107 335
Подписчики
-4624 часа
-3747 дней
-2 08430 день
Архив постов
በሊድ መመረዝ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ!
በዓለም አቀፍ ደረጃም ሆነ በኢትዮጵያ በሊድ መመረዝ አሳሳቢ ጉዳይ እየሆነ መምጣቱን የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ ገለፁ።ስለሊድ ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመው ሁለተኛው ብሔራዊ በሊድ መመረዝን የመከላከል ቀን ተከብሯል።
በዚሁ ወቅት ዶክተር ደረጀ፤ በዓለም አቀፍ ደረጃም ሆነ በኢትዮጵያ በሊድ መመረዝ አሳሳቢ ጉዳይ እየሆነ መጥቷል ብለዋል። ከሶስት ህፃናት በአንዱ ላይ ከፍተኛ የሆነ የሊድ መመረዝ መጠን ይገኛል ሲሉም እንደማሳያ አንስተዋል።
ይህ አስደንጋጭ በመሆኑ በትኩረት መስራት ይጠይቃል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ሊድ በተለያዩ ስፍራዎች ላይ የሚገኝ ቢሆንም በስፋት ውሃ ላይ፤ እንዲሁም በዕለት መገልገያ ቁሶች ላይም ይገኛል ነው ያሉት።
እንደ ዶክተር ደረጀ ገለፃ፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚከሰተው ሞት ውስጥ 23 በመቶ የሚሆነው ከአካባቢ ብክለት ጋር ተያይዞ የሚከሰት ነው።
የውሃ ብክለትና ቆሻሻን በአግባቡ ካለማስወገድ የሚመጣ ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃ ፈተና የሆነውን የአካባቢ ብክለት ለመከላከል ሁሉም ሊረባረብ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
በኢትዮጵያ ከግብርና ወደኢንዱስትሪ በሚደረገው ሽግግር ኬሚካሎችን የመጠቀምና የማምረት ፍላጎ እያደገ መጥቷል። ይህም ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚሻ መሆኑን አስገንዝበዋል።
በሊድ መመረዝ ምክንያት አዕምሮ አድገት ውስንነት፣ የአዕምሮ ነርቭ ጉዳት፣ የደም ማንስ፣ የመፀነስ ችግር፣ የኩላሊት ጉዳት እንዲሁም የመራቢያ አካላት ላይ ጉዳት የሚያደርስ ነው ብለዋል።
ዶክተር ደረጀ አክለውም ጉዳቱ ቀለል ተደርጎ የሚወሰድ አይደለም፤ ለዚህም የቆሻሻ አወጋገድ ስርዓትን ማሻሻል፣ የስራ ቦታ ደህንነትን ማስጠበቅ ይገባል ነው ያሉት።
ሊድ በተፈጥሮ የሚገኝ መርዛማ ብረት አይነት ሲሆን፤ የዓለም ጤና ድርጅት እ.ኤ.አ በ2021 ጥናት መሰረት በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ ከ1 ነጥብ 5 ሚለዮን ሰዎች በላይ በሊድ መመረዝ ይሞታሉ።
እንዲሁም በአፍርካ ደረጃ በየዓመቱ ከ55 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በሊድ መመረዝ የሚጠቁ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ከሶስት ሕፃናት አንዱ በሊድ መመረዝ እንደሚጠቃ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡
Via Gazette Plus
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 37
ፈጣን ምላሽ
በደቡብ ኢትዮጵያ በቫይራል ሄመሬጂክ ፌቨር (VHF) ወረርሽኝ የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ፈጣን ምላሽ ሰጠ!
የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተጠረጠረ የቫይራል ሄመሬጂክ ፌቨር (VHF) ወረርሽኝ ዙሪያ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ከኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና ከክልላዊ የጤና ባለስልጣናት ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።
የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ 8 ሰዎች በቫይረስ ሊያዙ እንደሚችሉ ተዘግቧል።
WHO ለዚህ ወረርሽኝ ምላሽ ለመስጠት አስቀድሞ የሚከተሉትን እርምጃዎች ወስዷል፦
1. ባለሙያዎች፣ መድኃኒቶችና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶች እንዲሁም ለጤና ሰራተኞች የሚሆን የግል መከላከያ ቁሳቁስ (PPE) ወደ ተጎዱ ከተሞች ተልኳል።
2. በወረርሽኙ የተጎዱ ማህበረሰቦች ውስጥ ንክኪን የመከታተል (Contact Tracing) ሥራን ድርጅቱ ይደግፋል።
3. ሊኖር የሚችለውን ድንበር ዘለል ስርጭት ለመከላከል ከደቡብ ሱዳን WHO ቢሮ ጋር በቅርበት እየተሰራ ነው።
4. የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ እንዳስታወቁት፣ ለአስቸኳይ ድጋፍ እንዲውል 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ) የአሜሪካን ዶላር ከWHO የአደጋ ጊዜ ፈንድ ለኢትዮጵያ ተለቋል። ድርጅቱ እንደ አስፈላጊነቱ ድጋፉን ለማሳደግ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።
የWHO ኃላፊዎች የኢትዮጵያ ጤና ባለስልጣናት መረጃውን በወቅቱ በማጋራታቸው እና ፈጣን ምላሽ በመስጠታቸው ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን፣ የዓለም ጤና ድርጅት ሙሉ ድጋፍ እንደማይለያቸው ቃል ገብተዋል።
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 36👎 6👀 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
ለኤሌክትሪክ ባስ አገልግሎት ፈጣን መንገድ ሊገነባ ነው!
