው ክለብ አል ናስር የሚያገኘው 300 ሚሊየን ፓውንድ ክፍያ እና ከሌሎች አጋሮች የሚያገኘው ገቢ ያለውን የሀብት መጠን ከፍ እንዳደረገለትም ነው የተገለጸው፡፡
በዚህም ክርስቲያኖ ሮናልዶ በብሉምበርግ የቢሊየነሮች ደረጃ ውስጥ መካተት የቻለ የመጀመሪያው የእግር ኳስ ተጨዋች መሆን ችሏል።
ሮናልዶ ከፖርቹጋል እግር ኳስ ፌዴሬሽን የምንጊዜም ምርጡ ተጨዋች በመባል በትናንትናው ዕለት የክብር ሽልማት እንደተሰጠው ይታወሳል፡፡
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ
❤ 66👏 47🥰 7😁 6
አዲሱ የተሽከርካሪ ሰሌዳ መለያ ቁጥር ይፋ ሆነ!!
የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አዲሱን የተሽከርካሪ ሰሌዳ መለያ ቁጥር ይፋ አድርጓል፡፡
ጉዳዩን አስመልክቶ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በመግለጫቸውም ሚኒስቴሩ አዲስ የተሽከርካሪዎች የመለያ ቁጥር ሰሌዳ አይነቶችና ምልክቶች መወሰኛና የአገልግሎት አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 1050/2017 ማዘጋጀቱን ጠቅሰዋል፡፡
በመመሪያው መሰረትም የተሽከርካሪ ሰሌዳ መለያ ቁጥር በአዲስ እንደሚተካ ነው ሚኒስትሩ የገለጹት፡፡
ከዚህ ቀደም የነበረው የተሽከርካሪ መለያ ቁጥር ሰሌዳ አመራረትና አሰረጫጨት የአሰራር ክፍተት እና የሃብት ብክነት ይስተዋልበት ነበር ብለዋል፡፡
በሀገር አቀፍ ደረጃ ነባሩ የተሽከርካሪ መለያ ሰሌዳ ቁጥር በአዲስ መተካቱን ጠቁመው÷ አዲሱ ሰሌዳ ከዚህ ቀደም የነበሩ የአሰራር ችግሮችን እንዲቀርፍ የአሰራር ሥርዓት የተዘረጋለት መሆኑን አስረድተዋል፡፡
አዲሱ የሰሌዳ ቁጥር ኢትዮጵያን የሚገልጹ መለያዎችን የያዘ እንዲሁም ዓለም ዓቀፍ መስፈርቱን የተከተለ ሲሆን÷ 50 ሺህ ታርጋዎችም በማሳያነት ተዘጋጅተዋል፡፡
የዲጂታል ሥራው ተጠናቅቆ የቅየራ ሒደቱ በቅርቡ ወደስራ እንደሚገባ የተናገሩት ሚኒስትሩ÷ በ2018 ዓ.ም ሙሉ በሙሉ ቀይሮ ለመጨረስ ዝግጅት መደረጉን አጽንኦት ሰጥተዋል፡
❤ 33👏 1
#MoE የዩኒቨርስቲ ምደባ ይፋ ሆነ።
በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ወስደው የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ እና ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) ትምህርታቸውን ለሚከታተሉ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ መደረጉን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።
ተማሪዎች ከአሁን ሰዓት ጀምሮ፦
Website: https://student.ethernet.edu.et
Telegram bot: @moestudentbot አማራጮች ምደባቸውን ማየት እንደሚችሉ ተገልጿል።
የRemedial ፕሮግራም ምደባ በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።
❤ 24👍 6👎 1
