Ayu Zehabesha-Official አዩ ዘሀበሻ
رفتن به کانال در Telegram
2025 سال در اعداد

262 883
مشترکین
-60124 ساعت
+7 0077 روز
+7 81230 روز
آرشیو پست ها
Photo unavailableShow in Telegram
በዲጂታል የክፍያ ተቋማት ላይ ተጥሎ የነበረው የባንክ እገዳ በከፊል ተነሳ‼️
- ከፍተኛ የንግድ ድርጅቶች ኃላፊዎች አሁንም በቁጥጥር ሥር ናቸው
የፌዴራል ባለሥልጣናት በዲጂታል ፋይናንስ ዘርፍ ላይ በወሰዱት እርምጃ ታግደው የነበሩ የባንክ ሂሳቦችን በከፊል አንስተዋል።
የፍትህ ሚኒስቴር ታኅሣሥ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ባስተላለፈው ትዕዛዝ፣ የያጉት ፔይ (YagoutPay) ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተሾመ ዓለማየሁን ጨምሮ የ50 ግለሰቦች የባንክ ሂሳቦች እንዲንቀሳቀሱ አዟል። እነዚህ የባንክ ሂሳቦች ከሦስት ሳምንታት በፊት፣ ህዳር 23 ቀን፣ በዘርፉ የታየ የፋይናንስ ብልሹ አሰራርን ለመመርመር በሚል ታግደው የቆዩ ናቸው።
በተጨማሪም፣ ለዘጠኝ ቀናት የባንክ ሂሳቦቻቸው ተገድበው የነበሩ 10 የዲጂታል ክፍያ (Gateway) ኩባንያዎች እገዳው ተነስቶላቸዋል።
የሚኒስቴሩ የሀብት ማስመለስ መምሪያ ዋና ዳይሬክተር ፀጋ ዋቅጅራ ውሳኔውን ለሁሉም ባንኮች በይፋዊ ደብዳቤ አሳውቀዋል።
እገዳው የተነሳላቸው የክፍያ ተቋማት አሪፍ ፔይ (ArifPay Financial Technologies): አዲስ ፔይ (AddisPay Financial Technologies): ፈናን ፔይ (FenanPay Solutions): ላኪ ፔይ (LakiPay Financial Technologies):
ስታር ፔይ (StarPay Financial Services): ያጉት ፔይ (YagoutPay)
ሳንቲም ፔይ (SantimPay Financial Technologies): ካቻ (Kacha Financial Technology): እና ሲናን ፔይ (Sinan Pay Solutions) ናቸው::
ምንም እንኳን የኩባንያዎቹ የባንክ ሂሳቦች ቢለቀቁም፣ የምርመራው ሂደት ግን ተጠናክሮ ቀጥሏል። የሳንቲም ፔይ፣ የቻፓ ፔይ (Chapa Pay) እና የአሪፍ ፔይ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አሁንም በፌዴራል ፖሊስ ቁጥጥር ሥር የሚገኙ ሲሆን፣ “ከፍተኛ የፋይናንስ ሕገ-ወጥነት” ተጠርጥረው ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው።
ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንደጠቆሙት፣ የምርመራው ዋነኛ ትኩረት የግብር ስወራ እና ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር (Money Laundering) ላይ ነው። የፌዴራል ባለሥልጣናት በፍጥነት እያደገ የመጣውን የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ጥብቅ ቁጥጥር ለማድረግና ሕጋዊ መስመር ለማስያዝ ቅድሚያ ሰጥተው መስራት እንደሚፈልጉ ይናገራሉ።
#አዩዘሀበሻ
=========≠============
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
❤ 85🙏 4👍 3🥰 3
00:59
Video unavailableShow in Telegram
ይህን ሰምተዋል Dema Hope Real Estate ዴማ ሆፕሰ ሪል እሰቴት በመሀል አዲሰ አበባ መገናኛ ሲግናል ,ቦሌ መድሀኒአለም መገናኛ ሾላ እና ቦሌ 24 ሙሉ ያለቁ ጠዋት ገዝተው ከሰአት የሚገቡበት እና ቦሌ መድሀኒአለም ኤድናሞል ጋር ግንባታቸው 90% የደርሱ እጅግ ቅንጡ የመኖርያ አፓርታማ ከባለ 1 መኝታ እሰከ 4 መኝታ ድረሰ እና የንግድ ሱቆች ከግራውንድ ጀምሮ ሸያጭ ላይ ነን በተጨማሪ የመኖርያ አፓርታርትመንቶቻችን እና የንግድ ሱቆቹ ዛሬ ገዝተው ዛሬ የካርታ ሰም ማዞር ይችላሉ ማየት ማመን ነው ፈጥነው ይደውሉ ።Dema Hope Real Estate ቅንጦት ይገባዎታል ። ለበለጠ መረጃ