በአዲስ አበባ ከተማ ለኤሌክትሪክ ባስ አገልግሎት የሚውል ፈጣን መንገድ ሊገነባእንደሆነ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ነው የገለጸው፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ እያሱ ሰለሞን እንደገለጹት ፈጣን መንገዱ በአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን እና በአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በጋራ የሚገነባ ነው።መንጠዱ15 ነጥብ 64 ኪሎ ሜትር ርዝመት ይኖረዋል።
ፕሮጀክቱ 20 ዘመናዊ ጣቢያዎችና 12 ተጨማሪ አገልግሎቶች የያዘ ነው ብለዋል፡ፕሮጀክቱ በቀን 400 ሺህ የሚደርሱ መንገደኞችን ማስተናገድ የሚችል መሆኑን ገልጸው፤ በየመዳሻዎቹ ከአንድ እስከ 15 ደቂቃ ባለው ጊዜ የሚደርስ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ርዝመት ከፒያሳ እስከ ጀሞ-3 ኮንዶሚኒየም ያሉትን መንገዶች የሚሸፍን ሲሆን ወጪውም የከተማው አስተዳደር እንዲሁም በአጋርድርጅቶች እንደሚሸፈን የዘገበው ኢፕድ ነው።
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 22👍 21😁 14👎 6👀 2🔥 1
ድብደባ የፈፀመው የውጭ ዜጋ ከሥራ ተሰናበተ
📌 በሃዋሳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ውስጥ የተከሰተ ግጭት በተመለከተ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ!
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን እና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በሃዋሳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በሚገኘው ቶዮ ሶላር ኩባንያ ውስጥ የተፈጠረው ግጭት የማጣራት ስራውን አጠናቋል።
የግጭቱ መንስኤ “በስራ ገበታ ላይ በተደጋጋሚ በሰዓቱ አልተገኘህም” በሚል በአንድ የውጭ ዜግነት ያለው ሱፐርቫይዘርና ኢትዮጵያዊ ሰራተኛ መካከል የተፈጠረ አምቧጓሮ መሆኑን ለመረዳት ችለናል።
አለመግባባቱ መፈታት የነበረበት የሰራተኞችን ሰብአዊ መብት በጠበቀ መልኩ በህግና በድርጅቱ ፓሊሲ እንጂ በፀብ መሆን እንዳልነበረበት መግባባት ላይ ተደርሷል። በመሆኑም በዚህ ክስተት ውስጥ ችግሩ እዚህ ደረጃ ላይ ሳይደርስ እንዲፈታ በወቅቱ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ያልተወጡ 5 ኃላፊዎች ላይ ኩባንያው እርምጃ ወስዷል።
1) በግጭቱ ቀጥተኛ ተሳትፎ የነበረውን የውጭ አገር ሰራተኛ የድርጅቱ የስነምግባር መመሪያ ባለማክበር እንዲሁም
2) ጉዳዩ የሚመለከተው የኩባንያው የስራ ኃላፊ ድርጊቱ በተፈፀመበት ወቅት ተገቢውን አስተዳደራዊ ክትትልና እርምጃ ባለመውሰዱ ምክንያት ከሥራ አሰናብቷቸዋል።
ከዚህ ጋር ተያይዞ ተጨማሪ ሶስት መካከለኛ ደረጃ ሥራ አስኪያጆችም ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ባለመወጣታቸው ምክንያት ከባድ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል። በዘላቂነትም እንደዚህ አይነት ችግሮች እንዳይደገሙ ስልጠናዎች ለኩባንያው ሰራተኞችና አመራሮች በቀጣይ የሚሰጥ ይሆናል።
ይህ ውሳኔ ቶዮ ሶላር ካምፓኒ ፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን እና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ለማንኛውም ዓይነት የስነምግባር ጉድለት፣ አካላዊና ስነልቦናዊ ጥቃት እንደማይታገሱ አመላካች ነው።
በዚህ አጋጣሚ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሚያስተዳድራቸው አስር ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች፣ አንድ ነፃ የንግድ ቀጠና እና ሶስት ፓርኮች የተቀናጀ መሰረተ ልማት ለባለሀብቶች እያቀረበ የሚገኝ ሀገራዊ ተቋም ነዉ። ተቋሙ በሚያስተዳድራቸው ሁሉም ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች እና ፓርኮች ውስጥ ለወጣቶች ሰፊ የስራ እድል እንዲፈጠር ከሚሰራው ስራ ጎን ለጎን የሠራተኞች ደህንነት፣ ክብር እና እኩልነት በማንኛውም አይነት ሁኔታ እንዳይጓደል ጥረቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል በዚሁ አጋጣሚ ለማረጋገጥ ይወዳል።