በጎፋ ዞን ተከስቶ በነበረው የመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎጂ ዜጎች የተሰበሰበ ከ60 ሚሊየን ብር በላይ ለመዝረፍ የሞከሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ ሐምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ሰለባ ለሆኑ ዜጎች የተሰበሰበ ከ60 ሚሊየን ብር በላይ ለመዝረፍ የሞከሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የዞኑ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አስታወቀ፡፡
የጎፋ ዞን መንግሥት ኮሙኒኬሽን መስከረም 27 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ላይ ባወጣው መግለጫ ሐምሌ 15/2016 ዓ/ም በተከሰተው እጅግ አስከፊ በሆነው መሬት መንሸራተት አደጋ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወገኖች ህይወታቸው ማለፉን አስታውሷል።
አደጋውን ተከትሎም ከሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ያሉ ወገኖቻችን፣ እንደሁም የተለያዩ አካላትና መንግስታት በዓይነትና በገንዘብ ድጋፍ በማድረግ የጉዳቱ ሰለባ ለሆኑ ወገኖቻችን በአግባቡ እንዲደርሳቸው የዞኑ መንግስት ተፈፃሚነቱን በቅረበት እየተከታተለ መቆየቱ የሚታወቅ ነው ብሏል መግለጫው፡፡
ሆኖም "የአገር ወስጥና የአለም አቀፍ ማህበረሰብ ለተጎጅ ሕብረተሰብ ክፈሎች የለገሱትን ድጋፍ ወደ ኪሳችን ገብቶ ካልበለፀግን በሚል አሰተሳሰብ የተጠመዱ አካላት ይህንን አስነዋሪና ስብዕና የጎደለውን ተግባር ለመፈፀም የወጠኑት ውጥን አልተሳካም" ብሏል።
❤ 27🤔 10
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ባወጣው መግለጫ፣ በአማራ ክልል ያለው የትጥቅ ትግል በህዝቡ ላይ ከባድ ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት እያስከተለ መሆኑን ገልጾ፣ የታጠቁ ኃይሎች ወደ ድርድርና ሰላማዊ መድረክ እንዲመጡ አጥብቆ ጠይቋል። ፓርቲው፣ ግጭቱ የሻዕቢያና የህወሓትን ስውር ዓላማ እያገለገለ መሆኑንም ከሷል።
የአብን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ወቅታዊ ሁኔታውን መገምገሙን ባስታወቀበት መግለጫው፣ በክልሉ ያለው የጸጥታ ችግር ተባብሶ ግድያ፣ እገታና ዘረፋ መስፋፋቱን አመልክቷል። "በግብታዊነትና በጠላት መንገድ መሪነት የተገባበት የትጥቅ እንቅስቃሴ" ሲል የጠራው ይህ ሁኔታ፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታ ውጪ እንዳደረገ፣ የንግዱ ማህበረሰብ ንብረቱን እንደተዘረፈና ታማሚዎች በህክምና እጦት ለሞት እንደተዳረጉ ፓርቲው ገልጿል።
🔴 ለችግሩ መባባስ ተጠያቂ ናቸው ያላቸው አካላት
አብን በመግለጫው፣ ለግጭቱ መቀጠልና ለህዝቡ መከራ በርካታ አካላትን ተጠያቂ አድርጓል። ከእነዚህም መካከል፦
* ራሳቸውን "የህዝብ ብቸኛ ወኪል" አድርገው የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦችና ቡድኖች፣
* በአማራ ስም የተደራጁ የዲያስፖራ ማህበራት፣
* የጦርነት ኢኮኖሚ ተዋናዮችና በሙስና የተዘፈቁ አመራሮች፣