0912323064
0921305626
2.15 MB
❤ 27👍 5🥰 2
Photo unavailableShow in Telegram
የሰዓት ገደብ‼️
የጋምቤላ ክልላዊ መንግሥት፣ ጋምቤላ ከተማን ጨምሮ የጸጥታ ችግር ባለባቸዉ አካባቢዎች ከዛሬ ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12:00 ሰዓት ድረስ የሚቆይ ሰዓት እላፊ ላልተወሰነ ጊዜ መጣሉን አስታወቀ።
የክልሉ መንግሥት ዛሬ ምሽት 11:30 ገደማ ባወጣው መግለጫ፣ ለሥራ ከተመደቡ የጸጥታ ኃይሎች በስተቀር ሰዎችም ኾኑ ተሽከርካሪዎች በሰዓት እላፊው ወቅት እንዳይንቀሳቀሱ ከልክሏል።
ከጸጥታ አካላት ውጪ በማናቸውም ቦታ ጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ክልክል መሆኑንም የክልሉ መንግሥት አስታውቋል። የክልሉ መንግሥት የሰዓት እላፊውን ያወጀው፣ በክልሉ በተለይም በጋምቤላ ከተማ እንዲኹም በጋምቤላ እና ኢታንግ ወረዳዎች ከኅዳር 28 ጀምሮ በተከሠቱ ግጭቶች እና የጸጥታ መደፍረስ ሳቢያ የሰዎች ሕይወት መጥፋቱንና የአካል ጉዳት መድረሱን ተከትሎ ነው።
በክልሉ ግጭት የተቀሠቀሠው፣ የጋምቤላ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኡመድ ኡጁሉ በታጠቀ ግለሰብ ከተገደሉ በኋላ ነበር።
የክልሉ መንግሥት በግጭቱ እስካሁን የስንት ሰዎች ሕይወት እንዳለፈ እና ከግጭቱ ጋር በተያያዘ ስንት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር እንዳዋለ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ይፋ አላደረገም። [ዋዜማ]
❤ 99👍 19🔥 9🙏 6💔 6🕊 1
Photo unavailableShow in Telegram
"2025 አስቸጋሪ ዓመት ነበር፤ ነገር ግን አትጨነቁ፣ ምክንያቱም የሚቀጥለው ዓመት ከዚህ የባሰ የከፋ ይሆናል" ሲሉ የጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ሜሎኒ ተናገሩ።
እሳቸው ይህንን መግለጫ የሰጡት በገና በዓል አከባበር ሥነ-ሥርዓት ላይ ለመንግሥት መስሪያ ቤት (ፓላዞ ቺጊ) ሠራተኞች ባደረጉት ንግግር ነው።
=========≠============
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
🥱 74❤ 35👌 28😢 15🔥 8🙈 7🥰 6👏 3
Photo unavailableShow in Telegram
#ቴምርሪልስቴት ሱቅ ሽያጭ የተንጣለለ ዘመናዊ ሞል በቃሊቲ(ገላን)
‼️ቃሊቲ ሱቅ ሽያጭ
👉2.5ሚሊዮን 23.5ካሬ ቅድመ ክፍያ500,000ብር 4ተኛ
👉2.6ሚሊዮን 26.8ካሬ ቅድመ ክፍያ 600,000ብር 3ተኛ
👉2.8ሚሊዮን 26.8ካሬ ቅድመ ክፍያ 800,000 ብር 2ተኛ
👉3.2ሚሊዮን 26.4ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 1ኛ
👉4.5ሚሊዮን 24ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን ግራውንድ
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
👇👇👇👇👇👇
+251939770177
+251996856273
https://t.me/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177
Telegram :@KalTemerRealEstate
❤ 12👍 1🥰 1
Photo unavailableShow in Telegram
አፋር በኤርትራ መንግሥት የዘር ማጥፋት እየተፈፀመበት ነው:-የቀይ ባሕር አፋር ዲሞክራሲያዊ ድርጅት‼️