ቶዮ ሶላር ለ2 ሺ ሰራተኞች የስራ እድል የፈጠረ በየወሩ ከ15 ሚሊዮን ዶላር በላይ ኤክስፖርት እያደረገ ያለ ድርጅት ነው።
(የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን)
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 26👍 18👎 1🔥 1
Repost from YeneTube
Фото недоступноПоказать в Telegram
በካሽ 100% ለሚከፍል 35% ቅናሽ
📍ሳር ቤት ቫቲካን
🎯65/35 አከፍፈል (35%ቅናሽ)
👉2መኝታ 81 ካሬ =5.8 ሚሊዮን ብር
👉2መኝታ 106 ካሬ=7.6 ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 139 ካሬ=9.9 ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 152 ካሬ= 11.8 ሚሊዮን ብር
🎯ቀስ ብሎ ለሚከፍል
👉2መኝታ 81ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%) = 1.78 ሚሊዮን ብር
👉2መኝታ 106ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%)=2.33ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 139ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%)= 3.06 ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 152ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%)=3.34 ሚሊዮን ብር
#ቀሪውን 80% ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት
* 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ 15%_25% ቅናሽ አዘጋጅተናል
ለበለጠ መረጃ
0901504245
0923579248
❤ 12
Фото недоступноПоказать в Telegram
ወቅታዊ የጤና ጉዳይን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 14😭 8👍 5👎 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
በጅንካ ከተማ ምንነቱ በመረጋገጥ ላይ ያለ ሄሞራጂክ ፊቨር በሽታ ተከሰተ፤ ስምንት ሰዎች በበሽታው ተጠርጥረዋል ተብሏል!
በደቡበ ኢትዮጵያ ክልል በጅንካ ከተማ ምንነቱ በመረጋገጥ ላይ ያለ የሄሞራጂክ ፊቨር (Hemorrhagic Fever) በሽታ መከሰቱን የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቁ።የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጋራ ባወጡት መግለጫ፣ እስካሁን ድረስ ስምንት ሰዎች በበሽታው እንደተጠረጠሩ ገልፀዋል።
መግለጫው፣ ከከልሉ ጤና ቢሮ ጋር በመሆን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተመዘገበውን ይህንን የበሽታ መንስኤ ለማወቅ እና ተጨማሪ ስርጭትን ለመግታት እንዲሁም ለመቆጣጠር ፈጣን ምላሽ ሰጪ ቡድን ወደቦታው በመላክ የመስክ ግምገማዎች እና የላብራቶሪ ምርመራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልጿል።
በተጨማሪም የማህበረሰብ ቅኝት፣ የንከኪ ልየታ፣የቤት ለቤት ልየታ እንዲሁም የህክምና አገልግሎት አሰጣጥን እያጠናከረ ይገኛል ብሏል።በመሆኑም መላዉ ሕብረተሰባችንና የሚመለከታቸዉ የባለድርሻ አካላት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሌላ ተጨማሪ መግለጫ እስከሚሰጥ ድረስ፤ ለመከላከል የሚከተሉትን ምከረ-ሃሳቦች እና ጥንቃቄዎች ተግባራዊ እንዲያደርጉ አሳስቧል።
በአፍ፣ አፍንጫ እና ሌሎች የሰውነት ከፍሎች የመድማት፣ትኩሳት፣ማስቀመጥ እና ማስመለስ ምልክት ሲኖር ወደ ህክምና ተቋማት መሄድና በወቅቱ የላቦራቶሪ ምርመራ ማድረግ እንደሚገባም አስገንዝቧል።በተጨማሪም፣ ምልክት ከታየበት ማንኛዉም ሰዉ ጋር ንክኪ በሚኖርበት ጊዜ ራስን የመከላከያ ዘዴዎችን መጠቀም፣ ሁልጊዜ እጅን በሳኒታይዘር ወይም በውሃና በሳሙና በመታጠብ ማጽዳት አስፈላጊ ነው ተብሏል።
Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 23😭 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
አቶ ታዬ ደንደአ ከቀረቡባቸው ሦስት ክሶች ከሁለቱ ነጻ ሲወጡ በአንደኛው ጥፋተኛ ተባሉ!
