መሠረተ ግእዝ | Meserete Ge'ez
رفتن به کانال در Telegram
የሀገራችን ቀዳማዊና ጥንታዊ ስለሆነው የግእዝ ቋንቋ መሠረታዊ ትምህርት የሚሰጥበት ቦታ ነው። እርስዎም አባቶቻችን ያቆዩልንን ቋንቋ በመማርና ለትውልድ በማስተላለፍ ኃላፊነትዎን ይወጡ። ለጥያቄና አስተያየት - @geezchanal
نمایش بیشتر2025 سال در اعداد

17 974
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-177 روز
-9130 روز
آرشیو پست ها
Photo unavailableShow in Telegram
🌺 ሰላም፡ለኵልክሙ የግእዝ ወዳጆች በሙሉ
እነሆ በአዲስ መልኩ ተመልሰን የ"ግእዝን በአንድ ወር" ኮርሳችንን በ፯ኛው ዙር የኦንላይን ትምህርት ለመስጠት ምዝገባ ጀምረናል።
📜 በመሆኑም የግእዝ ቋንቋን መሠረታዊ ትምህርት ለጀማሪዎች ዘመኑን በዋጀ መልኩ ለመስጠት ቅድመ ዝግጅታችንን በመጨረሳችን ከታች በተቀመጠው መሠረት በመመዝገብ ጥንታዊ ቋንቋችንን እናጥና ዕንወቅ።
📖 የሚሰጠው ትምህርት፦ የግእዝ ቋንቋ መሠረት (መሠረተ ግእዝ)
⏳ የሚጀምርበት ቀን፦ ግንቦት 2
🌐 የሚሰጥበት ቦታ ፦ በቴሌግራም
...........................
✅ የመመዝገቢያና የበለጠ ማብራሪያ ቦታ በዚህ ገብተው ያግኙ👇
👉 [https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdugh4KZ5HpGX5Xh1jbX1LbAvgN5E6kGOkx7hD7nytXu5eLbA/viewform?usp=sf_link] 🤏
..........................................................
🆔 ሞልተው እንደጨረሱ @MGeez24 በዚህ ገብተው ID በመቀበል ምዝገባውን ያጠናቅቁ + ለበለጠ መረጃ ደውለው ያግኙን። ሠናይ፡ጊዜ።
🈸
መሠረተ፡ግእዝ
@MesereteGeez◦0977682046Photo unavailableShow in Telegram
🌺 ሰላም ቤተሰቦቻችን ፡ እነሆ በ"ግእዝን በአንድ ወር" ኮርሳችን ባለፉት ዙሮች ሲማሩ ከቆዩ ተማሪዎች መካከል ከፍተኛ ውጤት አምጥተው ያጠናቀቁ ተማሪዎችን የምናወዳድርበት የጥያቄና መልስ መርሐ ግብር ነው።
🕰 የፊታችን ሰኞ ከሰዓት 9፡45 ጀምሮ በመሰባሰብ ይህንን የትምህርት መርሐ ግብር እንድንታድም በአክብቶት እንጣራለን።
🌐 በ @MesereteGeez ቴሌግራም ቻናል VoiceChat ይጠብቁን። ሼር እያደረግን ሌሎችንም እናሳትፍ። መልካም ጊዜ።
.......................................................
▶️ መሠረተ ፡ ግእዝ 2015 ዓ.ም https://www.YouTube.com/channel/UCA_P-T7Z1UcP-1kdEKjld-g
👍 24❤ 1
የፑቲን ሀገር ሩሲያ የአማርኛን ቋንቋ በሩሲያ ትምህርት ቤቶች ማስተማር ልትጀምር መሆኗን አስታውቃለች።
በሞስኮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የእስያ እና የአፍሪካ ሀገራት ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር አሌክሲ ማስሎቭ እሁድ እለት በሩሲያ-አፍሪካ አለም አቀፍ የፓርላማ ጉባኤ ላይ እንደተናገሩት ሩሲያ የአፍሪካ ቋንቋዎችን አማርኛንና ስዋሂሊን በሩሲያ ትምህርት ቤቶች ለማስተማር እየተዘጋጀን ነው ብለዋል።
እንደሚታወቀው ቻይና አማርኛ ቋንቋን በመጀመሪያ ዲግሪ እያስተማረች ነው። ትምህርቱ በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ (BFSU) መሰጠት ጀምሯል። ከጀርመን ታዋቂ ከሆኑት ዩኒቨርስቲዎች አንዱ የሆነው ሀምቡርግ ዩንበርሲቲ የአማርኛ ት/ ት ማስተማር ከጀመረ መቶ ዓመት አልፎታል።