ድርጅቱ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ፤ የኤርትራ መንግሥት ከ1993 ዓ.ም ጀምሮ በኤርትራ ደናክል አካባቢ የሚኖሩ የቀይ ባሕር አፋሮች ላይ መንግሥታዊ የዘር ማጥፋት የመብት ጥሰት እየፈፀመ ቆይቷል ብሏል።
የድርጅቱ ሊቀመንበር ኢብራሂም ሀሩን በመግለጫው እንደተናገሩት፤ የኤርትራ መንግሥት በአፋሮች ላይ ከሕግና ከፍርድ ውጭ ግድያዎችና ዘር ተኮር ጭፍጨፋ፣ ያለፍርድ ማሰርና ማሰቃየት፣ መሰወር፣ የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ በግዳጅ ማፈናቀል እየፈፀመ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በቋንቋችን እንዳንማር በመከልከል፣ መስጊዶችን በመዝጋት እና የቁርአን ትምህርትን በመከልከል የቀይ ባሕር አፋር ሕዝብን ባህልና ማንነት በማጥፋት ላይ መሆኑንም ተናግረዋል።
ከቀይ ባሕር አሳ ማጥመድ መከልከልን ጨምሮ ኢኮኖሚያዊ መብቶችን በመጣስ የሕልውና አደጋ ውስጥ አስገብቶናል ሲሉም፤ የድርጅቱ ሊቀመንበር ኢብራሂም ሀሩን አስረድተዋል።
በዚህ ምክንያት በርካታ የቀይ ባሕር አፋሮች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው እየተሰደዱ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የኤርትራ መንግሥት ዓላማ የቀይ ባሕር አፋሮችን ከቀይ ባሕር ማስለቀቅ መሆኑንም ሊቀመንበሩ ተናግረዋል።
ድርጅቱ የኤርትራ መንግሥት በኤርትራ አፋሮች ላይ እያደረሰ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት የተመለከተ ክስ ለአፍሪካ የሰብዓዊ እና ሕዝባዊ መብቶች ኮሚሽን ማቅረቡን ገልጿል፡፡
❤ 130🥱 17👍 11😢 5🙊 5😎 4🔥 3🙏 2💔 2
Photo unavailableShow in Telegram
📱 በኢትዮጵያ ትልቁ እና ታማኙ የሊንኪደን አካውንት ተከራይ Bussines Team አሁንም በርካታ አካውንቶችን ተከራይቶ ለቢዝነስ አላማ ማስተዳደር ይፈልጋል።
📱 ከፍተኛ ኮኔክሽን ወይም ረጅም አመት ያስቆጠሩ አካውንቶች የተሻለ ክፍያ ያገኛሉ፡፡
የእርስዎን አካውንት ደህንነት እንደራሳችን አካውንት አድርገን እንጠብቀዋለን።
☎️ ስልክ ፦ 0923526669
💬 በውስጥ መስመር ➡️ ያግኙን
@Bussinessteam23
🔵 የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ➡️
@linkBussinessteam
❤ 12👍 3🔥 3👌 3👏 1
Update‼️
ሰላሌ የጠንቋይ እና የመተተኛ ሀገር ነው በሚል በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው ቪዲዮ ከፍተኛ ቅሬታ መፍጠሩን ተከትሎ ሴቷ በህግ ቁጥጥር ስር የዋለች ሲሆን ነብይ ሄኖክ ግርማን ለመያዝ እየተሰራ እንደሚገኝ ታውቋል።
አዩዘሀበሻ
=========≠============
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
4.71 KB
👏 190❤ 62🙏 23🥱 18👍 12🔥 12😢 8😎 6🤷♂ 5🙊 2🎉 1
🖥️ አዲስ ቲቪ መግዛት አይጠበቅቦትም!
🎄ለገና ቤቶ ላይ ሚጨምሩት በረከት🎄
🎁አሁን በቲቪያችሁ YouTube ሆነ Netflix መጠቀም ፤ ካሻዎም የፈለጎትን ጌም አዉርደዉ መጫወት ይችላሉ 👏
🎁 በማንኛዉንም አይነት ቲቪ ( ቦርጫሙም ሆነ ፍላት) አንዴ ይሄንን ዕቃ ገዝተዉ ካለምንም ወረሀዊ ክፍያ ከስራ መልስ በቤትዎ በመረጡት የዩቱብ ሾዉ ፈታ ይበሉ👍
📍Storage: 128gb
📍Ram 8GB
📍4k resolution
✅ያሉበት ድረስ ባለሙያ እንልካለን✅
🚚አዲስ አበባ ላይ ፈጣንና በ 40 ደቂቃ ዉስጥ የሚደርስ ነፃ ዴሊቨሪ ሲኖረን ክፍለ ሀገር ላላችሁ በፖስታ ቤት እንልካለን።
ዋጋ 💸4999 ብር ብቻ
Inbox 📨 @Dubaitera_shop
Call📞 0990050575
📞0990050575
#ብልሆች ከኛ በማዘዝ ደስታን እያጣጣሙ ነዉ እርሶስ🫵
🛍ሌሎች ዕቃዎችን ለማየት
👉@Dubai_Tera2 ን ይቀላቀሉ!