የቀድሞው የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ እና የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት አባል አቶ ታዬ ደንደአ በዐቃቤ ሕግ ከቀረቡባቸው ሦስት ክሶች ፍርድ ቤት በሁለቱ በነጻ ሲያሰናብታቸው በአንዱ ግን ጥፋተኛ ተባሉ።
ማክሰኞ ኅዳር 3/2018 ዓ.ም. የአቶ ታዬን ጉዳይ የተመለከተው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሕገ መንግሥት እና በሕገ መንግሥት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ችሎት ከቀረቡለት ሦስት ክሶች የጦር መሣሪያ ሕግን በመተላለፍ በቀረበባቸው ክስ ሆነው እንዳገኛቸው ወስኗል።
አቶ ታዬ ነጻ የተባሉባቸው ክሶ "ከጠላት ጋር ማበር" አና የአገር መከላከያ ሠራዊተነ ለመምታት "ዝግጅት አድርገዋል" የሚሉት ሁለት ከባድ ክሶች ናቸው።ተከሳሹ አሁን በፍርድ ቤት ነጻ የተባሉባቸው ክሶች ከዚህ ቀደም በፍርድ ቤት ታይተው ውድቅ ተደርገው የነበረ ቢሆንም፣ ነገር ግን በድጋሚ እንዲታዩ መወሰኑ አይዘነጋም።
በዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ፤ ዐቃቤ ሕግ በፍርድ ቤት ካቀረባቸው መከራከሪያዎች መካከል አቶ ታዬ በፌስቡክ ገጻቸው ያጋሩት መረጃ "ታጣቂዎች መንግሥትን መገዳደራቸውን ተቀባይነት ያለው የሚያስመስል ነው" የሚለው ይገኝበታል።በተጨማሪም ከመታሰራቸው በፊት አቶ ታዬ ከቢቢሲ ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስም ዐቃቤ ሕግ ለክሱ ማጠናከሪያነት ጠቅሶ ነበር።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c2emyevd127o
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 27
Фото недоступноПоказать в Telegram
ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ማስተላለፍ አገልግሎት እንዲሰጡ ፈቃድ የተሰጣቸውን ድርጅቶች ስም ዝርዝር ለሕዝብ ይፋ አደረገ!
-የታገደውን ራማዳ ፔይ (ካህ) በሕጋዊ አስተላላፊዎች ዝርዝር ውስጥ ዳግም አካተተ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በኢትዮጵያ የገንዘብ ማስተላለፍ አገልግሎት እንዲሰጡ የተፈቀደላቸውን የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶችን ስም ዝርዝር ለሕዝቡ ይፋ አድረገ።ባንኩ ዛሬ ህዳር 3 ቀን ባወጣው መግለጫ፣ ከ 90 በላይ ለሚሆኑ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች የገንዘብ ማስተላለፍ አገልግሎት እንዲሰጡ ህጋዊ ፍቃድ ማግኘታቸውን አስታውቋል።
መግለጫው፣ ቀደም ሲል የገንዘብ ማስተላለፍ አገልግሎት እንዳይሰጥ ታግዶ የነበረው እና ዋና መሥሪያ ቤቱ በአሜሪካ ቨርጂኒያ ግዛት የሚገኘው ራማዳ ፔይ (ካህ) ድርጅት በሕጋዊ የገንዘብ አስተላላፊዎች ዝርዝር ውስጥ ዳግም እንዲካተት ተደርጓል ብሏል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እንዳስታወቀው፣ ውሳኔው ላይ የተደረሰው በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ አጠቃላይ ግምገማ ከተካሄደ በኋላ ነው። መግለጫው፣ በሀገሪቱ ሕግና ደንብ መሠረት በድርጅቱ ላይ አስፈላጊው የቁጥጥር እና የክትትል ሂደት መደረጉንም ጠቅሷል።
ባንኩ አክሎም፣ በአሁኑ ጊዜ አገልግሎት እንዳይሰጡ ታግደው የሚገኙ ሌሎች የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች ሁሉ የሀገሪቱን ሕግና ደንብ የሚጠይቀውን መስፈርት ለማሟላት አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስዱ አሳስቧል።
Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 18
Фото недоступноПоказать в Telegram
ስለመጪው ምርጫ ሂደትም ሆነ የጊዜ ሰሌዳን የተመለከተ ውይይት ከመደረጉ አስቀድሞ፤ የኢትዮጵያ መንግስት በሰባት መሰረታዊ ቅደመ ሁኔታዎች ላይ “አፋጣኝ” እና “ተጨባጭ” እርምጃዎችን እንዲወስድ ዘጠኝ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና አንድ የፓርቲዎች ስብስብ ጠየቁ።
መንግስት እና ገዢው ፓርቲ ቅድመ ሁኔታዎቹን በማሟላት፤ ለሁሉም ወገኖች “ነጻ እና ፍትሃዊ የሆነ” የውድድር ምህዳር እንዲፈጥሩ ፓርቲዎቹ ጥሪ አቅርበዋል።
ዘጠኙ ፓርቲዎች እና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች አንድነት መድረክ (መድረክ) የተሰኘው የፓርቲዎች ስብስብ ጥሪውን ያቀረቡት “በኢትዮጵያ ነጻ እና ፍትሃዊ ምርጫን ለማካሄድ የሚያስችሉ ሁኔታዎችን መፍጠርን” በተመለከተ ዛሬ ረቡዕ ህዳር 3፤ 2018 በጋራ ባወጡት መግለጫ ነው።
ፓርቲዎቹ በዚሁ መግለጫቸው፤ ለመጪው ጠቅላላ ምርጫ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እያደረገ ያለውን “እንቅስቃሴ” በቅርበት እየተከታተሉ መሆኑን ገልጸዋል።
ምርጫ ቦርድ ሂደቱን እያከናወነ ያለው በህግ ከተሰጠው ተግባር እና ኃላፊነት አንጻር መሆኑን እንደሚገነዘቡም ፓርቲዎቹ አስታውቀዋል።
ሆኖም ቦርዱ የጀመረው እንቅስቃሴ ለምርጫ “አስቻይ ሁኔታዎች” መኖራቸው “ባልተረጋገጠበት” እየተደረጉ ያለ በመሆኑ፤ “ጥረቱ ሁሉ ትርጉም አልባ መሆኑን በግልጽ መናገር እንፈልጋለን” ሲሉም ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው አስፍረዋል።
ዘጠኙ ፓርቲዎች በዛሬው መግለጫቸው የ2018 ዓ.ም. ጠቅላላ ምርጫ ባለፈው ጊዜያት ከተካሄዱት “የተለየ” እና “አስተማማኝ ሰላም ለመገንባት” የሚያስችል እንዲሆን፤ ምቹ ሁኔታ መፍጠር “አማራጭ” ሳይሆን “ቅድመ ሁኔታ መሆኑን” አጽንኦት ሰጥተዋል።
Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 12👎 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
ጥራቱ በየነ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ሆነው ተሾሙ!