አማርኛ ቋንቋን በ2007 ዓ.ም.የአፕል የቴክኖሎጂ ማዕከል አማርኛን ከዓለም ግዙፍ ቋንቋዎች ተርታ መድቦ የቴክኖሎጂ ቋንቋ አድርጎታል። በ2008 ዓ.ም. የጎግል የቴክኖሎጂ ማዕከል የመተርጎሚያ ቋንቋ አድርጎታል። Dstv'ም የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና፣የኦሊምፒክ ውድድሮችን ጨምሮ የእንግሊዝ ኘሪሚየር ሊግ ፣ የስፔን ላሊጋ ፣ የጣሊያን ሴ ሪ ኤ እንዲሁም ቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎችን በአማርኛ ቋንቋ እንዲተላለፉ ከወሰነ አመት አስቆጥሯል።
አማርኛ በUS አሜሪካ የመንግስት ቋንቋም ነው። እንዲያውም በአሜሪካዋ ቨርጂኒያ ግዛት አሌክሳንድሪያ ዳሽ የሚባለው የከተማ አውቶቢስ ላይ "እንኳን ወደ #WESTEND በደህና መጣችሁ!" የሚል ጽሁፍ ማየትም የተለመደ ነው።
👍 40❤ 19👎 1🔥 1
🈯️ ቋንቋ እና ሃይማኖት
በሮማውያን ዘመን ላቲን Latin (ሮማይስጢ) ሰውንና እግዚአብሔር ማግባባት የሚችል ብቸኛ ቋንቋ እንደሆነ ስለሚታሰብ ፤ ቃላዊ ሆነ ጽሑፋዊ ውዳሴ አምላክ ከላቲን ቋንቋ ውጪ ቢቀርብ "ባዶ ጩኸት" ነው ተብሎ ይታመን ነበር።
በዓረቡም ዓለምም ቢሆን የእሰልምናው ሥርዓተ አምልኮ፤ 'ሶላቱም' ሆነ ትምህርቱ በዐረብኛ ቋንቋ መቅረቡ መንፈሳዊ ዕሴት እንዳለው ስለሚታመን ቋንቋውን በማይናገሩ ሀገሮች ሳይቀር ሥራ ላይ ሲውል እንመለከታለን።
ይህ አስተሳሰብ በእኛም ሀገር ለብዙ ዘመናት ሰፍኖ መቆየቱ አያጠያይቅም። እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ጸሎቱና ማኅሌቱ፣ ውዳሴውና ቅዳሴው ከግእዝ ቋንቋ ውጪ በሌላ ቋንቋ ቢቀርብ እንደዓለማዊ ጉዳይ የሚቈጠርበት ሁኔታ ነበረ።
ለምሳሌ በድሮ ጊዜ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ በቤተክርስቲያን አገልግሎት እንዳይሰጥበት አንዳንድ አባቶች ይከላከሉ እንደነበር አንድ ትውስታ ነው።
ከዚህም ሌላ በዐሥራ ዘጠኝ ኀምሳዎቹ መጨረሻ (1950's) አካባቢ ባንዳንድ የክፍለ ሀገር ከተሞች በ"ክብረ ተዋሕዶ" ወይም በ"ሃይማኖተ አበው" መዋቅር ሥር የተቋቋሙ ወጣቶች በቤተክርስቲያን ተሰባስበው የአማርኛ መዝሙሮችን መዘመር ሲጀምሩ ጊዜውን የታዘቡ ሰዎች ነበሩ።
❔ይህን ሁሉ የተነሣው፤ ልሳነ ግእዝ ከሃይማኖት ጋር መተሳሠሩ ያስገኘለት ፋይዳ አለ? ወይስ የለም? የሚለውን ለመመለስ ነው።
ቋንቋ ለሃይማኖት መስፋፋት፣ ሃይማኖት ለቋንቋ ዕድገት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ቀላል አለመሆኑን ሁሉም ሰው ይገነዘባል። የግእዝ ቋንቋ በከፍተኛ ደረጃ ወደ ብሔራዊ ቋንቋነት ሊያድግ የቻለ ከዐራተኛው ምእተ ዓመት (301 - 400) አጋማሽ ጀምሮ ባብዛኛው ጉዳያቸው ሃይማኖታዊ የሆነ ትርጉም ሥራዎች ስለተሠሩበት ነበር።
የሃይማኖትና የቋንቋ ቁርኝት ጥቅምም ድክመትም እንዳለው መረዳት እንችላለን። ለምሳሌ ዐረብኛ ቋንቋ ከሰባተኛው ምእተ ዓመት (601-700) ጀምሮ እስከ ዘመናችን ድረስ ግለቱ ሳይበርድ እምነቱን እያስፋፋ እሱም አብሮ እያደገ ነው። ላቲን እና ግእዝ ግን አልቀናቸውም።
መጽሐፍ ቅዱስ በእንግሊዝኛ እና በሌሎችም የአውሮፓ ቋንቋዎች መታተምና መሰበክ ሲጀምር ላቲን እየተዳከመ እንደመጣ ሁሉ ፤ የኛው ግእዝም አማርኛ የጽሑፍ ቋንቋና የሃይማኖት መስበኪያ እየሆነ ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ የላቲን ፈንታ ደርሶበታል።
✴️ ይቀጥላል...