12.95 MB
❤ 22👍 2🥰 1😢 1💯 1
Photo unavailableShow in Telegram
የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ አገልግሎት ለማግኘት የሚያመለክቱ ተገልጋዮች የሚከተሉትን ቅድመ-ሁኔታዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል‼️
1. በጀርባው ላይ የኮሌጁ ኃላፊና ሬጅስትራር ፊርማና ማህተም ያለበት ኦሪጅናል/temporary / ዲግሪ፤
2. በጀርባው ላይ የኮሌጁ ኃላፊና ሬጅስትራር ፊርማና ማህተም ያለበት ኦሪጅናል ትራንስክሪፕት/Student Copy/፤
3. ዲግሪውን ለመማር በመግቢያነት የተያዘ ኦሪጅናል ዲፕሎማ ወይም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሰርተፊኬት፤
4. ዲግሪውን ለመማር በመግቢያነት የተያዘው የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ከሆነ በሀገር አቀፍ የት/ት ምዘናና ፈተናዎች አገልገሎት ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ ፤
5. ዲግሪውን ለመማር በመግቢያነት የተያዘው ዲፕሎማ ከሆነ ዲፕሎማው በተገኘበት ክልል የቴክኒክና ሙያ ኤጀንሲ ወይም የዞን/የከተማ መስተዳደር የሥራና ስልጠና ቢሮ ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ የደረጃ 4 ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት (COC) ፤
6. የዲግሪ መግቢያው ከውጭ በተገኘ የትምህርት ማስረጃ ከሆነ ከባለስልጣኑ የተገኘ የአቻ ግመታ ደብዳቤ፤
7. የሁለተኛ/የማስተርስ/ ዲግሪን ለማረጋገጥ ከሆነ ደግሞ በቅድሚያ የመጀመሪያው ዲግሪ ከላይ በተገለፀው መንገድ መረጋገጥ ይኖርበታል፤
8. የስም ለውጥ ካለ የፍርድ ቤት ውሳኔ የተላፈበት ማስረጃ፤
9. የማመልከቻ ክፍያ በኤሌክትሮኒክ ክፍያ በቴሌ ብር እና በሲኢቢ ብር ፤
10. ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የፋይዳ ልዩ ቁጥር FIN፤
11. ስካን (Scan) የተደረገ ሶስት በአራት (3x4) ጉርድ ፎቶግራፍ እና
12. ከላይ የተጠቀሱትን ሁሉም ማስረጃዎች አንድ አንድ ስካን (Scan) በማድረግ ባሉበት ሆነው በበይነ መረብ https://neta.gov.et ማስፈንጠሪያን በመጠቀም ማመልከት ይችላሉ፤
በተጨማሪም ቀጠሮ አስይዘው በአካል ሲመጡ በባለጉዳዩ ወይም ሕጋዊ የውክልና ሰነድ ባላቸው ተወካዮች አማካኝት ሁሉንም የትምህርት ማስረጃ ዋናውን ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
=========≠============
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
❤ 105👍 16😭 9🔥 4🙏 4🥱 2😢 1🎉 1
🇷🇺 ከዛሬ ጀምሮ ይህ ተቻለ።
የሩሲያን ከውስጥ የሚያሳይ ቻናላችን አሁን በአማርኛ ተጀምሯል።
🇷🇺🤝🇪🇹ሩሲያና ኢትዮጵያ በዘመናት የተሸለመ ክብርና ወዳጅነት ታሪክ አላቸው።
የሩሲያ ጉዳዮችን በአማርኛ የሚያቀርብ ቻናል ከዛሬ ጀምሮ ተጀምሯል።
መረጃው በቀጥታ እንዲደርስ ነው።
📍"በሩሲያ በፍቅር የተቀረ" የሚባል ቻናል ስለ አገራችን ያለውን ነገር ይነግራል።
— ከሞስኮና ከክልሎች የሚመጡ ዜናዎችና ቪዲዮዎች
— የሰዎች ዕለታዊ ሕይወት፤ ከተሞችና ክልሎች
— ፖለቲካና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች
— ባህል፤ ማህበረሰብና ዘመናዊ ሩሲያ