የሀዋሳ ከተማ ም/ቤት ዛሬ ህዳር 3 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ አቶ ጥራቱ በየነን የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ አድርጎ ሾሟቸዋል።
በአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ ሲሰሩ የቆዩት አቶ ጥራቱ በትላንትናው ዕለት የክብር ሽኝት ተደርጎላቸዋል።
(የሲዳማ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ)
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 19😭 3🔥 1😁 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
ኢትዮጵያ ከ50 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች የሚታደሙበትን ጉባኤ እንድታስተናግድ ተመረጠች!
ኢትዮጵያ ከሁለት ዓመት በኋላ የሚካሄደውን የዓለማችን ዋነኛውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ፀባይ ለውጥ ጉባኤን እንድታስተናግድ ብራዚል ውስጥ እየተካሄደ ባለው የዘንድሮ ስብሰባ ላይ ተመረጠች።ኮፕ በመባል የሚታወቀውን እና በየዓመቱ ከሚካሄደውን የአየር ፀባይ ለውጥ ጉባኤ በአውሮፓውያኑ 2027 የሚደረገውን "ኮፕ32" ኢትዮጵያ እንድታስተናግድ የተመረጠችው ናይጄሪያን በመብለጥ ነው።
ኮፕ የሚለው ስያሜ 'ኮንፈረንስ ኦፍ ፓርቲስ' የሚሉት ቃላት ምህጻረ ቃል ሲሆን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ፀባይ ለውጥ ስምምነት ማዕቀፍ ስር የሚካሄድ የዓላማችን ዋነኛው የአካባቢ ጥበቃ ጉባኤ ነው።በጉባኤው ከአሜሪካ በስተቀር መላው የዓለም አገራት እና ሌሎችም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች የሚታደሙ ሲሆን፣ ወሳኝ ድርድሮች እና ስምምነቶች የሚደረሱበት ነው።
ይህ ዓመታዊ ጉባኤ መካሄድ የጀመረው በአውሮፓውያኑ 1992 የአየር ፀባይ ለውጥ የዓለማችን ስጋት መሆኑ በመንግሥታቱ ድርጅት ተቀባይነት አግኝቶ ከስምምነት ከተደረሰ በኋላ ነው።ኢትዮጵያ ይህንን ጉባኤ ለማዘጋጀት መመረጧ በጉባኤው አጀንዳ ላይ እና በማብቂያው ላይ በሚተላለፉ ውሳኔዎች ላይ ከፍተኛ ሚና እንዲኖራት እንደሚያደርግ የሮይተርስ ዘገባ ያመለክታል።
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 32😁 8👍 2⚡ 1🔥 1
Repost from YeneTube
Фото недоступноПоказать в Telegram
በካሽ 100% ለሚከፍል 35% ቅናሽ
📍ሳር ቤት ቫቲካን
🎯65/35 አከፍፈል (35%ቅናሽ)
👉2መኝታ 81 ካሬ =5.8 ሚሊዮን ብር
👉2መኝታ 106 ካሬ=7.6 ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 139 ካሬ=9.9 ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 152 ካሬ= 11.8 ሚሊዮን ብር
🎯ቀስ ብሎ ለሚከፍል
👉2መኝታ 81ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%) = 1.78 ሚሊዮን ብር
👉2መኝታ 106ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%)=2.33ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 139ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%)= 3.06 ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 152ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%)=3.34 ሚሊዮን ብር
#ቀሪውን 80% ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት
* 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ 15%_25% ቅናሽ አዘጋጅተናል
ለበለጠ መረጃ
0901504245
0923579248
❤ 2
ዩኒቨርሲቲዎች በለብለብ እያስተማሩ ማስመረቃቸውን እንዲያቆሙ፣ ስኬታቸው የሚለካውም ባስመረቁት ተማሪ ብዛት ሳይሆን በተማሪዎቻቸው ብቃት ሊሆን እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ(ፕ/ር) አሳሰቡ፡፡
በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ በተደረገ ምልከታ ትምህርት ማስተማር ያልጀመሩ ዩኒቨርሲቲዎች አሉ ሲሉ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡ የዩኒቨርሲቲዎች የጥራት መለኪያ የሚሆነው በየዓመቱ በሚያስመርቁት የተማሪ ብዛት ሳይሆን በሚፈጥሩት ተወዳዳሪ የሰው ሀይል ብቻ ነው ብለዋል፡፡
ሚኒስትሩ ይህን ያሉት 34ኛው የትምህርት ጉባኤ በንግግር ሲከፍቱ ነው፡፡ፕሮፌሰር ብርሃኑ እንዳሉት ኢትዮጵያም አሁን ቴክኖሎጂዎችን ከሌሎች ሀገራት እየቀዳች ነው ይህ ጥሩ ነው ነገር ግን ከወዲሁ ማሰብ ያለብን እስከመቼ ነው የምንቀዳው ሲሉ ጠይቀዋል ፡፡