* ሻዕቢያና ህወሓት ግጭቱን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እየተሳተፉ መሆናቸውን ጠቅሷል።
"ሕዝባችን የእነዚህ ጠላቶች የትብብር ድር መስሪያ ሆኗል" ያለው መግለጫው፣ ይህ ሁኔታ የአማራን ህዝብ አንድነት በማዳከም ለከፋ የደህንነት ስጋትና የህልውና አደጋ እንዳጋለጠው አስረድቷል።
🔴 የቀረቡ የመፍትሄ አቅጣጫዎችና ጥሪዎች
ፓርቲው፣ የጦርነት ፖለቲካ ዘላቂ መፍትሄ እንደማያመጣ በማመን፣ ለተለያዩ አካላት ጥሪ አቅርቧል።
* ለታጠቁ ኃይሎች፦ አሁን ያለው የትጥቅ እንቅስቃሴ ህዝቡን እየጎዳና ለታሪካዊ ጠላቶች በር እየከፈተ መሆኑን ተገንዝበው፣ "ወደ ድርድርና ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ መድረክ" እንዲመጡ አሳስቧል።
* ለፌዴራል መንግስት፦ የህዝብን ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ ኃላፊነቱን እንዲወጣ፣ ታጣቂ ቡድኖች ወደ ድርድር እንዲመጡ የሚያበረታታ የፖለቲካ ምህዳር እንዲፈጥርና "ሁለት ቢላ በሚበሉ" የፖለቲካና የጸጥታ አመራሮች ላይ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቋል።
* ለክልሉ መንግስት፦ በውስጡ ያሉትን "ከወያኔያዊ አስተሳሰብ ነጻ ያልወጡና የጎጥ ፖለቲካ ሰለባ የሆኑ" አካላትን ለይቶ በህግ ተጠያቂ እንዲያደርግ አጥብቆ ጠይቋል።
* ለአማራ ህዝብና ለመላው ኢትዮጵያውያን፦ የአማራ ህዝብ በስሙ የሚነገድበትን "የፖለቲካ ንግድና የባንዳነት ተግባር" በቃኝ እንዲልና ሁሉም ኢትዮጵያውያን ለሰላም የሚደረገውን ጥሪ እንዲደግፉ ጥሪ አቅርቧል።
በማጠቃለያው፣ የአብን መግለጫ በክልሉ ያለው የትጥቅ እንቅስቃሴ ከአሁን በኋላ የህዝቡን ጥቅም እንደማያስከብርና ብቸኛው መፍትሄ ሰላማዊ ውይይት መሆኑን በማስመር ላይ ያተኮረ ነው።
❤ 38👎 20😁 4🤔 2
Photo unavailableShow in Telegram
ቤት ፈላጊዎች በራሳቸው አካውንት ገንዘባቸውን ቆጥበው ቤት እንዲወስዱ ይደረጋል ተባለ ፡፡
ቤት ፈላጊዎች በግል የባንክ አካውንታቸው ገንዘባቸውን ቆጥበው የሚፈልጉት አይነት ቤት ተሰርቶላቸው የሚወስዱበት አዲስ ፕሮጀክት ይፋ ሆኗል ያሉት ኮምፓስ ፕሮፐርቲስ እና ጎህ የቤቶች ባንክ ናቸው።
ዛሬ ይፋ የተደረገው አዲስ ፕሮጀክት በሌላው አለም የሪል ስቴት ዘርፍ በስፋት ስራ ላይ የዋለ በሃገራችን ግን እስካሁን ያልተተገበረ አሰራር ነው ሲሉ የኮምፓስ ፕሮፐርቲስ የስራ ሃላፊዎች ገልፀዋል::
ቤት ፈላጊው ቤቱ ተጠናቆለት ካርታ ሲረከብ ብቻ ገንዘቡን ለቤት ገንቢው ያስተላልፋል በተባለለት በዚህ ፕሮጀክት ቤት መግዛት የሚፈልግ ግለሰብ በቅድሚያ 500 ሺ ብርተቀማጭ በማስገባትና በሚፈልገው የቤት ካሬ መሰረት በየወሩ በራሱ ስም በጎህ ቤቶች ባንክ ደብተር ከፍቶ መቆጠብ እንደሚጠበቅበት ተገልጿል፡፡ ለቁጠባውም 15% ወለድ ይታሰብለታል ተብሏል፡፡
በዚህ ሃደት ውስጥ ግን ገንዘቡ በራሱ በግለሰቡ አካውንት የሚቀመጥ እንጂ ወደ ኮምፓስም ሆነ ወደ ጎህ አካውንት የሚገባ ምንም አይነት ገንዘብ አይኖርም ሲሉ አመራሮቹ ኣሳውቀዋል። ቤት ገዢዉ የቆጠበውን ገንዘብ ማውጣት ከፈለገ ለባንኩ ቀድሞ በማሳወቅ ማዉጣት እንዲችል አሠራር ተቀምጧል ሲሉም አከለዋል::
❤ 57👍 24😁 7👏 4🤔 3