❤️ ይቀላቀሉ፤ ስለ ሩሲያ ይወቁ - https://t.me/+qT6tcupdy0AyNjNi
❤ 35👍 17🥰 4❤🔥 2
Photo unavailableShow in Telegram
የቤታቸውን አጥር ያላደሱ እና ግራጫ ቀለም ያልቀቡ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የመብራት እና የውኃ አገልግሎት አታገኙም መባላቸውን ተናገሩ‼️
በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የመኖሪያ የቤታቸውን አጥር ግራጫ ቀለም ያልቀቡ፣ አምፖል ያልሰቀሉ፣ እንዲሁም በአካባቢያቸው የደኀንነት ካሜራ ያልገጠሙ ነዋሪዎች “የመብራት እና የውኃ አገልግሎት አታገኙም” ተብለናል ሲሉ መናገራቸውን ፎርቹን ጋዜጣ ዘግቧል። ከሚኖሩበት ቀበሌ በመጡ የመንግሥት ኃላፊዎች፤ በሀገር ደረጃ እየተሠራ ካለው የኮሪደር ልማት ጋር ተያይዞ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን “ማስዋብ” አለባችሁ የሚል መመሪያ እንደተሰጣቸው ዘገባው አመላክቷል። በየአካባቢው “ዋና ዋና ቦታዎች ላይ” ይሰቀላል የተባለው የደኅንነት ካሜራው ያስፈለገው፤ በከተማዋ ነዋሪዎች ዘንድ በተደጋጋሚ የሚነሳ የደኅንነት ጥያቄ በመኖሩ ነው ተብሏል።
ለነዋሪዎቹ ከተሰጣቸው መመሪያዎች ውስጥ፤ ሁሉም የመኖሪያ ቤቶች አጥር በተመሳሳይ መልኩ ግራጫ ቀለም መቀባት ያለባቸው ሲሆን ከዚህ የተለየ ቀለም መጠቀም እንደሌለባቸው ተግልጾላቸዋል። የከተማዋ ኃላፊዎች ይህን መመሪያ “በፍጥነት ያልተገበረ” ነዋሪ ለቅጣት እንደሚዳረግ መናገራቸው ተሰምቷል።
ቅጣቱ የሚፈፀመው ነዋሪውዎቹ መንደራቸውን “የማስዋብ” ሥራ ማከናወናቸውን በድጋሚ ከተፈተሸ በኋላ መሆኑ ተመልክቷል። ይህን ያላከናወነ ግለሰብ እንደ “መብራት” እና “ውኃ” ያሉ መሠረተ ልማቶች ይቋረጥበታል መባሉን ከዘገባው ላይ ተመልክተናል።
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ዘነበወርቅ በተሰኘው አካባቢ የሚኖሩት ወ/ሮ አሰገደች ባሕር የተባሉት የ 80 ዓመት አዛውንት፤ “በ 3 ቀናት ውስጥ” የመኖሪያ ቤት አጥራቸውን በድጋሚ ገንብተው ግራጫ ቀለም እንዲቀቡ እና የውጭ አምፖል “በፍጥነት” እንዲሰቅሉ ማሳሰቢያ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል። በልጃቸው ወርሃዊ ገቢ የሚተዳደሩት እኒህ አዛውንት የታዘዙትን ተግባር ማከናወን እንደማይችሉ አስረድተዋል። የታዘዙት አጠቃላይ አጥራቸውን የማደስ ሥራ እስከ 20,000 ብር የሚያስወጣቸው ሲሆን ይህን ያህል ገንዘብ ማግኘት እንደማይችሉ ለኃላፊዎቹ ቢገልጹም የተለየ ምላሽ አለማግኘታቸውን ወ/ሮ አሰገደች ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ፤ የከተማ ውበት እና የአረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ፤ የወይዘሮ አሰገደችን ምክንያት አይቀበሉም በከተማዋ አስተዳደር የወጣውን ስታንዳርድ ላለመፈጸም “ድህነት ምክንያት” አይሆንም ሲሉ ተናግረዋል። የቢሮ ኃላፊው ከዚህ ቀደምም በተመሳሳይ መልኩ በሰጡት አስተያየት በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች እየተሰራ በሚገኝ የኮሪደር ልማት “የተፈናቀለው ድህነት እንጂ ደሀ አይደለም” ሲሉ መናገራቸው አይዘነጋም። መንግሥት ምግብ ለማግኘት ለሚቸገሩ ነዋሬኦችን ሊረዳ ይችላል ነገር ግን ለዚህ ሲባል ሕግ ሊያላላ አይችልም ማለታቸውን ጋዜጣው ዘግቧል። አሁን ላይ አንድ ጋሎን ቀለም 1,600 ብር፣ ኤጋ ቆርቆሮ 1,300 ብር፣ የደኀንነት ካሜራ ከ 4,000 እስከ 13,000 ብር እንደሚሸጥ ተገልጿል።