የተማረ የሰው ሀይል ለማፍራትና ተወዳዳሪ ባለሞያ ለመፍጠር ከፈለግን ጥራት ያለው ትምህርት መስጠት አለብን ይህን ለማድረግ መሰረት እየጣልን ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡ዩኒቨርስቲዎች ከዚህ በኋላ ለተማሪዎቻቸው ዲግሪ ሲሰጡ ከሌላው አለም ጋር በዘርፋቸው ተመራቂዎችን ተወዳዳሪ ማድረግ ሲችሉ ብቻ ነው፤ ስራቸውን ተወጥተዋል ማለት የምንችለው ይላሉ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፡፡
የትምህርት ፍትሃዊነት ማለት በየቦታው ትምህርት ቤት መክፈት ሳይሆን የትምህርት ጥራት እንደ ሀገር እኩል ማዳረስ ስንችል ነው የከፈለው የተሻለ ትምህርት የሚያገኝና ድሃው ከዚያ ያነሰ የትምህርት ጥራት የሚያገኝ ከሆነ ነገ ላይ የተረጋጋ ሀገር እንዳንገነባ ሊያደርገን ይችላል ብለዋል፡፡
ያደጉ ሀገራት የተማረ የሰው ሀይል በተለየ መንገድ ወደ ሀገራቸው እየሳቡ ነው ያሉት የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ኢትዮጵያም የፈጠራ አቅም ላላቸው እና ብቁ ለሆኑ ተማሪዎች የሚሆን ስነ ምህዳር ከወዲሁ መፍጠር አለባት ይላሉ፡፡
በቅርብ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተዘዋውረን ስንመለከት የመጀመሪያ ሳምንት ክፍለ ጊዜን ያላስተማሩ መምህራን መኖራቸው ተገንዝበናል ዩኒቨርሲቲዎች ይህንን መቆጣጠርና ማስተካከል አለባቸው ሲሉም ተናግረዋል፡፡
Via Sheger
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 51👎 14👍 9😁 4🔥 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2017 በጀት ዓመት በሀገር ደረጃ በዲጂታል አማራጮች ከተከናወነው አጠቃላይ የገንዘብ ዝውውርና ክፍያ 73 በመቶ የሚሆነውን መሸፈኑን አስታውቋል።
ባንኩ ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት፣ ባለፈው በጀት ዓመት በባንኩ ዲጂታል አማራጮች ብቻ ከ13 ትሪሊዮን ብር በላይ ግብይት ተከናውኗል።
መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በአጠቃላይ በሀገሪቱ ከ17.7 ትሪሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ዝውውርና ክፍያ በተለያዩ የዲጂታል አማራጮች ተፈጽሟል።
ይሄ የተገለጸው ባንኩ የዲጂታል አገልግሎቶቹን የበለጠ ለማጠናከር በሚል "ሲቢኢ በጄ" የተሰኘ አዲስ የዲጂታል የቁጠባና የብድር አገልግሎት በይፋ ባስጀመረበት መድረክ ላይ ነዉ።
የባንኩ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት አቶ ኤፍሬም መኩሪያ ፤ ሲቢኢ በጄ ደንበኞች የሲቢኢ ብር መተግበሪያን በመጠቀም ያለምንም ማስያዣ እስከ 150 ሺህ ብር ብድር እንዲያገኙ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።
አገልግሎቱ ለመንግስት ሰራተኞች ቅድሚያ የሚሰጥ ሲሆን፣ ደሞዛቸውን በሲቢኢ ብር አካውንት የሚያገኙ ሰራተኞች ወርሃዊ ደሞዛቸውን ታሳቢ ባደረገ መልኩ የብድር አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ ተብሏል።
Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 19👍 3
Repost from YeneTube
Фото недоступноПоказать в Telegram
በካሽ 100% ለሚከፍል 35% ቅናሽ
📍ሳር ቤት ቫቲካን
🎯65/35 አከፍፈል (35%ቅናሽ)
👉2መኝታ 81 ካሬ =5.8 ሚሊዮን ብር
👉2መኝታ 106 ካሬ=7.6 ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 139 ካሬ=9.9 ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 152 ካሬ= 11.8 ሚሊዮን ብር
🎯ቀስ ብሎ ለሚከፍል
👉2መኝታ 81ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%) = 1.78 ሚሊዮን ብር
👉2መኝታ 106ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%)=2.33ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 139ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%)= 3.06 ሚሊዮን ብር
👉3መኝታ 152ካሬ
ቅድመ ክፍያ(20%)=3.34 ሚሊዮን ብር
#ቀሪውን 80% ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት
* 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ 15%_25% ቅናሽ አዘጋጅተናል
ለበለጠ መረጃ
0901504245
0923579248
❤ 7
በተቀናጀ መንገድ ሕገ-ወጥ የውጭ ምንዛሪ አሻጥሮችን ሲፈጽሙ የተደረሰባቸው አንድ መቶ አስራ ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ!