◌◌◌□▢🪻መሠረተ ፡ ግእዝ🪻▢□◌◌◌
@MesereteGeez ◦ @MesereteGeez
@MGeez24
👍 25❤ 4🤩 1
Repost from TgId: 1216366241
نمایش همه...Photo unavailableShow in Telegram
አዲስ መጽሐፍ ምረቃ መርሐ ግብር
📜 መዝገበ አኀዝ ዘኢትዮጵያ 📜
⏰ እሑድ መጋቢት ፲፯ ከቀኑ ፯ ሰዓት
በ፬ኪሎ ቅድስት ሥላሴ አዳራሽ
አዘጋጅ ፦ መጋቤ አእላፍ መ/ር በፍቃዱ መንገሻ
መጽሐፉን ለማግኘት በስልክ -
አልቦ ፱ -፺፰-አልቦ፭-፵፮ | አልቦ ፱-፵፬-አልቦ፮-፸፯-፺
@MesereteGeez
@MesereteGeez @MesereteGeez
📜 “ንግባእኬ ፡ ኀበ ፡ ጥንተ ፡ ነገር"
“ወደ ቀድሞ ነገር እንመለስ" በሚል ርእስ በሐመረ ብርሃን የብራና ሥራዎች ድርጅት ዐውደ ርእይ ተካሄደ ።
በዐውደ ርእዩ የብራና ሙሉ ዝግጅት እና የቅዱሳን ሥዕላት በብራና ላይ እንዴት እንደሚሳሉ የሚያሳይ ትዕይንት ሲሆን ፤ የሀገራችንን የቀድሞ የብራና ሥራ ዳግም ወደ አሁኑ ዘመን የሚመልስ ሥራ ነው ።
ሐመረ ብርሃን የተመሠረተው ከአራት ዓመታት በፊት ሲሆን ዋና ዓላማ አድርገው የተነሡት ከአባቶች የተማሩትን ጥበብ በማወቅ ለትውልድ እንዲተላለፍ ማድረግ ነው ። ወደፊትም ማኅበሩን ወደ ሥልጠና ማዕከል ለማሳደግም ትልቅ ሥራ እየሠሩ ይገኛሉ። በዚህ በአራት ዓመት ጊዜያቸውም አንድ ዓመት ከስድስተ ወር የፈጀ ውስጡ በሐረግና በሥዕላት የተዋበ መሉ የቅዳሴ መጽሐፍ በብራና አዘጋጅተዋል። በተጨማሪ የተለያዩ መጻሕፍትን እና ቅዱሳን ሥዕላትን በብራና አዘጋጅተው ለዕይታ አቅርበዋል።
🛖 የሐመረ ብርሃን አድራሻ ፦ ፒያሳ አሮጌው ፓስታ ቤት ግቢ ውስጥ
መጋቢት ፮ ቀን ፳፻፲፭ ዓመተ ምሕረት
................................
🌺 መሠረተ ፡ ግእዝ 🌺
@MesereteGeez
@MesereteGeez @MesereteGeez
01:25
Video unavailableShow in Telegram
📜 ልዩ የሆነ የዕደ ጥበብ መርሐ ግብር 📜
በሐመረ ብርሃን የብራና መጻሕፍት ሥራ ድርጅት
ከመጋቢት 1-3 በሐመረ ብርሃን አይቀርም
አድራሻ ፦ ፒያሳ አሮጌው ፖስታ ቤት ግቢ ውስጥ
ለበለጠ መረጃ ፦ 0944-24-00-00
📜 መሠረተ፡ግእዝ 📜
@MesereteGeez
@MesereteGeez
@MesereteGeez 👈
18.31 MB
Photo unavailableShow in Telegram
👉 ለኮምፒውተር ሳይንስ እስከ መጥቀም የሚያደርሱ በርካታ ቀመርን የያዙ የግእዝ ፊደላት በያዙት ጥበብ ላይ ከፍተኛ ጥናት ያጠኑ ኢትዮጵያውያን ተመራማሪዎች፣ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ላይ ያሉ ሳይንቲስቶች የሚሳተፉበት ሳይንሳዊ ጉባኤ
👉 Historians have recognized Ethiopia as an ancient civilization with the earliest known governance system but most of all for its unique and efficient writing system, the Ethiopic Scripts (aka, Geez Script).
👉 We cordially invite you all to join us to the first conference series on Saturday, March 11, 2023 at 10:00 AM EST (6:00 PM Addis Ababa Time; በአዲስ አበባ አቆጣጠር ከምሽቱ 12 ሰዓት)
👉 Please register as soon as you possibly can to enable us to make the necessary adjustments with audience attendance protocols.
Please also find a conference flyer in the attachment. Thank you.
Here below is the link for registration:
HERE / https://us06web.zoom.us/webinar/register/WN_ZX1kAg12R82A3sa-1VYxrw