=========≠============
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
❤ 100😢 57😭 18🤨 7👍 6🙈 6🔥 3👏 3🙊 1
00:59
Video unavailableShow in Telegram
ይህን ሰምተዋል Dema Hope Real Estate ዴማ ሆፕሰ ሪል እሰቴት በመሀል አዲሰ አበባ መገናኛ ሲግናል ,ቦሌ መድሀኒአለም መገናኛ ሾላ እና ቦሌ 24 ሙሉ ያለቁ ጠዋት ገዝተው ከሰአት የሚገቡበት እና ቦሌ መድሀኒአለም ኤድናሞል ጋር ግንባታቸው 90% የደርሱ እጅግ ቅንጡ የመኖርያ አፓርታማ ከባለ 1 መኝታ እሰከ 4 መኝታ ድረሰ እና የንግድ ሱቆች ከግራውንድ ጀምሮ ሸያጭ ላይ ነን በተጨማሪ የመኖርያ አፓርታርትመንቶቻችን እና የንግድ ሱቆቹ ዛሬ ገዝተው ዛሬ የካርታ ሰም ማዞር ይችላሉ ማየት ማመን ነው ፈጥነው ይደውሉ ።Dema Hope Real Estate ቅንጦት ይገባዎታል ። ለበለጠ መረጃ
0912323064
0921305626
2.15 MB
❤ 16👍 4🙏 4
00:13
Video unavailableShow in Telegram
ለፌደራል ፖሊስ‼️
ይህ በምስሉ ላይ የሚታዩት ፕሮፌት ሄኖክ ግርማ የተባሉ ገለሰብ በቤተ-እምነት ውስጥ ባደረጉት ንግግር “ሰላሌ የጠንቋይ ሀገር፣ የመተት ሀገር” በማለት በጅምላ በሰላሌ ህዝብ ላይ የስም ማጥፋት ንግግር ያደረጉ በማህበራዊ ሚዲያ በተንቀሻቃሽ ምስል ሲመላለስ ተስተውሏል። ይህ ንግግር የህዝቡን ስም የሚያንቋሽሽ እና የሰላሌ ህዝብ ከሌሎች ማህበረሰብ እንዲገለል ብሎም በህዝቡ እና ከፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተከታይ ህዝቦች ዘንድ ግጪት ሊቀሰቅስ የሚችል ነው። ስለዚህ የሚመለከተው አካል ይህ አፀያፊ ነግግር ባደረጉ ግለሰብ ላይ እርምጃ ይወስዳል ተብሎ ይጠበቃል።
ማንኛውም ግለሰብ ወይም ቡድን የፈለገውን ሀይማኖት የመከተል መብት ቢኖረውም አንድን ማህበረሰብ በጅምላ መሳደብ እና መፈረጅ ተገቢ አይደለም።
(አዩዘሀበሻ)
=========≠============
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
4.71 KB
❤ 307👍 84🥱 22👏 20🤷♂ 17🙏 12😎 11🔥 9🥰 6🙊 5🦄 2
00:59
Video unavailableShow in Telegram
ይህን ሰምተዋል Dema Hope Real Estate ዴማ ሆፕሰ ሪል እሰቴት በመሀል አዲሰ አበባ መገናኛ ሲግናል ,ቦሌ መድሀኒአለም መገናኛ ሾላ እና ቦሌ 24 ሙሉ ያለቁ ጠዋት ገዝተው ከሰአት የሚገቡበት እና ቦሌ መድሀኒአለም ኤድናሞል ጋር ግንባታቸው 90% የደርሱ እጅግ ቅንጡ የመኖርያ አፓርታማ ከባለ 1 መኝታ እሰከ 4 መኝታ ድረሰ እና የንግድ ሱቆች ከግራውንድ ጀምሮ ሸያጭ ላይ ነን በተጨማሪ የመኖርያ አፓርታርትመንቶቻችን እና የንግድ ሱቆቹ ዛሬ ገዝተው ዛሬ የካርታ ሰም ማዞር ይችላሉ ማየት ማመን ነው ፈጥነው ይደውሉ ።Dema Hope Real Estate ቅንጦት ይገባዎታል ። ለበለጠ መረጃ
0912323064
0921305626
2.15 MB
❤ 38👍 5🥰 3💔 2👏 1