በተቀናጀ መንገድ ሕገ-ወጥ የውጭ ምንዛሪ አሻጥሮችን ሲፈጽሙ የተደረሰባቸው አንድ መቶ አስራ ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስታወቀ።አገልግሎቱ ለኤኤምኤን በላከው መረጃ እንዳስታወቀው፥ መንግሥት ተግባራዊ ያደረገውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በመጻረር በተደራጀ መንገድ በሚፈጽሙ ሕገ-ወጥ የውጭ ምንዛሪ አሻጥሮች ዙሪያ በተቀናጀ መልኩ ምስጢራዊ የመረጃ ስምሪት ሲከናወን ቆይቷል፡፡
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፣ የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፣ የክልል የፀጥታ አካላት እና በህብረተሰቡ ጥቆማ በተደረገ የተቀናጀ ሥምሪት በፋይናንስ አሻጥር የተሰማሩ አንድ መቶ አስራ ሁለት ኢትዮጵያውያንና የተለያዩ የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን፤ ከሕገ -ወጥ ተግባሩ ጋር ትስስር የነበራቸው አምስት መቶ አስራ ዘጠኝ የባንክ አካውንቶች መታገዳቸውን እንዲሁም የተለያዩ ኤግዚቢቶች መያዛቸውን መግለጫው አመልክቷል፡፡
ሕገ- ወጥ ሃዋላዎች ፣ የገንዘብ ዝውውሮች፣ የውጭ ምንዛሪ ስወራዎች ፣ የግብር ስወራዎች፣ ሕገ- ወጥ ገንዘብን ሕጋዊ የማስመሰልና ሌሎች ተመሳሳይ ወንጀሎች በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሲያስከትሉ እንዲሁም አሸባሪዎችንና የታጠቁ ቡድኖችን ለመደገፍ ሲውሉ መቆየታቸውን መግለጫው አመልክቷል፡፡በተለይም ሕገ- ወጥ በሆኑ ዓለም አቀፍ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች፤ ሕገ- ወጥ የውጭ ምንዛሪ ማስተላለፊያ መተግበሪያዎች፤ የክሪፕቶ ከረንሲ መተግበሪያዎች፤ ሕገ-ወጥ የሃዋላ አዘዋዋሪዎችና ደላላዎች፤ በወጪና ገቢ ንግድ ላይ አሻጥር የፈፀሙ አስመጪዎችና ላኪዎች እንዲሁም ሕጋዊ ንግድ ሳይኖራቸው በሕገ-ወጥ ሃዋላ ላይ በመሰማራት ከፍተኛ ገንዘብ በማንቀሳቀስ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ባደረሱ አካላት የማያዳግም ሕጋዊ እርምጃ መወሰዱን መግለጫው ጠቁሟል፡፡
በተለያዩ ዓለማት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሚልኩት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ የብሔራዊ ባንክን መመሪያ በሚጥስ ሁኔታ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሲያስከትሉ የቆዩ ሕጋዊ ፈቃዳቸው በፈጸሙት ተደጋጋሚ ጥፋት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተሰረዘባቸው ዓለም አቀፍ የሃዋላ አስተላላፊዎችና ሕገ-ወጥ የሃዋላ ድርጅቶችም እርምጃው የተወሰደባቸው ናቸው ብሏል።
በተጨማሪም በሀገር ውስጥ ሕገ- ወጥ የውጭ ምንዛሪ ማስተላለፊያ መተግበሪያዎችን በመጠቀም ሀብትን ከሀገር በማሸሽ ላይ ያሉ ድርጅቶች ባለቤቶችም በቁጥጥር ሥር ውለዋል ነው ያለው።የብሔራዊ ባንክ ሕግን በሚጥስ ሁኔታና ያለምንም ፈቃድ የክሪፕቶ ከረንሲ መተግበሪያን በመጠቀም በሕገ- ወጥ መንገድ የውጭ ምንዛሪን ሲያዘዋውሩ የነበሩ አካለት ላይም እርምጃ መወሰዱንም መግለጫው አመልክቷል፡፡