የኢትዮጵያ ብር ዋጋ በተያዘው የአውሮፓዊያን ዓመት ብቻ ከአሜሪካ ዶላር አንጻር ዋጋው በ15 በመቶ ማሽቆልቆሉን ብሉምበርግ ዘገበ። ብር ባሁኑ ወቅት ከአርጀንቲናው ፔሶ እና ከቱርኩ ሊሬ ቀጥሎ በዓለም ደካማው መገበያያ ገንዘብ መሆኑን ዘገባው ጠቅሷል። የብር ዋጋ ወደፊትም ኢትዮጵያ የውጭ እዳዋን ማሸጋሸግ ከመቻሏ ጋር የተሳሰረ ሆኖ እንደሚቀጥል ዘገባው አመልክቷል። መንግሥት የአገሪቱን 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ብድር መልሶ ለማዋቀር ከወራት በፊት ከአበዳሪዎች ኮሚቴ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ላይ መድርሱ ይታወሳል። ኾኖም የአገሪቱ የወጪ ገቢ ማደግ፣ የመንግሥት የበጀት ክፍተት መቀነስ እንዲሁም መንግሥት ከ1 ቢሊዮን ዶላር የዩሮቦንድ ያዥ ዓለማቀፍ ኢንቨስተሮች ጋር በቦንዱ አከፋፈል ላይ ስምምነት ሊደርስ ይችላል የሚለው ተስፋ፣ በብር ላይ ያለውን ጫና ሊያቃልለው እንደሚችል ባለሙያዎች እምነታቸውን ገልጸዋል ተብሏል። ባኹኑ ወቅት መደበኛው የ1 ዶላር መግዣ ዋጋ 151 ብር ሲሆን፣ በትይዩ ገበያ ደሞ ወደ 180 ብር አሻቅቧል።
=========≠============
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
😭 90❤ 86😢 13🤨 11💯 3🙏 2🤷♂ 1🥱 1
Photo unavailableShow in Telegram
የሳውዲ አረቢያ የሰው ኃይል እና ማህበራዊ ልማት ሚኒስቴር በሀገሪቱ በሚገኙ የቤት ሠራተኞች የደመወዝ አከፋፈል ላይ መሠረታዊ ለውጥ ማድረጉን አስታወቀ‼️
በአዲሱ መመሪያ መሠረት፣ ከፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ጀምሮ ማንኛውም አሠሪ ለቤት ሠራተኞች የሚከፍለውን ደመወዝ በጥሬ ገንዘብ (Cash) መስጠት የሚከለከል ሲሆን፣ ክፍያው በይፋዊ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መስመሮች ብቻ እንዲከናወን ተደንግጓል።
ይህ ውሳኔ በተለይ በኢትዮጵያ እና በሳውዲ አረቢያ መንግሥት መካከል እ.ኤ.አ በ2023 የተፈረመውን የሁለትዮሽ የሥራ ስምሪት ስምምነት ተከትሎ ወደ ሀገሪቱ ለገቡ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን ትልቅ የምስራች ሆኗል።
አዲሱ አሠራር የሠራተኞችን የደመወዝ መብት ከማስከበር ባለፈ፣ ክፍያዎች በወቅቱ መፈጸማቸውን የሚያረጋግጥና በአሠሪና ሠራተኛ መካከል የሚፈጠሩ የክፍያ አለመግባባቶችን በዘላቂነት የሚፈታ መሆኑ ተገልጿል።
እንደ ሚኒስቴሩ ገለጻ፣ የደመወዝ ክፍያው የሚፈጸመው በ"ሙሳነድ" (Musaned) የዲጂታል መድረክ አማካኝነት በታወቁ ባንኮች ወይም የዲጂታል የገንዘብ ማስተላለፊያ መተግበሪያዎች (Digital Wallets) በኩል ይሆናል።
ሠራተኞች ደመወዛቸውን በጥሬ ገንዘብ መጠቀም በሚፈልጉበት ጊዜ በስማቸው በሚወጣ የ"ማዳ" (Mada) የባንክ ካርድ አማካኝነት በማንኛውም የገንዘብ ማውጫ ማሽን (ATM) መጠቀም ይችላሉ። ይህም ሠራተኞች ያጠራቀሙትን ገንዘብ ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ወደ ሀገራቸው ለቤተሰቦቻቸው እንዲልኩና የሥራ ውላቸው ሲጠናቀቅ የሚገባቸውን ጥቅማጥቅም በቀላሉ እንዲያገኙ ይረዳቸዋል።
ይህ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት እኤአ ከሐምሌ 2024 ጀምሮ ደረጃ በደረጃ ተግባራዊ ሲደረግ የቆየ ሲሆን፣ ከጥር 2026 ጀምሮ ግን ለማንኛውም አሠሪና ሠራተኛ አስገዳጅ ይሆናል። ውሳኔው የሳውዲ አረቢያን የቤት ሠራተኛ ዘርፍ ዘመናዊ ለማድረግና የሠራተኞችን ሰብአዊና ቁሳዊ መብቶች ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለመጠበቅ የሚደረገው ጥረት አካል መሆኑ ታውቋል።
=========≠============