በሀገሪቱ ብሔራዊ ጥቅም ላይ በማነጣጠር ሲፈጸም የነበረው ኢኮኖሚያዊ አሻጥር ትላልቅ የመንግሥት ፕሮጀክቶችን ለማስተጓጎል፤ ሕዝብ በመንግሥት ላይ ቅሬታ እንዲያድርበት እንዲሁም የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እንዳያንሰራራ በተቀናጀ መንገድ ሲፈጽሙት የነበረ መሆኑንም አንስቷል፡፡
የሀገርን ደኅንነት ስጋት ላይ በሚጥሉ እና የሀገርን ኢኮኖሚ በሚጎዱ አሻጥሮች ላይ ተሳታፊ የሆኑ አካላትን በመከታተል የማያዳግም እርምጃ ለመውሰድ የተጀመረው የተቀናጀ ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት በመግለጫው፥ መላው ሀገር ወዳድ ዜጋ መሰል ወንጀሎችንና ወንጀለኞችን በማጋለጥ እያደረገ ያለውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል፡፡
Via AMN
@YeneTube @FikerAssefa
❤ 41👎 5👍 1🔥 1😁 1😭 1
የኢትዮጵያ መንግሥት፣ በቅርቡ ከትግራይ ክልል ወደ አፋር ክልል ተተኩሰዋል የተባሉ የከባድ መሳሪያ ጥይቶችን እየመረመረ መሆኑ ተሰማ።
ይህ ክስተት፣ ለሁለት ዓመታት የዘለቀውን ደማሳሽ ጦርነት ያስቆመው የ2022 የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት (CoHA) "እየተሸረሸረ" [fraying] ነው የሚለውን ስጋት አጠናክሮታል።
የመከላከያ ምንጮች ለዘ-ሐበሻ እንደገለጹት፣ መንግስት የተገኙትን ጥይቶች በመሰብሰብ ምርመራ እያካሄደ ነው። የምርመራው አላማም፣ "ሕወሓት ከዚህ ቀደም ሲጠቀምባቸው ከነበሩት የተለዩ አዳዲስ መሳሪያዎች ሊኖሩ ይችላሉ" የሚለውን ስጋት ለማረጋገጥ መሆኑን ምንጮቹ አክለዋል።
ይህ አዲስ ወታደራዊ ውጥረት የተከሰተው፣ በዘመናዊ አፍሪካ ታሪክ እጅግ ገዳይ ከሆኑ ጦርነቶች አንዱን ያስቆመው የፕሪቶሪያ ስምምነት፣ በተለያዩ ምክንያቶች አደጋ ላይ መውደቁን አንድ አዲስ ትንታኔ ባመለከተበት ወቅት ነው።
ሪፖርቱ፣ በቅርቡ በትግራይ እና በአፋር ክልሎች መካከል የተከሰቱት ግጭቶች፣ እንዲሁም በትግራይ አመራሮች እና በፌደራል ባለስልጣናት መካከል "እያደገ ከመጣው እምነት ማጣት" ጋር ተዳምረው፣ ከ2022 መገባደጃ ጀምሮ የተገነባው ስስ ሰላም አደጋ ላይ መውደቁን አመልክቷል።
ትንታኔው ለአሁኑ አለመተማመን በዋነኛነት "ዘገምተኛ እና ወጥነት የጎደለው የስምምነቱ አፈጻጸም" መሆኑን ይጠቁማል።
ምንም እንኳን በሁለቱ ዋና ተዋጊ ኃይሎች መካከል መጠነ ሰፊ ውጊያ ቢቆምም፣ እንደ ትጥቅ መፍታት፣ የታጋዮችን መልሶ ማዋሃድ እና ተፈናቃዮችን መመለስ ባሉ ቁልፍ ድንጋጌዎች ላይ መዘግየቶች እና የጋራ ውንጀላዎች ተበራክተዋል።
የፌደራል መንግሥት፣ የትግራይ ባለስልጣናት "ሙሉ በሙሉ ትጥቅ አልፈቱም" እንዲሁም "በአማራ ክልል ከሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ጋር ይተባበራሉ" ሲል ይከሳል።
የትግራይ ክልል አመራሮች በበኩላቸው፣ የፌደራል መንግሥት አስፈላጊ አገልግሎቶችን፣ አስተዳደራዊ ገደቦችን ማንሳትን እና ፖለቲካዊ ራስን በራስ የማስተዳደር መብትን በማረጋገጥ በኩል "እግሩን እየጎተተ ነው" ሲሉ ይከሳሉ።
በተለይም በሁለቱ ክልሎች አወዛጋቢ በሆነው የትግራይ-አፋር ድንበር ላይ እንደ አዲስ ያገረሸው ግጭት፣ የቆዩ ቁርሾችን በመቀስቀስ ለሰላሙ ስምምነት ትልቅ አደጋ መደቀኑን ሪፖርቱ አስገንዝቧል።
ትንታኔው ሲያጠቃልል፣ ይህ የሰላም ስምምነት ሙሉ በሙሉ መፍረስ፣ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለመላው የአፍሪካ ቀንድ መረጋጋት "አስከፊ" አንድምታ እንደሚኖረው አስጠንቅቋል።
@Yenetube @Fikerassefa
❤ 33😁 9🔥 1