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
❤ 237👍 37👏 17🥰 10🔥 3😎 2
Photo unavailableShow in Telegram
ከ1ሺህ ዶላር ወደ 3000‼️
🇺🇸 የአሜሪካ መንግስት በገዛ ፈቃዳቸው ለሚወጡ ስደተኞች የ3,000 ዶላር ክፍያ ማበረቻ አቀረበ‼️
የአሜሪካ መንግስት ባልተሟላ ሰነድ (Undocumented) ሀገሪቱ ውስጥ ለሚገኙ እና በገዛ ፈቃዳቸው ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ለሚመርጡ ስደተኞች አዲስ የማበረታቻ ፕሮግራም ይፋ አድርጓል።
የፕሮግራሙ ዝርዝር መረጃዎች፦
🔹 የገንዘብ ድጋፉ መጠን፦
ቀደም ሲል ከነበረበት $1,000 ወደ $3,000 ከፍ ብሏል።
🔹 የጉዞ ወጪ፦
ወደ ትውልድ ሀገር የሚቆረጥ የአንድ መንገድ የአውሮፕላን ትኬት ሙሉ በሙሉ በመንግስት ይሸፈናል።
🔹 የጊዜ ገደብ፦
ፕሮግራሙ ለተወሰነ ጊዜ ብቻ የሚቆይ ሲሆን እስከ ታህሳስ 31፣ 2025 (December 31, 2025) ድረስ ይቆያል።
🔹 እንዴት መመዝገብ ይቻላል? ፍላጎት ያላቸው አመልካቾች "CBP Home" በተሰኘው ይፋዊ የመንግስት መተግበሪያ (App) በኩል መመዝገብ አለባቸው።
ይህ ክፍያ እንዲሁ በነጻ የሚሰጥ ገንዘብ አይደለም። ክፍያው የሚፈጸመው ግለሰቡ በገዛ ፈቃዱ ከአሜሪካ መውጣቱ ሲረጋገጥ እና ሁሉንም መስፈርቶች ሲያሟላ ብቻ ነው።
ይህ ፕሮግራም በ2025 መጀመሪያ ላይ በ$1,000 ክፍያ ተጀምሮ የነበረ ሲሆን፣ አሁን እንደ አመት ማጠቃለያ ስልት ክፍያው ወደ $3,000 አድጓል።
ባጭሩ:-
1 እስከ $3,000 የጥሬ ገንዘብ ክፍያ
2. ነጻ የአውሮፕላን ትኬት
3. እስከ 2025 መጨረሻ የሚቆይ
4. በራስ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ነው"ብሏል።
=========≠============
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
❤ 95😎 15👏 8🤨 7👍 6😢 1
Photo unavailableShow in Telegram
📱 በኢትዮጵያ ትልቁ እና ታማኙ የሊንኪደን አካውንት ተከራይ Bussines Team አሁንም በርካታ አካውንቶችን ተከራይቶ ለቢዝነስ አላማ ማስተዳደር ይፈልጋል።
📱 ከፍተኛ ኮኔክሽን ወይም ረጅም አመት ያስቆጠሩ አካውንቶች የተሻለ ክፍያ ያገኛሉ፡፡
የእርስዎን አካውንት ደህንነት እንደራሳችን አካውንት አድርገን እንጠብቀዋለን።
☎️ ስልክ ፦ 0923526669
💬 በውስጥ መስመር ➡️ ያግኙን
@Bussinessteam23
🔵 የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ➡️
@linkBussinessteam
❤ 18💯 5🔥 4👍 3😭 3👏 2
Photo unavailableShow in Telegram
የአፈና ዜና‼️
በአማራ ክልል እና በትግራይ ክልል መካከል የማንነት እና የወሰን ጥያቄ ከሚነሳባቸው ቦታዎች አንዱ በሆነው በራያ አላማጣ ወረዳ ጥሙጋ ቀበሌ እና በአላማጣ ከተማ 04 ቀበሌ ሀርኪሳ ጎጥ ዛሬ ከሌሊቱ 9:30 አጠቃላይ 19 ሰዎች በታጣቂዎች ወደአልታወቀ ቦታ መወሰዳቸውን የደረሰኝ መረጃ ያመላክታል። ከእነዚህ ታጋቾች ውስጥ ቄስ ካህሳይ ቢወጣ የራያ ሀገረ ስብከት ስብከተ ወንጌል ሀላፊ እንደሚገኙበት ምንጮች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።
(አዩዘሀበሻ)
=========≠============
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
😭 116❤ 66😢 30💔 27👍 22🙈 13🤷♂ 8🥰 3🎄 3🔥 1
